September 28, 2009

የሰሞኑ የዜና ርዕስ የሆኑት አባ ሰረቀ ማን ናቸው? በአሜሪካ ምን ምን ሲሰሩ ኖሩ?

(ደጀ ሰላም፤ ሰፕቴምበር 27/2009)፦
ሰሞኑን በማኀበረ ቅዱሳንና በጠቅላይ ቤተ ክህነት አንድ መምሪያ መካከል የተፈጠረው ውጥረት ፈንድቶ መውጣቱንና መንግሥትን ማሳተፉን ከሰማን ወዲህ ስማቸውን በጉልህ መስማት ከጀመርናቸው ሰዎች መካከል አንደኛውና ግንባር ቀደሙ ሰሜን አሜሪካ የነበሩትና በደንብ የምናውቃቸው “አባ ሰረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል” ናቸው። ስለዚህ ይህ ጽሑፍ ስለኚሁ ሰው የአሜሪካ ቆይታ እውነተኛ እማኝነት ይሰጣል። ቤተ ክርስቲያናችንን የሚመሯትና ነገ ጳጳስ ይሆናሉ ተብለው የሚጠበቁት እኚህ ሰው ምን ዓይነት ሰው እንደሆኑ ያብራራል።

አባ ሰረቀ የዛሬ 15 ዓመት አካባቢ ወደ አሜሪካ ሲመጡ ለመጀመሪያ ጊዜ የሄዱት ወደ ሎስ አንጀለስ ካሊፎርኒያ ነበር። በዚያም አባ ኃ/ሥላሴ ከተባሉ አባት ጋር የጻድቁን የአቡነ አረጋዊን ቤተ ክርስቲያን ማገልገል ጀምረው ነበር። ይሁን እንጂ አባ ሰረቀ ከመጡበት ጊዜ ጀምሮ የሄዱበት አካባቢ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናትን ሰላም በማወክና በመበጥበጥ የታወቁ እንደመሆናቸው አቡነ አረጋዊንም ወዲያውኑ መበጥበጥ ጀመሩ። የአቡነ አረጋዊ ቤተ ክርስቲያንን ቦርድ በመቅረብ “መቀደስና ማገልገል የምፈልገው በትግርኛ ቋንቋ ብቻ ነው” ማለት ጀመሩ። በዚህም የዘወትር አገልግሎት የሚሰጥባቸውን ግዕዝንና አማርኛን ዜሮ አደረጓቸው። ቦርዱን በመጠምዘዝና በማሳመን በትግርኛ ብቻ እንዲቀደስ ለማድረግም ችለው ነበር።

በዚህ መልክ ከ6-8 ወራት ከቆዩ በኋላ በቦርዱ አባላት መካከል እንደገና ጥርጥር፣ አለመግባባትና ልዩነት በመፍጠር ለመክፈል ሞከሩ። ወደ ትግርኛ የቀየሩት ቅዳሴ አላዋጣ ሲላቸው ወይም “ስልታዊ ለውጥ” ማድረግ ሲፈልጉ እንደገና “ወደ አማርኛና ግዕዝ” መመለስ ፈለጉ። በዚህ ጊዜ ቦርዱ እምቢ አለ። “ለምን መጀመሪያ ወደ ትግርኛ ወሰዱን ለምን ይመልሱናል? እኛ የእርስዎ መጫወቻ አይደለንም። ደግሞ የቤተ ክርስቲያናችን አባላት ለምደውታል” ብለው እምቢ አሉ።

አባ ሰረቀ ይህ አልሳካላቸው ሲል ዲሲ አካባቢ ከሚገኘው የመድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ተጋጭተው የወጡ የትግርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎችን በማስተባበር “ቤተ ክርስቲያን ለመክፈት” ተስማሙ። ይህ ከመድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን የወጣው ቡድን ያን ጊዜ የአሜሪካ ሀ/ስብከት አሁን የኢየሩሳሌም ሊቀ ጳጳስ የሆኑትን ብፁዕ አቡነ ማትያስን በማነጋገር “በትግርኛ ብቻ አገልግሎት የሚሰጥበት ቤተ ክርስቲያን ለመክፈት” ሞክረው ሳይሳካላቸው የቀሩ እንደነበሩ ጉዳዩን የሚያውቁ ሰዎች ይናገራሉ። እናም በሎስ አንጀለስ አቡረ አረጋዊ ያልተሳካላቸው አባ ሰረቀ ቨርጂኒያ ሌላ የአቡነ አረጋዊ ቤተ ክርስቲያን “ከፈቱ”። የሎስ አንጀለስ ምዕመናንን ያሳሳቱት ሳይበቃ የቨርጂኒያዎችንም አጭበርብረው በዘረኛ መንፈሳቸው የዋኃኑን አጠመዷቸው። ትናንትና አባ ሰረቀ “የከፈቱት አቡነ አረጋዊ ቤተ ክርስቲያን” ዛሬ ደግሞ አባ ኃ/ሚካኤልን የመሰሉ መናፍቅ መነኩሴ አቅፎ ይዟል። (አስተዳዳሪው ቀሲስ ተከስተ የተባሉ ወጣት ቄስ ናቸው)። አባ ኃ/ሚካኤል ከአባ ሰረቀ ሚሽን ተቀብለው ወደ አሜሪካ የመጡ መሆናቸው በስፋት ይነገራል፤ ይታወቃልም።

አባ ሰረቀ ወደ ቨርጂኒያ እንደመጡ የሀገረ ስብከቱን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማትያስን በመቃወም ማስተማር ጀመሩ። ብፁዕ አቡነ ማትያስን ብቻ ሳይሆን በጠቅላላው ጵጵስናንና ፕትርክናን በመቃወም “ጳጳስም፣ ፓትርያርክም አያስፈልግም” እያሉ ዐውደ ምሕረቱን ከያዙ ጀምሮ በትግርኛ ብቻ በመቀደስና ማስተማር ክፍፍልን መዝራት ጀመሩ። “ጳጳስ አያስፈልግም አዲስ ቤተ ክርስቲያን ለመክፈት ከሆነ እኔ ራሴ ‘መባረክ’ና መክፈት እችላለሁ” ማለት ጀመሩ። በዚህ የተጀመረው ልዩነት ሰፍቶ አቡነ አረጋዊን ራሱን ለሁለት ለመከፈል አበቁት።

ከዚያም የቤተ ክርስቲያኑን ስምና ንብረት በመውሰድ ጥለው ወደ አሌክሳንደሪያ (ቨርጂኒያ) ሄዱ። በዚያው ስም አቡነ አረጋዊ ብለው በመሰየም “አዲስ ቤተ ክርስቲያን ከፈቱ”። በአባ ሰረቀ ጎትጓችነት ተታለው ከመድኃኔዓለም ወጥተው የነበሩትም ምእመናን ልዩነታቸው በማቻቻል ከቀደመው ቤተ ክርስቲያናቸው ጋር ታረቁ። ይሁን እንጂ አባ ሰረቀ ንብረታቸውን በሙሉ ዘርፈው እንደወጡ እንዲቀሩ አልፈቀዱላቸውም። የሕግ ዕውቀት ያላቸው ሰው በማነጋገርና ርዳታ በማግኘት አባ ሰረቀን ሕግ ፊት አቆሟቸው። አባ ሰረቀም የወሰዱትን ሀብትና ስም በሙሉ በግድ ለመመለስ ተገደዱ። በሕግ ፊት የተዋረዱት አባ ሰረቀም አቡነ አረጋዊን አስረክበው ሲያበቁ በቅ/ጊዮርጊስ ስም “አዲስ ቤተ ክርስቲያን በቨርጂኒያ ከፈቱ”። ይህ ቤተ ክርስቲያን ዛሬም በቨርጂኒያ እንደሚገኝ ይታወቃል።

አባ ሰረቀ በዚህ መልክ ቤተ ክርስቲያንን ሲከፋፍሉና ሲያዋርዱ ቆይተው ጊዜ እየተቀየረ ሲሄድ “ጳጳስ የመሆን ሌላ ጾር ሲነሣባቸው” በፊት “አያስፈልግም” ሲሉት የነበረውን “ጵጵስና፣ ፕትርክና እና ቅዱስ ሲኖዶስ” ሸውደው “እጅ ሰጥተው” የአቡነ ጳውሎስ ጋሻ ጃግሬ ሆነው ወደ ኢትዮጵያ ገቡ። አባ ሰረቀ የዲሲና አካባቢው ማህበረ ካህናት ጉባዔ አባል በነበሩባቸው ዘመናት ሁሉ እያጥላሉ ሲሳደቡ የነበሩትን ፓትርያርክ “ካለ እርስዎ ሰው የለም፣ ቅዱስ የለም” ብለው ጫማ ስመው የመምሪያ ኃላፊነት ሽልማት ተሰጣቸው። ይሁን እንጂ ሲጓጉለት የነበረው ጵጰስና ሳይሳካላቸው ቀረ። የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት የሆኑ ብፁዓን አባቶች “እንዲህ ዓይነቱን ወንበዴ፣ ቤተ ክርስቲያንን ሲያሰቃይ የኖረ ሰው እንዴት ጵጵስና እንሾመዋለን” በማለታቸው ሳይሳካ ቆይቶ ነበር። ውስጥ አዋቂዎች እንደሚናገሩት ከሆነ በመጪው ጥቅምት በሚደረገው የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ ጵጵስና እንዲሾሙ ይቀርባሉ ከሚባሉት አባቶች መካከል አንደኛው እኚሁ ዘረኛ መነኩሴ አባ ሰረቀ ብርሃን እንደሚሆኑ ታውቋል።

አይ ዘመን፤ የሚገርመው እኚህኑ አባ ሰረቀን ዛሬ እሑድ በተላለፈው የሀገር ፍቅር ሬዲዮ ላይ ድምጻቸውን ሰማነው። ያውም የቤተ ክርስቲያን “ጠበቃና ተቆርቋሪ” ሆነው። አይ ቤተ ክርስቲያን!!! መከራሽ አያልቅ!!!
ቸር ወሬ ያሰማን
(http://www.addisadmass.com/news/news_item.asp?NewsID=1462)

41 comments:

ኢትዮጵያዊ said...

ሰረቀ ብርሃነን እኮ የለየለት ነው። ፓስተር ዳንኤልን ጠይቁ ስለሱ በስፋት ይነግራችኋል።

Anonymous said...

ውድ “ኢትዮጵያዊ”
እስቲ ትንሽ ንገረን፤ የምታውቀውን።

Anonymous said...

ze ሎሳአንጀለስ

Am not surprised by (serqe)or by Abune Paulos,Dear deje selam modertor to put more info please try to find Abune Matyas phone and call him and ask him in detail who serq is or ask Abba Haileselase about serqe to put more info for yr readers.

Anonymous said...

ሰላም ደጀ ሰላማውያን አባ ሰረቀ እኮ ከንጉሴ ሁለት ምላስ በተቃረነ መልኩ የተናገሩት አለ፣:90%ቱ እዉነተኛ አገልጋዮች ናቸው ማለታቸዉ እኮ፣እኔ እንደ አባል እኮ 90% እዉነተኛ አገልጋዮች መሆናችንን አላዉቅም በአስሩ ፐርሰንት ምክንያት ንጉሴ የሰይጣን ማኅበር በማለቱ አፈረ::አገልግሎቱ አንዳይገታ በማለት አገልግሎቱ ጠቃሚ መሆኑን ነገሩት እሱ እንዲዘጋ የነበረው ፍላጎቱ ባዶ ሆነ::

Anonymous said...

I like the interview of Abba Sereqe because he is 1000% better than Neguse.I didn't expect this testimony from Abba Sereqe.Eventhough he is enemy of MK,he speaks many good testimonies about it.Negusse becomes angry.He doesn't support Negusse.Mk continues and Abba says we will work together with Mk.It is a big shame on Neguse negest ze Haset of Hager geday negusse

Anonymous said...

As I know that MK begs the Sunday School Department and Betekhenet to audit but they don't know even the word Audit.Mahberu likes Audit which is its life,but Negusse ,why do you ask the audit of Betekhenet which can't be audited for the last centuries.But there are auditors in the name but non-functionals.Negusse repeats the words"I am happy"so many times because in the contrary,he is being ashamed by the decision

Anonymous said...

Anonymous said...

As I know that MK begs the Sunday School Department and Betekhenet to audit but they don't know even the word Audit.Mahberu likes Audit which is its life,but Negusse ,why do you ask the audit of Betekhenet which can't be audited for the last centuries.But there are auditors in the name but non-functionals.Negusse repeats the words"I am happy"so many times because in the contrary,he is being ashamed by the decision

gud fela said...

"Assa Gorguary ZENDO yawetal"
the money of mahberekidusan can be audited it is good.Do the church as a whole as auditer or do the church knows how much money she have .Why we never heared any report about the audit of our money given to the church? AUDIT EVERY CHURCH.

Anonymous said...

Leave Aba Sereke and attach Abawoldetensae so he don't preace!!!

Anonymous said...

Hey last Anno.. Do you mean

Leave Aba Sereke and attack Abawoldetensae so he don't preach!!!

aleka said...

ጥያቄ ለማህበረ ቅዱሳን

አባ ሰረቀ እንድተናገሩት ከሆነ ምንም አስጊ ነገር አላየሁም
የኔ ጥያቄ ግን
1ኛ ቤተ ክህነቱ ኦዲት አድርጋችሁ አያውቅም ወይ?
2ኛ ንዋየ ቅድሳትን ከየገዳሙ ስታወጡ ማደራጃ መምሪያው አያውቅም ወይ?
3ኛ ከምታስገቡት ገቢ ማደራጃ መምሪያው ያገኛል ወይ?አግንቶ ከሆነ ማደራጃ መምሪያውም ተጠያቂ ነው
4ኛ ኦዲት ብትደረጉ የሚያስፈራችሁ ነገር አለ ወይ? ለምን በራሳችሁ አትተማመኑም? ነውር ካልተገኘባችሁ ደግሞ ምን ያስጮሃችኃል?
5ኛ በማደራጃ መምሪያው በኩል ብታልፉ እንቅፋት የሚሆንባችሁ ምኑ ነው? የሥራ መጋተት ?ወይስ ሌላ ምሥጢር አላችሁ?
6ኛ እናንተን በመፍራት አንገታቸውን የደፉ ሰባኪዎች እነማን ሊሆኑ ይችላሉ ?
7ኛ የናንተ አባል ሆነው ቄስ የሆኑ ሰዎች መቀደስ አይችሉም ወይ? ክህነት ማን ሰጣቸው? ቄስ የሚያሰኘው መቀደስ ነው ወይ? እንደዚህ ከሆነ ደግሞ የማይቀድሱ ነገር ግን ቤተ ክህነት ብዙ ዘመን የሰሩ ሰዎችን አውቃለሁ የቅስና መመዘኛው ምንድን ነው?
8ኛ ተሃድሶዎች በናንተ ላይ የሚያነሱት ዋና ጥያቄ ምድን ነው?
የኦዲት? የቅስና? የገንዘብ? ወይስ የዶክትሪን? በናንተና በተሃድሶዎች መካከል ያለው ጠብ በደንብ አልገባንም
እባክችሁ እነዚን አጭር ጥያቄዎች ለህዝብ መልሱ

በጣም ከሚወዳችሁ አንዱ፡ነኝ

ጥያቄ ለተሃድሶዎች
ተሃድሶዎች በቤተ ክርስቲያን ቦታ እያዛችሁ መምጣታችሁ ይነገራል?
1ኛ ቢሮ አላችሁ ወይ? አድራሻችሁ የት ነው?
2ኛ ተሐድሶ ማለት ምን ማለት ነው?
3ኛ በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ ያላችሁ ጥያቄ ምንድን ነው? የአስተዳደር ወይስ የዶክትሪን?
4ኛ ከማህበረ ቅዱሳን ጋር ያላችሁ መሰረታዊ ልዩነት ምንድን ነው?በማህበረ ቅዱሳን ላይ ያላችሁ ጥያቄ ምንድን ነው?
5ኛ እናንተ ገቢያችሁን ከሄት ታገኛላችሁ ?ገቢ ካላችሁ ኦዲት ትደረጋላችሁ ወይ?
6ኛ በፕሮቴስታንትነት ትታማላችሁ ፤በናንተና በፕሮተስታንት መካከል ያላችሁን ልዩነት ብትነግሩን?
7ኛ እናንተ ትቀድሳላችሁ ወይ? ክህነት አላችሁ? አላማችሁ ምንድን ነው?
ራሳችሁን ለሕዝብ ግለጡ
ስለናንተ ከማህበረ ቅዱሳን ሰምተናል ግን ከናንተ መስማት ደግሞ እንፈልጋለን።

Anonymous said...

ሰላም ደጀሰላማውያን፣

ዛሬ በንጉሴን ራዲዮ ከአባ ሰረቀ ጋር የተድረገውን ቃለ መጥይቅ አድመጥኩት፤ ንጉሴን ያሳፈረ ነበር፤ እርሱ በጅምላ የሚጠላ ሲሆን እርሳቸው ግን አስተዳደሩ እንጅ ዘጠና ፐርሰንቱ አባል መልካም እንደሆነ ተናግረዋል፤ ለንጉሴ ኪሳራና አሳፋሪ ነው ፤ ስራውን ወደ ኋላ ማየት እና ማፈር የሚችል ከሆነ፡

እርሳቸውም ያልተረዱት ነገር ቢኖር በስራ አመራሩና በአባላቱ መካከል ምን ያህል የጠበቀ መተማመንና ግንኝኙነት እንዳለ ነው፤ ስንመርጣቸውና ይህን ሃላፊነት ስንሰጣቸው በምን አይነት ሁኔታ እንደሆነ ያወቁ ቢሆን ይህን መከፋፈል አይሞክሩትም ነበር፤ የማህበረ ቅዱሳን አመራር መሆን ማለት እኮ እርሳቸው እንዳሉት ሳይሆን ጊዜውንና ገንዘቡን ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የበለጠ የሚያውል ፤ በአባላቱ ስም በማህበሩ ላይ የሚመጣውን መከራ ከፊት ሆኖ የሚቀበል ማለት ነው፤ ይህ ደግሞ ምን ያህል በአባላቱ ዉስጥ እንደሰረጸ ቢያወቁት ኖሮ አፋቸውን ሞልተው ፤ አመራሩን በምቾትና በብልሹ አስተዳደር አይከሱትም ነበር፤ በእውነት በጣም ቅንነት ይጎላቸዋል፤ ይህን አለም ከናቀ መነኩሴ የምሰማው አልመሰለኝም ፤በአንድ ወቅት እዚሁ ድህረ ገጽ ላይ ያነበብኩትን ‘ልብስና ምላስ’ የሚለውን ጽሁፍ ነው ያስታወሰኝ፤

የማህበሩን አመራር ማለት የምፍልገው እንዲበረቱና እንደዚህ በክፋት የተነሱ ወገኖች ለጊዜው እንጅ ፍጻሚያቸው እንደማያምርና እነርሱ ግን በርትተው እንዲሰሩ፤ እንዲሁም በጸሎት የበለጠ እንዲበረቱ አደራ እላለሁ፤ በሰውኛ ሲታይ የመከራ ጊዜ ይመስላል፤ ነገር ግን ምናልባት አምላካችን እንዳሚያውቀው እስከዛሬ ማህበሩ በውስጥ የሚቀበለውን መከራ አለም እንዲያውቅውና ወደፊት ለሚኖረው ሃላፍነትና የስራ ግዜ ብዙ ሰዎች ከጎኑ እንዲሰለፉ፤ በተለይ እዚህ በውጩ አለም ያሉትን፤ የሚያደርግበት መንገድ ሊሆን ይችላል፤ አደራችሁን የበለጠ መበርታት አለባችሁ፤ ለዚህ ደግሞ አምላካችን ከጎናችሁ ይሁን፤ እመብርሃን ብርታት ትሁናችሁ፤

እኛም አባላቱ ከምንግዜውም በላይ የምንተጋበት ጊዜ፤ ‘እየሩሳሌም ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ’ ብለን የገባነውን ቃል አስበን እየሩሳሌም የተባላች ቤተክርስቲያንን የበለጠ ማሰብ አለብን፤ በጸሎትም ከምንጊዜውም በላይ መበርታት አለብን፤ ለሁሉም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሁል ግዜ ከእናንተ ጋር ነኝ እንዳለ፤ ከእኛ ጋር ይሁንና ይርዳን፤ በክፋት የተነሱ ወገኖችንም መልካም ልቦና ይስጥልን፤ አሜን!!!

አቤል

Anonymous said...

Ohhhhhhhhhhhh Dear Lord,
Hear our voice, Listen to us!!!
Deliver us from evil...
Keep your children....
And with you, we will never surrender ...
May you bless Ethiopia with credible and Christian fathers!!!

Ethiopiawi said...

How our problems tremendous!. Is Memihir Zebene such a kind of man?
Is he selfcentered?.And really the cross of Brave and Righteous Man Abune Petros in his hand? If so how he dare to touch the Cross of Hero with his hand?. Min yahil zirkirkachin wota? Oh Lord Almighty Please heed to us? Don't leave your people and the Promis Land?.

Peace be with you all. Amen.

Anonymous said...

aleka asked a question. I think his questions are good. I want to answer one of them. Regarding "Newayate kidisat" in exhibitions, you must know that even if all of the things in the exhibition are sold, they don't give you lots of price. They are not many as the enemies wanted to exagerrate. "keyegedamatu be exibition sem yemiwetaw ejig betam bizu yehager habt.." eyalu siyaganinu tilq zerfiya yemikahed yasmeslutal. The truth is, they are only sample books, and mesenqo and icons which, even if they were sold, donot make a significant difference in the pocket of mahibere kidusan. Besides, nowadays, due to inconvenience, many of them are simply substituted by pictorial descriptions.

But directly answering ur question, yes the churches know exactly what is borrowed; and yes, they get it back!!

Anonymous said...

Selam lenante yihun dear brothers and sisters

I heard the interview of Abba Sereqe and I am so happy to hear 90% of the work that MK contributes to our church is remarkable from his own mouth. But also, I am so surprised that MK is accused on the TV for minor issues for the remaining 10% unsatisfactory results that MK has been providing as Abba Sereqe said with the “sera amerar abalat”. The one thing I think Abba Sereqe should understand is that 90% accomplishment as he said it is the result of “sera amerar abalat”. I wish I can do a little for my church.

Anonymous said...

+++

It is good to know three important things from the interview between Serqe and Negusie:

1. Negussie doesn't know and repeat what he said yesterday. When Serqe says MK is good and the church need its service, then he switches from saying 'MS' to accepting MK as a good and important organization. I haven't heard him saying MK as MS. Amazing! Negussie is not using his mind, rather others (Serqe, Paulos, Abay (TPLF in general) are using him.
2. The other main problem with Serqe was that he needs the language of the church to be in tigregna as mentioned before. Why Negussie hasn't asked him about this issue? Why Serqe is now telling us the church needs MK, and his target is few (10%) individuals? If the target and the problem was with few individuals, then why Paulos and TPLF (not the government) warned MK? The warning was for MK, not for few individuals. Those who are called '10% few individuals' are the reperesentatives of the whole MK. Serqe accused MK as MK, but now he is saying that 90% of MK members are needed for the church, and his problem is only with 10% individuals. How did he know that they are exactly 10%?
3. When Negussie asked Serqe how MK should be audited, he said that all the chuch fathers should implement Paulos's decission. How is that possible? Paulos couldn't manage the church and the church is currently divided into two Synod's. Some accepts the Synod in Ethiopia and the rest are not governed by Ethio Synod. With this real situation how is it possible for the church, which couldn't manage itself well, to audit 17 years journey? Is that realistic?

The above three points cleary shows that Serqe has no the ability and capacity to be the head. However, he is appointed as the head of his current position because only he is from Tigray, and Paulos and TPLF have their own aim. We have seen this on TV that how Abay (TPLF) is close to Paulos and Serqe, the right hand of Paulos.

All these will pass. It is just a matter of time! But history will remember it forever, and ever!!!

mhariew said...

Dear yehagere sewoch;
First I would say to Anonymous ;

"Sew Men yakelale Bilu Yetenagewwen" sihone ezih ga gen yetsafewen new. I guessed you who are you?
Please hulem ende semeh tekarani atehun.

Ye hagere sewoch sew yefelgew yebel yefelegewn yawera" sew yeteketele sew siewedek abero yewedekale" ena selerasachen entseleye Egzio seweren cher aseman Enebel!

Lebene ena kulaliten yale mesareya ,yale microscope meremero atareto yemyaye amalek ale there fore be meskelu yemibedelu kalu aganeneten be meskelu endegedel ensum yetefalu. Anechenek ,anerebesh wegenoche adera selebetekersyan yasaseben entseleye ezih becha maweratachen menm value yelewm.


sele MK
enesu kezerefu,betekerstayan laye ke negedeu " Amalakachen be meder betemelalesebet seat yanesawen jiraf" enesu lay yarefal.kalhone gen zeme belo eyeseru endayseru enekefat lemehon yemiteruten lay yarefal.jirafu eruke aydelm.

ye ene meleket entseleye ,ende be neoh zemen medere endatsedat hulu betekerstayanem yanetsatal.

lezihu entseleye.
weye betekerstyan hoye mekerash beza, Egziabhere yenesa telatochum yebetenu belale ena egnam enebel. yemyawekun lebe endisetachew
May God bless us and our Orthodox Tewahedo Amen

Zmekane Eyesus said...

I respect individuals' opinion unless it contains insult and hate. I want to remind you guys, we have to accept problems are common in ever part of the word and people cannot be perfect at all times. So, please try to solve the problems one by one, otherwise, it is gonna blow out at once and break our ultimate objective. In this regard, I do not like the comment given about Zebene, even if I do share the concern.
Regarding Aba Sereqe dramatized allegation of MK, I believe that most people would understand it as untrue and baseless. He does not even know that the MK leaders have been voted every two years in addition to the many and clear criteria set forth to be a candidate. So, blaming the leaders who are voted with transparency is not only attacking the leaders it is also attacking the whole members.
All the assets, both monetary and material, have been monitored, audited and inspected on a timely manner. And reports have been produced every year and open to the public revision. But, His Holiness Paulos and his close allay Aba Sereqe do not want this procedure, because it is exposing them. We never saw “Betekihnet” audit report open to the public for the last 17 years. Since people are looking modern and spiritual endeavor from MK, most Sunday schools started to ask auditing and other management issues. Why Sunday schools are starting to ask these issues now? Because they are be able to see auditing and other modern procedures during MK's annual meeting. This irritates Patriarch Paulos and his allays. So if he is really interested to see where MK's money is going he has to respect the association’s annual meeting invitation and go to evaluate their all over performance. Nobody prevent him to go in the annual meeting and give his opinion. Rather he preferred public officials to show his earthly power.
By the way the annual meeting contains Arc Bishops, Bishops, other church leaders, priests, people, university students, Sunday school students, and members of MK. But, nobody asks about auditing. Why? Because the jobs performed are much higher than the amount of money budged. Plus, the report is clear, transparent and blameless. I do not have any concern regarding outside auditing, but I am deeply concerned that we are facing two problems in the process:
Primarily, Aba Sereqe is not doing his job. Our Sunday schools are not getting what they are supposed to get from their upper leaders. They need well-studied curriculum; they need permanent teachers; they need improved management; they need text books; they need so many help. When Aba Sereqe is concentrating to accuse MK, he completely abandoned his job behind. We need to see changes around our Sunday schools, like changes that MK brought for the church.
Secondly, MK is now under extreme work pressure. There are plenty of jobs which they need to be done today. But, they are spending their time to give answers to the false allegations of Aba Sereqe. This will be manifest on their outcome.
Lastly, I invited everyone who really wants to know what real MK is. They are heartily welcomed to express any issues/concerns to the nearest office.

Tesfa said...

I am really wondering if Aba Sereqe knows what he is talking. He is talking inconsistent and contradictory ideas. First how can an association have 90% valuable members and contribute something helpful to the church with a bad leadership, as he said? Second don't you know that it is those 90% members who elected their leaders to implement their (members) decision on behalf of them? Third the interviewer and Aba Sereqe are contradicting on what they think and what they are talking about MK. This shows the fallacy of the blames against MK by Aba Sereqe and by Nigussie. Fourth how on earth a country's high ranking officials interfere on the issue of MK and the department unless otherwise there is something which they are planning to conduct against MK. I think it is like " Libeluat yamarachewn amora jigra yiluatal" Any ways this implies for me and worries me that there might be a hidden agenda by the government and aba Paulos to do something against MK by using Aba Sereqe

Selam qoyu

Yigermal said...

Aba Sereke said that 90 % of MK members are innocent. He has problem with 10 % i.e the administrators.
It is funny he doesn’t know the “10 %” are elected by the ”90 %”.

Zmekane Eyesus said...

To Ewnetu.

Please, do not insult people if you believe in Jesus. Sometimes, you may be upset by people opinion, but your comments have been always full of insult. Teach people mercy and politeness by giving descent and christian critics. I believe you gonna listen me if you are really a member of EOTC, otherwise I am not going to read your comments any more.

Anonymous said...

ሰላም “እውነቱ”፡

አሁን ደግሞ ትንሽ የበግ ለምድ ለብሰህ መጣህ፤ እስከዛሬ ተስፋ የቆረጠ ሰው አይነት ነበር አጻጻፍህ አሁን በእነ አባ ሰረቀ ስራ ትንሽ ተስፋህ ያገኘህ ይመስላል፤ አባቶች ለማለት በቃህ፤ ለምን አባቶችህን የምትሰማ ከሆነ የፀኑትንና ያለፉትን እንደ አቡነ ተክለ ሓይማኖት ያሉትን አባቶች አትሰማም፤ ወይ ጉድ ለሁሉም ነገር አጋጣሚ ነው የምትፈልጉት… ይገርማል እኮ!

ልቦና ይስጥህ ወንድሜ… የምታሳዝን ፍጡር …

mhariew said...

Hello Dear anbabaeyan ena asteyayet sechi zemedoche,

esti ande lefegegeta letaleleachu:

sewoch sikeldu"dero Joro teleke Neberech alu gude eysemach eyeteshemakekech endezih aterch" ha ha aha

Dear Tesfa,ante yemetamlkew mane endehone hedeh ezih eyew "www.ettewahedo.webs.com" keza yanet manenet yegebahale.

sele enanete manenet videowchu meskariwoch nachew,aganenet yecheferbachuwale meskienoch.

esti hedeh anetm yalebeh 250 or more kehone aswtetehe (temekeh ) na keza bewala asteyayet tesetaleh.

Seu hulu sele mahebere Kidusan Lemen yekeorekoral? Yemayawek sew kale bacheru ene lenegerachu?
Ensu "asa gorgwari zendo yawetal new" Enesu ene sefere west eyenoreku yehonewn slaweke senet gude asayetewenal keza bewala awekachewalhu esun lene tewulegn ketelchu telwachew. ene gen nefse eskitefa ewedachewalhu,bertu tenkeru tsegawen yabezalchu,kidus micheale yerdachu,

ehe hulu ensu laye yeminchachawe yemenafek menfes yalebt new ,melse be mesetet yasaferwachewal,gudachew yawetalu lezih new .ehe yemayekad ewnet new.


Maheber seyatn yemetelu enanete eselamoch demo erefu,tewachew.enanete yemetamelkuetn sataweku atezarefu,yenanete gude bezu selehone"shola bedefen" kalfelegachu tebku yenanet gude weto yetayal bekereb gize ,betfat yemeyamen hezbe gar tebere yelenm, yebiladen zeroch nachu,enanet ye pakistan zere alebn telu yele?hagerachen erse berse letabalute new? yemetefelguet pls leave us?

Ethiopian eske zare atseneto yakomat ahunem yatsenatal.Liatefat yemifeleg kale hageritu sayhone erasu yetefal.

Aba hailemichale wenejelwachew yawetueten gude resachut ende??

lehulum neger tekarani alew.acher ena geltse neger.

dege ena kefu,
gobezena ,senef,
sere fete ena ,erefte yata

ere bezu bezu

lebe yesten MK laye manetater akumu
cher yaseman

ኢትዮጵያዊ said...

“ድንቄም መካሪ”
መታደስም በሉ መጥፋት ማኅበረ ሰይጣንም በሉ ምናምን ፡ ደብትራም ብሉ አስማተኛ ወዘተ….
በመጀመሪያ እናንት ከግብረ ሰዶማዊነት ውጡ ከዚያ መነጋገር እንጀምራለን።
ዶሮ ብታልም ጥሬዋን …… አትድከሙ ኢትዮጵያ የእግዚአብሔር ናት።

Anonymous said...

Tehadeso, here you are

www.ettewahedo.webs.com said...

Tewhedeso. Here you are

Anonymous said...

መበለቶችም ቅሚያቸው እንዲሆኑ፥ ድሀ አደጎችንም ብዝበዛቸው እንዲያደርጉ፥ የድሀውን ፍርድ ያጣምሙ ዘንድ፥ የችግረኛውንም ሕዝቤን ፍርድ ያጐድሉ ዘንድ የግፍን ትእዛዛት ለሚያዝዙ፥ ክፉንም ጽሕፈት ለሚጽፉ ወዮላቸው!ኢሳ. 10:1

ewnetu said...

Dear Zemekan Eyesu

I hear you my Brother
እንደዛ ለማድረግ እሞክራለሁ ነግር ግን አሳ ጎርጋሪ ዘንዶ ያወጣል እሚባለወ ስለሆነባቸው ነው ሳንነካቸው ነካኩን እና ልናጠፋቸው ተነሳን
ነገር ግን በክርስቶስ ኢየሱሰ ወንድሞቼ ወገኖቼ የሆኑንት የማጥፋት መብትም ፍላጎትም ኖሮኝ ሳይሆን በርሃን ከጨለማ ጋር ዝምድና የለው ም ብዬ ነው

ማህበረ ሰይጣን በኔና በኔን መሰሎች ይህን አይነት እይታ አለው

1. ጸረ ሰላም
2. ጸረ ወንጌል
3. ጸራ ዶግማ እና ቀኖና
4. ጸረ አባቶች
5. ጸረ አነድነት
6. ጸረ ፍቅር
እንዲሁም
1. ተሳዳቢ
2. አላዋቂ
3. አሳዳጅ
4. ገንዘብ አምላኪ
5. ጠንቁይ
6. ሴሰኞች
7. ሃሰተኞች/ በነጠላ እየተሸፋፈኑ በደም መጨማለቅ
8. ገዳዬች
9. ከፋፋዮች
10. በአጠቃላይ እምነት የለሽ ከልቶች ወይም ኤቲየስቶች ናቸው

ይህንን ሁሉ ግን ለውጦ ሰላም የሚያመጣው አንድ ነገር ብቻ ነው
ንስሃ
በንስሃ ታጥበው በይቅርታ ከመጡ ግን እኛም የበደልናቸው ካለ በደስታ ይቅርታ ለመጠየቅ ዝገጁ ነን ነገር ግን
የይቅርታወ ነገር ለሚቀጥሉት 20 አመታት የሚሆን አይመስለኝም ግን ለሁሙም የጌታ ፍቃድ ይሁን ብለን ዝመ አልን

ይቆየን
4

mhariew said...

ሰላም ለእናንተ ይሁን::
ወይ ጉድ!

እውነቱ: ላንተ ነው::
እኔ ማ ቅ አይደለም::

1. you are blaming thousndes of memebers but you are single person are you sure you know better than those?? I wounder MK Tesadabi telaleh But I see its you do that.

Oh God why you don't Open your eyes? or antem Betekerstayn Btebeteh Gudeh awetubeh? Ehe hulu sele MK yeminchachawe eko Tekemachun askerubachu.you know your Heart.deal with your Heart not with MK.
secondly you speak holysprit words
and with in few seconds slang.why you do so my Bro/sis??
thirdly :
manew ante feraj yaderegeh?? endayeferdebeh selraseh tetenekeke please? Medhanialem Bayfelegachew Aysebesebachewm, eskahunem ayakoyachewm,

forthly mechersha laye letsfekew tiks ye Helina mestawet Binoreh anteneteh new.sew sele erasu ezawe tsefo erasun manenetu siaberarara ahun ayehu.

Mahbere seytanema ke Egziabhere kale tebabarinet yelachewm. atefi.gedayoch. etc nachew.
MK manen new yegedelew??
endyawem bekumneawen yemote tewelde astemero ke metfo suse(drag) wede bete EGziabhere ametu enji. But hulum Fetsim aydelm.
ene ande yedekeme sew ayetehm yehonal 100% sel MK hulem taweraleh.endyawem Mefeekereh Mahebere seyatan telaleh.Please leave them they have to do a lots of work.
lastly.
esti ante keserahew ande kume neegere 1 asayen yebekanal.
do you know "little Knoweledege is dangerous" esti Tseleyebet Yaberalehal. God Bless you.Emebete ateleyeh.
cher ensenebet

Smuel wondimu said...

Y,WM xB wLD mNfS QÇS bSM½ bxµL½ bGBR ƒST s!çn# bÆ?RY b?LW½ bml÷T dGä xND ÂcWÝÝ XNdz!H Æl DNQ ngR xND s!çn# ƒST½ ƒST s!çn# xND YƧl#½ YHM L† ƒSTnT rqEQ X bsW xXMé y¥YmrmR Slçn MS-!R YƧLÝÝysW LJ h#l#N ymmRmR ymrÄT mBT |LÈN kxM§k# yts-W mçn# b!¬wQM yfȶN Æ?RY -Æ×c$N lmgNzB Ws#N kçnW xQÑ b§Y

Anonymous said...

Addis Admass reported - y¥Hbr QÇúN X yb¤t KHnT ¥d‰© mM¶Ã F_Å

http://www.addisadmass.com/news/news_item.asp?NewsID=1462

Eunetu Tawoke said...

Dear Eunetu

I know where you are and why you just write nonsense and hatful coments . You don't have any thing to do. As our father said "SERA YATA MENKUSE KOBUN KEDO YISEFAL". Because being not doing anything could lead them for such an evil deed. So here in US people don't have time to hear such hate and arrogant words. If you get a chance you would have seen what is life. But with your behavior I don't think, you will qualify to join US since the place is to work not to talk,
By the way, I don't think you have been born in Ethiopia or from Ethiopian family. You don't have sense of homer. How come you hate people like this? How come as a Christian say this much.? I don’t think even the devil dislike people like this. At least they are human being; think twice what ever they have been through they are Christian. Why don’t you fight with others, like who killed innocent Christians?
Any ways Egziabehr Lib Yisteh Engi Ante Erasu LIBUSANE SIAG SEYTAN NEHE.
“YEMIATEW SEYTAN ENDEMIYAGESA ANBESA BEZURYIACHIK...YAGESAL”
To tell you the fact, no one will read your message. You have alrady opened your blog..AY TINSH SEW

To my brothers/sisters………
Please forgive him. He is sick. Don’t even try to comment his words. Don’t even read his nonsense duskier. He might change his user name but you will know him by his words.

Egzaibehr Libona Yisteh..

Anonymous said...

Leave your comment
Dear Dejeselamaweyan,
Please be civil and Christian when you post your comments. Unchristian and heretic comments are no more tolerated.
ውድ ደጀ ሰላማውያን፣
በሰለጠነና ክርስቲያናዊ በሆነ መንገድ አስተየቶቻችሁን እንድትሰጡ ትለመናላችሁ። ከዚህ በሁዋላ ኢ-ክርስቲያናዊና የኑፋቄ አሽክላ የሚዘሩ አስተያየቶችን አንታገስም።
ቸር ወሬ ያሰማን።
ደጀ ሰላም

Anonymous said...

የመንግስቱ ቃል (ጥቅምት 1ኛ እሁድ)

ዛሬም ጉልበታም ነኝ!

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ ለዓለም ዓለም አሜን!

“የይሁዳም ልጆች በጌልገላ ወደ ኢያሱ ቀረቡ ቄኔዛዊውም የዮፎኒ ልጅ ካሌብ አለው። ለአምላክህ ሰው ለሙሴ ስለ እኔና ስለ አንተ እግዚአብሔር በቃዴስ በርኔ የተናገረውን ነገር ታውቃለህ። የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ ምድርን እሰልል ዘንድ ከቃዴስ በርኔ በላከኝ ጊዜ እኔ የአርባ ዓመት ሰው ነበርሁ እኔም በልቤ የነበረውን ቃል መለስሁለት። ከእኔ ጋር የወጡ ወንድሞቼ ግን የሕዝቡን ልብ አቀለጡ እኔ ግን አምላኬን እግዚአብሔርን ፈጽሜ ተከተልሁ። ሙሴም በዚያ ቀን፦ አምላኬን እግዚአብሔርን ፈጽመህ ተከትለሃልና እግርህ የረገጠው ምድር ለአንተና ለልጆችህ ለዘላለም በእርግጥ ርስት ይሆናል ብሎ ማለ። አሁንም፥ እነሆ፥ እግዚአብሔር ለሙሴ ይህን ቃል ከተናገረ በኋላ፥ እስራኤል በምድረ በዳ ሲዞሩ፥ እርሱ እንደ ተናገረኝ እግዚአብሔር እነዚህን አርባ አምስት ዓመት በሕይወት አኖረኝ አሁንም፥ እነሆ፥ ለእኔ ዛሬ ሰማንያ አምስት ዓመት ሆነኝ። ሙሴም በላከኝ ጊዜ እንደ ነበርሁ፥ ዛሬ ጕልበታም ነኝ ጕልበቴም በዚያን ጊዜ እንደ ነበረ፥ እንዲሁ ዛሬ ለመዋጋት ለመውጣትም ለመግባትም ጉልበቴ ያው ነው። እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ይሆናል፥ እግዚአብሔርም እንደ ተናገረኝ አሳድዳቸዋለሁ።” መጽ. ኢያሱ ወልደ ነዌ 14፥6-12

ቀደም ብሎ እግዚአብሔር ለሙሴ እንደተናገረው ለወገኖቹ ሊሰጥ ያለውን ምድር አስቀድመው እንዲስልሉ ከእያንዳንዱ ነገድ አንዳንድ ሰው ይልክ ዘንድ እንደተናገረው የእግዚአብሔር ባርያም ሙሴ አምላኩ እንደተናግረው ከየነገዱ አሎቆችም አንዳንድ መርጦ ምድሪትዋን እንዲሰልሉ በላካቸው ጊዜ የአንዳንዶች የአሠሣቸው ውጤት ይህን ይመስል ነበር። “ምድሪቱንም ሰልለው ከአርባ ቀን በኋላ ተመለሱ። በፋራን ምድረ በዳና በቃዴስ ወዳሉት ወደ ሙሴና ወደ አሮን ወደ እስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ ሄደው ደረሱ ወሬውንም ለእነርሱና ለማኅበሩ ሁሉ ነገሩአቸው፥ የምድሪቱንም ፍሬ አሳዩአቸው። እንዲህም ብለው ነገሩት። ወደ ላክኸን ምድር ደረስን፥ እርስዋም ወተትና ማር ታፈስሳለች፥ ፍሬዋም ይህ ነው። ነገር ግን በምድሪቱ የሚኖሩ ሰዎች ኃያላን ናቸው። ከተሞቻቸውም የተመሸጉ እጅግም የጸኑ ናቸው ደግሞም በዚያ የዔናቅን ልጆች አየን። በደቡብም ምድር አማሌቅ ተቀምጦአል በተራሮቹም ኬጢያዊና ኢያቡሳዊ አሞራዊም ተቀምጠዋል ከነዓናዊም በባሕር ዳርና በዮርዳኖስ አጠገብ ተቀምጦአል።” ዘኁ. 13፥25-29

በአሥሩ ሰላዮች የቀረበው ሪፖርት (የስለላ ውጤት)፥

*

የሰለልናት ምድር ወተትና ማር ታፈሳለች፥
*

በምድሪቱ የሚኖሩ ሰዎች ኃያላን ናቸው፥
*

በዚያም የኤናቅን ልጆች አየንበደቡብ በኩል አማሌቅ ተቀምጠዋልበተራሮች ኬጢያዊና ኢያቡሳዊ አሞራዊም ተቀምጠዋል፣
*

በባህር ዳርና በዮርዳኖስ አጠገብ ከነናዊ ተቀምጠዋል፣
*

ከተሞቻቸው የተመሸጉ እጅግ ጽኑአን ናቸው የሚል ነበር።

እውነት ነው እነዚህ ከላይ የምንመለከታቸው ነጥቦች ምድሪትዋን ይሰልሉ ዘንድ ከተላኩ ሰዎች መካከል በ10 ሰላዮች የቀረበ ሪፖርት ትክክለኛና ያልተጋነነ ውጤት ነበር። ውጤት ይዘው የመጡ የአሥሩ ሰዎች (ሰላዮች) ድምዳሜም “በኃይል ከእኛ ይበረታሉና በዚህ ሕዝብ ላይ መውጣት አንችልም” የሚል ነበር (ቁ. 13 ይመልከቱ)። ከተላኩ 12 ሰላዮች መካከል ሁለቱ ማለት ካሌብና ኢያሱ ግን እንዲህ አሉ ይላል “ነገር ግን በእግዚአብሔር ላይ አታምፁ እንደ እንጀራ ይሆኑልናልና የምድሪቱን ሰዎች አትፍሩ ጥላቸው ከላያቸው ተገፍፎአል፥ እግዚአብሔርም ከእኛ ጋር ነው አትፍሩአቸው ብለው ተናገሩአቸው።” ይላል (በዘኁ. 14፥9)።

የሚደንቀው አሥሩም ሆኑ ሁለቱ መልዕክተኞች (ሰላዮች) ይሰልልዋት ዘንድ የተላኩት ምድር አንድ ምድር ነበርች በምድሪትዋም ያዩትና ያስተዋሉትም ነገር ቢኖር አንድ አይነት ነበር ሆነም ግን ልዩነቱ ያለው አሥሩ ሰላዮች አስቀድሞ ተስፋ የሰጠውን እግዚአብሔር ኃይሉና ተአምራቱ በመርሣት ባዩት አስደንጋጭ ነገር በመወሰድ ገና ለገና በራሳቸው ላይ “እንዲህ ከሆነማ እኛ ማለት በእነዚህ ሰዎች ፊት እንደ እንበጣ ነን ምንም ዋጋ የለንም የሚሻለው ወይ ባለንበት መሞት ነው ካልሆነ ደግሞ ወደኋላ መመለስ ነው እንጂ ዓይናችን እያየ በራሳችን ላይ ጉድጓድ አንቆፍርም” በማለት ውርደትንና ሽንፈትን በራሳቸውና በህዝባቸው ላይ ሲያውጁ ዘወትር ትምክህታቸውና መከታቸው እግዚአብሔር ያደረጉ ኢያሱና ካሌብ ግን የሚያዩትን እውነታ እንደ እውነታ በመቀበል አስቀድሞ ሁሉን የሚያውቅ፣ አህዛብ ሁሉ በፊቱ በገንቦ እንዳለች ጠብታ ናቸው ተብሎ ይተነገረለትን እግዚአብሔር የተናገራቸውን መለስ ብለው አሰቡና በዛች ቅጽበትም ነፍሳቸው በእምነት ተሞልታ በራሳቸውና በህዝባቸው ላይ ድልን አወጁ “እንደ እንጀራ ይሆኑልናል” በማለትም የእምነት ጦር ጋሻቸውን አነሱ።

ካሌብ ስለ አሠሣው ውጤት በልቡ የሞላውን ለእግዚአብሔር ባርያ ለሙሴ ሲናገር “እንደ እንጀራ ይሆኑልናልና!” ሲል የተናገረውን በማስታወስ ብቻም ሳይሆን ያ ትናንት የነበረው የቆረጠ፣ ተዋጊና ሁኔታዎችን እንደ አምላኩ እይታ ገልብጦ የሚያነብ ልብ ስፍራው ሳይለቅ የቅናቱ እሳት ሳይዳፍን እንዳለ ለመሆኑ “ዛሬም ጉልበታም ነኝ! ለመዋጋት ለመውጣትም ለመግባትም እግዚአብሔርም እንደ ተናገረኝ አሳድዳቸዋለሁ።” ሲል በ 85 ዓመቱ ተዋጊነቱን ያረጋገጠ።

የእግዚአብሔር ሰው ሆይ! ሥሜን በአህዛብ መካከል አሰድበዋልና፤ የጠራኋቸውና የቀባኋቸው ባሪያዎቼም አሳደዋልና፤ ህዝቤም በእውነትና በመንፈስ እንዳያመልከኝ በተረትና ሥጋዊ ትምህርታቸው ከመንገዴ ፈቀቅ አድርገዋልና፤ ክብሬንም ንቀዋልና በምሰራበት ጊዜ አነተ ገንዘቤ ትሆናለህ ለሚለው የእግዚ አብሔር ጥሪ ምላሽ ምን ይሆን? የጠላቶችህ ዲግሪና ዲፕሎማ፣ የአባላቶቻቸው ቁጥር ብዛታቸውና ፉከራቸው፣ በገንዘብም ሆነ በሰው ኃይል ዘመናዊ በሆነ መልኩ መደራጀታቸው፣ ታላላቅ ብለህ በምታስባቸው ሰዎችና ድርጅቶች ያላቸው ተቀባይነትና ተሰሚነታቸው እንደ አስሩ ሰላዮች ያርበደብድህ ይሆን? ወይስ እንደ ካሌብና ኢያሱ ለእግዚአብሔር ክብር አምጣ አምጣ ያሰኝሃል? እውን ውጫዊ ማንነታቸው ማስፈራታቸውስ ቢሆን በሙሉ ኃይልህና በልበ ሙልነት ቆርጠህ እንዳትወጣ እንቅፋት ፈጥሮብህ ይሆን? ወዳጄ ሆይ! እግዚአብሔር የጠላቶችህ የልባቸው ጣብያ ጠልፎ ይሰጥህ ዘንድ የቀረቡልህ ጥቂት ጥያቄዎችን በታማኝነት ለራስህ መልስ ለመስጠት ሞክር ሥፍራህ የለቀቅህ እንደሆነ በምህረት በወደ ቦታህ ትመለሳለስ ባስቀመጠህ እንደሆንክም የበለጠ ትበረታለህ።

Anonymous said...

ትልቅ ሥራ ለምሥራት ትልቅ ሆነህ መወለድም ሆነ ከትልቅ ቤተሰብ መምጣት አይጠበይቅብህም! ትልቁንና ክንደ ብርቱ እግዚአብሔር ማወቅና በእሱ መታወቅ ከመመዘኛዎች ሁሉ የላቀ፣ በቂና ከበቂ በላይ ነው። እግዚአብሔር ከቆረጠ ልብ ይቆማልና ቁረጥ። ከቆረጥክ እግዚአብሔር ከዚህ የተለየ ነገር በካሌብ እና በባርያው በኢያሱ ከሰራው የበለጠ በአንተ ይሰራል። ለምን?

*

የቆረጠ ልብ- አይሆንም ተብሎ ተስፋ የተቆረጠበት ፋይል የተከፈተለት ያለቀለትና የተበጠሰ ክር ይቀጥላል፤
*

የቆረጠ ልብ- አንደበቱና የውስጥ ሃሳቡ በይቻላል! የተቀባና የተሞላ ነው፣
*

የቆረጠ ልብ- በቃልም ይሁን በሥራ ስንፍና አያውቀውም፣
*

የቀረጠ ልብ- የተለየ እይታ የተገጠመለት የላኪውን እይታ የሚያይ ነው፣
*

የቆረጠ ልብ- ምንም በሌለበት በምድረበዳ የሚበላና የሚጠጣ ያቀርባል፤
*

የቆረጠ ልብ- ታሪክ ይገለብጣል!
*

የቆረጠ ልብ- አዲስን ያልተለመደ እንግዳ ነገርን ያደርጋል!
*

የቆረጠ ልብ- መልካምን ቀን አይጠብቅም! “ቀናቶች ክፍዎች ናቸው” ተብሎ እንደተጻፈ አመቺ ባልሆነ ሁኔታ ውስጥ ሆኖ እንኳን ክፉውን በመልካም እየመነዘረ ያለ አንዳች ሥጋት ይወጣል ይገባል!
*

የቆረጠ ልብ- በእውነተኛ ድፍረትና በአስተሳሰብ ጥራቱ ተለይቶ ይታወቃል፣
*

የቆረጠ ልብ- ያለው ችግርንና መከራን በጥንቃቄ እንደየአመጣጣቸው ይቀበላቸዋል እንጂ ከቶ ሥጋትና ፍርሃት አይታይበትም፣
*

የቆረጠ ልብ- ላመነበት ዓላማ እስከ ሞት ድረስ ራሱን ያስገዛ ማንነት ያለው ጀግና ነው፣
*

የቆረጠ ልብ- የጠላቶቹን ድምጽ እየሰማ እንደ ገደል ማሚቶ የሚያስተጋባ ሳይሆን የአምላኩን ክንድ ታምኖ ድምጽን የሚከለክል ነው፣
*

የቆረጠ ልብ- በትናንት ታሪክ ልቡን የሚያሳርፍ ሳይሆን ለበለጠ ክብር የኋላውን እየረሳ ወደ ፊት የሚዘረጋ አዲስ ክብር የሚጠማ ነው፣
*

የቆረጠ ልብ- የአባቱ ቤት ቅናት ይበለዋል፣
*

የቆረጠ ልብ- መሆንና ማድረግ ከሚፈልገው ነገር ሁኔታዎች አያቆሙትም፣
*

የቆረጠ ልብ- የትም ይስፈር የት ለተፈጠረበት ዓላማ ከመኖር አይቦዝንም፣

የቆረጠ ልብ አለህ ወዳጄ? ትናንት ልብህ የነደደበት ጉዳይ ዛሬ ሁኔታዎች አላስጣልሁም? ኑሮ፣ አከባቢ፣ ትዳር፣ ቤተ-ሰብ፣ ብልጽግና፣ ቀይ መብራት አብርተው አላስቆሙህም? ዛሬም ለመውጣትም ለመግባትም ብርቱ ነኝ! የሚያቆመኝ የለም ትላልለህ? የህይወቴ መጀመሪያና መጨረሻ የመኖሬ ትርጉም ዛሬን የማየቴ ምሥጢር ዓላማዬ ነው ትላለህ? ነገሮች አይጎትቱሁም? ወንጌል አቋሜ ነው! ብለህ ብዙ ሸሎቆና ህብረ መከራ ባየህበት ጊዜ ያልነበሩ ዛሬ የታመንከውን አምላክ እንደ ቃል-ኪዳኑ በብድራት ሲጎበኝህ የከበቡህ ውጠው አያስቀርሁም? ዛሬም እንደትናንቱ ወጥተህ ለመግባት ዝግጁ ነህ?

አንተ ጽኑና ኃያል የእግዚአብሔር ባርያ! መጽሐፍ በ1ኛ ዮሐ. 5፥4 “ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ዓለምን ያሸንፋልና፤ ዓለምንም የሚያሸንፈው እምነታችን ነው።” እንዲል መሸነፍም ማሸነፍም፣ ስኬትም ውድቀትም፣ ከፍታም ዝቅታም፣ ድልም ሽንፈትም፣ መውረስም ሆነ መወረስ በእጅህ ላይ ናቸው። በላይ ላይህ የጣልከው ካባ ሳይሆን በውስጥህ ያለውን ሃሳብ እሱ ይወርስሃል። “የሚያቆመኝ የለም! ዛሬም ጉልበታም ነኝ!” ያለ ካሌብ የ 85 ዓመት የዕድሜ ባለጸጋ ሰው ነበር። ካሌብ ሥጋው ቢያረጅም ውስጡ ግን ብርቱና ጽኑ ኃያልም ሰው ነበረ።

በልብህ ያለህ ምንድ ነው? የጠላት ነገር ሲነሳብህ ውስጥህ ምን ይላል? ሌሎች ያወሩትና የለፈፉትን ትደግማለህ? ወይስ እንደ ካሌብ እይታህን እንደ ዳዊት አሰማምህን ቀይረህ በልብህ ያለውን ትናገራለህ? ወዳጄ ሆይ! በውስጥህ ያለውን ሌላ ምንም ሊሆን አይችልም። የከበረውን ከእግዚአብሔር የሆነውን ዓላማ ብቻ ነው በውስጥህ የተቀመጠው። ይህን ቀብረህ ግን ደምህ በማያውቀው ላይ ራስህን ጥለህ ለራስህ ዓላማ ብትሮጥ ከሌላው ይልቅ ግርፋቱ በአንተ ላይ እጅግ ይበዛል። ከእግዚአብሔር ያይደለ ከሥጋ ፈቃድ የሆነውን የምታሳድደው ነገር ቢኖር እሱ ያንተ አይደለም።

አንተ በአንተነትህ የሚያቆምህና የሚያኖርህ ከላይ የተቀበልከው ወረድኩ ስትል የሚያነሳህ ደከምኩ ስትል የሚያበረታህ ጉልበት የሚሆንህ እንጂ ይህ የእኔ ነው ስትል እንደ ጥላ የሚሸሽህ አይደለም። ትናንት ተዋግቼ አሸንፌአለሁ ዛሬም እዋጋለሁ እንዲል ካሌብ በየትም ሥፍራ ሁን በግዞትም በስደትም በእናት አገርህ ምድርም ሁን በተቀመጥክባት ምድር ራስህን እንደ ባርያ መንከባከብ ተውና እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ነው ብለህ በራስህ ላይ ተቆጣ። የሚዋጋ ልብ ይኑርህ። እውነቱ ደግሞ አንተ አሸናፊ ብቻ ሳትሆን ከአሸናፊዎች ሁሉ ትበልጣለህ።

መጽሐፍ በ2ኛ ቆሮ. 10፥10 ላይ “ከእነርሱም አንዳንዶች እያዳንጎራጎሩ በሚጠፋውም እንደጠፉ አታንጎራጉሩ” ተብሎ እንደ ተጻፈ በተሰጠ፣ ባለህ ኃይልና ሥልጣን መውጣትና መግባት መተማመንም አቅቶህ በሰው ሰውኛ ሚዛን ራስህን እየመዘንክና ጠላት በሚናገርብህ፣ በሚያስወራብህ ቋንቋ ጀሮህን እየጣልክ መቆዘም፣ ወደኋላ ማለትና ማጉረምረም በመንገድ ሊያስቀርህ እንደሚችል መዘንጋት የለብህም።

ጠላትህ “አንበጣ” ነህ ሲልህ አንተም በተራህ በሰማኸው ተወስደህ ድምጹ ፍርሃትና ድንጋጤ ጥሎብህ ተቀብለህ አዎ! ነኝ ብለህ የተቀበልክ እንደሆንክ ሌላ ምንም ዓይነት ምሥክር አያስፈልግህም አንበጣ ለመሆንህ! ነኝ ካልክ ነህ ያለጥርጥር። የምትታደግ በእጅህ ሥራ ድልን የምታቀዳጅ በከፍታ ላይ የምታስቀምጥ የጸናች የእግዚአብሔር እጅ ደግሞ የጠላቶቻቸውን ድምጽ ሰምተው ወደኋላ በሚመለሱና በሚያፈግፉ ሳትሆን አምላኬ እንዳለኝ ነኝ እያሉ በሚገሰግሱ፣ የቆረጠ ልብ ባለው፣ ሁኔታዎች ውጠው በማያስቀራቸው፣ ዘመኑን እየዋጀ በሥልጣን በሚመላለሱና ዘወትር ነፍሳቸው በአምላካቸው ሃሴት በሚያደጉ ታማኝ ባርያዎች ናትና ይህ በረከት አያምልጥህ።የእስራኤል ቅዱስ እግዚአብሔር ሀገራችንና ቤተ-ክርስትያናችን ይጠብቅ!

ዛሬም ጉልበታም ነኝ!

ዘትሩዝ ፋይተር

www.thetruthfighter.net

Anonymous said...

I am just curious who Nigusiie is? I just listened the interview between aba sereqe and Nugussie.Being curious; I continued to review the past interviews. Based on the past radio programs, by any standard this is not a radio at all. Even the morally low people elsewhere in the world do not behave like Nigussie behaves. I feel so sorry for him. Suddenly, I thought I heard a voice familiar with me. It was aba paulos's voice(so called patriarch). Again now I am listening the so called Sunday school head aba sereqe. What a shame on them. It looks like this group of people has a mission to vanish our church. Ethiopians should aware of this covert mission. I will repeat again shame on paulos, shame on sereqe for joining the child of Satan nigusiie who doesn’t know what to speak, how to speak, when to speak. We Ethiopians in DC metro area know him very well that is a tool of TPLF. Now we know aba sereqe and paulos are on the same planet where TPLF is. You guys stop fulling us. We all know who you are, what missions you have. Now you start talk about auditing for getting what you are supposed to do-spreading the gospel.You should be audited first before the innocent Mahibre Kidusan is audited. All you car is money.That is what I heard on “radio”.You can’t live without the church money.You can’t make your own. You are leaches. You are sucking the churches money now you are ready to snatch the money from MK who generously gives to our poor brothers and fathers in the wilderness. Please stop it.

Angry meamen

Anonymous said...

Ewnetu,

I am so tired of reading your nonsense comments. I am very sorry for you that your little brain is full of nothing but hatred and evil words. What is the reason behind your anger towards MK? Is it because they exposed your identity/minfikina before you spread your nufake? Please stop torchering yourself and do some constructive thing in your life.

ኢትዮጵያዊ said...

እኔ የምለው እንደዚህ በየፊናው ተከፋፍለን ከምንበላላ አንድ ሆነን ለቤተክርስቲያናችንና ለሀገራችን እንድንሠራ እስኪ እባካችሁ የሚያስማማ ሽማግሌ እንፈልግና እርስ በርሳችን እንታረቅ።
ወይ አለመታደል!

Anonymous said...

ደጀ ሰላሞች ትምህርት ሰጭ አስተያየቶችን እያጠፉ ስድቦችን ብቻ ያስቀራሉ ስለዚህ እውነትን ለመወያየት እዚህ ላይ ይጫኑ ማህበረ ቅዱሳን ወይስ ማህበረ ሰይጣን

solomon said...

Feb16,2009 Addis admass newspaper had interview with this person and Mk.it may give you what is going on this hot issue

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)