October 23, 2009

ቅ/ሲኖዶስ የሰንበት ት/ቤቶች ማ/መምሪያ በሊቀ ጳጳስ እንዲመራ ወሰነ

(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 23/2009)፦ ቅ/ሲኖዶስ በዛሬ የስብሰባ ውሎው የሰንበት ት/ቤቶች መምሪያ በሊቀ ጳጳስ እንዲመራ ወሰነ።

ቅዱስ ሲኖዶስ በአባ ሰረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል ሥር የነበረውን በመተው ከበላይ ሊቀ ጳጳሱን አቡነ ቀሌምንጦስን ሾሟል ተብሏል።
በተያያዘ ዜናም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ዋና መምሪያዎች የሆኑት የስስብከተ ወንጌል ሐዋርያዊ አገልግሎት እንዱሁም የሰበካ ጉባዔ መምሪያዎች በሊቃነ ጳጳሳት እንዲመሩ አባቶች መድቧል። በዚህም መሠረት ለስብከተ ወንጌሉ ብፁዕ አቡነ ማርቆስን፣ ለሰበካ ጉባዔ ደግሞ ብፁዕ አቡነ ያሬድን መሰየሙ ታውቋል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ዜና ርዕስ የሆነው ይኽ መምሪያ በሥሩ የሚተዳደረው ማህበረ ቅዱሳን ላይ እየፈጸመ በነበረው ሕግ ዘለል እርምጃ ፖለቲካዊ ትርጉም ይዞ የመገናኛ ብዙሃን መነጋገሪያ መሆኑ አይዘነጋም።

በዚህ አኳያ የሰንበት ት/ቤቶች መምሪያ በሊቀ ጳጳስ የሚተዳደር ከሆነ አባ ሰረቀ የሥራ ሃላፊነት ምን እንደሚሆን ለጊዜው ግልጽ አልሆነም።

21 comments:

ሰይፈ ሚካኤል said...

Whatever the quencequence, realy it is good news...
Congra to all who share my idea.

solomon said...

እግዚአብሔር ለቤቱ ይቀናልና እኛ አገልጋዮቹ ዝም ብለን ከእኛ የሚጠበቅብነን እንስራ፤፡ሐማ ወደ መሰቀያ ከመሄዱ በፊት ንስሀ ይግባ፤ ማህበሩም በርትቶ ይስራ፤እግዚአብሄር እንኳን ከታሰበ ከተወረወረ ጦር ይሰውራል ።”እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ባይሆን ጠላቶቻችን በዋጡን ነበር” ነው ያለ ቅ.ዳዊት

Anonymous said...

የእመብርሃን ነገር መገለጥ ጀመረ። እውነት ፈጣሪ እኮ ቤተክርስቲያንን ለማንም አይተዋትም። በእውነት በሳል እና የአርቆ አሳቢነት ርምጃ ነው። ……እዩ እንግዲህ ምድረ ተሃድሶ ሁላ ስድብ እና ዛቻ መጻፍ ሲጀምሩ ታዘቡ!! …..የአባቶቻችን አምላክ፣ ከዚህ የበለጠ በጎ ዜናን ያሰማንማ!! ቅዱስ መልዐኩን ልኮ ፈጣሪ ቤተክርስቲያናችንን እንዲህ ይታደግልን እንጂ!!

Anonymous said...

አቤት አቤት አቤት! ይህ ሁሉ የሰሞኑና ያፈው ዓመት ግርግር እኮ አንድ ፕላኔት የሚያወርድ ይመስል ነበረ…. አሁን እስቲ ማን ምን አመጣ? እንዲያው ዝም ብለው ሲፎክሩ ማህበረ ቅዱሳን አባላትን በሙሉ በጥይት ቆልተው የሚጨርሱት ይመስሉ ነበር እኮ! እውር ቢሸፍት እስከጓሮ፡፡ ማኅበረ ቅዱሳንን አንድ ነገር ብቻ ያጠፋዋል- ያውም ለጊዜው- እሱም ሁሉንም የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች በጅምላ መጨረስ ነው፡፡ ሃ ሃ ሃ…! እንዲያ ካላደረጉ በቀር ማኅበረ ቅዱሳንም ሆነ ያሰራጨው መልእክት ከወጣቱ ዘንድና ከእኛም ከምዕመናን ዘንድ ስለማይጠፉ፡ አባ ጳውሎስና ግብረ አበሮቻቸው ጫካ ገብተው ትግል ቢጀምሩ ይሻላቸዋል… ሃ ሃ ሃ…

ተሃድሶን የመሳሰሉ የኮምፒተር አርበኞችን እንኩዋ እኛ እንበቃቸዋለን፡፡ ደሞ ለመጠዛጠዝ! ሃ ሃ ሃ!

Anonymous said...

ተስመገን፡ራሱ፡እግዚአብሔር፡ያውቃልና፡የሚሰራውን መጠበ
ቅ፡ነው
እግዚኦ፡መሐረነ፡ክርስቶስ!
በእንተ፡እግዚእትነ፡ማርያም፡
Ke Ziway

Anonymous said...

እኔ በጣም የገረመኝ “ተዋሕዶ መቼ ነው የምታበራው…. መቼ ነው ነገረ ሃይማኖትን የምተሰብከው” እል ነበር!! እሷ ልጄ የምግባር ባለቤት ናትና በተግባር ስትፈጽም ቆይታ አሁን ደግሞ በቃልም ልትናገር ወገቧን አጥብቃ እየተነሳች ነው!! ብጹአን አባቶቻችንን ማስተዋልና ጥበብ ይስጥልን! በእድሜ ያቆይልን እንጂ ገና ብዙ ዜና እንሰማለን! …..ከሁሉ በላይ ደስ የሚለው የስብከተ ወንጌል ክፍሉ በሊቀ ጳጳስ መመራቱ ይበል የሚያስብል ነው።

ቸር ወሬ ያሰማን! እመ አምላክ ወላዲተ አምላክ አትለየን!

solomon said...

ሰው ዝም ብሎ የእግዚአብሔርን ማዳን ቢጠባበቅ ጥሩ ነው።የተቀመጣችሁ ተነሱ ይላል ዲያቆን በቅዳሴ።የተኛ ፤ያንቀላፋ የደከመው ካለ አሁን ይንቃ።ከእኛ ጋር ያሉት ከእነርሱ ጋር ካሉት ይበልጣሉ እና አትፍራ እተባባልን ልንበረታታ ይገባል።

Anonymous said...

የማኅበረ ቅዱሳን አባላት : አሁን ተረጋጉና ራሳችሁን ፈትሹ :

የሆነ ቦታ ስማችሁ በክፉ ሲነሳ : ለምን ተነካን : ለምን ተደፈርን : የሚለውን እልከኛ ሀሳባችሁን ተወት አድርጉና ወደ ራሳችሁ ወደ ውስጣችሁ ተመልከቱ ::

ምን መልካም ሰራን ?
ምንስ ስህተት ፈጸምን ? ብላችሁ ቆም ብላችሁ አስቡ ::

እነዚህን ሽማግሎችና የዋሃን አባቶች ጳጳሳት በተለያየ ዘዴ እየቀረባችሁና እያታላለችሁ በእጅና በእግራቸው ከገባችሁ በሗላ : እነሱን ሳይቀር ወደ መናቁ ደረጃ መድረሳችሁን አስተውሉ ::

እንድታገለግሉ መድረኩን ሲፈቅዱላችሁ : እነሱ እኮ ምንም አይሰሩም እኛ ነን ሁሉንም ነገር የምንሰራው :
ማኅበረ ቅዱሳን ባይኖር ኖሮ ቤተ ክርስቲያኗ ትዘጋ ነበር የሚሉና በትዕቢት የተነፉ አባላት በውስጣችሁ እንዳሉ አስተውሉ ::

ሁሉ አማራሽን....... እንደተባለው :
በቂ ችሎታ ሳኖራቸው : በዲቁና አስተካክለው መቀደስ የማይችሉትንና ማዕጠንት እንኳን በቅጡ መወዝወዝ የማይችሉትን አባሎቻችሁን : ቀሲስ ዕገሌ : እያላችሁ : ቤተ ክርስቲያኗን : በተራው ኪዳን በማይደግም ቄስ ሞላችሗት :
ይህም ሳይበቃ : መነኮሳት ወደ ገዳማቸው ይግቡ : ቄሶቹ እንበቃለን የሚሉ : እነ አቶ ቄሶች የማኅበራችሁ አባላት በርክተዋል ::


ሌላውን ለመክሰስና ስም ለማጥፋይ ብቻ ሳይሆን የራስንም ስህተት ማራም ይገባል ::

ፍጹም ነኝ : አልሳሳትም : የሚል ሰው ግብዝነትና ፈሪሳዊነት እንደሚያጠቃው መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል

አባ ሰረቀ ብርሃን : ለተለያዩ የአብነት ትምሕርት ቤቶች ስንት ነገር ሲያደርጉ የኖሩ ቅን አባት ናቸው ::

የናንተን ሀሳብ ስላልተቀበሉ እንጅ : ወዳጃች ሁ ቢሆኑ ኖሮር : ይህኔ ስንት ቅድስና ትናገሩላቸው ነበር ::

እባካችሁ የተሰጣችሁን መክሊት አባቶችን ለመከፋፈልና
የራሳች ሁን ድርጅታዊ አሰራር ለማስፋፋት ብቻ አትጠቀሙት ::

ማኅበራት በጊዜያቸው ያልፋሉ : ቤተ ክርስቲያን ግን እስከ ምጽዓት ትኖራለችና ::

ባካችሁ የማኅበርና የግል ጉዳያችንን እናቆይና ስለአንዲት ቤተ ክርስቲያን ሰላምና መጠናከር እንስራ ::

ነገር ማባባስና ጋዝ ማርከፍከፉን ትታችሁ ለሰልምና ለእርቅ ስሩ ::

አምላክ ለሁላችንም በጎ ህሊና ያድለን

አሜን

Sentun ayehu said...

Whatever it is to me GOOD NEWS, gena enayalen enesemalen bezu bezu neger, selezihe Egeziabear mene yesenewal. DS, thank you for the update information. but we need full story as soon as you can.

Sentun Ayehu

Moona said...

GOD is with us !
you see how he gave shame for our enemy.
O! Lord thank you.You have your own plan ...
God will solve our problem according to his plan.
I Praise YOU Lord Almighty.

Nisir said...

so what is special? it is not changes of personality, but what is going to be done by the person appointed that matters for church. Don't rush to conclusion.
wait!are those people ready for change or just for cover up?

Anonymous said...

መድኃኔ፡ዓለም፡ክርስቶስ፡ገና፡ብዙ፡ያሳየናል።
ብዙም፡ያሰማናል።በቆራጥነት፡የጥፋት፡ርኩሰ
ትንና፡አስተጋቢዎቹን፡በመስቀሉ፡መቋቋም፡
አለብን።

በጎውን፡በደስታ፡ስንቀበል፣በማር፡የተለወሰ፡ የጥፋት፡መርዝን፤ግን፡በጥንቃቄ፡ማስወገድ፡
ግዳጅ፡ነው።ይህ፡የተዋሕዶ፡እምነታችንና፡የ
ቅድስት፡ቤተ፡ክርስቲያናችን፡ጉዳይ፡ስለሆነ፡
የደረሰብንን፡ፈተናና፡ግፍ፡በማነህ፡ማነሁና፡
በተድበሰበሰ፡ሁናቴ፡ተቋጭቷል፡ከማለት፡በ
መታቀብ፡እግዚእነ፡ኢየሱስ፡ክርስቶስ፡እንደ
ሚመራን፡በንቃትና፡በትጋት፡እየጸለይን፡በተ
ጋድሏችን፡መበርታት፡ይገባናል!


በእውነተኛ፡ንስሐ፡ላይ፡ለሚመሠረት፡አንድነት
የመስቀሉ፡ሕግ፡ስለሆነ፡ከዚያ፡ዝንፍ፡ሳንል፡እንድ
ንቀበል፡ሁሉም፡እስቲገለጥ፡ድረስ፡በጸሎት፡እንጠ
ብቅ።

ከሁሉም፡በላይ፡ቤተ፡ክህነት፡አስተድዳደር፡መጽ
ዳት፡አለበት።ዝርፊያው፣በቤተሰብ፡ተወጥሮ፡የተ
ያዘው፡የቤ.ክ.መዋቅርና፤ከዚህም፡ጋር፡አብሮ፡የ
በቀለው፡የማጅራት፡መቺዎች፡ቡድን፡ያደረሰው፡
ውርደትና፡በደል፡ሁሉ፡ግልጥልጥ፡ባለ፡ሁናቴ፡ተ
ወግዞ፡እንዲወገድ፡ካልተደረገ፡እውነተኛ፡አንድነ
ት፡ይመሠረታል፡ማለት፡ከክርስቶስ፡ትምህርት፡
ውጭ፡መሆኑን፡እናስተውል!

"ድካማችሁ፡በጌታ፡ከንቱ፡እንዳይሆን፡
አውቃችኋልና፡የምትደላደሉ፥የማትነ
ቃነቁም፥የጌታም፡ሥራ፡ሁልጊዜ፡የሚ
በዛላችሁ፡ሁኑ።"
1ኛ፡ቆሮንቶስ፡ምዕራፍ፡15፡ ቁ.58

ኃያሉ፡እግዚአብሔር፡በንስሐ፡የጠራ፡አንድነትን፡ለ
አባቶችና፣ለመላው፡የተዋሕዶ፡ሕዝበ፡ክርስቲያን፡ያ
ድለን።

ከጥፋት፡ርኩሰት፡ይጠብቀን!ያድነን!አሜን።


ሰይፈ፡ገብርኤል።

gorgoreyos said...

good dicstion!!! abatoch bizu kenanit entibikalen.aba/ seriq tehadso selhon bedinb mermirut. from amrica

Anonymous said...

Selama
In the Name of the Father, the Son and the Holy Sprit, One God Amen!
We are not against any body except Satan. Let us remove hate, rumor mongering and promote forgiveness and love each other. We shall be ready to render greater financial and professional contribution to the new department heads of betekinhet to the spread of the Gospel of the unrevised apostlic church to our Brothers in Gambela, South and North Omo and Benshanguel Gumez, for the Development of Monasteries, establishment of modern abinet schools in all nationalities and care centers for orphans and disabled under the guidance of the Holy Synod. We shall make also the Church the center for the green revolution for environmental conservation.
People have also to be ready to bring understanding between the Fathers at home and in Diaspora to bring an end to the division of the church in Diaspora.

Our Fathers Thank you!
God Bless Ethiopia

Anonymous said...

It is time to consider get a capable person(nOT NECESSARILY BISHOP) heading Sundayschool department and assimilate MK under it. Why have defacto sundayschool?,like MK? Or Choirs associations here and there?

Anonymous said...

አሁን የሚያሳስበው እርሳቸው ከቦታው መነሳታቸውና ሌላ ሰው(ሊቀ ጳጳስ)መሾሙ ሳይሆን በቦታው የተቀመጡት አባት የማህበሩን አላማ ተገንዝበው ለወንጌል ይፋጠናሉ ወይ? ነው ያለበለዚያ ጉልቻ ቢለዋወጥ ወጥ አያጣፍጥም ወይንም ትሻልን ሰድጀ ትብስን አመጣሁ ይሆናል ነገሩ

tad said...

Celebrate for what? Because the bishops are moving to privatize each and every post in the church? What makes the bishop to be the most qualified? His robe? Are they not those who caused all those problems? Give each bishop additional post and EOC problems will be solved????

Anonymous said...

He who says he is in the light and hates his brother, is in the darkness even until now.

He who loves his brother remains in the light, and there is no occasion for stumbling in him.
But he who hates his brother is in the darkness, and walks in the darkness, and doesn't know where he is going, because the darkness has blinded his eyes.

1ST JOHN 2:9-11

Anonymous said...

በሚያደርጉት የዕብሪት ትንኮሳ ነው ::

የደጀ ሰላም ሳይት አዘጋጆች ሆይ !

አባላቱ ስህተቶቻችውን ለማስተዋል ሊጠቀሙበት እንዲችሉ : በነሱ ላይ የሚነሱ የተቃውሞ ጽሑፎችን እንዲነበቡ ዕድል ባትነፍጓቸው ጥሩ ነው እላለሁ ::

በመጨረሻም አንድ ለማንሳት የምፈልገው ነጥብ

ማኅበረ ቅዱሳንን የተቃወመ ሁሉ መናፍቅ ነው ተሃድሶ ነው እያልን ራሳችንን አናታል ::

ተሃድሶ የራሱ የሆነ የተለየ አጀንዳ ያለው ቡድን ነው ::

እኛ እየተናገርን ያለነው : ከቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለን እውነተኛ ልጆቿ ስንሆን

ማኅበረ ቅዱሳንን : እንዳንጠላውም እንዳንወደውም ግራ እያጋባን ይገኛል ::

ስለዚህ አባላቱ ትዕቢታቸውንና መመጻደቃቸውን ትተው እንደ ድሯቸው በቅንነት ይስሩ : ያን ጊዜ ሁላችንም እጅ ለጅ ተያይዘን በፍቅር እንሰራለን ::

""ይህኛው የማኅበር ልጅ ነው : ያኛው ግን አይደለም"" የሚለው ድርጅታዊ አሰራራቸው ብዙዎቻችንን እያሰናከለንና ግራ እያጋባን ነው ::

የማኅበር ልጅነት ከቤተ ክርስቲያን ልጅነት ሊበልጥና ዋናውን ማኅበረ ምእመናን ሊወክል መቸም አይችልም ::

ሳይታወቃችሁ እያደረጋችሁ ያላችሁት ይህንኑን ነውና ባካችሁ
. ከስህተታችሁ ተመለሱ
. ራሳችሁን መምሩ :
. ለአባላቶቻችም ስልጠና ስጡ ::

Anonymous said...

ማኅበረ ቅዱሳንን በግልጽ ከሚቃወማቸው ይልቅ
በድብቅ .
. የሚጠላቸው
. የሚረግማቸው
. የተለያዩ ስውር መሰናክሎችን የሚያስቀምጥባቸው : ይበዛል ::

ይህ ሁሉ የሆነበት ምክንያትም
አባላቱ በሚያደርጉት የዕብሪት ትንኮሳ ነው ::

የደጀ ሰላም ሳይት አዘጋጆች ሆይ !

አባላቱ ስህተቶቻችውን ለማስተዋል ሊጠቀሙበት እንዲችሉ : በነሱ ላይ የሚነሱ የተቃውሞ ጽሑፎችን እንዲነበቡ ዕድል ባትነፍጓቸው ጥሩ ነው እላለሁ ::

በመጨረሻም አንድ ለማንሳት የምፈልገው ነጥብ

ማኅበረ ቅዱሳንን የተቃወመ ሁሉ መናፍቅ ነው ተሃድሶ ነው እያልን ራሳችንን አናታል ::

ተሃድሶ የራሱ የሆነ የተለየ አጀንዳ ያለው ቡድን ነው ::

እኛ እየተናገርን ያለነው : ከቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለን እውነተኛ ልጆቿ ስንሆን

ማኅበረ ቅዱሳንን : እንዳንጠላውም እንዳንወደውም ግራ እያጋባን ይገኛል ::

ስለዚህ አባላቱ ትዕቢታቸውንና መመጻደቃቸውን ትተው እንደ ድሯቸው በቅንነት ይስሩ : ያን ጊዜ ሁላችንም እጅ ለጅ ተያይዘን በፍቅር እንሰራለን ::

""ይህኛው የማኅበር ልጅ ነው : ያኛው ግን አይደለም"" የሚለው ድርጅታዊ አሰራራቸው ብዙዎቻችንን እያሰናከለንና ግራ እያጋባን ነው ::

የማኅበር ልጅነት ከቤተ ክርስቲያን ልጅነት ሊበልጥና ዋናውን ማኅበረ ምእመናን ሊወክል መቸም አይችልም ::

ሳይታወቃችሁ እያደረጋችሁ ያላችሁት ይህንኑን ነውና ባካችሁ
. ከስህተታችሁ ተመለሱ
. ራሳችሁን መምሩ :
. ለአባላቶቻችም ስልጠና ስጡ ::

Anonymous said...

እግዚአብሔር፡ተዋሕዶ-ኢትዮጵያን፡ከመጣባት፡
ሁሉ፡ጥቃት፡ያድናት።

ዛሬ፡ትግሉ፡ከአውሬው፥ማለትም፡ከጥፋት፡ርኩሰ
ት፡ጋር፡ስለሆነ፣አንዳንዶች፡ከመናፍቃን፡ጋር፡ከመ
ደረብ፡በስህተት፡ከሆነ፡ራሳችሁን፡ለዩ!ሁለት፡ወዶ፡
አይሆንም።


የጓዳችንን፡ችግር፡እኛው፡ራሳችን፡መፍታት፡ስን
ችል፣የመናፍቃንን፡ዱላ፡አንስተን፡የቤተ፡ክርስቲ
ያንን፡ልጆች፡መደብደብ፡ከፓስተሮች፡የመጣ፡መ
ሆኑን፡እንወቅ።ይህ፡ለበጎ፡አይደለም።!
\
እስቲ፡በመጀመሪያ፡በፓትርያርኩ፡የተጠመደብን፡
ወጥምድ፡ይፈታ፤ከዚያ፡ቀስ፡እያልን፡ቤታችን
ን፡እናጸዳለን።ቦ፡ጊዜ፡ለኩሉ!!!

ሰይፈ፡ገብርኤል።

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)