October 30, 2009

በቅዱስ ዮሐንስ ጠበል ከሆድ ውስጥ ወፍ ወጣ


(ማኀበረ ቅዱሳን ስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ)፦ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በደብረ ወልደ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ እና በመካነ ጎለጎታ ቅድስት ማርያም ጠበል ሰሞኑን ከአንዲት እኅት ከሆዷ ጥቁር ወፍ ወጣላት፡፡ በክርስትና ስሟ መንበረ ማርያም ተብላ የምትጠራው እኅት ለ20 ዓመታት ያህል በሆድ ሕመማት ስትሰቃይ መቆየቷን የምትናገረው መንበረ ማርያም፤ ስቃይዋን በዘመናዊው ሕክምና ለማስታገስ ያልሔደችበት ቦታና ያልወሰደችው መድኃኒት የለም፡፡ ይሁንና የምትወስደው ሕክምና ለጊዜው ስቃይዋን ከማስታገስ በስተቀር ከሕመሟ ልትድን ባለመቻሏ ከዚህ በኋላ ይግደለኝ እንጂ ሕክም ናም ሆነ መድኃኒት መጠቀም የለብኝም፤ ብላ ጠበል ለመጠመቅ እንደ ወሰነች ትናገራለች፡፡ በውሳኔዋም መሠ ረት ወደ ወልደ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን ጠበል በመሄድ ስትጠመቅ በላይዋ ላይ የሰፈሩ 681 አጋንንት እንዳሉ በላይዋ ላይ ያደሩት የሰይጣን ሠራዊት ለፍልፎ በጥቁር ወፍ አምሳል ከሆዷ ውስጥ ሊወጣላት ችሏል፡፡


ምእመናን በዕለቱ ከሆዷ ውስጥ በትውከትነት እንደ ጥይት ተወርውሮ የወጣውን ጥቁር ወፍ ከነሕይወቱ በማየት በቪዲዮ በመቅረጽ የእግዚአብሔርን ድንቅ ተአምር እንደ መሰከሩ ተገልጿል፡፡

የስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራ ሰምቶ ይህንኑ ወፍ የወጣላትን መን በረ ማርያምንና ያጠመቋትን አባት ሊቀ ትጉኃን ስሙር አሐዱን በማነጋገር ድርጊቱ እንዴትና ምን ይመስል እንደነበር በሰፊው ዘግቧል፡፡

እግዚአብሔር ሥራው ድንቅ ነው፤ ተዓምሩ ዕፁብ ነው፤ ተነግሮ አያልቅም፤ ይህን ሥራውን መመስከር ደግሞ የእኛ ተግባር ነው፡፡ ለረጅም ዓመታት በሕመም ስትሰቃይ የነበረች በስመ ጥምቀቷ መንበረ ማርያም የተባለች ወጣት የእግዚአብሔርን የድንቅ ሥራው መገለጫ ሆናለች፡፡

ለዚህች እህት እግዚአብሔር ያደረገላት ገቢረ ተአምር ሲሰሙት ለጆሮ የሚከብድ፤ እንዲሁም በወቅቱ ድር ጊቱ ሲፈጸም የተመለከቱ ምእመናንን ሁሉ ያስደመመ ነበር፡፡ «ማን ያርዳ የቀበረ፤ ማን ይናገር የነበረ» ነውና ሥረ መሠረቱ ምን፣ እንዴትና መቼ ሆነ? የሚለውን ጉዳይ እሷው ባለታሪኳ እንዲህ ትተርክልናለች፡፡

«ያመኝ የነበረው ገና የአራት ዓመት ልጅ እያለሁ እሰቃይ ነበር፡፡ ለምሳሌ የራስ ምታት፣ ነስር፣ የሆድ ቁርጠት፣ የአንጀት ኢንፌክሽን ወዘተ እየተባለ በመታመም ሁልጊዜ ሐኪም ቤት እመላለስ ነበር፡፡ እናቴ እንደ ነገረችኝ የሕመሙ መነሻ ወተት ነው፡፡ «ወተት ጠጥተሽ የአንጀት ኢንፌክሽን ያዘሽ» ያለችኝ እናቴ በየክሊኒኩ እየወሰደችኝ ስታስመረምረኝ መድኃኒት እንደሚያዙልኝ አጫውታኛለች፡፡ ራሴን ማወቅ ስጀምር ትምህርት ቤት ገብቼ ስማር ሆዴን ያመኛል፡፡ በተለይ በበጋ ወራት ተምሬ ሁለት ወር ክረምት በሚሆንበት ወቅት ክፉኛ ያመኛል» ስትል ተናግራለች፡፡

መንበረ ማርያም በሕመሟ መጥናት ብዙ ጊዜ ሐኪም ቤትና ክሊኒክ ተመላልሳ እንደታከመች ገልጻል ናለች፡፡ ነገር ግን ጠበልስ አልሞከረች ይሆን? የሚለው ጥያቄ አጫረብንና ጠየቅናት፤ እርሷም ስትመልስ «በዚያን ወቅት ቤተሰቦቼ የሚያስቡት ሐኪም ቤት የሚባለውን እንጂ ጠበልን አልነበረም፡፡ እኔም ቢሆን በወ ቅቱ ጠበልን አላሰብኩትም፤ ብቻ ሐኪም ቤት ሔጄ የተለያየ መድኃኒት ይታዘዝልኛል እወስዳለሁ፡፡ ለጊዜው ያስታግሥልኛል፤ ጨርሶ ግን ሊያድነኝ አልቻለም፡፡ ይባስ ብሎ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስጄ ጥሩ ውጤት በማምጣት አራት ኪሎ ዩኒቨርሲቲ ገብቼ የመጀመሪያ ዓመት መማር ስጀምር በሽታው ክፉኛ አሰቃየኝ፡፡ ያስጨንቀኛል፣ ከፍተኛ የራስ ምታት ሕመም ይሰማኛል፤ ማጥናት አልችልም ነበር፡፡ የሴሚስተር ፈተና ደርሶ ሁለት ሳምንት ሲቀረው አንደኛው ዐይኔ ውስጡ ሲቆስል ሌላኛው ዕንባ ማፍሰስ ጀመረ፡፡ ዕንባው ያለምንም ማቋረጥ ለ24 ሰዓታት ይወርዳል፡፡ ቤተሰቦቼ ሁኔታው አላምር ቢላቸው ወደ አንዲት ታዋቂ የዐይን ሐኪም ወሰዱኝ፡፡ እሷም 'በሕይወቴ እንዲህ ዐይነት ነገር ዐይቼ አላውቅም፤ ዐይኗ ውስጥ ቁስል አለና የመታት ነገር አለ ወይ?' ብላ ጠየቀች፡፡ ይሁንና ቤተሰቦቼም ሆኑ እኔ ምንም ነገር የመታኝ ነገር እንደሌለ ለዶክተሯ ነገርናት፡፡ በየሰዓቱ የሚደረግ ጠብታ አዛልኝ ለጊዜው ተሻለኝ፡፡ የከፍተኛ ትምህርቴን ግን ሳልማር ለሁለት ዓመት ያህል አቋረጥኩ» ትላለች የሕመሙን አስከፊነት የምትናገረው መንበረ ማርያም፡፡

መንበረ ማርያም እንደገለጸችልን በጤና መታወክ ሳቢያ ለጊዜው ትምህርቷን ብታቋርጥም ለትምህርቷ ያላት ቁጭት ከፍተኛ ስለነበር በሽታው መጣ ሔድ እያለ ቢያስቸግራትም ከዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በመግባት ትምህርቷን በሥራ አመራር የትምህ ርት ዘርፍ ለአራት ዓመታት ያህል ተከታትላ በ1996 ዓ.ም በዲግሪ ተመርቃለች፡፡

ይሁንና ሌላ ያላሰበችው ችግር ገጠማት፤ ይህስ ምን ይሆን? ለዚህም መንበረ ማርያም ስትናገር «የወር አበባዬ ከመጣበት ጊዜ አንሥቶ አሁን እስከዳንኩበት ጊዜ ድረስ በየወሩ በጣም እያመመኝ ክፉኛ ያሰቃየኛል፡፡ ስቃዩን ለማስታገሻ እያልኩ ፓ¬ራሲታሞል ክኒን በየአራት ሰዓት ልዩነት ሁለት ሁለት ፍሬ በመዋጥ በቀን 10 ፍሬ እወስድ ነበር፡፡ ሐኪም ቤትም ብሔድ የሚሰጡኝ መርፌ ነው፡፡ አልሻል አለኝ፡፡ የሕክምና ባለሙያዎቹ 'አግብታ ትውለድ፤ ሴቶች እንዲህ ዐይነት ሕመም ሲሰማቸው ይሻላቸዋልና መውለድ አለብሽ' ብለው አስተያየት ይሰጡኛል» ትላለች፡፡

እንደ መንበረ ማርያም አገላለጽ ብዙ ጊዜ መድኃኒትም መዋጥ ሌላ ችግር /Side-effect/ ስላለው መድኃ ኒት መውሰዱን ታቋርጣለች፤ «ከድጡ ወደ ማጡ» እንዲሉ ይባስ ብሎ በየወሩ ያማት የነበረው እንደ አዲስ የማያቋርጥ የማኅፀን ሕመም ይሰማት ጀመር፡፡ በዚህን ጊዜም በታወቁ የማኅፀን ሐኪም በመታየት በወር አበባ ሳቢያ የተነሣ በማኅፀኗ ውስጥ ትናንሽ ዕጢዎች እንዳሉ ይነገራትና የወር አበባዋ ከመምጣቱ በፊት ለአንድ ሳምንትና ከመጣም በኋላ ለአንድ ሳምንት የሚወሰድ ከባድና በጣም ውድ የሆነ መድኃኒት ይታዘዝላ ታል፡፡ ይህ የሆነው ከሁለት ዓመት በፊት ነው፡፡

«በዚህን ጊዜ የመጨረሻ ቁርጥ ውሳኔ ወሰንኩ» ትላለች መንበረ ማርያም፡፡ «መሞቴ ለማይቀር ነገር ለምን እሰቃያለሁ? በመድኃኒትስ ለምን እቃጠላለሁ?» በማለት ወደ ጠበል ቦታ ለመሔድ ወሰነች፡፡ ጠበሉን እንድትሞክር ያነሣሣትና ምክንያት የሆነቻት ደግሞ ጓደኛዋ እንደሆነች ተናግራለች፡፡ «አንድ ጓደኛዬ እንደ እኔ ዓይነት ሕመም ይሰማት ስለነበር ጻድቃኔ ማርያም ሔዳ ጠበል ጠጥታ እንደዳነች ነገረችኝ፡፡ እኔም ጠበል መጠጣትና መጠመቅ እንዳለብኝ መከረችኝ፡፡ መድኃኒቱን አቋርጬ ጠበል መጠመቅ ጀመርኩ፡፡ እየጾምኩ በተከታታይ ጠበሉን ስጠጣና ስጠመቅ በየወሩ የወር አበባዬ ሲመጣ ያመኝ የነበረውን ተወኝ፡፡ በመቀጠል ከማኅፀኔ ሥጋ ነገር ተቆርጦ ወጣ፡፡ በዚህ ጊዜ ቤተሰቦቼ «እጢው ወጣልሽ» በማለት ተአምር አሉ፡፡ ሥጋ መሰል ባዕድ አካል ከወጣልኝ በኋላ ምንም ዓይነት ስሜት ሳይሰማኝ ጤነኛ ሆንኩ፤ ጠበሉንም አቋረጥኩት» በማለት ገልጻለች፡፡

በዚህ መልኩ ለውጥ ያገኘችበትን ጠበል ስታቋርጥ ዳግም ሕመሙ ጀመራት፡፡ መንበረ ማርያም ትናገራ ለች፡፡ «ጠበሉን ለአንድ ዓመት እንዳቋረጥኩ በሽታው በባሰና በሚያስፈራ መልኩ ተመልሶ መጣ፡፡ እንደገና ጠበሉን መጠጣት ጀመርኩ፤ በዚህን ጊዜም ደጋግሞ የሆነ ነገር በሕልሜ ያሳየኛል፤ በሆነ መንገድ ላይ በጣም ጥቁርና ትልቅ ሰውዬ ዝም ብሎ ቆሞ ዐያለሁ፣ ቀጥሎ እኔ ሕፃን ልጅ ታቅፌ ሳመልጥ እሱ ትልቅ ድንጋይ ይዞ እየተከተለ በማስፈራራት ሲያሯሩጠኝ ዐያለሁ፡፡ ይህን ያየሁት በድሮው ቤታችን መገናኛ አካባቢ ነው፡፡

የመንበረ ማርያም ዋናው ታሪክ የሚጀምርው በግንቦት ወር 2001 ዓ.ም ነው፡፡ በዕለተ ሰንበት እሑድ ቀን ቅዳሴ አስቀድሳ ስትመለስ እንደተለመደው የወር አበባ ይታያትና በቃላት ሊገለጽ በማይችል ሁኔታ በጽኑ ትታመማለች፡፡ መንበረ ማርያም እንደገለጸችው «መጽሐፈ አርጋኖን ይዛ ከአንዱ ክፍል ወደ አንዱ ክፍል እየተንቆራጠጠች 'ወይኔ! እመቤቴ ኧረ አድኚኝ' እያለች መኝታ ክፍሏ ሆና ስታጣጥር በድንገት በግድግዳ ላይ የተሰቀለውን የቅዱስ ሚካኤል ሥዕል ታያለች፡፡ እያጣጣርኩ በክፍሌ ውስጥ ቁጭ ብዬ ድንገት የተሰቀለውን የቅዱስ ሚካኤል ሥዕል ቀና ብዬ ማየት ስጀምር የፌዝ ሳቅ መሳቅ ጀመርኩ፡፡ በዚህን ጊዜ ራሴን እየለወጠኝ ነው፤ አልፎ አልፎ እንጂ ምን እንደምሠራም አላውቅም፤ መጣሁልህ ይላል፡፡ እንደዛር ማጓራት ጀመርኩ፤ አባቴ ሲሰማ ደነገጠ፡፡ እሱ እንደነገረኝ ሁለት እጄን ይዞ የቅዱስ ገብርኤል ጠበል እየረጨ 'አንተ ማነህ?' ሲለው 'እባክህ አንተ አታውቀኝም! ዝም ብለህ ነው፤ ተቃጠልኩ ጊዜዬ ሲደርስ የምለቅበት ቀን አለ፡፡ እሷን የያዝኩት ከማኅፀን ጀምሮ ያሳደግኳት እኔ ነኝ' በማለት ለፈለፈ፡፡ በመቀጠል 'እናቷንም የገደልኩ እኔነኝ' ሲል ራሱን ገለጠ» በማለት መንበረ ማርያም አስረድታለች፡፡ እናቷ በካንሰር ሕመም ምክንያት በ1995 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውንም ገልጣልናለች፡፡

በቅዱስ ሚካኤል ሥዕል ሳቢያ ማንነቱን የገለጠው ሰይጣን እንደያዛት ስታውቅ፣ የትመጠመቅ እንዳ ለባት ታስባለች፡፡ በመጨረሻም በደብረ ወልደ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን ሔዳ ጠበል መጠመቅና መጠጣት ትጀምራለች፡፡ በአምስተኛው ቀን ያደረባት ርኩስ መንፈስ መለፍለፍ ይጀምራል፡፡ በተለይ ሰኔ 10 ቀን 2001 ዓ.ም በዕለተ ረቡዕ ስትጠመቅ 681 አጋንንት እንደ ሠፈረባት ይለፈልፋል፡፡ ብዙ ሰው እንደጨረሰና አሁንም ብዙዎችን እንደያዘ ገልጾ እርሷ ላይ ሲደርስ ግን እንደተጋለጠ ተናግሯል፡፡ «ምእመናን እንደነገሩኝ ከሆነ «አንቺ ስትጮኺ እንደ አንበሳ ነው፤ የሚያስፈራና ከአንቺ የሚወጣ ድምፅ አይመስልም ብለውኛል፡፡ እኔ ግን በመሐሉ «መድኃኔዓለም መጣ» የሚል ድምፅ ሰማሁ እንጂ ራሴን አላውቅም፡፡ መጨረሻ ላይ ራሴን ሳውቅ ከእኔ የወጣውን ጥቁር ወፍ ይዘው አሳዩኝ፡፡ አላመንኩም፡፡ ሰው እልል እያለ 'አይዞሽ ተነሽ እመቤታችን ከነልጇ የሠራችልሽ ተአምር በጣም ድንቅ ነው፡፡ ተነሥተሽ ድንቅ ተአምሯን ትመሰክሪያለሽ' አሉ፡፡ ልብሴን ለብሼ ስወጣ ብዙ ምእመናን ቆሞ በሞባይልና በቪዲዮ የወጣውን ጥቁር ወፍ ይቀርጻል፡፡ ከሆዴ የወጣው ትልቅ አፍ ያለው ወፍ ደም ጎርሶ በሕይወት ለተወሰነ ደቂቃ ልቡ ይመታል፡፡ እኔ ራሴን አላመንኩም፤ ደስታ አይሉት ሐዘን ተደበላለቀብኝ፣ ሰውነቴ ከላይ እስከታች ይርዳል» ስትል የእግዚአብሔርን ድንቅ ተአምር መስክራለች፡፡

ሰኔ 10 ቀን ከ681 አጋንንት ውስጥ ሰማንያው ጥቁር ወፍ ሆኖ ሲወጣ ሰኔ 12 ቀን ሌሎች ቀሪዎቹ በጉንዳን መልክ ወጥተናል ብለው በመለፍለፍ ለቀቁ፡፡ በወቅቱም የጠበሉ ቦታ በጉንዳን ተወሮ እንደነበር መንበረ ማርያም ገልጻለች፡፡ ያ በሕልሟ ሲያባርራት ያየችው ጥቁር ሰው እርኩስ መንፈስ እንደሆነና ሕፃኑ ደግሞ መድኃኔዓለም ሆኖ እንዳዳናት አምና ተርጉማዋለች፡፡

መንበረ ማርያም ስለተደረገላት ድንቅ ተአምር ሰኔ 10 እና 21 ቀን 2001 ዓ.ም የእመቤታችን ክብረ በዓል ዕለት በቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ቤተክርስቲያን በመድረክ ላይ ወጥታ ለሕዝበ ክርስቲያኑ መስክራለች፡፡

በመጨረሻ ያነሣንላት ጥያቄ «የተደረገልሽን ተአምር እንዴት ትገልጭዋለሽ?» ነበር፡፡ እሷም «እግዚአብሔር ያደረገልኝን ድንቅ ተአምር በቃላት ልገልጸው አልችልም፡፡ ኃያሉ እግዚአብሔር እኔን አድኖኛል ምስጋና ይድረሰው፡፡ እኔ ግን የማተኩረው ስለተደረገልኝ ተአምር መመስከር ብቻ ሳይሆን ስለማስተላለፈው ነገር ነው፡፡ ይኽም እግዚአብሔር እንዲህ ማዳን እየቻለ ሰይጣን ሊሰለጥንብን አይገባም፡፡ በሥራ፣ በትምህርት ቤትና በዕለት ተዕለት ሥራችን ላይ ውጤታማ እንዳንሆን መሰናከል እየሆነ ነው፡፡ ሕይወታችንን እያበላሸ መሆኑን አልተረዳንም፡፡ ስለዚህ ስመ ክርስትና ብቻ ይዘን መቀመጥ ሳይሆን በጾም በጸሎት እግዚአብሔርን ማገልገል ይኖርብናል፡፡ ከንስሓ አባት ጀምሮ የሃይማኖት አባቶችም ማስተማር አለባቸው፡፡ እያንዳንዱ ሰው ራሱን ይመርምር፤ ክፉ መንፈስን መዋጋት አለበት» ብላለች፡፡

«ማየት ማመን ነው» እንደተባለው በወቅቱ በደብረ ወልደ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስና በመካነ ጎለጎታ ቅድስት ማርያም የጠበል ቦታ ሲያጠምቋት የነበሩትና ድርጊቱን የተመለከቱት ሊቀ ትጉኃን ስሙር አሐዱ ስለሁኔታው እንዲነግሩን ጠይቀናቸው እሳቸውም ታሪኩን እንዲህ አወጉን፡፡ «ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለም፤ ነገሩ ተአምር ነው፡፡ ከዚህ በፊት በእርኩስ መንፈስ የታሰሩ፣ የተተበተቡ ሰዎችን በእግዚአብሔር ኃያልነትና መስቀል በመታገዝ በላያቸው ያለውን አጋንንት አስለቅቄያለሁ፡፡ ይህ ግን ልዩና በሕይወቴም ገጥሞኝ የማያውቅ ነው፡፡ በዕለቱ እኅታችን መንበረ ማርያም ወደምትጠመቅበት ክፍል ስትገባ ጀምሮ በጣም ትጮሃለች፡፡ በመስቀል እያጠመቅሁ ምንድን ነህ? ስለው አጋንንት ነን አሉ፡፡ ቀጥሎ ስንትናችሁ? አልኩት 600 አጋንንት ነን አሉና እውነቱን አውጣ ብዬ አጥብቄ ስይዘው 680 ብሎ ለፈለፈ፡፡ መጨረሻ ላይ 681ኛ ተልከስካሽ የዛር መንፈስ እንዳለ ገልጾ ከሰኔ 10 ቀን 2001 ዓ.ም ጀምሮ በተከታታይ በአራት ቀናት ውስጥ ተከፋፍሎ ወጣ» ብለዋል፡፡

እንደ እሳቸው አባባል ሰኔ 10 ቀን 2001 ዓ.ም 80ው ጥቁር ወፍ ሆኖ ሲወጣ፤ በነጋታው «593ቱ ጉን ዳን ሆኜ እወጣለሁ» ብሎ ጮኸ፤ ሲለቅ ወዲያውኑ ከየት መጣ ሳይባል አካባቢውን ጉንዳን ወረረው፡፡ በሦስተኛው ቀን ደግሞ ሰባት ሲወጣ ከሰባቱ አንዷ ብቻ ሴት ሆና ተገኘች፡፡ እሷም «ከውጭ ሀገር ነው የመጣነው፤ ሥራችን ተመሳሳይ ፆታዎችን ማጋባት ሲሆን በውጭው ዓለም አጥለቅልቀነው ወደ አፍሪካና ኢትዮጵያ በብዛት እየገባን ነው» ብላ ተናግራለች፡፡

«በመጀመሪያ ዋናውና አለቃው ' አጋንንት ጥቁር ወፍ ሆኖ ሲወጣ 600ው ሠራዊት ነኝ ብሎ ወጣ፡፡ አለ ቃውን አጋንንት» እንዴት ብለህ ነው የምትወጣው» ስለው እንደ አንበሳ አጓርቼ እወጣለሁ አለ፡፡ ልጅቷ እንደ አንበሳ እያጓራች ሳለ ጥቁር ወፍ በደም ተለውሶ ከሆዷ ውስጥ በአፏ ወጣ፤ ሲወጣም ልክ እንደ አየር ሞገድ ተወርውሮ ገንዳ ነገር ላይ አረፈ፡፡ ይህ እርኩስ መንፈስ ወፍ ሆኖ ሲወጣም ግፊት ስለነበረው እኔን ሁሉ ገፍትሮኛል፡፡ የወጣው ጥቁር ወፍ ከነሕይወቱ በመሆኑ ለተወሰነ ደቂቃ የማስካካት ድምፅ አሰምቷል፡፡ ለግማሽ ሰዓት ያህልም በሕይወት ቆይቶ ምእመናን ዐይተውታል፡፡ ድርጊቱ የሁሉንም መንገደኛ ቀልብ የሳበ ስለነበር መናፍቆች ሳይቀሩ ተመልክተው በእመቤታችን ድንቅ ተአምር ተገርመ ዋል፡፡ በተለይ አንድ ከነቀምት የመጣ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ በተአምሩ ተደንቆ ሲያለቅስ ዐይቻለሁ» በማለት ሊቀ ትጉኃን ስሙር አስረድተዋል፡፡

«አጋንንቱ መንበረ ማርያምን እንዴት እንደያዛት ስጠይቀው በተለያየ ምክንያት በይበልጥ በዛር ውላጅ ሲወርድ ሲዋረድ በዘር ሐረግ የመጣ እንደሆነ ለፍልፏል፡፡ ለ20 ዓመታት ያህል በሆዷና በማሕፀኗ ላይ ከፍተኛ ጫና በማድረስ ያሰቃያት እንደነበር ዘርዝሯል፡፡ በወር አበባዋ ጊዜ ምጥ እያበዛ ያሰቃያት እንደነበር ተናግሯል፡፡ እመቤቴ፣ እመቤቴ እያለች የእመቤታችን ማርያምን ስም እየጠራች አስቸገረችኝ እንጂ ሆዷን ኦፕራሲዮን አስደርጌ በሰበብ ልገድላት ነበር» ሲልም ተናግሯል ይላሉ፡፡

«ድርጊቱ በጣም የሚከብድ እና በእኔ ላይ የደረሰ ያህል ተሰማኝ፤ እኔም በሁኔታው በጣም ያዘንኩበትና ያለቀስኩበት ነው፡፡ ምክንያቱም ይህ ድርጊት በእኔ ላይ ተከስቶ ቢሆን ኖሮ ምን ልሆን እንደምችል ትንሽ ቆም ብዬ ማሰብ ጀመርኩ፡፡ እሷ ግን እጅግ በጣም ጠንካራ፣ በእምነቷ ጽኑ ነች፡፡ በእምነቷ ጽናት እግዚአብሔር ድንቅ ሥራውን ሠራላት፡፡ አሁን ሙሉ ለሙሉ ጤነኛ ነች ብለዋል፡፡ እርኩስ መንፈሱ አባቷን ሳይቀር ሌሎች ሰዎችንም ይዣለሁ ብሎ በመለፍለፍ ልጅቷ ቤት ድረስ በመሔድ መጥተው እንዲጠመቁ ተናግሬያለሁ» በማለት ሊቀ ትጉኃን ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም «የማስተላልፈው መልእክት አለ፡፡ እግዚአብሔር ብዙ ሥራ ይሠራል፤ እግዚአብሔር እኛ እንድንድን የማያደርግልን ነገር የለም፡፡ ከዚች እኅት ትልቅ ትምህርት አግኝተንበታል፤ የክርስቶስ ስልጣን ይህን ዐይነት የሚሠራ ከሆነ እኛ የት ነን? ብለን ማሰብ አለብን፡፡ ትንሽም ብትሆን እምነት ያስፈልጋል፡፡ ስለዚህ ወደ እግዚአብሔር በመቅረብ ጠበሉን፣ እምነቱን ልንጠጣ ይገባል፤ ሥጋና ደሙን ልንቀበል ያስፈልጋል፡፡ ይህ ከሆነ መዳን እንዳለ ማመን ይገባል» ሲሉ ሊቀ ትጉኃን ስሙር አሐዱ አስረድተዋል፡፡

በርግጥም መንበረ ማርያምና አጥማቂዋ ሊቀ ትጉኃን እንደገለጡት በየጠበሉ ቦታ ሲታይ በርኩስ መንፈስ በመተት፣ በዛር፣ በአጋንንትና በመሳሰሉት የተያዙ ሰዎች በእግዚአብሔር ኃይል ሲፈወሱ ማየት ጉድ ያሰኛል፡፡ ሰይጣን የምንፈራው ሳይሆን ታግለን የምናሸንፈው መሆኑን ማንም ሰው ሊያውቀውና ሊረዳው ይገባል፡፡ አውቆም በጾም በጸሎት እርምጃ ሊወሰድ ይገባል፡፡ የበለጠ ደግሞ መምህራን ሓላፊነት ወስደው ማስተማር ይኖርባቸዋል፡፡
ምንጭ፦ ማኀበረ ቅዱሳን ስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ
ተአምሩ የወጣበት የድረ ገጽ አድራሻ፦

49 comments:

Anonymous said...

ይሄን ታምረ ማርያም ላይ ተጽፎ ቢሆን ኑሮ እናምን ነበር?ለሚቀጥለው ትውልድ ሊጻፍ አይገባም ትላላችሁ?በታምረ ማርያም ውስጥ መጨመር የለበትም?የሚቀጥለው ትውልድስ ይሄን ምን የለው ይሆን?ሳያዩ የሚያምኑ ብጹዐን ናቸው ያለው ይሄን ያጠቃልላል?እግዚአብሄር የሚሳነው የለም የሚነው እንዲህ አይነቱን ነው?

tesfa said...

እሕቴ እንኳ እግዚአብሔር ይቅር አለሽ እግዚአብሔር መልካም ነው ምህረቱን አድርጎልሻል ክብር ለስሙ ይሁን ምስጋና አምልኮና ስግደት ይብዛለት አሜን!!!

zeyigerm said...

በልዎ ለእግዚአብሔር ግሩም ገብርከ። እግዚአብሔር ድንቅ አምላክ ነው። ልጆቹ ተስፋ እንዳንቆርጥበት በየጊዜው ድንቅ ድንቅ ታምራትን በሀገራችን እያደረገ እያሳየን ነው። የኢትዮጵያ አምላክ መቸም ቢሆን ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን አይተዋቸውም።

አንተ ቸር አምላክ ለዚህ ውለታህ ምን ይከፈልሃል? ጌታ ሆይ እባክህ አስተዋይ ልቡና ስጠን።

መንበረ ማርያም ምን አይነት እድለኛ ሰው ነሽ?!.

እግዚአብሔር ሆይ ዐይን እያለቸው ለማያዩ፣ ጀሮ እያላቸው አንሰማም ላሉ፣ በቅዱሳን ላይ ለሚሳለቁ ፣ እውነትን ላለማየትና ላለመስማት ልቦናቸውን ለዘጉ እባክህ ልቡና ስጣቸው?

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!.

Anonymous said...

Ewnet!!!
I believe some people are lost their mind. when they got a chance they couldnt speeak up any better things like the first commentator with the name anonymous. in this world there is a lot of crazy people and a lot of people going to be crazy . it is wonderful story for those truely beleive in God but it might a kind of simple story for those believe in the left side/ diablos (menafikan). Teamire marian min ametaw ahun. alyam nufake yetezerabet libachew yafelekew hasb new? people might play around vergin merry, but every body will get their own lesson for what they/we said in front of God one day. Whatever menafikan said merry is the mother of Jesus christ. we beleive in teamire Mariam until we die. PEOPLE MAY THINK WE ARE BELIEVING FOR NOTHING BUT THEY DON'T UNDERSTAND (menafikan)WHEN THEY BELIEVE IN teamire PASTER (ROASTER). SO DON'T EVER PLAY AROUND TEAMIRE MARIAM.

Anonymous said...

ለአራተኛ ጸሀፊ
የመጀመርያዊ ጸሀፊ ካንተ ጋር ይስማማል፤እኔ እንዳነበብኩት የገባኝ በታምረ ማርያም የተጻፈውም ታምራት ሁሉ እነደዚህ ነው፤ ስለዚህ እግዚአብሄር በቅዱሳኑ አድሮ ብዙ ያደርጋልና የታምራት መጻህፍትን እመኑ ነው የሚለው፤ለማመን ግዴታ ማየት ወይንም በዘመኑ መኖር የለብንም የሚል ይዘት ያለው አስተያየት ይመስለኛል፤እስቲ እንደገና አንብበው።

tesfa said...

መከራ ክፍል 2 ካለፈው የቀጠለ

3ኛ መከራ ይሠራናል

አንድ ሰው ማን ፈጠረህ ቢሉት "እግዚአብሔር " ካለ በኋላ
"ነገር ግን ገና አላለቅሁኝም"አለ ይባላል።
እኛስ እግዚአብሔር እንዲሠራን ፈቃደኞች ነንን? አንድ ቋጥኝ በቋጥኝነቱ ጥቅም አይሠጥም ደግሞም ውበት የለውም ።

ቋጥኝ ድንጋይ ስንመለከት ስሜት አልባ ነው የምንሆነው።ለምንድን ነው? ስንል በቋጥኝነቱ ምንም ውበት ስለሌለው ነው።ቋጥኙ ለጥቅም እንዲውል ከተፈለገ መፈንቀል አለበት።ቋጥኝ የሚፈነቀለው በከባድ መሳሪያ ወይም በደማሚት ነው ።የመፈንቀል ሂደቱ አስቸጋሪና ፈታኝ ነው።ከዚያም በካባድ መሳሪያ ይከሰከሳል ።በዚህ ጊዜ ትልቅነት ቀርቶ ትንሽነት ይመጣል፡ከዚያም ለሚፈለገው አገልግሎት ይቆራረጣል በማበጠሪያም እየተበጠረ ይንገዋለላል። ውጤቱም ዛሬ የምናያቸውን ውብ ህንጻዎችና ምቹ መንገዶች መፍጠር ነው ።ቋጥኙ ለጥቅም እንዲውል ያለፈባቸው መንገዶች ትልቅነትን አስቀርተው ትንሽነትን አምጥተዋል።

በትልቅነት ትልቅ ሥራ አይሠራምና ።አሁንም ቋጥኙ ውብት ያለውን ሥራ ለመሥራት የሚያሳምሙ ሂደቶችን አልፏል።መፈንቀል፤መከስከስ፤መቆራረጥ፤መቀረጽ፤መበጠር፤እነዚህ ሁሉ የሚያሙ ሂደቶች ናቸው።ውጤታቸው ግን ጥቅምና ውበት ነው።

ምናልባት ለራሳችን በሰጠነው ትልቅ ግምት ተኮፍሰን ተቀምጠን ይሆናል፤የፈለግነውን እየተናገርን፤በመሰለንም እየፈረድን እንኖር ይሆናል፤ትልቅ ሆነንም ለራሳችንና ለሰዎች ከብደን ይሆናል።
ግን ጠቃሚዎች አይደለንም ።እግዚአብሔር እንዲህ ሆነን እንድንኖር አይፈቅድም ።ከተደላደልንበት ሥፍራ ያነሣናል፤ሰዎች በስንፍና የወደቁበት ከመሰለን ትንሽ ሥፍራ ይጠለናል።ውጤቱም
በተሰበረ መንፈስ ውስጥ የሚገኘውን ፍቅርና ትሕትና ያላብሰናል።
ደርባባ ጳጳስ ከመሰለው ኑሯችን ቀለል ያለና ሁሉም ሰው ሳይሳቀቅ የሚቀርበው ተወዳጅ ሰው ያደርገናል።አትንኩን ባይነት ይቀርና ከመብት ፍቅር ይበልጥብናል ።ሰዎች እንደኔ ይሁኑ የሚለው ሕጋዊነት ይቀርና ለሰዎች የጸጋውን ኃይል ብቻ እንለምናለን።

እኛን ለማዘዝ ለእግዚአብሔር የምንቀለው ሰዎች እንሆናለን።ቃሉ እንዲህ ይላል"ወደዚህ ወደ ትሑት መንፈሱም ወደተሰበረ በቃሌም ወደሚንቀተቀጥ ሰው እመለከታለሁ"ኢሳ66፡2

እግዚአብሔር በመከራ ውስጥ ይሠራናል።አንድ ፎቶ አንሺ ፎቶውን
ካነሳ በኋላ መልኩ እንዲወጣ ፊልሙን በጨለማ ውስጥ ያሳልፈዋል።
በጨለማ ውስጥ የሚያሳልፈው መልኩ እንዲወጣ ነው።እግዚአብሔር እውነተኛ መልካችን እንዲወጣ በሕይወት ውጣ ውረድ ውስጥ ያሳልፈናል።


4ኛ ክንዱን ይሳየናል

የሰው ልጅ ለመልካም ነገር ራሱ ያቅድ ይሆናል።ክፉ ንነገር ግን በሰው ልጅ ያቅድበታል።የነበረውንም ሀብት ፤የነበረውንም ጤና
አጥቶ ክዚህ ዓለም በፊት እንዳልነበረው እንደገና ይመኛል።ቢሆንም በዚህ ሁሉ ውስጥ እግዚአብሔር ክንዱን ያሳየናል።እምነት የረጋ ነገር ሳይሆን የሚያድግ ነገር ነው።ዕለት ዕለትም ማደግ አለበት።
እምነታችን ከሚያድግበት ዋና ዋና ነገሮች አንዱ የግዚአብሔርን ክንድ ማየት ነው።ስለ እግዚአብሔር ያለን እውቀት በጨመረ ቁጥር በርሱ ላይ ያለን እምነት ያድጋል።ከዚህ በተጨማሪ ግን በጎደለንና አቅም ባጣንበት ጉዳይ ላይ የእግዚአብሔርን ክንድ ስናይ እምነታችን ያድጋል።

የእግዚአብሔርን ክንድ የምናየው በመከራ ውስጥ ስናልፍ ነው።በመከራ ውስጥ የግዚአብሔርን ክንድ ካየን በምንም የማንነቃነቅ ጽኑ ሰዎች እንሆናለን።በሽታችን የእግዚአብሔርን ፈዋሽነት፤ጉስቁልናችንም የእግዚአብሔርን ረዳትነት የምናይበት በመሆኑ ደስ ሊለን ይገባል።
እግዚአብሔር በማይታለፍበት ቦታ መንገድ ሲሰጠን፤አላሳልፍ ያለንን ጋሬጣ ሲያነሳልን፤የጠላትን ደጅ ሲያወርሰን፤የጠሉንን ወዳጅ ሲያደርግልን፤ማንም በማይገኝበት ቦታ ሲገኝልን ፤ይበልጥ እንወደዋለን ።የእስራኤላውያን አስቸገሪ የበርሃ ጉዞ አንዱ አላማው የእግዚአብሔርን ክንድ ለማሳየት ነው።በእርግጥም በታመምን ጊዜ ሲያድነን ፤እግዚአብሔር ፈዋሽ ነው የሚለው ቃል ይገባናል።

መጽሐፉ እንዲህ ይላል"አቤቱ ምሕረትህ ረዳኝ ፤አቤቱ፤ለልቤ እንደ መከረዋ ብዛት ፤ማጽናናትህ ነፍሴን ደስ አሰኛት"መዝ93{94}19
ይቀጥላል...

Orthodox unit said...

O' God you are great! How could this happened? Does it have scientific reason for a bird to grow in human body?

That is why we call it Miracle. Beyond our thought, beyond our knowledge. Yekidusan Amlak Egziabher Ayleyen

Unknown said...

2 በኢየሩሳሌምም በበጎች በር አጠገብ በዕብራይስጥ ቤተ ሳይዳ የምትባል አንዲት መጠመቂያ ነበረች፤ አምስትም መመላለሻ ነበረባት።

3 በእነዚህ ውስጥ የውኃውን መንቀሳቀስ እየጠበቁ በሽተኞችና ዕውሮች አንካሶችም ሰውነታቸውም የሰለለ ብዙ ሕዝብ ይተኙ ነበር።

4 አንዳንድ ጊዜ የጌታ መልአክ ወደ መጠመቂያይቱ ወርዶ ውኃውን ያናውጥ ነበርና፤ እንግዲህ ከውኃው መናወጥ በኋላ በመጀመሪያ የገባ ከማናቸው ካለበት ደዌ ጤናማ ይሆን ነበር።
John 5

God Bless Faithful and Give faith to Teteratariwoch(Menafic)
God is always with us even though we want to depart from HIM. Glory to God

Anonymous said...

congratulations sister for being delivered .
with pleasre

John Ze Baptist said...

The first anonymous, I agree with you. There are lots of Miracles that are being done all over the country these days. But we are not recording them and adding them to in our Miracle books. We have to begin wring these things in modern way. Check miracles at Tsadikanie Mariam, Shenkora Yohannes, Bole Gorgorios , Shinkuru Michael, KidaneMihret and all over the country.

God is showing his sign even for people who don't believe.

God Bless Tewahedo and Ethiopia!!!

40minch said...

የእግዚአብሔር ተአምር እና ምህረቱ መቼም ተነግሮና ተጽፎ አያልቅም ። እግዚአብሔርን አመስግኑት ምህረቱ ለዘላለም ነውና። በቀራንዮ መስቀል ላይ ሆኖ ሳለ እናትና አማላጅ ደጋፊ ሆና ለተሰጠችን ለቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ምስጋና ይድረሳት ። መቼም የጻድቁ ቅዱስ ዮሃንስ ፀበል የማይሰራው ስራ የለም ።

እግዚአብሔር ለእናቱ ለቅዱሳኑና ለሰማእታቱ የሰጠው ቃልኪዳን ለዘላለም ነውና ኢአማንያንም ሆኑ መናፍቃን ፤ ይህን ሁሉ ድንቅ የእግዚአብሔር ተአምር አይተው የደነደነ ልባቸውን ከፍተው ወደ ቀጥተኛዋ እምነት መጥተው አብረን የእግዚአብሔርን እንድናመሰግን የዘወትር ጸሎታችን ሊሆን ይገባል።

እንግዲህ ማህበረ ቅዱሳን ማለት እንደዚህ አይነት የቤተክርስቲያን ድምጽ እንጂ ሌላ ምንም እንዳይደለ በወሬ ሳይሆን በተግባር የምናይ ነን። ቃለ ህይወት ያሰማልን ፤ ለማህበረ ቅዱሳን መጽሄት አዘጋጆች።

Anonymous said...

ወመጽሓፈ ሥርዓቶሙሰ ፡ ተተርጎመት እምነገረ አረቢ ፡ ለግዕዝ ፡ብሔረ ኢትዮጵያ ፡በመዋዕለ ፡ ጳጳሳቲነ አባ ሚካኤል ፡ ወአባ ገብር ኤል፡ ወኤጲስ ቆጶስነ ፡አባ ዮሓንስ ፡እምአመ ወፅኡ ውስተ ብሔረ ኢትዮጵያ በ፫ቱ ዓመት። አባ ሚካኤልና አባ ገብርኤል ፡በሚባሉ ጳጳሳት ዘመን ፡ አባ ዮሓንስም፡ ኤጲስ ቆጶስነት ፡በተሾመ ወራት ከግብፅ ወደ ኢትዮጵያ በወጡ ፡በሦስት ዓመት ፡ የሥርዓታቸውም መጽሓፍ ፡ ከአረብ ቋንቋ ለኢትዮጵያ ሰዎች ፡በግዕዝ ቋንቋ ተተረጎመች ።« መቅድመ ተአምረ ማርያም» ከዚህ ቃል እንደምንረዳው እሑድ እሑድ የሚነበብልን ተአምረ ማርያም ግብፃውያን የጻፉት ወይም በግብፅ ሃገር የተፈጸመ ተአምር እንደሆነ እንረዳለን ፡ ለመሆኑ እናታችን ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም በአሥራት ሃገሯ ኢትዮጵያ ተአምር አትሰራም ያለ ማነው ?ሌሎቹ ቅዱሳን በተሰጣቸው ቃል ኪዳን ተአምራት አይፈጽሙም ያለ ማነው? ስለዚህ እኛ ኢትዮጵያውያን ፡ በስንክሳር ውስጥ የተጻፈውን ያየን እንደሆነ፡ ሮማውያን ፡ ግብፃውያን፡ የሌሎቹንም ሃገሮች ጻድቃን ሰማዕታት ነው፡ በብዛት የሚያነሳው ፡ ለምን ሁልጊዜ አባቶቻችን የሌላውን ይጽፋሉ ፡ይህን ስል ገድላቸው ትሩፋታቸው ለምን ተጻፈ ለማለት አይደለም ፡ « አባቱን አያውቅ አያቱን ናፈቅ» የሚል የአባቶቻችንን አነጋገር ያስታውሰናል፡
ስለዚህ ማለት የፈለኩት በቅዱስ ዮሓንስ ጠበል ወፍ ወጣ ሲባል የኢትዮጵያ ሊቃውንት፡ በግዕዝ ቋንቋ ጽፈው ደጉሰው ፡በማስቀመጥ ለትውልድ እንዲተላለፍ፡ ማድረግ አለባቸው ። ይህን ተአምር ያሰሩ አጋዕዝተ ዓለም ሥላሴ ክብር ምሥጋና ይድረሳቸው ።

Anonymous said...

Many of the comments are realted to the subject are not compatable.How an orthodox Christan always write about Menafikan? -let them go thier way and we are expected to keep and grow ours.

teach us Tolerance,passion and truthfullness compared to the Holy bible and the chronicles.Do not teach us compared to others view.Not only Menafikan but also we have those Muslims,Jew etc

Don't compare just tell me the truth and preach the the way I live not the others.

I don't care about others I want be saved from the way I live in Thwahedo.
Here for example it is about the girl who has got the chance to be relifed from her burden.Nothing else don't mention about Menafikan as they are not involved in any of the truth we read.

Fasil From Jerusalem prophet road

Anonymous said...

እንዴ ታምረ ማርያም አንበህ አታውቅም እንዴ?በኢትዮጵያም የተፈጸሙ ተጽፈዋል፣መነሻ የሆነን ግን የግብጻውያን ጳጳሳት አባቶች በጀመሩት ላይ ነው፥ዛሬ እንዲህ እንዳልክ ወንድም ነገ ደግሞ አንዳንዶች እንደተሰነካከሉ ፣መጽሃፍ ቅዱስ እኮ የእስራኤል ታሪክ ነው ለምን የራሳችን ኢትዮጵያዊ የሆነ የኛን ታሪክ የያዘ መጽሓፍ አይኖረንም ብለህ ትክዳለህ፣በጣም ትልቅ ጥርጥር ውስጥ ገብተህ እየዳከርክ ነው፣ወይም አወቅሽ አወቅሽ ሲሏት የቄስ ሚስት መጽሓፍ አጠበች እንደተባለው፣አንተም አወኩ አወኩ እያልክ በክህደት እየሰጠምክ ነው፣ተጠራጣሪ አትሁን፥

Anonymous said...

We couldn't help our EOC and we begin to fantasize with TEAMIREMARIAM.I Remember Abba Amha climbing St. Marry church in 1992 to see the fake revelation of St Marry. For some of you, your God is happy and delighted to see cutting off and mutilating some bodies nose and tongues because he refused to bow to Meskel.Could you please stop using St. Marry's name for the sake of advertising your emotions. Leave St. Marry alone.We all agree that the saints have done a lot of miracles. But our gedles and dirsanats are way out of the mainstream teachings of EOC.

Anonymous said...

The above anonymous,did you read the Bible says that"the Prophet Elias slaughtered 850 idols worshers who didn't obey the teaching of Elias"?Ok,look,the Deqiqe Estifa opposed the teaching of the Bishops who testify the intercession of Saint Mary;They didn't listen;the King together with the Bishops advised once,twice but they started to spoil others true believers by their tongue;At the end, to save others from their heretic,the peoples together with the king blamed them and the heretics were slaughtered;Don't be foolish;Peoples were decision makers.you are escaped now.If you were at that time when you spread this kind of heresy like protestants and tehadiso,you have would have been slaughtered.Please use you time for repentance;If you continue in this kind of heresy,the angles can slaughter you(yiqezfuhan).You will see it

Anonymous said...

Tesfa and Others,

I am deeply sorry for your unrepentant and adamant soul. God is always ready to save you if you are ready to accept the Truth. That Truth is Him and only Him. Christ is our God, Creator, and Savoir. He does not intercede. He did it once on the cross. Now, He is in His Power and Glory. St. Mary is the Chosen Mother of Christ, Our God. Generations thanks Her and gets Her blessing. Luke 1: 26-55; Psalm 44). Through St. John, the Beloved, She is given to be the mother of those Christians who dare to travel until the Cross. We believe that Her intercession is perfect. Who are you to counter God’s Will? He is the One who chooses, not you. Let, alone St. Mary, His Mother, from Her He took the flesh and with her he spent 30 long and lovely years before he began preaching, he promise to us to share the benefits and graces of those Prophets and Saints if you give water to those who are thirsty in their names. (Matthew 10)
Tesfa, it is obvious to everybody that the root cause of you problem has nothing to do with believing the intercession of Saints and Prophets. It is in you belief of the Nature of Christ. You don’t believe Him as God, Creator, and equal in Essence with His Father and The Holy Spirit. (John 14) Do you believe this? Tell us in clear words. Don’t try to dodge questions and confuse people, as menafikans usually do. If you say Christ is amalage (Blessed be His Name), then there is no place for Saints and Prophets.
This is that differentiates Protestants form Orthodox and Catholics. Ancient, Aplostelic Churches believe that Christ is God and equal in Essence with His Father and The Holy Spirit. (There are other differences in the latter, but not important for this discussion) So, what type of spirit is that who make you believe Christ is Amalage.
Please pray to God. He will reveal the Truth to you.

Anonymous said...

እኔ ተአምር ተሰራ ብሎ የሚገረም ሰው ይደንቀኛል።መደነቅ ያለብን እግዚአብሄር በሽተኛ ማዳን ባይችል ነው፤እንኳን የማርያም ጸበል የሀኪም መድሀኒት በሽተኛ ያድን የለም ወይ?
ክርስቶስ በስጋው ወራት በተመላለስ ጊዜ ብዙ ድንቅ ታምራትን ሲያደርግ ግማሹ ህዝብ ይሄን ያደረገው ራሱ እግዚአብሄር ነው ሲሉ ጥቂት የማይባሉትና እውቀት አለን የሚሉት ግን በሰይጣን ስም ይሄን አደረገ ብለው አምላክነቱን ተጠራጠሩ።
አሁንም እያየነው ያለነው ይኔን ነው።” ካላየሁ አላምንም” የሚል ጠማማ ትውልድ፤በሽተኛዋ ድኛለሁ እያለች ….ሌላ ሌላ ማለት የጤነኛ ሰው አስተሳሰብ አይደለም፡ይልቅ እንደ መዝሙረኛው ዳዊት “እግዚአብሄርን ስራህ ድንቅ ነው በሉት” ነው ማለት ያለብን።ይሄን ተአምር በእንግሊዝኛ ና በአረበኛ ተርጉሞ ለሌላው አለም የሚደርስበትን ዘዴ አፈላልጉና በምስል አስደግፋችሁ ዌብ ሰይት ላይ ልቀቁት፤ አምላካችን በቅዱሳኑ ላይ አድሮ የሰራውን ያውቅ ዘንድ ለአለም ስበኩ።

shegaw said...

ምን ሀኪም ቤት ብቻ ሰው ቃሊቻ ቤት ሄዶ ይፈወስ የለም ወይ እንዴት ነው ከፍ ዝቅ የሚያደርጋችሁ? እምነት በተአምር ላይ የተመሰረተ አይደለም። ማህበረ ሰይጣን እንደሆነ ያልተማረውን ማኅበረሰብ ይባስ ማደናገር እንጀራው ነው?

shegaw said...

ምን ሀኪም ቤት ብቻ ሰው ቃሊቻ ቤት ሄዶ ይፈወስ የለም ወይ እንዴት ነው ከፍ ዝቅ የሚያደርጋችሁ? እምነት በተአምር ላይ የተመሰረተ አይደለም። ማህበረ ሰይጣን እንደሆነ ያልተማረውን ማኅበረሰብ ይባስ ማደናገር እንጀራው ነው::

Anonymous said...

Different people responded to my comments. My respose goes like this.
1. For the one who is taking delight with what Zerayaiqob did I say this. I do't think you have read or understood what Jesus,yours and my savior, said when St. Peter took and cut off that boy's ear so that he could defend Jesus. Put off your sword those who respond by sword will perish by sword. Jesus sent His disciples to the world not to kill those who oppose them, but die for the gosple. I think you have the illusion of mixing Gihad with martyrodm. Read your gosple attentively. Don't become eratic and radical. You don't find a single saint who mass murded people excep your Zarayaikob. I am very sad you and the likes playing your cheap AMALAG game in the name of our virgin and Holy mother of God. She is a very passionate and God fearing lady. She would prefer die herself instead of the king mass murder people for any reason.I are you going to kill me those who don't accept you mass murder theory in the future if you become a king? I hope you don't. Think of things in New Testament context.
Thanks

Anonymous said...

MK, you have dropped the real ball,Your Fake Holy Synod, and now shifting the gear to making business in the name of Tsebel,Teamir....

Anonymous said...

Tesfa and others,

Don't try to dodge (madbesbes) as usual. You have to answer the question raised in clear words to prove that you are member of EOTC.

'Do you believe Christ is God and The Creator, and equal in Essence with His Father and The Holy Spirit?

We can discuss the rest once we know the answer to the above question. I know you will not dare to answer it because you know that is the basis for our difference.

Anonymous said...

Shegaw,

It is in your religion, Protestantism, that miracle is at the centre of preaching. For us, miracle is a daily event. Except to witness what God has done to us through His chosen Saints and Prophets, we do not make it at the centre of preaching His Words. But, you have to know that 'God listens to the prayer of the righteous'. (John 4)
Once you bring the magician issue, let me give you a bit of comparison (similarity) with Protestantism
1/ When Protestant claim The Holy Spirit (Blessed be His Name) be on them, they fall down, spread their body all over the ground, and utter words which have no meaning at all. The magician does the same. The difference is you do it in the name of God (Blessed be His Name) while the Magician does it openly.
2/ Protestants insult Saints who are chosen by God Himself, and the Magician does the same.
3/ When you claim that spirit on you, your prophecies are full of worldly issues as if this world is forever. The Magician does the same.
4/ Some Protestants when they found that their religion is false, and want to be converted, they fear they will die, as if Christ (blessed be His Name) is cruel. People who go to magicians say the same.
5/ During a debate, on religion issues, when a protestant is about to lose, his body starts to shake and throw strong words, as if God is to take vengeance on Him and the other side. The same is with a magician. When the Magician believes that somebody is challenging his Spirit, he spread his hand, utter strong words, and promises that the challenger will be punished soon.
One can continue this way and tell you more. But, it is not important.
Believe me, soon, you will see that those who left from their Church will realize your true nature and come back and repent.

Anonymous said...

አይ መፈላሰፍ !ቅዱስ ጴጥሮስ ክርስቶስን ሊይዝ የመጣውን ጀሮውን ሊቆረጥ ስለሞከረ ‘ኢየሱስ በሰይፍ የሚገድሉ በሰይፍ ይጠፋሉ አለ’ ጥሩ ይሄው ጴጥሮስ መንፈስ ቅዱስን ሊያታልሉ የሞከሩትን እንዳእናንተ ያሉትን በዘመነ ክርስትና ሐናንያና ሰጲራን በሞት እንዲቀጡ አደረገ(ሐዋ ስራ 5-1) እርሱንም ነፍሰ ገዳይ ልትሉት ነው?

Anonymous said...

ክብርና፡ምሥጋና፡ለመድኃኔ፡ዓለም፡ክርስቶስ።
ይህ፡ፈውስ፡እግዚአብሔር፡ኢትዮጵያን፡የብዙ፡
ምልክቶች፡መገለጫ፡እንዳደረጋት፡ነው።

ዲያቢሎስ፡በተለያየ፡መልክ፡የሚሞግተንም፡በ
ዚሁ፡ምክንያት፡እንደሆነም፡እናውቃለን።

ፀረ-ተዋህዶዎችን፡እርር፡ድብን፡የሚያደርጋቸ
ው፣እንዲህ፡ያለው፡የእግዚአብሔር፡ምሕረት፡ለ
ሉተርና፡ሰይጣናዊ፡ትምህርቱ፡እጣቸው፡የጥብል
ያኮስ፡መስተንግዶ፡መሆኑ፡ነው።

ከተዋህዶ፡እምነት፡ወደ፡ክህደትና፡ዲያቢሎሳዊ፡
ዘበት/ንትርክ፡ዓለም፡መውደቅ፡ምንኛ፡አሳዛኝ፡
ነው? እግዚአብሔር፡ርትዕት፡ወደሆነችው፡ተዋ
ህዶ፡እምነት፡በምሕረቱ፡እንዲመልሳችሁ፡ንስሐ፡
ግቡ።ፆምና፡ጸሎትም፡በሥርዓት፡ጀምሩ!

በተዋህዶ፡ቅዱሳን፡ላይ፡ማላገጣችሁን፡አቁሙ።
ትታችኋት፡ወደ፡ፈረንጅ፡እምነት፡ከሔዳችሁ፡
በኋላ፣ይህ፡ከተዋህዶ፡ደጅ፡አልጠፋ፡ማለቱ፡ምን፡
ይባላል?!

ለምን፡እዛው፡ፈረንጆች፡አባቶቻችሁ፡ካሉበት፡አ
ትወሰኑም?!እናንተም፡ውስጥ፡የገቡት፡አጋንንት፡
እንዲወጡላችሁ፡ከሆነ፡ንስሐ፡ገብታችሁ፡ተጠመ
ቁ!ዛሬ፡የምታላግጡባት፡ወላዲተ፡አምላክ፡ታም
ን፡ታሳያችኋለች!

ማህበረ፡ቅዱሳን፡በርቱ!የስምዐ፡ጽድቅ፡አዛጋጆች
ና፡ዜና፡አቅራቢዎችም፡በርቱ!የእግዚአብሔርን፡
የምሕረት፡ሥራዎች፡በጥራትና፡በጥንቃቄ፡ከምድ
ረ፡ኢትዮጵያ፡እየተከታተላችሁ፡አሰሙን።

የሚሟገተንም፡ዲያቢሎስ፡ይደንግጥ፤ካለንበት፡ይ
ጥፋ!መዳንን፡የታደሉትም፡ይዳኑ!

የመናፍቃንን፡ዘበትና፡ሙግት፡መድኃኔ፡ዓለም፡
ይፋረድልናል!

የተዋህዶ፡ልጆች፡በያለንበት፡እንበርታ!


እግዚአብሔር፡ተዋህዶ-ኢትዮጵያን፡ይባርክ!
አሜን፣አሜን፣አሜን።

ሳሙኤል፡ዘአሰቦት።

Anonymous said...

አጼ ዘርዓ ያዕቆብ የወሰዱት ርምጃ ትክክል ነው ልክ እንደ ቅዱሱ ነቢይ ኤልያስ፣እንደ ቅዱስ ጴጥሮስ፣ሀሰተኞች 850 የበኣል ክህናት በኤልያስ ታርደዋል፣ሁለት ሀሰተኛ ባልና ሚስት በቅ/ጴጥሮስ እንዲገደሉ የተደረገው፣ቀጣፊዎች ስለነበሩ ነው፥አሁንም መናፍቃን በቅዱሳን ላይ ስለሚዘብቱ ካልተመለሱ በቅዱሳን መላእክት ይታረዳሉ፥ሰይፍ የሚያነሱ በሰይፍ ይጠፋሉ የተባሉ ለሃይማኖት፣ለሃገር ሰይፍ ያነሱትን ለነጻነታቸው የተዋጉትን ሳይሆን በግፍ ሰይፍ አንሰተው ለሚገድሉ ነው፥ነብዩ ኤልያስ ሀሰተኞችን በሰይፍ ቢያሳርድም በሰይፍ አልሞተም እንዲያውም እስካሁን ሞትን ሳይቀምስ ይኖራል፣ክርስቶስም በሓዲስ ኪዳን በደብረ ታቦር ላይ ከሙሴ ጋር ጠርቶ ክብሩን አሳይቶታል፣ታላቅ ሥራ የሰራ ነብይ ነውና፥አጼ ዘርዓ ያዕቆብ በመናፍቅ አንደበት ሊነሱ ሊሰደቡ አይገባም፥ እሳቸው እነዚያን መናፍቃን ባያጠፉአቸው ኖሮ አሁን ኢትዮጵያ እንደ ተስፋ ያሉ መናፍቃን ሀገር ሆና ትቀር ነበር፥አሁን በዓለም የተለየ እውነተኛ ሃይማኖት የያዘች፣ጥንታዊ ቅርስ ያላት ውድ ሀገር አናገኝም ነበር፥ሃይማኖታችንንታሪካችንን፣ቅርሳችንን፣ወዘተ ከሚያጠፉ ተሃድሶዎች ታደጉልን፥መናፍቃን የሚገባቸውና ወቅቱ የሚጠይቀ እንደዚያ ያለ ርምጃ ነበርና ነው ተስፋ፣1ጴጥ2፣14"ስለ ጌታ ብላችሁ ለሰው ሥራዓት ሁሉ ተገዙ፥ለንጉሥም ቢሆን ከሁሉ በላይ ነውና፥...ክፉ የሚያደርጉትን ለመቅጣት ...ከርሱ[ከእግዚአብሔር] ተልከዋልና፥ተገዙ" ቁጥር 18 ላይም ...ለበጎዎችና ገሮች ጌቶቻችሁ ብቻ ሳይሆን ለጠማሞች ደግሞ በፍርሀት ሁሉ ተገዙ"ውንድም ክርስቲያን ከሆን ይህንን ት ዕዝቅዝ አክብር፥ያንተ ወገኖች ለንጉሡ አልገዛም ብለው ተወገሩ፥ንጉሡ የጠየቋቸው ግን ለአምላክ እናት እና በደሙ ለተቀደሰው መስቀሉ እጅ እንዲነሱ ነበር፥እምቢ ብለው ቢቀመጡ እኮ ጥሩ ነበር ሌላውም እንዳይሰግድ የክህደት ትምህርት ሲያስተምሩ ንጉሱ ለህዝቡ ጠባቂና የወላዲተ አምላክ ፍቅር ስላለው፤ርምጃ ወሰደባችው፥

Unknown said...

እንዱህ በንጉሡ ላይ ክፉ የምትጽፍ እጅ እና የምትለፈልፍ ምላስ በ አጼ ዘራ ያዕቆብ ግዜ ብትገኝ ኖሮ እሷን አያርገኝ፥ፈጣሪ በሰጠው ሥልጣን ጥሩ ቅጣት ለነ ተስፋ ይሰጡለን ነበር

Anonymous said...

Thank God your days are over in Ethiopia and EOC. Now we are under grace not "Zeayaikob".I give respect and honour to the mother of God not the way some secterain people want me to do. But as the way bible teaches me. I don't idolize mass murder and mutilation of bodies which happend as a ritual for demonic enternainment. I am sad this is wriiten in my dearest EOC books because of you and the like mercyless guys.If your logic works,why oppose Jimma's mass murder? What is the difference b/n you and the gihadists?Is it because you kill with the tanks which has cross on its top. The gihadists also have the banner of half moon on their weopons. But for us the real EOC members, our weopon is the real cross which doesn'n kill but the cross which Christ died on for my sins and yours. The real cross saves and heals not kill. The real St. Marry is passionate not take delight with the mutilation of people. It will not be long before our EOC apologize for those mistakes as the Catholic church did for Jewish murder.
Thanks.

Anonymous said...

MK began its Hammer publications with the story of "Boreda'. I knew it was bogus and lies. There wasn't any miracle there, there wasn't any Tabot found there. Lastly it was Abune Zekarias who had to get a new Tabot to establish there. Even the 'so called Abba Wolde Gabrael' found to be lier and ended up in jail. We can defend our EOC teachings with out lies and bogus stories. I don't see any difference b/n you guys and protestant cultish preachers. Our EOC deserves better.Lastly you said Tabot refused to walk?????.Stop your business of lies.

Anonymous said...

for us the real EOC members, our weopon is the real cross which doesn'n kill but the cross which Christ died on for my sins and yours. The real cross saves and heals not kill

ከጴጥሮስ በላይ ሪል ክርስቲያን አንተ ማን ነህ?.(Act 5-1)

Anonymous said...

Don't wander around when you are asked a tough question. Don't go to the issue of Tabot and miracle, which the Holy Bible talks about clearly, before answering the question I asked you earlier. I repeat the question below. It is one of the most important questions whose answers prove whether you are a protestant or not.

'Do you believe Christ is God and The Creator, and equal in Essence with His Father and The Holy Spirit?

We can discuss the rest once we know the answer to the above question.

You appear to insult those protestant preachers. What are you first of all?

Anonymous said...

You said “... But for us the real EOC members, our weopon is the real cross which doesn'n kill but the cross which Christ died on for my sins and yours.” Good try to fool the innocents. No Christian is as peaceful in history as Ethiopian Orthodox Tewahido Christians. Poor children in the street prefer to beg rather than snatch as is customary in many protestant Africans. The well-to-dos prefer to donate to the poor rather than have a spending spree, naked, in Las Vegas etc, like the Western Protestants.
In terms of jihadist sentiment, mass murder is the history of Protestants.
In the 15th - the 17th century, Protestantism inundated Western Europe, during this period hundreds of thousands of Catholic Christians were slaughtered mercilessly and with kings backing. Britain was converted into Protestantism after the King officially converted and ordered everyone under his rule should follow suit or persecuted. Do you know how many were killed? Read History. Tens of thousands of Christians slaughtered in Germany and Scandinavian countries with a series of protestant uprisings.
Atse Zere Yakob, was a reasonable and religious king. He didn’t do like you masters did in Europe. He gave them the chance to repent. He even created a forum debate if they have a point to make. Like you today, the Dekike Estifanos, at that time, could not make a point based on the Bible. So, he told them to repent. Some did and few didn’t. Those unwilling tried to spoil the innocent, like you are doing today. A King is a king. He had to take decisions in order to protect the innocent, God fearing and religious public. Do you compare this with what your masters did in Europe?

Anonymous said...

I am not to defend what the European missionaries did to our innocent Africans fathers and mothers. I strongly condemn what they did in the name of gosple. I strongly agree with you as well that EOC did less harm compared to the European missionaries. But that didn't give any legitimacy to kill a single person in the name of faith. Jesus didn't say kill one person to teach gosple to the world. No way sir. I am only pointing to the mistakes ignorant kings did in the name of our beloved EOC name. I don't pretend to salute mutilations and torture what so ever I love my heritage. I am sure in your heart you feel the same eventhough you refuse to admit publicly.I understand why you don't admit. You think you might expose your church .I can share that sentiment to some degree,but not to the degree of correcting "saluting the fake books'.
Thanks

Anonymous said...

Do you think our King killed thousand and thousand of blacks and native west Indians in North America? Let me tell you my brother/sister, your Protestant churchs did it. Don't go back it doesn't help for your salavation. God is the only one pure perfect. I am christian I am against killing so do you want me to insult St. Peter like you.

Anonymous said...

why st peter kills two people in (Acts 5-1) can anyone give me biblical reason?please i want to learn .it looks illogical for me

Anonymous said...

You are a liar. No bigger liar than you. You don't have the moral to insult us. You learn lies from your father. You insult God’s Saints and Angels but you consider yourselves as Saints. That is what your father does when he was Arc Angle.

Here, you try to appear as an EOTC (you intentionally missed T from EOTC) member and defender of it.
No. Don’t be fool. We know you. You are a wolf in sheep skin. If you don't believe that Christ is God, The Creator, and equal in Essence with His Father and The Holy Spirit, and St. Mary is the Mother of Christ, The Creator, no matter how you try, you would not get any loophole to sneak in. You should know that, through the intercessions of St. Mary and the Saints, God wards you and your father off, and protect us from your evil intentions. That is how EOTC survived for 2000 years.

Anonymous said...

" በተዋህዶ፡ቅዱሳን፡ላይ፡ማላገጣችሁን፡አቁሙ።
ትታችኋት፡ወደ፡ፈረንጅ፡እምነት፡ከሔዳችሁ፡
በኋላ፣ይህ፡ከተዋህዶ፡ደጅ፡አልጠፋ፡ማለቱ፡ምን፡
ይባላል?!

ለምን፡እዛው፡ፈረንጆች፡አባቶቻችሁ፡ካሉበት፡አ
ትወሰኑም?!እናንተም፡ውስጥ፡የገቡት፡አጋንንት፡
እንዲወጡላችሁ፡ከሆነ፡ንስሐ፡ገብታችሁ፡ተጠመ
ቁ!ዛሬ፡የምታላግጡባት፡ወላዲተ፡አምላክ፡ታም
ሯን፡ታሳያችኋለች!

የሚሟገተንም፡ዲያቢሎስ፡ይደንግጥ፤ካለንበት፡ይ
ጥፋ!መዳንን፡የታደሉትም፡ይዳኑ!

የመናፍቃንን፡ዘበትና፡ሙግት፡መድኃኔ፡ዓለም፡
ይፋረድልናል!

የተዋህዶ፡ልጆች፡በያለንበት፡እንበርታ!


እግዚአብሔር፡ተዋህዶ-ኢትዮጵያን፡ይባርክ!
አሜን፣አሜን፣አሜን። "

Andom said...

Glory to GOD, thank you Lord! There are zealions of God's miracles aroud, but we are often blind to see them. Bless us!

Anonymous said...

are you people lost your mind??? what a bulshit beleive is this? please open your mind and be rational. a bir came out of her stomach kkkk funy funy how many people you are going to decive for how long? anyway this the so called Orthodx is deying

ETHIODURUS QURAN TRANS. said...

ጥፋተኛ ቤትሰቦቹዋ ናቸው በልጅነቱዋ አፉዋን ክፍት አድርገው ወፍ እንዲገባባት ያደረጉት ቅቅቅቅ

Anonymous said...

አቡ አዩብ እሷ ሆድ ዉስጥ የነበረው ወፍ መሆኑን ካመንክ አንተ ሆድ ስጥ ደግሞ ሰይጣን ከብዙ ሰራዊቱ ጋር እንዳለ እመን እሺ አተጠራጠር፣መኖራቸውን ለማረጋገጥ ከፈለክ ወደ ልጂቱ ወደ ተጠመቀችበት ጠበል ህደህ ተጠመቅ፣ታያቸዋለህ፥አለበለዚያ እንደ ዚህ ያል ክህደት ሲያስለፈልፉህ ኑረው በነፍስህም በሥጋህም ያጠፉህልም፥ይህ እንድሚሆን ርግጠኛ ሁን እሺ ABU Ayub

Melkamu said...

Thank you, Lord! Miracles from God are infinite.

What do we learn from such miracles?

I learn that we Ethiopians, specially our, naturally weak, female Ethiopians are getting spiritually even weaker. This ain't a good sign! I am saddened by the fact, that our sister was having those horrendous pains for a very long time, yet, either she or familiy members and friends were unable to think of our "Lord" his blessed "Tsebel" immediately. To the contrary, she had hope and faith in the worldly medical miracles, in man-made-magic.

I learn, that we all are in the hands of a very patient and forgiving God.

I learn, that the Ethiopian Nation, like the nation of Israel, is challenged and exploited by several bad spirits that are produced by its internal and external enemies.

May God continue helping us defeating them!

Anonymous said...

to all dejeselamaweyan one of the comment written above(see below) by Deje salm who delibrately misspelled the blogger's name to cheat you. Awak!
"ዘግይቶ የደረሰን ዜና ከልጅቱዋ ሆድ የወጣው ወፍ ሳይሆን የዶሮ ጫጩት መሆኑን በባለሙያዎች ተረጋግጦዋል ። ልጅቱዋም በየመንደሩ እየዞረች ጫጩቶችን ስታገኝ ትቀረጥፍ እንደነበር እማኞች መስክረዋል።
እኛም በስሜት ተውጠን ሳናጣራ በሬ ወለደ ወሬ ማናፈሳችን ብቁዋፍ ላይ የሚገኘውን አማኝ መበተን ስለሚሆንብን ሃቁን ተናግረናል።

ደጀ ስላም"

Unknown said...

Slam said the above negative messages which he learns from his father devil(Seyttan).we know him;Slam,if you want,I will tell you the address of Menbere Maryam and she can explain about the True Ethiopian Orthodox Tawihdo religion which gives her Holy water(TTEbel)

Anonymous said...

To ABU AYUB, mehertetab and the like,

You really need to repent, kneel down and pray to God for His mercy.

The ways you write above indicate that you brain and heart are fully controlled by Devil. You are defending him, and prefer to mock on God's work.

Do you think you can invalidate God's work by lying? Is that what Protestantism mean? It is good for us to know your true nature. But, I am still sorry for you. I really do.

May God reveal you the truth! Amen

Unknown said...

Above anonymous,what are you saying,ABU AYUB and others opposed this miracle which is done by Almighty God.don't you know english?read again my message;I oppose the writing of Abu ayub but your blindly write against me;then are your eyes fully covered and controlled by devil?

Anonymous said...

To Mehereteab

I am deeply sorry. I apologize for that. I think you would understand that. It was an honest mistake. May God's Mercy be upon you?

Ye Egziabeher Mehiret, Ye Dingle Mariam Amalagenet kehulachen gar yehun! Amen!

Anonymous said...

To Mehereteab

I am deeply sorry. I apologize for that. I think you would understand that. It was an honest mistake. May God's Mercy be upon you!

Ye Egziabeher Mehiret, Ye Dingle Mariam Amalagenet kehulachen gar yehun! Amen!

November 02, 2009

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)