September 23, 2009

“የማኀበረ ቅዱሳንን አገልግሎት ማደናቀፍ የሀገሪቱን የሃይማኖቶች ሚዛን ያዛባል” የሃይማኖት አጥኚ

(ደጀ ሰላም፤ ሰፕቴምበር 23/2009)፦ መንግሥት ማኀበረ ቅዱሳንን በተመለከተ የሚወስደው ማንኛውም እርምጃ በኢትዮጵያ ያለውን የሃይማኖቶች ሚዛን እንደሚያዛባው አንድ የሃይማኖት አጥኚ ገለፁ።

ማንነታቸው እንዳይገለጽ የጠየቁት እኚኹ ባለሙያ ከፕሮቴስታንቶችና ከሙስሊሞች እንቅስቃሴ አኳያ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አሁን ካለችበት አሳዛኝ ሁኔታ በባሰ ችግር ውስጥ እንዳትገባ የረዳት ማኀበረ ቅዱሳን መሆኑን ጠቅሰው የማኀበሩ አገልግሎት ላይ ሳንካ መፍጠር በእምነቶች መካከል ያለውን ሚዛናዊነት በማይጠበቅ መልኩ ስለሚያዛባው ለወደፊቱ በሀገሪቱ ውስጥ ትልቅ ችግር ሊፈጥር እንደሚችል አብራርተዋል።


ጉዳዩ የአንድ መምሪያና አንድ ማኀበር ሆኖ ሳለ ቅዱስ ሲኖዶስና ቋሚው ሲኖዶስ ወይም የጠቅላይ ቤተ ክህነት አስተዳደር ጉባዔ ሳያውቀው ታላላቅ የመንግሥት ባለሥልጣናትን መጋበዝ ያስፈለገበት ሁኔታ ግልጽ እንዳልሆነላቸው የገለፁት እኚሁ ባለሙያ ለጊዜያዊ ጥቅም ተብሎ የሚወሰድ እርምጃ ትልቅ መዘዝ ይዞ ሊመጣ እንደሚችል አስረድተዋል። ጉዳዩ የአንድ ማኀበር ጉዳይ ብቻ ተደርጎ መወሰድ የለበትም፣ ሀገሪቱ ካለችበት ጂኦ-ፖለቲካዊና ሃይማኖታዊ ስብጥር ጋርም ተያይዞ መመርመር አለበት ያሉት ባለሙያ ከሶማሊያ የወቅቱ ሁኔታ፣ ከኤርትራ፣ ጂቡቲና ሱዳን የእምነት ይዘትና ዓለማቀፋዊ የአክራሪነት አደጋ ጋር መመዘን እንዳለበት አብራርተዋል።

የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በገጠማት የአስተዳደር ችግር ቅዱስ ሲኖዶሷ ራሱ ፈተና ውስጥ በመግባቱ ራሱ ሊመለከተውና ሊፈታው ይገባ የነበረው እንዲህ ዓይነቱ ጉዳይ በሙሉ ወደ ውጪ አካላት እየተገፈተረ “ኑና ዳኙን” መባሉ እንዳስገረማቸው ባለሙያው አትተዋል።

5 comments:

Anonymous said...

+++
I think MK also help the Govermnt teaching truth spritual tought for young and productive age people inorder to deacrese Corruption and instead stand for truth. Goverment can test the students in all unversity who are member of church how they are in a good manner.
If goverment send his hand to Mk means send his hand to all ethipian christian and create another big enemy inside his heart.
Abatoch begedam yalachihu lenegestate lib endesetachewu Tseliyu.
GOD bless our church
+++

ተመ ስገን said...

ልብ ሊባሉ የሚገባቸው ቋንቋዎች!
. የሃይማኖት አጥኚ?
. ባለሙያ?
. የረዳት ?
. ትልቅ ችግር ?
. ሚዛናዊነት ?
የአንድ መመሪያ?
ጊዚያዊ ጥቅም?

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የቅድስት አርሴማ ቤ/ክ said...

Dear brothers and sisters:-If we are really children of God, the temptation which MK is facing now is God's calling for repentance to all of us under EOTC. As we already know this MK's problem is the manifestation of the problem of our church which we are going through. The solution of this deep rooted problem is in the hand of God. He will bring a multidimensional peace if and only if we can return back from our evil ways of behavior such us, dividing integrity, ethnicity, debating on silly things, not caring for the sheep spreaded through out the country, bringing confusion to the innocent Christians, using God's word for unnecessary arguments. This is really the right time for us to be united, repent, pray, fast and cry as the people of Nineveh Jonah:3-5 did. If we can do this our merciful father will surely bring a persisting peace and blessing to our church and the country as a whole.

Let the love and peace of our Lord and Saviour Jesus Christ be with our church and the whole country!!!

Anonymous said...

Oh Mk, nothing will happen to you...
All are earthly things...

Anonymous said...

እረ ለመሆኑ ማበረ ቅዱሳን ማበረ ምናምን ለምን ያስፈልጋል ?

ለምን ሁሉም አማኝ ማለትም
ቄሱም በቄስነቱ
ሰንብተ ተማሪዎችም በዚያው አገልግሎታቸው
ምመናኑም በምመናነንታቸው
ኮሚቴዎችም በየኮሚቴነታቸው በያሉበት አጥቢያቸው አያገለግሉም ?

ማህበረ እገሌ ወገሌ እያሉ ቤተ ክርስቲያንን መከፋፈል ለምን አስፈለገ ?

እንደኔ እንደኔ : በግለሰቦች የሚመሩ ማህበራት ሁሉ ፈራርሰው
ሁሉም አሁን ባለው የቤተ ክርርስቲያን መዋቅር ውስጥ ተካተው በያሉበት አጥቢያ ቢያገለግሉ ለቤተ ክርስቲያን አንድነት የሚጠቅም ይመስለኛል

አለበለዚያ ግን የማህበር ደጋፊና ተቃዋሚ በመባባል እየተነቃቀፉ : ለመልካም ጊዜ የሚጠቅመውን ጊዜ በጭቅጭቅ ማሳለፍ ተገቢ አይደለም ባይ ነኝ

መበረቅዱሳኖችም እኮ ሳያስቡትና ሳይፈልጉት ከብዙ አባቶችና ምመናን ጋር እየተጋጩ : የሚቃወማቸውን ሁሉ በደፈናው ተሀድሶ ምናምን የሚል ተቀጥያ እየለጠፉ የመደዳ ጥላቻና የማይፈለግ ቡድን ውስጥ እየገቡ ናቸው

የዚህ መጨረሻ ደግሞ ጥሩ ወዳልሆነ የእርስ በእርስ መበታተን ያመራናል

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)