October 26, 2009

ቅ/ሲኖዶስ በብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ዝውውር ላይ የጀመረውን ውይይት ሳይፈጽም ቀረ


(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 25/2009)፦
ዛሬ ቀጥሎ በዋለው የቅ/ሲኖዶስ ስብሰባ በብፁዕ አቡነ ሳሙኤል የዝውውር ቦታ ጉዳይ ሲወያይ ውሎ አጀንዳውን ሳይቋጭ ተበትኗል። በትናንትና ውሎው ብፁዕነታቸውን ከአዲስ አበባ አንሥቶ ወደ ሌላ ቦታ ለማዛወር ከስምምነት የተደረሰ ቢሆንም ‘የት ይመደቡ?” የሚለውን ተመልክቶ ምክረ ሐሳብ (ፕሮፖዛል) እንዲያመጣ የተመደበው ኮሚቴ ባመጣው ምርጫ ስምምነት ሳይገኝ ቀርቷል።

ልማት ኮሚሽን፣ ሕጻናት ማሳደጊያ ወይም ትንሣዔ ዘጉባዔ የሚሉ ምርጫዎች ከመጡ በሁዋላ ብፁዓን አባቶች “ልማት ኮሚሽን ይመደቡ” የሚለውን በድምጽ ብልጫ ቢወስኑም ቅዱስ ፓትርያርኩ “እርሱ ቦታ ሌላ ሰው አለበት” በማለታቸው ከስምምነት ሳይደረስ ቀርቷል። በድምጽ ብልጫ የተወሰነውም ውሳኔ በእርሳቸው አለመስማማት ሳይሳካ ቀርቷል ማለት ነው።


ቅዱስ ሲኖዶስ ብድምጽ ብልጫ የሚሠራ ቢሆንም በእንዲህ ዓይነቱ አጋጣሚ ፓትርያርኩ “ድምጽን በድምጽ የመሻር” (ቬቶ) መብት (? ?) ውሳኔዎች ይታጠፋሉ። የዛሬው የአቡነ ሳሙኤል ምደባ ጉዳይ በቬቶ ከተሻረ በሁዋላ ጉባዔው መበተኑ ታውቋል። ስብሰባው ይጠቃለላል ብለው ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስማት የመጡ ጋዜጠኞችም ባዶ እጃቸውን ተመልሰዋል።
ጉባዔው ነገ ቅዱስ ፓትርያርኩ ወደ ሌላ ቦታ የሚሄዱ በመሆናቸው የማይቀጥል ሲሆን ሲመለሱ ወደ ረቡዕ አካባቢ ይደረግ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።
በተያያዘ ዜና ትናንት ተነሥቶ ለውይይት ሳይቀርብ የቀረው የማህበረ ቅዱሳን ጉዳይ ዛሬም በሌላ አባት በድጋሚ ተነሥቶ እንደነበር ታወቀ። በመምሪያውና በማህበሩ መካከል ያለው ችግር ሙሉ በሙሉ እንዲፈታ የጠየቁ አንድ አባት ሐሳባቸውን ለመወያያነት ለማብቃት የሞከሩ ቢሆንም ሳይሳካ ቀርቷል ተብሏል።
ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን

5 comments:

zeyigerm said...

Abune Paulos is the one who needs our prayer, not for the usual system as father prays for sons and and the vice versa. But he is full of evil spirit. And I said let's pray for him to save his soul. He has no, as in my imagination, any possitive thinking to develope the church he lead. He is just take the position as secular power. He has never open his mouth even for once in his 17 yrs power for christians presecuted and killed both by anti-tewahedos and the Goverment itself. So, as this point of view this is difficult to say he stands for the church, except need of power and this world's reward.
So, let's pray for our fathers to do their responsibility properly. Never expect something better from Abune Paulos.

His regretion was for strategy formulated by woyane and to attack Abune Samuel.

Those who have the power to pray please pray for those negligent Papasat to save their life and in addition to shorten their souls on power and earth. As much as they live they will not leave their power willingly.And similarly as they are in power, the church gets crisis and crisis, we lose many of our mi'emenans .
May God Bless Ethiopia and our Church.

Anonymous said...

I feel so sad and desparate that we were expecting the Holy Synod to discuss the very important issue of saving the church and retain the ultimate power of the Holy Synod, but we are hearing that the Papasat fighting for thier position and title. So sad and disappointing.

Let the Almighty God find a solution for his house.

John Ze Baptist said...

Why come the need for transferring of Abune Samuel? Is it because he opposes non-christian behavior of Aba Paulos? For sure, I think it is because of this. And it is really shame.

Brothers, I don't believe the problem is solved unless that man get out of his post.

May God be with the Holy Synod!

Anonymous said...

+++
Where is our petition DS?

Ze Zeway

Anonymous said...

የሚከተሉት፡3ት፡ነጥቦች፡ምንኛ፡ለከባድ፡አደ
ጋ፡እንደተጋለጥን፡ያመለክታሉ።

ልብ፡ብለን፡እናስተውል!!!


1)አባቶች “ልማት ኮሚሽን ይመደቡ” የሚለውን በድምጽ ብልጫ ቢወስኑም ቅዱስ ፓትርያርኩ “እርሱ ቦታ ሌላ ሰው አለበት” በማለታቸው ከስምምነት ሳይደረስ ቀርቷል።

2)ቅዱስ ሲኖዶስ ብድምጽ ብልጫ የሚሠራ ቢሆንም በእንዲህ ዓይነቱ አጋጣሚ ፓትርያ
ርኩ “ድምጽን በድምጽ የመሻር” (ቬቶ) መብት (? ?) ውሳኔዎች ይታጠፋሉ።

3)ጉባዔው ነገ ቅዱስ ፓትርያርኩ ወደ ሌላ ቦታ የሚሄዱ በመሆናቸው የማይቀጥል ሲሆን ሲመለሱ ወደ ረቡዕ አካባቢ ይደረግ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።


የጥፋት፡ርኩሰት፡ሲኖዶሱን፡እንዴት፡እንዳቃለለ
ው፣ረግጦ፡እንደያዘውና፣እንዳዋረደው፡እንመልከ
ት!የግል፡ኩባንያ፡እንኳ፡እንዲህ፡በትዕቢት፡በተወ
ጠሩ፡ዓመጸኞች፡አይመራም።

"ቬቶ"ደግሞ፡የቤተ፡ክርስቲያን፡ስብሰባ፡የሚምመ
ራበት፡ደንብ፡አይደለም።የአውሬውን፡ፖለቲካዊ፤
አኪያሂያድና፡የተፋጠነ፡ሸፍጥ፡ልብ፡እንበል!

ከ"ይቅርታ፡አድርጉልኝ፡" እስከ፡በ"ቬቶ፡የአባቶ
ችን፡ውሳኔ፡አሻፈረኝ፡ማለት፡ቅጥፈትን፡እንጂ፡
ቅንነትን፡አያመለክትም!

ኤንዴትስ፡ተደርጎ፡ነው፡የጳጳሳቱን፡ጉባኤ፡በመር
ገጥ፡"ወደ፡ሌላ፡ቦታ፡ስለሚሂዱ"ስብሰባው፡ሊቀጥ
ል፡አይችልም፡የሚባለው?!

የሰውዬውን፡ዓመፅና፡ንቀት፡እንመልከት!

በዚህ፡አያያዝ፡ነገ፡ሰውዬው፡በ"ቬቶ" ወስኛለሁ፡በማለት፡ቤተ፡ክርስቲያናችንን፡ከሮም፡
ሥር፡እንድትሆን፡አሳልፈው፡ቢሰጡንስ?!እግራ
ቸው፡ወደ፡ሮም፡ያሰላው፡እንዲሁ፡ነው፡የሚል፡ይ
ኖር፡ይሆን?!

በካቶሊኮቹ፡ሲኖዶስ፡የተገኙት፡በ"ቬቷቸው"ይ
ሆን?ወይስ፡ጉዳዩ፡በኢትዮጵያ፡ጳጳሳት፡ተጠንቶ፡
የተወሰነ፡እርምጃ?ለነገሩማ፡ልብሱም፡የሚያመለ
ክተው፡ሮምን፡መሆኑ፡መች፡ተሳነን!

ይህ፡ከሱስንዮስ፡ወዲህ፡በገሃድ፡ሮማውያን፡ቤተ፡ክ
ርስቲያናችንን፡የተዳፈሩበት፡ወቅት፡መሆኑን፡ስን
መለከት፣ታላቅ፡ተዋሕዶ-ኢትዮጵያዊ፡ሐዘን፡
ይሰማናል!


ለአንድ፡"ፓትርያርክ"ከሲኖዶስ"የበለጠ፡ምድራ
ዊ፡ቀጠሮ፣ያውም፡በሲኖዶስ፡መሐል፣አለን?!ሊኖ
ርስ፡ይገባልን?!

ይኸውና፡የንቀት፡ንቀትና፡የማን፡አለብኝ፡ዓመፅ፡
በገሃድ፡እየተገለጠ፤ነው!

ቤተ፡ክርስቲያናችን፡ከፍተኛ፡የውስጥ፡አደጋ፡ላ
ይ፡ስለምትገኝ፤የተዋሕዶ፡ልጆች፡በሙሉ፡እንጠ
ንቀቅ።እንወቅበት!ቤተ፡ክርስቲያናችንን፡እንጠ
ብቃት!ለሁሉም፡ሳናውቅ፡ደረሰብን፡እንዳንል፡እ
ንዘጋጅ!

መድኃኔ፡ዓለም፡ይርዳን፣ፍርዱንም፡ይስጠን!!!


ቅድስትና፡ድንግል፡የሆነችው፡እናታችን፡እመ፡ብርሃን፡ከኛ፡ጋር፡ትሁንልን!!!
አሜን፤አሜን፤አሜን።


ሳሙኤል፡ዘአሰቦት።

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)