October 30, 2009

በቅዱስ ዮሐንስ ጠበል ከሆድ ውስጥ ወፍ ወጣ


(ማኀበረ ቅዱሳን ስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ)፦ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በደብረ ወልደ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ እና በመካነ ጎለጎታ ቅድስት ማርያም ጠበል ሰሞኑን ከአንዲት እኅት ከሆዷ ጥቁር ወፍ ወጣላት፡፡ በክርስትና ስሟ መንበረ ማርያም ተብላ የምትጠራው እኅት ለ20 ዓመታት ያህል በሆድ ሕመማት ስትሰቃይ መቆየቷን የምትናገረው መንበረ ማርያም፤ ስቃይዋን በዘመናዊው ሕክምና ለማስታገስ ያልሔደችበት ቦታና ያልወሰደችው መድኃኒት የለም፡፡ ይሁንና የምትወስደው ሕክምና ለጊዜው ስቃይዋን ከማስታገስ በስተቀር ከሕመሟ ልትድን ባለመቻሏ ከዚህ በኋላ ይግደለኝ እንጂ ሕክም ናም ሆነ መድኃኒት መጠቀም የለብኝም፤ ብላ ጠበል ለመጠመቅ እንደ ወሰነች ትናገራለች፡፡ በውሳኔዋም መሠ ረት ወደ ወልደ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን ጠበል በመሄድ ስትጠመቅ በላይዋ ላይ የሰፈሩ 681 አጋንንት እንዳሉ በላይዋ ላይ ያደሩት የሰይጣን ሠራዊት ለፍልፎ በጥቁር ወፍ አምሳል ከሆዷ ውስጥ ሊወጣላት ችሏል፡፡


ምእመናን በዕለቱ ከሆዷ ውስጥ በትውከትነት እንደ ጥይት ተወርውሮ የወጣውን ጥቁር ወፍ ከነሕይወቱ በማየት በቪዲዮ በመቅረጽ የእግዚአብሔርን ድንቅ ተአምር እንደ መሰከሩ ተገልጿል፡፡

የስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራ ሰምቶ ይህንኑ ወፍ የወጣላትን መን በረ ማርያምንና ያጠመቋትን አባት ሊቀ ትጉኃን ስሙር አሐዱን በማነጋገር ድርጊቱ እንዴትና ምን ይመስል እንደነበር በሰፊው ዘግቧል፡፡

እግዚአብሔር ሥራው ድንቅ ነው፤ ተዓምሩ ዕፁብ ነው፤ ተነግሮ አያልቅም፤ ይህን ሥራውን መመስከር ደግሞ የእኛ ተግባር ነው፡፡ ለረጅም ዓመታት በሕመም ስትሰቃይ የነበረች በስመ ጥምቀቷ መንበረ ማርያም የተባለች ወጣት የእግዚአብሔርን የድንቅ ሥራው መገለጫ ሆናለች፡፡

ለዚህች እህት እግዚአብሔር ያደረገላት ገቢረ ተአምር ሲሰሙት ለጆሮ የሚከብድ፤ እንዲሁም በወቅቱ ድር ጊቱ ሲፈጸም የተመለከቱ ምእመናንን ሁሉ ያስደመመ ነበር፡፡ «ማን ያርዳ የቀበረ፤ ማን ይናገር የነበረ» ነውና ሥረ መሠረቱ ምን፣ እንዴትና መቼ ሆነ? የሚለውን ጉዳይ እሷው ባለታሪኳ እንዲህ ትተርክልናለች፡፡

«ያመኝ የነበረው ገና የአራት ዓመት ልጅ እያለሁ እሰቃይ ነበር፡፡ ለምሳሌ የራስ ምታት፣ ነስር፣ የሆድ ቁርጠት፣ የአንጀት ኢንፌክሽን ወዘተ እየተባለ በመታመም ሁልጊዜ ሐኪም ቤት እመላለስ ነበር፡፡ እናቴ እንደ ነገረችኝ የሕመሙ መነሻ ወተት ነው፡፡ «ወተት ጠጥተሽ የአንጀት ኢንፌክሽን ያዘሽ» ያለችኝ እናቴ በየክሊኒኩ እየወሰደችኝ ስታስመረምረኝ መድኃኒት እንደሚያዙልኝ አጫውታኛለች፡፡ ራሴን ማወቅ ስጀምር ትምህርት ቤት ገብቼ ስማር ሆዴን ያመኛል፡፡ በተለይ በበጋ ወራት ተምሬ ሁለት ወር ክረምት በሚሆንበት ወቅት ክፉኛ ያመኛል» ስትል ተናግራለች፡፡

መንበረ ማርያም በሕመሟ መጥናት ብዙ ጊዜ ሐኪም ቤትና ክሊኒክ ተመላልሳ እንደታከመች ገልጻል ናለች፡፡ ነገር ግን ጠበልስ አልሞከረች ይሆን? የሚለው ጥያቄ አጫረብንና ጠየቅናት፤ እርሷም ስትመልስ «በዚያን ወቅት ቤተሰቦቼ የሚያስቡት ሐኪም ቤት የሚባለውን እንጂ ጠበልን አልነበረም፡፡ እኔም ቢሆን በወ ቅቱ ጠበልን አላሰብኩትም፤ ብቻ ሐኪም ቤት ሔጄ የተለያየ መድኃኒት ይታዘዝልኛል እወስዳለሁ፡፡ ለጊዜው ያስታግሥልኛል፤ ጨርሶ ግን ሊያድነኝ አልቻለም፡፡ ይባስ ብሎ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስጄ ጥሩ ውጤት በማምጣት አራት ኪሎ ዩኒቨርሲቲ ገብቼ የመጀመሪያ ዓመት መማር ስጀምር በሽታው ክፉኛ አሰቃየኝ፡፡ ያስጨንቀኛል፣ ከፍተኛ የራስ ምታት ሕመም ይሰማኛል፤ ማጥናት አልችልም ነበር፡፡ የሴሚስተር ፈተና ደርሶ ሁለት ሳምንት ሲቀረው አንደኛው ዐይኔ ውስጡ ሲቆስል ሌላኛው ዕንባ ማፍሰስ ጀመረ፡፡ ዕንባው ያለምንም ማቋረጥ ለ24 ሰዓታት ይወርዳል፡፡ ቤተሰቦቼ ሁኔታው አላምር ቢላቸው ወደ አንዲት ታዋቂ የዐይን ሐኪም ወሰዱኝ፡፡ እሷም 'በሕይወቴ እንዲህ ዐይነት ነገር ዐይቼ አላውቅም፤ ዐይኗ ውስጥ ቁስል አለና የመታት ነገር አለ ወይ?' ብላ ጠየቀች፡፡ ይሁንና ቤተሰቦቼም ሆኑ እኔ ምንም ነገር የመታኝ ነገር እንደሌለ ለዶክተሯ ነገርናት፡፡ በየሰዓቱ የሚደረግ ጠብታ አዛልኝ ለጊዜው ተሻለኝ፡፡ የከፍተኛ ትምህርቴን ግን ሳልማር ለሁለት ዓመት ያህል አቋረጥኩ» ትላለች የሕመሙን አስከፊነት የምትናገረው መንበረ ማርያም፡፡

መንበረ ማርያም እንደገለጸችልን በጤና መታወክ ሳቢያ ለጊዜው ትምህርቷን ብታቋርጥም ለትምህርቷ ያላት ቁጭት ከፍተኛ ስለነበር በሽታው መጣ ሔድ እያለ ቢያስቸግራትም ከዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በመግባት ትምህርቷን በሥራ አመራር የትምህ ርት ዘርፍ ለአራት ዓመታት ያህል ተከታትላ በ1996 ዓ.ም በዲግሪ ተመርቃለች፡፡

ይሁንና ሌላ ያላሰበችው ችግር ገጠማት፤ ይህስ ምን ይሆን? ለዚህም መንበረ ማርያም ስትናገር «የወር አበባዬ ከመጣበት ጊዜ አንሥቶ አሁን እስከዳንኩበት ጊዜ ድረስ በየወሩ በጣም እያመመኝ ክፉኛ ያሰቃየኛል፡፡ ስቃዩን ለማስታገሻ እያልኩ ፓ¬ራሲታሞል ክኒን በየአራት ሰዓት ልዩነት ሁለት ሁለት ፍሬ በመዋጥ በቀን 10 ፍሬ እወስድ ነበር፡፡ ሐኪም ቤትም ብሔድ የሚሰጡኝ መርፌ ነው፡፡ አልሻል አለኝ፡፡ የሕክምና ባለሙያዎቹ 'አግብታ ትውለድ፤ ሴቶች እንዲህ ዐይነት ሕመም ሲሰማቸው ይሻላቸዋልና መውለድ አለብሽ' ብለው አስተያየት ይሰጡኛል» ትላለች፡፡

እንደ መንበረ ማርያም አገላለጽ ብዙ ጊዜ መድኃኒትም መዋጥ ሌላ ችግር /Side-effect/ ስላለው መድኃ ኒት መውሰዱን ታቋርጣለች፤ «ከድጡ ወደ ማጡ» እንዲሉ ይባስ ብሎ በየወሩ ያማት የነበረው እንደ አዲስ የማያቋርጥ የማኅፀን ሕመም ይሰማት ጀመር፡፡ በዚህን ጊዜም በታወቁ የማኅፀን ሐኪም በመታየት በወር አበባ ሳቢያ የተነሣ በማኅፀኗ ውስጥ ትናንሽ ዕጢዎች እንዳሉ ይነገራትና የወር አበባዋ ከመምጣቱ በፊት ለአንድ ሳምንትና ከመጣም በኋላ ለአንድ ሳምንት የሚወሰድ ከባድና በጣም ውድ የሆነ መድኃኒት ይታዘዝላ ታል፡፡ ይህ የሆነው ከሁለት ዓመት በፊት ነው፡፡

«በዚህን ጊዜ የመጨረሻ ቁርጥ ውሳኔ ወሰንኩ» ትላለች መንበረ ማርያም፡፡ «መሞቴ ለማይቀር ነገር ለምን እሰቃያለሁ? በመድኃኒትስ ለምን እቃጠላለሁ?» በማለት ወደ ጠበል ቦታ ለመሔድ ወሰነች፡፡ ጠበሉን እንድትሞክር ያነሣሣትና ምክንያት የሆነቻት ደግሞ ጓደኛዋ እንደሆነች ተናግራለች፡፡ «አንድ ጓደኛዬ እንደ እኔ ዓይነት ሕመም ይሰማት ስለነበር ጻድቃኔ ማርያም ሔዳ ጠበል ጠጥታ እንደዳነች ነገረችኝ፡፡ እኔም ጠበል መጠጣትና መጠመቅ እንዳለብኝ መከረችኝ፡፡ መድኃኒቱን አቋርጬ ጠበል መጠመቅ ጀመርኩ፡፡ እየጾምኩ በተከታታይ ጠበሉን ስጠጣና ስጠመቅ በየወሩ የወር አበባዬ ሲመጣ ያመኝ የነበረውን ተወኝ፡፡ በመቀጠል ከማኅፀኔ ሥጋ ነገር ተቆርጦ ወጣ፡፡ በዚህ ጊዜ ቤተሰቦቼ «እጢው ወጣልሽ» በማለት ተአምር አሉ፡፡ ሥጋ መሰል ባዕድ አካል ከወጣልኝ በኋላ ምንም ዓይነት ስሜት ሳይሰማኝ ጤነኛ ሆንኩ፤ ጠበሉንም አቋረጥኩት» በማለት ገልጻለች፡፡

በዚህ መልኩ ለውጥ ያገኘችበትን ጠበል ስታቋርጥ ዳግም ሕመሙ ጀመራት፡፡ መንበረ ማርያም ትናገራ ለች፡፡ «ጠበሉን ለአንድ ዓመት እንዳቋረጥኩ በሽታው በባሰና በሚያስፈራ መልኩ ተመልሶ መጣ፡፡ እንደገና ጠበሉን መጠጣት ጀመርኩ፤ በዚህን ጊዜም ደጋግሞ የሆነ ነገር በሕልሜ ያሳየኛል፤ በሆነ መንገድ ላይ በጣም ጥቁርና ትልቅ ሰውዬ ዝም ብሎ ቆሞ ዐያለሁ፣ ቀጥሎ እኔ ሕፃን ልጅ ታቅፌ ሳመልጥ እሱ ትልቅ ድንጋይ ይዞ እየተከተለ በማስፈራራት ሲያሯሩጠኝ ዐያለሁ፡፡ ይህን ያየሁት በድሮው ቤታችን መገናኛ አካባቢ ነው፡፡

የመንበረ ማርያም ዋናው ታሪክ የሚጀምርው በግንቦት ወር 2001 ዓ.ም ነው፡፡ በዕለተ ሰንበት እሑድ ቀን ቅዳሴ አስቀድሳ ስትመለስ እንደተለመደው የወር አበባ ይታያትና በቃላት ሊገለጽ በማይችል ሁኔታ በጽኑ ትታመማለች፡፡ መንበረ ማርያም እንደገለጸችው «መጽሐፈ አርጋኖን ይዛ ከአንዱ ክፍል ወደ አንዱ ክፍል እየተንቆራጠጠች 'ወይኔ! እመቤቴ ኧረ አድኚኝ' እያለች መኝታ ክፍሏ ሆና ስታጣጥር በድንገት በግድግዳ ላይ የተሰቀለውን የቅዱስ ሚካኤል ሥዕል ታያለች፡፡ እያጣጣርኩ በክፍሌ ውስጥ ቁጭ ብዬ ድንገት የተሰቀለውን የቅዱስ ሚካኤል ሥዕል ቀና ብዬ ማየት ስጀምር የፌዝ ሳቅ መሳቅ ጀመርኩ፡፡ በዚህን ጊዜ ራሴን እየለወጠኝ ነው፤ አልፎ አልፎ እንጂ ምን እንደምሠራም አላውቅም፤ መጣሁልህ ይላል፡፡ እንደዛር ማጓራት ጀመርኩ፤ አባቴ ሲሰማ ደነገጠ፡፡ እሱ እንደነገረኝ ሁለት እጄን ይዞ የቅዱስ ገብርኤል ጠበል እየረጨ 'አንተ ማነህ?' ሲለው 'እባክህ አንተ አታውቀኝም! ዝም ብለህ ነው፤ ተቃጠልኩ ጊዜዬ ሲደርስ የምለቅበት ቀን አለ፡፡ እሷን የያዝኩት ከማኅፀን ጀምሮ ያሳደግኳት እኔ ነኝ' በማለት ለፈለፈ፡፡ በመቀጠል 'እናቷንም የገደልኩ እኔነኝ' ሲል ራሱን ገለጠ» በማለት መንበረ ማርያም አስረድታለች፡፡ እናቷ በካንሰር ሕመም ምክንያት በ1995 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውንም ገልጣልናለች፡፡

በቅዱስ ሚካኤል ሥዕል ሳቢያ ማንነቱን የገለጠው ሰይጣን እንደያዛት ስታውቅ፣ የትመጠመቅ እንዳ ለባት ታስባለች፡፡ በመጨረሻም በደብረ ወልደ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን ሔዳ ጠበል መጠመቅና መጠጣት ትጀምራለች፡፡ በአምስተኛው ቀን ያደረባት ርኩስ መንፈስ መለፍለፍ ይጀምራል፡፡ በተለይ ሰኔ 10 ቀን 2001 ዓ.ም በዕለተ ረቡዕ ስትጠመቅ 681 አጋንንት እንደ ሠፈረባት ይለፈልፋል፡፡ ብዙ ሰው እንደጨረሰና አሁንም ብዙዎችን እንደያዘ ገልጾ እርሷ ላይ ሲደርስ ግን እንደተጋለጠ ተናግሯል፡፡ «ምእመናን እንደነገሩኝ ከሆነ «አንቺ ስትጮኺ እንደ አንበሳ ነው፤ የሚያስፈራና ከአንቺ የሚወጣ ድምፅ አይመስልም ብለውኛል፡፡ እኔ ግን በመሐሉ «መድኃኔዓለም መጣ» የሚል ድምፅ ሰማሁ እንጂ ራሴን አላውቅም፡፡ መጨረሻ ላይ ራሴን ሳውቅ ከእኔ የወጣውን ጥቁር ወፍ ይዘው አሳዩኝ፡፡ አላመንኩም፡፡ ሰው እልል እያለ 'አይዞሽ ተነሽ እመቤታችን ከነልጇ የሠራችልሽ ተአምር በጣም ድንቅ ነው፡፡ ተነሥተሽ ድንቅ ተአምሯን ትመሰክሪያለሽ' አሉ፡፡ ልብሴን ለብሼ ስወጣ ብዙ ምእመናን ቆሞ በሞባይልና በቪዲዮ የወጣውን ጥቁር ወፍ ይቀርጻል፡፡ ከሆዴ የወጣው ትልቅ አፍ ያለው ወፍ ደም ጎርሶ በሕይወት ለተወሰነ ደቂቃ ልቡ ይመታል፡፡ እኔ ራሴን አላመንኩም፤ ደስታ አይሉት ሐዘን ተደበላለቀብኝ፣ ሰውነቴ ከላይ እስከታች ይርዳል» ስትል የእግዚአብሔርን ድንቅ ተአምር መስክራለች፡፡

ሰኔ 10 ቀን ከ681 አጋንንት ውስጥ ሰማንያው ጥቁር ወፍ ሆኖ ሲወጣ ሰኔ 12 ቀን ሌሎች ቀሪዎቹ በጉንዳን መልክ ወጥተናል ብለው በመለፍለፍ ለቀቁ፡፡ በወቅቱም የጠበሉ ቦታ በጉንዳን ተወሮ እንደነበር መንበረ ማርያም ገልጻለች፡፡ ያ በሕልሟ ሲያባርራት ያየችው ጥቁር ሰው እርኩስ መንፈስ እንደሆነና ሕፃኑ ደግሞ መድኃኔዓለም ሆኖ እንዳዳናት አምና ተርጉማዋለች፡፡

መንበረ ማርያም ስለተደረገላት ድንቅ ተአምር ሰኔ 10 እና 21 ቀን 2001 ዓ.ም የእመቤታችን ክብረ በዓል ዕለት በቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ቤተክርስቲያን በመድረክ ላይ ወጥታ ለሕዝበ ክርስቲያኑ መስክራለች፡፡

በመጨረሻ ያነሣንላት ጥያቄ «የተደረገልሽን ተአምር እንዴት ትገልጭዋለሽ?» ነበር፡፡ እሷም «እግዚአብሔር ያደረገልኝን ድንቅ ተአምር በቃላት ልገልጸው አልችልም፡፡ ኃያሉ እግዚአብሔር እኔን አድኖኛል ምስጋና ይድረሰው፡፡ እኔ ግን የማተኩረው ስለተደረገልኝ ተአምር መመስከር ብቻ ሳይሆን ስለማስተላለፈው ነገር ነው፡፡ ይኽም እግዚአብሔር እንዲህ ማዳን እየቻለ ሰይጣን ሊሰለጥንብን አይገባም፡፡ በሥራ፣ በትምህርት ቤትና በዕለት ተዕለት ሥራችን ላይ ውጤታማ እንዳንሆን መሰናከል እየሆነ ነው፡፡ ሕይወታችንን እያበላሸ መሆኑን አልተረዳንም፡፡ ስለዚህ ስመ ክርስትና ብቻ ይዘን መቀመጥ ሳይሆን በጾም በጸሎት እግዚአብሔርን ማገልገል ይኖርብናል፡፡ ከንስሓ አባት ጀምሮ የሃይማኖት አባቶችም ማስተማር አለባቸው፡፡ እያንዳንዱ ሰው ራሱን ይመርምር፤ ክፉ መንፈስን መዋጋት አለበት» ብላለች፡፡

«ማየት ማመን ነው» እንደተባለው በወቅቱ በደብረ ወልደ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስና በመካነ ጎለጎታ ቅድስት ማርያም የጠበል ቦታ ሲያጠምቋት የነበሩትና ድርጊቱን የተመለከቱት ሊቀ ትጉኃን ስሙር አሐዱ ስለሁኔታው እንዲነግሩን ጠይቀናቸው እሳቸውም ታሪኩን እንዲህ አወጉን፡፡ «ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለም፤ ነገሩ ተአምር ነው፡፡ ከዚህ በፊት በእርኩስ መንፈስ የታሰሩ፣ የተተበተቡ ሰዎችን በእግዚአብሔር ኃያልነትና መስቀል በመታገዝ በላያቸው ያለውን አጋንንት አስለቅቄያለሁ፡፡ ይህ ግን ልዩና በሕይወቴም ገጥሞኝ የማያውቅ ነው፡፡ በዕለቱ እኅታችን መንበረ ማርያም ወደምትጠመቅበት ክፍል ስትገባ ጀምሮ በጣም ትጮሃለች፡፡ በመስቀል እያጠመቅሁ ምንድን ነህ? ስለው አጋንንት ነን አሉ፡፡ ቀጥሎ ስንትናችሁ? አልኩት 600 አጋንንት ነን አሉና እውነቱን አውጣ ብዬ አጥብቄ ስይዘው 680 ብሎ ለፈለፈ፡፡ መጨረሻ ላይ 681ኛ ተልከስካሽ የዛር መንፈስ እንዳለ ገልጾ ከሰኔ 10 ቀን 2001 ዓ.ም ጀምሮ በተከታታይ በአራት ቀናት ውስጥ ተከፋፍሎ ወጣ» ብለዋል፡፡

እንደ እሳቸው አባባል ሰኔ 10 ቀን 2001 ዓ.ም 80ው ጥቁር ወፍ ሆኖ ሲወጣ፤ በነጋታው «593ቱ ጉን ዳን ሆኜ እወጣለሁ» ብሎ ጮኸ፤ ሲለቅ ወዲያውኑ ከየት መጣ ሳይባል አካባቢውን ጉንዳን ወረረው፡፡ በሦስተኛው ቀን ደግሞ ሰባት ሲወጣ ከሰባቱ አንዷ ብቻ ሴት ሆና ተገኘች፡፡ እሷም «ከውጭ ሀገር ነው የመጣነው፤ ሥራችን ተመሳሳይ ፆታዎችን ማጋባት ሲሆን በውጭው ዓለም አጥለቅልቀነው ወደ አፍሪካና ኢትዮጵያ በብዛት እየገባን ነው» ብላ ተናግራለች፡፡

«በመጀመሪያ ዋናውና አለቃው ' አጋንንት ጥቁር ወፍ ሆኖ ሲወጣ 600ው ሠራዊት ነኝ ብሎ ወጣ፡፡ አለ ቃውን አጋንንት» እንዴት ብለህ ነው የምትወጣው» ስለው እንደ አንበሳ አጓርቼ እወጣለሁ አለ፡፡ ልጅቷ እንደ አንበሳ እያጓራች ሳለ ጥቁር ወፍ በደም ተለውሶ ከሆዷ ውስጥ በአፏ ወጣ፤ ሲወጣም ልክ እንደ አየር ሞገድ ተወርውሮ ገንዳ ነገር ላይ አረፈ፡፡ ይህ እርኩስ መንፈስ ወፍ ሆኖ ሲወጣም ግፊት ስለነበረው እኔን ሁሉ ገፍትሮኛል፡፡ የወጣው ጥቁር ወፍ ከነሕይወቱ በመሆኑ ለተወሰነ ደቂቃ የማስካካት ድምፅ አሰምቷል፡፡ ለግማሽ ሰዓት ያህልም በሕይወት ቆይቶ ምእመናን ዐይተውታል፡፡ ድርጊቱ የሁሉንም መንገደኛ ቀልብ የሳበ ስለነበር መናፍቆች ሳይቀሩ ተመልክተው በእመቤታችን ድንቅ ተአምር ተገርመ ዋል፡፡ በተለይ አንድ ከነቀምት የመጣ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ በተአምሩ ተደንቆ ሲያለቅስ ዐይቻለሁ» በማለት ሊቀ ትጉኃን ስሙር አስረድተዋል፡፡

«አጋንንቱ መንበረ ማርያምን እንዴት እንደያዛት ስጠይቀው በተለያየ ምክንያት በይበልጥ በዛር ውላጅ ሲወርድ ሲዋረድ በዘር ሐረግ የመጣ እንደሆነ ለፍልፏል፡፡ ለ20 ዓመታት ያህል በሆዷና በማሕፀኗ ላይ ከፍተኛ ጫና በማድረስ ያሰቃያት እንደነበር ዘርዝሯል፡፡ በወር አበባዋ ጊዜ ምጥ እያበዛ ያሰቃያት እንደነበር ተናግሯል፡፡ እመቤቴ፣ እመቤቴ እያለች የእመቤታችን ማርያምን ስም እየጠራች አስቸገረችኝ እንጂ ሆዷን ኦፕራሲዮን አስደርጌ በሰበብ ልገድላት ነበር» ሲልም ተናግሯል ይላሉ፡፡

«ድርጊቱ በጣም የሚከብድ እና በእኔ ላይ የደረሰ ያህል ተሰማኝ፤ እኔም በሁኔታው በጣም ያዘንኩበትና ያለቀስኩበት ነው፡፡ ምክንያቱም ይህ ድርጊት በእኔ ላይ ተከስቶ ቢሆን ኖሮ ምን ልሆን እንደምችል ትንሽ ቆም ብዬ ማሰብ ጀመርኩ፡፡ እሷ ግን እጅግ በጣም ጠንካራ፣ በእምነቷ ጽኑ ነች፡፡ በእምነቷ ጽናት እግዚአብሔር ድንቅ ሥራውን ሠራላት፡፡ አሁን ሙሉ ለሙሉ ጤነኛ ነች ብለዋል፡፡ እርኩስ መንፈሱ አባቷን ሳይቀር ሌሎች ሰዎችንም ይዣለሁ ብሎ በመለፍለፍ ልጅቷ ቤት ድረስ በመሔድ መጥተው እንዲጠመቁ ተናግሬያለሁ» በማለት ሊቀ ትጉኃን ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም «የማስተላልፈው መልእክት አለ፡፡ እግዚአብሔር ብዙ ሥራ ይሠራል፤ እግዚአብሔር እኛ እንድንድን የማያደርግልን ነገር የለም፡፡ ከዚች እኅት ትልቅ ትምህርት አግኝተንበታል፤ የክርስቶስ ስልጣን ይህን ዐይነት የሚሠራ ከሆነ እኛ የት ነን? ብለን ማሰብ አለብን፡፡ ትንሽም ብትሆን እምነት ያስፈልጋል፡፡ ስለዚህ ወደ እግዚአብሔር በመቅረብ ጠበሉን፣ እምነቱን ልንጠጣ ይገባል፤ ሥጋና ደሙን ልንቀበል ያስፈልጋል፡፡ ይህ ከሆነ መዳን እንዳለ ማመን ይገባል» ሲሉ ሊቀ ትጉኃን ስሙር አሐዱ አስረድተዋል፡፡

በርግጥም መንበረ ማርያምና አጥማቂዋ ሊቀ ትጉኃን እንደገለጡት በየጠበሉ ቦታ ሲታይ በርኩስ መንፈስ በመተት፣ በዛር፣ በአጋንንትና በመሳሰሉት የተያዙ ሰዎች በእግዚአብሔር ኃይል ሲፈወሱ ማየት ጉድ ያሰኛል፡፡ ሰይጣን የምንፈራው ሳይሆን ታግለን የምናሸንፈው መሆኑን ማንም ሰው ሊያውቀውና ሊረዳው ይገባል፡፡ አውቆም በጾም በጸሎት እርምጃ ሊወሰድ ይገባል፡፡ የበለጠ ደግሞ መምህራን ሓላፊነት ወስደው ማስተማር ይኖርባቸዋል፡፡
ምንጭ፦ ማኀበረ ቅዱሳን ስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ
ተአምሩ የወጣበት የድረ ገጽ አድራሻ፦

ጥያቄ፦ "ቅዱስ ሲኖዶስ ስለ ማኀበረ ቅዱሳንስ ምን ወሰነ? የአዲስ አበባ ሀ/ስብከትስ ጉዳይ?"

ጥያቄ፦
Dear deje selam! Do you have any information about the today´s meeting of the Holy Synod? You have written about the transfering of Abune Samuel to development commission of EOTC. Could you answer the following my questions please?
1.Who is appointed as an archbishop to A.A Hagere Sebket?
2.What kind of decision is passed to solve the problem of Mahebere Kedusan?
It was one of the expected agendas.

መልስ፦

(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 29/2009)

የትናንትናው የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ስለ ማኀበረ ቅዱሳን ጉዳይ እንዲነጋገር ብፁዓን አባቶች ጠይቀው እንደነበር ታውቋል። በተለይም የመምሪያው ሃላፊ አባ ሰረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል በቅርቡ ለመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ሳቀር ግልባጭ በማድረግ ባሠራጩት አጉራ-ዘለል ደብዳቤ የተበሳጩት የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ ጉዳዩ እንዲመከርበት ጠይቀው እንደነበር ተጠቁሟል።

ይሁን እንጂ ቅ/ሲኖዶሱ በጊዜ እጥረት በመቸገሩ ምክንያት ይህንን አጀንዳ ሊመለከተው አልቻለም። ይልቁንም በመምሪያው ላይ የተሾሙት ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ መፍትሔ እንዲፈልጉለት ኃላፊነቱ ለርሳቸው ተሰጥቷል ተብሏል። እንደ ተባለው ከሆነ ብፁዕነታቸው የመምሪያውን ችግር በመቅረፍ ከማጀት ወደ አደባባይ ለወጣው “ጉድ” መፍትሔ ይሰጡታል።

በተያያዘ ዜና የዚህ ሁሉ እሰጥ-አገባ መነሻና መድረሻ የሆነው ሀብታሙ የአዲስ አበባ ሀገረ ስክበት ጉዳይ እንዴት እንደተቋጨ እርግጠኛ የሆነ መልስ የላትም ደጀ-ሰላም። ውላ-አድራ ግን ዘርዘር ያለ “ሪፖርታዥ” ለማቅረብ ትሞክራለች።
ቸር ወሬ ያሰማን አሜን

October 29, 2009

የአፍሪካ ወጣት ወንዶች ክርስቲያናዊ ማህበር (ወወክማ) ሕብረት ጉባኤ አዲስ አበባ ውስጥ ተጀመረ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 19 ቀን 2002 (ኢ.ዜ.አ) - ለአምስት ቀናት የሚቆይ የአፍሪካ ወጣት ወንዶች ክርስቲያናዊ ህብረት ጉባኤ አዲስ አበባ ውስጥ ዛሬ ተጀመረ፡፡ ኢትዮጵያ የወወክማን ጉባኤ ስታስተናግድ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው፡፡ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስብሰባ ማእከል የተጀመረውን ጉባኤ በንግግር የከፈቱት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ብጹህ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ወጣቶች የወደፊቱ ህይወታቸው ብሩህና ተስፋ የተሞላበት እንዲሆን በመቻቻልና እርስ በእርስ በመደጋገፍ መስራት ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡

ወጣቶች ነገ እንዲኖራቸው ለሚሹት መልካም ህይወት ዛሬ ላይ ቆም ብለው በእርጋታና በጥንቃቄ መራመድና ማሰብ እንዳለባቸው የመከሩት ብጹእነታቸው የአፍሪካ የወደፊት ተስፋዋ የተማሩና በስነ ምግባር የታነጹ ወጣት ዜጎቿ መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡

የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ አስቴር ማሞ እንዳሉት በኢትዮጵያ በሚካሄዱ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ የወጣቶችን አቅም ለማጎልበት እና ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ ለማስቻል መንግስት ብሄራዊ የወጣቶች ፖሊሲ ቀርጾ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ በወጣቶች ዙሪያ የቀረጻቸውን ፖሊሲዎች ተግባራዊ ለማድረግም ፖለቲካ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮችን የተመለከቱ የወጣቶች የልማት ማእቀፍ አዘጋጅቷል፡፡

ባለፉት ሁለት አመታት ብቻ እንኳ በተለያዩ መስኮች ከ72 ሺህ በላይ የወጣት ድርጅቶች በመላው አገሪቱ ተመስርተዋል፡፡
እንዲያም ሆኖ ወጣቶች ያሉባቸው ሁሉን አቀፍ ችግሮች በመንግስት ጥረት ብቻ ይፈታሉ ብለው እንደማያስቡ ገልጸዋል፡፡ እናም ሚኒስትሯ የሁሉም አካላት የተባበረ ጥረት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል፡፡

የኢትዮጵያ ወጣት ወንዶች ክርስቲያናዊ ማህበር /ወወክማ/ ፕሬዚዳንት ዶክተር ብርሃኑ ታደሰ በበኩላቸው ማህበሩ በ1952 በቀዳማዊ ሃይለ ስላሴ ዘመነ መንግስት መቋቋሙን ገልጸዋል፡፡ ማህበሩ በንጉሱ ጊዜ የሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች መልካም የሚባሉ እንደነበሩ ያስታወሱት ፕሬዚዳንቱ የደርግ መንግስት ማህበሩን ሙሉ በሙሉ እንዳይንቀሳቀስ በማገዱ የማህበሩ እንቅሰቃሴ ተቋርጦ መቆየቱን ገልጸዋል፡፡

ማህበሩ ዳግም ተመስርቶ መንቀሳቀስ የጀመረውም እ ኤ አ ከ1992 ጀምሮ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም 15 ሺህ አባላት እንዳሉት ተናግረዋል፡፡ በአራት ክልሎች ዘጠኝ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች አሉት፡፡
ፕሬዚዳንቱ እንዳሉት ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ የተጀመረው የአፍሪካ ወወክማ ህብረት ጉባኤ ዋነኛ አጀንዳም ወጣቱ ትውልድ የወደፊቱ አገር ተረካቢ በመሆኑ ከተመልካችነት ወደ ተዋናይነት እንዲሸጋገር ለማስቻል ሲሆን በየአገሩ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ በመገንዘብ መጪውን ጊዜ ለመቀየስ በሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ ለመምከር ነው፡፡
ወወክማ በህብረተሰቡ ውስጥ ዝቅተኛ ህይወት ያላቸውንና ጉዳት የደረሰባቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች በተለይም ወላጆቻቸውን በሞት ያጡ ህጻናትን፣ ሴተኛ አዳሪዎችን፣ ጎዳና ተዳዳሪዎችን ምንም አይነት የፖለቲካ፣ የሃይማኖትና የብሄር ልዩነት ሳያደርግ እገዛ በማድረግ ላይ እንደሆነም ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ ወወክማ 124 አባል አገራት ያሉት የአለም አቀፉ ወወክማዎች ህብረት አባል ነው፡፡

ደጀ ሰላማችን ሰላም እንድትሆን!


(ከብርሃኑ አ.)
ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ትኩረቷ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሆነ፣ ባለቤቷንና ማንነቷን ለመግለጽ አይን አፋር የሆነች ነገር ግን ከቤተክርስቲያኒቷ የውስጥ አዋቂዎች መረጃ የምታገኝ መሆኑ የማይጠረጠር ደጀ ሰላም የተሰኘች ብሎግ የብዙዎችን ትኩረት እየሳበች መጥታለች። ፈጥኖ ደራሽነቷና የሰማችውን ሳትደብቅ እንደወረደ ማቅረቧ በብዙዎች ዘንድ ተነባቢ አድርጓታል። ደጀ ሰላም የምትዘግበው ሁሉ እውነት ነው ለማለት ባያስደፍርም የቤተክርስቲያኒቷን ወቅታዊ ሁኔታዎች ለመረዳት ከየትኛውም ይልቅ ጥሩ የመረጃ ምንጭ መሆኗ አሌ የማይባል ሀቅ ነው። የሚገርመው መጽሐፍ “…ባለበት አሞሮች በዚያ ይሰበሰባሉ።” እንዲል ደጀ ሰላምን የሚከታተሉት የቤተክርስቲያኒቷ ልጆች ብቻ ሳይሆኑ መናፍቃን ጭምር መሆናቸው ነው። በተለይም መናፍቃኑ የሚያነሷቸውን ሃሳቦችና ቤተክርስቲያንን የሚነቅፉበትን ሁኔታ በሚገባ ለተመለከተ ቤተክርስቲያን ምን ያህል ጠላቶች እንደከበቧት ለመረዳት ይቻላል። ለዚህም ነው ለብዙ ዓመታት በዚህች ብሎግ ላይ “በአስተያየት” መልክ በተደጋጋሚ እየተሰጡ ያሉ ሀሳቦችን ስከታተል ቆይቼ ጥቂት ለማለት የፈለኩት።

የቤተክርስቲያናችን አብዛኛዎቹ አገልጋዮች ዘመናዊ ሥልጠና የሌላቸው በመሆኑና “የተማሩት” የቤተክርስቲያኒቷ ልጆች ደግሞ “ብእረ-አፈር” መሆናቸው በቤተክርስቲያናችን ላይ የተከፈተውን የሳይበር ጦርነት የዳዊትና የጐልያድ ግጥሚያ አስመስሎታል (ምንም እንኳን ውጊያው የእግዚአብሔር ቢሆንም)። ይኸንን ለማለት ያስደፈረኝ በደጀ ሰላም ላይ በመናፍቃኑ እየተሰራ ያለውን ሸፍጥ በመረዳቴ ነው።
የቤተክርስቲያን ጠላቶች ደጀ ሰላም ላይ ምን እየሰሩ ነው?
እውነተኛ ጠላትም የሚታወቀው በክፉ ቀን ነው። እውነትም በተፋፋመ ጦርነት መካከል ለወገን ጦር በሚዋጋው ወታደር ላይ ከኋላ አድብቶ ከሚተኩስ የበለጠ ምን ዓይነት ጠላት ይኖራል? በአሁኑ ወቅት መናፍቃን ይልቁንም በተሐድሶ ስም የተደራጁት እያደረጉ ያሉት ይኸንን ነው። ቤተክርስቲያናችን በተለያዩ ውስጣዊና ውስጣዊ ችግሮች በተጠመደችበት በዚህ ወቅት ካለማሰለስ የቤተክርስቲያንን የውስጥ ድክመት ሽፋን በማድረግ አላማቸውን በማስፈጸም ላይ ይገኛሉ። ደጀ ሰላም ላይ በያንዳንዱ ጉዳይ ላይ ሳያሰልሱ ሰፋ እና ዘርዘር ያለ “አስተያየት” የሚሰጡት እነዚህ መናፍቃን ሲያሻቸው የቤተክርስቲያኒቷን ትምህርት አጣመው የሚያቀርቡ፣ ሲያሻቸው ለእነሱ መሰሪ አላማ እንቅፋት የሆኑባቸውን እንደ ማህበረ ቅዱሳን ያሉ ስብስቦችን መልካም ተግባር ጥላሸት እየቀቡ በምእመናን ልቡና ጥርጣሬ በመዝራት፣ ጊዜያዊውን አስተዳደራዊ ችግሮች በማጋነን ምእመናንን በአባቶች ላይ ያላቸው አመለካከት እንዲቀየር የተለያዩ ፈጠራዎችን በመጨመር የሚጽፉ ብዙ መናፍቃንን አይተናል። አንዳንድ የቤተክርስቲያኒቷ ልጆች መናፍቃኑ ለሚያነሷቸው ጉዳዮች ምላሽ ለመስጠት የሚያደርጉት ጥረት የሚደነቅና መንፈሳዊ ተግባር ቢሆንም እነርሱ አውቀውና አልመው የሚያደርጉት ከመሆኑ አንጻር አደብ የሚያስገዛቸው አይመስልም። ምክንያቱም እነርሱ የተላኩበት አላማ ለማስፈጸም እንጂ የተሳሳቱት ነገር ካለ ተረድተው ለመመለስ የተዘጋጀ ልቡና የላቸውም። ይልቁንም ብዙዎች የዋሃንን ግራ ሊያጋባ የሚችል የተዛባ አስተያየታቸውን ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ይዘራሉ። አላማቸው አንድና አንድ ሲሆን ይኸውም የቤተክርስቲያኒቷን ትምህርትና ሥርዓት መቃወም፣ ቤተክርስቲያናችንን ታሪክ አልባና ቅርስ አልባ በማድረግ ባለማዊነት አስተሳሰብ የተጠለፈች ቤተክርስቲያን እንድትሆንና በስተመጨረሻም እንደ ምእራባዊያኑ ሀገራችንን እምነት አልባ ማድረግ ነው።
ምን ማድረግ ይቻላል?
የቤተክርስቲያናችን ወቅታዊ ሁኔታዎች ልንረዳበትና ችግሮች ሲኖሩ ጠቃሚ ውይይቶች ልናደርግበት የምንችልባቸው እንደ ደጀ ሰላም ያሉ የውይይት መድረኮች በመናፍቃኑ የጥፋት አጀንዳ መጠለፍ የለባቸው። በመሆኑም ፦
1. የቤተክርስቲያንን መሠረታዊ ትምህርት ለማዛባት የሚሞክሩ አስተያየቶች በብሎጓ ላይ እንዳይስተናገዱ በአዘጋጆቹ ጥረት ቢደረግ፤ ይህንንም በማድረግ መናፍቃኑ ለሚሰጡት አስተያየት ወይም የተዛባ መረጃ ማስተባበያ ለመስጠት የሚባክነውን የውይይት ጊዜአችንንና ሃሳባችንን ስለ ቤተክርስቲያናችን ጉዳይ ተገቢ ውይይት ለማድረግ እንጠቀምበታለን፤
2. ምንም እንኳን የቤተክርስቲያኒቷ አስተዳደራዊ ችግሮች በአደባባይ ጭምር ውይይት ሊደረግባቸው ቢገባም ተጨባጭ መረጃዎች ላይ ያልተመሰረቱ አሉቧልታዎችን በአስተያየት ሰጪዎች ሲሰጡ ማገድ፤
3. ስለቤተክርስቲያናችን ችግሮች ስንወያይ ግለሰቦች ላይ ከማተኮር ይልቅ የችግሩ ምንጭ እና መፍትሔዎች ላይ የሚያተኩር ውይይቶችን ማበረታታት፤
4. በብሎጉ ላይ የሚደረጉ ውይይቶች ሰበብ እየፈለግንና እየተነቃቀፍን እርስ በእርስ የምንለያይበት ሳይሆን ሁሉንም የቤተክርስቲያን ልጆች በአንድነት የሚያሳትፍ እንዲሆን ጥረት ማድረግ፤ ለዚህም ማንኛውንም ዓይነት አባቶችንም ሆነ ምእመናንን ለመከፋፈል የሚሞክሩ ዘገባዎችን፣ አስተያየቶችን ያለመቀበል፤
በአጠቃላይ ደጀ ሰላማችን ሰላም እንድትሆንና የመናፍቃን መጠቀሚያ እንዳትሆን ሁላችንም በንቃት ልንጠብቃት ይገባል።

++++++++++
ደጀ ሰላም
ግለሰቦች ለሚጽፏቸው ጽሑፎች “ደጀ-ሰላም” ኃላፊነቱን አትወስድም። ደጀ-ሰላም ራሷ ያዘጋጀቻቸውን ጽሑፎች “ደጀ-ሰላም” ብላ ትጠቅሳለች። ኃላፊነቱን የምትወስደው ለነዚያ ጽሑፎች ብቻ ነው።
ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን

የአቡነ ሳሙኤል ልማት ኮሚሽን ላይ መሾም ምን አንድምታ አለው?

(ደጀ ሰላም Oct 28/2009)፦

የዛሬ ረቡዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ውሎ ምን ይመስላል? ቅዱስ ሲኖዶስ በዛሬው ውሎው በዐቢይነት በብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ምደባ ዙሪያ የተጀመረውንና በእንጥጥል የተላለፈውን አጀንዳ ከዳር በማድረስ ብፁዕነታቸውን ለልማት ኮሚሽን ኃላፊ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል። እስካሁን ቦታውን ይዘው የነበሩት የፓትርያርኩ የረዥም ጊዜ ቀኝ-እጅ አቡነ ገሪማ ነበሩ።

የጥቅምት የቅ/ሲኖዶስ ጉባዔን አብዛኛ ሰዓት በወሰደው የአቡነ ሳሙኤል ምደጋ ጉዳይ ቅዱስ ፓትርያርኩ ለብቻቸው፣ ሌሎች አባቶች በአንድነት የቆሙ ሲሆን ፓትርያርኩ ግን በደፈናው “አይሆንም፣ አይቻልም፤ አይቻልም ብያለኹ” በማለታቸው ብቻ ውሳኔ ሳያርፍበት ቆይቷል። ቅዱስ ፓትርያርኩ በመጨረሻ አንስተዋል እንደተባለው ከሆነ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል መቐለ ካልሄዱ የቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ኃላፊ እንዲሆኑ ሐሳብ አቅርበው ነበር። በአዲስ አበባ ዛሬ እስከ 10 ሰዓት (4ፒ.ኤም) ድረስ በተካሄደው ስብሰባ ማጠቃለያ አቡነ ሳሙኤል የልማት ኮሚሽንን ቦታ መያዛቸው ተረጋግጧል። ልማት ኮሚሽን ከ1972 እ.ኤ.አ ጀምሮ የተለያዩ ምግባረ ሰናይ ተግባሮች የሚፈጸም የቤተ ክርስቲያናችን ትልቅ ተቋም ነው። ገጠር ልማት፣ ውሃ ማውጣት፣ በግል ንጽሕና፣ በኤች.አይ.ቪ ኤይድስ፣ በስደተኞች፣ በጾታና ዕድገት፣ በሰላም ዙሪያ እንዲሁም አህጉረ ስብከትና አጥቢያዎች ዙሪያ ፕሮጄክቶችን በመቅረጽ የሚሠራ ትልቅ ድርጅት ነው። ልማት ኮሚሽን ይህንን ሁሉ ሥራ የሚሠራ ይሁን እንጂ የሚታማበትና የሚወቀስበት ብዙ ጉዳዮች አሉ።

የመጀመሪያው ሠራተኞቹ ቤተ ክርስቲያኒቱን የሚቃወሙ ፕሮቴስታንቶች ጭምር መሆናቸው ነው። ስለዚህ ጉዳይ በተለያዩ ጊዜያት የተጠየቁ ኮሚሽነሮች “ዋናው ሥራቸው ነው” እያሉ ኢመልሱ ነበር። የቤተ ክርስቲያኒቱን ደሞዝ እየበሉ ቤተ ክርስቲያኒቱን የሚሰድቡት እነዚህ ሰዎች ለምን እንደዚያ እንዲያደርጉ እንደሚፈቀድላቸው ለብዙ ኦርቶዶክሳውያን የሚገርም ጉዳይ ነበር።

ሁለተኛው የልማት ኮሚሽን ችግር ገንዘቡ በጥንቃቄ ለታለመለት ሥራ ብቻ እንደማይውል መታማቱ ነው። በዚህ ጉዳይ ከሚታሙት ሰዎች መካከል ደግሞ ቅዱስ ፓትርያርኩ አንደኛው ናቸው። ፓትርያርኩ ለገንዘብ ብክነቱ አስተዋጽዖ አድርገዋል የሚባሉት “የሥጋ ዘመዶቻቸውን” ያለ ብቃታቸው በመመደባቸው ነው። ለዚህ ዓይነቱ ሕገ ወጥነት ሌላው አስተዋጽዖ የሚያደርጉት በበላይ ጠባቂነት የሚሾሙ እንደ አቡነ ገሪማ ያሉ ጳጳሳት ናቸው። የአቡነ ሳሙኤል በቦታው መሾም ትልቅ አንድምታ የሚኖረው ከዚህ አንጻር ነው። በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ላይ እንደታዩት ከሆነ ለዚህ ዓይነቱ የሙስና ተግባር አይመቹም፣ የሥራ ሰውም ናቸው፣ ለቤተ ክርስቲያናቸውም ፍቅር አላቸው።

ቅ/ሲኖዶስ በዚህ የጥቅምት ጉባዔው 17 አጀንዳዎች ላይ የተወያየ ሲሆን ነገ ማጠቃለያ ተደርጎ ለጋዜጠኞች መግለጫ ከመሰጠቱ በፊትም ሌሎች “ጥቃቅን” ጉዳዮች ላይ ሊወያይ ይችላል።

October 28, 2009

ስለ ቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ የEthiopia zare ሪፖርታዥ፦ “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አባቶች ውዝግብ ተቋጨ”

(ደጀ ሰላም Oct 28/2009)፦ ከዚህ በታች የቀረበው የዛሬ Oct 28/2009 የEthiopiazare ሪፖርታዥ ነው። መልካም ንባብ።
ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን
+++++
  • አቡነ ሳሙኤል የልማትና ተራድኦ ኮሚሽን ስልጣን ፀደቀላቸው
Ethiopia zare (ረቡዕ ጥቅምት 18 ቀን 2002 ዓ.ም. October 28, 2009)፦
አቡነ ሳሙኤል እጣ የወጣላቸው የልማትና ተራድኦ ኮሚሽን ተቋም ኃላፊና በመሆን እንዲሰሩ ዛሬ ረቡዕ ጥቅምት 18 ቀን 2002 ዓ.ም የፀደቀላቸው መሆኑን የአዲስ አበባ ምንጮቻችን ገለጹ።

ፓትሪያርክ አቡነ ጳውሎስ በሌሎች የቅዱስ ሲኖዶስ ጳጳሳት ላይ በመንግሥት ሰዎች የታገዘ ተጽዕኖአቸውን በማሳረፍ ላይ ቢሆንም ቅዳሜ ጥቅምት 14 ቀን 2000 ዓ.ም በአጠቃላይ ስምምነት ያበቃል የተባለለት የሲኖዶሱ ጉባኤ ለሰኞ ጥቅምት 16 ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ የተያዘለት ጉባኤ በአባ ጳውሎስ ዕምቢኝ ባይነት በዕለቱም መፍትሔ አልተገኘለትም።


የቤተክህነት ምንጮች ውዝግቡ እልባት ሊያገኝ ያልቻለው “አቡነ ጳውሎስ የአባ ሳሙኤልን የሥራ ምደባ እኔ ባልኩት መሠረት ይፈጸም፤ የሲኖዶሱ አባላት አባ ሳሙኤል ዕጣ በወጣላቸው መሠረት የልማትና ተራድኦ ኮሚሽን ተቋም ሃላፊ ሆነው ይቀመጡ መባሉን አልቀበልም በማለታቸው ነበር። ይልቁንም አቡነ ጢሞቲዎስን ጨምሮ ሌሎች ጳጳሳትን በመዝለፍና በማንጓጠጣቸውም ምክንያት ነው” ብለዋል።

ፓትሪያርክ አቡነ ጳውሎስ አባ ሳሙኤልን ከአዲስ አበባ ወደ መቀሌ አርቀው በመወርወር በእሳቸው አስተዳደር ዙሪያ ተነስቶ የነበረውን ጥያቄ በሙሉ ለማዳፈን የሚፈልጉ ሲሆን፤ ከእሳቸው በተቃራኒ ወገን የቆሙ የሲኖዶሱ አባቶች ደግሞ የሥራ ምደባ በሲኖዶሱ ውሳኔና በተመደበው ፈቃድ ወይም በዕጣ መሆን ይገባዋል እንጂ አባ ጳውሎስ በሚሰጡትና ሊታጠፍ አይገባውም እያሉ በአምባገነንነት በሚሞግቱበት ትዕዛዝ መሆን የለበትም” የሚለውን አቋም ይዘዋል።

ብዙሃኑ ጳጳሳት ከአባ ሳሙኤል ወገን ሆነው በአዲስ አባባና በአቅራቢያው ወይም በአሰበተፈሪ ይመደቡ ይህም ካልሆነ በልማትና ተራድኦ ኮሚሽን ውስጥ እንዲሠሩ ይሁን” የሚል ሃሳብ አቅርበው ነበር “ማንም ሊያስፈራራኝና ሊዝትብኝ አይችልም……” ያሉት አባ ጳውሎስ “ ተፈፃሚ መሆን ያለበት የእኔ ሃሳብ ብቻ ነው” በሚለው አቋማቸው ጸንተው እንደነበር ታውቋል።

ከእነ አባ ሳሙኤል ጋር የተጣሉበትን በቤተሰብ የመሥራት ችግር ጥያቄ ለማለዘብ ዋንኛ ተቀናቃኛቸውን ወደ መቀሌ ለማዝመት፣ የአዲስ አበባንም ሀገረስብከት በ5 ቦታ ለመሸንሸን ያላቸውን ፍላጎት ከጥቅምት 11 ቀን 2002 ዓ.ም ጀምሮ በተደጋጋሚ አንፀባርቀዋል።

አቡነ ሳሙኤል በመግቢያ ንግግራቸው ብዙሀን አባቶችን በሚማርክ መልኩና ታላቅ አባት መሆናቸውን በሚያስመሰክር ሁኔታ ጉባኤውን ጥፋት አጥፍተው እንደሆነ ይቅርታ በመጠየቅና ራሳቸውን ዝቅ በማድረግ የነበረ ሲሆን ብዙ አባቶችም የአቡኑን ወነመቀሌ መሄድ ተቃውመው እንደነበር ለመረዳት ችለናል። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ህግና ደንብ መሰረት የአባቶች ሹመት በእጣ ሳይሆን በፈቃዳቸው በሲኖዶሱ ውሳኔ እንዲሆን ያዛል።

ስለ ቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ የሪፖርተር ጋዜጣ ሪፖርታዥ:- "የቅዱስ ሲኖዶሱ ጉባዔ ያለስምምነት ተበተነ"


(ደጀ ሰላም Oct 28/2009)፦ ከዚህ በታች የቀረበው የዛሬ Oct 28/2009 የሪፖርተር ጋዜጣ ሪፖርታዥ ነው። ስለ ቅ/ሲኖዶስ ጉባዔ ጥሩ ተደርጎ ማጠቃለያ የተሠራበት ከመሆኑ አንጻር “ደጀ-ሰላም” እስካሁን ሳታሰልስ ስትዘግብ ለቆየችው ማጠናከሪያ  ይሆናል። መልካም ንባብ።
ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን
+++++++


የቅዱስ ሲኖዶሱ ጉባዔ ያለስምምነት ተበተነ
ልዩነት የፈጠረው የአቡነ ሳሙኤል ምደባ ጉዳይ ነው

በታምሩ ጽጌ

(ሪፖርተር፤ Oct 28/2009)፦
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ጥቅምት 11 ቀን 2002 ዓ.ም. በእርቅና በጸሎት ተጀምሮ ጥቅምት 15 ቀን 2002 ዓ.ም. ያለ ስምምነት መበተኑን ከተሳታፊዎቹ አንዳንድ አባቶች በተለይ ለሪፖርተር ጋዜጣ ገለጹ፡፡


ጉባኤው ያለ ስምምነት የተበተነበትን ምክንያት አባቶቹ ሲያስረዱ፣ ለጉባኤው ቀርበው የነበሩት 18 አጀንዳዎች ላይ ውይይት ተደርጐ በሰላም ካጠናቀቀ በኋላ፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ሳሙኤልን በእጣ እንዲመደቡ፣ በእጣው ውስጥም ከተካተቱት ትንሣኤ ማተሚያ ቤት፣ የሕፃናት ጉዳይ ድርጅት፣ የልማትና ተራድዖ ኮሚሽን እና በመንበረ ፓትርያርክ ትምህርትና ማሰልጠኛ ክፍል መካከል፣ የቤተ ክርስቲያኗ የልማትና ተራድዖ ኮሚሽን በመውጣቱና ቅዱስ ፓትርያርኩ በመቃወማቸው ነው፡፡

የአቡነ ሳሙኤልን አዲስ ምደባ በተመለከተ ከጥቅምት 14 ቀን 2002 ዓ.ም. ጀምሮ አዲስ አጀንዳ የቀረበ መሆኑን የገለጹት አባቶች፤ ”የት ይመደቡ” ለሚለው ጥያቄ ቅዱስ ፓትርያርኩ፤ መቀሌ እንዲመደቡ የመጀመሪያ ጥቆማ ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡

ቀደም ብሎ ከግንቦት ወር እስከ ሐምሌ 2001 ዓ.ም. በነበረው ውዝግብ የተነሣ በትግራይ ሕዝብ በኩል ተቀባይነት ሊያገኙ ስለማይችሉ፣ በልማትና ተራድኦ ኮሚሽን ቢመደቡ የተሻለ እንደሚሆን አንድ የሲኖዶሱ አባል ሌላ ጥቆማ መስጠታቸውን አባቶቹ ገልጸዋል፡፡ “እርሳቸው ረአቡነ ሣሙኤልሪ ከውጭ ይሁኑና ምደባውን በተመለከተ እኛ እንነጋገር” በሚል ሌላ አባል ሐሳብ ቢያቀርቡም ምላሽ አለማግኘታቸውን ተናግረዋል፡፡

በሀገረ ስብከቱ ለረጅም ዓመታት መሥራታቸውን፣ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ትዕዛዝ ብዙ የማይረሱ ሥራዎችን መሥራታቸውንና ብዙ ፈተናዎችንም ማለፋቸውን በመግለጽ ንግግራቸውን የጀመሩት አቡነ ሳሙኤል፤ በአንድ ቤት ታምቀው ይሠሩ ለነበሩ የቤተ ክርስቲያኒቱ አገልጋዮች ባሠሩት ሕንፃ ውስጥ በመመደብ፣ የሀገረ ስብከቱን ሥራ ቀና እንዲሆን ማድረጋቸውን ተናግረው፤ “ጥፋተኛ ተብዬ ከሀገረ ስብከቱ ብወጣም ደስተኛ ነኝ፤ አይከፋኝም” ማለታቸውን አባቶቹ ገልጸዋል፡፡

“አባቶች ባዘዙኝ ቦታ ለመሥራት ፈቃደኛ ነኝ፡፡ አባታችንና አባቶቻችን ያሳዘንኳችሁ ካለ ይቅር በሉኝ” በማለት እርቅ ወርዶ እንደነበር አንዳንድ የጉባኤው ተካፋይ አባቶች አስታውሰዋል፡፡

አቡነ ሳሙኤል ተናግረው ሲያበቁ፣ ቅዱስ ፓትርያርኩ “መቀሌ መድቤዎታለሁ” ሲሉ ሌሎቹ ሁለት የሲኖዶሱ አባሎች ደግሞ የሀገረ ስብከቱን ፋይናንስ በሚያጣራው ኮሚቴ በየጊዜው ለቃለ ምልልስ ስለሚፈለጉ አሰበ ተፈሪ ወይም በአዲስ አበባ ዙሪያ ቢመደቡ የተሻለ እንደሚሆን ሐሳብ አቅርበው እንደነበር ተሳታፊ አባቶች ተናግረዋል፡፡

ቅዱስ ፓትርያርኩ ስለተባሉትም ሆነ ስለተጠቆሙት ቦታዎች ምንም ምላሽ ባለመስጠታቸው፤ የሲኖዶሱ አባላት የተለያዩና ጠንካራ አስተያየቶች መሰንዘራቸውን ተሳታፊ አባቶች ገልጸዋል፡፡

ቅዱስ ሲኖዶሱ እንደሚያዘው፣ አንድ አባት የሚመደቡት በፈቃዳቸው እንጂ በግድ መሆን እንደሌለበት በመግለፅ ተጽዕኖ መደረግ እንደሌለበት የጉባኤው አባላት አስተያየት መስጠታቸውን ተሳታፊ አባቶች ተናግረዋል፡፡

“እኔ እዚህ የመጣሁበትንና የተወለድኩበትን ዕለት ረግሜዋለሁ” በማለት አስተያየት በሰጡት አንድ አባት በሰጡት አስተያየት፣ ሦስት አባቶች ተመርጠው ቦታውን አጥንተው እንዲያቀርቡ ሐሳብ ማቅረባቸውን ታውቋል፡፡

ቅዱስ ፓትርያርኩ ስብሰባው በአግባብና በስርዓት እንዲመራ እንዲያደርጉ አባላቱ መጠየቃቸውንና አንዳንዶቹም ይቅርታ በመጠየቅ አቋርጠው በመውጣት፣ ከሰዓትም ሳይመለሱ መቅረታቸውን ተሳታፊ አባቶች ገልጸዋል፡፡

አንዳንድ የሲኖዶሱ አባላት በሰጡት አስተያየት፣ ቅዱስ ሲኖዶሱ ለማኝና ተለማኝ መሆን እንደሌለበት ተናግረው፣ “የሰላም ሲኖዶስ ከሆነ ለምን በሰላም አንፈታውም” ሲሉ ቅዱስ ፓትርያርኩ “ያላለቀ ጉዳይ አለ፡፡ ከአንድ ወር በኋላ ቅዱስ ሲኖዶሱ ይሰበሰባል፤ ወይም ይደርና እንነጋገር” በማለታቸው ለጥቅምት 15 ቀን 2002 ዓ.ም. መቀጠሩን ተሳታፊ አባቶች ተናግረዋል፡፡

ለጥቅምት 16 ቀን 2002 ዓ.ም. በይደር የተቀጠረው ጉባኤ በጸሎት ከተከፈተ በኋላ የአቡነ ሳሙኤል ጉዳይ ሦስት ሰዎች ተመርጠውና አጥንተው እንዲመጡ እንዲደረግ የሚል አስተያየት ሲነሳ፤ ቅዱስ ፓትርያርኩ “ወደመረጥኩት ሀገረ ስብከት ቢሄዱ የተመረጠ ነው” ማለታቸውን ተሳታፊ አባቶች ገልጸዋል፡፡

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አስተዳደር ጉዳይንና የፋይናንስ ኦዲት ሪፖርት እንዲያቀርብ የተሰየመው ኮሚቴ፤ ..የፋይናንስ ኦዲት ሪፖርት እንዳልደረሰለትና ተጨማሪ ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቆ አስተዳደርን በተመለከተ ባቀረበው ሪፖርት ችግሩ የቤተ ክርስቲያኗ መሆኑን በመናገር የምትመራበት ስርዓት እንደሌላትና ሕግም ቢኖር እርስ በርሱ የሚጋጭ መሆኑን በገለጸው መሠረት አቡነ ሳሙኤል አስተያየት መስጠታቸውን ተሳታፊ አባቶች ተናግረዋል፡፡

አቡነ ሳሙኤል በሰጡት አስተያየት፤ አጣሪ ኮሚቴው ስለ ሀገረ ስብከቱ አስተዳደር ጉዳይ ባደረገው ሪፖርት ችግሩ በሙሉ የቤተ ክርስቲያኗ መሆኑን እንጂ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ችግር ባለመሆኑና ጥፋተኛ ስላልሆኑ ወደ ሥራቸው እንዲመልሷቸው በድጋሚ መጠየቃቸውን ተሳታፊ አባቶች ገልጸዋል፡፡

በሰላማዊ መንገድ ቅዱስ ሲኖዶሱ በፈለገው ቦታ እንዲመድባቸው በድጋሚ አስታውሰው፤ “በቀድሞ ቦታዬም ቢሆን ችግር ስለሌለብኝ በሕግም ቢሆን እገባለሁ” ብለው ከተናገሩ በኋላ፣ በሁሉም የሲኖዶሱ አባላት ዘንድ ለጥቂት ደቂቃዎች ያህል ዝምታ ሰፍኖ እንደነበር ተሳታፊ አባቶች ተናግረዋል፡፡

እሑድ ጥቅምት 15 ቀን 2002 ዓ.ም. ከሰዓት በኋላ ባደረጉት ስብሰባ ቅዱስ ፓትርያርኩ ስብሰባውን ሲጀምሩ እንደተናገሩት፤ በግንቦት 2001 ዓ.ም. ስብሰባ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በአምስት ይከፈል ሲባሉ ረአቡነ ሳሙኤልሪ አሻፈረኝ ማለታቸውን ነገር ግን ከቦታቸው ይነሱ አለማለታቸውን፤ እራሳቸው ባመጡት ጣጣ እዚህ መድረሳቸውን፣ በአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ (ቪ.ኦ.ኤ) “ፓትርያርኩ ለ17 ዓመታት ምንም አልሰሩም” በማለት ስም የሚያጠፉ አንዳንድ አባቶች መኖራቸውን በመግለጽ “አታስፈራሩኝ፤ ዛቻ ለማንም አይጠቅምም” በማለት መናገራቸውን ተሳታፊ አባቶች ተናግረዋል፡፡

ከብዙ ልመናና አስተያየት በኋላ ሦስት አባቶች (አቡነ ኤልሳዕ፣ አቡነ አትናቴዎስና አቡነ ፊልጶስ) ተመርጠው አቡነ ሳሙኤል ሊመደቡ ይችላሉ ያሏቸው ቦታዎችን መምረጣቸውን የተናገሩት ተሳታፊ አባቶች፤ አራት ቦታዎች (ትንሣኤ ማተሚያ ቤት፣ የሕፃናት ጉዳይ ድርጅት፣ የልማት ኮሚሽንና የመንበረ ፓትርያርክ ትምርትና ስልጠና ክፍልን) መምረጣቸውን ተናግረዋል፡፡

ከቃለ አዋዲ ውጭ በእጣ እንዲመደቡ ቢደረግም ዕጣው ሲወጣ “ልማት ኮሚሽን” የሚለው በመውጣቱ ቅዱስ ፓትርያርኩ “በፊትም ብያለሁ፤ አሁንም አልስማማም” በማለታቸው፣ የተወሰኑ የሲኖዶሱ አባላት ጉባኤውን ጥለው በመውጣታቸው ጉባኤው ያለ ውጤት መበተኑንና ድርጊቱም ብዙ አባቶችን ያሳዘነ መሆኑን ተሳታፊ አባቶች ገልጸዋል፡፡

ለቅዳሜ ጥቅምት 14 ቀን 2002 ዓ.ም. 5፡00 ሰዓት ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል በሚል ጋዜጠኞቹ ተጠርተው የነበረ ቢሆንም “ይቅርታ ልጆቼ ስብሰባው ስላላለቀልን ለነገ (እሑድ) 9፡00 ሰዓት ተመለሱ” በማለት ቅዱስ ፓትርያርኩ አሰናብተው፣ በማግስቱ ጋዜጠኞች በተባሉበት ሰዓት ደርሰው እስከ 11፡30 ከቆዩ በኋላ “ይቅርታ ስብሰባው ለረቡዕ ስለሚቀጥል ሐሙስ ጥቅምት 19 ቀን 2002 ዓ.ም. መግለጫው ይሰጣል” በሚል አቡነ ገሪማ (የተራድኦ ልማት ኮሚሽኑ የበላይ ጠባቂ ሊቀ ጳጳስ) ጋዜጠኞቹን በድጋሚ አሰናብተዋል፡፡

ቅዱስ ሲኖዶሰ ያቋረጠውን ስብሰባ በዛሬው ዕለት ይቀጥላል ተብሎ እንደሚገመት ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች አረጋግጠዋል፡፡
+++++++++

ደጀ ሰላም
በቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ዜናዎችን፣ አስተያየቶችን፣ ጥያቄዎችን፣ መልሶችን የምታወጣ የጡመራ-መድረክ ናት። ግለሰቦች ለሚጽፏቸው ጽሑፎች “ደጀ-ሰላም” ኃላፊነቱን አትወስድም። ደጀ-ሰላም ራሷ ያዘጋጀቻቸውን ጽሑፎች “ደጀ-ሰላም” ብላ ትጠቅሳለች። ኃላፊነቱን የምትወስደው ለነዚያ ጽሑፎች ብቻ ነው።
ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን

October 27, 2009

ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ ሳይሰበሰብ ዋለ፤ ነገ ይቀጥል ይሆናል

• የአቡነ ሳሙኤልን የሥራ ሁኔታ እንዲያጣራ የተቋቋመው ኮሚቴ “ጥፋት” አላገኘባቸውም፤
• አባ ሰረቀ የተቃውሞ “ጋዜጣ” እያዘጋጁ ነው፣
(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 27/2009)፦ ካለፈው ሐሙስ ጀምሮ ሲካሄድ የሰነበተው የቅ/ሲኖዶስ የጥቅምት ጉባዔ ዛሬ ሳይሰበሰብ የዋለ ሲሆን ምክንያቱ ቅዱስ ፓትርያርኩ ለሥራ ጉዳይ ወደ አኩሱም በማቅናታቸው መሆኑ ታውቋል። ጉባዔው ነገ በድጋሚ በመሰብሰብ ወሳኝ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል። ባለፉት ጥቂት ዓመታት አዲስ አበባን በሥራ አስኪያጅነት እና በሊቀ ጳጳስነት ባስተዳደሩበት ጊዜ “የሚያስመሰግን ሥራ ሠርተዋል” የሚባሉት የብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ጉዳይ ገና እልባት አላገኘም። ቅዱስነታቸው አዲስ አበባ የተመለሱ ስለሆነ ስብሰባው ነገ ይቀጥል ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።


በተያያዘ ዜና የብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ሀገረ ስብከት በሆነው አዲስ አበባ ተፈጽሟል የተባለውንና ከሀ/ስብከታቸው እንዲነሡ ያስከሰሳቸውን የ“ሙስናና የአስተዳደር ችግር” እንዲያጣራ ባለፈው ግንቦት ወር 2002 ዓ.ም ማግስት የተቋቋመው ኮሚቴ ሊቀ ጳጳሱን ከተሰነዘሩባቸው “የጥፋት አስተያየቶች” ነጸ አውጥቷቸዋል። ብፁዕነታቸው ጥፋት ባልተገኘባቸው ሁኔታ ይልቁንም በኮሚቴው ማጣራት “አስመስጋኝ” ሥራ ሠርተው ሳለ ከሀ/ስብከታቸው እንዲነሱ መወሰኑ አስገራሚ ሆኗል።

በሌላ ተያያዥ ጉዳይ ከሰንበት ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ፈላጭ ቆራጭነታቸው ጋብ እንዲሉ የበላይ ሊቀ ጳጳስ የተሾመባቸው አባ ሰረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል ይህንና ተያያዥ ጉዳዮችን በተመለከተ ያላቸውን ተቃውሞ ለመግለጽ አንድ ጋዜጣ በማዘጋጀት ላይ መሆናቸው ታውቋል። በመምሪያው ስም ያሳትሙታል ተብሰሎ በሚጠበቀው በዚህ ጋዜጣ ላይ ቅ/ሲኖዶስ አባላት አባቶችን ጨምሮ ሌሎችንም ይጠቅሱበታል ተብሎ ይጠበቃል። አባ ሰረቀ በቦታቸው ያላቸው ሥልጣን ከቀነሰ “የልብ የልባቸውን” ተናግረው በፊት ወደነበሩበት ወደ አሜሪካ ሳይሄዱ አይቀርም የሚል አስተያየት አለ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ዓለም አቀፋዊ የምእመናን ማሕበር መግለጫ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ዓለም አቀፋዊ የምእመናን ማሕበር መግለጫ
WORLD ASSOCIATION OF PARISHIONERS OF THE ETHIOPIAN ORTHODOX TEWAHEDO CHURCH
10107 Branwood Circle, Dallas, TX 75243, U.S.A. WWW.eotcipc.org
Tel: (469)855 8488 (214)697 8928; (813)312 1502; e-mailmiimenan@yahoo.com
መስከረም 18 ቀን 2002 ዓ/ም

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ፤ አሐዱ አምላክ፤ አሜን።
ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
ቅዱስ ሲኖዶስ፤
ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ
ለብፁዓን የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት
አዲስ አበባ።

ጉዳዩ፤ በቤተክርስቲያናችን፤ ሰላም፤ አንድነትና ዘላቂ እድገት እንዲገኝ ስለ ማድረግ፤

በመጀመሪያ፤ ለቅዱስ ሲኖዶሱ ያለንን እጅግ ከፍ ያለ አክብሮት እየገለጽን፤ ለብፁዓን የቅዱስ ሲኖዶሱ አባላት
የእግዚአብሔር ሰላምታችንን በትሕትና እናቀርባለን።
እኛ በዓለሙ ሁሉ ተሰራጭተን የምንገኝ ተባባሪዎች የቤተክርስቲያናችን ምእመናን በቅርቡ በቅዱስ ሲኖዶሱ
አባላት መሀል በተከሰተው ውዝግብና ባጋጠሙት ድርጊቶች እጅግ ተሳቅቀናል፤ አዝነናልም። ሆኖም፤ በጥቅምት
ወር 2002 ዓ/ም የቅዱስ ሲኖዶሱ ስብሰባ ስለሚከናወን ጉባኤው ለቤተክርስቲያናችን የተሙዋላ ሰላምና አንድነት
እንዲያስገኝና የዘለቄታ እድገት የሚያመቻች ስልት እንዲተልም የበኩላችንን ግንዛቤና ማሳሰቢያ ከዚህ በታች
በአክብሮት እናቀርባለን። የቅዱስ ሲኖዶሱ ጉባኤም በቤተክርስቲያናችን ላይ ተጋርጠው የሚገኙትን እጅግ ከባድ
ችግሮች ለማስወገድ ተገቢ የሆኑ መፍትሔዎችን እንደሚያስገኝ ያለንን ፅኑ ተስፋ በቅድሚያ እንገልጻለን። ስለዚህ፤
ቅዱስ ሲኖዶሱ፤ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት፤ ከዚህ በታች የምናቀርባቸውን ሀሳቦች በጥሞና ተመልክቶ ቅድስት
ቤተክርስቲያናችንን ለዘለቄታ በሚያጠናክርና በሚያስፋፋ ስልት ተገቢውን ውሳኔ እንዲያደርግ እንማጸናለን።
1. ስለ ቅዱስ ሲኖዶሱ ሥልጣን፤
እንደሚታወቀው፤ በ1991 ዓ/ም በቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ የተደነገገው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
ሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ 5 የቅዱስ ሲኖዶስን ሥልጣን እንደሚከተለው በግልጽ አስቀምጦታል፤
“1. በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው ቅ/ሲኖዶስ የመንበረ ሐዋርያት ወራሽ ስለሆነ በቤተ ክርስቲያኒቱ
የመጨረሻው ከፍተኛው ሥልጣን ባለቤት ነው።
2. ከማንኛውም የቤተ ክርስቲያኒቱ የሥልጣን መዋቅር ሁሉ የበላይ አካል ቅዱስ ሲኖዶስ ስለሆነ
ሕጎችን፤ ልዩ ልዩ ደንቦችንና መመሪያዎችን የማውጣትና የዳኝነት ሥልጣን አለው።”
2
ከላይ በሁለቱ ንኡስ አንቀጾች እንደተገለጸው፤ የቅዱስ ሲኖዶስ ሥልጣን በማያሻማ ሁኔታ በግልጽ የተደነገገ ስለሆነ
በቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ወቅት በወገናዊነትም ሆን በዓለማዊ ጥቅም ፍለጋ ምክንያት በማንም የውጪም ሆነ የውስጥ
አካል ተጽእኖ እንዳይሸረሸርና እንዳይዛባ በእግዚአብሔር ስም ከፍ ባለ ትሕትና እንጠይቃለን።
2. ስለ ሰላምና አንድነት፤
በአባቶቻችን መካከል የተፈጠረው አለመግባባትና መከፋፈል አደባባይ ወጥቶ መዘባበቻ በመሆኑ በአባቶቻችን ላይ
በቀላሉ የማይፋቅ ታሪካዊ ትዝብት ያተረፈላቸው መሆኑ ግልጽ ነው። ይህ ሁኔታ ቤተ ክርስቲያናችንን እጅግ
በሚያሰጋና በሚያሳስብ ሁኔታ አደጋ ላይ ጥልዋታል። ይህ በአባቶች መካከል የተከሰተው መከፋፈል፤ መኖቆርና
አንድነት ማጣት፤ በአመራር ደረጃ የሚታየው ግዴለሽነትና ብቃት ማጣት፤ ምእመናንን ግራ ያጋባው ስደተኛ
ሲኖዶስ በመባል ያስከተለው መወጋገዝና የቤተ ክርስቲያናችን መከፋፈል አዝማሚያ መታየት እነዚህና ሌሎችም
ሁኔታዎች ለቤተ ክርስቲያናችን ጠላቶች መጠናከርና መስፋፋት አመች ሁኔታ ፈጥሮላቸዋል። ስለዚህ የቅዱስ
ሲኖዶስ አባላት እነዚህን ለቤተ ክርስቲያናችን በጣም አደገኛ የሆኑትን ክስተቶች በማጤንና በማሰላሰል፤
በክርስቲያናዊ አስተሳሰብና ይቅር ባይነት በመካከላችሁ የተፈጠረውን አለመግባባትና መከፋፈል አስወግዳችሁ
በፍጹም ፍቅርና ሕብረት በመወያየት ቤተ ክርስቲያናችንን ከተጋረጡባት አደጋዎች እንድታድኑዋት በጌታችን፤
በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስና በእናቱ በቅድስት ድንግል ማርያም ስም ከፍ ባለ ትሕትና እንማጸናችሁዋለን።
3. ስለ አስተዳደር ጉድለት፤
በባለሙያ የተጠና መዋቅር፤ ግልጽና የማያሻማ የአስተዳደር ደንብ፤ ዓላማው ግልጽ የሆነ የአጭር፤ የመካከለኛና
የረዥም ጊዜ እቅድ የሌለው ማንኛውም ተቁዋም፤ ብክነት፤ ሙስና፤ አድልዎ፤ የሥራ ቅልጥፍና ማጣትና
የመሳሰሉት የአስተዳደር ብልሹነት የሚታይበት መሆኑ አያጠራጥርም። ቤተ ክርስቲያናችንንም እዚህ ምስቅልቅልና
አደጋ ላይ ጥሎ ለውድቀት ከዳረጉዋት ምክንያቶች ውስጥ አንዱ ይህ ሁኔታ መሆኑ እውነት ነው። በተለይ እንደ
ቤተ ክርስቲያናችን ያለ ግዙፍ ተቁዋም በየመስኩ በሚገኙ ባለሙያዎች የተጠና መዋቅር፤ በመዋቅሩ ላይ
የተመሠረተ ግልጽና የማያሻማ የአስተዳደር ደንብ፤ በቤተ ክርስቲያኒቱ ዓላማዎች ላይ የተመሠረተ የአጭር፤
የመካከለኛና የረዥም ጊዜ ጥርት ያሉ እቅዶችና በእቅዶቹ ላይ የተመሠረቱ ምእመናንንና ምእመናትን በሰፊው
የሚያሳትፉ የሥራ ፕሮግራሞች በባለሙያዎች ተጠንተው እንዲዘጋጁ ማድረግ ቤተ ክርስቲያናችንን ከውድቀት
ለማዳን አማራጭ የማይገኝለት ጉዳይ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል። ስለዚህ ቤተ ክርስቲያናችን ትክክለኛውን አቅጣጫ
ይዛ በመጉዋዝ እየተስፋፋችና እየተጠናከረች በመሔድ በሕገ ቤተክርስቲያናችን በአጠቃላይ የተደነገጉትን
መንፈሳዊውንና ዓለማዊውን ዓላማዎቹዋን ግብ ለማድረስና ከገጠሙዋት ችግሮች መላቀቅ እንድትችል እላይ
በጠቀስናቸው አማራጭ በማይገኝላቸው ጉዳዮች ላይ የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ሥርነቀል
ውሳኔ እንዲያስተላልፍ
በማክበር እናሳስባለን።
4. ስብከተ ወንጌልን ስለ ማጠናከርና ስለ ማስፋፋት፤
በሕገ ቤተ ክርስቲያናችን እንደሚከተለው ተደንግጉዋል፤
አንቀጽ 7 ቁጥር 7 “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት በአገር ውስጥና በውጭ አገር እንዲስፋፋ
ያደርጋል።”
ነገር ግን፤ ከላይ በተጠቀሰው ሕገ ቤተ ክርስቲያን መመሪያ መሠረት የተወሰደው እርምጃ እጅግ አነስተኛ ነው።
እንደሚታወቀው፤ በአገራችን በኢትዮጵያ የቤተ ክርስቲያናችን ምእመናንና ምእመናት ስለ እምነታቸው በቂ
ትምሕርት ስለማያገኙ በብዛት ወደ ሌሎች እምነቶች እየፈለሱ በመሔዳቸው የቤተ ክርስቲያናችን እምነት
ተከታዮች ቁጥር እየቀነሰ ከመሔዱም በላይ በተለይ በገጠሩ የሚኖሩት ምእመናን ስለ ወንጌልም ሆነ ስለ
እምነታችን ያላቸው ግንዛቤ እጅግ አነስተኛ መሆኑ የታወቀ ነው። በአንጻሩ፤ የሌሎች እምነት ተከታዮች ቁጥር
እየጨመረ መሔዱ ብቻ ሳይሆን እያንዳንዱ የሌላው እምነት ተከታይ እምነቱን እንዲቀበል በስልት ተምሮ
የተቀበለውን እምነት በጣፈጡ ቃላት ለእኛው እምነቱን ያስተማረው ለሌለውና ለማያውቀው ምእመን እየሰበከ
ባል ሚስቱን፤ ሚስት ባልዋን ሲያስኮበልሉ ይታያሉ። ከኢትዮጵያ ውጪ በመላው ዓለም ተሰራጭተው በሚገኙ
ኢትዮጵያውያን ጥረትና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንም ፕሮግራም በውጭ ሐገሮች በብዛት
3
በተቁዋቁዋሙት አብያተ ክርስቲያናት የሚገኙ ካሕናት የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን እምነት በይፋ ለሌሎች ዜጎች
ስለማያስተምሩ ቤተ ክርስቲያናችን ብዙ የሌሎች ዜጎች ምእመናንንና ምእመናትን አባል ማድረግ ስትችል
የሚያስተምራቸው ስለሌለ እምነታችንን የተቀበሉ የውጭ ሐገር ዜጎች በጣም ጥቂት ናቸው። ስለሆነም፤ ከላይ
የተጠቀሰውን ችግር ቀስ በቀስ ማስወገድና ስብከተ ወንጌልን በስፋት እያሰራጩ ኢትዮጵያውያንና የውጭ ዜጎች
ምእመናንና ምእመናትን ቁጥር ማብዛት የሚቻልበት ዘዴዎች በቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ዘንድ የሚታወቁ ቢሆንም
ለመጠቆም ያህል የወንጌል መልእክተኞቻችን በሐገራችን ቁዋንቁዋዎችና በሌሎች ዜጎች ልዩ ልዩ ቁዋንቁዋዎች
በብዛት ማሠልጠንና እንደ ሌሎቹ እምነት አስተማሪዎች በየገጠሩ በቤተ ክርስቲያን ብቻ ሳይሆን በየመንደሩ
እየተዘዋወሩ እንዲያስተምሩ ማድረግ፤ በመጻሕፍት ብቻ ሳይሆን በቀላሉ የሚነበቡ በራሪ ወረቀቶችን በልዩ ልዩ
ቁዋንቁዋዎች በብዛት እያዘጋጁ ማሰራጨት፤ በመገናኛ ብዙኅን ማለት በሬዲዮ፤ በቴሌቪዥን፤ በድረገጽና
በመሳሰሉት ትምሕርተ ወንጌልን፤ እምነታችንና ቀኖናችንን ማሰራጨት ስለሚቻል ቅዱስ ሲኖዶስ በዚህ አስፈላጊና
አሳሳቢ ጉዳይ ላይ ውይይት አድርጎ አመርቂ ውሳኔ እንደሚያስተላልፍ እናምናለን።
5. ደብሮችንና ገዳሞችን ስለ መርዳት፤
ከደርግ ዘመን ጀምሮ፤ ቤተክርስቲያናችን አብዛኛውን ንብረቷን ስለ ተዘረፈች ብዙ ደብሮችና ገዳሞች ችግር ላይ
ይገኛሉ። በብክነት ምክንያት፤ ከምእመናን የሚገኘውም በትክክሉ እንዲደርሳቸው አልተደረገም። በተከሠተው
መናቆር ምክንያትም፤ ውጪ ሐገሮች ያሉት ምእመናንም በሚችሉት መርዳት አልቻሉም። በተጨማሪም፤ እጅግ
አሳሳቢ ሆኖ የቆየው፤ ታሪካዊው የኢየሩሳሌሙ “ዴር ሡልጣን” (1) ገዳማችን የሚያስፈልገው ጥገና
ስላልተከናወነለት የመፍረስ አደጋ ላይ ነው። ስለዚህ፤ ቤተክርሲቲያናችን ካላት ገቢ፤ ደብሮችና ገዳሞች ተገቢውን
ድርሻቸውን እንዲያገኙ፤ ለዘለቄታውም ራሳቸውን እንዲችሉ ተገቢ በሆነ ሥልት እንዲጠቀሙና፤ ከውጪም
የሚገኘው ድጋፍ እንዲዳብር፤ የእሥራኤል መንግሥትም የኢየሩሳሌም ገዳማችን እንዲጠገን ፈቃዱ እንዲሆን፤
ቅዱስ ሲኖዶሱ ተገቢ የሆነ ጠንካራ ሥልት አዘጋጅቶ ሥራ ላይ እንዲያውል በማክበር እናሳስባለን።
6. ስለ ትምህርት ማስፋፋትና ማጠናከር፤
ስለ ቅዱስ ሲኖዶስ የወጣው ሕገ ቤተክርስቲያን፤ አንቀጽ 7 ስለ “የቅዱስ ሲኖዶስ ሥልጣንና ተግባር”½
እንደሚከተለው ደንግጓል፤
ቁጥር 8፤ “የክርስቶስን ወንጌለ መንግሥትና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን ያስተምራል ያስፋፋል።”
ሆኖም፤ ቤተክርስቲያናችንን ካጋጠሟት እጅግ ከባድ ችግሮች አንዱ የአብነት ትምሕርት ቤቶች መዳከም ነው።
ቀድሞም ሆነ በአሁኑ ዘመን፤ የአብያተ ክርስቲያናችን ሕልውና መሠረት የአብነት ትምህርት ቤቶች መሆናቸው
ይታወቃል። ገዳማትንና አድባራትን የሚያገለግሉት ካህናት ምንጭ የአብነት ትምህርት ቤቶች ናቸው። የብፁአን
ወቅዱሳን ፓትሪያርኮች፤ የብፁአን ሊቃነ ጳጳሳትና ኤጲስ ቆጶሳት ምንጭ የአብነት ትምሕርት ቤቶች ናቸው።ስለዚህ
የእነዚህ አብነት ትምህርት ቤቶች መዳከም ማለት የቤተ ክርስቲያን መዳከም ማለት መሆኑ እውነት ነው።
ከአስተዳደር ችግሩ በተጨማሪ የገጠሬው ምእመን በከፋ ድሕነት ስለሚሰቃይ ለቆሎ ተማሪውና ለአስተማሪው
የተለመደ ቸርነቱን ሊያበረክትለት አልቻለም። ለጋሽ የነበረው የኢትዮጵያ ገበሬ ተመጽዋች በመሆኑ የቆሎ
ተማሪዎችና መምህራኖቻቸው የእለት ጉርሳቸውንና የዓመት ልብሳቸውን ከገበሬው በምጽዋት ማግኘት ስላልቻሉ
ወደየከተማው በመሰደድ ላይ ናቸው። በዚህ ምክንያት፤ የቤተክርስቲያናችን ምንጭ የሆኑት የአብነት ትምሕርት
ቤቶች አስጊ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ። ውጪ ሀገሮች ላሉት ምእመናንም ተገቢ የሆኑ የሥልጠና ማእከሎች
(1) ማሕበራችን ስለ ታሪካዊው የኢየሩሳሌም ገዳማችን ለእስራኤል መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትር የሚያቀርበውን
አቤቱታ በዓለምአቀፍ
ደረጃ በማስፈረም ላይ መሆኑን የሚያሳየውንና ያሰራጨውንም መግለጪያ በድረገጹ
በwww.eotcipc.org½ይመልከቱ።
4
ስላልተቋቋሙላቸው በቤተክርስቲያናችን ትምሕርት የጠለቀ እውቀት ሊያገኙ አልቻሉም። ስለዚህ፤ የአብነት
ት/ቤቶች እንዲጠናከሩና ውጪ ሐገሮችም የቤተክርስቲያናችን ት/ቤቶች እንዲቋቋሙ፤ ቅዱስ ሲኖዶሱ ለጉዳዩ ልዩ
ትኩረት በመስጠት በባለሙያዎች ጥናት ላይ የተመሠረት ዘላቂ መፍትሔ እንዲያስገኝለት በትሕትና እናሳስባለን።
7. አክራሪዎች ስላደረሱት ጥቃት፤
ቤተክርስቲያናችንን ካጋጠሟት እጅግ መራርና አስቆጪ ጥቃቶች አንደኛው አክራሪ እስላሞች ካሕናትንና
ምእመናንን አሰቃቂ በሆነ መንገድ መጨፍጨፋቸው፤ ደብሮችንና ገዳሞችን ማቃጠላቸውና ከጠላት ሐገሮች
በሚያገኙት ገንዘብ ቤተክርስቲያናችንን በብዙ መንገድ መፈታተናቸውን መቀጠላቸው ነው። በተለይ በ1997 እና
1998 ዓ/ም ከምሥራቅ ሐረርጌ ክፍለ ሐገር ጋራሙለታ ጀምሮ በምዕራብ እስከ ኢልባቦርና ከፋ ክፍላተ ሐገራት
ባሉት አገሮች በባሌና አርሲ ብዙ አብያተ ክርስቲያናት የፈረሱና የተቃጠሉ፤ ብዙ ካህናት የተሰየፉ፤ እንደ እንስሳ
የተቀሉ፤ ተገድደው የሰለሙ መሆናቸው ያደባባይ ምሥጢር ነው። ስለዚህ ሁሉ ግፍ፤ በቤተክርስቲያናችን አመራር
ምን እንደ ተከናወነና ምን ክትትል በመደረግም ላይ እንዳለ የሚታወቅ ነገር የለም። የተከናወነው አሰቃቂ ግፍ
ተጀመረ እንጂ ያበቃለት አለመሆኑን፤ እንዲያውም የባሰ ጥቃት ሊከሰት እንደሚችል አውቆ፤ ነቅቶ እንዲጠብቅ
ለቤተ ክርስቲያናችን ምእመናን በሰፊው ማስገንዘብ ያስፈልጋል። ስለዚህ፤ ቅዱስ ሲኖዶሱ ይህን ከባድ ጉዳይ
በዝርዝር በማጥናት ተገቢው ሕጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ እንዲሁም ቤተክርስቲያናችን ለራሷ ብቁ፤ ለዘመኑ አመች
የሆነ ሕጋዊ መከላከያ እንዲኖራት ለማድረግ የሚያስችል ሥልት አዘጋጅቶ ሥራ ላይ ማዋል የሚያስፈልግ መሆኑን
በአክብሮት እናሳስባለን።
8. ስለ ድሕነት፤
ከላይ በተጠቀሰው ሕገ ቤተክርስቲያን፤ አንቀጽ 6 ቁጥር 6 አንደኛው የቅዱስ ሲኖዶስ ዓላማ እንደሚከተለው
ተገልጿል፤
“የሰው ዘር ሁሉ ከርሃብ፤ ከእርዛት፤ ከበሽታና ከድንቁርና ተላቆ በሰላምና በአንድነት በመተሳሰብና
በመረዳዳት በመንፈሳዊ ሕይወት እንዲኖር ማስተማርና መጸለይ፤”
የሐገራችን ሕዝብ እጅግ በከፋ የድሕነት አረንቋ ፍዳውን እያየ መሆኑ የታወቀ ነው። ቤተክርስቲያናችንንም
ለእምነቱ መጠጊያ፤ ለረሐቡም ማስታገሺያ እንድትሆንለት ይፈልጋል። በዚህ ረገድ፤ ቤተክርስቲያናችን ለደኸየውና
ለታረዘው ወገናችን በበለጠ ሁኔታ ደራሽ እንድትሆን ተገቢ ሥልት እንዲቀየስና ሥራ ላይ እንዲውል፤ ቅዱስ
ሲኖዶሱ አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስድ በትሕትና እናሳስባለን።
9. መደምደሚያ፤
ከላይ የዘረዘርናቸው ጉዳዮች የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኩዋይ ትኩረት የሚገባቸው መሆኑ ቢታወቅም፤ ምእመናን
መፍትሔ የሚሹባቸው ሌሎች ችግሮችም አሉ። ከነዚህ ውስጥ ጥቂቱን ለመጥቀስ፤ (ሀ)ቃለአዋዲውን
ስለ
ማሻሻል፤ (ለ) መጠናት ስለሚገባቸው ድርሳናት፤ ገድላት፤ ውዳሴያትና ታምራት፤ (ሐ) የምእመናትን ተሳትፎ ስለ
ማጠናከር፤ (መ) ቅዱስ ቁርባኑን ባለመቀበል፤ አብዛኛዎቹ ምእመናንና ምእመናት በቅዳሴያችን በግልጽ እንደ
ተቀመጠው፤ የእግዚአብሔርን ሕግ አፍራሾች ሆነን ስለ መገኘታችን፤ ወዘተ ይገኙበታል።
ቅዱስ ሲኖዶሱ መልካም ፈቃዱ ሆኖ፤ ከላይ የዘረዘርናቸውን ጉዳዮች በጥሞና ተመልክቶ አስፈላጊውን መመሪያ
እንዲሰጥና ቅድስት ቤተክርስቲያናችን ሰላምና አንድነት የሰፈነባት፤ በተሟላ ሥልት፤ አቅድና፤ ፕሮግራም
የምትንቀሳቀስ፤ በቅልጥፍና፤ በግልጽነትና በአስተማማኝ ቁጥጥር የምትሠራ፤ ስብከቷና ትምሕርቷ ለዓለም ሕዝብ
ሁሉ የሚዳረስ፤ የማትደፈር፤ ራሷን የቻለች፤ ምእመኖቿም በእምነታቸው የጸኑ የብዙ ሐገሮች ዜጎች እንዲሆኑ
እንዲያደርግ የሁልጊዜም ጸሎታችን ነው።
ቅዱስ ሲኖዶሱ፤ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት፤ ባሁኑ ጊዜ በቤተክርስቲያናችን ላይ የተጋረጡትን ከባድ ችግሮች
በሚገባ እንዲወጣ ለቸሩ የኢትዮጵያ አምላክ ተንበርክከን እንጸልያለን። አሜን።
እጅግ ከፍ ካለ የአክብሮት ሰላምታ ጋር፤
ኢዮኤል ነጋ
የማሕበሩ ዋና ጸሐፊ።
ጽሑፉን በፒ.ዲ.ኤፍ ለማንበብ ይህንን ይጫኑ።

October 26, 2009

The Ongoing Crimes of “Patriarch Abune” Paulos against the Ethiopian Orthodox Church

Ze Debrezeit Kidus Rufael
When ever the history of the Ethiopian Orthodox Tewahido Church is raised, one finds the archbishops and patriarchs who contribute a lot for the expansion, growth and glorification of the Church. Abune Fremnatos the first Patriarch of Ethiopia has accomplished his apostolic duty by preaching the nation and translating religious and other canonical books to the Ethiopic language Geez. His effort to spread Christianity in Ethiopia has been intensified by the nine saints who introduced and expand monastic life for the church.


The 13th century archbishops of Ethiopia Archbishops Abune Michael and Abune Gabriel, who played significant role in reconciling administrative and theological split between Bete Tekle Haymanot and Bete Ewstatitos and protected the church from the herestic teaching of Estifanos, can never be forgotten1. During the reign of Susnyos, Archbishop Selama died defending his faith from Jesuits missionary plot2 .The recent past 20 th century story also tells us how Archbishop Petros, Archbishop Michael, Patriarch Baslious and Patriarch Teweflos died for their religion and beloved country .

The third Patriarch of Ethiopian Orthodox church, His Holiness, Abune Tekle Haymanot died for the same reason .He preferred to die of hunger than handing over the historic church right and pride to the atheist Communist Junta3. Though Ethiopian Orthodox Church history is full of such martyrs and committed church fathers act, Patriarch Paulos, the fifth Ethiopian Patriarch, is exercising a strange and odd behavior like nepotism, dictatorship, xenophobia, ethnocentrism and the likes which have never been exercise before, in the millennium old history of the apostolic church.4

The rise of the dictator Patriarch Paulos
The author of the memoirs of the journalist, Tesfaye Gebre Ab, who was very close to the key intelligence officers of the state, in his book argues that Patriarch Paulos enthronement and Patriarch Merkorios dethronement was engineered by the ruling
government. I don’t want to get deep down to this issue since there are many controversies being raised from different sides. But let us examine how this patriarch,
step by step, became a tyrant.

The first “apostolic duty” Patriarch Paulos did, soon after his enthronement, was to
change the 1,600 years old different traditions of the church. Unlike his predecessor, he
declared that the dress for a Patriarch should be white and for the first time in the history of the church he ordered this costly new dress and publicize that this should be the dress of a Patriarch. During that time it was fascinating for the faithful when they observe that the new Patriarch first task was to worry for his dress design and color. Though many scholars of the church were against his new dress style for violating the age old tradition, some took it for granted considering his relatively young age and the cultural influence he may have faced from his stay in United States of America while studying for his masters and PhD. He then changed the previous title of Patriarch and came up with new and long title: Patriarch Paulos, head of all Archbishops of Ethiopia, Ichege of the see of Tekle Haymanot and archbishop of Axum. It was fascinating for every follower of the church, again, why this patriarch was so hungry of power and authority this much. The reason why he singled out and took the title of Axum Archbishop was also a puzzle for many.

No Patriarch before him has claimed such centrality of power. But his thirst for power
and authority doesn’t stop there. After some years he claimed that the Holly synod shall
be accountable to him. The Holly synod, for the last 1,600 years, was accountable for The Holly Ghost. But Patriarch Paulos, shockingly, claimed this power. Surprisingly
surprising!

His dangerous and meaning less reformation act initiated huge resistance from
everywhere. Archbishops who are members of the Holly synod like the late Abune
Selama, Abune Kerlos and etc expressed their serious opposition. Aleka Ayalew Teamiru, the foremost scholar of the church zealously criticized and rejected his proposal.5

Different monks, priests, hermits did the same. The faithful protested strongly against
him. But the response from his side was militaristic. Hermit who used to critically oppose
him was gunned down by his entourage pistol 6. The vocal critic of him, Aleka Ayalew,
was fired out of his job, as simple as garbage, with no recognition for his 50 year of
service in various positions and passed away eventually7. For the reasons, which
historians may decode it in the future; his major opponents like Abune Selama were
pronounced dead in various occasions. The opposition of the public in many churches,
for the newly emerged ill administration in the church, was crushed by police forces.8
The patriarch who was supposed to protect the followers of Ethiopian Orthodox church
from spiritual crisis became source of crises for the church and the followers. Since his
anointment, the church lost millions of dollars through corruption9. Promotion by merit,
for the key administrative position of the church, was changed to promotion by blood ties and kinship. The spiritual father who was anointed to be the father of all the 47, million followers became the source of xenophobia10 All this unethical, dictatorial and visionless management of the patriarch for the last 17 years costed the church a lot. As per the report of the recent census, 2007, the church lost millions of its followers. This is the first time in the history when the church lost this much followers since the invasion of Ahmad Ibn Ibrihim al-Ghazi, commonly called Gragn Ahmed11. Members of the Holly Synod Archbishops exactly depicted the situation of the church under Patriarch Paulos like this,” Patriarch Paulos killed the Ethiopian Orthodox Church, we the other archbishops buried the church killed by his holiness by failing not to oppose him(the Patriarch )” 12

The Current Challenge the Church faced the Patriarch’s response
Recently the three big religious movements: Judaism, Christianity (different
denominations) and Wahabiyism , backed by huge finance and powerful states are in
competition for the soul of the country. Israel has shown its commitment to immigrate
Falashmura i.e “Christians who are apparently the descendants of Jews who accepted
Christianity under the influence of European or Ethiopian Church missionaries during the second half of the 19th century.”13 Parliament members are expressing the plan to airlift thousands of Christians from the strong hold of Ethiopian orthodox Christian city,
Gondar, to Israel. No question these new immigrants will convert their religion to
Judaism which is another loss for the church 14

Muslim fundamentalists are also working so hard to Wahabiyaze Ethiopia as fast as
possible. United States, British, Germany and many other countries elites, politicians,
reporters and religious leaders have exposed this fact and are advising for the church to
wake up. The German Newspaper paper 15, “Bund Freier Evangelischer” Gemeinden
Kdor had reported that the Arab countries were spending multi millions of petro dollars
to completely transform Ethiopia into a Muslim country within twenty years.( it is
quoted by Admas, Amharic periodical published in Zurich, May 1992. The London
based Islamic Watch October/November 1992 alleges Libya’s huge and secret plan of
Wahabiyasing Ethiopia like this: "Col. Ghadafi is reported to be financing a plan to turn
Ethiopia into an exclusively Islamic country by the end of the century”16

. Many more
Arab countries are fueling billions of dollars to change the nation to their Wahabiy camp
soon.17 Here I am not talking against Islam but the fundamentalist wehabiya movement
which never allows social mix and tolerance with Orthodox Christians and others. The
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council (EIASC) have also genuinely and responsibly
announced the danger of the expansion of these fundamentalist again and again like this
“. Members of the EIASC state that the Wahhabists believe in supremacy and do not tolerate
a mix of Muslims and Christians. The majority of Ethiopian Muslims continued to enjoy
collegial relationships with their neighbors, attending cross cultural and religious ceremonies
such as weddings and funerals. The Wahhabists within the country shun this type of social
mixing.” 18
Different non orthodox Christian denominations have also huge projects to attract
Ethiopian population to their respective camp.Vatican have started new operation to
Catholicize Africa, Ethiopia included19. Different protestant denominations, being backed
up by westerns, are also busy of hunting souls of Ethiopia. The followers of the Ethiopian Orthodox Tewahido church are the pray and the target be it for the Jewish,
fundamentalist, Catholic or protestant movement since a huge segment of the population of Ethiopia is follower orthodox religion still and for the inefficient leadership Abune Paulos is exercising in maintaining its flocks .

It was definitely clear that the church cannot keep its ground and accomplish its pastoral
service under the existing leadership as a result concerned and committed archbishops
like Abune Matios, Abune Samuel, Abune Kerlos and other confronted the Patriarch.

They strongly criticized the Patriarch for his visionless leadership and even requested to
limit the power of the Patriarch and conduct a new administrative reform which can makethe church conduct its apostolic mission effectively. 20

The shocking response
The response for the quest, raised by members of the holly synod, was one and the same. “Unknown gangs” raided the compound of the Bete Kihnet, broke the residence of the opposing archbishops who confronted the patriarch for administrative reform and gave strict warning and intimidation.21 On this coordinated raid, even police was not allowed to enter the compound of Bete kihnet and save the archbishops from the gangs, despite the continuous plea they made to Federal police by phone. These “unknown gangs” also attempted a murder trail to the journalist (he was seriously beaten with angle iron) of the reputed newspaper Addis Neger for extensively reporting the oppositions of the archbishops against the patriarch. It is also good to bear in mind that all these crimes were being done with in few meters from the national presidential palace of Arat kilo On the long awaited synod meeting of October 2009, which was expected to resolve this problem, it was exposed that those archbishops who were asking for visionary leadership and freedom of the church were told not to raise any issue about such things and Mahibere Kidusan by EPRDF government officials22. With in that day, the government owned Ethiopian News Agency reported that “the Church fathers have resolved their difference”. Funnily enough the news came before the end of the synod meeting.23

The Patriarch game still has continued. By the time when multi millions are reported to
have converted their religion from orthodox to other religion, EOTC church Patriarch
Abune Paulos gave an award for high performance of the church.24

He further expressed that he strongly support the recent expansion of Catholics in Africa (Ethiopia) like this “I am really very happy to participate to this Synod of the Catholic Church on Africa. …I carry my support as a friend and a brother to this endeavor of the Catholic Church for Africa. I thank His Holiness for the invitation and I wish to him a long life and a fruitful ministry.”25

I am not questioning the constitutional right of every religion. But Catholics have
committed a significant atrocities and crime in Africa. When the fascist Italy invaded
Ethiopia, Catholics bishops have blessed the poison gas and other weapons which were used to kill Ethiopian Orthodox Monks and priests and other citizens. They even gave their golden cross as a support to the invading army. To that end concerned Ethiopians were asking, time and again, Vatican to apologize for that dark history. But his holiness has zero courage to confront such issues. Rather to warmly welcome them.
By the time when the church needs more supporting man power, Patriarch Paulos
responded by giving warning and intimidation to Mahibere Kidusan , an association
under Sunday school department which is strongly fighting to defend Tewahido church
and its tradition.

Ethiopian Orthodox Tewahido Church is under pressure and danger. The visionless,
irresponsible and ethnocentric leadership of Patriarch Paulos and the unnecessary huge negative interference of EPRDF government on the issue of the church are threatening the legacy of the church.

In a nut shell His Holiness has became a shame and a spiritual parasite to the church. If
the church is needed to exist in the coming centuries, avoiding him is an imperative task.

Orthodox Tewahido Church is in danger. The followers of the church and others
concerned Ethiopians should think now, before the time is over.
Reference
1. Church in Africa: 1450-1950 by Adrian Hastings. Oxford history of Christian Church
2. The History of Ethiopian Orthodox church by his Holiness Abune Gorgorios
3. The History of Ethiopian Orthodox church from the birth of Christ up to the
millennium. A special book published for the Millennium celebration
4. VOA Amharic service interview with Abune Matiwos archbishop of Jerusalem,
2009. http://www.quatero.net/pdf/Zeregnenet_Be_betekehenet.pdf
5. http://www.aleqayalewtamiru.org/excommunication.html
6. http://en.wikipedia.org/wiki/Abune_Paulos
7. http://www.aleqayalewtamiru.org/excommunication.html
8. http://en.wikipedia.org/wiki/Abune_Paulos
9. http://www.ethiopianreview.com/content/10480
10. http://www.ethiopianreview.com/content/10480
11.
12. http://deje-selam.blogspot.com/2009/07/blog-post_9834.html
13. http://www.haaretz.com/hasen/spages/1122973.html
14. ibid.
15. Bund Freier Evangelischer” Gemeinden Kdor
16. The London based Islamic Watch October/November 1992
17. International Religious Freedom Report 2004, Ethiopia
http://atheism.about.com/library/irf/irf04/blirf_ethiopia.htm
18. http://www.zenit.org/article-27089?l=english
19. http://www.zenit.org/article-27314?l=english
20. Addis neger Newspaper Meskerem 16, 2001
21. http://deje-selam.blogspot.com/2009/10/blog-post_5208.html
22. ibid.
23. http://www.ethiotube.net/video/6278/ETV-News--Ethiopian-Orthodox-Churchstarts-
its-summit-to-discuss-main-dividing-topics
24. http://deje-selam.blogspot.com/2009/10/blog-post_719.html
25. http://www.zenit.org/article-27087?l=english

ኢህአዴግና የሃይማኖት ፖለቲካ

(በየማነ ናግሽ)
(Reporter:Oct.25/2009):-ኢትዮጵያ ውስጥ ከዚህ በፊት ባልተለመደ መልኩ እዚህም እዝያም የሃይማኖት ግጭቶች ተከሰቱ ሲባል መስማት የተለመደ እየሆነ መጥቷል፡፡ የሃይማኖት አባቶች ያለ አንዳች ልዩነት የእያንዳንዳቸው ሃይማኖት አቋም ሰላምን መስበክ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ ገዥው ፓርቲ በበኩሉ በሃይማኖት ሽፋን የሚነሱ እነዚህ ግጭቶች መንስኤ ሃይማኖቶች ውስጥ ተወሽቀው በሽፋንነት የሚጠቀሙ ፖለቲከኞች እንዳሉ ይፈርጃል፡፡ የአክራሪነት አስተሳሰብም ከኪራይ ሰብሳቢነት ነጥሎ ማየት እንደማይቻል ይገልፃል፡፡ ተቃዋሚዎች በበኩላቸው፣ ኢህአዴግ የሚጠቀምበት አንዱ የማሸማቀቂያ መንገድ መሆኑን በመግለፅ፣ “ፍረጃውን” ያስተባብላሉ፡፡

ሥልጣን ላይ ያለው ገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግ፣ በቅርቡ ከፍተኛ ትኩረት እሰጣችኋለሁ ከሚላቸው አጀንዳዎች መካከል የሃይማኖት ጉዳይ ዋነኛ እየሆነ መጥቷል፡፡ በየሁለት ወሩ ለህትመት የሚበቃው የድርጅቱ የንድፈ ሃሳብ መፅሄት በተከታታይ ሰፊ ትንታኔ ከሰጠባቸው ጉዳዮች የሃይማኖት ግጭቶችና አክራሪነት ይገኝበታል፡፡ በቅርቡ የወጣው 2ኛ ዓመት ቅፅ 2 ሐምሌ - ነሐሴ 2001 “አዲስ ራዕይ” መጽሔት፣ ከአመራር መተካካተ ቀጥሎ ሰፊ ትንታኔ የተሰጠበት ጉዳይ “የሃይማኖት አክራሪነት”ን ነው፡፡ ኢሕአዴግ ከዚህ በፊት ባወጣው “አዲስ ራዕይ” መጽሔትም የሃይማኖት ግጭቶች መንስኤና ተያያዥ ጉዳዮች ተንትኗል፡፡

ኢሕአዴግ በሃይማኖት ሽፋን እየተነሱ የሚገኙ ግጭቶች እያሳሰበው እንደሆነ ለጉዳዩ ከሰጠው ሰፊ ሽፋንና ትንታኔ መገንዘብ ይቻላል፡፡ ገዢው ፓርቲ በተለይ በምርጫ 97 ተሸነፉ የሚላቸውና ሌላ አማራጭ ፈልገዋል የሚላቸው ተቃዋሚዎች “የከሰሩ ፖለቲከኞች” ብሎ የሚጠራቸው ሲሆን፣ የሃይማኖት ሽፋን በመጠቀም ግጭቶች እየቀሰቀሱ እንደሆነ ይገልፃል፡፡ እነዚህ በተለይ በእስልምናና በክርስትና ሃይማኖት ተወሽቀው ግጭት እይቀሰቀሱ ነው ያላቸው ፖለቲከኞች ለግጭቶቹ መነሻ ዋነኞች መሆናቸው የወነጀለ ሲሆን፣ አሁን ያለው ስርዓትና ራሳቸው ሃይማኖቶች የመከባበርና የመቻቻል እንጂ የግጭት ምንጭ እንዳልሆኑ መንደርደሪያውን ያስቀምጣል፡፡ ተቃዋሚዎች ግን ውንጀላውን አይቀበሉትም፡፡ ይልቁንስ ይህንን ተቃዋሚ የፖለቲካ ሃይሎችን የማሸማቀቅ ተግባር እንደሆነ ይገልፃሉ፡፡

ኢሕአዴግ የሃይማኖት አክራሪነት ከሰላምና ልማት ማስፈን አንፃር የተመለከተበት ሁኔታ አለ፡፡ በተለይ ከዴሞክራሲ አንፃር የሃይማኖት ነፃነት፣ የሃይማኖት እኩልነት፣ የሃይማኖትና የመንግሥት መለያየት ከኢፌዲሪ ህገመንግሥትና ከስርዓቱ አንፃር ሰፊ ትንታኔ ሰጥቶበታል፡፡

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በተከታይ ብዛትም ሆነ በአመጣጣቸው ግንባር ቀደም ሚጠቀሱት የእስልምናና የክርስትና እምነት መካከል የሚፈጠረው ግጭት፣ ብዙዎችን ያሳስባል፡፡ ይህ ኢትዮጵያ ውስጥ ያልተለመደና አዲስ ክስተት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበራከተ መምጣት መንግሥት፣ ሕዝብንና ምሁራንን እያነጋገረ ነው፡፡ አንዳንድ ምሁራን በግጭቶቹ መነሻ ጥናት በማቅረብ መፍትሄ ይሆናል ያሉትን እየጠቆሙ ነው፡፡ ሕዝቡም በተለያዩ አጋጣሚዎች እነዚህ ግጭቶች የጥቂቶች አጀንዳ እንደሆነ ሲገልፅ በስፋት ይስተዋላል፡፡ የሃይማኖት አባቶችም ቢሆኑ፣ በተለያዩ አካባቢዎች በተለይ ሃይማኖትን መሰረት አድርገው የሚነሱ ግጭቶች ለመፍታት እየተንቀሳቀሱ እንደሆኑ ይገልፃሉ፡፡ በየፈርጃቸው ሰላምንና ፍቅርን ይሰብካሉ፡፡ የእያንዳንዱ ሃይማኖት ተከታዮችም ግጭት ቀስቃሾቹን ለሕግ እንዲቀርቡ ሲጠይቁ ይስተዋላሉ፡፡ ታዲያ የሃይማኖት ግጭቶች መንስኤ ምንና ማን ይሆን?

መንግሥታት ስልጣናቸውን ከሃይማኖት የመነጨ አድርገው በሚሰብኩበት ወቅት፣ አንድን ሃይማኖት (ከመንግሥት ጋር የተጠጋው) በሌሎች ላይ የበላይ ሆኖ ሌሎችን ሲጨቆን የነበረበት ሁኔታ ሩቅ አይደለም፡፡ በአሁኑ ዘመን ግን በአብዛኛው የዓለም መንግሥታት የሚከተሉት መርህ ሃይማኖትና መንግሥት የተለያዩበት አንዱ በሌላው ላይ ጣልቃ የማይገቡበት ሴኩላር መንግሥት (Secularism) እየተባለ የሚጠራው ነው፡፡ ኢትዮጵያም ውስጥ ከአክሱም ዘመነ መንግሥት ጀምሮ በተዋረድ የመጣው ስርወ መንግሥት እስከ አፄ ኃ/ሥላሴ ዘመን ሃይማኖትና መንግሥት የተደባለቁበት ሁኔታ ስለነበር፣ ክርስትና (ኦርቶዶክስ) እምነት የበላይ የሆነበትና ሌሎች በእኩል የማይታዩበት ሁኔታ ነበር፡፡ በደርግም ጊዜ መንግሥትና ሃይማኖት እንዲለያዩ ቢደረግም፣ ሃይማኖቶች እንደፈለጉ በነፃነት የሚንቀሳቀሱበት ማዕቀፍ አልነበረም፡፡

ኢሕአዴግ ባስፀደቀው የኢፌዲሪ ህገመንግሥት፣ መንግሥትና ሃይማኖት የተለያዩ እንዲሆኑ ማድረግ ብቻ ሳይሆን፣ ማንኛውም ሰው እምነቱ በነፃነትና በእኩልነት እንዲተገብርና እንዲያስፋፋ የሚፈቅድ ነው፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በኢትዮጵያ ታሪክ በሕዝቡ መካከል የነበረው የመቻቻልና የእርስ በርስ መከባበር የሚያደፈርስ ግጭቶች እየታዩ ነው፡፡

አብዮታዊ ዴሞክራሲ ስለ አክራሪነት

ኢህአዴግ እንደሚለው፣ የሃይማኖት አክራሪነት የተለያዩ ወገኖች በተለያየ መመዘኛ ቢያዩትም፣ ድርጅቱ ከራሱ ስርዓት አንፃር ይመለከተዋል፡፡ “የዴሞክራሲ ስርዓታችን ሁሉም ዜጎች የእምነት ነፃነት እንዳላቸው ያስቀምጣል፡፡ ዜጎች የራሳቸውን የእምነት ነፃነት ማስከበር ይችሉ ዘንድ የሌላውን የእምነት ነፃነት መከበር እንዳለበት ያስቀምጣሉ፡፡ አክራሪነት የምንለው ይህንን መሠረታዊ የዴሞክራሲ መርህ በሃይማኖት ሽፋን መቃወም ነው” ይላል፡፡

ኢሕአዴግ ይህ የአክራሪነት አመለካከት በሁሉም ሃይማኖቶች ውስጥ የሚታይ እንደሆነ፣ በአንድ ሃይማኖት ውስጥም የተለየ አመለካከት ባላቸው ላይ አክራሪነት በተግባር እንደሚታይ ይናገራል፡፡ “አክራሪነት በአንድና ሁለት ሃይማኖቶች ብቻ ያልታጠረና አንዱ መሠረታዊ መገለጫው የራሱን የእምነት ነፃነት የሌላን ዜጋ የእምነት ነፃነትን በመሸራረፍ በማፈንና በማንቋሸሽ ለማስከበር የሚደረግ መሆኑ ነው፡፡ ይህ አመለካከት በሃይማኖት ሽፋን የሚካሄድ ፀረ ዴሞክራሲ ነው” ይላል፡፡

ይህ በሁሉም ኃይማኖቶች ተከታዮች የሚፈፀም ፀረ ዴሞክራሲ አመለካከት እንደሆነ ሲያስረዳ፣ ..ጥቂት ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች እንደ ድሮው ሁሉ ኦርቶዶክስ ክርስትና የመንግሥት ሃይማኖት እንዲሆን፣ ከሌሎች የተለየ መብትና ጥቅም እንዲኖረው ይመኛሉ፡፡ . . . በሌላ በኩል አንዳንድ ሙስሊሞች የሃይማኖት ብዙኅነት ባለበት አገር እነሱም እስልምና ነው ብለው ያመኑበት መመሪያ በመንግሥትና በመንግሥት ተቋሞች አማካኝነት እንዲፈፀም፣ እስልምና የመንግሥት ሃይማኖት እንዲሆን ሲከጅሉ ይታያሉ.. በማለት በተለያየ ደረጃም ቢሆን “የአክራሪነት ዝንባሌ የተጠናወታቸው” የሁሉም ሃይማኖቶች አባላት እንዳሉ ይገልፃል፡፡

አክራሪነት - ኪራይ ሰብሳቢነትና የ..ከሰሩ ፖለቲከኞች..

ኢሕአዴግ እያንዳንዱ ሃይማኖቶች ውስጥ አሉት ካላቸው የአክራሪነት አመለካከቶች በተጨማሪ፣ የአክራሪነት ምንጭ ያላቸው ሃይሎች መኖራቸውን ይገልፃል፡፡ ድርጅቱ በዋናነት በኢትዮጵያ ለሃይማኖት አክራሪነት ምንጮች የሚላቸው የታሪክ ቅሪትና ዓለም ዓቀፉ የአክራሪነት ዘመቻ ናቸው፡፡ ድርጅቱ እነዚህ ምንጮች በኢትዮጵያ ተፅዕኖ የሚያሳድሩበት ሁኔታ፣ እነዚህ የአክራሪነት አመለካከቶች ሊያስተናግድና ሊቀበል የሚችል የፖለቲካ ሁኔታና የፖለቲካ ሃይሎች መኖራቸውን ያምናል፡፡

ኢሕአዴግ በዚህ የአክራሪነት አመለካከት ምቹ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ድህነትና ኋላ ቀርነት በግንባር ቀደምትነት ይጠቅሳል፡፡ ይህንን የሚያስረዳውም፣ በቅረቡ በአዲስ አበባ በርካታ ሕዝብ ለችግር የተጋለጠበት የአተት በሽታ “አለመማርና ኋላ ቀርነት” የወለደው እንደሆነ፣ በጠበል ቦታዎች የሆነውን በመግለፅ ነው፡፡ ሁኔታው በማንም ሌላ ሰው ላይ ቀጥተኛ ጉዳት ባያደርስም፣ ጠበሉ የታጠቡ ሰዎች ያስከተለባቸው የአተት በሽታ እንደመፈወስ መመልከታቸው ኋላ ቀርነትና አለመሰልጠን ..ከአክራሪ አመለካከት.. ጋር እንዴት ሊዛመዱ እንደሚችሉ ድርጅቱ ተመልክቷል፡፡

እንደ ገዥው ፓርቲ ትንታኔ፣ ድህነትና ኋላ ቀርነት ግን የአክራሪነት አመለካከቶች እንዲስፋፉ ይፈቅድ እንደሆነ እንጂ የአክራሪነት እንቅስቃሴ መፍጠር አይችሉም፡፡ ድርጅቱ አገሪቱ ከሃይማኖት ጋር በተያያዘ ያላትን የታሪክ ቅሪትና ዓለም አቀፍ አክራሪነት የሚያራግቡ የፖለቲካ ሃይሎች ናቸው ሲል በተቃዋሚዎች ላይ ጣቱን ይቀስራል፡፡

“በአገራችን የአክራሪነት አደጋ ቀላል ተደርጎ የማይወሰድበት ደረጃ ላይ የደረሰው ይህንኑ በማራገብ የፖለቲካ አላማቸውን ለማራመድ የሚፈልጉ የጥፋትና የኪራይ ሰብሳቢ ሃይሎች ስላሉ ነው” የሚለው ኢሕአዴግ፣ አንዳንድ ዓማፂ ሃይሎች በተለይ ከኤርትራ መንግሥት ጋር ያካሂዱታል ያለው የጥፋት ሥራ በመግለጫነት ያስቀምጣል፡፡ አገር ውስጥ ያሉት ተቃዋሚዎችም ቢሆኑ፣ ህጋዊና ህገወጥ ተግባራትን እያጣመሩ ይህንን አመለካከት ከማራገብ ወደ ኋላ አይሉም ይላል፡፡

ኢሕአዴግ እንደሚለው ተቃዋሚዎች ህብረተሰቡ በጥፋት መንገድ ለመምራት፣ ሁለት መንገድ ይጠቀማሉ፣ ብሔርና ሃይማኖት፡፡ በአሁኑ ወቅት የብሔር ጥያቄ በዴሞክራሲያዊ መንገድ እልባት ያገኘ በመሆኑ፣ ሃይማኖትን በሽፋን ለመጠቀም በአማራጭነት እንደሚጠቀሙበት ይወነጅላል፡፡ “ዋናው መሳሪያቸው ትምክህተኝነትና ጠባብነት በማራገብ በብሔር ጥያቄ ዙሪያ ለመፍጠር የሚሞክሩት የጥፋት እንቅስቃሴ ቢሆንም ሃይማኖትንም በመሳሪያነት ከመጠቀም አልቦዘኑም”፡፡

ኢሕአዴግ ቀደም ብሎም እንዳለው “የከሰሩ ፖለቲከኞች” የሚላቸው “ህጋዊና ህገወጥ” መንገድ እያጣቀሱ የሃይማኖት አክራሪነት ያራግባሉ የሚላቸው ተቃዋሚ ወገኖች እነማን እንደሆኑ ተጨባጭ ምሳሌ ባያቀርብም፣ የኤርትራ መንግሥት ጀሌዎች የሚላቸው እንደ ኦነግ የመሳሰሉ ሃይሎች ግን ይጠቅሳል፡፡ በተለይ ሃዋርጂያ የተባለው የእስልምና አክራሪ ቡድን አባላት አብዛኛዎቹ የኦነግ አባላት የነበሩና በምህረት የተፈቱ እንደሚገኙባቸው ይጠቁማል፡፡ ገዥው ፓርቲ እንደሚለው፣ በኦርቶዶክስ ሃይማኖት ውስጥ ትርምስ ለመፍጠርና ከሌሎች ተከታዮች ጋር ግጭት ለመቀስቀስ የሚሞክሩት የደርግና የተለያዩ የትምክህት ሃይሎች ቅሪቶችም አሉ፡፡ “ከ97 ምርጫ በኋላ አንዳንድ በአሜሪካ የሚገኙ ጳጳሳት ቅንጅት በመራው ሰልፍ ላይ የሃይማኖት አባትነት ካባቸውን እንደለበሱ ከመሰለፍም አልፈው አስተባባሪ ሆነው መታየታቸው በቂ ማረጋገጫ ነው” ይላል፡፡ አንዳንዱም የገንዘብ ምንጭ አድርገው ይጠቀሙበታል የሚለው ኢሕአዴግ፣ “የሃይማኖት አክራሪነትና ኪራይ ሰብሳቢነት በአገራችን ያላቸው የማይነጣጠል ትስስር” መገንዘብ የአክራሪነት ባህሪና ገፅታ ለመረዳት ያስችላል የሚል እምነት አለው፡፡

በእርግጥ፣ ኢሕአዴግ እንደሚለው ተቃዋሚዎች በሃይማኖት ግጭት እናተርፋለን ብለው ያስባሉ? ወይስ ገዥው ፓርቲ ትክክለኛ ባልሆነ መንገድ ተቃዋሚዎችን እየፈረጀና እየነጠለ ይሆን? በትክክል በእንደዚህ ዓይነት ወንጀል የተሰማሩ ተቃዋሚዎችስ ሕግ ፊት መቅረብ የለባቸውም? ተቃዋሚዎችስ በሃይማኖትም ሆነ በብሔር ሽፋን ግጭት እንዳይቀሰቀስ ምን ያህል ጥንቃቄ ያደርጋሉ? የሚሉና የመሳሰሉ ጥያቄዎች በጉዳዩ ላይ ሊነሱ የሚችሉ ናቸው፡፡

በዓማፂነት እየተንቀሳቀሱ የሚገኙት ሃይሎች መንግሥት እንደሚለው ሁሉ ከደሙ ንፁህ ናቸው ማለት ይከብዳል፡፡ በተለያዩ መንገዶች የኢትዮጵያን አንድነት ለማተራመስ ሌት ተቀን ደፋ ቀና ከሚለው የኤርትራ መንግሥት ጋር ..እጅና ጓንት.. ሆነው የሚሰሩ ወገኖች የፖለቲካ ዓላማቸውን ለማራመድ የማይፈነቅሉት ድንጋይ እንደሌለ ከሚያደርጉት እንቅስቃሴና ከሚያወጡዋቸው መግለጫዎች መገንዘብ እንደሚቻል ብዙዎች ይናገራሉ፡፡ በአገር ውስጥ በህጋዊነት የሚንቀሳቀሱ ወገኖች ግን “አጠቃላይ ፍረጃ” ይሉታል፡፡

አብዛኛዎቹ ተቃዋሚዎች እንደሚሉት፣ ኢሕአዴግ በአገር ውስጥ በሚፈጠር ማንኛውም ጥፋትና ችግር በእነሱ ላይ ማላከክ ይወዳል፡፡ የፖለቲካ ምህዳሩን ከሚጠቡበት መንገድ አንዱ እንደሆነና ኢሕአዴግ ተቃዋሚዎች ከሕዝብ ለመነጠል፣ ለማጥቃትና ለማሸማቀቅ እንደሚጠቀምበትም ይገልፃሉ፡፡ “ይህንን ግን ለችግሩ መፍትሄ አይሆንም” ይላሉ፡፡

የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ዶ/ር ሃይሉ አርአያ፣ “የሃይማኖት የአክራሪነት አመለካከት ምንጭ የ፣ከሰሩ ፖለቲከኞች፣ ናቸው” የሚለውን የኢሕአዴግ ፍረጃ “ራሱ የከሰረ አመለካከት” ይሉታል፡፡ ዶ/ር ሃይሉ ለሪፖርተር እንደገለፁት፣ “ኢሕአዴግ ራሱ የፈጠረውን ችግር መፍታት ሲያቅተው በእኛ ላይ ማላከክ አመሉ ነው” ያሉ ሲሆን በገዢነት ደረጃ እንዲህ የዘቀጠ አስተሳሰብ ማራመዱ አሳፋሪ እንደሆነ ይከራከራሉ፡፡ ለሃይማኖት መከባበር እንጂ ለግጭት ምክንያት የምንሆንበት ምንድን ነው? ሲሉም ይጠይቃሉ፡፡

የዓረና ትግራይ ሊቀመንበር የመድረክ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ገብሩ አስራት በበኩላቸው፣ ይህንን ሃሳብ ይጋራሉ፡፡ ኢሕአዴግ ማንኛውም ዓይነት ችግር ሲፈጠር በጉዳዩ ላይ ከማተኮር ይልቅ “እገሌ ያለው ነው፣ እገሌ ያስተጋባው ነው” በማለት በተቃዋሚዎች ላይ ጣቱን ይቀስራል ብለዋል ለሪፖርተር፡፡ እንዲያውም፣ የሕዝቡ የአስተሳሰብ ንቃተ ህሊና ዝቅ አድርጎ የመመልከት ውጤት መሆኑን ይናገራሉ አቶ ገብሩ፡፡ “ሕዝቡ የቧንቧ ውሃ አይደለም፡፡ በተወሰኑ ቡድኖች አመለካከት ብቻ የሚነዳ”፡፡ በሃይማኖትም ሆነ በሌሎች ምክንያቶች የሚነሱ ግጭቶች የራሳቸው ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ መነሻ እንደሚኖራቸው ገልፀው፣ ያንን ከስርዓቱ አንፃር ከመፈተሽ ይልቅ ተቃዋሚዎች የፈጠሩት ችግር ነው ማለት በራሱ መፍትሄ አይሆንም ይላሉ፡፡ “ስልጣንን በብቸኝነት ተቆጣጥሮ መኖር የሚፈልግ ነው ግጭቶች እያባባሰ የሚንቀሳቀስ”ም ይላሉ፡፡ አቶ ገብሩ፣ በሃይማኖት ዙሪያ ግጭት የሚቀሰቅስ ወገን አይተውም ሰምተውም እንደማያውቁ ገልፀው፣ “ይሄ የፖለቲካ ጉዳይ ሳይሆን የሕግም ጥያቄ ነው፡፡ እንዲህ ያደረገ አካል ካለ ሕግ ፊት መቅረብ ይኖርበታል” ይላሉ፡፡

ኢሕአዴግ የሃይማኖት አክራሪነት አመለካከት ከኪራይ ሰብሳቢነት አስተሳሰብና ከኋላ ቀርነት የሚያይዘው ሲሆን፣ እንደ መንግሥትም እንደ ድርጅትም በተደራጀ መልኩ የችግሩን ምንጭ ለማድረቅ እንዲህ ዓይነት አመለካከቶች በሕግም ሆነ በፖለቲካ እታገላቸዋለሁኝ ይላል፡፡ ተቃዋሚዎች በበኩላቸው እነዚህ አመለካከቶችና ግጭቶች አጠቃላይ የፖለቲካ ሁኔታ የፈጠራቸው በመሆኑ፣ መንግሥት ተቃዋሚዎች ላይ ጣት ከመቀሰር ፖሊሲውና ችግሩ ላይ እንዲያተኩር ያሳስባሉ፡፡ የሃይማኖት አባቶች የሚሰብኩት ሰላም የሚደነቅ ቢሆንም፣ በሃይማኖት ተቋማት የሚሰራጩ አንዱ በሌላው ላይ ያነጣጠሩ አንዳንድ ጽሑፎች መታረም እንዳለባቸው አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ፡፡


ቅ/ሲኖዶስ በብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ዝውውር ላይ የጀመረውን ውይይት ሳይፈጽም ቀረ


(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 25/2009)፦
ዛሬ ቀጥሎ በዋለው የቅ/ሲኖዶስ ስብሰባ በብፁዕ አቡነ ሳሙኤል የዝውውር ቦታ ጉዳይ ሲወያይ ውሎ አጀንዳውን ሳይቋጭ ተበትኗል። በትናንትና ውሎው ብፁዕነታቸውን ከአዲስ አበባ አንሥቶ ወደ ሌላ ቦታ ለማዛወር ከስምምነት የተደረሰ ቢሆንም ‘የት ይመደቡ?” የሚለውን ተመልክቶ ምክረ ሐሳብ (ፕሮፖዛል) እንዲያመጣ የተመደበው ኮሚቴ ባመጣው ምርጫ ስምምነት ሳይገኝ ቀርቷል።

ልማት ኮሚሽን፣ ሕጻናት ማሳደጊያ ወይም ትንሣዔ ዘጉባዔ የሚሉ ምርጫዎች ከመጡ በሁዋላ ብፁዓን አባቶች “ልማት ኮሚሽን ይመደቡ” የሚለውን በድምጽ ብልጫ ቢወስኑም ቅዱስ ፓትርያርኩ “እርሱ ቦታ ሌላ ሰው አለበት” በማለታቸው ከስምምነት ሳይደረስ ቀርቷል። በድምጽ ብልጫ የተወሰነውም ውሳኔ በእርሳቸው አለመስማማት ሳይሳካ ቀርቷል ማለት ነው።


ቅዱስ ሲኖዶስ ብድምጽ ብልጫ የሚሠራ ቢሆንም በእንዲህ ዓይነቱ አጋጣሚ ፓትርያርኩ “ድምጽን በድምጽ የመሻር” (ቬቶ) መብት (? ?) ውሳኔዎች ይታጠፋሉ። የዛሬው የአቡነ ሳሙኤል ምደባ ጉዳይ በቬቶ ከተሻረ በሁዋላ ጉባዔው መበተኑ ታውቋል። ስብሰባው ይጠቃለላል ብለው ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስማት የመጡ ጋዜጠኞችም ባዶ እጃቸውን ተመልሰዋል።
ጉባዔው ነገ ቅዱስ ፓትርያርኩ ወደ ሌላ ቦታ የሚሄዱ በመሆናቸው የማይቀጥል ሲሆን ሲመለሱ ወደ ረቡዕ አካባቢ ይደረግ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።
በተያያዘ ዜና ትናንት ተነሥቶ ለውይይት ሳይቀርብ የቀረው የማህበረ ቅዱሳን ጉዳይ ዛሬም በሌላ አባት በድጋሚ ተነሥቶ እንደነበር ታወቀ። በመምሪያውና በማህበሩ መካከል ያለው ችግር ሙሉ በሙሉ እንዲፈታ የጠየቁ አንድ አባት ሐሳባቸውን ለመወያያነት ለማብቃት የሞከሩ ቢሆንም ሳይሳካ ቀርቷል ተብሏል።
ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን

October 25, 2009

ቅ/ሲኖዶስ በሁለት አጀንዳዎች ላይ የጀመረውን ውይይት ሳይፈጽም አሳደረ

(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 23/2009)፦
ቅዱስ ሲኖዶስ በዛሬው ውሎው ስለ አዲስ አበባ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሲወያይ ውሎ ሳይጨርስ ለነገ አሳደረ። በሌላ በኩል አባ ሰረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል በማህበረ ቅዱሳን ላይ በቅርቡ ጽፈው በበተኑትና ለመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ሳይቀር ግልባጭ ባደረጉት ጠንካራ ደብዳቤ ዙሪያም ሐሳቦች ተሰጥተዋል ተብሏል።

አቡነ ሳሙኤልን በተመለከተ በተደረገው ረዥም ውይይት ቅዱስ ፓትርያርኩ “አቡነ ሳሙኤል ወደ መቐለ መቀየር አለባቸው” የሚል ሐሳብ አጠንክረው ይዘዋል። “ወደ አሶሳና ጋምቤላ ከመላክ መቐለ መላክ ሳይሻል ስለማይቀር ሐሳቡን ብትቀበሉት ይሻላል” በሚል ፓትርያርኩ ጫና ለማድረግ የሞከሩ ቢሆንም ቅ/ሲኖዶስ ሐሳቡን ሳይቀበለው ለበለጠ ውይይት ለነገ አሳድሮታል። አንዳንድ የቅ/ሲኖዶስ አባላት ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ከአዲስ አበባ እንዳይቀየሩ፣ መቀየራቸው ካልቀረ ግን ወደ ልማት ኮሚሽን የበላይ ጠባቂ ሆነው እንዲዛወሩ ሐሳብ አቅርበዋል ተብሏል።

በተያያዘ ዜናም ማህበረ ቅዱሳንን በተመለከተ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ ባነሱት ሐሳብ “በአባ ሰረቀ በኩል ማህበሩን በተመለከተ እየተሄደ ያለው አካሄድ ጥሩ ስላይደለ ጉዳዩ በሰላም ይፈታ” የሚል ሐሳብ እንዳቀረቡ የተጠቆመ ሲሆንብፁዕ አቡነ አብርሃምም ይህንኑ በመደገፍ ሐሳብ መስጠት ጀምረው እንደነበር ታውቋል። ቅዱስነታቸው በዚህ ጉዳይ ዙሪያ መነጋገር ፤ ለጊዜው አስፈላጊ አለመሆኑን በመጥቀስ ጉዳዩ ውይይት እንዳይደረግበት ዘግተዋል ተብሏል። ምናልባት በነገ ዕለት ጉዳዩ በድጋሚ ይነሣ ይሆናል የሚል ግምት ግን አለ።
ይህ የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ነገ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።
ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን

October 24, 2009

ቅዱስ ፓትርያርኩ “ይቅርታ አድርጉልኝ አባቶቼ፤ ሰዎች አሳስተውኝ ነው” አሉ፤

(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 23/2009)፦ ቅዱስ ፓትርያርኩ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ከቅ/ሲኖዶስ አባላት አባቶች ጋር ሰላም ለመፍጠር ባደረጉት እንቅስቃሴ በቅርቡ ስለተፈጠሩት ችግሮች “ሰዎች አሳስተውኝ ነው” ማለታቸውን ምንጮቻችን አስታወቁ።

“እርቅ ለማውረድ” በሚል በተከናወነ የሽምግልና ውይይት ላይ ቅዱስነታቸው ተናግረዋል እንደተባለው ከሆነ ከብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ጋር ያላቸው አለመግባባትም ሆነ ሌሎች ተመሳሳይ ችግሮች የተፈጠሩት ሰዎች ስላሳሳቷቸው መሆኑን መናገራቸው ተሰምቷል። ምንጮቻችን ጨምረው እንዳብራሩት ቅዱስነታቸው “ሰዎች ያሳሳቷቸው” ስለየትኛው እንደሆነ፣ የአባቶች በር መሰበርን ይጨምር አይጨምር ግን አላወቁም።

ቅዱስ ሲኖዶስ ካለፈው የግንቦት ወር ወዲህ ጠንካራ ችግር የገጠው ሲሆን የዚህ ውጣ ውረድ አካል የሆኑትና ስማቸው በተደጋጋሚ የሚነሣው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የነበሩት አቡነ ሳሙኤል ከፓትርያርኩ ጋር እርቅ ማውረዳቸው የተሰማ ሲሆን ይህ ማለት ግን ከዚህ በፊት ያነሱትን አጀንዳ ትተዋል ማለት እንዳልሆነ ታውቋል። ከአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ስለተነሱበት ሁኔታ ቅ/ሲኖዶስ በነገው ውሎው ይነጋገራል ተብሎ ይጠበቃል።

በተያያዘ ዜና ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ያለ አ/አበባ ሀ/ስብከት ፈቃድ በየትኛው የአዲስ አበባ ደብርና ገዳም ሄደው መቀደስም ሆነ ማስተማር እንዳይችሉ የሚያግድ ደብዳቤ መውጣቱ ታወቀ። ታይቶም ተሰምቶም በማይታወቅ ሁኔታ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በራሳቸው ፈቃድ ተነሥተው፣ ሄደው እንዳይቀድሱ እንዳያስተምሩ “እገዳ” የተጣለባቸው የዲሲና አካባቢው ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም በመርካቶ ራጉኤል ሲቀድሱ የብፁዕ አቡነ ሳሙኤልን ስም በቅዳሴ በመጥራታቸው እንደሆነ ታውቋል።

በቅርቡ ከኦስትሪያ መጥተው የሥራ አስኪያጅነትን ሃላፊነት በተቀበሉት በቀሲስ ፋንታሁን ሙጬ ፊርማ ወጪ የተደረገው ይኸው ደብዳቤ አባቶችን ማስቆጣቱ ታውቋል።

October 23, 2009

ቅ/ሲኖዶስ የሰንበት ት/ቤቶች ማ/መምሪያ በሊቀ ጳጳስ እንዲመራ ወሰነ

(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 23/2009)፦ ቅ/ሲኖዶስ በዛሬ የስብሰባ ውሎው የሰንበት ት/ቤቶች መምሪያ በሊቀ ጳጳስ እንዲመራ ወሰነ።

ቅዱስ ሲኖዶስ በአባ ሰረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል ሥር የነበረውን በመተው ከበላይ ሊቀ ጳጳሱን አቡነ ቀሌምንጦስን ሾሟል ተብሏል።
በተያያዘ ዜናም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ዋና መምሪያዎች የሆኑት የስስብከተ ወንጌል ሐዋርያዊ አገልግሎት እንዱሁም የሰበካ ጉባዔ መምሪያዎች በሊቃነ ጳጳሳት እንዲመሩ አባቶች መድቧል። በዚህም መሠረት ለስብከተ ወንጌሉ ብፁዕ አቡነ ማርቆስን፣ ለሰበካ ጉባዔ ደግሞ ብፁዕ አቡነ ያሬድን መሰየሙ ታውቋል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ዜና ርዕስ የሆነው ይኽ መምሪያ በሥሩ የሚተዳደረው ማህበረ ቅዱሳን ላይ እየፈጸመ በነበረው ሕግ ዘለል እርምጃ ፖለቲካዊ ትርጉም ይዞ የመገናኛ ብዙሃን መነጋገሪያ መሆኑ አይዘነጋም።

በዚህ አኳያ የሰንበት ት/ቤቶች መምሪያ በሊቀ ጳጳስ የሚተዳደር ከሆነ አባ ሰረቀ የሥራ ሃላፊነት ምን እንደሚሆን ለጊዜው ግልጽ አልሆነም።

Mahibere Kidusan, The Next Target?


By Ze Debre Zeit kidus Rufael
(zedebrezeitkidusrufael@yahoo.com)

Ethiopian Orthodox Tewahido Church (EOTC) is one of the ancient apostolic churches, having multi million followers with in and out side Ethiopia. This historic church has flourished for more than 1,600 years in the country, serving its followers and fulfilling the orders of Christ. It has also contributed significant share for the civilization of the country. The educational, health, economic, political, social and many other affairs of the country were significantly handled by the church scholars. Spiritual fathers even were playing fundamental role in defending the country against foreign invasion. The history of the priests who marched to Adwa, carrying the Arc of St Giorgis and the patriotic death of the archbishop martyr Abune Petros are some of the testimonies to this premise.

Recently however, the news being aired about the Ethiopian Orthodox Tewahido Church is being scary and gloomy. The Holly synod of the church is splited in two: one in the country and the other abroad. The synod in Addis Ababa has ex communicated the synod abroad, and vice versa. Racism is said to be deep rooted problem in the church .Some administrators and even bishops of church are also said to be highly corrupted. To this end, members of the holly synod have been accusing the unpopular Patriarch Abune Paulos. Though Ato Abay Tsehaye, State security and intelligence advisor, is said to have created concord and platform, the group of archbishops which is master minded by Abune Samuel, is still opposing Patriarch Abune Paulos and is requesting for administrative reformation. (1)

To curb this, it has been reported that supporters of Abune Paulos have created a lot of mace. The house of the archbishops, who protested Abune Paulos administration, was broken by “unknown” gangs. The rest archbishops were intimidated and harassed. When the dust seems settled, for the time being with the opposing archbishops, the wave of attack targeted the spiritual youth association which is suspected of being supporter of the opponent archbishop group. The patriarch, the intelligence advisor of the state, the federal affairs minister and some official of the church called for an emergency meeting and passed amazing decision against Mahibere Kidusan, one of the strong spiritual associations EOTC had. (2)

The crimes of Mahibere Kidusan according to pro Patriarch Paulo’s Groups:

The incident was like this. All of a sudden Aba Sereke Birhan, the newly appointed head for the Sunday School Department of EOTC, started questioning Mahibere Kidusan. With in few days, he called for a meeting to resolve the administrative problem encountered with this association.Ato Abay Tsehaye, the intelligence and security advisor of the state and Dr Shiferahu Tekle Mariam , federal affairs minister were invited to settle this administrative problem between the department head and the association (3) . One can imagine how much silly can it be when officials at ministry level are invited to participate on the meeting which was intended to resolve the administrative problem between one spiritual association and its department head. The actual reason was far beyond that, actually.

On the meeting Aba Sereke, accused Mahibere Kidusan for many seemingly administrative things. Addis Admas and Addis Neger has reported upon the issue extensively .Hereunder are some of the major crimes Mahibere Kidusan committed as per the officials (4)

1. በ1993 በቅድስት ማርያም በተ ክርስትያን ለመጠለል የመጡ ተማሪዎች በፖሊስ ሲወሰዱ በተ ክርስትያን መጠለያ ባልመስጠትዋ አፍረናል ብለው በጋዙጣቸው መገግለጫ አወጡ
2. there is a sign that the executive members of Mahibere Kidusan are inclining towards politics
3. The news paper of this association is trying to create gap between the government and the followers of EOTC. The evidence according to them was the commentary posted about the last census
4. The association is trying to create again gap in between the fathers (?) of the church and the followers of the religion
It is beyond funny when Aba Sereke accuses Mahibere Kidusan for reporting the unfairness of the agreement to hand over students who were sheltered in Saint Marry church in 1993, on its newspaper Simea Tsidk. During that time, the students don’t want to participate on any kind of violence and went to the church of Saint Marry, in search of peace. Other students also went to another place for the same purpose. But those students who were in Saint Mary church was taken by security force and thrown to different jails. This was ridiculous. Reporting this was crime of Mahibere Kidusan for Aba Sereke and the officials.

The validity and the reliability of the result of the recent census conducted in Ethiopia was also questionable for many citizens and any logical person. For reason which is hard to accept, millions are missing. Besides, the issue whether monks, hermits and nuns who are living in far places and in accessible monasteries and nunneries are counted or not was also under debatable question. Shedding light upon this issue was a crime Mahibere Kidusan committed for Aba Sereke and the officials.

Archbishops’ house was broken, for the simple reason that they opposed the corruption, racism and other unethical deeds in the church. Even some were intimidated and harassed. Opposing this open crime is again wrong as per the eyes of the “enlightened” officials.

Despite the strong opposition and evidence Mahibere Kidusan portrayed for not involving in politics, the ministers have insisted it has shown inclination. Ato Abay has also given warning for it: a warning for no valid reason.

Recent propagandas against Mahibere Kidusan
Pro government Medias,fans of the Patriarch’s and others are posting different article about Mahibere Kidusan since then. Aiga forum, Pro EPRDF government web page has posted the following analysis regarding the secret network between Addis Neger newspaper (notorious newspaper according to them) and Mahibere Kidusan.

“አዲስ ነገር የተመሰረተችው ከተመሳሳይ ሙያ የፈለሱ ተመሳሳይ እድሜ ባላቸው፣የተቀራረቡ የትምህርት ደረጃና ተመሳሳይ የፖለቲካ አቋም ባላቸው
ሰዎች ነው፡፡ በርካታዎቹ አምደኞችና አዘጋጆች ቀደም ሲል የቤተ ክህነት
ዲያቆናት የነበሩ፣ የማህበረቅዱሳን አባላትና በቅንጅት ዙሪያ የተሰባሰቡ
የፖለቲካ ፓርቲዎች አባላትና ጠንካራ ደጋፊዎች የነበሩ ሰዎች ናቸው ፡፡

ከዚህ አንፃር በሕትመቶቹ ይዘት ላይ በጉልህ
ተፅፎ የሚታየው የአዲስ ነገር ድርጅታዊ ባህል ፀረ ዴሞክራሲያዊ ፣ ሁሉን
ኮናኝ (Nihilist) ፀረ-ስርአተኛ (anti establishment) እና ጽልመተኛዊ
መሆኑ አያጠያይቅም፡፡ የሚንቀሳቀሱበት ድርጅታዊ ባህልም ዴሞክራሲያዊ
ስርዓቱን የማፍረስ ተልእኮና ግቦች ያሉት ጥርሱ ተበልቶ ያለቀ የአሮጌ
ባህል መዘውር ተደርጎ ለወሰድ ይችላል ፡፡ ይህ የአዲስ ነገር ፀለምተኛና፣
ፀረ ሥርአት ዝንባሌ በዴሞክራሲያዊ አገሮች ፕሬሶች የመንግስትን
ክንዋኔዎች በመተቸት ከሚያቀርቧቸው መጣጥፎች ጋር አንዳችም
ተመሳሳይነት እንደሌለው መጤን ይኖርበታል፡” (5)
Christian and Muslim “religions scholars” have opened new web pages and blogs to denounce Mahibere Kidusan. Mahibere Erkusan is the blog opened by the “Muslim elites” and Mahibere Seytan is of the concerned Christians. These scholars of different faith are speaking the same language to express the sinof Mahibere Kidusan. The” Muslim” blog express Mahibere Kidusan like this:

“This is to expose the real objective behind the so called mahabera 'Qudusan'. While mehaber means association in Amharic Qudusan stands for holy. The association portrays itself as a religious organization, but its activities proves that its objective is political and mainly to subjugate Muslims. In fact due to its anti-Islam and anti-Muslim activities many call it mehabera-erkusan (the cursed-association). It plays a very sophisticated political game and to make sure the superiority of the Church and the revival of the old monarchies. Some of the political parties are even under the mercy of this fanatic organization…. This association is well financed and well organized that even many Muslims recently claim that the government is reflecting its influence. They are behind the recent provocations and it is the core of Christian islandists. In fact many claim that they have already overtaken the guideline of many governmental sects (especially educational institutions) and they are closer than ever to effectively overtake the power.” (6)

Ethiomuslim webpage columnist have also expressed its view for Mahibere Kidusan like this
“Mahbera Qidusan is a band of illogical, anti-Ethiopia dabtaras who happen to get some kind of uncritical western academics” 7

The other dedicated “orthodox Christian’s” on their new blog, with the name Mahibere Kidusan weys Mahibere Seytan, also warn that this association is a political organization. A new book is also published in title Mahibere Kidusan weys Mahibere Seytan by these concerned “orthodox Christians”. It is amazing when Muslim scholars and Christian scholars agree and share the same term to accuse a Christian orthodox association for this and that story. The protestant pastors have also showed their hatred for this association .The International Christian Concern, citing Christian pastors in Ethiopia has also reported like this:

“Christian sources said a group within the EOC called "Mahibere Kidusan" ("Fellowship of Saints")…. The increasingly powerful group's purpose is to counter all reform movements within the EOC and shield the denomination from outside threats.” (8)

In a nut shell, many “concerned religious bodies” are repeating Ato Abay Tsehaye's sentence in different words. Though the name of the organizations differs, the idea they generate is the same. Even the words they used to denounce Mahibere Kidusan are similar. It seems that they originate from the same root source. .

The Suspected Invisible Plot
Long before, the popular Ethiopian webpage ECAD9 forum has exposed governments plan to arrest prominent religious leaders. No question that this plan targets Mahibere Kidusan members. Deje Selam another spiritual blog on its October 21, issue has posted the sad news to that end

“የመንግሥት የደህንነት መሥሪያ ቤት ቅዱስ ሲኖዶስን ለመጫን በቤተ ክርስቲያናቱ የውስጥ ተግባር በገቡበት ጉዳይ ዛሬ ከስድስት የማያንሱ ብፁዓን አባቶችን ለጊዜው ቦታውን ወዳላወቅነው ቦታ በመውሰድ ነገ በሚጀመረው ስብሰባ ላይ ስለ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤልም ሆነ ስለ ማህበረ ቅዱሳን ምንም እንዳይናገሩ ማስጠንቀቂያ መስጠታቸውን ምንጮቻችን ገለፁ።” (9)

Many things are getting very clear now. Though the constitution prohibits any government involvement in religious activities, practically government bodies are dictating as to what religious leaders should discuss and what not, in the holly synod. I don’t think so that even the then Marxist government did this. Why do government requested the archbishops not to raise the issue of Mahibere Kidusan on their meeting? It is self explanatory. After few days arrest news on targeted members of this association like Dn Daniel Kibret will be announced.


Its Dangerous Aftermath

I know different bodies have different attitudes about Mahibere Kidusan. Despite what so ever feelings and attitudes we have however, no one denies the significant contribution this association made to EOTC. This association, hand in hand with different concerned bodies, has established Gibie Gubaes in every higher learning institutions of Ethiopia. For the first time in Ethiopian History of Ethiopia, Mahibere Kidusan has prepared spiritual curriculum and structured spiritual education for these institution students. One can state many achievements the association did: the books, magazines, tracts, newspapers and etc published; the projects implemented for different ancient monasteries, the spiritual songs released , the web pages constructed, the radio station started and so on.

Attacking Mahibere Kidusan is attacking all these sacred objectives and deeds. By the time when every religious institution is so organized to steal sheep, weakening and eventually dismantling the churches strong youth structure do have its own negative impact for the church .Every follower of Tewahido Christian, despite what so ever difference we have, shall fight this attempt.

The government bodies should also think upon what they are doing critically. Dismantling a peaceful spiritual association which do have around 50,000 highly educated members may have its own grave consequence. Their irresponsible act is leading many youths to another extreme end. Many members are expressing their anger through various means since the very beginning of this attempt. It may even lead to other crises in the country since government officials are intimidating innocent youths who have never involved in any type of conspiracy except exercising their religion peacefully. Government may boast for crushing so many political riots and parties and consider dismantling Mahibere Kidusan as a simple task. It is advisable if the government thinks upon it again and again.

The zeal and anger every member is exhibiting now is a huge potential for the association too. Members are seen and heard expressing their commitment more than any other time. In the mean time, the nation from east up to west has got the opportunity to truly know who Mahibere Kidusan is Those at the leading position of this association should devise method to tap this huge resource to the betterment of the church.

References
1. http://deje-selam.blogspot.com/2009/10/blog-post_03.html
2. http://www.addisadmass.com/Yesemonun/news_item.asp?NewsID=279
3. Addis Neger News paper , Meskerem 16, 2009
4. Addis Admas, October 04,2009
http://www.addisadmass.com/Yesemonun/news_item.asp?NewsID=279
5. http://aigaforum.com/articles/comment_on_addisneger.pdf
6. http://mahaberaerkusan.blogspot.com/2009/04/mahabera-qudusan-by-its-own-words.html
7. http://ethiomuslimsmedia.com/muslim/index.php?option=com_content&view=article&id=104:obsession-of-the-mahbera-qdusan&catid=3:newsflash
8. http://www.rightsidenews.com/200909266611/global-terrorism/prison-terms-upheld-for-two-christians-in-ethiopia.html
9. http://ecadforum.com/blog/2009/04/11/103-ecadf-news-addis-ababa/
10. http://deje-selam.blogspot.com/2009/10/blog-post_5208.html

የለንደን ቅ/ማርያም ቤተ ክርስቲያን ለቅ/ሲኖዶስ ጥሪ አቀረበ


(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 22/2009)፦ ርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅ/ማርያም ቤተ ክርስቲያን “የወቅቱን የቤተ ክርስቲያናችንን ችግር አስመልክቶ ለቅዱስ ሲኖዶስ “ቤተ ክርስቲያንን የማዳን ጥሪ” አቀረበ።

ሙሉ መግለጫውን ለመመልከት ይህንን  ይጫኑ።

መግለጫውን የላኩልንን ወንድም/ እህት በደጀ ሰላም ስም ከልብ እናመሰግናለን።

ቸር ወሬ ያሰማን፣

አሜን

October 22, 2009

ኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት - "በቤተክርስቲያኗ አባቶች መካከል ተፈጥሮ የነበረው አለመግባባት መፈታቱ ተገለፀ"


ውድ ENA፦ ለመሆኑ እነዚህ የተባሉት አባቶች መቼ ተገናኝተው ተነጋገሩ? በምን ጉዳይ ላይ ተነጋገሩ? ማን ዳኛቸው? ነው ወይስ እነ እንትና የሰጡትን ማስጠንቀቂያ እንደ ችግር መፍቻ ተቆጠረ። ወይ ጉድ!!!
ለማንኛውም ደጀ-ሰላማውያን እሰቲ አንብቡት።
ቸር ወሬ ያሰማን፣ አሜን
+++++++
አዲስ አበባ, ጥቅምት 12 ቀን 2002 (ENA/ኢትዮጵያ ዜና አገለግሎት) - በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሐዶ ቤተክርስቲያን የኃይማኖት አባቶች መካከል ተፈጥሮ የነበረው መጠነኛ አለመግባባት በቅን መንፈስና አባታዊ በሆነ መንገድ መፈታቱን የቤተክርስቲያኗ ፓትርያርክ ብጹዕ ውቅዱስ አቡነ ጳውሎስ አመለከቱ፡፡ በዓመት ሁለት ጊዜ የሚካሄደው የቤተክርስቲያኗ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ዛሬ ተጀምሯል፡፡

ፓትርያርኩ ጉባኤውን ሲከፍቱ እንደተናገሩት ዓለም በየጊዜው ከፍተኛ የእድገት ለውጥ በምታመጣበት በአሁኑ ወቅት ሁሉም ወገን ችግሮቹን በሰላማዊ መንገድ በመፍታት ለሀገሩን ልማት ዕድገት የበኩሉን አስተዋፅዖ ማበርከት አለበት ብለዋል፡፡

የመደማመጥና የመተሳሰብ ብሎም የመረዳዳት ባህል በማጎልበት ለሕዝብና ለሀገር አርአያ መሆን እንደሚያስፈልግ አመልክተው በቅርቡ በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ተፈጥሮ የነበረው መጠነኛ ችግርም አባታዊና መንፈሳዊ በሆነ መንገድ መፈታቱን ተናግረዋል

የሰላም ባህል እንዲስፋፋም መደማመጥ፣መከባበር መወያየትና አንዱ የሌላውን ሐሳብ መረዳት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ ከዚህ አኳያም ቤተክርስቲኗ የሰላምና የእርቅ እንዲሁም አብሮ በሰላም የመኖርና የመቻቻል ስሜት እንዲጎለበት ጥረት ማድረግ እንዳለባትም ገልፀዋል፡፡

ፓትርያርኩ እንዱሉት ክርስቲያኖች በአኗኗራችን ሰላም ለሚሰፍንበት ስነ ምግባር ተጠቃሽ ምሳሌዎች መሆን ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡

ቤተክርስቲያኗ እስካሁን ያከናወነቻቸው ተግባራት የሚያስመሰግኑ ናቸው ያሉት አባ ጳውሎስ ከዚህ ይበልጥ ለመሥራት በሙሉ ኃይል እንድተነሳም የላቀ ተሳትፎ እንደሚጠበቅባትም አመልክተዋል፡፡

ለዚህ ደግሞ ከሁሉም በላይ የውስጥ አንድነትን በማጠናከርና የወቅቱን ሁኔታ በመከተል የበለጠ ሥራ እንደምትሠራ ተናግረዋል ።

የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትን በአምስት ዞኖች መመደብ፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ ጉዳይ እንዲያጣራ የተሰየመው ገለልተኛ ኮሚቴ ሪፖርት ላይ ተወያይቶ ውሳኔ መስጠት እንደሆኑም አመልክቷል፡፡

በተጨማሪም የዘመኑን በጀት ማጽደቅ፣ የቤተክርስቲያኒቱን የቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደር ጉዳይ፣ ከየአህጉረ ስብክቱ የሚቀርቡ ልዩ ልዩ ጉዳዮችና በሌሎች ርእሶችም ላይ የሚወያይ ሲሆን የተለያዩ ውሳኔዎችን እንደያሳልፍም የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዘግቧል ።

(ሰበር ዜና) መንግሥት አባቶችን አስጠነቀቀ ተባለ

• ከተወሰዱት አባቶች መካከል አንዱ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ናቸው
(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 21/2009)፦ የመንግሥት የደህንነት መሥሪያ ቤት ቅዱስ ሲኖዶስን ለመጫን በቤተ ክርስቲያናቱ የውስጥ ተግባር በገቡበት ጉዳይ ዛሬ ከስድስት የማያንሱ ብፁዓን አባቶችን ለጊዜው ቦታውን ወዳላወቅነው ቦታ በመውሰድ ነገ በሚጀመረው ስብሰባ ላይ ስለ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤልም ሆነ ስለ ማህበረ ቅዱሳን ምንም እንዳይናገሩ ማስጠንቀቂያ መስጠታቸውን ምንጮቻችን ገለፁ።
(ፎቶ፦ ከግራ ወደ ቀኝ፦ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል እና ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ)

መንግሥት ፓትርያርኩ የሚፈጽሙትንና እየፈፀሙ ያሉትን ጥፋት ሙሉ በሙሉ በመከላከል ይልቁንም ችግሩን ለማስተካከል አባቶች የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ፊት ለፊት በመቃወም፣ ከዚያም አልፎ አባቶችን እንዲህ ባለ ሁኔታ በማስፈራራት በመፈጸም ላይ ያለው ስሕተት ብዙ መዘዝ ሊያመጣ እንደሚችል ምንጮቻችን አብራርተዋል።

ዝርዝሩን እንደደረሰን እናቀርባለን።

October 21, 2009

"ቤተክርስቲያን በልማቱ መስክ የምታደርገውን ተሳትፎ ይበልጥ አጠናክራ ትቀጥላለች":- የዓመቱ ምርጥ ቀልድ

(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 21/2009)፦
ይህ ከዚህ በታች ያለው የ“ENA” ዜና ስለ ቤተ ክርስቲያናችን “ዕድገት” እና “ጥንካሬ” የሚያትት ነው። በርግጥ ለሚዲያው ፍጆታ እና “ለመሸዋወድ” ይጠቅም ካልሆነ በስተቀር ቤተ ክርስቲያናችን ያለችበት ሁኔታ መቸም አይጠፋንም። ገዳሞቻችን እንዴት እንዳሉ፣ ምዕመናችን ያለ እረኛ እንዳለ፣ የገጠር አብያተ ክርስቲያናት “የካህን ያለህ” እያሉ በመዘጋት ላይ መሆናቸው የአደባባይ ምሥጢር ነው። ለቤተ ክህነት ሃላፊዎች ግን ይህ ሁሉ የለም፤ ሻምፓኝ ለመክፈት፣ ኬክ ለመቁረስ ደግሞ አሁን “የልማት አርበኞች” የምትባል ፖለቲካ ቀመስ ፋሺን ጀመሩ። አሳፋሪዎች!!!አዲስ አበባ, ጥቅምት 11 ቀን 2002 (አዲስ አበባ)- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከመንፈሳዊ አገልግሎት ጎን በልማቱ መስክ የምታደርገውን ተሳትፎ ይበልጥ አጠናክራ እንደምትቀጥል አስታወቀች፡፡ ቤተክርስቲያኗ በተለያዮ የልማት ዘርፎች የተሳተፉ 45 አብያተ ክርስቲያናትን ትናንት ሸልማለች፡፡
ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ የአለም አብያተ ክርስቲያናት ፕሬዚዳንት አብያተ ክርስቲያናቱ ሲሸለሙ እንደገለጹት ቤተክርስቲያን በልማት መስክ በስፋት በመሳተፍ ለአገር እድገት የበኩሏን አስተዋጽኦ እያበረከተች ናት፡፡
በአሁኑ ወቅተ በርካታ አብያተ ክርስቲያናት በልማት ዘርፍ በመሳተፍ ውጤት እያስመዘገቡ ነው ያሉት ፓትርያርኩ ይህ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልጸዋል፡፡

በሰሩት የልማት ስራ ለሽልማት የበቁት አብያተ ክርስቲያናት የተመረጡት ከመላው አገሪቱ ሲሆን ጳጳሳትና የሰበካ ጉባኤ አባላቱ ልማትን የበለጠ አጠናክረው መቀጠል እንዲችሉ ጀኔሪተር፣ የውሃ ፓንፕ፣ ኮምፒውተርና ሌሎች ሽልማቶች ተሰጥቷቸዋል፡፡

ሽልማቱን ከተቀበሉት መካከል የናዝሬት ዶብረ ፀሐይ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ መላከፀሐይ አባ ገብረማሪያም ወልደሐዋርያት እንዳሉት ቤተክርስቲያን በልማቱ መስክ መሳተፏ ለድሕነት ቅነሳው የበኩሉን አሰተዋጽኦ እያበረከተ ነው፡፡

ናዝሬት ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ከተገነባው ትምህርት ቤት በወር እስከ 76 ሺህ ብር ገቢ የሚገኝ በመሆኑ የቤተክርስቲያኗ አገልጋዩች ከተረጂነት መላቀቃቸውን ገልፀዋል፡፡

ሌላው ተሸላሚ የምስካይየ ሕዙናን መድሐኒ አለም ገዳም ዋና ፀሐፊ ቀሲስ ሰይፉ ጌታቸው በኩላቸው ሽልማቱ ቤተክርስቲያን የጀረችውን የልማት ስራ አጠናክራ እንድትቀጥል ያበረታታል ብለዋል፡፡

በአሁኑ ወቀት ቤተክርስቲያን በትምህርት ቤት፣ በጤና ጣቢያ እንዲሁም በሌሎች የማሕበራዊ አገልግሎቶች ላይ በመሳተፍ እራሷን መቻሏን አመልክተው ሁሉም ይህንኑ ፈለግ መከተል እንደሚገባቸው ተናግረዋል፡፡

ቤተክርስቲያን በልማሑ ዘርፍ መሳተፏ ከአገልጋዮጓቿ አልፎ ሕብረተሰቡን የሚረዳ በመሆኑ ይህንኑ በማጠናከር በአሁኑ ወቅት ገዳሙ በ19 ሚሊዮን ብር የኮሌጅ ግንባታ እያካሔደ መሆኑን ጨምረው ገልፀዋል፡፡

የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባዔ ነገ ይጀመራል፣ አባቶች ምንም እንዳይናገሩ እየተነገራቸው ነው፤

• የመንግሥት ባለሥልጣናት ብፁዓን አባቶችን ለብቻ ለማነጋገር ሞክረዋል


(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 21/2009)፦ በጉጉት ሲጠበቅ የቆየው የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባዔ ነገ ሐሙስ ጥቅምት 12/2002 ዓ.ም (10.22.2009) እንደሚጀመር ሲጠበቅ ዓመታዊው የሰበካ መንፈሳዊ ጉባዔ በበኩሉ በትናንትናው ዕለት ተፈጽሟል። ዛሬ በዋዜማው ጸሎት ይደረጋል። በዚህ ጉባዔ ለመገኘት አባቶች የተሰባሰቡ ሲሆን ያለፈውን ተቃውሞ የመሩት ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ ግን መታመማቸው ታውቋል። ከሕመማቸው አገግመው ከስብሰባው ይገኙ አይገኙ እንደሆነ አላወቅንም።

በዓመት ሁለት ጊዜ የሚከናወነው የቅ/ሲኖዶስ ጉባዔ በጉጉት እንዲጠበቅ ያደረገው በቅዱስ ፓትርያርኩና በቅ/ሲኖዶስ አባላት መካከል በተነሣው የሕገ ቤተ ክርስቲያንና የአስተዳደር ጉዳይ ልዩነት መሆኑ ሲታወስ በዚሁ ሰበብ የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ከሥልጣናቸው መታገዳቸው አይዘነጋም።

ባለፈው ግንቦት በጀመረውና እስከ ሐምሌ አጋማሽ በዘለቀው ልዩነት ቅዱስ ፓትርያርኩ ሕገ ቤተ ክርስቲያንን አልቀበልም በማለት ሲገፉ፣ የእርሳቸውን ሐሳብ እንደግፋለን የሚሉ ወገኖች ደግሞ የርሳቸውን ተቃዋሚ አባቶች ቤት በመሰባበር፣ አባቶችን በማፈንና ዛቻና ማስፈራሪያ በማድረስ ታሪካዊ ስሕተት ፈጽመዋል። እስካሁን በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ባልዋሉት በነዚህ ወንበዴዎች ድርጊት የቤተ ክርስቲያኒቱ ልጆች በእጅጉ ያፈሩ ሲሆን ድርጊቱ በየአቅጣጫው ሲወገዝ መቆየቱ ይታወሳል። የድርጊቱን ፈጻሚዎች ማንነት ለማጣራት በተደረገው ግላዊ አሰሳ ነገሩ ከፓትርያርኩ አቡነ ቀሲስ (የቅርብ ረዳት) የወጣ ትዕዛዝ መሆኑ ላይ የደረሰ ሲሆን የመንግሥት የደህንነት ክፍል እጅም እንዳለበት አሳማኝ ፍንጮች አሉ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የቤተ ክርስቲያንን ጉዳይ እሸመግላለሁ በማለት ላይ የሚገኙት የመንግሥት የደህንነት መሥሪያ ቤት ሃላፊ አቶ አባይ ፀሐዬ በትግራይ አህጉረ ስብከት የሚገኙ ሊቃነ ጳጳሳትንና ጉዳዩ የሚመለከታቸውን ሰዎች በመሰብሰብ ልዩ ምክክር ማድረጋቸው ታውቋል። በቅዱስ ሲኖዶስ አባላት አባቶች አነሳሽነት የተንቀሳቀሰውንና ቤተ ክርስቲያኒቱን ከፓትርያርክ ጳውሎስና ከዘመዶቻቸው አስነዋሪ አስተዳደር ለመታደግ በተጀመረው እንቅስቃሴ እረፍት ያጣው መንግሥት የትግራይን ጳጳሳት በመሰብሰብ “አረጋጉ” ማለቱ ታውቋል። ማረጋጋት ማለት አቡነ ጳውሎስን አትናገሩ፣ ፀጥ እረጭ ብላችሁ ተገዙላቸው፣ ቤተ ክርስቲያናችሁ ስትጠፋ ተመልከቱ ማለት እንደሆነ ለጊዜው አልታወቀም።
በሌላም በኩል ሰሞኑን የደረሱን መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከሆነ የመንግሥት ተወካዮች በቀጥታ በቤተ ክርስቲያኒቱ ጉዳይ በመግባት አባቶች ስለ ፓትርያርኩ ምንም እንዳያነሡ መመሪያ ቢጤ በመስጠት ላይ ናቸው። “እርሳቸው ተሻሽለዋል፤ ችግሩ ይፈታል” በሚል ማግባቢያ በመደለል ላይ ያሉት እነዚሁ ባለሥልጣናት በቤተ ክህነቱ ያለው ሙስናና የዘር አሠራር “ተሻሽሏል” ለማስባል የተወሰኑ የፓትርያርኩ ዘመዶች ከቦታቸው እንዲነሡ ተደርገዋል። በዚህም መሠረት የፓትርያርኩ ረዳት አቶ ሙሉጌታና ፀሐፊያቸውና የምታስሾመው የምታስሽረው አፀደ የተባለች ዘመዳቸው የተቀየሩ ሲሆን እነዚህን ሰዎች ማንሣታቸው “የቤተ ክርስቲያንን ችግር እንደቀረፉ” ተደርጎ እንዲቆጠርላቸው ያደረጉት መሆኑ ታውቋል።
ከዚህ ባሻገር የተቃውሞ በሮችን ሁሉ ለመዝጋት “ይናገራሉ” ተብለው የሚታሰቡ አባቶች ላይ የተጀመረው የስም ማጥፋት ዘመቻ ተጧጡፏል። ራሱን የፓትርያርኩ ሕጋዊ ወኪል ነኝ የሚለውና ከዚህ በፊት በጥንቆላ ሥራ ላይ ተሰማርቶ በቤተ ክርስቲያኒቱ ስም ሲነግድ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ሕጋዊ ክስ አቅርበው ሥራውን ያቆሙበት “ጌታቸው ዶኒ” (አሁን ቄስ ነኝ ባይ) በተባለው ሰው በተጻፈና ትናንት ለሕትመት በበቃ “መሰናዘሪያ” በተሰኘ የአዲስ አበባ ጋዜጣ ላይ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤልና ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጥቃቱ ዒላማ ሆነዋል። ይኸው ግለሰብ ከዚህ በፊት “ኢትዮ-ቻነል” በተባለ ጋዜጣ ላይ አባቶችን የሚያብጠለጥል፣ ፓትርያርኩ ተጠሪነታቸው ለቅዱስ ሲኖዶስ መሆን የለበትም ቅ/ሲኖዶስ ለፓትርያርኩ ተጠሪ መሆን አለበት የሚል ጽሑፍ ያወጣ መሆኑ ይታወሳል። ግለሰቡ የቤተ ክርስቲአንን ችግር በማጣመም “መፈንቅለ ፓትርያርክ ሊደረግ ነው፤ ማህበረ ቅዱሳን ፓትርያርኩን ሊገለብጥ ሲል ተያዘ” ማለቱም ታውቋል።
በሌላም ነገ በሚጀመረው በዚሁ ጉባዔ ላይ የማህበረ ቅዱሳን ጉዳይ ይነሣል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ከጉባዔው የተወሰኑ ቀናት ቀድሞ አባ ሰረቀ ብርሃን የተባሉት የሰንበት ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ሃላፊ የጻፉት ማህበረ ቅዱሳንን የተመለከተ ደብዳቤ ለሰበካ ጉባዔ ስብሰባ ለመጡት አባቶች መታደሉ ታውቋል። የመንግሥት ባለሥልጣናት በተገኙበት ስለ ማህበረ ቅዱሳን የተደረገው ስብሰባ ውጤት ይዟል የተባለው ይኸው ደብዳቤ በዋና ሥራ አስኪያጁ በብፁዕ አቡነ ይስሐቅ ፊርማ እንዲወጣ ሲጠበቅ ብፁዕነታቸው “ስብሰባውን አላምንበትም፤ ደብዳቤውንም አልጽፍም” በማለታቸው አባ ሰረቀ እንደጻፉ ታውቋል። ከደብዳቤው በተጨማሪም የስበሰባው ቃለ ጉባዔ ነው የተባለና በዕለቱ የተገኙ አባቶች የፈረሙበት ወረቀት ተያይዞ የቀረበ ሲሆን ስለ ጉዳዩ አስተያየታቸው እንዲሰጡ የተጠየቁ ስብሰባው ላይ የተካፈሉ አባቶች ግን ቃለ ጉባዔው ላይ አለመፈረማቸውን፣ የሆነ ሰው የነርሱን ፊርማ አስመስሉ መፈረሙን ተናግረዋል። ጉዳዩንም በቅ/ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ በቁጭት ተናግረዋል። “ይህንን ሁሉ የሚያደርገው ሰረቀ ነው፤ እንዴት ፊርማችንን አስመስሎ ይፈርማል” ማለታቸውንም ምንጮቻችን ገልጸዋል።

October 16, 2009

ለኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ: Petition

(ደጀ ሰላም፤ አክቶበር 16/2009)፦ ፔቲሽኑን ለመፈረም ወደዚህ ይሂዱ፤


ውድ ደጀ ሰላማውያን፣ ለብዙ ጊዜ ስንጠብቀው የነበረው ለቅዱስ ሲኖዶስ የምናቀርበው “ፔቲሽን” እነሆ በዚህ መልኩ ተዘጋጅቷል። ይህንን ጽሑፍ ያዘጋጁትን ወንድሞች እህቶች ከልብ እናመሰግናለን። እነሆ በማንበብ ለሚመለከታቸው ሁሉ ለማድረስ ትሞክሩ ዘንድ ደጀ ሰላም በትህትና ታሳስባለች።
ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ከምንገኝ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ተከታዮች፣
ለኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ
አዲስ አበባ።
ቀን፦ ጥቅምት 6/2002 ዓ.ም
መግቢያ
ቤተ ክርስቲያናችን መሠረቷና ጉልላቷ ክርስቶስ ሆኖ ከተመሠረተ ጀምሮ ሕዝቦቿን በፍቅር በሰላም በአንድነት ስትመራ ስለ ክርስቶስ ወንጌል እና በሰማያት ስላለው ክብር ስትመሰክር እስከ ዛሬ ደርሳለች። ሆኖም እስከ ዛሬ የደረሰችው ያለ ችግር እና ያለ ፈተና አይደለም። ታሪክ እንደሚያስታውሰን ፈተናዋ ብዙ ቢሆንም በሁሉ ላይ ሥልጣን ያለውን እግዚአብሔርን በመያዟና በትክክለኛው የእግዚአብሔር ቃል የሚሄዱ፣ ከዚህ ዓለም ተድላና ደስታ ይልቅ ለእግዚአብሔር ራሳቸውን ጃንደረባ ያደረጉ ልጆች ስለነበሯት ነው። እነርሱ ፈተናውን በመንፈሳዊ ድል አሸንፈው ለእኛ አስተላልፈውልናል።ይህም ከአባቶቻችን የተሰወረ አይደለም።

የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር በክርስቶስ ወንድሞቻችን በሚሆኑ በግብጽ አባቶቻችን ተይዞ ቢቆይም በእግዚአብሔር ፈቃድ በአባቶቻችን ያላሰለሰ ጥረት ቤተ ክርስቲያን ከራሷ ልጆች ጳጳሳትን መሾም ከጀመረች ጀምሮ የማይናቁ ተግባራትን አከናውናለች። ቤተ ክርስቲያን በአሁኑ ጊዜ ጥሩ ጥሩ የአገልግሎት ጅምሮች ቢኖሯትም እንኳን መሥራት ከሚገባት ብዙ ተግባር አኳያ ሲታይ ገና ምንም ያልተነካ እንዲያውም ለሕልውናዋ እንኳን የሚያሰጋት ፈተናዎች በተጋረጡበት ዘመን ላይ ትገኛለች።

በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ የምናያቸው ችግሮችን ለመፍታት ሁሉም የቤተ ክርስቲያኒቱ አካላት (ምዕመናን፤ ካህናት፤ ቅዱስ ሲኖዶስ) እና በልዩ ልዩ ቦታዎች በቤተ ክርስቲያኒቱ አስተዳደር ያሉ ሰዎችን የሚመለከት ነው። እነዚህን አካላት ሁሉ የሚያዝዝ በቤተ ክርስቲያን ላይም ሙሉ ሥልጣን ያለው ቅዱስ ሲኖዶስ ስለሆነ ቅዱስ ሲኖዶሱ ለቤተ ክርስቲያኒቱ የሚያስፈልጋትን እያቀደ ቢያዝዝ ችግሮቹ በአብዛኛው እንደሚፈቱ እናምናለን።
የዚህ ደብዳቤ ዓላማም ቤተ ክርስቲያን ያለችበትን ዘመን በመዋጀት ለምዕመናን ምሳሌ እና አርአያ በመሆን በነገር ሁሉ የሚጠበቅባትን ለመሥራት እንድትዘጋጅ እንደ ቤተ ክርስቲያን ልጅነታችን ለማሳሰብ፤ በአሁኑ ጊዜ በአባቶቻችን መካከል የተፈጠረው አለመግባባት እልባት እንዲያገኝም ለማመላከት ነው። ይህን ሐሳብ ከዚህ በታች ስማችን የተያያዘ የቤተ ክርስቲያኒቱ አማኞች ተወያይተን ያጸደቅነው ሲሆን ምንም እንኳን ሁሉንም ምዕመናን አግኝቶ ማሳተፍ ባይቻልም ይህ ሀሳብ ሀሳባቸው መሆኑን ለማወቅ አያዳግትም። በመሆኑም ቅዱስ ሲኖዶስ በሚገባ ጊዜ ሰጥቶ ይህንን ሐሳባችንን እንዲመለከትልን እና የምዕመናንን ጥያቄዎች ችላ እንዳይልብን በአክብሮት እንጠይቃለን።
ክፍል አንድ
በቅዱስ ሲኖዶስ ውስጥ ስላሉ ችግሮች
በአሁኑ ጊዜ በቅዱስ ሲኖዶስ አባላት መካከል የተከሰተው ችግር ምዕመናንን በጽኑ ያሳዘነ፣ የቤተ ክርስቲያንን ጠላት ያስደሰተ፣ እግዚአብሔርን ያስቀየመ ነገር ነው። ቅዱስ ሲኖዶስ አባላቱ ብጹዓን አበው ሰዎች በመሆናቸው የሐሳብ አለመግባባት ቢፈጠር ሁሉም የተለያየ ሐሳብ ሊኖራቸው ስለሚችል አይገርመንም። ሆኖም ከቤተ ክርስቲያን ሕግ፣ ሥርዓትና ደንብ ውጭ እንዲሁም መመሪያችን ከሆነው ከእግዚአብሔር ቃልም በተቃራኒ የተፈጸሙት ነገሮች የሚያሳዝኑ እና አንገትን የሚያስደፉ እንደነበረ አባቶቻችንም ራሳችሁ የምታውቁት ጉዳይ ነው።
በመሆኑም ይህንን ችግር አስመልክቶ አቋማችንን እና ወደፊት ሊደረጉ ስለሚገባቸው ጉዳዮች እንደሚከተለው እንገልጻለን።

1. በአባቶች መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ተከትሎ በአንዳንድ የቤተ ክርስቲያኒቱ ጳጳሳት ላይ የተከሰተው የማስፈራራት እና የድብደባ ሙከራ ፍጹም የተወገዘ ተግባር ነው። ይህን ያደረጉ አካላትም በህግ ፊት ቀርበው እንዲጠየቁ ቤተ ክርስቲያን መንግሥትን እንድትጠይቅ፣ ቤተ ክርስቲያንም በቀኖናዋ መሰረት ተገቢውን እርምት እንድትሰጣቸው።
2. ቤተ ክርስቲያን መንፈስ ቅዱስ በሾማቸው ጳጳሳት ብቻ እንድትመራ ፤አንዳንድ ግለሰቦች የሚያደርጉት ጣልቃ ገብነት እንዲቆም፤
3. ለወደፊት በሲኖዶስ አባላት መካከል ችግር/አለመግባባት/ ቢኖር በቤተ ክርስቲያን በጸሎት እንዲታሰብ የሚደረግበት ሁኔታ እንዲመቻች፤
4. ከቤተ ክርስቲያን አባቶች መካከል ማንም በስጋዊ እና በሚያስነውር ስራ ቢገኝ ቤተ ክርስቲያን በቀኖናዋ መሰረት ማረም እና ማስተካከል እንጂ ለምዕመናንም ሆነ ለማያምኑ ሰዎች አሳልፋ እንዳትሰጥ፤
5. የቅዱስ ፓትርያርኩን ሐሳብ በተቃወሙ አንድ ሊቀ ጳጳስ ላይ የተጻፈውን ሰም አጥፊ ጽሑፍ የጻፉም ሆነ ያሰራጩ ግለሰቦች ኦርቶዶክሳውያን ከሆኑ ቤተ ክርስቲያን ባላት ሕግ መሠረት እንድትጠይቃቸው። ለወደፊትም በዚህ ዓይነት መንገድ አባቶችን ለማሳፈር እና ለማሸማቀቅ በሚሰራ ሥራ የቤተ ክርስቲያናችን ሰዎች ተባባሪ እንዳይሆኑ እንዲሁም ይህ ሥራ በይፋ እንዲወገዝ፤
6. ቅዱስ ሲኖዶስ የሚያሳልፋቸውን ውሳኔዎች የቅዱስ ሲኖዶስ አባላትም ሆኑ አጠቃላይ የቤተ ክርስቲያኒቱ ምዕመናን እንዲያከብሯቸው፤
7. ቅዱስ ሲኖዶስ ቤተ ክርስቲያኒቱን የሚመራ የመጨረሻው አካል በመሆኑ ከጊዜው ጋር እንድትራመድ የሚያደርጋትን አሠራር በውስጡ ለመዘርጋት በአንድ ልብ እና በመንፈስ ቅዱስ ለቤተ ክርስቲያን እንዲሠራ፤
8. ቅዱስ ሲኖዶስ በራሱ አባላት መካከል ችግር ቢፈጠርበት እንኳን በሳል ሊቃውንትን እና ምዕመናንን እየጠራ እንዲያማክር እንጂ ነገሩ የማይመለከታቸው ሰዎች በቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ እንዳይጋበዙ፤
9. ማንኛውም የቤተ ክርስቲያኒቱ ጳጳስ ከቤተ ክርስቲያኒቱ ሊያገኝ የሚችለውን የሕግ ከለላ እና ደኀንነት ማግኘት እንዲችል እንዲደረግ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።

ክፍል ሁለት
በቅዱስ ሲኖዶስ እና በውጭ ያሉ አባቶችን (የቀድሞ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላትን) ግንኙነት በተመለከተ

ቤተ ክርስቲያን በቅርቡ ከተከሰቱባት ታላቅ ፈተናዎች እና አሳዛኝ ጉዳዮች አንዱ በስሟ የሚጠራ ሌላ አካል መቋቋሙ ነው። ይኸውም “ስደተኛው ሲኖዶስ” በመባል የሚታወቀው እና መቀመጫውን በሰሜን አሜሪካ ያደረገው በቀድሞው ፓትርያርክ የሚመራው አካል ነው። እኛ ምዕመናን በሁለቱ አካላት መካከል የሃይማኖት ልዩነት እንደሌለ እንገነዘባለን። የሃይማኖት ልዩነት ሳይኖር በአስተዳደራዊ ችግር ምክንያት ቤተ ክርስቲያን መከፋፈሏ እኛ ምዕመናን አርአያ የምናደርገው አባት እንደሌለን ያሳየን እና አባቶች ምን ያክል ለመንጋቸው እንደአማይራሩ የሚጠቁም አሳዛኝ ድርጊት ነው። በመሆኑም ሁለቱን አካላት በተመለከተ የሚከተለውን አቋም ለቅዱስ ሲኖዶስ ለማቅረብ እንወዳለን።

1. ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ህልውና እና ስለ ምዕመናን ሲሉ ቀርበው እንዲነጋገሩ እና ችግራቸውን በጠረጴዛ ዙሪያ ለመፍታት እንዲሞክሩ፤
2. ሁሉም የቤተ ክርስቲየን አባቶች በመፈቃቀር እና በአንድነት ላይ የተመሠረተ አገልግሎት እንዲኖራቸው ለማድረግ ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።

ክፍል ሶስት
አጠቃላይ የቤተ ክርስቲያን ችግሮችን ስለመፍታት

ቤተ ክርስቲያናችን ቀላል የማይባሉ ችግሮች በዙሪያዋ እየተደቀኑባት ይገኛል። በመሆኑም እነዚህን ችግሮች መረዳት እና በተቻለ መጠንም መፍትሄ መስጠት ይገባል። ከዚህ በታች ያሉ ችግሮችን በጥልቀት የተወያየንባቸው ስለሆነ ቅዱስ ሲኖዶስ በራሱ መፍታት የሚችላቸውን በራሱ እንዲፈታ ባይችል ግን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር ችግሮችን መፍታትን እንዲቻል እንጠይቃለን።

ሀ. ከቤተ ክርስቲያኒቱ ውጭ ያሉ የቤተ ክርስቲያን ችግሮች፡ ቤተ ክርስቲያን በአሁኑ ጊዜ ከእርሷ ውጭ ያሉ እና ቢቻል መጥፋቷን ባይቻል ደግሞ መድከሟን የሚፈልጉ አካላት መኖራቸው ግልጥ ነው። በመሆኑም ከመንግሥት ጋርም ሆነ ከሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ችግሮቹ የሚፈቱበት ሁኔታ እንዲመቻች እንጠይቃለን። ከችግሮቹም መካከል፦
1. በአክራሪ ሙስሊሞች አማካይነት በምዕመናን እና በቤተ ክርስቲያን ላይ የሚደርሰው ትንኮሳ እንዲገታ፤
2. ምዕመናን በእምነታቸው እንዳይኖሩ ቤተ ክርስቲያንን እምነት እና ትውፊት በአጠቃላይ የእርሷ የሆነውን ሁሉ እያጥላሉ እና እየዋሹ የሚናገሩ መናፍቃን አላግባብ ድንበር ዘለል ትችት እንዲቆም፤
3. ቤተ ክርስቲያን በትውልዱ ዘንድ ተቀባይነት እንዳይኖራት ታሪክን እያዛቡ የሚያቀርቡ ግለሰቦች እና አካላት እየጨመሩ መምጣታቸው እንደ ቤተ ክርስቲያን ልጅነታችን የሚያሳስቡን ስለሆነ ችግሮቹ ትኩረት እንዲሰጣቸው በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።

ለ. በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ ያሉ የቤተ ክርስቲያን ችግሮች፦ ቤተ ክርስቲያን ከውጭ ከሚደርስባት ችግር ይልቅ ለድክመቷ እና ወደ ዃላ እንድትሄድ እያደረጋት ያለው በራሷ ቤት ውስጥ እየተፈጠሩ ያሉት ችግሮቿ ናቸው። በመሆኑም ቅዱስ ሲኖዶስ የሚከተሉትን የቤተ ክርስቲያን የውስጥ ችግሮች እንዲፈቱ የሚያደርግበትን ሁኔታ በጥልቀት እና በሰከነ መንፈስ አይቶ እንዲያሻሽል የሚከተሉትን ሐሳቦች እናቀርባለን።
1. በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እየተፈጸሙ ያሉት የአስተዳደር ችግሮች ትኩረት እንዲሰጣቸው እና እንዲፈቱ፦ አሁን ባለው የቤተ ክርስቲያን ሁኔታ ከአንድ አጥቢያ እስከ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ድረስ ልንናገረው ከሚገባው በላይ የአስተዳደር በደል እና ሙስና እንዳለ ተረድተናል። ቤተ ክርስቲያን ትልቅ ተቋም ባለ ድርሻ አካላቶቿም ብዙዎች በመሆናቸው ይህችን ታላቅ መንፈሳዊት ተቋም በሚገባ በተደራጀ እና በተጠና መንገድ ማስተዳደር ይገባል።
2. አለመተማመን እና እርስ በእርስ መናቆር ከቤተ ክርስቲያን አገልጋይ አካላት ዘንድ እንዲጠፋ፦ ቤተ ክርስቲያን አሁን ባለችበት ደረጃ ብዙ አገልጋዮች ቢኖሯትም እርስ በእርስ አንዱ አንዱን ሲከስ ይታያል። በመሆኑም በእያንዳንዱ ቡድን መካከል ያለውን ችግር ለመፍታት ቅዱስ ሲኖዶስ ዋናው በመሆኑ ሁሉንም አገልጋዮች በፍቅር እና በአንድነት፤ በመተሳሰብ እና በመከባበር እንዲሰሩ መመሪያ እንዲሰጥ። ችግሮችም ሰፈጠሩ የሚመለከታቸውን አካላት እንዲያናግር እና እንዲያርም፤
3. የተቀናጀ እና የተጠናከረ አሠራር አለመኖሩ፦ አገልጋዮች እርስ በእርሳቸው የሚናቆሩ በመሆናቸው፤ ቤተ ክርስቲያንን የሚመራው ቅዱስ ሲኖዶስም አባቶች እንደሚናገሩት በሚገባ መልኩ እየተንቀሳቀሰ ባለመሆኑ ቤተ ክርስቲያን ወጥነት ያለው እና የተቀናጀ ሥራ እየሰራች አይደለም። በዚህም በሐገር ውስጥ ደረጃ እንኳን ወጥነት ያለው እና ለትውልድ የሚተላለፍ መሰረት የሚጥል ሥራ መስራት አልተቻለም። ስለዚህ ለዚህም ተገቢው መፍትሔ እንዲሰጠው፤
ክፍል አራት
ቤተ ክርስቲያን በርእይ እና በዕቅድ እንድትሠራ ስለማድረግ
ዘመናችን በርእይ እና በዕቅድ የሚመሩበት እና ስለ እያንዳንዱ ነገርም በጥንቃቄ በመመርመር ትክክለኛውን መንገድ ችግር ካለበት እየለዩ የሚሰሩበት ጊዜ ነው። ቤተ ክርስቲያን ትልቅ ተቋም እንደመሆኗ እና አገልግሎቷም ሕዝብን ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ማቅረብ በመሆኑ በዕቅድ እና በርእይ ልትሠራ ይገባታል። ሁሉን ፈጻሚ እግዚአብሔር ቢሆንም ግን ቤተ ክርስቲያን የዛሬ አምስት ዓመት፤ አሥር ዓመት፤ ሃያ እና ሃምሳ ዓመት ውስጥ ልትሠራተቸው እና ልትደርስባቸው የሚገባትን ግቦች እየተለመች ልትሠራ ይገባታል። በአሁኑ ጊዜ ግን በቅርብ ያጋጠሟትን ችግሮቿን በመፍታት ላይ ያነጣጠረ ሥራ አቅዳ ልትሰራ ይገባታል።

በሁሉም አገልግሎቷ ማቀድ ቢኖርባትም እንኳን ለወደፊቷ ቤተ ክርስቲያን በጣም አስፈላጊ በሆኑ በሚከተሉት ጉዳዮች ላይ አቅዳ ርዕይ እና እቅድ ኖሯት ልትሠራባቸው ይገባል እንላለን።
1. አሁን ባለው አካሄድ ቤተ ክርስቲያን ከአስርት ዓመታት በኋላ በገጠር አካበቢ የሚረከቧትን መምህራን እና ካህናትን ማግኘት አዳጋች ይሆናል።ለዚህም ደግሞ በአሁኑ ጊዜ በየገጠሩ በአገልጋይ እጦት እየተዘጉ ያሉ አብያተ ክርስቲያናት ከቅዱስ ሲኖዶስ የተሰወረ አይደለም። በመሆኑም ወደ ፊት በገጠሪቱ ኢትዮጵያ በሁሉም አካባቢዎች አገልጋዮችን እንዴት ማፍራት እንደሚቻል፤ ባይቻል ደግሞ በገጠሪቱ ያሉ ምዕመናን እንዴት ማገልገል እንዳለባት ሁኔታዎችን አይታ ልታቅድ ይገባታል።
2. ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችንን በሀገራችን እንዳላት ምዕመና ብዛት እና ጥንታዊት እንደመሆኗ የሚጠበቀውን ያክል በማኀበራዊ ዘርፍ እየተንቀሳቀሰች አይደለም። የዚህም ምክንያት ከበጀት ጋር የተያያዘ ምክንያትም ሊኖረው እንደሚችል ማወቅ ቢቻልም የአቅሟን ያክልም እየተንቀሳቀሰች ስላልሆነ ክርስቲያናዊ ተራድዖ ኮሚሽኑ በሚገባ ተጠናክሮ ሥራውን እንዲቀጥል ቢደረግ፤ ይህንንም ከዓለም አቀፍ ለጋሾች እና ከምዕመናን ጋር በቅርበት የሚሰራበት ሁኔታ እየተጠና ታቅዶ መሠራት ይኖርበታል።
3. ቤተ ክርስቲያን የምትኖረው በምዕመናን በሚያወጡት ስዕለት እና አስራት መሆኑ ይታወቃል። ሆኖም አሁን ካላው ኑሮ ውድነት አንጻር ምዕመናን የሚያደርጉት አስተዋፅኦ ብቻውን የካህናትን ኑሮ ደህና ደረጃ ላይ እያደረሰው አይደለም። ካህናትም በተለይ በከተማ ያሉ ካህናት ሙሉ ቀን በአገልግሎት ተጠምደው የሚኖሩ አይደሉም። በመሆኑም ቤተ ክርስቲያን ካህናት ከአገልግሎታቸው በተጨማሪ አንዳንድ ሥራዎችን እንዲሰሩ የምታበረታታበት ሁኔታ እንዲመቻች የሚሆንበትን ሁኔታ እንድታቅድ።
4. ቤተ ክርስቲያን ዘመናዊ አስተዳደርን በማስፈን አሁን እየተፈጠሩ ያሉ እንደ አላግባብ የቤተ ክርስቲያን ስራ ቅጥር፤ ገንዘብ መባከን፤ሊቃውንት ተገቢ ቦታ አለማግኘትን፤ጎቦ፤እና ሙስናን የመሳሰሉ ነገሮችን ፈጽማ መቆጣጠር፣ ማረምና ማስወገድ ይኖርባታል።
5. ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ አገልግሎቷን ለራሷ ልጆች እየፈጸመች ቢሆንም እንኳን ከሀገራችን ውጭም ክርስትናውን ልታሳያቸው የሚገቡ ብዙ ሕዝቦች እና ሀገራት አሉ። በመሆኑም ቤተ ክርስቲያን ወንጌልን በሀገር ውስጥ በተጠናከረ መልኩ የምታስተምርበትን፣ ለውጭው ዓለምም ውጤት ያለው አገልግሎት አጠናክራ የምትጀምርበትን ሁኔታ ልታቅድ ይገባታል።
6. ቤተ ክርስቲያን በራሷ ውስጥ የሚከሰቱ ጉዳዮችን በጥልቀት የሚመለከት እና ተግባራዊ ስራ የሚሰራ የህግ ክፍል እንዲኖራት ያስፈልጋል። ይህም ቤተ ክርስቲያን ከውጭ አካላት የሚሰነዘርባትን ማነኛውም ዓይነት ችግር በባለቤትነት ተከታትሎ አግባብ ባለው ህግ ፊት መብቷን የሚያሰከበር ይሆናል።ከዚህም በተጨማሪ በአብያተ ክርስቲያናት፤ በማኀበራት፤ በቀሳውስት፤ በአጠቃላይ በቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች መካከል የሚፈጠሩ ችግሮች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንዲፈቱ መደረግ አለበት። ይህም የቤተ ክርስቲያንን ገመና በቤተ ክርስቲያን ውስጥ መጨረስ ያስችላል።
7. የቤተ ክርስቲያን አስተዳደርም ሆነ ስርዓታችን በየጊዜው ሃይማኖትን በማይቃረን መሰረት ሲኖዶስ እያየ ከጊዜው እና ከትውልዱ ጋር የሚሄድበትን መንገድ ማመቻቸት ይኖርበታል።
8. ከውስጥም ሆነ ከውጪ የሚጠየቁ ሃይማኖታዊ ጥያቄዎችን በአግባቡና በተደራጀ መልኩ ለመመለስ የሊቃውንት ጉባዔ እንዲጠናከር፤ የሊቃውንት ጉባዔም የቤተ ክርስቲያንን ትምህርተ ሃይማኖት፣ ሥርዓትና ትውፊት በግልጽ ለጠያቂዎች ሁሉ መመለስ እንዲችልና ተግባራዊ የሆነ ሥራ መሥራት እንዲችል እንዲደረግ፤ ማንኛውንም ሃይማኖት ነክ ጉዳዮች በተመለከተ በሙሉ ሥልጣን የሚወስንበት አሠራር እንዲመቻችለት፤ ጥናት የሚፈልጉ ሃይማኖታዊ ጉዳዮችን ማጥናት እንዲችልም ሁኔታዎች እንዲመቻቹለት እንጠይቃለን።
በጠቅላላው ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ራሷን ችላ፣ ራሷን አስተዳድራ፣ የራሷን ችግር በራሷ ፈትታ የተሠማራችበትን ሃይማኖታዊና ማኀበራዊ ተልእኮ እንድትወጣ ቅዱስ ሲኖዶሱ ኃላፊነቱን በሙሉ ተረክቦ እንዲሠራ እንጠይቃለን።
እግዚአብሔር ሀገራችንንና ተዋሕዶ ሃይማኖታችንን ይጠብቅልን።
በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የምንገኝ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምእመናን፣
ጥቅምት 6 ቀን 2002 ዓ.ም
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)