October 27, 2009

ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ ሳይሰበሰብ ዋለ፤ ነገ ይቀጥል ይሆናል

• የአቡነ ሳሙኤልን የሥራ ሁኔታ እንዲያጣራ የተቋቋመው ኮሚቴ “ጥፋት” አላገኘባቸውም፤
• አባ ሰረቀ የተቃውሞ “ጋዜጣ” እያዘጋጁ ነው፣
(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 27/2009)፦ ካለፈው ሐሙስ ጀምሮ ሲካሄድ የሰነበተው የቅ/ሲኖዶስ የጥቅምት ጉባዔ ዛሬ ሳይሰበሰብ የዋለ ሲሆን ምክንያቱ ቅዱስ ፓትርያርኩ ለሥራ ጉዳይ ወደ አኩሱም በማቅናታቸው መሆኑ ታውቋል። ጉባዔው ነገ በድጋሚ በመሰብሰብ ወሳኝ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል። ባለፉት ጥቂት ዓመታት አዲስ አበባን በሥራ አስኪያጅነት እና በሊቀ ጳጳስነት ባስተዳደሩበት ጊዜ “የሚያስመሰግን ሥራ ሠርተዋል” የሚባሉት የብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ጉዳይ ገና እልባት አላገኘም። ቅዱስነታቸው አዲስ አበባ የተመለሱ ስለሆነ ስብሰባው ነገ ይቀጥል ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።


በተያያዘ ዜና የብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ሀገረ ስብከት በሆነው አዲስ አበባ ተፈጽሟል የተባለውንና ከሀ/ስብከታቸው እንዲነሡ ያስከሰሳቸውን የ“ሙስናና የአስተዳደር ችግር” እንዲያጣራ ባለፈው ግንቦት ወር 2002 ዓ.ም ማግስት የተቋቋመው ኮሚቴ ሊቀ ጳጳሱን ከተሰነዘሩባቸው “የጥፋት አስተያየቶች” ነጸ አውጥቷቸዋል። ብፁዕነታቸው ጥፋት ባልተገኘባቸው ሁኔታ ይልቁንም በኮሚቴው ማጣራት “አስመስጋኝ” ሥራ ሠርተው ሳለ ከሀ/ስብከታቸው እንዲነሱ መወሰኑ አስገራሚ ሆኗል።

በሌላ ተያያዥ ጉዳይ ከሰንበት ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ፈላጭ ቆራጭነታቸው ጋብ እንዲሉ የበላይ ሊቀ ጳጳስ የተሾመባቸው አባ ሰረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል ይህንና ተያያዥ ጉዳዮችን በተመለከተ ያላቸውን ተቃውሞ ለመግለጽ አንድ ጋዜጣ በማዘጋጀት ላይ መሆናቸው ታውቋል። በመምሪያው ስም ያሳትሙታል ተብሰሎ በሚጠበቀው በዚህ ጋዜጣ ላይ ቅ/ሲኖዶስ አባላት አባቶችን ጨምሮ ሌሎችንም ይጠቅሱበታል ተብሎ ይጠበቃል። አባ ሰረቀ በቦታቸው ያላቸው ሥልጣን ከቀነሰ “የልብ የልባቸውን” ተናግረው በፊት ወደነበሩበት ወደ አሜሪካ ሳይሄዱ አይቀርም የሚል አስተያየት አለ።

16 comments:

Anonymous said...

I it is better to ask God to bring the bright day to our church. There is nothing nice thng we can hear. So please wendemoch and Ehtoch Tseleyu.

Egziabeher yerdan.

Anonymous said...

ቅዱስነታቸውም ሆኑ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት መነኮሳት አይደሉም እንዴ፡፡ ታዲያ ምነው እንዲህ ስጋውያንና ፈሪዎች ሆኑ፡፡ የቀድሞው ፓትሪያርክና ተከታዮቻቸው ፈራን ብለው አገር ጥለው ጠፍተው የራሳቸውን ጎጆ ቀለሱ፡፡ የቀሩት ደግሞ መለካውያን ሆኑ፡፡ እግዚኦ!

Ze Dima said...

"የቅ/ሲኖዶስ የጥቅምት ጉባዔ ዛሬ ሳይሰበሰብ የዋለ ሲሆን ምክንያቱ ቅዱስ ፓትርያርኩ ለሥራ ጉዳይ ወደ አኩሱም በማቅናታቸው መሆኑ ታውቋል።"
Is there any other urget and sacred meeting than the meeting of the Holly synod. Is it not the apex all the bodies of the church. Then where is going? To do what in Axum? or is there any other plot?

Anonymous said...

“አባ ሰረቀ በቦታቸው ያላቸው ሥልጣን ከቀነሰ “የልብ የልባቸውን” ተናግረው በፊት ወደነበሩበት ወደ አሜሪካ ሳይሄዱ አይቀርም የሚል አስተያየት አለ።”
Do you think that America will be save heaven for him? I don’t think so

Anonymous said...

"አክሱም"፡ምን፡ተፈጠረና፡ነው፡ሰውዬውን፡የ
ሲኖዶሱን፡ስብሰባ፡አስጥሎ፤የሚያስኬድ?!

ይህ፡ለሲኖዶሱ፡ያላቸውን፡ንቀት፡ያመለክታል።
ይህን፡አለመረዳት፡በቤተ፡ክርስቲያናችን፡ላይ፡በ
መፈጸም፡ያለ፡የበደል፡በደል፡ነው!

ጎበዝ፣ምሥጢሩ፡መመሪያ፡ለመቀበል፡እዚያው፡
አዲስ፡አበባ፡ውስጥ፡ያለ፤"ፓትርያርካዊ"፡ጉዞ፡መ
ሆኑን፡እንረዳ!

ተዋህዶ፡ኦርቶዶክስን፡ቀለው፡አቀለሏት!!!

መድኃኔዓለም፡የሚበጀውን፡ያድለን!

እመ፡ብርሃን፡ከኛ፡ጋር፡ትሁን!

እግዚኦ፡መሐረነ፡ክርስቶስ!

በእንተ፡እግዚእትነ፡ማርያም፡
መሐረነ፡ክርስቶስ!

አሜን፤አሜን፤አሜን።


ሰይፈ፡ገብርኤል።

Anonymous said...

Talakun guba'e sayfetsimu wede aksum mehedachewu lemengawu na lebetekiristiyan yemayigedachewu silal honuu newu gin sinodoskalkome aksum indeminoor alawekum?gin aytaweqim menoriachewu vatikan/Rome/yihon !

HANA said...

አረ የ ሰው ያለህ ……እኝህን ሰው የሚገላግለን ማን ይሆ
መቺም የቤተሰብ ጉዳይ ሆኖ ባቸው ይሆን ?
እሳቸውም ተቸገሩኮ! መቸም የስጋ ነገር!
ምንአይነት ንቀት ነው እንዲህ ያድረባቸው
አክሱም እነዲህ አይነት ሰው አልበቀለባትም
አክሱም ማልት ፣የቅዱሳን አገር ፣የሀይማኖት መብቀያ
የነአብርሀ ወ አዕብሐ አገር ምንጉድ የሆን የመጣብን
በድሜ ዪ እነዲህ አይነት ውርደት በ/ቤተ/ክ ላይ
የግፍግፍ ደርሶባት አያውቅም
መድሀኔአለም ክርስቶስ የቤተክርሰቴአን አምላክ ይፍርድባቸው.

Thank you DS

gorgoreyos said...

ygermal; ato seriqe mikaget gemir!!! ewnwtgna korat papa yetfa! wyzemn!!

Anonymous said...

ውነትም ሰረቀ ። ውነትን ሰረቃት ።ሰራቂ ።

Anonymous said...

ሰውየው ለፓርቲ ሰብሰባ ነው መሰለኝ የተጠሩት።ወይ ጉድ የመንፈስ ቅዱስን ስብሰባ ረግጦ የሚህድ ፓትርያክ።አይ አባት
፤አይ ፓትርያክ

ኮተሊኩ ለስብሰባ said...

ኮተሊኩ ለስብሰባ ሲጠራቸው ቫቲካን ለመድረስ ቸኩለው ነበረ። አዚህ ግን አቁዋርጠው ወጡ።ይሕ ሲኖዶስ ከዛ ያነሰ ከብር ነው ያለው ማለት ነው?
ባመት ሁለት ጊዚ የሚደረግን ሰብሰባ ረግጦ መውጣት ምን የሚሉት ንቀት ነው። ባባ ጳውሎስ ዘመን ምን ያልታየ ነገር አለ።

Anonymous said...

seerqe means ""be light" bu not thief

Dan said...

"የቅ/ሲኖዶስ የጥቅምት ጉባዔ ዛሬ ሳይሰበሰብ የዋለ ሲሆን ምክንያቱ ቅዱስ ፓትርያርኩ ለሥራ ጉዳይ ወደ አኩሱም በማቅናታቸው መሆኑ ታውቋል።"

By this act he has DEFILED the holy synod -with him as a patriarch the synod is no longer holy or synod

He defied, openly refused to obey or conform to the cannon of the church and the authority of the synod

The synod should tell him to stay in Axum and assign ዓቃቤ ፓትርያርክ until The Lord God "call him home"

Anonymous said...

+++

How and why our patriaric give priorty for Axum???????
The Holy Synode gave permission to go Axum?
Abatachin ebaqewoti remember that you are representative of St. Petrose Likehawareyat.
Ze Aberha we atsebiha gedam

Anonymous said...

" 8. መላው የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ብፁ
አን አባቶች ከአባ ጳውሎስ የከፋፍለህ ግዛው ሴራ ተጠብቃችሁ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቅዱስ ደሙ በመሠረታት ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ለተፈጠረውችግር ዘላ
ቂ መፍትሔ ለመስጠት የቀድሞ ብፁአን አ
ባቶችን አሠረ ፍኖት በመከተል በፆም በጸሎ
ት፣ሌት ተቀን ደከመን ሰለቸን ሳትሉ አንድ ሆናችሁ ቤተክርስቲያንን ከችግር በመታደግ አባታዊና ታሪካዊ ግዴታችሁን እንድትወጡ በታላቅ ትሕትና እንጠይቃለን።

9. መላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ካህናትና ምእመናን በተከሰተ
ው ኢ-ክርስቲያናዊና ሕገ ወጥ ነገር ተስፋ ባለመቁረጥ እንደዚሁም ደግሞ የቤተክርስ
ቲያናችንን አንድነትና ሰላም ለማይሹ አጽ
ራረ ሃይማኖት ቦታ ባለመስጠት ከምንም
በላይ ለቅድስት ቤተክርስቲያን አንድነትና ሰላም መጠበቅ፣ ለቅዱስ ሲኖዶስ የበላይነት መረጋገጥ፣ ለሕገ ቤተክርስቲያን መከበር በጥብዓት ከተነሱ ብፁዓን አባቶቻችን ጎን በመቆምና አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ በማድ
ረግ የበኩላችንን አስተዋጽኦ እንድናደርግ ሃይማኖታዊ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

የሰላም አምላክ ሰላማዊ ኢየሱስ ክርስቶስ ለቤተክርስቲያናችን ሰላምን ይስጥልን።

የእምነ ጽዮን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን።
አሜን።

ርእሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን
ቅድስት ማርያም

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ
ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን

ጥቅምት 3 ቀን 2002 ዓ.ም፣
ለንደን፤ ብሪታንያ።"

የሚከተለውን፡መጠቆሚያ፡በመጫን፡
ሙሉውን፡ጽሑፍ፡ማንበብ፡ይቻላል፤

http://www.ethiomedia.com/course/london_debre_tsion.pdf

SAMUEL said...

This is meaningless thought. As I know, Aba Serekebirhan is a man of goal. He is a dedicated person the serve the church. Believe it or not, appointed an archbishop for the Sunday Schools Department is good for Aba Serekebirhan. He gets a supporter for his plan. Because, he has not been fighting for his benefit except for the church’s benefit. I am sure; he is not going to stop fighting for the truth. For Aba, America is nothing. He did not get anything from it except serving the Ethiopian Community. አባ ሰረቀብርሃን ያ ሁሉ ዘመን አሜሪካ ሲኖሩ እንደሌሎች ለራሳቸው ንብረት ያላከማቹ፡ ለራሳችው ቤት ያልሰሩ፡ መኪና ወዘተ. ያለገዙ። ነገር ግን በ—ይን የሚታይና በእጅ የሚዳሰ ለችግረኞች ስራ እየሰሩ የሚገኙ አባት ናቸው። ስለዚህ ሊቀ ጳጳስ ስለተሾመ ወደ አሜሪካ ይመጡ ይሆናል የሚለው አስተሳስብ የማይታሰብ ነው። እንዲያውም በጣም ዕድለኛ ናቸው። ያለውን ችግር የሚጋራቸው አባት በማግኝታቸው። በስልጣን የማይመኩ መሆናቸው ብናውቅም ሊቀ ጳጳስ በመሾሙ የሚቀነስባቸው ነገር እንደሌለ የታወቀ ነው። አትርሱ ውሸትና ስንቅ እያደረ ይጎድላልና ለምንጽፈውና ለምንናገረው ብናስብበት መልካም ነው።

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)