September 28, 2009

ቤተ ክርስቲያናችንን እየተፈታተናት ያለው ከሁለቱ የመንግሥት አካላት የትኛው ነው?

(ደጀ ሰላም፤ ሰፕቴምበር 27/2009)፦ ከዚህ በታች ያለው ጽሑፍ ሪፖርተር ጋዜጣ በዛሬ እሑድ እትሙ ካተመው ርዕሰ አንቀጽ የተወሰደ ነው።
(ሪፖርተር ጋዜጣ SUNDAY, 27 SEPTEMBER 2009)፦ በአሁኑ ጊዜ ገዢው ፓርቲ ሁለት ዓይነት አካላት ይዞ እየተጓዘ ነው፡፡ አሁንም ለሕዝብ ብለው ለመሰዋዕትነት የተዘጋጁ አሉ፡፡ በተፃራሪው ደግሞ ለአገርና ለሕዝብ ደንታ የሌላቸው ለፍትሕና ለዴሞክራሲ አለርጂክ የሆኑ መፈክራቸው "የትም ፍጪው ጥቅማ ጥቅሙን አምጪው" የሆኑም አሉ፡፡

የሚያሳስበው ሁለት አይነት መሆናቸው ብቻ ሳይሆን አሉታዊው በአዎንታዊው ላይ፣ እኩዩ በሰናዩ ላይ የበላይነት እየያዘ መምጣቱ ነው፡፡ ያለው ሁኔታ እንዴት ነው ነገሩ? የሚል ስጋት እያስከተለ መምጣቱ ነው፡፡ በአንፃራዊነት የተሻለ ጊዜ ነው በሚባልበት ወቅት እንደዚህ ያለ አስቸጋሪና ፈታኝ ወቅት ቢመጣ ለአገር ይቆማሉ ወይ? የሚል ጥያቄ እየተነሳ ነው፡፡
ጋዜጣው እንዳተተው ከሆነ መንግሥት በሁለት አካላት መካከል “ዥዋ ዥዌ” እያለ መሆኑን “በጥቁርና በነጭ” በግልጽ አስቀምጦታል። ነገሩ እኛንም በጣም አስገረመን፣ ጥያቄም እንድንጠይቅ አደረገን። የአባቶችን ቤቶች የሰበረው ወይም ሲሰበር ዝም ያለው የትኛው ቡድን ነው? ቅዱስ ሲኖዶስ በነጻ እንዳይንቀሳቀስ የሚያስፈራራው የትኛው ቡድን ነው? ወዘተ ወዘተ …

9 comments:

Anonymous said...

The negative anti Ethiopian Group is Wr. Azeb Mesfin Group. This group is about money (TIKIM). Every bodiy know this EKUY group supported Abune Samuel and his Kudeta group (Ethiopian from addis call this group FINDATA PAPASAT)

Anonymous said...

S. c=^¡

And he was given a mouth speaking great things and blasphemies, and he was given authority to continue for forty-two months. 6 Then he opened his mouth in blasphemy against God, to blaspheme His name, His tabernacle, and those who dwell in heaven. 7 It was granted to him to make war with the saints and to overcome them. And authority was given him over every tribe, tongue, and nation. 8 All who dwell on the earth will worship him, whose names have not been written in the Book of Life of the Lamb slain from the foundation of the world. 9 If anyone has an ear, let him hear.

Anonymous said...
This comment has been removed by a blog administrator.
Anonymous said...

Dear DS, Egziabher sirachihun yibark ... GOD is using you to tell the truth in this difficult time of our church ... GOD bless your work

Anonymous said...
This comment has been removed by a blog administrator.
Anonymous said...

አንድ አውሬ ላይ ያለው ሁለት አንገት
የአውሬውን ሥራ ከመስራት ውጪ ሌላ
ዓላማ የለውም።

አንድ አካል ሁለት አንገት እንጂ፣ የመግ
ቢያው አረዕስት አንዳቀረበው፣ የተለያየ
"ሁለት አካል" የሚለው አቀራረብ ስህተት
ነው።

አገራችንና ዓለም የሚገኙበትን ጊዜ በጥንቃ
ቄ ካለመረዳት የቀረበና በትምህርተ ወንገል
ያልተመሰረተ ተራ ዕይታ ነው።

የጥፋት ርኩሰት አንድ ነው። አገራችንንና
ቤተ ክርስቲያናችንን የሚያምሰው ይኸው "አንድ አውሬ" እንደሆነ በነቢያትና በሐዲ
ስም ተነግሮናል። በተጨባጭም፣በአገራችን የሚታየው ከ"አባ"ሰረቀ፣ "ፓትርያርኩ"
እስከ ማጅራት መቺዎቹና አቶ አባይ ፀሐዬ
ድረስ የሚሠሩት ሥራ አንድ ወጥና አንድ
አመራር እንደሆነ ሳይዘገይ ዛሬውኑ መገንዘ
ብና ከአውሬው ለመዳን ክርስቲያናዊ ግዳጃች
ን ሁሉ ለመወጣት ነቅተንና ተግተን መነሳት ይገባናል።

"ጊዜውን ዋጁት" የሚለውም ትምህርት ይ
ህንኑ ተረድተን የድኅንት መንገድ እንድን
ጓዝ አስቀድሞ የተሰጠን ማስጠንቀቂያም ነው!

እግዚእትነ ማርያም ተዋሕዶ-ኢትዮጵያን
ትጠብቅልን!


ሳሙኤል ዘአሰቦት።

Anonymous said...

A person wrote in his memoir about Hitlor hti sway:
First he came after unions and I didn't say any thing because I wasn't in the unions, then he came after socialists and I didn't say anything because I wasn't a socialist,then he came after Jewish people and I didn't say anything because I wasn't a Jew, then at last he came after me and nobody came for me because nobody was left no say anything.
You see MK members,may be you are by yourself like this person because you didn't say anything when everybody was being killed and chased out his country by weyane tugs.

Anonymous said...

The last Anonymous wrote:
"You see MK members,may be you are by yourself like this person because you didn't say anything when everybody was being killed and chased out his country by weyane tugs."


ልትጠቅስ የፈለግኽውን ታሪክ በአጥጋቢ ግንዛቤ
ላይ ልትመሠርተው አልቻልክም።የሰሙትን ለመድገም ብቻ መቸኮሉ የትም አያደርስም!

"you didn' say anything when everbody was being killed..." የሚለውን አነጋገርህን አንደኛ "ሁሉም ሲገደሉ
ና ሲሰደዱ..."የሚለው ንግግር፣ እሬሳዎች ተሰደዱ የሚል መሆኑን የተገነዘብከው አይመስልም! ክስንም በእውነት ላይ መሥርቶ፣ ከማስረጃ ጋር ማቅረብ ለሁሉም ጠቀሚታ ይኖረዋል።

ትኩረትህ ግን ቂም በቀልና ክስ መሆኑ ያሳዝናል!

በአሁኑ ታላቅ የፈተና ሰዓት፣ ዓላማህ ማኅበረ ቅዱሳንን ለመክሰስና ለመወንጀል ብቻ መሆኑ ዞሮ ዞሮ አንተንም ይጎዳሃል፤ ለቤተ ክርስቲያናችንም ምንም የሚያበረክተው በጎ
ነገር የለም።

ቤተ ክርስቲያናችን ስላጋጠማት ችግር ሊኖርህ
የሚችለውን አስተዋፅዖ ብትታስነብበን ምንኛ ሁላችንም በተጠቀምንበት ነበር።

ግና ቂምና በቀል በውስጥህ በማየሉ አስተዋፅዖህ
የክፋትን መንገድ ተከተለ።ይህ ደግሞ ከክርስቲያናዊ በጎነት ውጭ በመሆኑ፣ ተገዥነቱ
ለእግዚአብሔር መንፈስ አለመሆኑ ግልጽ ነው።

መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በምሕረቱ ይጎብኘን!
አሜን።

ሳሙኤል ዘአሰቦት

Ewnetu Kalie said...

ሰላም ለናንተ ይሁን እውነትን ለምትፈልጉና አስተያየታችሁን ስትሰጡ delete እየተደረገባችሁ ለተቸገራችሁ። በመጀመሪያ ደጀ-ሰላም/ደጀ-በጥብጥ የማህበረ ቅዱሳን እንደሆነ ሳታውቁ የቀራችሁ አይመስለኝም። ስለሆነም አስተያየታችሁን ካልወደዱት በተለይ ደግሞ ጉዳቸውን የሚያወጣ ከሆነ ያለምንም ጥርጥር delete ያደርጉታል። Delete ያደርጋሉ እንዳይባሉ ግን አንዳንዶቹን አስተያየቶች ያስቀሩታል።

ሌላ ለእውነት የቆመ መወያያና አስተያየት መስጫ blog አለ። እዚህ ላይ ይጫኑ ማህበረ ቅዱሳን ወይስ ማህበረ ሰይጣን
ይጎንኙ አስተያየቶንም ይስጡ። ወደፊት ብዙ መወያያ ነጥቦች ይኖራሉ።

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)