November 3, 2009

ቤተ ክህነት “ደጀ ሰላም”ን ወነጀለ

(ደጀ ሰላም፤ ኖቬምበር 3/2009)፦
“ደጀ ሰላም” የጡመራ መድረክን የጠቀሰ የክስ ዶኩመንት ሰሞኑን ከቤተ ክህነት ይፋ ሆነ። በሰንበት ት/ቤቶች ማ/መምሪያ እና በማህበረ ቅዱሳን መካከል በተነሣው ውዝግብ ደጀ ሰላምን በማስረጃነት የጠቀሱት የመምሪያው ሃላፊዎች መሆናቸውን ዶኩመንቱ (PDF)ገልጿል። ደጀ ሰላም ጁላይ 9/2009 ያወጣችውን የሚከተለውን ዜና በማስረጃነት በመጥቀስ በቅዱስ ፓትርያርኩና በመንግሥት ባለሥልጣናት ፊት የከሰሰሱት የቤተ ክህነት ባለሥልጣናት ደጀ ሰላምን “የማህበረ ቅዱሳን” መሆኗን ጠቅሰዋል።
ደጀ ሰላም በወቅቱ ያወጣችው ዜና ከዚህ በታች ተያይዞ ቀርቧል።

(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 9/2009)
• “ከዚህ በሁዋላ ከፓትርያርኩ ጋር አብረን አንሠራም” ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ፤ ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ
• “ሀገረ ስብከቴን ተረከቡኝ” ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል፣
• ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ፣ ያልተጠበቁ የፓትርያርኩ ደጋፊ፣
• ፓትርያርኩ “ተቃዋሚዎቻቸውን ይበቀላሉ” ይባላል፣
• አቡነ ሳሙኤልን ስላገቱት ሰዎች ፌዴራል ፖሊስም አያውቅም፣

ቅዱስ ሲኖዶሱ ያረቀቀውን ቃለ ጉባዔ ሳያጸድቅ፣ የጀመረውን አጀንዳ ሰይቋጭ፣ ቤተ ክርስቲያኒቱን ሜዳ ላይ ጥሎ ወደ ቤቱ ገብቷል። ከስምምነት ላይ የተደረሰበት ውሳኔ በፊርማ እንዳይጸድቅ ብፁዓን አበው እስጢፋኖስ፣ ኤጲፋንዮስና ጎርጎርዮስ የሞት ሽረት ትግል አድርገው፣ አባቶችን በጥብጠው ውሳኔው እንዲከሽፍ አድርገዋል። በተለይም በምዕራብ ኢትዮጵያ በጀመሩት መልካም አገልግሎት በሕዝቡ እየተመሰገኑ የነበሩት ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ ይህንን ገዳይ አቋም እንዴት ሊይዙ እንደበቁ እንቆቅልሽ ሆኗል። ገሚሱ በገንዘብ ተገዝተው ነው ሲል ሌላው ደግሞ ውስጠ ዘ በሆነ ማስፈራሪያ ሊሆን ይችላል እያለ ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ወደ አሸናፊነቱ እየመጡ ያሉት ፓትርያርኩ የበቀል በትራቸውን እንደሚመዙ እየተጠበቀ ነው። የመጀመሪያ ተጠቂዎች የሚሆኑት በአዲስ አበባ የሚገኙ ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች ሲሆኑ ባለፈው ሳምንት በብፁዕ አቡነ ሳሙኤል መሪነት ስብሰባ ካደረጉ በሁዋላ የፓትርያርኩን ድርጊት የሚቃወም መግለጫ ማውጣታቸው ይታወሳል። ከዚህም ባሻገር ይህንን ሁሉ ሕዝብ ያስተባብርብኛል ያሉት ማህበረ ቅዱሳንም ላይ ጥርሳቸውን ነክሰዋል ተብሏል።
የቤተ ክህነቱ ድራማ ዛሬ ሲተወን ጠዋት በማለዳው ስብሰባ እንዳይገቡ የታገቱት ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ለምን እንደታገቱ ፌዴራል ፖሊስ ራሱ አያውቅም። የደህንነት ክፍሉ ደግሞ ለደህንነታቸው ብዬ ነው ብሏል። ድራማው ሊቀ ጳጳሱን ከስብሰባው በማስቀረት ውሳኔውን ማክሸፍ ከሆነ በርግጥም ዘዴው ሰርቷል ማለት ይቻላል።መንግሥት በበኩሉ ጉዳዩን እያጠናው እንደሆነ ውስጥ አዋቂዎች ገልጸዋል።

በተያያዘ ዜና ፓትርያርኩ የተነሣባቸውን ተቃውሞ ለመስበርና አባቶችን አንገት ለማስደፋት የሚሆን ገንዘብ ራሳቸው በግላቸው ከሚያዙበት ከቁልቢ ገብርኤል ካዝና ወጪ መደረጉ ታውቋል። የብሩ መጠን ለጊዜው ባይታወቅም ገንዘቡ ለአንዳንድ የፖሊስ ሃላፊዎች፣ ደህንነቶችና ጉልበት ላላቸው ሰዎች መበተኑ ሲታወቅ መንግሥት በውስጡ ሌላ መንግሥት ያለበት አስመስሎታል። እስከ ዛሬም በመንግሥት ስም ቤተ ክርስቲያኒቱን እግርተወርች አስረው ሲበሏት፣ ሲግጧትና ሲያዋርዷት የነበሩ ሰዎች የፓትርያርኩ ዘመዶችና ወዳጆች ብቻ ሳይሆኑ በመንግሥት ሥልጣን ላይ የተንፈራጠጡ ሰዎችም መሆናቸው እየተገለጸ መጥቷል። መንግሥት ጉዳዩን አጣርቶ ሕገ ወጦቹ እጃቸውን ከቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ እንዲያነሱ ያደርጋል ተብሎ ይገመታል።

ነገሩ በዚህ ከቀጠለ ቤተ ክርስቲያኒቱ ቅዱስ ሲኖዶስ አላት ለማለት እንደማያስደፍር አንድ ሊቀ ጳጳስ ተናግረዋል። ከዋሺንግተን ዲሲ ተጠርተው የተሾሙት የሲዳሞ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስና የሥራ አስፈጻሚው አባል ብፁዕ አቡነ ፋኑኤልም በበኩላቸው “ሀ/ስብከቴን ተረከቡኝ” ማለታቸው ተሰምቷል። በርግጥም ሊቀ ጳጳሱ እንዲህ ካደረጉ ጳጳሳት የሥራ መልቀቂያ የሚያስገቡበት፣ በቅዱስ ሲኖዶስ ሳይሆን በፓትርያርክና በሴት ወይዘሮዎች ብቻ የሚመራ ቤተ ክህነት ይፈጠራል ማለት ነው።
አንድ አስተያየት ሰጪ እንደተናገሩት የፊታችን ሰኞ ስብሰባ ይደረጋል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ስብሰባው የተጠራው በቅዱስ ፓትርያርኩ ከመሆኑ አንጻር ምንም ተለየ ነገር አይጠበቅም። ቅዱስነታቸው የፊታችን እሑድ በዓለ ሲመታቸውን እንደሚያከብሩ ይታወቃል።
ለማንኛውም ደጀ ሰላም በበኩሏ “ተስፋ አንቁረጥ፣ እግዚአብሔር ሥራው ድንቅ ነውና” ትላለች።
ቸር ወሬ ያሰማን፣

አሜን22 comments:

Orthodox unit said...

Yea, they should. Because DS is revealing the truth on each problem in the church and Aba Paulos. They know they will not perform good things which will be appreciated by the true members of the church. Let they do good things so that you will post encouraging news.

This is Deje Selam not Zena Tewahedo (news paper of patriarch) which worships aba paulos. Continue in your work, if in case they may correct themselves at least to be respected.

gorgoreyos said...

wy mekaget!DS bestrong!''yabedie bezu yaweralna!!!

Anonymous said...

ስለ፡ቤተ፡ክርስቲያናችን፡ችግር፡መንፈሳዊንና፡
ተገቢ፡መፍትሄ፡እንድናገኝ፡ወደኋላ፡የሚያሰኘ
ን፡አንዳችም፡ነገር፡ሊኖር፡አይችልም።

የችግራጭን፡ምንጭና፡መሠረት፡የሆኑት፡ፓት
ርያርኩ፡ናቸው።ከተዋሕዶ፡እምነት፣ሥነ፡ሥርዓ
ት፡እጅጉን፡ርቀዋል።አላይ፡አላደምጥ፡አሉ፡እ
ንጂ፡ተዋሕዶ፡ኢትዮጵያ፡እንዳለ፡ነው፡አርግፎ፡
የተዋቸው!

ሕዝበ፡ክርስቲያን፡ይታዘበኛል፡የሚል፡አስተሳ
ሰብ፡የላቸውም።ሥስልጣንና፡ሥጋዊ፡ኑሮ፡አሸ
ንፏቸው፤ጳጳሳትን፡ማስድደብደብና፡በዘመዶቻ
ቸው፡ቤተ፡ክርስቲያንን፡ማስመዝበሩ፡ተስማም
ቷቸዋል፡፡ማዘንና፡ትዕግስት፡አይታይባቸውም።

የሕዝቡን፡ልብ፡ትርታ፡አድምጡልኝ፡የሚሏቸው፡
ለእውነት፡የቆሙ፡ከርሳቸው፡ዘንድ፡አይገኙም።
በዚህም፡ሳቢያ፡ሥልጣን፡ፈላጊ፡አሞካሾችና፡ዓለ
ማውያን፡እንደነ፡"አባ፡"ሰረቀ"ያሉ፡/ከወይዛዝ
ርቶቻቸው፡ችምር፣የጥፋት፡መሣሪያዎች፡በርሳቸ
ው፡ዘንድ፡ሞገስ፡በማግኘታቸው፡በየለቱ፡በቤተ፡
ክርስቲያን፡አገልጋዮች፡ላይ፡ክሱንና፡ውንጀላው
ን፡ተያይዘውታል።

ይህ፡ሁሉ፡መርገምት፡ሊፈጸም፡የቻለው፡ዛሬ፡ቤ
ተ፡ክህነት፡የወደቀችበት፡የጥፋት፡አመራርና፡ለ
መታረም፡የማይሻ፡አስተዳደር፡መሆኑን፡በጥቂቱ፡
እራሱ፡ሲኖዶሱም፡ተወያይቶበታል።ምን፡ያረጋ
ል፡ዓመጽ፡አየለና፡ቅዱሱን፡ጉባኤ፡አረከሰው!ው
ጤት፡አልባ፡አደረገው!!

ፓትርያርኩም፡ልባቸው፡ጧት፡ማታ፡ሮም፣ሮም፡
እያለባቸው፡ከኢትዮጵያ፡የምንኩስና፡ታሪክና፡ሥ
ርዓት፡ውጪ፡ልታይ፤ልታይ፣እያሉ፡ሲሯሯጡ፡ያየ
ና፡የሰማ፡የተዋሕዶ፡ሕዝበ፡ክርስትያን፣ዓይኑ፡ብቻ፡
ሳይሆን፡ልቡም፡እያለቀሰ፡ነው!

ይህን፡ለማድረግ፡የበቁት፡በራሳቸው፡ማን፡አለብኝ
ነት፡ብቻ፡እንጂ፡ሲኖዶሱ፡ተወያቶበትና፡ፈቅቅዶ
ላቸው፡እንዳልሆነ፡የታወቀ፡ነው።

እርሳቸው፡እንዲህ፡የሚኩራሩበት፤"የዓለም፡አብያ
ተ፡ክርስቲያን"ድርጅትም፣ለሥልጣን፡ያላቸውን፡
ተሸናፊነት፡አስተውሎ፡ነው፡የዚሁ፡የፕሮተስታን
ቶች፡ድርጅት፡"ፕሬዚደንት!"ያላቸው።ያሳዝናል!


አይ፡መበገር!አይ፡መደፈር!የጥንቶቹ፡አባቶቻች
ን፡እንዲህ፡ያለ፡መዓት፡መድረሱን፡አይተውና፡ሰ
ምተው፡ምን፡ይበሉ?!በዘመነ፡ሱስንዮስና፡ሙሶሊ
ኒ፡የፈሰሰው፡ደም፡እንዲህ፡በዓመጽ፡ሲረገጥ!ሮሞ
ቹማ፡ምን፡ያድርጉ፡ሰተት፡ብሎ፡የተዋሕዶ፡ፓት
ርያርክ፡እጓዳቸው፡ከች፡ሲል!

አይ፡ሐፍረት፡ማጣት!አይ፡ዓመጽ!

የኢትዮጵያ፡መነኮሳት/ሰማዕታት፡ዕንባና፡ደም፡
ይፍረደን!

የተክለ፡ሃይማኖት፡ልጆች፡እያለቀሱ፡ነውና፡ደብ
ረ፡ሊባኖስ፡አልቅሺ!አባታችንን፡ምነው፡በጸሎት
ህ፡ረሳኸን፡በይው!

በተዋህዶ-ኢትዮጵያ፡ላይ፡ስለደረሰው፡ጥቃት፡
ንገሪው!አልቅሺበት!

ተክልዬ፡እግዚኦ፡መሐረነ፡ክርስቶስ፡እያለ፡ስለኛ፡
እንዲማልድ!

ፓትርያርክ፡ጳውሎስ፡ለመሆኑ፡ይህ፡ሁሉ፡የተዋ
ሕዶ፡ሕዝብ፡ሰቆቃ፡ይሰማዎት፡ይሆን?!!

አይ፡ሐፍረት፡ማጣት!አይ፡ዓመጽ!

ንስሐ፡ይግቡና፡ይኸን፡የኮተሊክ፡ልብስዎ፡ወድያ፡
አውልቀው፡ጥለው፣ጥቁሩን፡ሳይሆን፡ቢጫውን፡የሐ
ዘንና፡የንስሐ፡ልብሳችንን፡ያጥልቁ!

ሞት፡ሳይቀድምዎት፡ከእግዚአብሔርና፡ከኢትዮ
ጵያውያን፡ልጆቹ፡ይታረቁ!

እስከ፡መቼ?!እስከ፡መቼ፡ድረስ?ኧረ፡እስከ፡መቼ፡
ልብዎ፡የደነድናል?!

የአቡነ፡ተክለ፡ሃይማኖት፡አምላክ፣ተዋሕዶ፡እምነ
ታችንን፣ሥርዓታችንንና፡ቅድስት፡ቤተ፡ክርስቲያ
ናችንን፡ከመጣው፡ጥፋት፡ይጠብቅልን!

አሜን፤አሜን፤አሜን።

ሳሙኤል፡ዘአሰቦት።

Anonymous said...

Deje selamawuyan,do you understand what tesfa calls himself"truth fighter"?From his writing i understand that truth fighter means "the fighting against truth",his words fully fight each other;it means he(tesfa) fights against truth;that is my conclusion from his writings;until now he fights against truths(Dogma,canoons,all teachings) of EOTC

Yegeremew said...

To Patriarch Aba Paulos and Aba Sereke

It is shame to blame everybody that work for the true faith of EOTC. In the 21st century, information is delivered freely. It is up to the reader to make the judgment. You better go to one monastery and pray for your people and the country for one week instead of engaging yourself in critics.

Anonymous said...

ጠቅላይ ቤተክህነት የሚገርሙ ሰዎች ስብስብ የሚገኙበት ግቢ ነው::ጥቂት እንኩዋ መንፈሳዊት የማይታይባቸው ሆዳሞች ጥርቅም::ይህ ታዲያ ዛሬ ዛሬ ባሰ እንጂ ቀድሞም የነበረ ነው::ልዩ ነቱ የዛሬዎቹ በደንብ የተደራጁ እና በፓትርያርኩ የሚደግፉ መሆናቸው ነው ልዩነቱ::
አቡነ ተ/ሓይማኖት ር.ሊ ጳጳሳት በነበሩ ጊዜ የአንዲት ደ.ኢትዮጲያ አውራጃ ቤተክህነት ሕንጻ በቤተክህነቱ ሰዎች ተሸጠ::ቤቱን የገዛው ግለሰብ የከፈለው በቤ/ክነቱ ምትክ አነስተኛ ቤት እና ለሊቀ ካህናቱ ባልደረቦቻቸው ገንዘብ ነበር::ግለስቡ መሃል ከተማ በሚገኘው የቤ/ክነቱ ቦታ ላይ ግንባታ ጀመረ::ምዕመናን ተደናገጥን:: በጣም ያደናገጠን ግንባታውን የሚያካሂደው ሰው ፕሮቴስታንት ነበር::ሰዎች ከየአጥቢያው ተመርጠው አቤት ለማልት ጠቅላይ ቤ/ክ ተላኩ::የጠቅላይ ቤ/ክ ሰዎች ከገንዘቡ ደርሷቸው ስለነብር ለሰውየው ፈርዱ አባታችን ጋር አላቀርብ አሉዋቸው::ስንቅ ጨርሰው ተቸግረው በመጨርሻ አባታችንን የሚያውቅ ተራ ምዕመን ከአባታችንን አቡነ ተ/ሐይማኖትን ጋር አገናኝትዋቸው ችግራቸውን አስርድተው እርሳቸውም አመስግነዋቸው ለቤተክርስቲያንና ለምዕመናን ፈርደዋል::ቦታውም ል ለቤተክርስቲያን ተምልስዋል ::የዚህ ጽሑፍ አቅራቢ ወላጅ አባት ተመርጠው ከሄዱት ሰዎች አንዱ ነው::አባቴ አባታችንን እቤታቸው ውስጥ ሰሌን ላይ እጥፍ ብለው ተቀምጠው እንዳገኟቸው በአድናቆት ይናገራል::
ስለእውንት የሚፍርድ አባት ይስጠን!

Anonymous said...

ሰሚ የለም ዝም ብላችሁ ነው የምትደክሙት አባ ጳውሎስ ማለት ፈርኦን ማለት ናቸው እግዚአብሔርን የናቁ በመሆናቸው እኔ ለሳቸው በጣም አዝናለሁ ምክንያቱም እግዚአብሔርን የናቁ ሰዎች መጨረሻቸው ሞት ነው በስራቸውም ያሉት ዘመዶቻቸው ፍጹም ክርስትና የሌላቸው ሆዳቸው አምላካቸው የሆኑ ሰዎች ናቸው ውሻ በበላበት ይጮሃል እንዲሉ እነ አባ ሰረቀ ነገ ሆዳቸው ሲጎድልባቸው በአባ ጳውሎስ ላይ ይነሳሉ እኔን በጣም የሚገርመኝ የስንት ሽ ዘመን ታሪክ ያላት ቤተክርስቲያን የካድሬዎች መሰብሰቢያ መሆኑዋ ነው ጥቂት ጊዜ ነው መድሃኔ ዓለም የድንግል ማርያም ልጅ ቢዘገይም የሚቀድመው የለም እመን እንጅ አትፍራ

ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋራ ይሁን አሜን

Unknown said...

i shame on you ds from were do you get the document? from deacon mulugeta site?

Dembla said...

i shame on you ds from were do you get the document? from deacon mulugeta site? bravo deacon.

Aba ... said...

ደጀ ብጥብጥ እንኳን የእውነት ነጸብራቅ ወደሆነቺው የወንድማችን ዲያቆን ሙሉጌታ ድህረ ገጽ በሰላም መጣችሁ መራጃውን ማቅረባችሁ ሁሉ እንዲያውቀው በማድረጋችሁ ደስታችን ከፍ ያለ ነው ቢሆንም ግን ምንጭ አለመጥቀሳችሁ ሌብነታችሁ አያጎላውም ትላላችሁ? ሌባ! ሌባ! ሊሰርቅ ሊያርድና ሊያጠፋ ይመጣል ብቅ ማለታችሁ ለካ ለስርቆት መሆኑ ነው?

Abunu said...

ደጀ ብጥብጥ እንኳን የእውነት ነጸብራቅ ወደሆነቺው የወንድማችን ዲያቆን ሙሉጌታ ድህረ ገጽ በሰላም መጣችሁ መራጃውን ማቅረባችሁ ሁሉ እንዲያውቀው በማድረጋችሁ ደስታችን ከፍ ያለ ነው ቢሆንም ግን ምንጭ አለመጥቀሳችሁ ሌብነታችሁ አያጎላውም ትላላችሁ? ሌባ! ሌባ! ሊሰርቅ ሊያርድና ሊያጠፋ ይመጣል ብቅ ማለታችሁ ለካ ለስርቆት መሆኑ ነው?

Anonymous said...

ደጀ ብጥብጥ እንኳን የእውነት ነጸብራቅ ወደሆነቺው የወንድማችን ዲያቆን ሙሉጌታ ድህረ ገጽ በሰላም መጣችሁ መራጃውን ማቅረባችሁ ሁሉ እንዲያውቀው በማድረጋችሁ ደስታችን ከፍ ያለ ነው ቢሆንም ግን ምንጭ አለመጥቀሳችሁ ሌብነታችሁ አያጎላውም ትላላችሁ? ሌባ! ሌባ! ሊሰርቅ ሊያርድና ሊያጠፋ ይመጣል ብቅ ማለታችሁ ለካ ለስርቆት መሆኑ ነው?

Akale weld said...

aba blessed for your information

ደጀ ብጥብጥ እንኳን የእውነት ነጸብራቅ ወደሆነቺው የወንድማችን ዲያቆን ሙሉጌታ ድህረ ገጽ በሰላም መጣችሁ መራጃውን ማቅረባችሁ ሁሉ እንዲያውቀው በማድረጋችሁ ደስታችን ከፍ ያለ ነው ቢሆንም ግን ምንጭ አለመጥቀሳችሁ ሌብነታችሁ አያጎላውም ትላላችሁ? ሌባ! ሌባ! ሊሰርቅ ሊያርድና ሊያጠፋ ይመጣል ብቅ ማለታችሁ ለካ ለስርቆት መሆኑ ነው?

kelifa zegudu said...

the question is from were did it get ds the pdf document?

Lord Judges said...

Do you guys expect that only Mulugeta has the document? Where did he get it from? Why not Deje Selam get it from other sources?

What is the problem if they took it from his site? No problem, the problem is as he is saying MK has stolen his document, he is also complaining here to be stolen again. He is very childish........

kelifa zegudu said...

ልብ በሉልኝ “ስካን” ተደርጎ የተቀመጠው እንካን አንድ አይነት ነው። ቀድሞ የወጣ የዲያቆኑ ደጀብጥብጥ ከየት አመጣው ከዲያቆኑ ድህረ ገጽ ካልሰረቀው በቀር መቼም ቤተ-ክህነት ስካን አድርጎ ነው የበተነው አይልም። ያም ሆነ ይህ ጥያቄው እንደዛ አይደለም አንተ ጠማማ በትክክል አንብበህ ለመረዳት ሞክር ለምን? ከዲያቆኑ ድህረ ገጽ በፊት አያወጣውም ደጀ ብጥብጥ ሌብነት አመል ሆኖበት እንጂ። ሰርቆ መለጠፉ አይደለም ምንጭ አለመጥቀሱስ ሁለት ጊዜ ሌብነት? አስተያየት ከመጻፍህ በፊት የሚድያ ና ዘገባ ህግና ሥርዓት ማወቁ ይበጀሃል ማሃል ሜዳ ከመጃጃል።

Mezemr said...

ማሽላ እያረረ ይስቃል ነው የሚባለው ደግ የሚበረታታ አኩሪ ሥራ ነው ደጀ ሰላማውያን ብላችሁ ብላችሁ ደግሞ ከመናፍቁ ዲያቆን ያለውንና የጻፈውን ሁሉ ደግማችሁ እያስተጋባችሁ መለጠፍ ጀመራችሁ? ወይስ የጓደኛ ሌባ ከዩት ሊስቅ ካላዩት ሊሰርቅ የሚለውን ወግ ደርሶባችሁ ነው?

Orthodox unit said...

by the way Kelifa zegudu is right the matterial (the pdf document)is the same and also the so called "deacon" was posted on 1st november and ds on 3th november wonderful what is going on?

Anonymous said...

guys let us give attention for the document posted by ds parrarely the document posted on www.thetruthfighter.net

Orthodox unit said...

Orthodox Unit, Can you please leave my pen name and produce your own pen name, I have been using this name for long period of time. If you cannot do that please inform me so that I will change my name.

Thanks,

Anonymous said...

ውሃ ቢወቅጡት እምቦጭ አትሁኑ እንጂ !
እስከ ዛሬ ስንወቅጠው የኖርነው የቤተክህነት ሰዎች ጠባይ አልገባችሁም ? አንዳንድ አንባብያን ግርም ትሉኛላችሁ::ዲ. ሙሉጌታና ደጀ ሰላም አንድ አይነት ዶክመንት ማግኘት ሊገረማችሁ አይገባም::እዛ የተቀመጡ ሰዎች ገንዘብ ካዩ ጉዳያቸው አይደልም:: ይቸበችቡታል!! አይደለም ወርቀት ቤተክርስቲያናችንን እኮ እየቸበቸቧት ነው::የሚያወያየንስ ይሄ የሌብነት እና የአምባገነንንት ጉዳይ አይደል እንዴ ? እንደ ይሁዳ ሳይሸማቀቁ ወዳጅ መስለው የሚሽጡ ንጋዴዎች ናቸውና አትደንቁ::ብትፈልጉ እናንትም መሸመት ትችላላችሁ.........
ጌታን እንኳ ሳይራሩ ሸጠውታል:: ጥቅማቸው ና ስልጣናቸው በልጦባቸው አሰድበውታል!

nafkoteyegetalij@gmail.com said...

አዎ ማሞ ሌላ ፎቶው ሌላ ይላሉ ይሄ ነው

ትላንትና አባቶቻችንን አነዴ ጎንደሬ አንዴ ትግሬ እያላችሁ ስትሰድቡ ዋላችሁ ግራ ሲገባችሁ ቶሎ አወጣችሁት የካም ዘሮች ጥፉ

በአባቶቻችን ወይንም በወንድማማቾች መካከል የዘረኝነትን ፍላጻ ስታነሱ እውነተኛ የተዋህዶ ልጆች ተነሱባችሁ የሰራችሁት ክፏኛ ስለተጠላና እናንተም ሰላፈራችሁበት ጽሁፉን አወጣችሁት ድሮም ከበቅሎ ልጅ አንጠብቅም ማህበረ ሰይጣን ትላንትናም ዛሬም ነገም የተዋህዶና የኢትዮጵያ ውስጣዊ ጣለት ነው ለመሆኡ የናንተን አመሰራረት ለሚያውቅ ሰው እኮ ልክ የጠንቁዩ ታምራት ገለታ ቢጠዎች ናችሁ በጥንቆላውና የንጹሃን ሴቶችን ክብረ ንጽህና ስት ገፉ ኖራችሁ ሰው አስገድላችሁ አልበቃ ሲላችሁ የዛር መንፈስ ያለባትን ሴት ከዚያ ባለጌ መስራች ዲያቆን ተብዬአችሁ ጋር አስማምታችሁ ከመንግስት ጋር ተዋዳችሁ ቅዱሰ ቴዎፍሊዎስን አስገደላችሁ ጠላትነታችሁን የማይረሰ ጌታ ግን አይምራችሁም አልፋችሁ ደርሳችሁ ደሞ ቅዱስ ተክለሃይማኖትን በመርዝ ገደላችሁ አልፋችሁ መታችሁ ቅዱስ መርቆሬዎስን ለመግድ አልተፈቀደላችሁም ለምን ተሰደደ ይመትሉትም እንደለመዳችሁት ለምን አልበላነውም ብላችሁ ነው ግን አለ አምላክ ፈቃድ ምንም አይሆንም እና ተዋረዳችሁ በሰሜን አሜሪካ ተሰዶ ቢወጣም ህዝቡን ከእንደ እናንተ አይነት መናፍቅ ተኩላ የክረስቶስን ደም ሊያስከብር ህዝቡን ይዟል አሁንም ቅዱስ ጳውሎስን ለማጥፋት ጣራችሁ ነገር ግን የእግዚአብሔርን ነገር የውም እምነት የለሽ የጠንቃዮች ማህበር /ማህበረ ሰይጠን አያጠፋውም

እውንት ተሸፍና ብትኖርም
መጋለጧ አይቀርም

ማህበረ ሰይጣን ከመሆን እስላም መሆን ይሻላል
ማለትም ሁሉ በሙሉ ሳያምኑ መኖር ይሻላል
ያመኑ እየመሰሉ ያመኑትን ከሚያጠፉ እርኩሶች

ገና ገና ገና ጉዳችሁን በቪዲዮ የሚያወጣው ሰው ይመጣል እናንተን አያርገኝ እንደ ጴጥሮስ ማሀበሩን አላውቀውም የምትሉበት ቀን እሩቅ አይደለም!!!!!!

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)