November 18, 2009

ላሊበላና አካባቢውን ለማልማት 135 ሚሊየን ብር ተመደበ

ደሴ ኀዳር 8/2002/ ዋኢማ/ በዓለም አቀፍ ደረጃ በቱሪዝም ማዕከልነቱ የሚታወቀውን የላሊበላ ከተማና የአካባቢውን የቱሪስት መስህቦች ለማልማት የዓለም ባንክ 135 ሚሊየን ብር መመደቡን የሰሜን ውሎ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ አስታወቀ።
የመምሪያው ኃላፊ አቶ አደማሱ ተገኝ ዛሬ ለዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል እንዳስታወቁት፤ ገንዘቡ የተመደበው በተያዘው ዓመት የላሊበላ ከተማን ጨምሮ በ42 ኪሎ ሜትር ዙሪያ የሚገኙ የቱሪዝም ሀብቶችን ለማልማት ነው።
አካባቢው ከፍተኛ የተፈጥሮ ሃብት መጎዳት የደርሰበት በመሆኑ ተራራማና ሜዳማ ስፍራዎችን መልሶ የማልማትና ኢኮሎጂውን የመጠበቅ ተግባር እንደሚከናወን ኃላፊው ገልጸው፤ ከሚለሙት የቱሪዝም ሀብቶች መካከል በላሊበላ ከተማ ዙሪያ የሚገኙት ብልባላ ጊዮርጊስ፣ ቅምቅሚት ሜካኤል፣ ይምርሀን ክርስቶስ፣ የቀይ ቀበሮ መገኛ የሆኑት የአቡነ ዮሴፍ ተራራና ዋሻዎች ይገኙበታል ብለዋል።


በላሊበላ ውቅር አብያተ-ክርስቲያናት ዙሪያ የሰፈሩና የተጠለሉ የኅብረተሰብ ክፍሎችንም ወደ ሌላ ስፍራ በማስፈርና በማቋቋም ቅርሶችን ከሰው ንክኪ ነጻ የማድረግ ተግባራት እንደሚከናወን የገለጹት ኃላፊው፤
ያረጁና ጉዳት እየደረሰባቸው ያሉ ቋሚ ቅርሶች እንደሚጠገኑ፣ የመንገድ፣ የውሃና የጤና ተቋማት እንደሚገነቡም ተናግረዋል።

ኘሮጀክቱ ረጅም ዕድሜ ያስቆጠሩ በላሊበላና አካባቢው የሚገኙ የተፈጥሮ፣ ሃይማኖታዊና ታሪካዊ የመስህብ ሀብቶችን ደኅንነት መጠበቅ፣ የቱሪዝም ሀብቶችን ተጨባጭ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ እንዲኖራቸው ማድረግና ለጎብኝዎች አመች የመሠረተ-ልማት አገልግሎት ማመቻቸት ላይ እንደሚያተኩር ከአቶ አደማሱ ገለጻ ለመረዳት ተችሏል።
Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)