November 10, 2009

“የበርሊን ግንብ” ከወደቀ 20 ዓመት ሞላው በቤተ ክርስቲያናችን የተገነቡት የመለያየት ግንቦች መቼ ይፈርሱ ይሆን?

(ደጀ ሰላም፤ ኖቬምበር 9/2009)፦ ዓለማችን የበርሊን ግንብ (1961-1989)የፈረሰበትን 20ኛ ዓመት አክብሯል፤ እያከበረ ነው። ይህ በአንድ ሕዝብ መካከል ተገንብቶ ቆየው አስቀያሚ የመለያየት ምልክት በሕዝቡ ቆራጥ እርምጃ ፈራርሷል። የግንቡ መፍረስ የሚያስተምረን ምንድር ነው?

ዛሬ በቤተ ክርስቲያናችን የተገነቡ ብዙ አስቀያሚና ኢ-ክርስቲያናዊ ግንቦች አሉ። በአስተዳደር ደረጃ የሀገር ውስጥ አስተዳደር፣ ገለልተኛ እና ስደተኛ። በዘረኝነቱ ደረጃ የጎንደር ቡድን፣ የሸዋ ቡድን፣ የትግራይ ቡድን ወዘተ። በፖለቲካ አስተያየት የኢሕአዴግ ደጋፊ፤ የኢሕአፓና ሌሎች በውጪ የሚገኙ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ደጋፊ፣ “ፖለቲካ ውስጥ አልገባም” የሚለው ደጋፊ ወዘተ።

በአገልግሎት ዘርፍ ደረጃ ካየነው ደግሞ፦ የግል ሰባክያንና መዘምራን፤ ማህበረ ቅዱሳንና ሌሎች ማህበራት፣ የቲዮሎጂ ኮሌጆች ምሩቃን ቡድን ወዘተ። በክህነት ደረጃ ሕጋውያን (ያገቡ) ካህናት በአንድ በኩል መነኮሳት በሌላ በኩል ወዘተ። ልዩነቱ ብዙ ዓይነት ነው።

ምናልባት ይኽ አባባል ደጀ ሰላም እየለጠጠች (እያጋነነች) ወይም አንዳንድ ሰዎች አስተያየት ሲሰጡ እንደተመለከትነው “እየፈጠረች” ያመጣችው ሊመስል ይችላል። እንደ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ልጅነታችን ግን ይህንን ማወቅ ይኖርብናል። ይህ መለያየት በጣም መሠረት የያዘ ነው። በዚህ ውስጥ ሁሉ የነዚህ ቡድኖች መጫወቻ የሆነው ምዕመኑ ነው። ልክ የጀርመን ሕዝብ “ከምስራቅና ከምዕራብ” የነበረው በአንድ ልብ “እምቢኝ” ብሎ ይለያዩት የነበሩትን “የግንቡን ባለቤቶች” እንዳሳፈራቸውም አሁንም ምዕመናችን የኛን “ግንብ ገንቢዎች” አሻፈረኝ ብሎ ሊያሳፍራቸውና ቤተ ክርስቲያኑን ከነዚህ ጥቅመኞችና የመለያየት ሰባኪዎች ነጻ ሊያወጣት ይገባዋል። ለዚይ ደግሞ ሥራው ተጀምሯል። ዛሬ መጻፍ የጀመርነው “ፔቲሽን” ነገ አንድ ደረጃ አድጎ “የምንላችሁን የማትቀበሉ ከሆነ በእኛው ገንዘብ እየተንደላቀቃችሁ ቤተ ክርስቲያናችንን እንድትጫወቱባት አንፈቅድላችሁም” የምንልበት ቀን ይመጣል። ያን ጊዜ ስደተኛው ሆነ ገለልተኛው፣ በሀገር ቤት በእነ እንቶኔ ጥይት የተማመነው ሁሉ ምንም መግቢያ አይኖረውም። ከበርሊን እንማር!!!
ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን

13 comments:

tad said...

I am amazed that DS's conscious developed to this stage. I can't agree with you more. These are the real walls we should be able to abolish if we want the authentic change for our church.
God bless the moderator of DS.

Anonymous said...

wekitawi melikit new lehulachinim libona yisiten amen

Anonymous said...

Thank you brothers, we need more preachers like you. Very sensitive and current issue. We are one and will continue being one. We are with you Deje Selam.

Anonymous said...

I think this is one of the critical issue we need to discuss as children of EOTC. The issue remind me an article I read several years ago on this very blog and I succeed to find it in the archive & pasted below:

የጎንደር ምንቸት ውጣ … የትግሬ ምንቸት ግባ -ዘመነ መሳፍንት በቤተ ክህነት
(ነመራ ዋቀዮ ቶላ - nemerra@gmail.com)
.....

በኢትዮጵያ መንበረ ሥልጣን ለመቀመጥ በተለያዩ ገዢዎችና ነገሥታት መካከል አያሌ ጦርነቶች እየተደረጉ አንዴ አንዱ አንዴም ሌላው እያሸነፉ፣ አንዴ መንግሥቱን ወደላስታ ሌላ ጊዜም ወደ ሸዋ በሌላውም ወደ ጎንደርና ትግሬ ሲያዘዋውሩት እንደቆዩ በመጨረሻም ጠንካራ መሪ በጠፋባቸውና መሳፍንቱ የይስሙላ ነገሥታ እያስቀመጡ እስከመግዛት እንደ ደረሱ የቅርቡ ታሪካችን እማኝ ነው፡፡ ይህ የጥቃቅን መሳፍንት ዘመን በታላቁ ባለ ራዕይ መሪ በቋራው አንበሳ በአጼ ቴዎድሮስ ከተፈጸመ በኋላ አገሪቱ በአንድነት ለመቆየት ችላ ነበር፡፡ እርሳቸውን ተከትለው የተነሱት የትግሬው ዮሐንስም አገሪቱን በአንድነት ለመጠበቅ ችለዋል፡፡ የአድዋው ባለድል እምዬ ምኒልክም ዓለምን ባስደነቀው ጀግንነታቸው፣ ለዕድገት ከነበራቸው ትልቅ ተስፋ ባለፈም ከሁሉም በተሻለ የአገርን አንድነት ለመጠበቅ ችለዋል (ምኒልክንና ኦሮሞን አስመልክተው ለሚነሱት ጥያቄዎች መልስ መስጠት ከርዕሱ ውጪ ስለሆነ ታልፏል)፡፡ ከዚያ ወዲህ አንደኛውኑ መንበረ መንግሥቱ ወደ መሐል አገር ተሸጋግሮ ሊቆይ ችሏል፡፡

ዘመነ መሳፍንት እንዲህ ባለው መልኩ ፍጻሜ አግኝቷል ቢባልም ሽኩቻውና ፉክክሩ ዛሬ ድረስ ቀጥሏል፡፡ ይህ በተለይ ግዘፍ ነሥቶ የታየው ባለፉት ሠላሳ ዓመታት በተደረጉት ‹‹የራስን ዕድል በራስ የመወሰን›› ትግሎች ነው፡፡ በዘመነ መሳፍንት አስተሳሰብና ኋላም ከኮምኒስቶች በተዳቀለው አመለካከት ላይ የተገነባው ውየናና የአገራችን ዘመነኛ ፖለቲካ ሁሉም ራሱን ለቤተ መንግሥቱ ሲያጭና ሲያፎካክር ቢቆይም የተሳካለት ግን የትግሬው መሳፍንት ልጆች የሚመሩት ወያኔ ነው፡፡ እነሆ እስከ ዛሬ መንበሩን ጨብጧል፡፡ ታዲያ ይህ ሁሉ ታሪክና ሐተታ ከቤተ ክህነቱ ጋር ምን አገናኘው መባሉ ተገቢ ጥያቄ ነው፡፡ በእኔ አመለካከት የቤተ ክህነታችንና የመነኮሳቱ ችግር ይኸው ሥልጣንን ለመያዝ የመሽቀዳደም መሳፍንታዊ አመለካከት ነው፡፡ ሐሳቤን ትንሽ ዘርዘር አድርጌ ላብራራ፡፡

ቤተ ክህነት ምንም እንኳን መንፈሳዊ አገልግሎት የሚከናወንበት መንፈሳዊ አስተዳደር ቢሆንም ለብዙ ዘመናት ከቤተ መንግሥቱ ጋር በነበረው ቅርበት ምክንያት ቤተ መንግሥቱ ውስጥ ያለው በጎም ሆነ ክፉ ስሜት ተጋሪ መሆኑ አይቀርም፡፡ ከዚህም ስሜት አንዱ ሥልጣንን በአካባቢ የመያዙ ጉዳይ ነው፡፡ ቀደም ብሎ ለረጅም ዘመናት ግብጻውያን ጳጳሳት እየተሸሙ ይላኩ ስለነበረ የአገሬው መነኮሳት ራሳቸው ከሁሉ በላይ አድርገው አዛዥ ናዛዥ ለመሆን ዕድሉ አልነበራቸውም፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን በአስተዳደር ራሷን ችላ፣ የራሷን ልጆች ጳጳሳት አድርጋ መሾም ስትጀምር ግን ለብዙ ጊዜያት ታፍኖ የቆየው ‹መሳፍንታዊ› አስተሳሰብ ተገለጠ፡፡ የሚሾሙትን አበው ሃይማኖት ሳይሆን ወንዝና አውራጃ ማጥናት፣ የራስን ‹ወገን› ለማብዛት መሽቀዳደም ተጀመረ፡፡ በዚህ ረገድ ሥልጣን ‹ከእጄ አምልጣ ሸዋ ገብታ ቀረች› የሚለው የጎንደር ቡድን በአቋራጭ የጥንት ‹‹የበላይነቱን›› (የበላይነት ከነበረ ማለት ነው) ለማስመለስ ቆርጦ ተነሣ፡፡ ከራሱ ቡድን ውጪ ያለ ቄስንም ጳጳስንም ከመጤፍ ሳይቆጥር ራሱን ብቻ እያኩራራና እያጋነነ፣ ሌላውን እየናቀና እየገፋ፣ የዘረኝነትን አዝመራ እያስፋፋና እያጎለመሰ ሄዶ ድንገት በትግሬዎቹ መሳፍንት ልጆች ኃይልና ብልጠት ተበልጦ ሁሉን ለማጣት ተገደደ፡፡ ፓትርያርኩ ከሥልጣናቸው ወረዱ፡፡ ሌሎቹም ጎንደሬዎች ይዘውት የነበረው ወንበር ከሥሩ ተፈነቀለ፡፡ ‹‹የጎንደር ወጪት ይውጣ … የትግሬ ወጪት ይግባ›› ተባለ፡፡ ሥልጣን ከጎንደር ወደ ትግሬ ገባች፡፡ መርቆርዮስ ወረዱ … ጳውሎስ ወጡ፡፡ በዘመነ መሳፍንትኛ ብትመለከቱት የቋራው ካሳ ወረደ የትግሬው ካሳ ተሾመ እንደማለት ነው፡፡ ዘረኝነትን እያስፋፉ በሌላው ሲቀልዱ ኖረው በራሳቸው ብልሃት የመጣ ሌላ ዘረኛ ወንበራቸውን ቀማቸው፡፡ ተደላድሎም ተቀመጠ፡፡ ዛሬ እርሱን በዘረኝነት ቢያሙት ማንም የሚሰማቸው የለም፡፡ ‹ስልቻ ቀንቀሎ … ቀንቀሎ ስልቻ››፡፡

መቸም ዛሬ እውነትን መፈለግ ሞኝነት ስለሆነ ‹‹አንዱ ባንዳ ሰደበኝ›› ወይም ምናልባት ‹‹አንዱ ወያኔ ስሜን አጠፋው›› ሊሉ ይችሉ ይሆናል፡፡ በእነርሱ የዘር ጨዋታ ውስጥ የለሁበትም፡፡ የማንም ፍርፋሪ ፈላጊም አይደለሁም፡፡ ሁለቱም ቡድን ቤተ ክርስቲያናችንን እያጠፋና እያመሰ መሆኑን ነው የማውቀው፡፡ ስለዚህ የዘረኝነትን በሽታቸውን በሃይማኖት ስም ከሚያስታምሙት ‹‹በሽታቸውን አውቀው መድኃኒት ቢፈልጉለት›› ይሻላል፡፡ ዘረኝነቱን እነርሱ ሲያስፋፉት ትክክል የሚሆንበትና እነ አባ ጳውሎስ ሲያደርጉት ግን ስሕተት የሚሆንበት ምክንያቱ አይታየኝም፡፡ ሁለቱም ቡድኖች የመሳፍንት ዘመን ተፍካካሪዎች እንጂ የሃይማኖት ሰዎች አይመስሉም፡፡ ግባቸውም ቤተ ክርስቲያኒቱን መጠበቅ፤ ማሳደግና ማስፋፋት አይደለም፡፡ ጭንቀታቸው የወንበር ጉዳይ ነው፡፡ የሚያሳዝነው ግን ይህንን ሁሉ ምዕመን እንዲህ ያለጠባቂና እረኛ ማስቀረታቸውና አባት አልባ ማድረጋቸው ነው፡፡ ስለዚህ በእውነት ለቤተ ክርስቲያን የሚያስቡ ሁሉ የነገሮችን ምንጭና መነሻ ማጤን አለባቸው፡፡ በሃይማኖትና በአገር ስም የግላቸውን ፈቃድ ለመፈጸም ደፋ ቀና የሚሉ ሰዎችን ስሜትና ፍላጎት ስናስፈጽም መኖር የለብንም፡፡ በተለይም ምዕመናን ከነዚህ ዘረኛ መነኮሳት ቅጥ ያጣ ውድድር ራሳቸውን ገሸሽ ማድረግ አለባቸው፡፡ እኛ በምንሰጣቸው ድጋፍ ነው እንዲህ ቤተ ክርስቲያኒቱን መጫወቻ ያደረጓት፡፡
(ይቀጥላል)

Anonymous said...

According to our sins and accusations,there will be more than these kinds of administrations from the government and the Church.For us,these problems by the rulers of the Country and the Church are minimum because we are full of hate,jealousy,sin,etc...As Gedle St.Zosimas tells that if we continue in our disobedience to Almighty God, Our Lord put cruel and killer leaders of the Church and the Country.For us,it is very good situation,we don't want repent;

Anonymous said...

Thank you Nemera,
It is really intersting article and comments if you read it carefully.
Bertulign,

Anonymous said...

Selam all:
Deje Selam: you have come up with a good message that all EOTC members everywhere should take to heart. Keep it up!

To "Anony..." who posted Ato "Nemera Waqeyo's " article:
I wouldn't say it is a bad comment/article. But we all have to try to stay objective on these kinds of difficult issues. Not every "Menekusie" or "Kahn" of EOTC is ethnocentric or racist or after his own glory. There are so many that would die for God's Church and for the unity and prosperity of EOTC. Remember that is how we get the great saints (fathers and mothers) of the Church.

But unfortunately they might be out numbered because of the division that is apparent in the laity (mi'emenan). If members everywhere were united, these problems would have died a long time ago. But problems stated above stay because most of us (members) prefer to stay indifferent. Actually, not many of us really care enough. It is all talk.
As the famous conservative of the 18th century once said: " All that is necessary for evil to triumph is for good men to do nothing". Hence, we all are part of the problem, some how.

What do you think ?
God bless,

"Wey sew kentu!" ale yagere sew.
Tazabiw

Anonymous said...

ይህ አጀንዳ በእርግጥም ወቅታዊ ነው ወቅታዊ ብቻም አይደለም መሰረታዊም ነው በየአቅጣጫው ያሉ የቤተ ክርስቲያኒቱ መሪዎችና አብዛኛዎቹ አገልጋዮች በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እንደነበሩት የእምነቱ መሪዎች ከመስመር ወጥተዋል ከዓላማቸውም ስተዋል ሰባኪዎቻችን ክርስቶስን ሳይሆን ራሳቸውን ነው የሚሰብኩት እኔ እበልጥ እኔ እበልጥ ፉክክር ነው የያዙት ተሰባኪዎችም የሰባኪዎች ቲፎዞ በመሆን እያንዳንዱ የሰባኪ እገሌ አድናቂ በመሆን የማይከፈለው አድቨርታይዘር ሆኖ ነው የሚታየው
ሁሉ ነገር ከስጋዊ ጥቅም ጋር ብቻ በመያያዙ መንፈሳዊነት ከሁሉም ዘንድ እንደ ጉም በኖ እንደ ጢስ ተኖ ጠፍቱዋል ገንዘብ፤ ውዳሴ ከንቱ ስልጣን የመንፈሳዊነቱን ቦታ ያለአንዳች ተቀናቃኝ ተቆጣጥረውታል ስለሆነም በትምህርቱ የምእመናንን ነፍስ ማርኮ ለንስሃ የሚየበቃ ሰባኪ ሳይሆን ለግዜው እንደተዋናይ አስቆና አዝናንቶ የሚሸኝ በዚህ ችሎታውም ከተሰባኪያኑ አድናቆትን የሚሻ ነው በዚህ ላይ እንደ እግዚአብሄር ፈቃድ ሳይሆን እንደ መድረኩ ባለቤተች ፈቃድና ፍላጎት እነርሱን አስደስቶ ድርጎውን ለማስጠበቅ የሚባዝን ነው የሚበዛው
እንዲህ አይነት እከብር ባይ ልቡና ይዘው የቤተ ክርስቲያኒቱን መድረክ የተቆጣጠሩ ሰባክያን ባሉበት ምእመኑ የመንፈስ መነቃቃትና መታደስ እንዴት ሊያገኙ ይችላሉ አቁዋም በሌላቸው ሲፋጅ በማንኪያ ሲበርድ በእጅ በሚመገቡ ኢትዮጵያ ሲሄዱ እዚያ ያለውን መንፈስ ጠብቀው የሚራመዱ ወዲህ ሲመጡ የዳያስፖራውን ፖለቲከኞች የልብ ትርታ አዳምጠው ስብከታቸውን በእነርሱ ስሜት የሚቃኙ እንደዚህ አይነቶቹ የስም ሰባኪያን እወርን አውር ቢመራው እንደተባለው በእነርሱ ቅኝት የተቃኘ ሁሉ እንኩዋን እራሱን ለለውጥ ሊያዘጋጅ የእውነትን አርማ ይዘው ለተነሱትን ሳይቀር እንቅፋት ነው

እና ወገኖች የእኛ ቤተ ክርስቲያን ችግር ሳስበው ሳስበው ደከመኝ አለ እንደተባለው ሰውየው እኔም ሳስበው ጭንቅላቴን ይከብደዋል ግን በደሙ የዋጃት ወልደ አብ ወልደ ማርያም ስለማይተዋት አንድ ቀን ቤቱን ያጠራል በዚያን ቀን እነዚህ በምእመናን ነፍስ ጢባጢቦ እየተጫወቱ ያሉት የቤተ ክርስቲያኒቱ መሪዎችና ሰባክያን የእጃቸውን ያገኛሉ ፍርድ ከእግዚአብሄር ቤት የሚጀምርበት ቀን ሩቅ አይደለም

Anonymous said...

Tazabiw:

I like your approach. You make sense. But can we, Ethiopians, be objective on any issue ? Do we even want to ? I don't know. I don't see that anywhere.

God bless,
Ankiro

Anonymous said...

The solution to our divisions is just like diagnosing a desease and prescribing the correct medicine.
1.When did this problem emerged?
2.Why did it happen?
3.Why has this division aggravated from time to time instead of becoming narrower and narrower?
4.What should we do now and in the future to overcome this CURSE and bring up unity both to our church and our country?
In my opinion,answering these questions genuinely may help
realize our dream-ONE COUNTRY,ONE TEWAHEDO.
Answers:
1.It has always been there to some extent,but it officially and widely started to spread as the kings of divide and rule came to power in 1991.They started to divide the country in ethinic/blood lines, and to everybody's surprise, the foolish opponents of this same evil policy repeated the same mistake to the advantage of the dividers.
2.Why? The reasons have two sides.The first one implied above- to weaken the unity of opposition and to blindly support in their/supporters view their leaders both in the palace and in the church.The other is based on a true cause-not to collaborate with the ethnocentric leaders and illegitmate church fathers.The cause was right,but the methods of reaction taken by the opponents of evil were, unintentionally, I believe, proved to have been to the benefit of the enemy.However, with all its predicments,saying no to ethnic politics and rejecting those religious fathers who supported this unchristian policies has always been RIGHT!
3.Why aggravated? Because:a.Smart and canny people took over the leadership positions of the opposition
b.Undercover prodividers have been doing their assignment successfully
c.We are all still foolish,have not learnt a lesson or two.
4.Solution: Stick to the true cause,unite as opposition,expolre new and effective strategy,appeal to GOD and pray hard.
May the GOD of Ethiopia give us Unity and Peace.

memher Werkineh said...

“የበርሊን ግንብ” ከወደቀ 20 ዓመት ሞላው በቤተ ክርስቲያናችን የተገነቡት የመለያየት ግንቦች መቼ ይፈርሱ ይሆን?"
መልስ፦ ሁላችን ለንስሐ ስንዘጋጅ። ደጀ ሰላም ይህን ርእስ ይዞ መቅረቡ መልካምና ወቅታዊም ይመስለኛል። እንግዲህ የብርሊን ግንብ ለምን ተገንብቶ እንደ ነበር? እነማን እንደ ግነቡትና ለምን እንደገነቡት? ምን ያህል እንደ ቆየ? አሁንም ለምን እንደፈረሰና በ እነማን እንደፈረስ? ለምን እንደ ፈረሰ? መመርመር ያሻል። በቤተክርስቲያናችን ከማለት በቤተክህንት የሚለውን ቃል ልጠቀም እፍልጋለሁ። ምክንያቱም በአገር ውስጥም ሆን በውጭ አገር የምትገኘው 2ኛውን ትርጉም የተሰጣት ቤተክስቲያን በምታበረክተው ሃይማኖታዊ አገልግሎት ልዩነት የላትምና። የመለያያት ልዩ ልዩ ግድግዳዎች የተገደግዱ ወይም ግንቦች የተገነቡ በቤተክህነት ስፍራ ነው። ይህ ማልት በአስተዳደራዊ ስልጣን ወይም በአምራር የበላይነት የመሆን ሽጉቻ ማለት ነው። እነዚህ ችግሮች ለማስወገደና የዘረኝንትን መንፈስ ለመቅረፍ፡ ማለት እንደተባለው የተገነቡትን የመለያያት ግንቦች ለመናድ፡ ያልፈውን ታሪካችን ማየት ያስፈልገናል። “ ነመራ ዋቀዮ ቶላ” በተባለው ለመገልጽ እንደተሞከረው ካለፈው ጠንካራና አስደናቂ ታሪካችን ባሻገር አስቀያምና ሳንሳሳል እንዲሁ ያስቀረን ይህ የዘረኝነት ወይም ያለመተማመንያና የመለያያት አስተሳሰብ ነው። ካለፈው የምንማረውም ይህ ነው። ሰለዚህ በቤተክህነታችንም ሆነ በአገራችን የተገነባው የመለያያት ግንብ መናድ የሚቻለው ሁላችን እያንዳንዳንዳችን ከዚህ የእደገትና የሰላም ጠንቅ የሆን የዘረኝነት መንፍስ ስንላቅቅ ብቻ ነው። ላፍታ ራሳችንን እንፈትሽና ከዚህ የተለይን መሆናችንንና አለመሆናችንን መረዳት እንችላለን። በመሆንም ይህ እርም መሆኑን በመገንዘብ ከመሪ እስከተመሪ ካለተረዳን ግንቡን ማፍረስ አይቻልም። ሌላስ ቀርቶ “ነምራ “የጎንደር ምንቸት ውጣ … የትግሬ ምንቸት ግባ -ዘመነ መሳፍንት በቤተ ክህነት” ብሎ የጻፈውን ልብ ብላችሁ ተመልከቱ። እውንትነት ያለው ሐሳብ ቢሆንም በቤተክህነት ላይ የተገነባው የመለያያት ግንብ በጎንደርና በትግራይ ብቻ አስመስሎ ማቅረብ ፍጽም ስሕተት ነው። አስቀድሜ ለመግልጽ እንደሞከርኩት አቅም ከማጣትና ብሎም ፈቃደ እግዚአብሔር ስላልተጨመረበት እንጂ በዚህ ርጉም መንፈስ ያልተጠቃ የለም። አንድ ነገር ለበላችሁ። በቤተክርስቲያናችን ከራስዋ ሊቃውንት ሊቃነጳጳትን መርጣ መሾም እንዳለባት በማመን ለአያሌ ዓመታት የተደርገው ክርክር ዕልባት አግኝቶ በንግስተ ነገስታተ ዘወዲቱ ዘመነንግስና። ኢትዮጰያ ከራስዋ ሊቃውንት ሊቃነጳጳት የመምረጥ ነፃነት ስታገኝ ይህ የቤተክህነት የዘር ቆጣራ እንደተጀመረ አያጠራጥርም። በተለይ ከደብረ ሊባኖስ ገዳም ( ዘኢተወልደ እምተክለሃይማኖት ) የጵጵስና ወይም የፕትርክና መአርግ አይሰጠውም በማለት) ደንግገውት እንደነበር የትናንትና ትዝታ ነው። በዚሁም ሁኔታ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፊሎስ የፓትረያርክ ስልጣን እንዳይሰጣቸው የተደረገው ተቃውሞ አይዘነጋም። ይሁን እንጂ ፀጋ እግዚአብሔር ወይም ስልጣን ያለ እግዚአብሔር ቅዱስ ፈቃድ ስለማይገኝ ኢሃይማኖታዊ የሆነ አስተሳሰብና ፍላጎት አለሰራም። ከዚህም የተነሳ እስከ አሁን ድረስ “ ነምራ ነኝ ባዩ” በጎንደርና በትግራይ ብቻ ሳይ ሆን በሽዋውም የነበረውና አሁንም ያለው የዘረኝነት መንፈስ ቃላል አይደለም፡፡ ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ጀምሮ እስከ ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ያለውን ሒደት ስንመለከት አንደ አይነት ነው። በስደት ያሉትን ሲኖዶሳችን ኢትዮጰያ ነው ነገር ግን አስተዳደሩን አንቀበልም የሚለው አባባል ከየት እንደመነጨ መገመት አያዳግትም። በመሆኑም የበርሊን ግንብ የፈረሰው በያንዳንዳንዱ የጀሪመናዊ ልብ የንደነትና የሰላም መንፈስ በመስፈኑና ያለፈው ተግባራቸው አግባብ እንዳልነበረ በመረዳታቸው ነው። ሰለሆነም በቤተ ክህነታችን የሚታየው የመለያየት ግንብ ለማፍራስ እያንዳንዳችን ጣታችንን ወደ ሌላ ሳንቀስር ጥፋቱ የጋራችን ነው የሚለውን አስተሳሰብ ስናመጣ ነው።
የሰላምና ይፍቅር አምላክ የልባችንን ዓይን ይክፈትለን።

Anonymous said...

To the last comment writer in Amharic,do not try to divert attention.There were administative weaknesses,incompetence and backwardness in the past.But your attempt to blame all and equate today's ethnocentric leaders in the church and in the government with the former ones is wrong.Ethiopia and the Ethiopian church have never been in such a dangerous situation in history.This is so because of the wrong political policies of the ruling group and its supporters in the church leadership.The integrity of the country and the sovereignity of the orthodox church were not negotiable under any circumstances during former leaders of the church or the state.This is not there now.If there is good offer,they are for sale today ! How may orthodox followers were sold out in the last 18 years? At least 10,ooo,ooo!And how much portion of the country????? BUT WE CAN CHANGE THE COURSE IF WE REALLY UNITED. UNITED IN VISION AND ACTION.Not more than 50 or less individuals are carrying out the destruction in that country and our church.So lets do our share.Those who pray, go ahead,those who do otherwise too,go on.WITH THE HELP OF GOD MAY VICTORY BE TO TEWAHEDO AND ETHIOPIA.

Anonymous said...

It is a good idea to discuss on such important issue for our church. But if we need a very sincere discusssion, we need to look the problem from the bottom. How come the church division started in 1991 or 1992 G.C? How the previous Patriach Abuna Merkorios left the position? Is that really legitiment to create another Synod in exile accroding to the church's Dogam and Canona? How can we bring the "independednt churchs" to the mother church? The split is continuing every where in America and other parts of the world. But just picking one part of the problem and try to solve the whole problem, in my opinion, is not realistic. To answer some of the questions posted by the previous bloggers, I do not remember that the ethnic division has exasperated in any previous Patriarchs as in the currnet patriarch. The current problem is the worst in our church's history. Let's discuuss on the above very improtant issues and then we will come to the solutions and also see if we all can stand together to solve the problem. If all of us united, God will be with us and also our sprititual fathers will listen to the memenan. Let's Pray and ask guidance from the Almighty God.

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)