September 25, 2009

ማኅበረ ቅዱሳን ስለራሱ ምን እያለ ነው?

(ደጀ ሰላም፤ ሰፕቴምበር 25/2009)፦ ስለማኅበረ ቅዱሳን ሌሎች የሚናገሩት እንዳለ ሆኖ ራሱ ማኅበሩ ስለራሱ የሚለውን ለመመልከት ወደ ድረ ገጻቸው ጎራ ስንል ከዚህ በታች ያለውንና ከማኅበሩ ሰብሳቢ ከቀሲስ ዶክተር ሙሉጌታ ሥዩም ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ አገኘን። ደጀ ሰላማውያን ቢያነቡት መልካም ነው ብለን ስላሰብን ከረዥሙ-ባጭሩ የተወሰኑ ጥያቄዎችንና መልሶቻቸውን እዚህ ለጥፈነዋል።
ቸር ወሬ ያሰማን
አሜን
+++++++
«ማኅበረ ቅዱሳን ለሁሉም ግልጽ አሠራር አለው»
በዲ/ን ማለደ ዋስይሁንና ሻምበል ጥላሁን
ስለማኅበረ ቅዱሳን ከተለያዩ አካላት የተለያዩ ጥያቄዎች እየተነሡ ናቸው፡፡ እነዚህ ማኅበሩ ላይ የሚነሡት ጥያቄዎች አንዳንዶቹ ማኅበሩን በትክክል ባለመገንዘብ በየዋህነት የሚነሡ ጥያቄዎች ሲሆኑ፤ አንዳንዶቹ ግን ማኅበረ ቅዱሳንን በተዛባ ሥዕል በመሣል ኅብረተሰቡ ውስጥ የተሳሳተ አመለካከት ለማስቀመጥ የሚሞክሩ ናቸው፡፡ እነዚህን የተዛቡ አመለካከቶች ለማጥራት፣ ማኅበሩን ባለማወቅ ከአንዳንዶች በየዋህነት ለሚነሡ ጥያቄዎችም ትክክለኛውን መልስ ለመስጠት እንዲሁም በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የማኅበሩን አቋም መግለጽ በማስፈለጉ ከማኅበሩ ሰብሳቢ ቀሲስ ዶክተር ሙሉጌታ ሥዩም ጋር ቆይታ አድርገናል፡፡ ተከታተሉን፡፡

ስምዐ ጽድቅ፡- በቅርቡ በቤተ ክርስቲያን አካባቢ በተከሰተው ችግር ማኅበረ ቅዱሳን ምን አቋም አለው? የብፁዓን አባቶችን የመደብደብ ሙከራ አስመልክቶ ምን ይላል? በአጠቃላይ በችግሩ ዙሪያ ያለው አቋም ምንድነው?

ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ሥዩም፡- ማኅበረ ቅዱሳን የተፈጠረውን ነገር አስመልክቶ በስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ 16ኛ ዓመት ቁጥር 182 ላይ አቋሙን ግልጽ አድርጎ አስቀምጧል፡፡ አሁን በአጭሩ ለመድገም ያህል ለቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ሁሉም መገዛት እንዳለበት ማኅበረ ቅዱሳን ያምናል፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ የሚመራው አካል ነው፡፡ ስለዚህ ለዚህ አካል ውሳኔ ሁሉም የመገዛት ግዴታ አለበት፡፡ ማኅበረ ቅዱሳንም ለዚህ የቤተ ክርስቲያኒቱን ጉዳዮች ለሚወስነው አካል ይሠራል፡፡ ከዚህ አንጻር አሁን በቤተ ክርስቲያን የተከሰተውን ችግር ቅዱስ ሲኖዶስ ሳይከፋፈል በጥልቀት ተወያይቶ ይፈታል የሚል እምነት ማኅበረ ቅዱሳን አለው፡፡

የብፁዓን አባቶችን ቤት መደብደብና ዛቻ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን ልዕልና የደፈረ አሳፋሪ ድር ጊት ነው፡፡ በእውነት ማኅበረ ቅዱሳን እንደሌሎች ማኅበራትና ምእመናን በሁኔታው በእጅጉ አዝኗል፡፡ ድርጊቱም አሳፋሪና አስነዋሪ እንደሆነ በልሳኖቹ ሐመርና ስምዐ ጽድቅ በመዘገብ የጉዳዩን አሳፋሪነት አሳውቋል፡፡ ጉዳዩንም እየተከታተለው ነው፡፡ መንግሥት ይሄንን አሳፋሪ ድርጊት ተከታትሎ ውሳኔ ይሰጣል የሚል እምነት አለን፡፡ በመንግሥት በኩል ስለ ጉዳዩ የሚገለጸውንም ውጤት እንደሁሉም ክርስቲያን በጉጉት እየጠበቀ ነው፡፡

ወደ መጨረሻው ጥያቄ መልስ ስመጣ ማኅበረ ቅዱሳን በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ ስለተከሰተው ችግር ያለው አቋም ሲጠቀልል ለቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔና የበላይነት ሁሉም መገዛት አለበት፡፡ ችግሩም በቅዱስ ስኖዶስ ይፈታል ብሎም ያምናል፡፡

ስምዐ ጽድቅ፡- የፖለቲካ አቋምን በተመለከተስ?

ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ- ከላይ ለመጥቀስ እንደሞከርኩት የእኛ ማኅበር ሃይማኖታዊ አገልግሎት ለመስጠት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ስር የተቋቋመ የአገልግሎት ማኅበር ነው፡፡ ስለዚህ ማኅበሩ እንደ ተቋም የሚሰጠውም አገልግሎት ሃይማኖታዊ ነው፡፡ ለየትኛውም የፖለቲካ ዓይነትና አደረጃጀት የሚያግዝ /የሚሠራ/ እንዲሆን መቼም ቢሆን ፍላጐቱ የለንም፡፡ በማኅበሩ መተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ አምስት እንደተቀመጠው «ማኅበሩ በማንኛውም የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ ምንም ዓይነት ጣልቃ ገብነት አይኖረውም» ይላል፡፡ የዚህን አንቀጽ ይዘት ተግባራዊ ለማድረግ እንዲቻል በማኅበሩ ያሉ የተወሰኑ አካላት በሓላፊነት ላይ እያሉ የማንኛውም የፖለቲካ አባል እንዳይሆኑ በ1998 ዓ.ም የሥራ አመራር ጉባኤያችን ወስኗል፡፡ በውሳኔውም መሠረት የሥራ አመራር ጉባኤ አባላት፣ የሥራ አስፈጻሚ ጉባኤ አባላት፣ የማኅበሩ መደበኛ መምህራን፣ የኤዲቶሪያል ቦርድ ጽ/ቤት አባላት፣ የኦዲትና ኤንስፔክሽን አገልግሎት ጽ/ቤት አባላት፣ ጋዜጠኞች፣ የማዕከላት ሰብሳቢዎች በሓላፊነት ላይ ያሉ መደበኛ አገልጋዮች የማንኛውም የፖለቲካ ¬ፓርቲ አባል አይሆኑም፡፡

ይህ ማለት ግን ¬ለፖለቲከኞች በማኅበሩ የማገልገል ዕድል አይኖራቸውም ማለት አይደለም፡፡ ለፖለቲካ ዓላማቸው ማኅበሩን መጠቀም ግን አይችሉም፡፡ ስለዚህ የትኛውንም የማኅበሩን አባል በግሉ የ«ሀ» ወይም የ«ለ» ¬ፓርቲ ደጋፊ፣ አባል ወይም አመራር እንዲሆን ወይም እዳይሆን ምንም ዓይነት ተቋማዊ ተጽዕኖ በማኅበሩ የሚፈጠርበት ዕድል የለም፡፡ ይህ ግን ሀገርን በመገንባት ረገድ ለአጠቃላዩ ማኅበረሰብ ትርጉም ያለው ልማታዊ ተግባራትን የማከናውን ዓላማና እንቅስቃሴ የለውም ማለት አይደለም፡፡ እንደሚታወቀው ቤተ ክርስቲያን በታሪኳ ያላት የሀገራዊ ልማት ተሳትፎ ከፍተኛ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ቀጣይነት እንዲኖረው ክርስቲያን ምሁራንና ወጣቶች ባላቸው አቅም ሁሉ ይሳተፋሉ፡፡ የልማት ተሳትፎአቸው ለሀገርና ለትውልድ እንዲጠቅም፣ ቤተክርስቲያንም ያላትን ድርሻ እድትወጣ በማሰብ ነው፡፡ ብዙዎቹ ልማታዊ ተግባሮቻችን ደግሞ በቀጥታ የቤተክርስቲያናችንን ጥቅም የሚያስጠብቁ በመሆናቸው እንቅስቃሴያችን ለሌላ ትርጉም በሚጋለጥ መልኩ የሚደረግ ነው የሚል እምነት የለንም፡፡

በእርግጥ እንደተባለው በሀገር ውስጥም በውጪም በ¬ፖለቲካ ወገንተኝነት ማኅበሩን ለማማት የሚፈለጉ ወገኖች እንዳሉ እናውቃለን፡፡ በጣም የሚገርመው ግን የሚሰጡት አስተያየቶች የተዘበራረቁ መሆናቸው በራሳቸው መሠረት የሌላቸው አስተያየቶች መሆናቸውን ያመለክታሉ፡፡ በሀገር ውስጥ ያለው ማኅበሩ የ«ሀ» ፖርቲ ደጋፊ ነው ሲል በውጪ ሀገር ያሉ አንዳንድ ወገኖች ደግሞ የ«ለ» ፖርቲ ደጋፊ ነው እያሉ ተጨባጭነት የሌለውና ምናልባትም የማኅበራችን አባላት በሆኑ የአንዳንድ ግለሰቦች ተሳትፎን መነሻ አድርጐ የሚሰጥ ሚዛናዊ ያልሆነ ድምዳሜ ነው፡፡ ዞሮ ዞሮ ግን ማኅበራችን ቅዱስ ሲኖዶስ በሰጠው መተዳደሪያ ደንብ ላይ ተመርኩዞ አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ሁሉ ባለው የፖለቲካ ሥርዓት ከሚቋቋመው መንግሥት ጋር መሥራት ሃይማኖታዊም ሕገ መንግሥታዊም ግዴታው ነው፡፡ ከዚህ ባለፈ ግን ማኅበሩ እንደተቋም የትኛውንም የፖለቲካ አስተሳሰብ /Ideology/ በመደገፍ ወይም በመቃውም ከፖርቲዎች ጋር ግንኙነት ስለሌለው /ስለማይኖረው/ ለማንም ስጋት ወይም ዕድል ልንሆን አንችልም፡፡ በዚህ ደረጃ ፈርጆን የሚነሣ አካል ካለ ግን ለመፈረጅ ያበቁትን የመረጃ ምንጮች እንዲመረምር በዚሁ አጋጣሚ ሳልጠቁም አላልፍም፡፡

ስምዐ ጽድቅ፡- ማኅበረ ቅዱሳን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ጋር ያለው ግንኙነት የሻከረ ነው፤ ማኅበሩም ለመምሪያው ለመታዘዝ ፈቃደኛ አይደለም የሚሉ አስተያየቶችም አሉ፡፡ እርስዎ እንደ ሰብሳቢ ምን ይላሉ?

ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ፡- ማኅበረ ቅዱሳን ሕገ ቤተክርስቲያን የቤተ ክርስቲያኒቱም ደንብና መመሪያዎች እንዲጠበቁ በጸኑ የሚሠራ ማኅበር ነው፡፡ ይህ ዋነኛ አጀንዳ ያለው አካል የማደራጃ መምሪያውን አሠራር ጠብቆ አይንቀሳቀስም ከተባለ -ራዶክስ /መጣረስ/ ይፈጥራል፡፡ ማኅበሩ በመምሪያው የአሠራር ሥርዓት ላይ ችግር የመፍጠር ፍላጐትም ሥልጣንም የለውም ነገር ግን መምሪያውን ከሚመሩት ግለሰብ ዓላማና አቅም ላይ ግን ጥያቄ አለው፡፡ መከሩ ብዙ ሠራተኞቹ ግን ጥቂት በሆኑበት ቤተክርስቲያን ውስጥ ለአገልግሎት የተሰማሩ ማኅበራት እና ሰንበት ት/ቤቶችን በመምራት ረገድ የሚከተሉት የራሳቸው ፖሊሲ እንደተመሪ /ባለድርሻ/ ምቹ አይደለም፡፡ ማኅበሩ ላይ አሉ የሚሏቸውን ችግሮች በውይይትና በክርስቲያናዊ የምክክር ሥርዓት ከመፈጸም ይልቅ በግልጽና በስውር የማኅበሩን ስም ማጥፋትን ሥራዬ ብለው ይዘዋል፡፡ የተለያዩ አካላትም በማኅበሩ ላይ የተዛባ አመለካከት እንዲኖራቸው ያላ ሠለሰ ሚና ተጫውተዋል፡፡ ማኅበሩ ችግር አለበት፤ ለመምሪያውም አይታዘዝም... ወዘተ የሚለውን የራሳቸውን ሓሳብ መነሻ አድርገው የሚጽፏቸውን ደብዳቤዎች ምስክር እያደረጉ መናፍቃን ደግሞ በመጻሕፍት አሳትመው ሲሰድቡን እያየን ነው፡፡ ስለዚህ ይህንን እያየን ማኅበረ ቅዱሳንን ከሚጠሉ መናፍቃን ጋር እርሳቸው ተመጋግበው እየሠሩ ነው ላለማለት ዋስትና አይሰጥም፡፡ የማኅበሩ አሠራር ችግር አለበት ብለው ቢያስቡ እንኳን ከሠሯቸው በጐ ተግባራት፣ የወጣት ምሁራን ክርስቲያኖች እንቅስቃሴን አስፈላጊነትና አሁን ቤተክርስቲያን ከአጽራረ ቤተ ክርስተያን በኩል እየደረሰበት ካለው ፈተና አንጻር በስብከተ ወንጌል ረገድ ያለውን ርምጃ በመመልከት ችግሮቹን ከሚመለከታቸው ከተለያዩ አካላት ጋር ተግባብቶ በመፍታት ግልጽ አሠራር ማስፈን ይገባቸው ነበር፡፡ ያንን አላደረጉም፡፡ ስለዚህ በአንዳንድ ማኅበሩ የአሠራር ችግሮች እንዳሉበት ለመምሪያውም እንደማይታዘዝ አድርጐ በማናፈስ ሺሕዎች የተሰለፉለትን ቤተክርስቲያን የመጠበቅ ተልእኮ ማነቆ እንዲያጋጥመው እያደረጉ ነው፡፡ ይህ ደግሞ በግለሰቡ ተልእኮ ላይ ማኅበሩ ጥርጣሬ እንዲያድርበት ሆኗል፡፡ ማኅበሩ ለ17 ዓመታት ከተለያዩ መምሪያ ሓላፊዎች ጋር በምክክር ሠርቷል፡፡ ውጤትም ማስመዝገብ ችሏል፡፡ እኛ ጥያቄያችን ዛሬ እርሳቸው ያገኙት አዲስ ነገር ምንድነው የሚል ነው፡፡

ስምዐ ጽድቅ፡- የመምሪያው ዋነኛ ጥያቄ የማኅበሩን ገንዘብና ንብረት ኦዲት በመደረጉ ጉዳይ ነው፡፡ ማኅበሩ በዚህ ላይ ያለው አቋም ምን ስልሆነ ነው ችግሮች የተፈጠሩት?

ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ- ማኅበራችን ለአገልግሎት የሚያስፈልገውን ከፍተኛ ገንዘብ በሀገር ውስጥና ከውጪ ሀገር ካሉ ከማኅበሩ አባላት የሚያገኘው በማኅበሩ የውስጥ ኦዲተሮች የሚሠሩት ሪፖርት ተአማኒነት ስላለውና የሚታዩ ውጤታማ ክንውኖችን መሠረት አድርጐ ነው፡፡ የኦዲት ሪፖርቱ የማይታመንና ግልጽነት የጎደለው ከሆነና ሥራችንም በጎና ውጤታማ ባይሆን ለቀጣዩ ተግባሮቻችን የሚሆን የገንዘብ መዋጮን መሰብሰብ ባልቻልን ነበር፡፡ ስለዚህ አባላቱ መዝናናት ሳያምራቸው በመጠን እየኖሩ ለቤተ ክርስቲያን ከሚከፈሉት ዓሥራት በኩራት ተጨማሪ ለማኅበሩ አገልግሎት የሚሰጡትን ገንዘብ፣ ጊዜና ንብረት በአግባቡ መያዝ የእያንዳንዱ አባል ሓላፊነት ያለባቸው አካላት ሁሉ ግዴታ ነው፡፡ ለዚህ ዋስትና የሚሰጠው ደግሞ የኦዲት ሥራው ነው፡፡ ስለዚህ የኦዲት ሥራን ለማኅበራችን ደኅንነት እንደ አንድ ግብ የምናስብ ነን፡፡ ቅዱስ ጳዉሎስ «ስለዚህ ለጋስ ስጦታ ማንም እንዳይነቅፋችሁ ተጠንቀቁ» ያለውን ቃሉን ሁሌ እናስባለን፡፡ ስለዚህ በየጊዜው የኦዲት ሥራዎች የውስጥ ኦዲተሮቻችን ይደረጋሉ፡፡ ያንን አለማድረጋችን ከማደራጃ መምሪያው ይልቅ የሚጐዳው ማኅበሩን ስለሆነ ስለነገሩን ሳይሆን ስለሚያስፈልገን መቼም ቢሆን እናደርገዋለን፡፡ ማኅበሩ በጠቅላላ ጉባኤው የቤተክርስቲያን መምሪያ ሓላፊዎች ባሉበት የሂሳብ ሪፖርት ያቀርባል፡፡ ጠቅላላ ጉባኤውም ሆነ የሚመለከተው አካል የሂሳብ ሪፖርቱ አላረካኝም በውጪ ኦዲተር ይቀርብ ብሎን አያውቅም፡፡ ጥያቄው ከቀረበ ምንግዜም ማድረግ ይቻላል፡፡

አሁን ግን የተሻለ አደረጃጀትና ሰፊ አገልግሎት በሀገር ውስጥና በውጪም መስጠት ስንጀምር መምሪያው በማኅበሩ አገልግሎት የማይደሰቱ ግለሰቦች እና አካላት ጉዳይ አስፈጻሚ ሆኖ መገኘቱ በእጅጉ ያሳስበናል፡፡ ከምንም በላይ ደግሞ የመመሪያ ሓላፊው የእኛን ስም ለማጥፋት በመ ጠመዳቸውና ጊዜያቸውን ለዚያ እየሠው በመሆኑ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ሰ/ት/ቤቶች ከመምሪያው የሚፈልጉትን ያህል ድጋፍ ለማግኘታቸው ከፍተኛ ጥርጣሬ አለን፡፡ ከሁሉ በላይ ሊያሰጨንቀን የሚገባ የቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ አገልግሎት እንጂ ሌላ አልነበርም በእኛ በኩል ግን የሚጠበቅብንን በማድረግ መልካም ግንኙነት እንዲኖረን ሁሌም እንሻለን፡፡ ችግራችንም ከመዋቅሩ /ከመምሪያው/ ጋር ሳይሆን ከመምሪያው ሓላፊ ጋር መሆኑ ሊታወቅ ይገባል፡፡
(ሙሉውን ቃለ ምልልስ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ)

7 comments:

G.Medhin said...

bo ezin semia leysmae!
yemisema joro yalew yisma!
He who has ears to hear, let him hear

Admasu said...

በዚያን ጊዜ የካህናት አለቆች የሕዝብም ሽማግሎች ቀያፋ በሚባለው በሊቀ ካህናቱ ግቢ ተሰበሰቡ፥ ኢየሱስንም በተንኰል ሊያስይዙት ሊገድሉትም ተማከሩ፥

ይህ ቃል ስለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተነገረ መሆኑን እንገነዘባለን፡፡ ቃሉን ልብ ብለን ስንመረምረው የካህናት አለቆቹም ሆኑ ባለስልጣናቱ ጌታችንን ለመክሰሰ የተነሱት በተንኮል ነው፡፡ ሃሳባቸውም መክሰስ ብቻ ሳይሆን መግደልም ጭምር ነበር፡፡ ባለስልጣናቱና ካህናቱ ጌታችንን የከሰሱት በብዙ ቢሆንም ጠቅልለን ስናያቸው ግን ሁለት ዋና ዋና ክሶች ነበሩ፡፡ ሃይማኖታዊና ፖለቲካዊ፡፡ የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ ይላል፤ የአይሁድ ንጉስ ነኝ ይላል፤ለቄሳር ግብር አትክፈሉ ይላል እና የመሳሰሉት ነበሩ፡፡ ይቀርቡ ከነበሩት ክሶች አንዳንዶቹ የሀሰት ክሶች ሲሆኑ፡ ለምሳሌም ለቄሳር ግብር አትክፈሉ አለ የሚለውን የመሳሰሉት ሌሎቹ ደግሞ ካለመረዳት የሚነሱ ነበሩ፡፡ ወደዝርዝሩ አልገባም፡፡ ዛሬ ይህንን ለመጻፍ የተነሳሁት ሰሞኑን በማኅበረ ቅዱሳንና በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ መካከል ያለውን አለመግባባት በተመለከተ በመንበረ ፓተርያርኩ የተደረገውን ስብሰባ የተመለከተ ዜና አይቼ በማዘኔ ነው፡፡ ማኅበረ ቅዱሳንን የማውቀው የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ሆኜ ጊቢ ጉባዬ ስከታተል ጀምሮ ነው፡፡ አገልግሎቱን አና ጥንካሬውን እረዳለሁ፡፡ የማኅበሩ አባል ሆኜ ለማገልገል ካንዴም ሁለቴ ተመዝግቤ በተለያዩ ምክንያቶች ሳልገፋበት ቀርቻለሁ፡፡ እነዚህ አጋጣሚዎችና የሕትመት ውጤቶቹ ሐመርና ስምዐ ጽድቅ መጽሐፍቶቹ ዐውደ ርዕዮቹ እና ሌሎች አገልግሎቶቹን በሚገባ ለማወቅ እድሉን ስለሰጡኝ በእንዲህ ያለ ሁኔታ ተከሶ ሳየው አዘንኩ፡፡ እናም ይህችን አጭር መልዕክት ማኅበሩን ለሚያውቁት ሁሉ ለመጻፍ ተነሳሁ፡፡ ሶስና በክፉ የርኩሰት ስራቸው አልተባበርም ባለቻቸው ጊዜ በሃይማኖትም በዓላማም የማይመሳሰሉ ሁለቱ ረበናት ከሰዋት በፍርድ አደባባይ ቆማ ሲያዩ ንጽህናዋን የሚያውቁ ሁሉ አለቀሱላት ተብሎ እንደተጻፈ ዛሬም ስለቤተክርስቲያንና ቤተክርስቲያንን በፍጹም ፍቅር በማገልገላቸው ለሚከሰሱ እና ለሚንገላቱ ሌላ ነገር ማድረግ ባንችል ቢያነስ እናልቅስላቸው፡፡ እግዚአብሔር ሁሉን ጸጥ የሚደርግላትን እንደ ነቢዩ ዳንኤል ያለ እውነትን በጥበብ የሚገልጽ አስኪያስነሳልን ድረስ ወደ ርሱ በጸሎት ማሳሰባችንን ቸል አንበል፡፡
ለማኀበሩ አባላትም እነደ ታናሽ ወንድም በርቱ ከፊት ይልቅ ጸንታችሁ ቁሙ ብዬ በትህትና መልዕክቴን ለማስተላለፍ እወዳለሁ፡፡ የመንግሰት የደህንነት ባለስልጣናትን ይዘው ሊያስፈራሩ የሚፈልጉትን ስታዩ አትደንግጡ ይልቁንም ከኛ ጋር ያለው ከነሱ ጋር ካለው ይበልጣል ብላችሁ ተጽናኑ፡፡ በጊቢ ጉባዬ በኩል ላለፋችሁ የማኅበሩ አባላት ወይም እንደኔ ዛሬ የማኅበሩ አባል ያልሆናችሁ በምርቃታችን ጊዜ የተሰጠንን ስጦታ አስታውሱት- መስቀሉን ማለቴ ነው፡፡ ብዙ ሚስጥር ያለው ነገር መሆኑን እያደር እንረዳዋለን፡፡ እኔ አስካሁን ከአንገቴ አልለየሁትም ሺዎች ደግሞ በልባቸው አትመው እንደያዙት አምናለሁ፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከጌታው የሚበልጥ ሎሌ የለም ብሎ እንዳስተማረን ሰድበውት ከሆነ ሰትሰደቡ አይክፋችሁ ከስሰውት ከሆነ በሀሰት ብትከሰሱ አትረበሹ በአጋንንት አለቃ ሰይጣንን ያስወጣል ብለውት ከሆነ ማኅበረ ሰይጣን ብለው ቢጠሩአችሁ አትደነቁ፡፡
አምላከ ቅዱሳን ሁላችንንም በይቅርታውና በምህረቱ ይጎብኘን፡፡
አድማሱ ነኝ

Anonymous said...

I read the whole message .it expressed in the cristian way.i think it covers main points to be discssed.God be with you

Anonymous said...

Dears
I wonder what they have planned. But for me there is some thing good God has planned. It was always like that and it would be the same now. God has never ever left his children in the hands of evils. We pray to our Father and He shall listen.
Don't panic or frustrate, Please stand steadfast to see his wonders.............

Melkamu said...

Tena yistelnge! Cheru Egziabher yetebareke ye Meskel Baal yadergelin! Happy Mesekel to All!

Anonymous said...

Dear Admasu,
Min Elihalehu Egziabher Yistih. Yihin bebetekirstiyan yetegafete fetena egziabher yabridlign,

Tesfa said...

Dear DS,

Thank you for reporting the reality to your readers. You reported what Niguse and his alliances said and accused of MK and also you reported what MK said and what it really means . I think that is what a balanced and real report is. And what it is to blog means. This will help us to make a healthy and constructive discussion and understand things better, what ever our stand might be. This is also a good model for others who are biased and out of reality. Let us keep like this and once more I will remind not to allow those elements like tehadeso to disturb this healthy and constructive discussion which is of paramount importance for our APOSTOLIC CHURCH

Redeate Egziabher ayileyen

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)