October 15, 2009

የጠቅላይ ቤተ ክህነት የሰበካ አጠቃላይ ሀገር አቀፍ ስብሰባ ነገ ይጀመራል፤ ቅ/ሲኖዶስ የሚቀጥለው ሳምንት

(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 15/2009):- የ2002 ዓ.ም ዓመታዊው የሰበካ መንፈሳዊ ጉባዔ ነገ አርብ ጥቅምት 6 ቀን 2002 ዓ.ም (ኦክቶበር 16) እንደሚጀመር ታወቀ።

ከመላው ኢትዮጵያ ከሚገኙ አህጉረ ስብከት እና ከአንዳንድ የውጪ ሀገራት የሚመጡ ተሰብሳቢዎች የሚሳተፉበት ይኸው ስብሰባ የየሀገረ ስብከቶቹ ሊቃነ ጳጳሳት፣ ሥራ አስኪያጆች፣ የምእመናን ተወካዮችና የሰንበት ት/ቤቶች ተጠሪዎች የሚወከሉት ታላቅ ጉባዔ ነው።

ከጥቅምት 6 እስከ 11 ቀን 2002 ዓ.ም (ኦክቶበር 16-21/2009) ይቆያል ተብሎ የሚጠበቀው ይህ ስብሰባ እንደ ተወካዮቹ ብዛት፣ እንደ ዓመታዊነቱ ብዙም ወሳኝ ጉዳዮች ላይ የመወያየት ልምድ የሌለው ሲሆን በተለይም ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ጉባዔው የቅዱስነታቸው ማሞገሻ በዓል ከመሆን ያለፈ ፋይዳ የሚነገርበት፣ የሚታቀድበት፣ የሚወያይበት አለመሆኑ ይታወቃል።
ምናልባት ከግንቦቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ወዲህ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ አስተዳደር፣ በቅዱስ ሲኖዶስ አባላት እና በፓትርያርኩ አካባቢ በተፈጠረው ውጥረት ምክንያት የዚህ ዓመቱ ስብሰባ የተለየ መልክ ካልያዘ በስተቀር የተለየ የሥራ ውጤት የሚጠበቅበት ስብሰባ አለመሆኑን ለቤተ ክህነቱ ቅርበት ያላቸው ሰዎች በሙሉ ይመሰክራሉ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ባለፈው ሐምሌ ወር የበር ሰበራ፣ ዛቻና ማስፈራሪያ የደረሰባቸው የቅ/ሲኖዶስ አባላት ብፁዓን አባቶች ለደህንነታቸው እንደሚሰጉና በዚህም ምክንያት ምናልባት ከቅ/ሲኖዶስ ጉባዔ ተሳታፊነታቸው ለመታቀብ እንደሚገደዱ እየተናገሩ መሆናቸው ተሰማ። ብፁዓን አበው ከየሀገረ ስብከታቸው ወደ አዲስ አበባ ለመምጣት “ዋስትና” ማግኘት እንደሚፈልጉ መናገራቸው ታውቋል። ይህንን የተመለከተውን ዝርዝር በቅርቡ እናስነብባችኋለን።
ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን
Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)