October 24, 2009

ቅዱስ ፓትርያርኩ “ይቅርታ አድርጉልኝ አባቶቼ፤ ሰዎች አሳስተውኝ ነው” አሉ፤

(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 23/2009)፦ ቅዱስ ፓትርያርኩ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ከቅ/ሲኖዶስ አባላት አባቶች ጋር ሰላም ለመፍጠር ባደረጉት እንቅስቃሴ በቅርቡ ስለተፈጠሩት ችግሮች “ሰዎች አሳስተውኝ ነው” ማለታቸውን ምንጮቻችን አስታወቁ።

“እርቅ ለማውረድ” በሚል በተከናወነ የሽምግልና ውይይት ላይ ቅዱስነታቸው ተናግረዋል እንደተባለው ከሆነ ከብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ጋር ያላቸው አለመግባባትም ሆነ ሌሎች ተመሳሳይ ችግሮች የተፈጠሩት ሰዎች ስላሳሳቷቸው መሆኑን መናገራቸው ተሰምቷል። ምንጮቻችን ጨምረው እንዳብራሩት ቅዱስነታቸው “ሰዎች ያሳሳቷቸው” ስለየትኛው እንደሆነ፣ የአባቶች በር መሰበርን ይጨምር አይጨምር ግን አላወቁም።

ቅዱስ ሲኖዶስ ካለፈው የግንቦት ወር ወዲህ ጠንካራ ችግር የገጠው ሲሆን የዚህ ውጣ ውረድ አካል የሆኑትና ስማቸው በተደጋጋሚ የሚነሣው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የነበሩት አቡነ ሳሙኤል ከፓትርያርኩ ጋር እርቅ ማውረዳቸው የተሰማ ሲሆን ይህ ማለት ግን ከዚህ በፊት ያነሱትን አጀንዳ ትተዋል ማለት እንዳልሆነ ታውቋል። ከአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ስለተነሱበት ሁኔታ ቅ/ሲኖዶስ በነገው ውሎው ይነጋገራል ተብሎ ይጠበቃል።

በተያያዘ ዜና ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ያለ አ/አበባ ሀ/ስብከት ፈቃድ በየትኛው የአዲስ አበባ ደብርና ገዳም ሄደው መቀደስም ሆነ ማስተማር እንዳይችሉ የሚያግድ ደብዳቤ መውጣቱ ታወቀ። ታይቶም ተሰምቶም በማይታወቅ ሁኔታ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በራሳቸው ፈቃድ ተነሥተው፣ ሄደው እንዳይቀድሱ እንዳያስተምሩ “እገዳ” የተጣለባቸው የዲሲና አካባቢው ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም በመርካቶ ራጉኤል ሲቀድሱ የብፁዕ አቡነ ሳሙኤልን ስም በቅዳሴ በመጥራታቸው እንደሆነ ታውቋል።

በቅርቡ ከኦስትሪያ መጥተው የሥራ አስኪያጅነትን ሃላፊነት በተቀበሉት በቀሲስ ፋንታሁን ሙጬ ፊርማ ወጪ የተደረገው ይኸው ደብዳቤ አባቶችን ማስቆጣቱ ታውቋል።
Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)