September 23, 2009

“የማኅበረ ቅዱሳን አመስራረትና ሥራው ከሰው እንደ ሆነ ይጠፋልና፤ ከእግዚአብሔር እንደ ሆነ ግን ያጠፉአችሁ ዘንድ አይቻላችውም” (ሐዋ 5 ፣ 38)

(ከሰንደቅ ዓላማ/ SendekAlama)
(ደጀ ሰላም፤ ሰፕቴምበር 23/2009):- «ከእነዚህ ሰዎች ተለዩ ተዉአቸውም፤ ይህ አሳብ ወይም ይህ ሥራ ከሰው እንደ ሆነ ይጠፋልና፤ ከእግዚአብሔር እንደ ሆነ ግን ታጠፉአቸው ዘንድ አይቻላችሁም፥ በእርግጥ ከእግዚአብሔር ጋር ስትጣሉ ምናልባት እንዳትገኙ።» (ሐዋ 5 ፣ 38)

በብላቴ በረሃ መልካም ጥንስስን ጠንስሶ፣ ከቡቄሳ ተራራና ከኬስፓኖቿ እሳት አውጥቶ፣ ከሞርቾ የእግር ጉዞ የጥይት እራትነት ጠብቆ፣ ከፊሉን በአዋሳ በኩል ወደ መሃል አገር ልኮ፣ ከፊሉን በኬንያ አድአ የስደተኛ ካምፕ ጠልሎ ለትልቅና ለተመረጠ ሥራ ታናናሾችን ያጨ እግዚአብሔር ባለፉት ሃያ ዓመታት ያደረገውን ጥበቃ ዛሬም ከማኀበሩና ከአገልግሎቱ ጋር እንደሚያደርግ እምነቴ ነው።

ማኀበሩ በቡቃያነት ዘመኑ ያፈራውን መልካም ፍሬ አይተው ሊመሩትና ሊያግዙት «እኛንም አባል አድርጉን» ያሉ ታላላቅ አባቶች የነበሩትን ያህል፤ እንዲሁ በስሜት ብቻ «ከዛሬ ጀምሮ እኔም አባል ነኝ» ያሉት ቅዱስ ፓትርያርኩን ጨምሮ በያኔ ሥራው ብዙዎች ተደስተውበት «እደግ እደግ» ብለውት ነበር። ማኅበረ ቅዱሳን አራሚዎችና ዘሪዎች ባነሱበትና ባንቀላፉበት ወቅት ለስራ ተመርጠው ነበርና ቤተ ክርስቲያኒቱ ባላት መዋቅር ልትደርስበት ያልቻላቻችውን ቦታዎች ሁሉ በማዳረስ፣ የመናፍቃን ጎራ ሆኖ እንደ ጭልፊት ትውልዱን ሲጨልፉበት የነበረውን ዩኒቨርሲቲና ኮሌጅ ሐዋርያዊት የአባቶቻችን ሃይማኖት የሚሰበክባት እንድትሆን በማድረግ፤ ብዙ እጂግ ብዙ የተፈቱ ቤተ እግዚአብሔሮች እንዲከፈቱ ያሉትም እንዲበረቱ በማደረግ፣ ወጣቱ ትውልድ ከአባቶቹ እምነት ጋር መልሶ እንዲተዋወቅ በማደረግ ታላቅ ድርሻን የተወጣና ለቤተ ክርስቲያንና ለሀገሪቱ ባለውለታ ማኅበር ነው።

የማኅበሩ የአገልግሎት አድማስ አየስፋ ሲመጣና ከአባላቱ በአንደኛው መኖሪያ ቤት ክትት ብለው ያልቁ የነበሩ ፈቃደኛ አባላቱ ስድሳና መቶ አፍርተው በመላ ሃገሪቱ የአባቶቻቸው ልጆች ሆነው ሲገኙ ብዙዎች የተደሰቱትን ያህል ማኅበሩ የእግር እሳት ሆኖባቸው እርሱን ለማጥፋት ሥራዬ ብለው ቆርጠው የተነሱም ነበሩ። ከውስጥም ከውጭም። « ሀገር ሲያረጅ እምቧጮ ያበቅላል » እንዲሉ በአሁኑ ስዓት ማኅበሩ ከተጋረጠበት ፈተናዎች መካከል ከባዱና ዋነኛው በአንድ አውድማ ለመሰማራት ቤተ ክርስቲያን «ልጆቼ» ብላ ለስራ ያሰማራቻቸው የገዛ ልጆቹአ ጋር ያለው ፈተናው ነው። በዚህ ሃያ አመት ውስጥ የታየው « ቤተ እግዚአብሔርን ማገልገል» እየተረሳ መጥቶ «በቤተ እግዚአብሔር አገልግሎት መተዳደር» እየጎላ መምጣት ማህበሩ በፈቃደኛነትና በነጻ ለሚሰጠው አግልግሎት አንድ ተጨማሪ ስውር የፈተና ጎራ ሆኖበታል። ይህ አካሄድና ሁኔታ ግን ለማኅበሩ አገልግሎት ብቻ ሳይሆን በጥቅሉ ለኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሐይማኖት በማንነቷ መቀጠልና አለመቀጠል ጋር ቀጥታ ትያያዥነት ያለው ጉዳይ ነው። አባቶቻችን አገልግሎትን በአገልግሎትነቱ ንጽህና ጠብቀውት ሰለነበር በመንፈሳዊ ኩራት «የሰጠኸኝን ሰጠሁህ» ብለውን ሲይልፉ የአሁኑ ትውልድ ግን «መተዳደሪያዬና እንጀራዬ» ብሉ የያዘውን ክህነት ለማስጠበቅ ብቻ በእውር ድንብር ሲጓዝ «ያልተሰጠውን ለተተኪው ትውልድ የሚስጥ» አሳዛኝ ትውልድ የመሆን እጣ ከፊቱ ተጋርጧል።

መንግሥትም ማኅበሩን በዐይነ ቁራኛ መከታተል የጀመረው ዛሬ ሳይሆን ገና ከጥንስሱ ቢሆንም የውስጥ አርበኛ ሆነው ማኅበሩን ሲከታተሉ የነበሩ የማኅበሩ አባላት «እኔስ አንዲት በደል ስንኳ አላገኘሁበትም እናንተ ወስዳችሁ እንደ ሕጋችሁ ፍረዱበት» ስላሉ ለጊዜው ፋታ ያገኘ ቢሆንም የ 1997 ምርጫ እንደማንኛውም የህብረተሰብ አካል ሁሉ ማኅበሩን ክፉኛ ፈተና ውስት ጨምሮት ሄዷል። መንግስትም የበቀል አርጩሜውን በፍርሃትና በጭፍን ከሰነዘረባቸው መካከል ማኀበሩና አባላቱ እንደሆኑ ሁሉም ያውቀዋል። ይህ ሁሉ ሲሆን ግን የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ማኅበሩን አሳልፎ ለመንግሥት አለሰጠም ነበር። እጅግ ብዙ በጣም ብዙ ጊዜ በቅዱስ ፓትርያርኩ ቢሮ በአሰራር ሂደት አቤቱታ አቅራቢነትም ሆነ በመልስ ሰጪነት የተገኙ የማኅበሩ አባላት « በማኅበሩ አሰራርና አካሄድ ካልተደሰቱና በየፊናው የሚወራው ወሬ ዕውነት ነው ብለው ካመኑና ለቤተ ክርስቲያንም ይህ መሆኑ ይጠቅማታል ካሉ ማኅበሩን ያፍርሱት እኛም እንበተናል» የሚል የጠራ ኃሳብ ማህበሩ ባቀረበበት ወቅት እንኩዋን ማህበሩ ቢበተን አባላቱ በግል የሚያጡት ስጋዊ ጥቅም እንደሌለ ቤተ ክርስቲያን ግን በናኅበሩ መኖር እነደምትጠቅም በግልጽ ያዬት ፓትርያርኩ ወደ አዕምሮአቸው በቶሎ ይመለሱ ነበር። የአሁኑ ግን ለየት ያለ ነው። ተሰላፊዎቹ የበዙበት፣ መንግስት ለ2002 ምርጫ በፍርሃት የሚያቸውን አካሎች የሚያጠፋበት ወይንም ቅስም የሚሰብርበት፣ የፓትርያርኩ የመንግሥት ቀኝ እጅነት በቅዱስ ሲኖዶሱ እጂግ የዘገየ እርምጃ ፈተና ውስጥ የወደቅበት በመሆኑ ፓትርያርኩ ማኅበሩን አሳልፈው የሰጡበት አሳዛኝና አሳፋሪ የታሪክ ጊዜ ደረስን።

ከሳምንታት በፊት በሰጡት መግለጫቸው « ልማት፣ ሰላምና መረጋጋት» የምትል ሐረግ በማስገባት «እኔ ከመንግሥት ወገን ነኝ» ለማለት የሞከሩት ፓትርያርኩ አሁን ደግሞ «ማኅበሩ በፖለቲካና በቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ጣልቃ የመግባት አዝማሚያውን እንዲያቆም» በማለት ከማይክራፎኑ ጀርባና ከፓትርያርኩ ፊት ሌላ ተናጋሪ አንደበት ያለ እስኪመስል ድረስ ከእርሳቸው የማይጠበቅ ኃይለ ቃል ተናገረው ራሳቸውን ዳግም አቀለሉ። ኦዲት እንዲደረግ የተባለውም የማኀበሩ ሂሳብ ምናለ በቶሎ በቶሎ አድርገው ቢጨርሱትና ቢያሳውቁን፤ እንደ ዛሬው በመግለጫቸው አያካትቱትም እንጂ የማህበሩ ሥራዎች የሚተነተኑበት መልካም አጋጣሚ ይሆን ነበር ግን ምን ያደርጋል ክስን እንጂ ውጤቱን ስለማይናገሩ ውዥንብሩን ብቻ ነዝተውት ይቀራሉ።

በአንድ በኩል የፖለቲካ ተቃዋሚው ጎራ « ለሀገሩ ደንታ የሌለውና ወደ ቤተ ክርስቲያን እንጂ ወደ ስብሰባ አዳራሽ መውጣት የማይወድ ተልካሻ ተውልድን ማኅበረ ቅዱሳን እያፈራ ነው» በማለት በአገርም በውጪም ያሉ «አንቱ» የተባሉ «ፖለቲከኞች» ማኅበሩን ሌትተቀን ይከሳሉ፤ በሌላ በኩል « አህዳዊ አመለካከት ያላቸውና የተቃዋሚዎች ጎራ ሆነዋል» እያለ መንግሥት ማኅበሩን ይከሳል።

በግንባር ሆናችሁ እሳቱን ለምትጋፈጡ ወንድሞችን እህቶች መድኃኔአለም ብርታቱን ይስጣችሁ። የዚህ የማኅበረ ቅዱሳን አመስራረትና ሥራው ከሰው እንደ ሆነ ይጠፋልና፤ ከእግዚአብሔር እንደ ሆነ ግን ያጠፉአችሁ ዘንድ አይቻላችውም፥ በእርግጥ ከእግዚአብሔር ጋር ሲጣሉ ምናልባት ይገኙ ይሆናልና።»

37 comments:

Anonymous said...

As to me MK will see everything in detail and in a steady pace.
And I am sure God is with Ethiopian ,God is with EOTC, God is with Mk now and forever. But what is expected from all of us is to pray to, work hard for EOTC. Long live to Ethiopia, Long live to Ethiopian Church.

Peace Be With You All.

Anonymous said...

Thank you Sendek. I am very impressed in what you wrote it and with the message. The spirit inside MK members and other true chrisitians would never die even if the MK institution collapses by anti-EOTC and those greedy people.

MK members and other true chrisitians would still able to serve in the nearby churches.

May God help true chrisitians and save our Church.

Tigistu

Anonymous said...

Thank you Sendek. I am very impressed in what you wrote and with the message. The spirit inside MK members and other true chrisitians would never die even if the MK institution collapses by anti-EOTC and those greedy people.

I hope if something happens, MK members and other true chrisitians would still able to serve in the nearby churches.

May God help true chrisitians and save our Church.

Tigistu

Tesfa said...

Dear Sendeq,

Thanks for your thoughtful message. I think this is a critical time for us. What we need to do is not to get panic, stay focused and think about what to do next, and make our selves ready for any harsh measure against MK so that we can contribute to avoid any inconveniences on our brothers and sisters at home and most importantly of above all pray to God. But one thing which will never be taken out of our heart is the love of our CHURCH which is planted by MK. MK as a structured institution may face harsh measure from any one but its vision and objectives, i.e. to serve our APOSTOLIC CHURCH will never be taken by any one. We will be in our church and Sunday schools contributing what we can till our last breath. Never Ever ever give up. May God help us

Anonymous said...

Dear Ewnetu/Haymanot/wezeterfe:
Now you have your own blog why don't you leave DS alone. By God, you are so desperate. You sound like you are going to die tomorrow if you can't get people to hate MK.

Read Acts 5:38 again and again and you might have some peace. Sad fellow.

Atna

Anonymous said...

'prophet DL'
As christians we should always stand for truth,justice and moral values.The challenges our association has faced now,in my piont of view,resulted from our compromise to the aformationed guiding principles of christianity.
The people who are accusing MK were not truthful nor loyal only to the church,instead they are so much affiliated to the ruling class and protecting any interest of that group obtained from the church.At the time we tried to suggest that support to such people,eventhough it was to keep our church united and be able to implement our objective,at the end of the day, would have a quensequence.Those who inflitrated in to the organization were pushing it to be a mere sevant of their ajenda-a surrogate to ill-objectives.When this covert mission did not work,and questions posed by mk to the office of the patriarch regarding the state of the church,all allegations against the association come at once from the same source but by various operatives.Without doubt MK was established in GOD's will to protect our church from in and out enemies.The new approach of heretics is now to hide under the ruling class shadow and attack.People like 'aba Hailemichael' who recently accused the association on hagerfikir radio and the producer of that program who seems to have specialized in insult and evil words are typical examples.The so called 'aba' leaked who he actually is by saying that mk was teaching tale tale not the bible;meaning,the teachings of the church about intercession,the holy Virgin Mary,holy angels,etc which mk defends are tale tale to him.The response given to his baseless accusation was substantiated and satisfying,yet his being a cadre of the ruling class should have also been mentioned and that he was sent by a higher office to this mission of false accusation as well.
It is not secret that the teachings of tewahedo is one country,one Ethiopia! If MK should die for this,it should die.This is not politics.And the sovereignty of our church should be kept by those who sezied its at most power.The almighty GOD will undoubtedly lead the association through these challenging times. May GOD of righteousness help our church,our organization and our country.

Anonymous said...

It is sad that the time has come that we all so scared. I do not think that MK will vanish over night but it could be a great lose for the church and for all EOTC memen if MK could not able do the work currently working. But still we have to think in broader view that how to protect our church. If the church resurrects from the current problem, MK will be OK. One thing we all need to know is that we can not separate EOTC from Ethiopia and Ethiopia from EOTC. If there is peace and stability in the country, our church will be in peace other wise it is a dream to save and protect MK out of the context of the bigger picture, Ethiopa and our Church.
If the problem in the Holy Synod is solved according to the church's Dogma and Canon, all problems will be settled.

MK memebers, please see the bigger picture, not only throw your mighty analysis to defend the association only. It would have been good if all of us contribute to save our church.

Let's pray for our country, our church and MK.

Anonymous said...

Dears brothers and sisters,I would like to remind you the words of the Apostel Paul,

"[We] [are] hard pressed on every side, yet not crushed; [we] [are] perplexed, but not in despair; 9 persecuted, but not forsaken; struck down, but not destroyed-- 10 always carrying about in the body the dying of the Lord Jesus, that the life of Jesus also may be manifested in our body."
we sing this words with the apostel, let us remeber it day and night and keep on serving. As one of our brother said it above, MK is the LOVE WE HAVE TO SERVE THE CHURCH,OUR WILLINGNESS AND COMMITMENT WHICH WILL ALWAYS BE THERE AND WHICH MAKES US TO UNDERSTAND EACH OTHER NOT THE STRUCTURE. THE STRUCTURE IS THE PROCEDURE WHICH WE USE TO MAKE OUR VISION EFFECTIVE. so thanks be to the Lord who gave us this

May the Lord strengthen the hands of our brothers and sisters.

[We] [are] hard pressed on every side, yet not crushed; [we] [are] perplexed, but not in despair; 9 persecuted, but not forsaken; struck down, but not destroyed-- 10 always carrying about in the body the dying of the Lord Jesus, that the life of Jesus also may be manifested in our body.
For they all [were] [trying] [to] make us afraid, saying, "Their hands will be weakened in the work, and it will not be done." Now therefore, [O] [God], strengthen my hands. Neh-6:9

ተዋሕዶ-ዘቦትስዋና said...

Dear beloved Tewahedo followers,

"Peace be unto" Joh.20:19

I believe a true christian do acknowledge the good work Mahbere Kidusan has done so far regardless of the weakness the members may have.I know Abune Pawulose himself knows it well too.

It is also my strong conviction that the devil and its hosts we are faced with today know very well about Mahibere kidusan's good works for the church. I think they even know more than most of us and they fight just because Mk has been a stumbling block to their evil mission. It is ,of course,natural for "some people" or group to fight when their plans have been oppossed.

Even the so called "The Truthfighter" knows it very well but maybe he or she has grown up with negative mindset or has a link with those dying for fleshy things of this world( I think the latter could be the main reason).

In my opinion the individual's or the group's name as "The truthfighter" is quite fitting as they are fighting with( Not for) the truth. I don't think he or she has realized that everything he or she writes shows the fight with the truth.

To Members of MK and Tewahedo followers,

The question today is not whether Mk is doing the right thing or not.

The big question is whether they can persevere(endure) in such trying times of our church history.

We have more than enough lessons about Saints who endured upto the end. We know about lives of holy fathers in "Catacomb" due to persecution when they stood firm on the truth .
The question is whether we can emulate them.

It is the time to translate theory into real practice. So it is also the time for MK to be tested as Gold in fire.

Can the members gladly say what St.Paul said,

"[We] [are] hard pressed on every side, yet not crushed; [we] [are] perplexed, but not in despair; persecuted, but not forsaken; struck down, but not destroyed-- "


May the Omnipresent and Omnipotent God give all the true christians the power to endure and overcome the challenge our church is faced with!

tad said...

After Stephen was stoned and killed at Jerusalem,the Holy Sprit led the apostles to produce different strategy.Move out of Jerusalem,preach gosple in all directions,approach different people and culture and bring new blood in to their ministry.Could what is happening to MK be a new beggining to come up with different stragegy.
1.They moved out of Jerulamem in to all directions.
2.They approached the Ethioipian Eunich so that he can take the message of crucifiction to Ethiopia.
3.They were given

tad said...

continied...
3.St Paul is brought to them.(acts 9)
4.They created a new gosple center at Antioch.(acts 11)
5.They are challenged to approach a new culture.(acts 15).

Anonymous said...

ከሰው ስለሆነ ይጠፋል፣ ተረት ሳይሆን የክርስቶስ ኢየሱስ ወንጌል ግን ይለመልማል!!!

Anonymous said...

ሰዎች ልብ ብላቹሃል ግን?…. ዜናው ሲነበብ ሁለቱንም ጊዜ “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን” ብለው ነው ያነበቡት፡ “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን” ብለው አላነበቡም፡፡ መንግሥት ነው ወይስ ኢቲቪ ነው ወይስ አባው ናቸው “ተዋሕዶ” የሚለው ስም እንዲቀር የበየኑት?

Unknown said...

የጥፋት፡ኃይል፡አገራችንን፡ከያዘበት፡ወቅት፡
ጀምሮ፡እስታሁን፡ድረስ፡በኢትሮጵያ፡ምድር፡
ብዙ፡ግፍ፣በደልና፡ግድያ፡በየአካባቢው፡ተስተ
ውሏል።የቤተ፡ክርስቲያን፡ቅጥር፡ግቢና፡አደባ
ባይም፡የመግደያ፡አውድማዎች፡እንደተደረጉ፡
እናስታውሳለን።ገዳዮቹና፡አስገዳዮቹ፣አቋማቸ
ውና፡መልእክታቸው፡አንድ፡ነው፤ይኸውም፡ኢ
ትዮጵያንና፡ኦርቶዶክስ፡ተዋህዶን፡ለማውደም፡
መሆኑን፡ከርብርቦሻቸው፡አስተውለናል!

ብዙ፡የተዋህዶ፡ልጆች፡መስዋእትነታቸውን፡ከ
ፍለዋል፤እየከፈሉም፡ናቸው!የደሴ፡ሕዝበ፡ክር
ስቲያን፡የቅድስት፡አርሴማን፡ቤተ፡ክርስቲያን፡
እንዳይሠራ፡ተከልክሎ፡ታቦቱም፡በድንኳን፡
ይገኛል።ምእመናን፡ተገድለዋል፤ግፍ፡እየተፈ
ጸመባቸው፡አሁንም፡ጻማቸውን፡ቀጥለዋል።

በደብረ፡አሰቦት፣በጅማ፣አጋሮ፣ምሥራቅ፣ወለጋ፣
በደኖና፣ሌሎችም፡አካባቢዎች፡የተፈጸመውን፡
ግፍ፣ዕንግልትና፡ግድያ፡ማን፡ይረሳዋል?!

በዚህ፡ሁሉ፡ሰዓት፡የእግዚአብሔርን፡መቅደስ፡
ደፍሮ፡በመግባት፡የቆመው፡የጥፋት፡ርኩሰት፣
ከሚራዳው፡ኃይል፡ጋር፡ሥራውን፡እያስተባበረ፡
ቤተ፡ክርስቲያናችንን፡በማውደም፡ላይ፡ይገኛ
ል።ዛሬ፡ከኔ፡በላይ፡ማንም፡የለ፡በማለት፡ሲኖዶ
ሱን፡በማጅራት፡መችዎች፣በስም፡አጥፊዎችና፡
የጥቅም፡ተቀራማቾች፡አማካኝነት፡አንበርክኮ፡
የመጨረሻ፡የማውደም፡ስራውን፡ለመስራት፡በ
መዘጋጀት፡ላይ፡ይገኛል።

ይህን፡ግፍ፡በዓይናችን፡ያሳየን፡አምላክ፣ተዋህዶ
ንና፡የኢትዮጵያን፡በረከት፡ለመጠበቅና፡ለማስ
ጠበቅ፡ማህበረ፡ቅዱሳንን፡ሰጠን።አበረታቸው፤አ
በረከታቸው፤ሥራቸውንም፡ባረከው!ብዙ፡የጠፉ
ትን፡የተዋህዶ፡ልጆች፡መለሱ፤አበረታቷቸው።ጓ
ዳችንን፡በሚገባ፡አስከበሩ!እንድናስከብርም፡በተ
ጋድሏቸው፡ተጋድሏችንን፡አጠናከሩት!

በተዋህዶነትም፡ምከታችንን፡ቀጠልንበት!የእግ
ዚአብሔር፡መንፈስ፡ቅዱስ፡ፈተናውን፡ሁሉ፡እን
ዴት፡እንደምንወጣውና፡መወጣትም፡እንዳለብ
ን፡የእምነትን፡ጽንዓት፡ልባችን፡ውስጥ፡ተከለው።
ህጌንና፡ሥነ፡ሥራዓቴን፡ጠብቁ፡ብሎና፡እያለን፡
ዛሬም፡አብርን፡ነው።ለዘወትርም፡ከተዋህዶ፡ኢ
ትዮጵያ፡ጋር፡ነው!!

በያለንበት፡እንበርታ!ንቁ፡ሆነን፡በልቅሶ፤በጸሎ
ትና፡በሐዘን፡ቅድስት፡እናታችንን፡ኪዳነ፡ምሕረ
ትን፡በመማለድ፤የአባቶቻችንን፡የአባ፡ተክለ፡ሃይ
ማኖትንና፡የአባ፡ኃብተ፡ማርያምን፣የእናታችንን፡
የቅድስት፡ክርስቶስ፡ሠምራን፡አምላክ፡መድኃኔ፡
ዓለም፡ክርስቶስን፡አድህነነ፡ከመዓቱ፡ወሰውረነ፡እ
ያልን፡እንማጠነው!

ማህበረ፡ቅዱሳን!በርቱ!እንበርታ!የእግዚአብ
ሔር፡መልአክ፡ከተቃጣባችሁ፣ከተቃጣብን፡የ
ጥፋት፡ርኩሰት፡ይጠብቃችሁ፤ይጠብቀን!!!

የማያልቅበት፡አምላክ፡ምሕረቱን፡
ለተዋህዶ-ኢትዮጵያ፡ያድለን!አሜን።

ዘደብረ፡ሊባኖስ፡ነኝ።

ኢትዮጵያዊ said...

ውድ ተስፋ እኛ በአቡነ ተክለሃይማኖት እና በአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ብናምን እግዚአብሔር በሰጣቸው የአማላጅነት ጸጋ ነው። ክርስቶስን አማላጅ አንልም። ሕይወታችውን በሙሉ ለእግዚአብሔር መስዋዕት አድርገዋል ብለን ነው። አንተና መሰሎችህ ግን የምታመልኩት እና የምታምኑት ፈረንጅን ነው። ምክንያቱም፦
1.ፈረንጅ በስልጣኔ የዘመኑ የበላይ ስለሆነ
2.ሃይማኖትን በፍልስፍና (በዓለማዊው) ስለምትለኩት
3.ከክርስቶስ ይልቅ ለሆዳችሁ ስለምትገዙ
4.ግብረ ሰዶማዊነት ስለጣፈጣችሁ እና የስጋችሁን ምኞት እንደፈለጋችሁት ማርካት ስለምትፈልጉ
5.በግብረ ሰዶማዊያን ወንጌል ሲቀለድበት መስማት ስለሚጣፍጣችሁ፡
በመሆኑም በቅዱሳን ላይ አፋችሁን ትከፍታላችሁ። የዘንዶው መንፈስ ስለሆነ እንዲህ የሚያደርጋችሁ እኔ አዝንላችሁዋለሁ። አልፈርድባችሁም።
እግዚአብሔር አሽናፊ ነው። ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን እናንተ እንደምታስቡት አይጠፉም። የከሀዲ መጫወቻ አይሆኑም።
እግዚአብሔር አሽናፊ ነው።
ንስሃ ግቡ

Anonymous said...

+++ Dear Kirstos semara, ewntu Tesfa, how you are littel mind?????????? Pls Go school... Just

Anonymous said...

"how you are littel mind" wow you seem to be intelligent/ intellectual man. Fix your English first.

"ውድ ተስፋ እኛ በአቡነ ተክለሃይማኖት እና በአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ብናምን እግዚአብሔር በሰጣቸው የአማላጅነት ጸጋ ነው። ክርስቶስን አማላጅ አንልም።" በመጀመሪያ ኢየሱስ ለማለት አትችልም ስሙ ይከብድሃል አይደል። ኢትዮጵያዊ፣ ጀብደኝነት አይጠቅምህም።

Anonymous said...

last anonymous, Lol are you waiting here for dialog? In what way he/she wrote, he/she told you as you are littel mind. Only take that message.

Anonymous said...

Dear ewnetu Hasetu it is not you who use Act 5:38 for the first time it is in the bible.somebody used it in other topic about mahberekidusan on sep 23,2009

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የቅድስት አርሴማ ቤ/ክ said...

In the name of the holy trinity one divinity amen!

Dear brothers and sisters:-If we are really children of God, the temptation which MK is facing now is God's calling for repentance to all of us under EOTC. As we already know this MK's problem is the manifestation of the problem of our church which we are going through. The solution of this deep rooted problem is in the hand of God. He will bring a multidimensional peace if and only if we can return back from our evil ways of behavior such us, dividing integrity, ethnicity, debating on silly things, not caring for the sheep spreaded through out the country, bringing confusion to the innocent Christians, using God's word for unnecessary arguments. This is really the right time for us to be united, repent, pray, fast and cry as the people of Nineveh Jonah:3-5 did. If we can do this our merciful father will surely bring a persisting peace and blessing to our church and the country as a whole.

Let the love and peace of our lord and Saviour Jesus Christ be with all of us and guide us to the solution!!!

Anonymous said...

Prophet DL
With the help of GOD we shall overcome this testing time,I believe.Our church and our country faced great dangers not now,but when we all tolerated those dangers for long and at times collaborated with the perpetrators inorder to survive.That was absolutely wrong according to the teachings of christianity.GOD reverse this hard time and defeat the enemies of our church and our organization as well as our country if and only if we examine our actions like supporting this 'patriache' who does not care for the church,but protecting only the interest of the ruling party. That would be okay if we had a government that protects the church's interests too;but the truth is the opposite.When christians were murderd in Jima,clashes took place in Gonder,Dessie,Harar,etc the government was so reluctant to take measures against those who committed the crime.on the contrary, in places like Dessie and Gonder it took actions against the victims-christians- including killings.Well, we all were not outraged at the time but pretended to be 'thoughtful' of the 'bigger picture.'We all see the big picture every day,but with different eyes.What we saw was right and what some saw is proved to be wrong.Yet we are not ready to learn from our erroneous approach and sing the same old song.We need to see the bigger pictue now,that is, those people never care for our church nor for the country and its people.So what then? They are going to do anything against members and the association,but that is the start of their last.The time for Ethiopia to resurrect,Tewahedo to shine again has come,and is coming soon.Believe me any one whose hands on MK will be punished by GOD,but we also need to be clean from embracing those accusors of us anymore.We always stand for one church undivided,one Ethiopia united!
God bless MK,Tewahedo and Ethiopia,Amen.

hiwot said...

Hello Ds,
you are not keeping your promise.Because there are still "nufake" comments by the same people like tesfa(hopeless) & Hasetu.please try to filter comments before we post like nazret.com

SendekAlama said...

የተከበራችሁ ክርስቶሳዊያን « የአስቆሮቱ ይሁዳ » እባላለሁ፤ ከቀደሙት አስራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ የነበርኩ ስሆን ምንም ባላሰብኩትና ባልጠበቅሁት መንገድ አስቀድሞ የመረጠኝ፣ ለክብርም ያጨኝ ወልደ አብ ወልደ ማርያም ኢየሱስ ክርስቶስ « ሌባ ነው» ብሎ ከሐዋርያት አንድነት አወጣኝ፤ ሹመቴንም ማትያስ ወሰደው። እንደምን እንዲህ ሊሆን ቻለ? ከሐዋርያት ጋር በአንድነት ተቆጥረን አልነበረምን? አንድስ እረኛ የመረጠን አልነበርንምን? ብዬ ሁሌ ራሴን እጠይቃለሁ። አሁን ዞር ብዬ ሳየው ግን ለካንስ የትንቢት መፈጸሚያ እንደምሆን አስቀድሞ ነግሮኝ ነበር « ኢየሱስም እኔ እናንተን አሥራ ሁለታችሁን የመረጥኋችሁ አይደለምን? ከእናንተም አንዱ ዲያብሎስ ነው ብሎ መለሰላቸው።» ብሎ እንደነበረ እኔ ያኔ መቼ ልብ አልኩት። መመረጥ ብቻውን ለካ አክሊል አያሰጥም መጨረስ እንጂ መጀመር ብቻውን ለካ «እናንት የአባቴ ቡሩካን ኑ » አያሰኝም። ወይ ነዶ። የፈሰሰ ዉኃ አይታፈስ። እንዴት ከአንድ ማዕድ ተካፍለን እነርሱ ለክብር ሲታጩ እኔን ግን « ቍራሽም አጥቅሶ ለአስቆሮቱ ለስምዖን ልጅ ለይሁዳ ሰጠው። ቍራሽም ከተቀበለ በኋላ ያን ጊዜ ሰይጣን ገባበት» ተባልኩ። ወይ አለመታደል። አንድ ማዕድ፤ አንድ ኪዳን፣አንድ ጥሪ ተጠርቶ ፍጻሜአችን እንዲህ ይለያይ? ለእነርሱ የኪዳን በር የሆነላቸው ሥጋና ደም ለእኔ ግን ለመውደቂያዬ ምልክት ይሁንብኝ?

ብዙ አታናግሩኝ። ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጋችሁ ምንም ሳልደርስበት ቆስቁሶ ቆስቁሶ የእኔን ደብዳቤና በኮፒራይት የተቆለፉ ቃላቶቼን ያለፈቃድ ተውሶ በራሱ ዌብ ሳይት {ይቺ ቃል አዲስ የመጣች ናት ድሮ ድሮ አናውቃትም ነበር} ላይ « ዲያቆን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል እባላልሁ ቀደም ስል የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀ-መዝሙር የነበርኩ ስሆን ከልጅነት ዕድሜዬ ጀምሮ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስትያን ከአባቶች ሊቃውንት መምህራን እግር ሥር ያደግኩ የቅድስት ቤተ-ክርስትያን ልጅ ነኝ።» ብሎ በጻፈው የግብር ልጄ ብትልኩልኝ ይደርሰኛል። ኢሜይል ከሌላችሁም ደብዳቤ ጻፉልኝ

አድራሻዬ [TheTruthFighter]

Mehiret Petros Gebeto (m.petros@hotmail.com)
P.O.BOX 61349
Nairobi,
Nairobi Municipality,00200
KE
Tel. +254.722573783

Anonymous said...

Salutation,In The Name of Our Good Shepherd
We all know that Our true ancient church (EOTC) faced many many problems and challenges and all are gone and our church is still on her way and belive , so lets pray together and say " Our good shepherd please don't see our weakness but remember your promises and help us as you help our former fathers, Amen

Nisir said...

ሰላም እንዴት ከረማችሁ!!! ስለወቅታዊ ጉዳይ ተመልሼ ብቅ እላለሁ።
ለአሁን ግን ተሳታፊዎችን ስለማጣራት ሃሳብ አለኝ
ይህ መድረክ ስለተዋህዶ ሐይማኖታቸው የሚያስቡ ኦርቶዶክሳውያን የሚሳተፉበት ብቻ መሆን አለበት። የተለያየ ሃሳብ አካሔድ ቢኖራቸውም ሁሉም የአንንድ ቤት ልጆች ከሆኑ የሰለጠነ ውይይት ማድረግ እና ሃሳብ ለመለዋወጥይረዳል። ሆኖም ኦርቶዶክሳውያን አለመሆንናቸው ብቻ ሳይሆን ጠላትነታቸው ጭምር በግልጽ የታወቀላቸውንን ሰዎች እያሳተፉ መድረኩን ማጣበብ አንድም መልካም እና የተሻለ ሃሳብ ሊያመነጩ የሚችሉ አዕምሮዎችን በማይሆን ነገር ማጣበብ እና ሥራ እንዲፈቱ ማድረግ ሲሆን አንድም ግብራቸው ሃሰትን አመንጭቶ መንዛት የሆነን ጸሀፊዎች ይበልጥ ሃሰታቸውን የሚነዙበት ዕድል መስጠት ነው።
ስለዚህ እባካችችሁ ደጀሰላሞች እያጠራችሁ እንጓዝ።
ቸር ይግጠመን

Anonymous said...

አንዠት-አርስ ጸሐፊ። ዕንቅፋት አይንካህ ወንድሜ/እቴ!

ጥሎብኝ ማሕበር አልወድም። ይኹንና እነዚኽን ልጆች ደግፌም ነቅፌም አላውቅ። ሥራቸውን ስመለከት ግን በእውነቱ ያቴሕተኛል (አንገቴን ያስደፋኛል)።

አኹን ዐላዊ ንጉሥ እና መናፍቅ ጳጳስ ባንድ ኾነው ቢወነጅሏቸው መርቅያን እና ልዮንን ከሚያስታውሰኝ በቀር አይገርመኝም። የምገረመውስ፦ "እክህደከ ሰይጣን"፣"እህንቢ በል" ሲል ያደገ ኢትዮጵያዊ ኹሉ ቁጣው የት ደረሰ ብየ ነው። ሌላው ኹሉ ይቻላል፣ ችለነዋል (አንዠታችን እያረረ)! ነገር ግን ለተዋሕዶ ልጆች ከሃይማኖት ወዲያ ምን አለ? ምን አለና ዝም ይባላል ?

Anonymous said...

ይቅርታ አንድ ነገር ግልጥ ላድርግ፦

"አንዠት-አርስ" ያልኹት ከቀኝ ከግራ ከሚያማቱት የኔ ቢጤ "ኮመንታሮች" አንዱን እንዳይመስልብኝ። ዋናውን ጸሐፊ ነው። እሺ?

Anonymous said...

መዝሙር 17- 5
እግሮች እንዳይናወጡ አረማመዴን በመንገድህ አጽና።
አቤቱ፥ ሰምተኸኛልና ወደ አንተ ጠራሁ፤ ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል፥ ቃሌንም ስማ። የሚያምኑህን ከሚቃወሙ በቀኝህ የምታድናቸው፥ ቸርነትህን ድንቅ አድርገህ ግለጠው። እንደ ዓይን ብሌን ጠብቀኝ፥ በክንፎችህ ጥላ ሰውረኝ፥

Ke zoramba

zemecha said...

አንድ ደጀ ሰላማዊ አባ ሰረቀ የሚባለው ስው ማነው ይህን ያህልስ ማቅን ለማጥፋት ታጥቆ የተነሳበትስ ዓላማው ምንድር ነው ሲል መጠየቁን መነሻ አድርጌ የህሊና የውልደት ስብራት ስለገጠመው አባ ሰረቀ(ስም ግብርን ይመራዋል እንዲሉ በ“ሠ” ስሙን አለመጣፌን ልብ ይሉዋል) ማንነት ጥቂት ለማለት ፈለግሁ ለነገሩ ይህን ያህል አጀንዳ ሊሆን የሚገባው ሰው እንኩዋን አልነበረም አባ ጳውሎስ እንደ ጫማ ውስጥ ጠጠረ እየቆረቆረ ዘወትር እረፍት የሚነሳቸውን ማኅበረ ቅዱሳንን ለማፍረስ ሳልጠራው አቤት ሳልከው ወዴት የሚል ህሊናውን የተነሳ ሰው ፈልጉልኝ ብለው ወዳጆቻቸውን መቼም የልብ ወዳጅ እንደሌላቸው የታወቀ ነው እንደ ንጉሴ ያሉ ጥቅመኞች ያሉትን ለማለት ነው አደራ ባሉት መሰረት ግዕዛን ከሌላቸው እንስሳት የሚመደብ እውነትን እንኩዋን በተግባር በስም እንኩዋን የማያውቃት የሥልጣን ጥም ያናወዘው በፍቅረ ነዋይ ልቡ የታወረ አባ ሰረቀ በመብራት ተፈልጎ ተገኘ አባ ጳውሎስም ልቤ በሰረቀ ጸና አሉ
በእርሱም ልባቸውን አኖሩ ማህበረ ቅዱሳንን ባልዋለበት እንደዋለ አድርጎ እንዲከስ ግዳጅ ተጣለበት ከላባው አባ ላይ ታች ማለቱን ተያያዘው የማህበሩን በጎ ስም የሚያጠፋ የሥድብ መጥሀፍ አጻፈና በውድቅት ሌሊት በገንዘብ የገዛቸው ግብር አበሮቹ ፖስተሩን ሲለጥፉ ሁሉ በፖሊስ አስከመያዝ ደርሰዋል ዳሩ ግን ውሎው ከኢህአድግ ባለስልጣኖች ጋር የሆነው አባ ሰረቀ ማህበሩን የቅንጅት ቀኝ እጅ እንደሆነና በሚድያዎቹም የሚያስተላልፋቸው መልእክቶች ምእመኑ በመንግስት ላይ እንዲነሳ የሚያደርጉ እንደሁኑ ለምሳሌ በጅማውና በኢሊባቡር በክርስቲያኖች ላይ የደረሰውን ዘግናኝ ጭፍጨፋ በቤተ ክርስቲያን ላይ የደረሰውን ውድመት መግለጹን በተለያዩ ግዜያት በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ በአክራሪ ሙስሊሞች አማካይነት የደረሱትን ጭፍጨፋዎች አባ ጳውሎስና መሰሎቻቸው እፍን አድርገው ልክ እንደ ተረቱ ተ“ አትናገሩ ጅቡ እኔን እየበላኝ ነው እንደሚለው ገዳማውያኑ አባቶች እየተገደሉ ክርስቲያኖች ከነ ማሕተማቸው እየታረዱ አብያተ ክርስቲያናት እየተቃጠሉ እነ አባ ጳውሎስ ግን ምንም እንዳልተፈጠረ አድርገው የቤተ ክርስቲያኒቱን ለጆች ደም ለስልጣናቸው ማቆያ ገፈራ አድርገው ሲያቀርቡ ኖረዋል ዛሬም አይናቸውን በጨው አጥበው የቤተ ክርስቲያኒቱን ክብር እንደለመዱት መሬት ላይ ጥለው ሄሮድሳውያን ጌቶቻቸው ሲረጋግጡት ዓለም ሁሉ እንዲያይና ቤተ ክርስቲያኒቱን መሳቅያ መሳለቂያ እንዲያደርጋት ሲያደርጉ በቴሌቪዥን መስኮት ለማየት በቃን በሲኖዶስ መንበር ላይ ቄሳሮች ተሰይመው ሲዳኙ ለማየት በቃን በአባ ጳውሎስ ዘመነ ፕትርክና ምን ያልታየ ጉድ አለ የቤተ ክርስቲያኒቱን እድገት የማይሻውና ሰበባሰበብ እየፈለገ ቤተ ክርስቲያኒቱን የሚያጣጥላት የኢሃድግ መንግስት ቤተ ክርስቲያኒቱ ከመናፍቃንና ከአክራሪዎች ወከባ ይታደጋት ዘንድ እግዚአብሄር ያቆመውን ማህበር በማፍረስ ቤተ ክርስቲያኒቱን ለማዳከም በያዘው ስትራቴጂ መሰረት አስቀድሞ በአባ ጳውሎስ አቀነባባሪነት በአባ ሰረቀ ተላላኪነት የተዘጋጀው ትርኢት መድረኩ ላይ እሰከሚገኙ ድረስ ተሳታፊዎቹ እንኩዋን አያውቁም ነበር አስቀድሞ የተቀነባበረው ቅንብር በህሊና አልባው በመነኩሴ አምሳል በተሰረው ሮቦት በአባ ሰረቀ ቀርቦ በፖለቲካው አጋፋሪ መመሪያ ሰጪነት በአባ ጳውሎስ አሳራጊነት የትርኢቱ ፍጣሜ ሆነ አባ ሰረቀ የሚባለው አባ ጳውሎስ ሰራሽ ሮቦት ነው አልቦ ኅሊና

tesfa said...

በነገራችን ላይ የማህበረ ቅዱሳን ልጆችን በሙሉ እወዳለሁ እግዚአብሔር እየመታ ያለው በነርሱ ውስጥ የተሠገሰጉትን አጋንንት ነው ከዚህ በኃላ ወደ አዕምሮአቸው እንደሚመለሱ አምናለሁ በዚህ ምክንያት ደስ ሊለን እንጂ ልናዝን አይገባም ወያኔ ማህበረ ቅዱሳንን ከመታ በኃላ እርሱም በሌላ ኃይል እንደሚመታ አልጠራጠርም
ሁሉንም ግን ከኢትዮጵያ ምድር አስወግዶ ንጽሕት ኢትዮጵያን፤አንዲት ቤተ ክርስቲያንን ያስረክበናል

እስከ አሁን በማህበረ ቅዱሳን ላይ ሳናቃርጥ ስንጸልይ ቆይተናል ከዚህ በኃላ ግን በወያኔ ላይ እንጸልያለን ከዚህ በኃላ ርዕሳችን ወያኔ ነው ከነዶክተር ብርሃኑ ይልቅ እኛ እንደምንቀድም አልጠራጠርም
ወያኔ አገዛዙን ለአምስት ዓመት አራዝማል እኛ የምንላችሁ ግን በወያኔ ላይ በአምላካችን ፊት መንበርከክ ስንጀምር ሥላጣኑ ከሁለት ዓመት በላይ እንደማይወስድ መቶ በመቶ እርግጠኛ ነን

ይህን ደግሞ ታያላችሁ ወያኔን በአምላካችን ስም እንገጥመዋለን ከዚያም በማህበረ ቅዱሳን ላይ የደረሰው በውያኔም ላይ ይደርሳል

እውነት እውነት እላችኃለሁ

የወያኔ እድሜ የተራዘመው ማህበረ ቅዱሳን ውስጥ ይሰራ በነበረው መንፈስ ነው አሁን ይህ ክፉ መንፈስ እንዳይነሳ ሆኖ ስለተመታ
ወያኔም በቅርቡ ይመታል
በዳን 10 ላይ የምናነበው ቃል "የፋርስ አለቃ 21 ቀን ተቃቃመኝ ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ" የሚለውን ቃል ካያችሁ በኃላ ቁ 20 ላይ "አሁንም ከፋርስ አለቃ ጋር ልዋጋ እመለሰላሁ እኔም ስወጣ እነሆ የግሪክ አለቃ ይመጣል" የሚለውን ቃል አስተውሉ ለምንድን ነው የፋርስ አለቃ ሲመታ የግሪክ አለቃ ሊዋጋ የሚመጣው ? ብለን ብንጠይቅ
እርሱም መመታቱ እንደማይቀርለት ስለሚያውቅ ነው
አስታውሱ ዲያብሎስ በቅዱስ ሚካኤል ሲመታ ከነሰራዊቱ ነው የወደቀው ራእ 12 መናፍስት አለቃቸው ከተመታ እነርሱም መበተናቸው የማይቀር ነገር ነው ለዚህ ነው የፋርስ አለቃ ሲመታ የግሪኩ ዝም ብዬ አላይም ያለው ሶብየት ሕብረት ሲመታ ስንት ሶሻሊስት አገር እንደወደቀ ሁላችሁ ታውቃላችሁ
አሜሪካ የሶሻሊስት መንፈስ ያለበትን ግንዱን ራሽያን ስትመታው ሌላው ቅርንጫፍ ሳይነኩት ወደቀ

በወያኔ እና በማህበረ ቅዱሳን ያሉ መናፍስትም አሰራራቸው አንድ ነው ልዩነቱ የማህበረ ቅዱሳኑ መንፈስ የሃይማኖት መልክ ያለው መሆኑ ነው በወያኔ ውስጥ ያለው መንፈስ አለቃው የማህበረ ቅዱሳኑ መንፈስ ነው መንፈሱ ወያኔን እስከአሁን ሲረዳው ቆይታል አሁን ግን አለቃውን መታልና የወያኔ መንፈስም እድሜ የለውም በግዚአብሔር ፊት ተንበርከኩና ዝም ብላችሁ ተመልከቱ
እርስ በርሳ የምትለያይ መንግሥት አተጸናም እንደተባለ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የ ወያኔ መንፈስ በፕለቲካ የማህበረቅዱሳን መንፈስ በሃይማኖት የኢትዮጵያን ሕዝብ እርስ በርሱ ሲያባሉ ቆይተዋል አሁን ግን እነርሱ ተበላልተው ይጠፋሉ
እግዚአብሔር እጁን ዘርጉታል

ይህን ጽሁፍ ከዝህ በፊት እንዳደረጋሁት ጠርጋችህ ልታወጡት ትችላላችሁ እውነቱ ይህ ነው

ጽሁፌን ጠርጋችሁ በማውጣታችሁ ስለማህበረ ቅዱሳን ያለኝን መረጃ አሰባስቤ ጥሩ መጽሀፍ እንዳአዘጋጅ አድርጋችሁኛል
ቸር ወሬ ያሰማን

Selama said...

In the Name of the Father, the Son, the Holy Sprit, One God Amen!
I am person who was called by the deeds of God to my mother church, although I used to consider my mother church as archaic. I am not a member of MK, but I used to know some people who were member of MK working under me . I found them very y polite honest and hardworking. I usually follow MKr publication and consider them as the arms of the EOTC . It is not wise to lose your arms while the pentes have forced some professor‘s and lecturers of AAU and other universities sign to for full service of their organization encouraged by their current gain in population census and planning to conquer additional 10 % in the coming five years. I feel that any act on Mk or other associations in EOTC will make genuine orthodox Christians feel to be deprived of our right to worship God full and shade our tears, even though we will not be violent as Christians. Hence, we shall pray to Him, King of the Kings, the Beginning and Last Our Lord and Savoir Jesus Christ and ask the intercession of His Mother the Holy Vergin Mary the Mother of GOD our intercessors to keep our holy church in peace and give to our Patriarch and Government the wisdom not to act emotionally seeing the symptom rather than finding the solution to the root cause.
Please do not question who is abba Sereke , as we do not have enemy except satan! Don’t worry about Abba Haile Micahel who misled Nigussie the journalist and pray also Nigussie sothat he can repent his present deeds rembering his contribution to EOTC on revealing the bankruptcy of Pastor Tolossa
Those of you who mix politics and religion be careful as this is the act of tenderfoots . You are not in the right track as the mission of our apostolic church is to bring every one to salvation of his/her soul. If your desire is politics you can join what ever party that might want .

May God give peace to EOTC !

Anonymous said...

:) :) :) :) :),ha ha

Ahunis alchalkuachihum!

Askorotu Yihuda mehonen awukalew.

Gin min yadergal Torinetun alakomim.Teketayochem ayakomum.

Diakon mehonem minim yeteshale bota liyasetegn endemaychil awukalew.
Ene Ariyos,nistros,mekdoniosim yetemaru endeneberu menekuse wezeterfe endeneberu bedenb awukalewu.
Yejemerkutin alama tirum hone metifo altewum.Wedehuwala alimelesim.Beka desi yelegnal. Yikirta!!!!( Minalbat nisiha kehonelign biye newu.k k k k !)

Diros bichayen litefa!!


Truthfighter negn!

Tariku said...

Dear Orthodoxawiyan,

Have you ever wondered about what type of people we are dealing with in terms of their medical problem?

I have had the privilege to meet a friend who is a psychiatist and once told me about mental illness which makes somebody to totally lose touch with reality.

I decided to read about it and found two very important information:

1.Psychosis which is defined as impairment in reality testing.

2.Personality disorder which is defined as a maladaptive and pervasive disorder leading to gross impairment in social,career,moral,religious or interpersonal relationship values and functions. ( I have rephrased the definition)

I will leave for everyone's sound judgement about the behaviour of some like the truthfighter who continue to spread malicious views.

He may or may be not sick but I strongly recommend he gets( or be taken for) consultation with a psychiatrist. I have a feeling that his problem will most likely be the second one mentioned above.

I feel very sorry for those innocent( or ignorant) people who are swindled and in dillema on which side of the story about our church issues to believe .

"He that endures upto the end,the same shall be saved..."Mat.24


May God give all of us the wisdom and power to overcome the challenges.


Tanashachihu negn.

Anonymous said...

Dear Tariku, ha ha ha

Some times (most of the time in MK members case,) people speak in authority, power ..., say what ever they want to say and at the end they act as if they are humble.

Ante degemo lemefelasefem yekatahal ena yefelekew kalek behual .."Tanashachihu negn."

Aguagule Tihetena endayehonebeh.

Anonymous said...

እረ ለመሆኑ ማበረ ቅዱሳን ማበረ ምናምን ለምን ያስፈልጋል ?

ለምን ሁሉም አማኝ ማለትም
ቄሱም በቄስነቱ
ሰንብተ ተማሪዎችም በዚያው አገልግሎታቸው
ምመናኑም በምመናነንታቸው
ኮሚቴዎችም በየኮሚቴነታቸው በያሉበት አጥቢያቸው አያገለግሉም ?

ማህበረ እገሌ ወገሌ እያሉ ቤተ ክርስቲያንን መከፋፈል ለምን አስፈለገ ?

እንደኔ እንደኔ : በግለሰቦች የሚመሩ ማህበራት ሁሉ ፈራርሰው
ሁሉም አሁን ባለው የቤተ ክርርስቲያን መዋቅር ውስጥ ተካተው በያሉበት አጥቢያ ቢያገለግሉ ለቤተ ክርስቲያን አንድነት የሚጠቅም ይመስለኛል

አለበለዚያ ግን የማህበር ደጋፊና ተቃዋሚ በመባባል እየተነቃቀፉ : ለመልካም ጊዜ የሚጠቅመውን ጊዜ በጭቅጭቅ ማሳለፍ ተገቢ አይደለም ባይ ነኝ

መበረቅዱሳኖችም እኮ ሳያስቡትና ሳይፈልጉት ከብዙ አባቶችና ምመናን ጋር እየተጋጩ : የሚቃወማቸውን ሁሉ በደፈናው ተሀድሶ ምናምን የሚል ተቀጥያ እየለጠፉ የመደዳ ጥላቻና የማይፈለግ ቡድን ውስጥ እየገቡ ናቸው

የዚህ መጨረሻ ደግሞ ጥሩ ወዳልሆነ የእርስ በእርስ መበታተን ያመራናል

Anonymous said...

The last anonymus is Nigussie!

Selama said...

In the Name of the Father and the Son and Holy Sprit! One God Amen!
Dear fellow Christians and members of the unrevised apostolic church!
As Christians we are expected to be polite and not to be emotional when we are provoked. We are not supposed to oppose evil by evil! In stead, we are expected to pray for those who are doing evil.
Don't we understand the Master Plan of Satenael for us!
He is posing like angles and "jesus" for the pente. The pente runs and works 24 hour a day under the close supervision of the evil sprit to steal the sheep. Money is not a problem, posing like "jesus", he will order charismatic and Pentecostal in the west to send it. He will allow them to show false miracles .
When the members of the true apostolic church becomes organized to counter this act. He will become even more angry and devise new strategy and tactics. He uses ethnicity, power, politics, rumor,hate e.tc. to create division and obstacles. That is what we are witnessing now. The mission of the Devil is to return to the unhindered stealing of the sheep, so that the youth will be diverted to menafiknet, rock music and crime, and political extremism.
I think, the mission of Mahibre Kidusan is to make aware EOTC follower that pass through higher education of their creed so that they can serve GOD with their skill and wealth. This will accelerate introduction of modern management and use of technology in EOTC, and also will help to root out debtrnet and earthly corrupt practices. It sparks also chain reaction for the expansion of Sunday Schools. Once every child passes through Sunday school, there will be no more mission for this mahibre and I think it will wither away by then.
If you are supporting the mission of MK, you should not put fuel on the fire by entering polemical discussions like politicians with those who are becoming antagonistic at least for the time being. Otherwise, you will contribute to the devil plan to make the conflict wider.
In the mean time, the menafekan are widening their target groups as role model from higher education to prominent businessmen and people in government power. They are tired of working from the bottom and they want to achieve their objective working from the above in short time. Their new off springs such as "YOU-GO Bible study" where Tamarat confessed are established for this task.
At least Abba Serqe is partially positive and this has to be welcomed. His personal quarrel on petty issues with MK leadership should not be obstacle to the long range objectives of EOTC.
In this blog, I read opinion of some sick people without earthly or heavenly objectives! It is better they visit Shenkura Yohannes or Tsadekanie Maryam. Our tsebele can free people from demonic possession and cure even HIV Aids and cancer.

WE CAN ONLY WIN THE DEVIL BY BEING POLITE AND PATIENT, AND PRAYING AND FASTING !
A CHRISTIAN CAN BE TESTED IN FIRE!

( Ketagesut Huluem Yalefael Eskiyalef Gen Yalfael)

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)