October 21, 2009

"ቤተክርስቲያን በልማቱ መስክ የምታደርገውን ተሳትፎ ይበልጥ አጠናክራ ትቀጥላለች":- የዓመቱ ምርጥ ቀልድ

(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 21/2009)፦
ይህ ከዚህ በታች ያለው የ“ENA” ዜና ስለ ቤተ ክርስቲያናችን “ዕድገት” እና “ጥንካሬ” የሚያትት ነው። በርግጥ ለሚዲያው ፍጆታ እና “ለመሸዋወድ” ይጠቅም ካልሆነ በስተቀር ቤተ ክርስቲያናችን ያለችበት ሁኔታ መቸም አይጠፋንም። ገዳሞቻችን እንዴት እንዳሉ፣ ምዕመናችን ያለ እረኛ እንዳለ፣ የገጠር አብያተ ክርስቲያናት “የካህን ያለህ” እያሉ በመዘጋት ላይ መሆናቸው የአደባባይ ምሥጢር ነው። ለቤተ ክህነት ሃላፊዎች ግን ይህ ሁሉ የለም፤ ሻምፓኝ ለመክፈት፣ ኬክ ለመቁረስ ደግሞ አሁን “የልማት አርበኞች” የምትባል ፖለቲካ ቀመስ ፋሺን ጀመሩ። አሳፋሪዎች!!!አዲስ አበባ, ጥቅምት 11 ቀን 2002 (አዲስ አበባ)- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከመንፈሳዊ አገልግሎት ጎን በልማቱ መስክ የምታደርገውን ተሳትፎ ይበልጥ አጠናክራ እንደምትቀጥል አስታወቀች፡፡ ቤተክርስቲያኗ በተለያዮ የልማት ዘርፎች የተሳተፉ 45 አብያተ ክርስቲያናትን ትናንት ሸልማለች፡፡
ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ የአለም አብያተ ክርስቲያናት ፕሬዚዳንት አብያተ ክርስቲያናቱ ሲሸለሙ እንደገለጹት ቤተክርስቲያን በልማት መስክ በስፋት በመሳተፍ ለአገር እድገት የበኩሏን አስተዋጽኦ እያበረከተች ናት፡፡
በአሁኑ ወቅተ በርካታ አብያተ ክርስቲያናት በልማት ዘርፍ በመሳተፍ ውጤት እያስመዘገቡ ነው ያሉት ፓትርያርኩ ይህ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልጸዋል፡፡

በሰሩት የልማት ስራ ለሽልማት የበቁት አብያተ ክርስቲያናት የተመረጡት ከመላው አገሪቱ ሲሆን ጳጳሳትና የሰበካ ጉባኤ አባላቱ ልማትን የበለጠ አጠናክረው መቀጠል እንዲችሉ ጀኔሪተር፣ የውሃ ፓንፕ፣ ኮምፒውተርና ሌሎች ሽልማቶች ተሰጥቷቸዋል፡፡

ሽልማቱን ከተቀበሉት መካከል የናዝሬት ዶብረ ፀሐይ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ መላከፀሐይ አባ ገብረማሪያም ወልደሐዋርያት እንዳሉት ቤተክርስቲያን በልማቱ መስክ መሳተፏ ለድሕነት ቅነሳው የበኩሉን አሰተዋጽኦ እያበረከተ ነው፡፡

ናዝሬት ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ከተገነባው ትምህርት ቤት በወር እስከ 76 ሺህ ብር ገቢ የሚገኝ በመሆኑ የቤተክርስቲያኗ አገልጋዩች ከተረጂነት መላቀቃቸውን ገልፀዋል፡፡

ሌላው ተሸላሚ የምስካይየ ሕዙናን መድሐኒ አለም ገዳም ዋና ፀሐፊ ቀሲስ ሰይፉ ጌታቸው በኩላቸው ሽልማቱ ቤተክርስቲያን የጀረችውን የልማት ስራ አጠናክራ እንድትቀጥል ያበረታታል ብለዋል፡፡

በአሁኑ ወቀት ቤተክርስቲያን በትምህርት ቤት፣ በጤና ጣቢያ እንዲሁም በሌሎች የማሕበራዊ አገልግሎቶች ላይ በመሳተፍ እራሷን መቻሏን አመልክተው ሁሉም ይህንኑ ፈለግ መከተል እንደሚገባቸው ተናግረዋል፡፡

ቤተክርስቲያን በልማሑ ዘርፍ መሳተፏ ከአገልጋዮጓቿ አልፎ ሕብረተሰቡን የሚረዳ በመሆኑ ይህንኑ በማጠናከር በአሁኑ ወቅት ገዳሙ በ19 ሚሊዮን ብር የኮሌጅ ግንባታ እያካሔደ መሆኑን ጨምረው ገልፀዋል፡፡
Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)