October 28, 2009

ስለ ቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ የEthiopia zare ሪፖርታዥ፦ “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አባቶች ውዝግብ ተቋጨ”

(ደጀ ሰላም Oct 28/2009)፦ ከዚህ በታች የቀረበው የዛሬ Oct 28/2009 የEthiopiazare ሪፖርታዥ ነው። መልካም ንባብ።
ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን
+++++
  • አቡነ ሳሙኤል የልማትና ተራድኦ ኮሚሽን ስልጣን ፀደቀላቸው
Ethiopia zare (ረቡዕ ጥቅምት 18 ቀን 2002 ዓ.ም. October 28, 2009)፦
አቡነ ሳሙኤል እጣ የወጣላቸው የልማትና ተራድኦ ኮሚሽን ተቋም ኃላፊና በመሆን እንዲሰሩ ዛሬ ረቡዕ ጥቅምት 18 ቀን 2002 ዓ.ም የፀደቀላቸው መሆኑን የአዲስ አበባ ምንጮቻችን ገለጹ።

ፓትሪያርክ አቡነ ጳውሎስ በሌሎች የቅዱስ ሲኖዶስ ጳጳሳት ላይ በመንግሥት ሰዎች የታገዘ ተጽዕኖአቸውን በማሳረፍ ላይ ቢሆንም ቅዳሜ ጥቅምት 14 ቀን 2000 ዓ.ም በአጠቃላይ ስምምነት ያበቃል የተባለለት የሲኖዶሱ ጉባኤ ለሰኞ ጥቅምት 16 ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ የተያዘለት ጉባኤ በአባ ጳውሎስ ዕምቢኝ ባይነት በዕለቱም መፍትሔ አልተገኘለትም።


የቤተክህነት ምንጮች ውዝግቡ እልባት ሊያገኝ ያልቻለው “አቡነ ጳውሎስ የአባ ሳሙኤልን የሥራ ምደባ እኔ ባልኩት መሠረት ይፈጸም፤ የሲኖዶሱ አባላት አባ ሳሙኤል ዕጣ በወጣላቸው መሠረት የልማትና ተራድኦ ኮሚሽን ተቋም ሃላፊ ሆነው ይቀመጡ መባሉን አልቀበልም በማለታቸው ነበር። ይልቁንም አቡነ ጢሞቲዎስን ጨምሮ ሌሎች ጳጳሳትን በመዝለፍና በማንጓጠጣቸውም ምክንያት ነው” ብለዋል።

ፓትሪያርክ አቡነ ጳውሎስ አባ ሳሙኤልን ከአዲስ አበባ ወደ መቀሌ አርቀው በመወርወር በእሳቸው አስተዳደር ዙሪያ ተነስቶ የነበረውን ጥያቄ በሙሉ ለማዳፈን የሚፈልጉ ሲሆን፤ ከእሳቸው በተቃራኒ ወገን የቆሙ የሲኖዶሱ አባቶች ደግሞ የሥራ ምደባ በሲኖዶሱ ውሳኔና በተመደበው ፈቃድ ወይም በዕጣ መሆን ይገባዋል እንጂ አባ ጳውሎስ በሚሰጡትና ሊታጠፍ አይገባውም እያሉ በአምባገነንነት በሚሞግቱበት ትዕዛዝ መሆን የለበትም” የሚለውን አቋም ይዘዋል።

ብዙሃኑ ጳጳሳት ከአባ ሳሙኤል ወገን ሆነው በአዲስ አባባና በአቅራቢያው ወይም በአሰበተፈሪ ይመደቡ ይህም ካልሆነ በልማትና ተራድኦ ኮሚሽን ውስጥ እንዲሠሩ ይሁን” የሚል ሃሳብ አቅርበው ነበር “ማንም ሊያስፈራራኝና ሊዝትብኝ አይችልም……” ያሉት አባ ጳውሎስ “ ተፈፃሚ መሆን ያለበት የእኔ ሃሳብ ብቻ ነው” በሚለው አቋማቸው ጸንተው እንደነበር ታውቋል።

ከእነ አባ ሳሙኤል ጋር የተጣሉበትን በቤተሰብ የመሥራት ችግር ጥያቄ ለማለዘብ ዋንኛ ተቀናቃኛቸውን ወደ መቀሌ ለማዝመት፣ የአዲስ አበባንም ሀገረስብከት በ5 ቦታ ለመሸንሸን ያላቸውን ፍላጎት ከጥቅምት 11 ቀን 2002 ዓ.ም ጀምሮ በተደጋጋሚ አንፀባርቀዋል።

አቡነ ሳሙኤል በመግቢያ ንግግራቸው ብዙሀን አባቶችን በሚማርክ መልኩና ታላቅ አባት መሆናቸውን በሚያስመሰክር ሁኔታ ጉባኤውን ጥፋት አጥፍተው እንደሆነ ይቅርታ በመጠየቅና ራሳቸውን ዝቅ በማድረግ የነበረ ሲሆን ብዙ አባቶችም የአቡኑን ወነመቀሌ መሄድ ተቃውመው እንደነበር ለመረዳት ችለናል። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ህግና ደንብ መሰረት የአባቶች ሹመት በእጣ ሳይሆን በፈቃዳቸው በሲኖዶሱ ውሳኔ እንዲሆን ያዛል።

Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)