October 27, 2009

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ዓለም አቀፋዊ የምእመናን ማሕበር መግለጫ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ዓለም አቀፋዊ የምእመናን ማሕበር መግለጫ
WORLD ASSOCIATION OF PARISHIONERS OF THE ETHIOPIAN ORTHODOX TEWAHEDO CHURCH
10107 Branwood Circle, Dallas, TX 75243, U.S.A. WWW.eotcipc.org
Tel: (469)855 8488 (214)697 8928; (813)312 1502; e-mailmiimenan@yahoo.com
መስከረም 18 ቀን 2002 ዓ/ም

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ፤ አሐዱ አምላክ፤ አሜን።
ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
ቅዱስ ሲኖዶስ፤
ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ
ለብፁዓን የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት
አዲስ አበባ።

ጉዳዩ፤ በቤተክርስቲያናችን፤ ሰላም፤ አንድነትና ዘላቂ እድገት እንዲገኝ ስለ ማድረግ፤

በመጀመሪያ፤ ለቅዱስ ሲኖዶሱ ያለንን እጅግ ከፍ ያለ አክብሮት እየገለጽን፤ ለብፁዓን የቅዱስ ሲኖዶሱ አባላት
የእግዚአብሔር ሰላምታችንን በትሕትና እናቀርባለን።
እኛ በዓለሙ ሁሉ ተሰራጭተን የምንገኝ ተባባሪዎች የቤተክርስቲያናችን ምእመናን በቅርቡ በቅዱስ ሲኖዶሱ
አባላት መሀል በተከሰተው ውዝግብና ባጋጠሙት ድርጊቶች እጅግ ተሳቅቀናል፤ አዝነናልም። ሆኖም፤ በጥቅምት
ወር 2002 ዓ/ም የቅዱስ ሲኖዶሱ ስብሰባ ስለሚከናወን ጉባኤው ለቤተክርስቲያናችን የተሙዋላ ሰላምና አንድነት
እንዲያስገኝና የዘለቄታ እድገት የሚያመቻች ስልት እንዲተልም የበኩላችንን ግንዛቤና ማሳሰቢያ ከዚህ በታች
በአክብሮት እናቀርባለን። የቅዱስ ሲኖዶሱ ጉባኤም በቤተክርስቲያናችን ላይ ተጋርጠው የሚገኙትን እጅግ ከባድ
ችግሮች ለማስወገድ ተገቢ የሆኑ መፍትሔዎችን እንደሚያስገኝ ያለንን ፅኑ ተስፋ በቅድሚያ እንገልጻለን። ስለዚህ፤
ቅዱስ ሲኖዶሱ፤ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት፤ ከዚህ በታች የምናቀርባቸውን ሀሳቦች በጥሞና ተመልክቶ ቅድስት
ቤተክርስቲያናችንን ለዘለቄታ በሚያጠናክርና በሚያስፋፋ ስልት ተገቢውን ውሳኔ እንዲያደርግ እንማጸናለን።
1. ስለ ቅዱስ ሲኖዶሱ ሥልጣን፤
እንደሚታወቀው፤ በ1991 ዓ/ም በቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ የተደነገገው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
ሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ 5 የቅዱስ ሲኖዶስን ሥልጣን እንደሚከተለው በግልጽ አስቀምጦታል፤
“1. በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው ቅ/ሲኖዶስ የመንበረ ሐዋርያት ወራሽ ስለሆነ በቤተ ክርስቲያኒቱ
የመጨረሻው ከፍተኛው ሥልጣን ባለቤት ነው።
2. ከማንኛውም የቤተ ክርስቲያኒቱ የሥልጣን መዋቅር ሁሉ የበላይ አካል ቅዱስ ሲኖዶስ ስለሆነ
ሕጎችን፤ ልዩ ልዩ ደንቦችንና መመሪያዎችን የማውጣትና የዳኝነት ሥልጣን አለው።”
2
ከላይ በሁለቱ ንኡስ አንቀጾች እንደተገለጸው፤ የቅዱስ ሲኖዶስ ሥልጣን በማያሻማ ሁኔታ በግልጽ የተደነገገ ስለሆነ
በቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ወቅት በወገናዊነትም ሆን በዓለማዊ ጥቅም ፍለጋ ምክንያት በማንም የውጪም ሆነ የውስጥ
አካል ተጽእኖ እንዳይሸረሸርና እንዳይዛባ በእግዚአብሔር ስም ከፍ ባለ ትሕትና እንጠይቃለን።
2. ስለ ሰላምና አንድነት፤
በአባቶቻችን መካከል የተፈጠረው አለመግባባትና መከፋፈል አደባባይ ወጥቶ መዘባበቻ በመሆኑ በአባቶቻችን ላይ
በቀላሉ የማይፋቅ ታሪካዊ ትዝብት ያተረፈላቸው መሆኑ ግልጽ ነው። ይህ ሁኔታ ቤተ ክርስቲያናችንን እጅግ
በሚያሰጋና በሚያሳስብ ሁኔታ አደጋ ላይ ጥልዋታል። ይህ በአባቶች መካከል የተከሰተው መከፋፈል፤ መኖቆርና
አንድነት ማጣት፤ በአመራር ደረጃ የሚታየው ግዴለሽነትና ብቃት ማጣት፤ ምእመናንን ግራ ያጋባው ስደተኛ
ሲኖዶስ በመባል ያስከተለው መወጋገዝና የቤተ ክርስቲያናችን መከፋፈል አዝማሚያ መታየት እነዚህና ሌሎችም
ሁኔታዎች ለቤተ ክርስቲያናችን ጠላቶች መጠናከርና መስፋፋት አመች ሁኔታ ፈጥሮላቸዋል። ስለዚህ የቅዱስ
ሲኖዶስ አባላት እነዚህን ለቤተ ክርስቲያናችን በጣም አደገኛ የሆኑትን ክስተቶች በማጤንና በማሰላሰል፤
በክርስቲያናዊ አስተሳሰብና ይቅር ባይነት በመካከላችሁ የተፈጠረውን አለመግባባትና መከፋፈል አስወግዳችሁ
በፍጹም ፍቅርና ሕብረት በመወያየት ቤተ ክርስቲያናችንን ከተጋረጡባት አደጋዎች እንድታድኑዋት በጌታችን፤
በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስና በእናቱ በቅድስት ድንግል ማርያም ስም ከፍ ባለ ትሕትና እንማጸናችሁዋለን።
3. ስለ አስተዳደር ጉድለት፤
በባለሙያ የተጠና መዋቅር፤ ግልጽና የማያሻማ የአስተዳደር ደንብ፤ ዓላማው ግልጽ የሆነ የአጭር፤ የመካከለኛና
የረዥም ጊዜ እቅድ የሌለው ማንኛውም ተቁዋም፤ ብክነት፤ ሙስና፤ አድልዎ፤ የሥራ ቅልጥፍና ማጣትና
የመሳሰሉት የአስተዳደር ብልሹነት የሚታይበት መሆኑ አያጠራጥርም። ቤተ ክርስቲያናችንንም እዚህ ምስቅልቅልና
አደጋ ላይ ጥሎ ለውድቀት ከዳረጉዋት ምክንያቶች ውስጥ አንዱ ይህ ሁኔታ መሆኑ እውነት ነው። በተለይ እንደ
ቤተ ክርስቲያናችን ያለ ግዙፍ ተቁዋም በየመስኩ በሚገኙ ባለሙያዎች የተጠና መዋቅር፤ በመዋቅሩ ላይ
የተመሠረተ ግልጽና የማያሻማ የአስተዳደር ደንብ፤ በቤተ ክርስቲያኒቱ ዓላማዎች ላይ የተመሠረተ የአጭር፤
የመካከለኛና የረዥም ጊዜ ጥርት ያሉ እቅዶችና በእቅዶቹ ላይ የተመሠረቱ ምእመናንንና ምእመናትን በሰፊው
የሚያሳትፉ የሥራ ፕሮግራሞች በባለሙያዎች ተጠንተው እንዲዘጋጁ ማድረግ ቤተ ክርስቲያናችንን ከውድቀት
ለማዳን አማራጭ የማይገኝለት ጉዳይ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል። ስለዚህ ቤተ ክርስቲያናችን ትክክለኛውን አቅጣጫ
ይዛ በመጉዋዝ እየተስፋፋችና እየተጠናከረች በመሔድ በሕገ ቤተክርስቲያናችን በአጠቃላይ የተደነገጉትን
መንፈሳዊውንና ዓለማዊውን ዓላማዎቹዋን ግብ ለማድረስና ከገጠሙዋት ችግሮች መላቀቅ እንድትችል እላይ
በጠቀስናቸው አማራጭ በማይገኝላቸው ጉዳዮች ላይ የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ሥርነቀል
ውሳኔ እንዲያስተላልፍ
በማክበር እናሳስባለን።
4. ስብከተ ወንጌልን ስለ ማጠናከርና ስለ ማስፋፋት፤
በሕገ ቤተ ክርስቲያናችን እንደሚከተለው ተደንግጉዋል፤
አንቀጽ 7 ቁጥር 7 “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት በአገር ውስጥና በውጭ አገር እንዲስፋፋ
ያደርጋል።”
ነገር ግን፤ ከላይ በተጠቀሰው ሕገ ቤተ ክርስቲያን መመሪያ መሠረት የተወሰደው እርምጃ እጅግ አነስተኛ ነው።
እንደሚታወቀው፤ በአገራችን በኢትዮጵያ የቤተ ክርስቲያናችን ምእመናንና ምእመናት ስለ እምነታቸው በቂ
ትምሕርት ስለማያገኙ በብዛት ወደ ሌሎች እምነቶች እየፈለሱ በመሔዳቸው የቤተ ክርስቲያናችን እምነት
ተከታዮች ቁጥር እየቀነሰ ከመሔዱም በላይ በተለይ በገጠሩ የሚኖሩት ምእመናን ስለ ወንጌልም ሆነ ስለ
እምነታችን ያላቸው ግንዛቤ እጅግ አነስተኛ መሆኑ የታወቀ ነው። በአንጻሩ፤ የሌሎች እምነት ተከታዮች ቁጥር
እየጨመረ መሔዱ ብቻ ሳይሆን እያንዳንዱ የሌላው እምነት ተከታይ እምነቱን እንዲቀበል በስልት ተምሮ
የተቀበለውን እምነት በጣፈጡ ቃላት ለእኛው እምነቱን ያስተማረው ለሌለውና ለማያውቀው ምእመን እየሰበከ
ባል ሚስቱን፤ ሚስት ባልዋን ሲያስኮበልሉ ይታያሉ። ከኢትዮጵያ ውጪ በመላው ዓለም ተሰራጭተው በሚገኙ
ኢትዮጵያውያን ጥረትና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንም ፕሮግራም በውጭ ሐገሮች በብዛት
3
በተቁዋቁዋሙት አብያተ ክርስቲያናት የሚገኙ ካሕናት የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን እምነት በይፋ ለሌሎች ዜጎች
ስለማያስተምሩ ቤተ ክርስቲያናችን ብዙ የሌሎች ዜጎች ምእመናንንና ምእመናትን አባል ማድረግ ስትችል
የሚያስተምራቸው ስለሌለ እምነታችንን የተቀበሉ የውጭ ሐገር ዜጎች በጣም ጥቂት ናቸው። ስለሆነም፤ ከላይ
የተጠቀሰውን ችግር ቀስ በቀስ ማስወገድና ስብከተ ወንጌልን በስፋት እያሰራጩ ኢትዮጵያውያንና የውጭ ዜጎች
ምእመናንና ምእመናትን ቁጥር ማብዛት የሚቻልበት ዘዴዎች በቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ዘንድ የሚታወቁ ቢሆንም
ለመጠቆም ያህል የወንጌል መልእክተኞቻችን በሐገራችን ቁዋንቁዋዎችና በሌሎች ዜጎች ልዩ ልዩ ቁዋንቁዋዎች
በብዛት ማሠልጠንና እንደ ሌሎቹ እምነት አስተማሪዎች በየገጠሩ በቤተ ክርስቲያን ብቻ ሳይሆን በየመንደሩ
እየተዘዋወሩ እንዲያስተምሩ ማድረግ፤ በመጻሕፍት ብቻ ሳይሆን በቀላሉ የሚነበቡ በራሪ ወረቀቶችን በልዩ ልዩ
ቁዋንቁዋዎች በብዛት እያዘጋጁ ማሰራጨት፤ በመገናኛ ብዙኅን ማለት በሬዲዮ፤ በቴሌቪዥን፤ በድረገጽና
በመሳሰሉት ትምሕርተ ወንጌልን፤ እምነታችንና ቀኖናችንን ማሰራጨት ስለሚቻል ቅዱስ ሲኖዶስ በዚህ አስፈላጊና
አሳሳቢ ጉዳይ ላይ ውይይት አድርጎ አመርቂ ውሳኔ እንደሚያስተላልፍ እናምናለን።
5. ደብሮችንና ገዳሞችን ስለ መርዳት፤
ከደርግ ዘመን ጀምሮ፤ ቤተክርስቲያናችን አብዛኛውን ንብረቷን ስለ ተዘረፈች ብዙ ደብሮችና ገዳሞች ችግር ላይ
ይገኛሉ። በብክነት ምክንያት፤ ከምእመናን የሚገኘውም በትክክሉ እንዲደርሳቸው አልተደረገም። በተከሠተው
መናቆር ምክንያትም፤ ውጪ ሐገሮች ያሉት ምእመናንም በሚችሉት መርዳት አልቻሉም። በተጨማሪም፤ እጅግ
አሳሳቢ ሆኖ የቆየው፤ ታሪካዊው የኢየሩሳሌሙ “ዴር ሡልጣን” (1) ገዳማችን የሚያስፈልገው ጥገና
ስላልተከናወነለት የመፍረስ አደጋ ላይ ነው። ስለዚህ፤ ቤተክርሲቲያናችን ካላት ገቢ፤ ደብሮችና ገዳሞች ተገቢውን
ድርሻቸውን እንዲያገኙ፤ ለዘለቄታውም ራሳቸውን እንዲችሉ ተገቢ በሆነ ሥልት እንዲጠቀሙና፤ ከውጪም
የሚገኘው ድጋፍ እንዲዳብር፤ የእሥራኤል መንግሥትም የኢየሩሳሌም ገዳማችን እንዲጠገን ፈቃዱ እንዲሆን፤
ቅዱስ ሲኖዶሱ ተገቢ የሆነ ጠንካራ ሥልት አዘጋጅቶ ሥራ ላይ እንዲያውል በማክበር እናሳስባለን።
6. ስለ ትምህርት ማስፋፋትና ማጠናከር፤
ስለ ቅዱስ ሲኖዶስ የወጣው ሕገ ቤተክርስቲያን፤ አንቀጽ 7 ስለ “የቅዱስ ሲኖዶስ ሥልጣንና ተግባር”½
እንደሚከተለው ደንግጓል፤
ቁጥር 8፤ “የክርስቶስን ወንጌለ መንግሥትና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን ያስተምራል ያስፋፋል።”
ሆኖም፤ ቤተክርስቲያናችንን ካጋጠሟት እጅግ ከባድ ችግሮች አንዱ የአብነት ትምሕርት ቤቶች መዳከም ነው።
ቀድሞም ሆነ በአሁኑ ዘመን፤ የአብያተ ክርስቲያናችን ሕልውና መሠረት የአብነት ትምህርት ቤቶች መሆናቸው
ይታወቃል። ገዳማትንና አድባራትን የሚያገለግሉት ካህናት ምንጭ የአብነት ትምህርት ቤቶች ናቸው። የብፁአን
ወቅዱሳን ፓትሪያርኮች፤ የብፁአን ሊቃነ ጳጳሳትና ኤጲስ ቆጶሳት ምንጭ የአብነት ትምሕርት ቤቶች ናቸው።ስለዚህ
የእነዚህ አብነት ትምህርት ቤቶች መዳከም ማለት የቤተ ክርስቲያን መዳከም ማለት መሆኑ እውነት ነው።
ከአስተዳደር ችግሩ በተጨማሪ የገጠሬው ምእመን በከፋ ድሕነት ስለሚሰቃይ ለቆሎ ተማሪውና ለአስተማሪው
የተለመደ ቸርነቱን ሊያበረክትለት አልቻለም። ለጋሽ የነበረው የኢትዮጵያ ገበሬ ተመጽዋች በመሆኑ የቆሎ
ተማሪዎችና መምህራኖቻቸው የእለት ጉርሳቸውንና የዓመት ልብሳቸውን ከገበሬው በምጽዋት ማግኘት ስላልቻሉ
ወደየከተማው በመሰደድ ላይ ናቸው። በዚህ ምክንያት፤ የቤተክርስቲያናችን ምንጭ የሆኑት የአብነት ትምሕርት
ቤቶች አስጊ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ። ውጪ ሀገሮች ላሉት ምእመናንም ተገቢ የሆኑ የሥልጠና ማእከሎች
(1) ማሕበራችን ስለ ታሪካዊው የኢየሩሳሌም ገዳማችን ለእስራኤል መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትር የሚያቀርበውን
አቤቱታ በዓለምአቀፍ
ደረጃ በማስፈረም ላይ መሆኑን የሚያሳየውንና ያሰራጨውንም መግለጪያ በድረገጹ
በwww.eotcipc.org½ይመልከቱ።
4
ስላልተቋቋሙላቸው በቤተክርስቲያናችን ትምሕርት የጠለቀ እውቀት ሊያገኙ አልቻሉም። ስለዚህ፤ የአብነት
ት/ቤቶች እንዲጠናከሩና ውጪ ሐገሮችም የቤተክርስቲያናችን ት/ቤቶች እንዲቋቋሙ፤ ቅዱስ ሲኖዶሱ ለጉዳዩ ልዩ
ትኩረት በመስጠት በባለሙያዎች ጥናት ላይ የተመሠረት ዘላቂ መፍትሔ እንዲያስገኝለት በትሕትና እናሳስባለን።
7. አክራሪዎች ስላደረሱት ጥቃት፤
ቤተክርስቲያናችንን ካጋጠሟት እጅግ መራርና አስቆጪ ጥቃቶች አንደኛው አክራሪ እስላሞች ካሕናትንና
ምእመናንን አሰቃቂ በሆነ መንገድ መጨፍጨፋቸው፤ ደብሮችንና ገዳሞችን ማቃጠላቸውና ከጠላት ሐገሮች
በሚያገኙት ገንዘብ ቤተክርስቲያናችንን በብዙ መንገድ መፈታተናቸውን መቀጠላቸው ነው። በተለይ በ1997 እና
1998 ዓ/ም ከምሥራቅ ሐረርጌ ክፍለ ሐገር ጋራሙለታ ጀምሮ በምዕራብ እስከ ኢልባቦርና ከፋ ክፍላተ ሐገራት
ባሉት አገሮች በባሌና አርሲ ብዙ አብያተ ክርስቲያናት የፈረሱና የተቃጠሉ፤ ብዙ ካህናት የተሰየፉ፤ እንደ እንስሳ
የተቀሉ፤ ተገድደው የሰለሙ መሆናቸው ያደባባይ ምሥጢር ነው። ስለዚህ ሁሉ ግፍ፤ በቤተክርስቲያናችን አመራር
ምን እንደ ተከናወነና ምን ክትትል በመደረግም ላይ እንዳለ የሚታወቅ ነገር የለም። የተከናወነው አሰቃቂ ግፍ
ተጀመረ እንጂ ያበቃለት አለመሆኑን፤ እንዲያውም የባሰ ጥቃት ሊከሰት እንደሚችል አውቆ፤ ነቅቶ እንዲጠብቅ
ለቤተ ክርስቲያናችን ምእመናን በሰፊው ማስገንዘብ ያስፈልጋል። ስለዚህ፤ ቅዱስ ሲኖዶሱ ይህን ከባድ ጉዳይ
በዝርዝር በማጥናት ተገቢው ሕጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ እንዲሁም ቤተክርስቲያናችን ለራሷ ብቁ፤ ለዘመኑ አመች
የሆነ ሕጋዊ መከላከያ እንዲኖራት ለማድረግ የሚያስችል ሥልት አዘጋጅቶ ሥራ ላይ ማዋል የሚያስፈልግ መሆኑን
በአክብሮት እናሳስባለን።
8. ስለ ድሕነት፤
ከላይ በተጠቀሰው ሕገ ቤተክርስቲያን፤ አንቀጽ 6 ቁጥር 6 አንደኛው የቅዱስ ሲኖዶስ ዓላማ እንደሚከተለው
ተገልጿል፤
“የሰው ዘር ሁሉ ከርሃብ፤ ከእርዛት፤ ከበሽታና ከድንቁርና ተላቆ በሰላምና በአንድነት በመተሳሰብና
በመረዳዳት በመንፈሳዊ ሕይወት እንዲኖር ማስተማርና መጸለይ፤”
የሐገራችን ሕዝብ እጅግ በከፋ የድሕነት አረንቋ ፍዳውን እያየ መሆኑ የታወቀ ነው። ቤተክርስቲያናችንንም
ለእምነቱ መጠጊያ፤ ለረሐቡም ማስታገሺያ እንድትሆንለት ይፈልጋል። በዚህ ረገድ፤ ቤተክርስቲያናችን ለደኸየውና
ለታረዘው ወገናችን በበለጠ ሁኔታ ደራሽ እንድትሆን ተገቢ ሥልት እንዲቀየስና ሥራ ላይ እንዲውል፤ ቅዱስ
ሲኖዶሱ አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስድ በትሕትና እናሳስባለን።
9. መደምደሚያ፤
ከላይ የዘረዘርናቸው ጉዳዮች የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኩዋይ ትኩረት የሚገባቸው መሆኑ ቢታወቅም፤ ምእመናን
መፍትሔ የሚሹባቸው ሌሎች ችግሮችም አሉ። ከነዚህ ውስጥ ጥቂቱን ለመጥቀስ፤ (ሀ)ቃለአዋዲውን
ስለ
ማሻሻል፤ (ለ) መጠናት ስለሚገባቸው ድርሳናት፤ ገድላት፤ ውዳሴያትና ታምራት፤ (ሐ) የምእመናትን ተሳትፎ ስለ
ማጠናከር፤ (መ) ቅዱስ ቁርባኑን ባለመቀበል፤ አብዛኛዎቹ ምእመናንና ምእመናት በቅዳሴያችን በግልጽ እንደ
ተቀመጠው፤ የእግዚአብሔርን ሕግ አፍራሾች ሆነን ስለ መገኘታችን፤ ወዘተ ይገኙበታል።
ቅዱስ ሲኖዶሱ መልካም ፈቃዱ ሆኖ፤ ከላይ የዘረዘርናቸውን ጉዳዮች በጥሞና ተመልክቶ አስፈላጊውን መመሪያ
እንዲሰጥና ቅድስት ቤተክርስቲያናችን ሰላምና አንድነት የሰፈነባት፤ በተሟላ ሥልት፤ አቅድና፤ ፕሮግራም
የምትንቀሳቀስ፤ በቅልጥፍና፤ በግልጽነትና በአስተማማኝ ቁጥጥር የምትሠራ፤ ስብከቷና ትምሕርቷ ለዓለም ሕዝብ
ሁሉ የሚዳረስ፤ የማትደፈር፤ ራሷን የቻለች፤ ምእመኖቿም በእምነታቸው የጸኑ የብዙ ሐገሮች ዜጎች እንዲሆኑ
እንዲያደርግ የሁልጊዜም ጸሎታችን ነው።
ቅዱስ ሲኖዶሱ፤ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት፤ ባሁኑ ጊዜ በቤተክርስቲያናችን ላይ የተጋረጡትን ከባድ ችግሮች
በሚገባ እንዲወጣ ለቸሩ የኢትዮጵያ አምላክ ተንበርክከን እንጸልያለን። አሜን።
እጅግ ከፍ ካለ የአክብሮት ሰላምታ ጋር፤
ኢዮኤል ነጋ
የማሕበሩ ዋና ጸሐፊ።
ጽሑፉን በፒ.ዲ.ኤፍ ለማንበብ ይህንን ይጫኑ።

41 comments:

tad said...

ማሻሻል፤ (ለ) መጠናት ስለሚገባቸው ድርሳናት፤ ገድላት፤ ውዳሴያትና ታምራት፤ (ሐ) የምእመናትን ተሳትፎ ስለ
ማጠናከር፤ (መ) ቅዱስ ቁርባኑን ባለመቀበል፤ አብዛኛዎቹ ምእመናንና ምእመናት በቅዳሴያችን በግልጽ እንደ
ተቀመጠው፤ የእግዚአብሔርን ሕግ አፍራሾች ሆነን ስለ መገኘታችን፤ ወዘተ ይገኙበታል።
Bold and honest.But why address the letter to the dead horse. HolySynod with out HolySprit is dead. The EOC holy Synod is souless.

gorgoreyos said...

weginochaie; ymesima segn aydel!!!

ferecha said...

Please watch this video about decision of Abune Shenouda III about "kidiste kidusan dingle mariam"

http://www.youtube.com/user/medhanialemeotcks#p/u/12/U2fplUxOgXc

Anonymous said...

We belive in the Living God. He has been watching, listening, and speaking.
I am afraid may be it is "The Rise of Samuel and the Fall of Eli and Sons (1 Samuel 3:1--4:22)"

Forgive me for that

tesfa said...

እንንተ መመናን እግዚአብሔር ይባርካችሁ ገና የልቤ ነገር ተጻፈ
ምንም አድልዎ የሌለበት ያልወገነ የማይኮንን የማያጸድቅ መግለጫ እናንተ የተሻለ እውነተኛ ቅዱስ ሐሳብ በማቅረባችሁ ልቤ በደስታ ተሞልቷል
መጠናት ስላለባቸው ድርሳናት ጭምር ማሰባችሁ የቤተ/ክርስቲአን ተስፋዎች ብያችኋለሁ
በርቱ

Anonymous said...

መደምደሚያውን Aንብቡት
ነፍሳቸውን ይማረውና ብፁE ሊቀ ጳጳስ Aቡነ ይስሐቅ Aቋቁመውት የነበረው ማኅበረ ዘተዋሕዶ በቤተ ክርስቲያናችን ደጀ ሰላም ጉባዔ Eንደሚያካሄድ የቦርዱ ሊቀ መንበር ባለፈው ሳምንት በቅዳሴ ሰዓት Aስታውቀው ስለነበር ይህ የተላለፈልኝ መልEክት Eሱን የሚመለከት መስሎኝ ነበር። Eውን ስብሰባውን የጠራው ማኅበረ ዘተዋሕዶ ሳይሆን ራሱን የምEመናን ጉባዔ ብሎ የሠየመው ቡድን ከሆነ በAቡነ ይስሐቅ ስም በመነገድ ብዙ ምEመናንን ለማደናገር ታስቧል ማለት ነው። ከቦርዱ Aካባቢ የውሸት መግለጫ መስጠት የተለመደ ስለሆነ “የቦርዱ ሰብሳቢ ለምን ይዋሻሉ?” ብዬ Aልጠይቅም።
ያም ሆነ ይህ መግለጫውን ሙሉ በሙሉ ለማንበብ ጊዜ ስላልነበረኝ ዓርማውን፣ ርEሱን፣ መግቢያውን፣ ንUሳን ርEሶቹን ቃኝቼ ወደ መደምደሚያው Aመራሁ። መደምደሚያውን Eስከማነብ ድረስ “ተመስገን፣ ለተዋሕዶ Eምነታችን በጎ የሚያስቡ Aሉ” Aልኩኝ። መደምደሚያውን ሳነብ ግን ስብሰባውን የጠሩት ሰዎች በምEመናን ስም ቅዱስ ሲኖዶሱን የሚያሳስቡት ከAቅማቸው በላይ የሆኑትንና ምEመናን ያልተጨነቁባቸውን ጉዳዮች Eንደሆነ ተሰማኝ። ሰዎቹ ከምEመናን ወገን Eንዳልሆኑም ከፍላጎታቸው ተረዳሁ። ከዚህ በፊት የገጠምኩት ስንኝ ትዝ Aለኝ።
“ተኩላ ለምድ ቢለብስ በግን ለመምሰል፣
መታወቁ Aይቀርም ሣር Aልግጥም ሲል።” ያልኩት
ውዳሴያት፣ ድርሳናት፣ ገድላትና ተዓምራት ይሻሻሉ ሲሉ መጀመሪያ Eነዚህን መጻሕፍት Aንብበው ያውቃሉ ወይ? የሚል ጥያቄ በAEምሮዬ መጣብኝ። ሁለተኛም መሻሻል Aለባቸው ሲሉ ከምን ተነስተው ነው? ትክክለኛው ታሪክ ተዛብቶ ለመጻፉ ከራሳቸው ስሜት በስተቀር ሌላ ምን ማስረጃ Aላቸው? ብዬ ጠየቅሁ። Eነዚህ ሰዎች Aላዋቂ ሳይሆኑ መናፍቃን Eንደሆኑ ተገነዘብሁ። በተለይም የፀሐፊውን ስምና ፊርማ ስመለከት Eሳቸውን በመሣርያነት የተጠቀሙባቸው ሰዎች ከበስተጀርባ Eንደተሰለፌ Aየሁ።
ለምን ውዳሴያት፣ ድርሳናት፣ ተዓምራትና ገድላት ላይ Aተኮሩ ቢባል በሌሎች ክርስቲያኖች ነን በሚሉ ዘንድ የማይገኙ በመሆናቸው ሃይማኖታችንን Eርቃኗን ለማስቀረት Eንደሆነ ለብዙዎቻችን የተሰወረ ይሆናል ብዬ Aልገምትም። Eነዚህ መጻሕፍት ያሰፈሯቸው Eውነታዎች በሃይማኖት Eንጂ በምርምር ሊረጋገጡ የማይቻሉ ናቸው። በዘመናዊያን ዘንድ ተቀባይነት ሊኖራቸው Aይችሉም። “የመስቀሉ ነገር ለማያምኑት ሞኝነት ሲሆን ለኛ ለምናምነው ግን የድኅነት ምልክት ነው” ተብሎ Eንደተጻፈ። መጻሕፍቱን ብዙ ሰዎች ስለማያነቧቸው Eነሱን ወደ ጎን ትተን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተጻፉት መካከል በዘመናውያኑ ዘንድ ተቀባይነት የማያገኙ ተዓምራት ብዙ Aሉ። ጥቂቶቹን Eዘረዝራለሁ፦
• ጌታችን መድኃኒታችን Iየሱስ ክርስቶስ ያለ Aባት ከEናት በድንግልና መወለዱ
• በባሕር ላይ በEግሩ መራመዱ
• ሁለት ዓሣና Aምስት Eንጀራ ለAምስት ሺህ ቤተሰቦች ጠግበው Eስከሚተርፋቸው ማብላቱ
• በተዘጋ ቤት መግባቱ
• AልAዛርን በሞተ በAራተኛው ቀን ከመቃብር ማስነሳቱ
• ዓይን ያልነበረውን ሰው Aፈር በምራቁ ለውሶ ግንባሩን Eንደቀባና ዓይን Eንዳበጀለት
• 38 ዓመት በAልጋ ቁራኛ የኖረውን መጻጉ Aልጋውን ተሸክሞ Eንዲሄድ ማዘዙ
• በሞተ በሦስተኛው ቀን ከመቃብር መነሳቱ
• ወደ ሰማይ ማረጉ 1
ሌሎችንም መጥቀስ ይቻላል። Eነዚህ ሁሉ በEምነት Eንጂ በሳይንስ ምርምር የማይቻሉ ናቸው። ከሰው AEምሮ በላይ ናቸው። Aንድ በጣም የቅርብ ወዳጄ ከ40 ዓመታት በፊት የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ Eንደነበረ ከAስተማሪው ጋር Aህያ በባሉን Aድርገው ወደ ሰማይ Eንደላኩ ሲነግረኝ Aህያዋ የት Eንደደረሰች ጠየቅሁት። “Eኛ በባሉን Aድርገን Aህያ መላካችንን Eንጂ Aህያዋ የት Eንደደረሰች የምናቀው ነገር የለም። የሷ ነገር Aላስጨነቀንም። የሆኖ ሆኖ ወደ ላይ የወጣ መመለሱ Aይቀርም” Aለኝ። Eኔም የAምላክን Eርገት Eያሰብኩ “ወደ ሰማይ ያረገው ከሰማይ ስለመጣ ነው። ከሰማይ ከወረደው በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም። ያም ሆኖ ‘በመጨረሻው ዘመን ለፍርድ Eመለሳለሁ’ ብሏል” Aልኩ በሆዴ። ወዳጄ “ከምድር የተነሳ ሁሉ ተመልሶ ወደ ምድር ይወድቃል” Eንዳለው ሁሉ “ከሰማይ የወረደ ተመልሶ ወደ ሰማይ ይወጣል” ብዬ ብነግረው ይገባው ይሆን? ብዬ Eራሴን ጠየቅሁ። ለነገሩ የወዳጄ Aባባል ጊዜው ያለፈበት ነው። የስበትን ኃይል Eያሸነፉ ከምድር ተነስተው ወደ ምድር ሳይመለሱ ለረጂም ጊዜ የሚቆዩ Aሉ።
በመግለጫው ላይ Eንደሚነበበው “ምEመናን መፍትሔ የሚሹባቸው ሌሎች ችግሮችም Aሉ” ብለው ከብዙ በጥቂቱ Aራቱን ብቻ ጠቅሰዋል። ሲኖዶሱ “Eህ” ካላቸው (ካዳመጣቸው) ሌሎችንም ይጨምራሉ። ስለ ቅዳሴና ታቦት Aላስፈላጊነት ማንሳታቸው የማይቀር ነው። በEነዚህ ነገሮች ምEመናኑ Eንደምን Eንደተቸገሩ Aላስረዱም። Eንዴትስ የምEመናኑን ስሜት ማወቅ Eንደቻሉ Aልገለጹም። የEነሱን ችግሮች የምEመናንም Eንደሆኑ ቆጥረዋቸዋል። ምናልባት Eነሱ ያልተስማሟቸውን ምEመናንም የማይስማሟቸው Aድርገው ገምተዋል።
ሀ) ቃለ Aዋዲው ይሻሻል ሲሉ ምኑ Eንደሚሻሻል Aላብራሩም። ምናልባት Eራሳቸውን የቤተ ክርስቲያን የበላይ ጠባቂዎች Aድርገው ስለቆጠሩ በሲኖዶሱ ምትክ ስማቸው Eንዲተካ Aስበው ይሆናል። ቃለ Aዋዲው ቅዱስ ሲኖዶስ ያወጣው የመተዳደርያ ደንብ ስለሆነ የተሻለ የAሠራር ዘዴ Eስከተገኘ ድረስ ሊሻሻል የሚችል ነገር ነው። ሆኖም ግን በየትም ይሁን የት የሲኖዶሱ የበላይነት የማያጠያይቅ ነው።
ለ) ድርሳናት፣ ውዳሴያት፣ ገድላትና ተዓምራት ለምን መጠናት ይገባቸዋል Eንደሚሉ መልሱን የሚያውቁት Eነሱ ናቸው። ጥርጣሬ Eንዳለባቸው፣ Eምነታቸው ያልተሟላ Eንደሆነ ግን ግልጽ ነው። ለምሳሌ ስለ Eመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በተጻፈው ውዳሴ በዋናነት የሚተላለፈው መልEክት የዓለምን ቤዛ ወይም መድኃኒታችንን Eንደወለደችልን ነው። ቅድመ ወሊድ ድንግል፣ ጊዜ ወሊድ ድንግል፣ ድኅረ ወሊድ ድንግል መሆኗን በመግለጽ Aምላክን ለመውለድ የተገባች፣ ከሴቶች ሁሉ የተመረጠች ቅድስት፣ ንጽሒት Eንደሆነች የሚያስረዳ ነው። በድንግልና ያለ ወንድ ዘር Aምላክን የመውለዷ ምስጢር በተጠራጣሪዎች ዘንድ ተቀባይነት የለውም። ክርስቲያን ነን ብለው ይህንን Eምነት የማይቀበሉ መናፍቃን ነበሩ፤ Aሁንም Eርዝራዦቻቸው Aሉ። የOርቶዶክስ ተዋሕዶ Eምነት ተከታዮች የሆን ከነሱ የምንለየው የAምላክንና የሰውን ውሕደት ስለምናምን ነው። ቃል ሥጋ ሆነ። Aምላክ ሰው ሆነ። ጌታችን Aምላካችን መድኃኒታችን Iየሱስ ክርስቶስ Eኛን ለማዳን ሲል የEመቤታችንን የቅድስት ድንግል ማርያምን ሥጋ ነስቶ ሰው ሆነ። ሰው በመሆኑ Aምላክነቱ Aልተጓደለበትም። Aምላክ ሰው በመሆኑ በተዘዋዋሪ ሰው Aምላክ ሆነ። ይህ የEምነታችን መሠረት ነው። ተዋሕዶ ያሰኘን ይህ ነው። ሶርያዊው ቅዱስ ኤፍሬም የEመቤታችንን ውዳሴ የጻፈው ይህን ሐቅ ተመርኩዞ ነው። Iትዮጵያዊውም ቅዱስ ያሬድ Aንቀጸ ብርሃንን የደረሰው ቃል ሥጋ ስለመሆኑ ምስጢር ነው። ይህ ቃል ሥጋ የመሆኑ ነገር ብዙ ሰዎች የተሰናከሉበት ነው። በEምነት ሳይሆን በምርምር መንገድ ስለነጎዱ Eውነቱን ስተዋል። ውዳሴ ማርያም ሆነ ውዳሴ Aምላክ ምኑ ነው የሚሻሻለው? “ሥራ ያጣ መነኩሴ ቆብ ቀዶ ይሰፋል” Aሉ። መነኩሴው Eውነት ሥራ ስለሌለው ነው Eንጂ ሥራማ ቢኖረው ኖሮ ደህናውን ስፌት Aጨማዶ መልሶ ሊሰፋው ቀድሞውኑ ለምን ይተረትረዋል?
...... continue

Anonymous said...

continued....
ሐ) በቤተ ክርስቲያናችን የሴቶችን ተሳትፎ ስለማጠናከር የጠቀሱት የሚያስቅ ነው። “ያለ ሴቶች ተሳትፎ Aብዮቱ ግቡን Aይመታም” ይሉ የነበረው Aባባል ባርቆባቸው መሰለኝ። በኛ ቤተ 2
ክርስቲያን ሴቶች የተከበሩ ናቸው። ብዙዎቹም ከወንዱ የበለጠ ሃይማኖተኞች ናቸው። “ተሳትፏቸው ይጠናከር ስትሉ ምን ተጓድሎባቸው Aይታችኋል?” ተብለው ቢጠየቁ ምናልባት “Aይቀድሱም፣ Aይሰብኩም፣ በጵጵስናም ደረጃ የበቁ የሉም” ይሉ ይሆናል። ጌታችን መድኃኒታችን Iየሱስ ክርስቶስ Aስራ ሁለቱን ሐዋርያት ሲመርጥ Aንዲትም Eንኳ ሴት ለምን Eንዳልቀላቀለ መልስ ሊሰጡን ከቻሉ ስለ ሴቶች ተሳትፎ መጠናከር ሊከራከሩ ይችላሉ።
መ) ቅዱስ ቁርባንን ስለመቀበል ጉዳይ ንስሐ የገባ፣ ሕግጋትን ያከበረ፣ ራሱን በክርስትናው መንገድ ያስገዛ፣ ቅዱስ ቁርባን Eውነተኛ የክርስቶስ ሥጋና ደም ነው Eሱን ብቀበል የዘላለም ሕይወትን Aገኛለሁ ብሎ የሚያምን ሰው መቁረብ ይችላል። ሌላ ቦታ Eንደሚደረገው Eንደቡና ቁርስ ይታደለን ከሆነ ነገሩ ያለ Eምነት በድፍረት መውሰዱ ፈጽሞ ካለመውሰዱ የሚሻልበት መንገድ ለኔ Aይታየኝም። ክቡር የሆነውን ለማቃለል ከመሞከር Aቅማችንን Aውቀን Aርፈን ብንቀመጥ ይሻላል። ሥጋና ደሙ Eንደሚያድን የማያምን ሰው ወሰደ Aልወሰደ ምን ያስጨንቀዋል? “ይዞ ሟች” ይሉ ነበር Aንድ Aባት Eየተሳደበ Eጃቸውን ለማሳት ሰበብ የሚሆንባቸውን ሰው። ውሎAቸው ከዘመናዊያን ጋር በመሆኑ የቀበጡት Aንድ ካህን በስተርጅና Eድሜያቸው የሥጋ ወደሙን ክብር በመዳፈር “ይኸ ተሸፋፍኖ የሚያስፈራራችሁን Aንድ ቀን ገላልጠን Eናሳያችኋለን። Eየፈራችሁ ከሱ ልትሸሹ Aይገባም” Aሉ። ከሳቸው የምጠብቀው ስላይደለ ማመን Aልቻልኩም። ይህን የሚናገሩት ሥጋ ወደሙን ለምEመናን ለማቀበል ከሌሎች ካህናት ጋር ሆነው ከመቅደስ Eየወጡ የተለመደውን ፀሎት Aቋርጠው ነው። ስለ ሥጋ ወደሙ ለመነጋገር ወይም ለመከራከር የEንግሊዝኛ ቃል ተጠቅመው “ዲቤት” ለማድረግ ለሳምንት ቀጠሮ ሰጡ። ከማን ጋር ሊከራከሩ ፈልገው Eንደነበረ ግን ግልጽ Aልነበረም። በቀጠሮAቸው ቀን ግን መልስ Aገኙ። ከምድር ሳይሆን ከሰማይ። Aንደበታቸው ተሳስሮ በAምቡላንስ ሄዱ። ከዚያች Eለት በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ Aልተመለሱም። “ምን ሆነው ነው?” ሲባል “ስትሮክ መትቷቸው ነው” ተባለ Eንጂ “መቅሰፍት Aግኘቷቸው ነው” የሚል Aልተሰማም። “በየከተማው Aልፎ Aልፎ Eንደዚህ ዓይነት ምልክት ቢታይ ኖሮ ቤተ ክርስቲያናችንን Aጉል የሚዳፈሩ ሰዎች Aርፈው ይቀመጡ ነበር” ብዬ Aሰብኩ፤ በEግዚAብሔር ሥራ ገብቼ።
ወደ መግለጫው ልመልሳችሁና መግለጫውን የፈረሙት የኛው የቦርድ ሰብሳቢ መሆናቸው ቤተክርስቲያናችን ለምን Eንደምትታወክ ትልቅ ፍንጭ ይሰጠናል። በጎ Aድራጎትን ሲዘጉ፣ የAባላትን ቁጥር ለመቀነስ ክርስትናውን ለማዳከም ሕግ ሲለውጡ የቆዩት ያለ ምክንያት Eንዳልሆነ ግልጽ Eየሆነ ነው። ተደብቆ ሳይከሰት፣ ተሸፋፍኖ ሳይገለጥ የሚቀር የለም። ቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ሰርገው የገቡ ፕሮቴስታንቶች Aሉ Eየተባለ የሚናፈሰው ወሬ ሀሰት Aይደለም።
በAንድ ወቅት ሰዎቹ በስማቸው የሚነግዱባቸው Aቡነ ይስሐቅ ሲናገሩ Eንደሰማኋቸው “በዚህ በሰለጠነው ዓለም ረጂም ዘመን በመቆየት የሚስተካከለኝ የለም። (በዚህ ሀገር በስደት ላይ ከሚገኙት ካህናት መካከል ማለታቸው ነው።) በዘመናዊው ትምህርትም የተሻልኩ Eንጂ ያነስኩ Aይደለሁም። Eስካሁን የኛን የተዋሕዶ Eምነት የሚያስንቅ Aላገኘሁም። ከEኛ Eምነት የተሻለ ቢኖር ኖሮ Eኔን ማን ይቀድመኝ ነበር? ሃይማኖታችን ወርቅ ናት። በፍልስፍናውም ሆነ በማናቸውም ረገድ የኛን ሃይማኖት የሚስተካከል Aላጋጠመኝም።” ብለው ነበር። ይኸ የምEመናን ማኅበር የተባለው ጥርቃሞ የAቡነ ይስሐቅ ተከታይ ነኝ የሚል ከሆነ Aጥንታቸው ይፋረዳል። Aቡነ ይስሐቅን የምናውቅ ሰዎችም ይህን ነገር ዝም ብለን በቸልተኝነት ልናልፈው Aይገባም። Eኔም ይህን ጽሑፍ ለመጫጫር የተነሳሳሁት ውሸትንና ምንፍቅናን ስለምቃወም ነው።
በየዘመኑ የተፈጸሙት ገድላት፣ ድርሳናትና ተዓምራት ተጽፈው ከትውልድ ወደ ትውልድ ተላልፈዋል። Eንኳን በዚህ ዘመን ያለነው ትውልድ ይቅርና ክስተቶቹ በተፈጸሙ ጊዜ ከነበሩትም መካከል ያላመኑ ነበሩ። ያላመኑ ስላልነበሩ ድርጊቶቹ Aልተፈጸሙም ነበር ለማለት Aይቻልም። Eምነት የሌለው ሰው ተAምራትን ለመቀበል Eንዴት ይቻለዋል? የጥንቱን ትተነው በዘመናችን ብዙ ተዓምራት ሲፈጸሙ Eንሰማለን፤ ስንቶቻችን Eንቀበል ይሆን? ሩቅ ሳንሄድ፣ በIትዮጵያ Eንኳ የሚደረገውን ትተን፣ Eዚሁ Eኛ ጋር ስንት የሚያስደንቅ ነገር Aይተናል፣ ሰምተናል። ምናልባት 3
Aንዳንዶቻችን Eንደ ቀላል ነገር ቆጥረናቸው Eንዲሁ Aልፈናቸው ይሆናል። Eኔ Eንኳ Aንድ ኃጢAተኛ ፍጡር በራሴና በቤተሰቤም ስንት ድንቅ ነገርን Aይቻለሁ። የኃጢAቴን ብዛት ተመልክቶ ላልናቀኝ Aምላክ ክብር ምስጋና ይሁን።
በቤተ ክርስቲያናችን ያደገች Aንዲት ወጣት ለከፍተኛ ትምህርት ወደ ኒወርክ Aካባቢ ሄዳ የኛን የሚመስል ቤተ ክርስቲያን ስታፈላልግ የሩሲያኖችንና የግሪኮችን ታገኛለች። በEምነት የሚመሳሰሉንን በማግኘቷ ደስ ብሏት በሰንበት Eለት ልታስቀድስ ስትሄድ ጫማ ሳያወልቁ ወንዶችና ሴቶች ተቀላቅለው ሲቀመጡ ታያለች። ይኸ ብቻ ሳይሆን ሁሉም መደዳውን ሲቆርቡ ታያለች። “Aጥብቆ ጠያቂ የናቱን ሞት ይረዳል” Eንዲሉ በጥያቄ ብዛት ታቦትም Eንደሌላቸው ትሰማለች። በዚህን ጊዜ Eዚያው Eመኖርያ ክፍሏ Aርፋ ተቀምጣ የኛኑ ቅዳሴ በቪዲዮ ማዳመጥ መረጠች። ወላጆቿ ይህንን ሲነግሩኝ “ ልጃችሁ Eኛ EግዚAብሔር የሚወደውን ትክክለኛውን Eምነት Eንደያዝን በመረዳቷ ልትደነቅ ይገባል። ሌላው ቢሆን ኖሮ የEነሱ ትክክል የኛ ስህተት Eንደሆነ በመቁጠር ይሰናከል ነበር። ትክክለኛውን ላመላከታትና ከስህተት ለጠበቃት Aምላክ ምስጋና Aቅርቡ” Aልኳቸው።
Eንግዲህ በዚህ Eኛ ባለንበት የፍጻሜ ዘመን ብዙ የሚያስቱ Eንደሚመጡ Aስቀድሞ ተነግሮናል። የያዝነውን Eውነት ሳንለቅ ከቆምንበት ሳንናወጥ የመንግሥቱ ወራሾች Eንድንሆን EግዚAብሔር ይርዳን። Aሜን። 4

Anonymous said...

ለእርስዎ ቃለ ህይዎት ያሰማልን ለመናፍቃኑም ልቦና ይስጥልን

Anonymous said...

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሚን

መደምደሚያውን Aንብቡት ላሉት አስተያየት ሰጪ

በሙሉ የእርሶን ሀሳብ በሙሉ ደግፋለሁ
የሚገርመው ከዲሲም የመጡትም የቦርድ ሊቀመበር
በሆኑበት ዘመን እኒሁ ባለሁበት ሲሉ የሰማሁት
ተነስዉ ለጠሎት የሚለው በዝጠቶዋል ለምን አይቀነስም?
ሲሉ ሰምቺ ፣ወይጉድ እንኲዋን በዚህ ዘመን ድርሳናቱን፤ቅዳሴውን፣
መልክታቱን፣ ታምሩን፣ወንጌሉን፣ዸፉልን አልተባሉ ጉዳአዘችን ፈጦ ይወጣ
ነበረ ፣እባብ የልቡን አይከቶ …….. ፣አረ ለመሆኑ እፍርት የማይሰማአቸው
ደረጃቸው የትእነደሆነ አለማወቃቸው፣ሊቀሊቃውንት አያሊው ፣ሊቀሊቃውንት
አባ ጉዪ አበራ….በቅርብ ያረፉት ፣በዚህ ባለቀበት ዘመን አረፉ ጂ፣ምንያህል
ባዝኑባችሁ፣ያሁሉ ድአካም፣ ለኛ ለሲቶች ማሰባችሁን ተዉለን
እንደወንጌሉ እንኑርበት ፣እንኵን ዘንቦብሽ…..American women
ከሁሉ በላይ የሆነችዉን እምባታችንን እያሰብን ፣ቅዱሳን አንእስታትን
እየዘከርን እንኖራለን፣አማላጅነታቸው ይርጋን
DS thank you so much you are doing
A great Job please continue
Let as know how is how.
It is such a nice job.
God bless you

Anonymous said...

Anonymous

Egziabher yistilin. Ene hule yettsfewn manbeb bich new srye, andken amlak sifekid etsfalew.

Egziabher betsebhi yibark

Anonymous said...

Thank you Deje Selam. The news you are publishing on your blog is so educative and informative. i am so much impressed. wwe are being updated on each event of our church . thank you

Anonymous said...

Damay said

እግዚአብሄር ይባርክልን ረጅም እድሜ ይስጥልን
እውነት በእውነት ሲመሰከር እንዲህ ነው

Anonymous said...

Damay said

እግዚአብሄር ይባርክልን ረጅም እድሜ ይስጥልን
እውነት በእውነት ሲመሰከር እንዲህ ነው

feqer said...

"እናንተን የተቀበለ እኔን ተቀበለ..."ማቴ10፣40 ተስፋ ይህ በፍጹም የማይገባህ ለምንድን ነው?ለምን አጣመህ ትተረጉመዋለህ?ፈጽሞ ሊገባህ አልቻለም፣አቡነ ተክለ ሃይማኖትን፣ቅዱስ መርቆርዮስን፣ቅዱሳንን ሁሉ የምንሰብከው በዚህ ቃል መሰረት ነው.በጻድቅ፣በነብይ፣በደቀ መዛሙርቱ ስም እንድናጠጣና ዋጋ እንደሚሰጠን የጋባለንን ቃል ኪዳን ለምን ታፈርሳለህ?ማቴ10፣42 አየህ ክርስቶስ ቅዱሳንን እንዴት እንደሚወዳቸው፣በኔ ስም ሳይል በደቀ መዝሙር ስም ለድሃ እንድናጠጣ መከረን፣አየህ ከራሱ ሲስቀድማቸው?ምን ዋጋ አለው ለአንተ እና ለመሰሎችህ አይገባችሁ፥በአንተ አባባል እስላምን ማጥመቅ እንደ ጨዋታ ቀላል ነው ያደረከው፣እንደ ድስኩርህ አይቀልም፥እናንተ እንደ ንስጥሮስ፣እንደ ጆቫ፣እንደ አሪኦስ፣ማይኖሪቲ(minority) ሆነህ ቀጥላለህ እንጂ ተዋህዶን ተሀድሶ ማድረግ አትችልም፥ሲኖዶስ ብቻ ሳይሆን ምእመናኑ አንዲት ነጥብ ከበተ ክርስቲያን ስርዓት አንዲት ነጥብ ብትቀየር ህዝቡ ርምጃ ይወስዳል፣በብዙዎች እምነት እናንተን ከቤተ ክርስቲያን ያባረራችሁ፣ሲኖዶስ፣ማኅበረ ቅዱሳን አይደለም፥ምእመናን ናቸው፣አሁንም፣ተዋህዶን የሚጠብቃት በፈጣሪ ርዳታ፣ምእመናን እንጂ ሲኖዶስ፣ማኅበርም አይደለም፣

solomon said...

እኔ የምለው እውነት ተንስኡ ለጸሎት የሚለው በዛ የሚባለው ከነርሱ ሀገር ቅዳሴ ስንት ቀን ሁኖ ቢያሳስባቸው ነው?ላንድ ቀን ቅዳሴ ነው ይሄ ሁሉ ግርግር?እኔ እስከማውቀው ተነሱ ሲበል ባይነሱም ማንም በጅራፍ እየገረፈ አላስወጣቸውም፤ ቁጭ ብለው ማስቀደስ ይችላሉ።

ተአምር ማለት ከሰው ህሊና በላይ የሆኑና ከተለመደው ነገር የተለየ ነው።እስከማውቀው ቤተ ክርስቲያን ሁለት የተአምር መጻሕፍት አሏት፤ተአምረ ኢየሱስና ተአምረ ማርያም ።መጀመርያው መጽሐፍ መድሀኒአለም ከርስቶስ በዚህ ምድር በስጋ ማርያም ተገልጦ ያደረገው ታምር ነው ይሄም መጽሐፍ የያዘው በመጽሐፍ ቅዱስ የተገለጡትን እና እኛ ያልሰማናቸውን ሌሎች የክርስቶስ ድንቅ ስራዎች ነው፡፡ምኑ ይቀነስ እንደሚሉ አይገባኝም? እግዚአበሔር ወደ ምድር ወርዶ የሰው ስጋ ከመዋሀድ የበለጠ ምን አይነት ታምር ተጽፎ ቢሆን ነው መናፍቃኑ ግራ የገባቸውና ለማመን የከበዳቸው? እነርሱስ በየአዳራሻቸው በየመጽሔቶችና ጋዜጦች እየሱስ እንዲህ አደረገ እያሉ ያወሩ የል?(ይሄን እነርሱ ታምር የሚሉትን እንደ መጽሀፍ ቢጽፉትና ቢያሳትሙት ኖሮ ሌላ ታምረ እየሱስ መጽሀፍ ሆነ ማለት ነው)በእኛ ቤተክርስቲያን ሲሆን ምኑ ይደንቃል?ጽፈን አስቀምጠን እግዚአብሔር እንዲህ ያደርጋል’ ተጽናኑ’ ብላ ለምእመናኖቿ ማንበቡ ጉዳቱ የት ላይ ነው?ክርስቶስ አይን ያልነበረውን ሰው ግንበሩ ላይ አይን ፈጠረበት የሚለውን የመጽሀፍ ቅዱስ ታምር ማመን የሚፈልግ ማመን ይችላል ፤”እንዴት?አድርጎ ፈጠረ” በሎ ለመመራመር መሄድ ወደ አለማመን ይወስዳል። አለማመን ስለሚቻል ታምራትን ስታነቡ ይህ በእግዚአብሔር ዘንድ ይቻላል ካላላችሁ በመጽሀፍ ቅዱስ ላይ ያሉትን ከ30 በላይ የክርስቶስ ታምራቶችም ቢሆን ማመን ላልፈለገ ምንም የሚያመጡት ነገር የለም። ታምራትን አንቀበልም የምትሉ ሰዎች መጽሀፍ ቅዱሱንም ትጠራጠሩታላችሁና እየተስለዋለ።በ2000 አመት ጊዜ ውስጥ ያደረገው ታምር አንድ ወይንም ሁለት መጽሀፍ ብቻ ነውን?

ሁለተኛው መጽሀፍ ታምረ ማርያም ነው ።እግዚአብሔር ለቃልኪዳኑ ታማኝ ነው፤በእኔ የሚያምን ከእኔ በለጠ ታምር ሊያደርግ ይችላል ባለው መሰረት የአምላክ እናት በልጇ ስላመነች ድንቅ ድንቅ ታምራትን አድርጋለች አሁንም ታደርጋለች።ለሚያምን ሁሉም ይቻላል።የቅዱስ ጴጥሮስ ጥላ በሸተኛ ፈወሰ የሚለው በአዋልድ መጻሐፍት (ታምረ ጴጥሮስ ብለን ለብቻው ጽፈን ብናሳትመው ኖሮ ትቀበሉት ነበርን?)ነገር ግን በመጽሐፍ ቅዱስ ብታምኑም ባታምኑም ተጽፏል።ታምራት ለማመን የሚያስቸግሩ ነገር ግን እውነት ናቸው።ማርያም አደረገችው ሲባል ለምን ኑፋቄ ይሆናል?መለኮትን የተሸከመችው ድንግል ማርያም ከጴጥሮስ ጥላ አንሳ ነውን? ባለቤቱን ካልናቁ አጥሩን አይነቀንቁ ይመስላል ።እግዚአብሔር በወዳጆቹ አድሮ ገና ብዙ ነገር ያደርጋል።ምን ይሳነዋል?

Anonymous said...

selam selomon

egziabherer abizito tsegawn yistih. some pepole need just excusses to practice what they want to do not what the holy book says.

feqer said...

አቤት፣አቤት ይህ መግለጫ ተስፋን እኮ አስፈነደቀው፣ለካ ከዘመዶቹ ከተሀድሶዎች የወጣ መግለጫ ስለሆነ ነው የፈነደቀው፥እነ ተስፋ ብለው ብለው በቤተ ክርስቲያናችን ስም መግለጫ ማውጣት ጀመሩ እንዴ?ተስፋ እባካችሁ መጀመሪያ ራሳችሁን በንስሃ አድሱ፣መጀመርያ ራስህን መርምር፣ምን እየሰራሁ ነው?በዉኑ ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ እንዳለው ጌታችን ትእዛዙን ጠብቂያለሁ?ቤተ ክርስቲያንን ላድስ ከማለቴ በፊት፣ሌላውን ከማስተማሬ በፊት፣ሌላውን ከመከሬ በፊት እኔ ታድሻለሁ?ራሴን ጠብቂያለህ?ራሴን አስተምሬያለሁ?ወዘተ... ብለህ ራስህን ጠይቅ፣በ አሁኑ ምግባርህ እንኳን ሌላውን ልታስተምር ይቅርና ራስህም በስድብ እና በጥላቻ ተሞልተህ ጨለማ ውስጥ ነው ያለህ፥ከቤተክርስቲያን መጽሃፍት እስቲ ማን ወንድ ነው ማሸሻል የሚችል?ከዚህ በፊት የነብያት ጾም በህዳር 16 መጀመሩ ወርቶ ሁልጊዜ በህዳር 15 ይጀመር ብሎ ሲኖዶስ ቢወስንም፣እስካሁን ይህንን ውሳኔ ያልተቀበሉ ከሊቃውንቱም ከምእመማኑም አውቃለሁ፥ምክንያቱም ከአሁኑ ውሳኔ የበፊቱን የቤተ ክርስቲያን አባቶች የሥርዓት ውሳኔዎች ነው ምእመናኑ የሚከበር የሚጠብቅ፥ የአሁኑን እማ እኮ እያየናቸው ነው፥ ስለዚህ ተስፋ እና መሰሎችህ ከቤተ ክርስቲያን መጽሃፍትም ሆነ ሥርዓት ይቀነሳል ይሻሻላል ብላችሁ የምትጠብቁ ከሆናችሁ ተስፋችሁን ቁረጡ፥እኛ ም እመናን የነበረው ያለው ይቻለናል፣እንዲቻቻል፣እንዲቀየር የምንፈልገው የለም፥ ይህንን ተላልፎ እቀይራለሁ የሚል የሲኖዶስ አባልም ይሁን፣የማኅበር፣ተሀድሶም ይሁን ተዋህዶ እኛ ምእመናን በፍጹም አንቀበለውም፥"ሃይማኖት እንደቀደሙት አባቶችችን "ነው የምንል፥ያለውን ለማሻሻል ማንኛውም አካል ብቃቱም፣ችሎታውም፣ሞራሉም የለውም፥የነበረውን የኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያንን ሥር ዓት የሚለውጥ ቢመጣ እንኳን ሰው የሰማይ መልአክም ቢሆን አንቀበለውም፣አንቀበለውም፣አንቀበለውም

feqer said...

(corrected)
አቤት፣አቤት ይህ መግለጫ ተስፋን እኮ አስፈነደቀው፣ለካ ከዘመዶቹ ከተሀድሶዎች የወጣ መግለጫ ስለሆነ ነው የፈነደቀው፥እነ ተስፋ ብለው ብለው በቤተ ክርስቲያናችን ስም መግለጫ ማውጣት ጀመሩ እንዴ?ተስፋ እባካችሁ መጀመሪያ ራሳችሁን በንስሃ አድሱ፣መጀመርያ ራስህን መርምር፣ምን እየሰራሁ ነው?በዉኑ ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ እንዳለው ጌታችን ትእዛዙን ጠብቂያለሁ?ቤተ ክርስቲያንን ላድስ ከማለቴ በፊት፣ሌላውን ከማስተማሬ በፊት፣ሌላውን ከመምከሬ በፊት እኔ ታድሻለሁ?ራሴን ጠብቂያለህ?ራሴን አስተምሬያለሁ?ወዘተ... ብለህ ራስህን ጠይቅ፣በአሁኑ ምግባርህ እንኳን ሌላውን ልታስተምር ይቅርና ራስህም በስድብ እና በጥላቻ ተሞልተህ ጨለማ ውስጥ ነው ያለህ፥ከቤተክርስቲያን መጽሃፍት እስቲ ማን ወንድ ነው ማሸሻል የሚችል?ከዚህ በፊት የነብያት ጾም በህዳር 16 መጀመሩ ቀርቶ ሁልጊዜ በህዳር 15 ይጀመር ብሎ ሲኖዶስ ቢወስንም፣እስካሁን ይህንን ውሳኔ ያልተቀበሉ ከሊቃውንቱም ከምእመናኑም አውቃለሁ፥ምክንያቱም ከአሁኑ ውሳኔ የበፊቱን የቤተ ክርስቲያን አባቶች የሥርዓት ውሳኔዎች ነው ምእመናኑ የሚያከበር የሚጠብቅ፥ የአሁኑን እማ እኮ እያየናቸው ነው፥ ስለዚህ ተስፋ እና መሰሎችህ ከቤተ ክርስቲያን መጽሃፍትም ሆነ ሥርዓት ይቀነሳል ይሻሻላል ብላችሁ የምትጠብቁ ከሆናችሁ ተስፋችሁን ቁረጡ፥እኛ ምእመናን የነበረው ያለው ይሻለናል፣እንዲሻሻል፣እንዲቀየር የምንፈልገው የለም፥ ይህንን ተላልፎ እቀይራለሁ የሚል የሲኖዶስ አባልም ይሁን፣የማኅበር፣ተሀድሶም ይሁን ተዋህዶ እኛ ምእመናን በፍጹም አንቀበለውም፥"ሃይማኖት እንደቀደሙት አባቶችችን "ነው የምንል፥ያለውን ለማሻሻል ማንኛውም አካል ብቃቱም፣ችሎታውም፣ሞራሉም የለውም፥የነበረውን የኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያንን ሥርዓት የሚለውጥ ቢመጣ እንኳን ሰው የሰማይ መልአክም ቢሆን አንቀበለውም፣አንቀበለውም፣አንቀበለውም

John Ze Baptist said...

I agree in most of the points but what does it mean
ቅዱስ ቁርባኑን ባለመቀበል፤ አብዛኛዎቹ ምእመናንና ምእመናት በቅዳሴያችን በግልጽ እንደ
ተቀመጠው፤ የእግዚአብሔርን ሕግ አፍራሾች ሆነን ስለ መገኘታችን፤ ወዘተ ይገኙበታል።

Does it mean to change some part of Kidasie or what?
Taking Kurban is our responsibility. It is not holy synod who is responsible for this.

Moona said...

በጣም የሚያሳፍር ጊዜ ነው::

John Ze Baptist said...

I agree in some and disagree in some of the points but what does it mean
ቅዱስ ቁርባኑን ባለመቀበል፤ አብዛኛዎቹ ምእመናንና ምእመናት በቅዳሴያችን በግልጽ እንደ
ተቀመጠው፤ የእግዚአብሔርን ሕግ አፍራሾች ሆነን ስለ መገኘታችን፤ ወዘተ ይገኙበታል።

Does it mean to change some part of Kidasie or what?
Taking Kurban is our responsibility. It is not holy synod who is responsible for this.

Anonymous said...

Solomon:
Do you think listening to Teamire mariam is going to replace holycommunion? Do you really believe that Mohammod married to a camel? Do you really belive devil became monk in Debrelibanos? Do you really belive Belaeseb after killing and eating 78 people went to heaven because he gave that little water? Does it make sense to you really? Do you really belive somebody goes to heaven just because he is buried in monastry?.....

Anonymous said...

www.eotcipc.org

ከላይ፡የተመለከተው፡አድራሻ፡ራሱን፡"የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ዓለም አቀፋዊ የምእመናን ማሕበር መግለጫ
WORLD ASSOCIATION OF PARISHIONERS OF THE ETHIOPIAN ORTHODOX TEWAHEDO CHURCH" ብሎ፡ስለሚጠራው፡ድርጅት፡ማወቅ፡ይቻላል።

ይህ፡ድርጅት፡በቅርቡ፡ብቅ፡ያለና፡ከብፁዕ፡አቡነ፡
ይስሐቅ፡ጋርም፡ሆነ፡በእርሳቸው፡ሥር፡ሲንቀሳቀ
ስ፡ከነበረው፡ማህበረ፡ኦርቶዶክስ፡ዘተዋሕዶ፡ጋር፡
አንዳችም፣ታሪካዊም፡ሆነ፡ወቅታዊ፡ግንኙነት፡እ
ንደሌለው፡ይህ፡ጸሐፊ፡ያረጋግጣል።

አባታችን፡መሥርተውት፡የነበረው፡ማህበረ፡ኦርቶ
ዶክስ፡ዘተዋህዶም፣እርሳቸው፡ካረፉ፡ወዲህ፡እንደ
ቀድሞው፡አይንቀሳቀስም።እርሳቸው፡ካረፉ፡ወዲህ፡
ይህ፡ጸሐፊ፡የተገኘበት፡አንድም፡ጠቅላላ፡ጉባኤ፡ተ
ጠርቶ፡አያውቅም።

ይህን፡የመንፍቃን፡መግለጫ፡ይህ፡ጸሐፊ፡የሚያው
ቃቸው፡ሁሉ፡ያወግዛሉ!

የቀረበውን፡መግለጫ፡ያቀረበው፡ድርጅት፡ከነስሙ፡
የሚያሰድንቅ፡ሆኖብን፡ብዙዎች፡ተወያይተንበታል።

ብቅ፡ሲልም፡ያነገበው፡የዴር፡ሱልጣንን፡ገዳም፡ች
ግር፡አንተርሶ፡መሆኑን፡አሁንም፡እድርጅቱ፡ዌብ፡
ሳይት፡በመግባት፡መረዳት፡ይቻላል።

የማይገለጥ፡እንደሌለ፡ሁሉ፣ይኸው፡ይህም፡በጊዜው፡
ተገለጠ!

የአባታችን፡የአቡነ፡ይስሐቅ፡ስምና፡እርሳቸውም፡
የሰበሰቡት፡ጉባኤ፡ከንዲህ፡ያለ፡ፀረ/ተዋህዶ፡መግ
ለጫ/ደብዳቤ፡ጋር፡አንዳችም፡ግንኙነት፡እንደሌ
ለው፡የታወቀ፡ይሁን።

ለአሁኑ፡ይህ፡በቂ፡ማስረጃ፡ነው።ዋናው፡ነገር፡መናፍ
ቃን፡በስንት፡የተለያየ፡ዘዴ፡መሐላችን፡ገብተው፡አ
ንድነታችንን፡ለማዳከምና፡ለማፍረስ፡በመጣር፡ላ
ይ፡መሆናቸውን፡መረዳቱ፣መገንዘቡና፡ተጋድሏችን
ን፡በጥንቃቄ፡ለማገባደድ፡መጣሩ፡ላይ፡ነው!

ወገንን፡ከጠላት፡እንዳንደባልቅ፡እንጠንቀቅ!

መድኃኔ፡ዓለም፡ክርስቶስ፡ተዋህዶ-ኢትዮጵያን፡
ከመጣብን፡የጥፋት፡ውዝንብርና፡ርኩሰት፡ያድነን!
አሜን፤አሜን፤አሜን።


ሰይፈ፡ገብርኤል።

Anonymous said...

"Blogger ferecha said...

Please watch this video about decision of Abune Shenouda III about "kidiste kidusan dingle mariam"

http://www.youtube.com/user/medhanialemeotcks#p/u/12/U2fplUxOgXc

October 26, 2009 "

ለአባ፡ሸኑዳ፡ካቅማቸው፡በላይ፡ነው፡እመ፡ብርሃን፡
ላይ፡"decision"ማድረግ።አላግባብ፡ባይንጠራ
ሩ፡ለእርሳቸውም፡ሆነ፡ለግብጽ፡ሕዝበ፡ክርስቲያን፡
ብጎ፡ነው።

የግብጽ፡ክርስቲያን፡የሚገኝበትን፡ሁናቴ፡አስመ
ልክቶ፡እንኳ፡"decision"ላድርግ፡ቢሉ፡እነሙ
ባረክ፡አይፈቅዱላቸውም!ሌላው፡የ"ቀሲስ"አስተ
ርአየና፡መሰሎቻቸው፡(የመናፍቃን፡"ተስፋ፡)የተ
ሐድሶ፡ሰዎች፡ሉተራዊ፡ዘመቻ፡መሆኑ፡ፍጹም፡አያ
ጠራጥርም!

ከ1600፡ዓመታት፡ባርነት፡በኋላ፡ከግብጽ፤ባርነት፡
የወጣን፡ስለሁነ፣ተንግዲህ፡እዚያ፡የሚያስመልሰን፡ም
ንም፡ጉዳይ፡የለንም።

ተዋህዶን፡የተሟላች፡ሃይማኖት፡አድርጎ፡እግዚእነ፡
ኢየሱስ፡ክርስቶስ፡ለኢትዮጵያውያን፡ስለሰጠን፡ክ
ብርና፡ምስጋና፡ይድረሰው።

በትዕቢት፡የሚፋላሰፉትን፡በምጽአት፡ጊዜ፡እንፋረ
ዳቸዋለን።

እመ፡ብርሃን፡ከጥፋት፡ርኩሰት፡ትጠብቀን!
ከልጇ፡ከወዳጇ፡ከእግዚእነ፡ኢየሱስ፡ክርስቶስ፡ዘንድ፡
ይቅርታን፡ትለምንልን!

አሜን፤አሜን፤አሜን።

ሰይፈ፡ገብረኤል።

Anonymous said...

“የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ዓለም አቀፋዊ የምእመናን ማሕበር” በአለሁበት በዳላስ-ቴክሳስ ከተማ በህዳር ወር 1999/ 2006 እንዳደረገው የበጎና ተስፋ ሰጪ ጉባኤ/ ማህበር ሆኖና ዋና ዋና አላማውም በተለይም በሀገራችን -የሚገኙትን ገዳማትንና የአብነት ት/ቤቶችን የማጠናከር ጉዳይ - በኢየሩሳሌም የሚገኘውን የዴር-ሱልጣን ገዳም ጉዳይ በተመለከትና - የአክራሪው እስልምና የመስፋፋት ጉዳይ ሆኖ ቢቀጥል ምንኛ ደስ ባልኝ። አሁንም በቅርቡ ባወጡት መግለጫ ውስጥ በአብዛኛው ፍሬ ሀሳብም የምጋራው ነው። ነገር ግን፡
“..…. (ሀ)ቃለአዋዲውን ስለ ማሻሻል፤ (ለ) መጠናት ስለሚገባቸው ድርሳናት፤ ገድላት፤ ውዳሴያትና ታምራት፤ …. (መ) ቅዱስ ቁርባኑን ባለመቀበል፤ አብዛኛዎቹ ምእመናንና ምእመናት በቅዳሴያችን በግልጽ እንደ ተቀመጠው፤ የእግዚአብሔርን ሕግ አፍራሾች ሆነን ስለ መገኘታችን፤ (ትምህርት አነሰን ለማለት ይሆን? ) ….” የሚለው ግን …….. ትልቁ ዳቦ …….! የማለት ያህል ነው።
ትልቅ ዝቅጠት!!

ከዳላስ

Anonymous said...

What they call "Alem Aqef" is not really alem aqef. It is an association built by certain groups of people from one area. We cannot afford this kind of division under the cover of "alem akef".

Please do not be shreud espcially with regard to our church.

Thank you and God bless

solomon said...

To anonymous who ask
"Do you really belive Belaeseb after killing and eating 78 people went to heaven because he gave that little water? Does it make sense to you really?"
ለምንድን ነው ገነት መግባቱ ቅር የሚልህ?ከበላኤ ሰብና በክርስቶስ ቀኝ ከተሰቀለው ማንኛው ለገነት የቀርባል(ፈራጁ አመላክ ነው)በቀኝ የተሰቀለው ለጥቂት ደቂቃ ነስሀ ስለገባ እንጅ አንድ ጠብታ ውሀ እንኳን ለተጠማ አለጠጣም ፤ስጋውና ደሙን አልተቀበለም ግን ገነት ገባ።ለምን ገባ?በቃ ገባ ‘ለምን?እንዴት’የሚል ጠያቂ በመንፈሳዊ አየን ቦታ የለውም።ክርስቶስ በደቀ መዝሙሬ ስም ቀዝቃዛ ውሀ ያጠጣ ዋጋው አይጠፋም ብሏል(ማቴ10 ቁ42)ገነት መግባት ብዙ ገንዘብ በመስጠት አይደለም።ነስሀ እና ያለህን ትሿን ከሰጠህ ዋጋ አለ
ታምሯን ማዳመጥ ቅዱስ ቁርባንን ይተካል ከእንግዲህ ስጋና ደሙ የእርሷን ታምር መስማት ነው አልተባለም፤መጽሀፍ የሚለው የቻለ(ነስሃ የገባ)ይቀበል ያልሆነለት በተለያየ ምክንያት ለስጋና ደሙ አልበቃሁም የሚል ከሆነ ተስፋ አይቁረጥ ማለት ነው፤በሌላ በኩል ደግሞ አዲስ ክርስቲየኖች አምነው ምስጢረ ቅ/ቁርባን አስኪቀበሉ ድረስ እግዚአብሄር በቀኙ እንደተሰቀለው ሽፍታ የቸርነቱን ስራ የሰራላችሗልና ባእምነታችሁ ተጽናኑ ማለት ነው፤ለመሆኑ ሽፍታው መቸ ቆርቦ ነው ገነት የገባ?የእግዚአብሄር ቸርነቱ ብዙ ነው።ማንስ በየቀኑ ይቆርባል?ማንም።
ሌሎችን በሌላ ጊዜ አሁን መሸ ደህና እደር

Anonymous said...

Solomon:
You see where you are heading? This is what is called sect and cult. If a faith contradict itself here and there that is not faith. Then why baptism?repentance?holycommunion? Just listen to Teamiremariam. May be it works for you and the likes,but for EOC it didn't and it doesn't. We didn't learn this of your teachings from the fathers. STUDY HARD WHAT IS ORTHODOXY. It is not emotions. It is principles.I know most of MK members are in huge battle with those dallas group.

solomon said...

To anonymouswho ask

"Then why baptism?repentance?holycommunion?
ስለ ታምረ እየሱስና ስለ በላኤ ሰብ ስለተግባባን እኔ እና አንተ አንድ እርምጃ ወደፊት ሂደናልና ጥሩ ነው፤ሌላ ቀን እነዚህን ጥያቄወች እናያለን የሚል እምነት የለኝ

እኔ ያልኩት ቅ/ቁርባን በታምረ ማርያም ይተካ አይደለም፤ አላልኩምም፤ አልልምም።ይህ ታምር የሚነበበው’ኮ ሰው ቆርቦ ወደቤቱ ሊሄድ ሲል ነው።ሰው ንስሀ ይግባ ፤ቅዱስ ስጋውንና ቅዱስ ደሙን ይጠጣ ነገር ግን ለዛሬ ባይሆንለት በጸጋ እግዚአብሄር ይጽናና ማለት cult የሚያስብል አይመስለኝም።በፈጠረህ እንዲህ አትበለኝ፤ወንድምህን ትሰድበኛለህ?እስኪ አንድ ጊዜ ልጠይቅህ “በቀኝ የተሰቀለው ሽፍታ በዚህ ቀን በአብ በወልድ በመንፈስቅዱስተጠመቀ፤በዚህ ቀን ንስሀ ገባ፤በዚህ ቀን ቅዱስ ቁርባን ተቀበለ “በለኝ።አትችልም። ገነት ገባ ግን እልሀለሁ፤፡ለምን ገባ?ክርስቶስ ከውሃና ከመንፈስ ቅዱስ ካልተወለዳችሁ ፤ስጋዮን ያልበላ ደሜን ያለጠጣ ያለው የታል?ብለህ ወደ ፍልስፍናና ጥርጥር አትሂድ የሚኮንንም የሚያጸድቅም ራሱ ክርስቶስ ነው።ቸር ሆኖ መሀሪ ሆኖ እምነቱን አይቶ ገነት አስገባው እንጅ ፕሮሲጀር እያየ ቲክ የሚያደርግ አምላክ አይደለም።አንድ ሽ አንድ ጥሩ ሰው ብትሆንም ያለ እግዚአብሄር ቸርነት አይጸደቅም።አንድ ምሳሌ ልስጥህ ሰው “በልቡ” አይቶ የተመኘ አመነዘረ ይላል፤አመንዝሮች ደግሞ ወደ እግዚአብሄር መንግስት አይገቡም።ስንት ሰው ይሆን እስኪሞት ድረስ “በልቡ” ሀጢያት የማይፈጽም?እግዚአብሄር ግን እንደሀጢያታችን ሳይሆን እንደቸርነቱ ይቅር ይለናል፤የእግዚአብሄርን ቸርነት አትርሳ።
አርእስት ስተን ብዙ ሂደናልና dsሞችን ይቅርታ ጠይቄአለሁ ፤ለወደፊቱ ከርእስ የወጣ ነገር መጀመርያ ባትደባልቁ ጥሩ ነው፤ከተጀመረ ግን እቀጥላለሁ።

Anonymous said...

In EOC we have doctrines and cannons. We don't just teach morality. Our moral and ethics teachings comes from our doctrines. We know God through his natures. If we are not bound our teachings by principles how come we are different from muslims?,protestants?..... No way sir. Don't campare one time incident with the broader principle. God is not going to chose randomly who goes to heaven and who don't. He has laid down principles.Believe in His son,repent your sins,get biptized and take holycommunion. These are the core teachings of our Lord and our church. You don't compromise on these principles and introduce a window entrance.Everybody has to come through the door.If your are concered about those who don't communion, you don't change the rule of the game. You have to teach them honestly and openly about the communion.Do you know why everybody don't don't take holycommunion in our church? it is because we scare them, we made taboo around it. Go to other sister orthodox chuches.
For the harsh word I apologize.

Anonymous said...

+++

""የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ዓለም አቀፋዊ የምእመናን ማሕበር መግለጫ መግለጫ ተስፋን እኮ አስፈነደቀው""

Ze Zeway Hamere Noh

solomon said...

ወንድሜ anonymous ሀሳብህ ግልጥ ነው
ሰው ሁሉ ይጠመቅ ንስሃ ይገባና ቅ/ቁርባን ይቀበል ዘንድ ቤተ/ክርስቲያን ዶገማዋ እንደሆነ አምናለሁ እርሱንም አስተምራለሁ።በድፍረት ቅ/ቁረባን እንዳይቀበሉ እና ፈሪሀ እግዚአብሄር እንዲኖርም ጨምሬ አስተምራለሁ።ለኢትዮጵያ ህዝብ ልናደርግ የሚገባን የያዙትን እምነት በመጽሀፍ በመደገፍ እምነታቸውን እንዲያጠነክሩ እንጅ የያዙትን እምነት እንዲጥሉ እና ጥቅስ አዋቂ ብቻ እንዳይሆኑ ነው፡ለዚህም መጽሀፍት ይቀነሱ ይጨመሩ እየተባለ ሰው ለቤተ ክርስቲያኑ ያለው ፍቅር እንዲቀንስና በእምነቱ ተጠራጣሪ እንዲሆን መደረግ የለበትም።
እዚህ አገር እንደምናው መጽሀፍ ቅዱስ አዋቂ ነገር ግን እምነት የሌለው ህዝብ ከእግዚአብሄር ጋር ህብረት የለውም።

Anonymous said...

Dear Solomon:
Do you think I am for the reduction of books. No. But what I am saying is for the eradication of those so called books which are inconsistent with the fundamental teachings of our doctrines. We have to be God fearing people. I agree. But there are a millions of good God fearing people in the world. We christians have basic ways of fearing God. Fearing God in Biblical ways. It is Him who gave us his body and blood. It is not because anybody deserves it. It is just because of His abundant mercy and salvation. Do you think rthe EOC faithful people don't take communion just because they are God fearing peopl? No.That is not true and denial. It is because we intimidate them. I have a lot of friends and family members who have died with out taking holy communion.You know what bTeamire mariam says" besela sostu eletat atisru endeehud senbet akburuachew. Doyou do it. You don't.If you don't why just read it everysunday? Lips exercise?

solomon said...

ወንድሜ anonymousእንዴት ነህ? እውነትም አንተ እንዳልከው መሆን የሚገባው በመጽሀፍ ቅዱስ ላይ ተመሰረተ የፍቅር ፍርሀት ነው፤ይሄ የካህናቱ የእኔና የአንተ ስራ መሆን ይገባዋል፤ከቤተሰብ ከተጀመረ’ኮ ሀገር ይሞላል ፤ብዙ ሰው ቀ/ቁርባን ሳይቀበል የሞተው በመፍራት ነው አላልኩም።ስለ ቅ/ቁርባን በቂ እውቀት ስለሌለው ነው ሚለው ያስማማናል ፤ስለዚህ ምእመኑ ራሱን በንስሀ እየፈተሸ ሲገባው በትህትና ሆኖ እንዲቀበል በእውቀት እንዲያድግ የእኛን ድርሻ እንወጣ።
ስለመጻህፍት ስታነሳ በሙሉ የቤተክርስቲያን መጻህፍት 100%ትክክል ናቸው ብየ አልልም።ለዚህ ብዙ ምክንያት መስጠት ይቻላል።አንኳን በቁጥር የማናውቃቸው የቤተክርስቲያን መጻህፍት ቀርቶ በቁጠር የተወሰነው መጽሀፍ ቅዱስም ከትርጉም ትርጉም ከቋንቋ ቋንቋ ይለያያል(መጀ.የዩሐ.መል 5 ቁ 7 በአማርኛው የተጻፈው በእንግሊዝኛው ከተጻፈው ፈጽሞ የተረራቀ ነው -ስላሴ የሚለውን ትምህርት የሚቃወም)።ነገር ግን መጽሀፍ ቅዱስ እንዲህ የለየለትን ትምህርት በቋንቋችን ሲጻፍ አውጥቶታልና አያስፈልግም አንልም።መጽሐፍ ቅዱስን ይህን ያህል መሰረዝ የሚችሉ ከሆነ በሌሎች ላይማ እንዴት እንደሚጨምሩና እንደሚቀንሱ ሳስበው ይገርመኛል፤እንዲህ ስል ሰው በዘፈቀደ የጻፈውን ሁሉ እንቀበል እንዳልሆነ ይሰመርልኝ፤በእውነት ዶግማ ላይ ህጸጽ ካለበት ሙሉ መጽሀፉን ሳይሆን በስህተት የገባውን ለይተን ማውጣት አለብን እንጅ እንዴው በደፈናው መጽሀፉን ማጥፋት አግባብ አይመስለኝም።ተግባባን?
በታምረ ማርያም ላይ 33 ቱን ቀናት መታሰቢያየ ናቸውና እንደ እሁድ ሰንበት አክብሩ የሚል መኖሩ ገርሞሀል፤ለእኔ ደግሞ አልገረመኝም ስህተት አይመስለኝም፤ጥያቄአችን ሊሆን የሚገባው በዐል ሲከበር እንደአይሁድ ሰንበት አከባበር እንዳልሆነ ነገር ግን እንደክርስቲያን እንዴት ሊሆን እንደሚችል በማስተማሩ ላይ ነው።በአል ማክበር በረከት ያሰጣል የሚል እምነትና ስምምነት እስካለን ድረስ።ሰው የማያከብረው ከሆነ ለምንድን እናነብለታለን? ያልከው ትንሽ ያላስተዋልከው ነገር ያለ መስለኛል እንኳን ታምረ ማረያም ላይ ያለ ህግ ቀርቶ ከ10ቱን ትእዛዛት ውስጥ አትዋሽ አትዘሙት ሰንበትን አክብር እና የመሳሰሉትን ህግጋትም አልሰሙምና በቃ 10ቱ ህግጋት ይቅሩ ወይንም መጽሐፍ ቅዱስ ይቅር አያስፈልግም አንልም፤lip exerciseአይመስለኝም ።

Anonymous said...

Is anybody say 'i don't take holy communion because i have heard TeamereMariam?'i never heard this thing before.Nobody sir .Even they may not know seach stetements in the book.All people know they have to take communion but they have little knowledge, not because of TeamereMariam

Anonymous said...

Solomon:
I applaud your honesty eventhough I still don't agree on you some pointys.. Comparing the 10 commandments with the 33 bealats. You know what I fail to live up to the 10 commandments? Yes you right. But I always tries to live up to it and make honest effort to correct myself. In case of teamiremariam you listen to them but never try to accomplish them. That is why I said lips service. If you don't even try to live up it and make any effort at all why read them.I am not hear to say that it is easy to challenge ourselves. It is hard as EOC is laging behibd in ever aspects as long as we radicalize ourselves and refuse to repent and correct our past mistakes. It is going to be another very long dark nights before we see a bright days for EOC unless the young genaration stars to leanr bible by heart. Culture and tradition are good, but only after studying biblical doctrines.Dear brother how many % of people take communion in your church? May be less than 1%, elderly and crying kids. The rest are spectaters.Are you going to tell me that "BEKEMEMIHRETKE" Teach principles. Yoy know what St. Paul was zelous and God fearing person when St. Steph was murderd. He even collaborated. But he was not right. Because he was short of knowing the principles of the new theoplogy. That is believing in Christ. Principle matters in the church. Not fantasy.We can fantasize with our traditions and customs. But in God's eye it is our faith which saves us.

solomon said...

in God's eye it is our faith which saves us.
ድንቅ አባባል! ዋናው እምነቱ ነው እነጅ የመጽሐፍ እውቀት አይደለም፤አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው እምነት ነው ፤ሰው እግዚአብሄር በጸበል እየፈወሰው እንደሆነ ያውቃል ፤እምነት ስላለው ይድናል።ስለጸበል ከመጽሀፍ ቅዱስ የት ላይ እንደሚገኝ ላያውቅ ይችላል ምንም ችግር የለውም ።እኔና አንተ ደግሞ ህዝቡ እምነቱን(እግዚአብሄር በጸበል እንደሚያድን)ሳንነካ በምናውቀው በመጽሀፍ ቅዱስ ልናበረታታው ይገባል።እኔና አንተም ስለ በጎ ነገር በክርስቲያናዊ መንገድ ተወያይተናልና አመሰግናለሁ

Anonymous said...

Solomon:
You are talking about the physical healing,I am talking about the heavenly healing. We didn't need the sacrifies of Jesus Christ for physical healings. We needed Him for eternal salvation. Tsebel heals fro physical illnes not from the spiritual. I have no problem if the Tsebel heals you. Jesus said work for the heavenly bread not for the one which perishes.Some oneu may be healed by Tsebel physically but he may end up in hell. That is why you need biblical knowledge. Tsebel for everybody,but Holycommunion only for those who believes Jesus died for his sins.I know people make a lot business from the Tsebel theory. Let them do it as long as they are not caught.
Thanks

solomon said...

ምን አይነት መዘባረቅ ነው?

Tsebel heals from physical illnes not from the spiritual.
vs
i know people make a lot business from the Tsebel theory. Let them do it as long as they are not caugt

እንግባባለን እያልኩ ነበር ነገር ግን አልተግባባንም።እኔ የማየውን አነተ አላየህም ወይንም አንተ የምታየውን እኔ አላየሁም።ቻው

Anonymous said...

Solomon:

Take five. You did it good!
If I 'm you I'll stop here and spend my time on other issues/ matters.

Anonymous said...

Solomon:

Take five. You did it good!
If I 'm you I'll stop here and spend my time on other issues/ matters.

new anonymous

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)