September 25, 2009

ይህ ሰው (አባ ሰረቀ) ማን ነው?

Dejeselamoch,
Who is Aba Sereke? Please post an article about him and what he did to our church, if you get information.
September 22, 2009
++++++++++++++++++++++++++++
(ከዘመቻ)
(September 25, 2009)አንድ ደጀ ሰላማዊ “አባ ሰረቀ የሚባለው ስው ማነው? ይህን ያህልስ ማቅን ለማጥፋት ታጥቆ የተነሳበትስ ዓላማው ምንድር ነው?” ሲል መጠየቁን መነሻ አድርጌ የህሊና የውልደት ስብራት ስለገጠመው አባ ሰረቀ (ስም ግብርን ይመራዋል እንዲሉ በ“ሠ” ስሙን አለመጣፌን ልብ ይሉዋል) ማንነት ጥቂት ለማለት ፈለግሁ።

ለነገሩ ይህን ያህል አጀንዳ ሊሆን የሚገባው ሰው እንኳን አልነበረም። አባ ጳውሎስ እንደ ጫማ ውስጥ ጠጠር እየቆረቆረ ዘወትር እረፍት የሚነሳቸውን ማኅበረ ቅዱሳንን ለማፍረስ “ሳልጠራው አቤት ሳልከው ወዴት የሚል፣ ህሊናውን የተነሳ ሰው ፈልጉልኝ” ብለው ወዳጆቻቸውን፣ (መቼም የልብ ወዳጅ እንደሌላቸው የታወቀ ነው፣ እንደ ንጉሴ ያሉ ጥቅመኞች ያሉትን ለማለት ነው) አደራ ባሉት መሰረት ግዕዛን ከሌላቸው እንስሳት የሚመደብ፣ እውነትን እንኳን በተግባር በስም እንኳን የማያውቃት፣ የሥልጣን ጥም ያናወዘው፣ በፍቅረ ነዋይ ልቡ የታወረ፣ አባ ሰረቀ በመብራት ተፈልጎ ተገኘ። አባ ጳውሎስም “ልቤ በሰረቀ ጸና” አሉ።

በእርሱም ልባቸውን አኖሩ። ማኅበረ ቅዱሳንን ባልዋለበት እንደዋለ አድርጎ እንዲከስ ግዳጅ ተጣለበት። ከላባው አባ ላይ ታች ማለቱን ተያያዘው። የማኅበሩን በጎ ስም የሚያጠፋ የሥድብ መጥሀፍ አጻፈና በውድቅት ሌሊት በገንዘብ የገዛቸው ግብር አበሮቹ ፖስተሩን ሲለጥፉ ሁሉ በፖሊስ አስከመያዝ ደርሰዋል። ዳሩ ግን ውሎው ከኢሕአድግ ባለስልጣኖች ጋር የሆነው አባ ሰረቀ ማህበሩን የቅንጅት ቀኝ እጅ እንደሆነና በሚድያዎቹም የሚያስተላልፋቸው መልእክቶች ምእመኑ በመንግስት ላይ እንዲነሳ የሚያደርጉ እንደሁኑ አቀረበ (ለምሳሌ በጅማውና በኢሊባቡር በክርስቲያኖች ላይ የደረሰውን ዘግናኝ ጭፍጨፋ በቤተ ክርስቲያን ላይ የደረሰውን ውድመት መግለጹን) ።

በተለያዩ ግዜያት በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ በአክራሪ ሙስሊሞች አማካይነት የደረሱትን ጭፍጨፋዎች፣ አባ ጳውሎስና መሰሎቻቸው እፍን አድርገው ልክ እንደ ተረቱ “አትናገሩ ጅቡ እኔን እየበላኝ ነው” እንደሚለው ገዳማውያኑ አባቶች እየተገደሉ፣ ክርስቲያኖች ከነ ማተባቸው እየታረዱ፣ አብያተ ክርስቲያናት እየተቃጠሉ፣ እነ አባ ጳውሎስ ግን ምንም እንዳልተፈጠረ አድርገው የቤተ ክርስቲያኒቱን ልጆች ደም ለስልጣናቸው ማቆያ ገፈራ አድርገው ሲያቀርቡ ኖረዋል።

ዛሬም አይናቸውን በጨው አጥበው የቤተ ክርስቲያኒቱን ክብር እንደለመዱት መሬት ላይ ጥለው ሄሮድሳውያን ጌቶቻቸው ሲረጋግጡት ዓለም ሁሉ እንዲያይና ቤተ ክርስቲያኒቱን መሳቅያ መሳለቂያ እንዲያደርጋት ሲያደርጉ በቴሌቪዥን መስኮት ለማየት በቃን። በሲኖዶስ መንበር ላይ ቄሳሮች ተሰይመው ሲዳኙ ለማየት በቃን በአባ ጳውሎስ ዘመነ ፕትርክና ምን ያልታየ ጉድ አለ የቤተ ክርስቲያኒቱን እድገት የማይሻውና ሰበባሰበብ እየፈለገ ቤተ ክርስቲያኒቱን የሚያጣጥላት የኢሃድግ መንግስት ቤተ ክርስቲያኒቱ ከመናፍቃንና ከአክራሪዎች ወከባ ይታደጋት ዘንድ እግዚአብሄር ያቆመውን ማኅበር በማፍረስ ቤተ ክርስቲያኒቱን ለማዳከም በያዘው ስትራቴጂ መሰረት አስቀድሞ በአባ ጳውሎስ አቀነባባሪነት በአባ ሰረቀ ተላላኪነት የተዘጋጀው ትርኢት መድረኩ ላይ እሰከሚገኙ ድረስ ተሳታፊዎቹ እንኩዋን አያውቁም ነበር። አስቀድሞ የተቀነባበረው ቅንብር በህሊና አልባው በመነኩሴ አምሳል በተሰረው ሮቦት በአባ ሰረቀ ቀርቦ በፖለቲካው አጋፋሪ መመሪያ ሰጪነት በአባ ጳውሎስ አሳራጊነት የትርኢቱ ፍጣሜ ሆነ።

በጠቅላላው አባ ሰረቀ ማለት አባ ጳውሎስ ሰራሽ ሮቦት ነው፤ አልቦ ኅሊና።

7 comments:

Anonymous said...

Selam Wondim,

please do not divert the topic. No one is talking about race. They are criticized with thier evil work, not with thier ethinicity. Please also do not write to be against...

Cher Yaseman!

Anonymous said...

I donot think this point is so much usefull. The most important thing that we need to focus now is on prayer, the devil always tries to mislead our attention from what is useful and spiritual.

Remember that, the association of 8000 christians in the first AD which was led by St. Stephen the diakon disintegrated by the evil and cruel deeds of the pharasies who do not want to accept the truth, but God was having plans. Now also even if, I donot believe God will let this to happen, but even if it happens God has plans which is more usefull to the church than what is now, as far as we remain steadfast with our spiritual feelings and thoughts. St.Paul told us, "Do not be like this world" we should look like our fathers but not ...

we need to pray to this fathers, Aba Paulose and Aba Sereke because in every thing they are the ones who are loosing. So let us come back to the main point, pray to your enemies and let us not revenge.

ሰይፈ ሚካኤል said...

Do not give what is holly to dogs - they will only turn and attak you.
Mt.7,6

Anonymous said...

ይነጋል!

ወገኖች እግዚአብሔር በአንድም በሌላም መንገድ ይናገራል። ብዙዎቻችን ለእምነትና ለእናት ቤተክርስቲያናችን ቀናዒነታችን የሚደገፍና የሚወደስም ነዉ። እንደክርስቲያን(የዘመኑን አነጋገር ልዋስና ማለት ነዉ) እንደክርስቲያን እገሌ ማነዉ፤ እገሊት ማናት፤ ቄሱ እንዲህ ናቸዉ፤ ጳጳሱ እንዲያ መባባሉ፤ ያስገምታል፤ ክርስቲያናዊ መስመርንም የጣሰነዉ ብዬ አምናለሁ። አባ ሰረቀ ማን ናቸዉ?(እኔ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ እናት ቤተክርስቲያኔ የተማርኩት አባ የተባሉትን አንቱ ማለት እንጂ መዘርጠጥን አይደለም) እናም እንዲህ ሲል የተፃፈዉ ጽሑፍ በተለያዩ የፖለቲካ ድረ ገፆች ላይ የማነበዉን ዓይነት ቆብ ቀዳጅ ሆነብኝ። እኝህ ሰዉ ክፋትን አልመዉ ጥፋትን ፈፅመዉ ከሆነ፤ ጠያቂያቸዉ የእዉነት አምላክ የሆነዉ ልዑል እግዚአብሔር ነዉ። የፈፀሙት ድርጊት ማኅበረ ቅዱሳንን ለመጉዳትም ይሁን ሌላ ጥፋት፤ ግመልም የሰረቀ መርፌ ሌባ ሌባ ነዉና፤ አትስረቅ ያለዉን ጌታ ህግ መጣሱ በዚህም በዚያም ያስጠይቃል። ማንም ካለጥያቄ ያቺን ፍርድ አያልፋትም። እናም ወገኖች አስተያየታችንን በክርስቲያናዊ ወግ እንድናደርገዉ እንደጠየቃችሁ ሁሉ እገሌ ማነዉ እያሉ ባለፈዉ ሰሞን በአንድ የቤተክርስቲያኒቱ አባት ላይ ያወረዷቸዉ መስሏቸዉ የስድብ ናዳ እናዳወረዱት ቀላሎች ያለ ኢክርስቲያናዊ መጣጥፍም ባትቀበሉ መልካም ነዉ።

ባይሆን ቃሉ እንደሚለዉ እግዚአብሔር በአንድም በሌላም መንገድ ይናገራልና ለምን ይህ ፈተና መጣብን፤ በእኛ አለመታዘዝና ሥርዓቱን መጣስ ነዉ? ያ ከሆነ አባታዊ ቁንጥጫ ነዉና እንታነፃለን፤ ወይስ ቤተእግዚአብሔርን ለመዳፈር የተነሳ ልምጭ? ያ ደግሞ ትግሉ ታግለዉ ከማይጥሉት ጋ ነዉና ዉጤቱን እናያለን። ለሁሉም ወደዉስጣችን እንመልከት። ችግሩ የትላይነዉ የሚለዉን ማወቅ የችግሩን መፍቻ ቁልፍ ማግኘት ማለት ነዉ።

ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋ ይሁን!

Anonymous said...

እረ ለመሆኑ ማበረ ቅዱሳን ማበረ ምናምን ለምን ያስፈልጋል ?

ለምን ሁሉም አማኝ ማለትም
ቄሱም በቄስነቱ
ሰንብተ ተማሪዎችም በዚያው አገልግሎታቸው
ምመናኑም በምመናነንታቸው
ኮሚቴዎችም በየኮሚቴነታቸው በያሉበት አጥቢያቸው አያገለግሉም ?

ማህበረ እገሌ ወገሌ እያሉ ቤተ ክርስቲያንን መከፋፈል ለምን አስፈለገ ?

እንደኔ እንደኔ : በግለሰቦች የሚመሩ ማህበራት ሁሉ ፈራርሰው
ሁሉም አሁን ባለው የቤተ ክርርስቲያን መዋቅር ውስጥ ተካተው በያሉበት አጥቢያ ቢያገለግሉ ለቤተ ክርስቲያን አንድነት የሚጠቅም ይመስለኛል

አለበለዚያ ግን የማህበር ደጋፊና ተቃዋሚ በመባባል እየተነቃቀፉ : ለመልካም ጊዜ የሚጠቅመውን ጊዜ በጭቅጭቅ ማሳለፍ ተገቢ አይደለም ባይ ነኝ

መበረቅዱሳኖችም እኮ ሳያስቡትና ሳይፈልጉት ከብዙ አባቶችና ምመናን ጋር እየተጋጩ : የሚቃወማቸውን ሁሉ በደፈናው ተሀድሶ ምናምን የሚል ተቀጥያ እየለጠፉ የመደዳ ጥላቻና የማይፈለግ ቡድን ውስጥ እየገቡ ናቸው

የዚህ መጨረሻ ደግሞ ጥሩ ወዳልሆነ የእርስ በእርስ መበታተን ያመራናል

Anonymous said...

Character assassination?Mk is good at this. But I think this is an old communist method which was used by many politicians in Ethiopia. By far Abba Tsereke is a better Priest compared to most of the priests whom MK adore.Mk let me telll you something. You can't kill everybody who challenges you on issues, please get courage and dialogue.

gorgoreyos said...

ato sereqe yetehadso telalakie yeb/kn telatnew!!!

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)