August 2, 2009

ሰበር ዜና (Breaking News) የፓትርያርኩ ረዳት በቁጥጥር ሥር ዋሉ

• “ታዝዤ ነው” የጥበቃ ክፍል ኃላፊ አቶ ብርሃኔ

(ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 1/2009): የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ረዳት (አቡነ ቀሲስ) አባ ዕንቁ ባሕርይ ከቤተ ክህነቱ የብፁዓን አባቶች ቤት የሌሊት ድብደባ ጋር በተገናኘ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ውስጥ አዋቂዎች ገለፁ።

Dear Dejeselamaweyan,
This news is refuted by Ben of Ethiopiafirst.com. Ben also insulted Deje Selam, for the reasons we did not know yet. We have one thing to say to brother Beniam though: this whole issue is not about you and us; it is about our Mother Church. Please stop the unwanted cyber war both of us do not want to wage. OK, brother? We don't think you understand the Church issue as an outsider. Leave the Church alone. As per the incarceration of Abba Enqu Baherey, we have reconfirmed his imprisonment. If there is any development as of then, we will report accordingly.
Cher Were Yaseman,
DS

+++++

ጁላይ 15/2009 ሌሊት ጨለማን ተገን አድርገው ወደ ብፁዓን አባቶች መኖሪያ ሕንጻ በመግባት ጥቃት ያደረሱትን ወንጀለኞች ጉዳይ በመመርመር ላይ የሚገኘው ፖሊስ የቤተ ክህነቱን ጥበቃ ክፍል ኃላፊ አቶ ብርሃኔን ... ባለፈው ረቡዕ በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ ማድረጉም ታውቋል። ግለሰቡ የግቢውን ጥበቃ የሚቆጣጠሩ እንኳን ሰው ወፍ ዝር ብትል የሚያውቁ ሆነው ሳለ ይህንን የሚያህል ትልቅ ወንጀል ሲፈጸም “ምንም አላውቅም” ማለታቸው ይታወሳል። ስለ ጉዳዩ ቃለ ምልልስ ልታደርግ የደወለችውን የዶቼቬሌ ጋዜጠኛ “ልጃቸው ነኝ” በማለት ለማታለል የሞከሩት አቶ ብርሃኔ ለፖሊስ ጉዳዩን እንዲፈጸም ያደረኩት “ታዝዤ ነው” ካሉ በሁዋላ በዋስ እንደተለቀቁ ታውቋል። አቶ ብርሃኔ ነገሩን ለማመን የተገደዱት ሌሎች ሁለት የጥበቃ ሰራተኞች ስለ መሩባቸው ነው ተብሏል።

ፖሊስ ምርመራውን በመቀጠል ጉዳዩ ወደ ቅዱስ ፓትርያርኩ ጽ/ቤት የመራው ሲሆን በዚሁ ምክንያት ለአቶ ብርሃኔ ትዕዛዝ በመስጠት ወንጀሉ እንዲፈጸም አስደርገዋል የተባሉት የፓትርያርኩ ረዳት አባ ዕንቁ ባሕርይ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ታውቋል። ለአቶ ብርሃኔ ትዕዛዝ ሰጥተዋል የተባሉት አባ ዕንቁ ባሕርይ “ያዘዝኩበት ወረቀት የታለ” በማለት ለማምለጥ መሞከራቸው ተሰምቷል። ጉዳዩ በዚሁ ከገፋ አባ ዕንቁ ባሕርይ ራሳቸው ከማን ትዕዛዝ እንደተቀበሉ በጉጉት የሚጠበቅ ምስጢር ይሆናል ማለት ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ወንጀሉን የፈጸሙት ሰዎች በሁለት መኪና ተጭነው ወደ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ግቢ የገቡት ሁሉም ሰው በሚገባበት በር ሳይሆን ፓትርያርኩና የተወሰኑ እንግዶች (ቪ.አይ.ፒዎች) የሚገቡበት የፓላሱ ዋና መግቢያ በር እንደሆነ ታውቋል። ከአባቶች ስልክ የተደወለለት ፖሊስ በሌላኛው በር ለመግባት ሲሞክር የጥበቃ ሰራተኞች “አገር ሰላም ነው” እያሉ የመለሱት በዚህ ምክንያት ነው ተብሏል።

አባ ዕንቁ ባሕርይ ሐሙስ ከተያዙ በሁዋላ ፍርድ ቤት ቀርበው የ14 ቀን ቀነ ቀጠሮ ተጠይቆባቸው ወደ ማዕከላዊ እስር ቤት ገብተዋል። ስለ ጉዳዩ አስተያየታቸውን የጠየቅናቸው ውስጥ አዋቂዎች አንድ አቡነ ቀሲስ (ረዳት) በራሳቸው ፍላጎት እንዲህ ዓይነት ትዕዛዝ ለመስጠት እንደማይሞክሩ ተናግረው ትዕዛዙ ከርሳቸው በላይ ከሆነ ሰው ሳይመጣ እንዳልቀረ ገምተዋል።
Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)