November 1, 2009

አዲስ አበባ ሀ/ስብከት ያለምንም መፍትሔ ወደ ሌላ የተስፋ ወር

(አቤል ወለቴ)
በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ሥር የሰደደውን የአስተዳደር ችግር ለማስወገድ ተጀምሮ የነበረው እንቅስቃሴ “ለመጨረሻ ጊዜ መፍትሄ ያገኝ ይሆን?” በማለት የተዋሕዶ ልጆች በያሉበ በተስፋ ሲጠባበቁት የቆየው የወርኃ ጥቅምት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ብዙዎቹም የተጠቀሱት ችግሮች መፍትሄ ሳይገኝላቸው በድጋሚ ለግንቦቱ ምልዓተ ጉባኤ አስተላልፎታል።

በሐምሌ ወር በአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ እና በሌሎችም የሕዝብ ግንኙነት ጣቢያዎች እንደሰማነው ብፁዓን አባቶች ቅዱስ ፓትርያርኩ ላይ አንስተውት የነበረው መሠረታዊ ጥያቄ ተድበስብሶ ታልፏል። ይህንንም ጥያቄ ባነሱት ብፁዓን አባቶች ላይ ጥቃት ያደረሱት የቤተ ክህነቱ ተናካሾች ለፍርድ አልቀረቡም።

የቤተ ክርስቲያኒቱን ዘመንን ያልዋጀ ብልሹ እና ኋላ ቀር የአስተዳደር ችግር መፍትሄ ከማበጀት ይልቅ፤ የግለሰቦች ፀብ በማስመሰል አለባብሰው በይቅርታ አልፈውታል። ይቅር መባባሉ መልካም ቢሆንም መሠረታዊ እና መልስ ይሹ ለነበሩት የአስተዳደር በደል ጥያቂዎች ግን ምላሽ ማግኘት ነበረባቸው። ሚሊየነር ከሆነው ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጋር ተያያዥነት ያለው የብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ጉዳይ ሶስት ሙሉ ቀን ፈጅቶ፣ ብፁዕነታቸውም ጊዜያዊ የሥራ መደብ አግኝተው፣ ችግሩም በዘላቂነት ሳይፈታ አሁንም ለግንቦቱ ምልዓተ ጉባኤ መተላለፉን ሰምተናል።
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ከሌሎች ሀገረ ስብከቶች በተለየ ሁኒታ በሕገ ቤተክርስቲያን ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት ሕግ ቢቀመጥለትም ሕጉም በትክክል እየተተረጐመ አይመስልም። ሕገ ቤተክርስቲያን “የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት በ1991 ዓ.ም ቅዱስ ሲኖዶስ ባወጣው ሕገ ቤተክርስቲያን አንቀጽ 35/ ንዑስ አንቀጽ 3 መሰረት የሚመራ የአስተዳደር ዐቢይ ኮሚቴ አለው። ዐቢይ ኮሚቴው በቅዱስ ሲኖዶስ ይሰየማል” ይላል።
የዐቢይ ኮሚቴው አባላት፦
• ከቅዱስ ሲኖዶስ አባላት የሚመረጡ ሦስት ሊቃነ ጳጳሳት ወይም ጳጳስት፣
• ከጠቅላይ ቢተክህነት ሶስት አባላት፣
• ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሚመረጡ ሦስት አባላት፣
• በድምሩ ዘጠኝ አባላት ይኖሩታል።
የዐቢይ ኮሚቴው ሰብሳቢ በቅዱስ ሲኖዶሱ ከተመረጡት ሊቃነ ጳጳሳት ወይም ጳጳስ ወይም የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ይሆናል። የዐቢይ ኮሚቴው የአገልግሎት ዘመን ሶስት ዓመት ሲሆን እንደ አስፈላጊነቱ የኮሚቴው አባላት በሙሉ ወይም በከፊል ለተጨማሪ ሦስት ዓመት ብቻ ሊመረጡ ይችላሉ። ዐቢይ ኮሚቴው ተጠሪነቱ ለቅዱስ ሲኖዶስ ይሆናል።
የተቀመጠው ሕግ ይህ ሆኖ ሳለ ቅዱስ ፓትርያርኩ ግን ሀብታሙን (ሚሊየነሩን) የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት “የራሴ ሀገረ ስብከት ነው” በማለት ፈላጭ ቆራጭ የአገዛዝ ክንዳቸው ሲሰነዝሩበት ይታያሉ።

Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)