October 25, 2009

ቅ/ሲኖዶስ በሁለት አጀንዳዎች ላይ የጀመረውን ውይይት ሳይፈጽም አሳደረ

(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 23/2009)፦
ቅዱስ ሲኖዶስ በዛሬው ውሎው ስለ አዲስ አበባ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሲወያይ ውሎ ሳይጨርስ ለነገ አሳደረ። በሌላ በኩል አባ ሰረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል በማህበረ ቅዱሳን ላይ በቅርቡ ጽፈው በበተኑትና ለመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ሳይቀር ግልባጭ ባደረጉት ጠንካራ ደብዳቤ ዙሪያም ሐሳቦች ተሰጥተዋል ተብሏል።

አቡነ ሳሙኤልን በተመለከተ በተደረገው ረዥም ውይይት ቅዱስ ፓትርያርኩ “አቡነ ሳሙኤል ወደ መቐለ መቀየር አለባቸው” የሚል ሐሳብ አጠንክረው ይዘዋል። “ወደ አሶሳና ጋምቤላ ከመላክ መቐለ መላክ ሳይሻል ስለማይቀር ሐሳቡን ብትቀበሉት ይሻላል” በሚል ፓትርያርኩ ጫና ለማድረግ የሞከሩ ቢሆንም ቅ/ሲኖዶስ ሐሳቡን ሳይቀበለው ለበለጠ ውይይት ለነገ አሳድሮታል። አንዳንድ የቅ/ሲኖዶስ አባላት ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ከአዲስ አበባ እንዳይቀየሩ፣ መቀየራቸው ካልቀረ ግን ወደ ልማት ኮሚሽን የበላይ ጠባቂ ሆነው እንዲዛወሩ ሐሳብ አቅርበዋል ተብሏል።

በተያያዘ ዜናም ማህበረ ቅዱሳንን በተመለከተ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ ባነሱት ሐሳብ “በአባ ሰረቀ በኩል ማህበሩን በተመለከተ እየተሄደ ያለው አካሄድ ጥሩ ስላይደለ ጉዳዩ በሰላም ይፈታ” የሚል ሐሳብ እንዳቀረቡ የተጠቆመ ሲሆንብፁዕ አቡነ አብርሃምም ይህንኑ በመደገፍ ሐሳብ መስጠት ጀምረው እንደነበር ታውቋል። ቅዱስነታቸው በዚህ ጉዳይ ዙሪያ መነጋገር ፤ ለጊዜው አስፈላጊ አለመሆኑን በመጥቀስ ጉዳዩ ውይይት እንዳይደረግበት ዘግተዋል ተብሏል። ምናልባት በነገ ዕለት ጉዳዩ በድጋሚ ይነሣ ይሆናል የሚል ግምት ግን አለ።
ይህ የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ነገ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።
ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን
Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)