October 22, 2009

ኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት - "በቤተክርስቲያኗ አባቶች መካከል ተፈጥሮ የነበረው አለመግባባት መፈታቱ ተገለፀ"


ውድ ENA፦ ለመሆኑ እነዚህ የተባሉት አባቶች መቼ ተገናኝተው ተነጋገሩ? በምን ጉዳይ ላይ ተነጋገሩ? ማን ዳኛቸው? ነው ወይስ እነ እንትና የሰጡትን ማስጠንቀቂያ እንደ ችግር መፍቻ ተቆጠረ። ወይ ጉድ!!!
ለማንኛውም ደጀ-ሰላማውያን እሰቲ አንብቡት።
ቸር ወሬ ያሰማን፣ አሜን
+++++++
አዲስ አበባ, ጥቅምት 12 ቀን 2002 (ENA/ኢትዮጵያ ዜና አገለግሎት) - በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሐዶ ቤተክርስቲያን የኃይማኖት አባቶች መካከል ተፈጥሮ የነበረው መጠነኛ አለመግባባት በቅን መንፈስና አባታዊ በሆነ መንገድ መፈታቱን የቤተክርስቲያኗ ፓትርያርክ ብጹዕ ውቅዱስ አቡነ ጳውሎስ አመለከቱ፡፡ በዓመት ሁለት ጊዜ የሚካሄደው የቤተክርስቲያኗ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ዛሬ ተጀምሯል፡፡

ፓትርያርኩ ጉባኤውን ሲከፍቱ እንደተናገሩት ዓለም በየጊዜው ከፍተኛ የእድገት ለውጥ በምታመጣበት በአሁኑ ወቅት ሁሉም ወገን ችግሮቹን በሰላማዊ መንገድ በመፍታት ለሀገሩን ልማት ዕድገት የበኩሉን አስተዋፅዖ ማበርከት አለበት ብለዋል፡፡

የመደማመጥና የመተሳሰብ ብሎም የመረዳዳት ባህል በማጎልበት ለሕዝብና ለሀገር አርአያ መሆን እንደሚያስፈልግ አመልክተው በቅርቡ በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ተፈጥሮ የነበረው መጠነኛ ችግርም አባታዊና መንፈሳዊ በሆነ መንገድ መፈታቱን ተናግረዋል

የሰላም ባህል እንዲስፋፋም መደማመጥ፣መከባበር መወያየትና አንዱ የሌላውን ሐሳብ መረዳት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ ከዚህ አኳያም ቤተክርስቲኗ የሰላምና የእርቅ እንዲሁም አብሮ በሰላም የመኖርና የመቻቻል ስሜት እንዲጎለበት ጥረት ማድረግ እንዳለባትም ገልፀዋል፡፡

ፓትርያርኩ እንዱሉት ክርስቲያኖች በአኗኗራችን ሰላም ለሚሰፍንበት ስነ ምግባር ተጠቃሽ ምሳሌዎች መሆን ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡

ቤተክርስቲያኗ እስካሁን ያከናወነቻቸው ተግባራት የሚያስመሰግኑ ናቸው ያሉት አባ ጳውሎስ ከዚህ ይበልጥ ለመሥራት በሙሉ ኃይል እንድተነሳም የላቀ ተሳትፎ እንደሚጠበቅባትም አመልክተዋል፡፡

ለዚህ ደግሞ ከሁሉም በላይ የውስጥ አንድነትን በማጠናከርና የወቅቱን ሁኔታ በመከተል የበለጠ ሥራ እንደምትሠራ ተናግረዋል ።

የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትን በአምስት ዞኖች መመደብ፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ ጉዳይ እንዲያጣራ የተሰየመው ገለልተኛ ኮሚቴ ሪፖርት ላይ ተወያይቶ ውሳኔ መስጠት እንደሆኑም አመልክቷል፡፡

በተጨማሪም የዘመኑን በጀት ማጽደቅ፣ የቤተክርስቲያኒቱን የቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደር ጉዳይ፣ ከየአህጉረ ስብክቱ የሚቀርቡ ልዩ ልዩ ጉዳዮችና በሌሎች ርእሶችም ላይ የሚወያይ ሲሆን የተለያዩ ውሳኔዎችን እንደያሳልፍም የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዘግቧል ።
Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)