August 6, 2009

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላይ የፈጸሟቸው ዐበይት ችግሮች

(ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 5/2009)
ውድ አንባብያን፣
ይህ አጭር ጽሑፍ የተወሰደው “የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዋና ዋና አንገብጋቢ ችግሮች እና መፍትሔዎች፦ ከፍተኛ ትኩረት የሚሻ” ከሚል በግንቦት 2001 ዓ.ም ተዘጋጅቶ ለቅዱስ ሲኖዶስ ቀርቧል ከተባለ ዘገባ ላይ ነው። የዶኩመንቱ አዘጋጅ ስም፣ ለምን ዓላማ እንደተዘጋጀ፣ በማንና ለማን ወይም ለነማን እንደቀረበ አይጠቅስም። ይሁን እንጂ ከያዘው መሠረታዊ የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ አንጻር “ስለ ቅዱስ ፓትርያርኩ” የሚናገረውን ብቻ ቀንጭበን አውጥተነዋል። ያወጣንበት ዓላማ ከተራ ስድድብና መወጋገዝ በመውጣት፣ ከግለሰቦች ደጋፊነትና ወገንተኝነት በመጽዳት ቅዱስ ፓትርያርኩም ከዚህ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ለማሳሰብ ነው።


መልካም ንባብ፤
ደጀ ሰላም
+++
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላይ የፈጸሟቸው ዐበይት ችግሮች የሚከተሉት ናቸው፦

(To read in a PDF format, click HERE.)
1. ለዘመናት በአንድነቷ የምትታወቀው ቤተ ክርስቲያናችን ቅዱስ ፓትርያርኩ ለግል ዝናና ስልጣናቸው ሲሉ በእልህ በሚፈጽሙት ድርጊት ቤተ ክርስቲያኒቱ ለሁለት ተከፍላለች፡፡ በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ በሚገኙ ምዕመናን መካከል ከፍተኛ ልዩነት ተፈጥሯል፡፡ በአባቶች መካልም በጥርጣሬና በጥላቻ ከመተያየት ባሻገር መወጋገዝን አስከትሏል፡፡ ይኸውም ዛሬ ከፈጠረው ችግር ባሻገር ለነገዋ ቤተ ክርስቲያን ለትውልድ የሚተርፍ ከፍተኛ ፈተና ነው፡፡ ለዚህም አንዱና ዋናው ምክንያት ቅዱስ ፓትርያርኩ ምንም ዓይነት የእርቅና የስምምነት በር እንዳይከፈት በማድረግ ወይም በመዝጋት እርቅ እንዳይመጣ ሰላምም እንዳይወርድ አፍነው በመያዛቸው ነው፡፡ ለምሳሌም በጥቅምት ወር 2000 ዓ.ም የቀረበውን የእርቅ ጥያቄ ውድቅ ማድረጋቸው ይጠቀሳል፡፡

2. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የሥራ አስፈጻሚነትና የአስተዳደር ሥልጣን በተመለከተ በሕገ ክርስቲያን አንቀጽ 30 ቁጥር 1 እስከ 21 እንደሰፈረው፡-
1. የቅዱስ ሲኖዶስ አስተዳደር በየጊዜው የሚወስናቸውን ጉዳዮች ከየቤተ ክርስቲያናቱና ከልዩ ልዩ መ/ቤቶች የሚቀርቡትን ጥያቄዎች በሕጉ መሠረት መፈፀምና ማስፈፀም፣
2. ዋናውን መ/ቤት፣ የኮሚሽኑን፣ የቦርዶችን፣ የድርጅቶችንና የመምሪያዎችን በአጠቃላይ በቤተ ክርስቲያኒቱ ሥር የሚገኙትን የሥራ ዘርፎችን ሁሉ ማስተዳደርና መምራት፣
3. ማንኛውንም የቤተ ክርስቲያኒቱን ገንዘብ በትክክል ገቢ መሆኑንና በሕጋዊ መንገድ ወጪ እየሆነ ለቤተ ክርስቲያኒቱ አገልግሎት መዋሉን መቆጣጠር፣
4. የመምሪያና የልዩ ልዩ ድርጅቶች ሓላፊዎችን እያጠና እና ፓትርያርኩን እያስፈቀደ መሾም፣ የሥራ ሓላፊዎችን የሥራ ዝውውርና ዕድገት በአስተዳደር ጉባኤ እየተጠና እየተወሰነ እንዲፈፀም ማድረግ፣
5. በየደረጃው ያለውን የሠራተኛ መብትና ግዴታ ማለትም የጡረታ፣ የጤና አጠባበቅ፣ የደረጃ ዕድገት፣ የፈቃድ አሰጣጥ፣ የዲስፕሊን ውሳኔ አፈጻጸም እና የመሳሰሉትን ሁሉ በሕጉ መሠረት መፈጸማቸውን መቆጣጠርና አመራር መስጠት፣
6. በበጀት የተመደበውን ማንኛውንም የቤተ ክርስቲያኒቱ ንብረት በፊርማው ማንቀሳቀስ፣
7. ማናቸውም የቤተ ክርስቲያኒቱ ገንዘብ ገቢና ወጪ በሕጋዊ የሂሳብ አያያዝና ደንብ መሠረት መሠራቱን መታተልና መቆጣጠር. . . ወዘተ እንደሚያካትት ተደርግጓል፡፡

ነገር ግን ይህን ድንጋጌ በመጣስና የጠቅላይ ቤተ ክህነቱን ዋና ሥራ አስኪያጅ ስልጣን በመጋፋት ቅዱስ ፓትርያርኩ በማን አለብኝነት አመመራቸው የወደዱትን ለመጥቀም ሲሉ አላግባብ ሹመዋል፣ የደረጃ እድገት ሰጥተዋል፣ ቀጥረዋል፣ አዛውረዋል፡፡ በግል የጠሉትንም ከቅዱስ ሲኖዶስ መመሪያ ውጪ ሽረዋል፤ ከደረጃ ዝቅ አድርገዋል፣ ደመወዝ አግደዋል፣ ከሥራ አባርረዋል፡፡ በዚህም የቤተ ክርስቲያኒቱን ገንዘብ ለከፍተኛ ብክነት ዳርገዋል፡፡

3. የሲኖዶሱን ሥልጣን በተመለከተ በሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ 7 በቁጥር 11 እና 12 ላይ ማለትም፡-
• በውጭ አገር ለአገልግሎት የሚመደቡ እንዲሁም በአገር ውስጥ ትምህርት ተምረው የውጭውን ትምህርት መማር የሚችሉ ካህናትን እየመረጠ እንዲላኩ የማድረግ፣
• ማንኛውም ሰው ቤተ ክርስቲያኒቱን ወክሎ ለሥራም ሆነ ለጉብኝት ወደ ውጭ አገር በሚላክበት ጊዜ ቅዱስ ሲኖዶስ እየፈቀደ መሆኑን ይደነግጋል፡፡
• እንዲሁም የፓትርያርኩን ሥልጣንና ተግባር በሚገልጸው አንቀፅ 15 ቁጥር 12 ላይ ፓትርያርኩ በውጭ ስብሰባ ለመገኘትም ሆነ ጉብኝት ለማድረግ በሚፈልጉበት ጊዜ ስለ ተልእኮው ጉዳይ አስቀድሞ በቅዱስ ሲኖዶስና ቋሚ ሲኖዶስ ማስወሰን እንደሚገባቸው ተደንግጓል፡፡

ነገር ግን ፓትርያርኩ ለቅዱስ ሲኖዶስ ባላቸው ንቀት ምልዓተ ጉባኤውን ሳያስፈቅዱ ክብረ ቤተ ክርስቲያንን በሚያስነቅፍ መልኩ ፕሮቶኮል ያልጠበቁ እንቅስቃሴዎችን አድርገዋል፡፡ ያለምንም ብቁ ምክንያትና ተልዕኮ በየጊዜው በቤተ ክርስቲያኒቱ ብር በተራ ስብሰባዎች ላይ ለመገኘት በተለያዩ ዓለማት አጀብ በማስከተል በመውጣት፣ የቤተ ክርስቲያኒቱን ገንዘብ ለስብከተ ወንጌል ከማዋል ይልቅ መንሸራሸሪያ አድርገውታል፡፡ በዚህም የድሀይቱን ቤተ ክርስቲያን ገንዘብ በከፍተኛ ደረጃ እንዲባክን አድርገዋል፡፡

4. የታላላቅ ገዳማት አበምኔቶችና የታላላቅ አድባራት አስተዳዳሪዎች በየሀገረ ስብከቱ ሊቃነ ጳጳሳት እየተመረጡ ሲቀርቡላቸው መዓርግ ስም እየሰጡ መሾም ሲገባቸው ከተሰጣቸው ሥልጣን ገደብ አልፈው ማንንም ሳይጠይቁ በመሾምና በመሻር ፓትርያርኩ ሕግን ተላልፈዋል፡፡ በተጨማሪም የተመደበ በጀት ይኑር አይኑር ሳይጠናና ሳይረጋገጥ “ዓላማዬን ያሳኩልኛል” ያሏቸውን ሰዎች ወደ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤትና አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት በመላክ፣ በግዴታም እንዲቀበሉ በማስገደድ ከሕግ የወጣ ተግባር ፈጽመዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ሀገረ ስብከቱንና አድባራቱን የእዳ ተሸካሚ አድርገዋቸዋል፡፡

5. የቤተ ክርስቲያኒቱ የሀገረ ስብከት አወቃቀር መሠረት የሚያደርገው የዞን አስተዳደርን ስለሆነ እንደመንግሥት አወቃቀር ከክልል መስተዳድሮች ጋር በቀላሉ ተቀራርቦ ለመሥራት የሚያስችል አሠራር የለም፡፡ ይህን ችግር ለመፍታት የመዋቅር ማስተካከያ ያስፈልጋል፡፡ በተለይም በአማራ፣ በትግራይ፣ በኦሮሚያ እና በደቡብ ክልሎች ቤተ ክርስቲያኒቱን በክልል ደረጃ ሊወክል የሚችል አሠራር ተዘርግቶ ቤተ ክርስቲያኒቱ ከየክልሎቹ መንግሥታት አሠራር ጋር በቀላሉ ተቀራርባ መሥራት የሚያስችላትን አወቃቀር መፍጠር ነበረባት፡፡ ሆኖም ፓትርያርኩ ስልጣኔን ይሸራርፍብኛል ከሚል አቋም ይህን ለመተግበር ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ችግሩ እስከ አሁን ዘልቋል፡፡

6. ጋጠ ወጥ በሆኑ ዘፈኖቿ በዓለም ዘንድ የምትታወቀውንና እነዚህ ዘፈኖቿን ኢትዮጵያ ውስጥ ለመዝፈን የመጣችውን (ቢዮንሴ የምትባል) ዘፋኝ በቤተ ክርስቲያን ዓውደ ምሕረት የቤተ ክርስቲያንን፣ የአባቶችንና የምዕመናን ክብር በሚነካ መልኩ የፈጸሙት አሳዛኝ ታሪካዊ ስህተት የእርሳቸውን መንፈሳዊ መሪነት ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ነው፡፡ በእርግጥ ግለሰቧ ቤተ ክርስቲያንን መጎብኘት ከፈለገች እንደማንኛውም ጎብኚ ልትጎበኝ ትችላለች፡፡ ነገር ግን ያ ሁሉ የዐውደ ምሕረት አጀብ አስፈላጊ አልነበረም፡፡ እርሳቸውም ቢሆኑ መነጋገር ካስፈለጋቸው በእንግዳነቷ በቢሮአቸው ጋብዘዋት ማነጋገር ሲችሉ ብጹዓን አባቶችን ሰብስበው ለስምንት ሰዓታት ሙሉ በቤተ ክርስቲያን ዐውደ ምሕረት ሲጠብቁ መዋላቸው የቤተ ክርስቲያኒቱን ክብር የሚያጎድፍና የምእመናንን አንገት ያስደፋ ተግባር ነው፡፡

7. የቅዱስ ሲኖዶስን ፈቃድና እውቅና ሳያገኙና የቤተ ክርስቲያኒቱን ቀኖና ሳይጠብቁ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናትን እንደ ቀበሌ ጽ/ቤት በመቁጠር የራሳቸውን ምስል ማስለጠፋቸውና ለዚህም የስዕል ሰሌዳ ያለ ቅዱስ ሲኖዶስ ፈቃድ የቤተ ክርስቲያኒቱን ገንዘብ ለግለሰቦች መበልጸጊያና ለብክነት መዳረጋቸው ቤተ ክርስቲያኒቱንና ምእመናንን ያሳዘነና በማሳፈር ላይ ያለ ጉዳይ ነው፡፡

8. ሕገ ቤተ ክርስቲያን በሚያዝዘው መሠረት ቅዱስ ሲኖዶስ ሳይፈቅድና አመራር ሳይሰጥ በራሳቸው የግል ፈቃድ ዝክረ ቤተ ክርስቲያን በማለት በሽልማት ስም ቤተ ክርስቲያንን የማይወክሉ ሰዎችን በማሰባሰብ ግልጽ ባልሆነ መንገድ በቤተ ክርስቲያኒቱ ስም በርካታ ገንዘብ የገቢና ወጪ ሕጋዊ አሠራር በሌለው መንገድ ከቤተ ክርስቲያኒቱም ጭምር እንዲሰበሰብ አድርገዋል፡፡ በዚህም ምዕመናን ቤተ ክርስቲያኒቱን በጥርጣሬ እንዲመለከቷት በር ከፍተዋል፡፡ ከራስ ወዳድነታቸው የተነሳ ለራሳቸው ስጋዊ ዝና ሲሉም የቤተ ክርስቲያኒቱን ታሪክ በትውልድ ፊት አጉድፈዋል፡፡

9. በመከራ ውስጥ አልፎ የቤተ ክርስቲያኒቱን ትምህርት ለተማረው ተገቢ ሥራ መደብ ከመስጠት ይልቅ ቤተ ክርስቲያኒቱን እንደግል ድርጅት በመቁጠር በዘመድ አዝማድ ወይዘሮዎችና አቶዎች ወሳኝ የቤተ ክርስቲያኒቱን ቦታዎች እንዲይዙ በማድረጋቸው ቤተ ክርስቱያኒቱን ለከፍተኛ ምዝበራና ውርደት አጋልጠዋል፡፡ እንዲህ ዓይነት ሥነ ምግባር የሌላቸው ወይዘሮዎችን በማረም ፈንታ ሽፋንና ደጋፊ በመሆን ቤተ ክርስቲያን ላይ ከፍተኛ በደል እየፈጸሙ ነው፡፡

10. በቤተ ክርስቲያኒቱ ገንዘብና ንብረት ላይ በማን አለብኝነት በማዘዝ ዛሬ ቤተ ክርስቲያኒቱ በከፍተኛ የገንዘብ እጥረት ላይ እንድትገኝ አድርገዋል፡፡

11. በአምባገነናዊ አስተዳደር ሂደታቸው የቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ፈረሰ፣ ንብረት ተዘረፈ፣ ገንዘብ ተመዘበረ፣ ቀኖና ተፋለሰ፣ አድልዎ ነገሰ፣ የሰው መብት ተጣሰ፣ ወዘተ በማለት ማስተካከያና እርምት እንዲደረግ የሚጠይቁ ብፁዓን አባቶችን ለማስደንገጥ ከሀገረ ስብከታቸው ያነሳሉ፣ በጠላትነትም ይፈርጃሉ፡፡ በመንግሥት ባለስልጣናት ስምም ያስፈራራሉ፡፡

12. ከሀገር ውጭ ያለችውን ቤተ ክርስቲያን እንዲያገለግሉ ብቃት ያላቸውን ሰዎች ከመላክ ይልቅ በገንዘብና በዘመድ አዝማድ የሚላከው ይበልጣል፡፡ በዚህ መልኩ የተላኩት ብዙ ሰዎች ለቤተ ክርስቱያኒቱም ዕድገት ሳይሆን ከሃገር መውጣታቸውን ለግል ጥቅማቸው ማስፈጸሚያ በማድረግ፣ ቤተ ክርስቲያኒቱን በማዋረድ ምዕመናንን እያሳቀቁ ከፍተኛ በደል እየተፈጸመ ነው፡፡
13. ለቤተ ክርስቲያኒቱ አገልጋዮች በመጡ የተለያዩ የውጭ የትምህርት ዕድሎች ዘመዶቻቸውን በቤተ ክርስቱያኒቱ ስምና ገንዘብ ልከዋል፡፡ የሔዱትም ሰዎች አብዛኞቹ በዚያው ስለሚቀሩ የተያዩ ኤምባሲዎችና ቆንስላ ጽ/ቤች ለቤተ ክርስቲያኒቱ ያላቸው እምነት በከፍተኛ ደረጃ ዝቅ እያለ መጥቷል፡፡ ይህም ለቤተ ዘመድ የሚሠሩት ተራ ጥቅማ ጥቅም ቤተ ክርስቲያኒቱን ብዙ የውጭ ሀገር ሰዎች በዝቅተኛ አይን እንዲመለከቷት አድርጓል፡፡

14. በዘመነ ፕትርክናቸው ከምንጊዜውም በላይ የስብከተ ወንጌል አገልግሎት መዳከሙ ብቻ ሳይሆን መጥፋቱ ግልጽ ነው፡፡ ለዚህም አንዱ ማሳያ ቤተ ክርስቲያኒቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ ያላት የምዕመናን ቁጥር መቶኛ ድርሻ በተዓምራዊ ፍጥነት እየቀነሰ መምጣቱ ነው፡፡ በአንጻሩም የሌሎች እምነት ተከታዮች በከፍተኛ ጥፍነት እያደገ መሆኑን የ1999 እና 2000 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የህዝብና ቤት ቆጠራ ውጤት በግልጽ እያሳየን ነው፡፡

15. በሙስናና በተለያዩ ከፍተኛ ችግሮች በደል ተገኝቶባቸው ከመንግሥት በግምገማ የሚባረሩ አካላትን ከጥፋታቸው ሳይታረሙ ከነችግራቸው በማቅረብ ቤተ ክርስቱያኒቱን የዘራፊዎች ዋሻ አድርገዋልታል፡፡

16. ያለምንም ይሉኝታ በቤተሰብና በቤተዘመድ በእውቅና እንዲፈጸም በሚያደርጉት የቅጥር ሂደት ባለሙያዎችና ምሁራን በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ ምንም ድርሻ አግኝተው ሙያቸውን ለቤተ ክርስቲያን ማበርከት እንዳይችሉ አድርገዋል፡፡

17. በየአህጉረ ስብከቶች የሚገኙ ገዳማት፣ አድባራትና አብያተ ክርስቱያናት እየተዘጉ ካህናትና አገልጋዮቿ በረሀብና በመተዳደሪያ እጦት እየተሰደዱ ባሉበት በአሁኑ ወቅት ፓትርያርኩ ግን ለዚህ አንዳች መፍትሔ ከመፈለግ ይልቅ ስለራሳቸው ዝናና ክብር የህዝብ ግንኙነት ሥራ እንዲሠራላቸው አሜሪካን ሃገር ለሚገኘው የሃገር ፍቅር ሬዲዮ አዘጋጅ 100‚000.00 (መቶ ሺህ ብር) እንዲሰጥ ማድረጋቸው ዕለት ዕለት የሚያስጨንቃቸው የራሳቸው ስምና ዝና መታወቅ እንጅ የቤተ ክርስቲያን ችግር መፍትሔ ማግኘቱ አለመሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡

18. ከቤተ ክርስቲያኒቱ አስተዳደር ጋር ተያይዞ በሀገር ውስጥ በየክልሉ እንዲሁም ከሀገር ውጭ በሚፈጠሩ ችግሮች በስተጀርባ እርሳቸው የተለያየ የጥቅም ግንኙነት ስለሚያደርጉ ለችግሮቹ መፍትሔ ለመስጠት አስቸጋሪ ደረጃ ላይ ተደርሷል፡፡ ለችግሮቹ መፍትሔ ከስጠትም ይልቅ ችግሮቹ በተከሰቱበት ሀገረ ስብከት አስተዳደር ውስጥ ጣልቃ በመግባት ግጭቶች እንዲባባሱ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡

19. በተለያዩ ጊዜያት የቤተ ክርስቲያኒቱን የኢኮኖሚያዊ ልማት ተሳትፎ ያሳድጋሉ፣ ገዳማትንና የአብነት ትምህርት ቤቶችን ከመዘጋት ያድናሉ ተብለው የታመባቸው የተለያዩ የልማት ፕሮጀክት ጥናቶች ለምሳሌ የቱሪዝም፣ የግብርናና ወዘተ ተግባራዊ እንዲሆኑ በቅዱስ ሲኖዶስ ከተወሰነ በኋላ ሥራ ላይ እንዳይውሉ ሆን ብለው አምባገነናዊ ሥልጣናቸውን በመጠቀም ተዳፍነው እንዲቀሩ አድርገዋል፡፡

20. ፓትርያርኩ በሚሰጧቸው የልብ ልብ ስለ ፓትርያርኩ እንጂ ስለ ቤተክርስቲያን የማያውቁና የማይጨነቁ ቤተ ዘመዶቻቸው ሊቃነ ጳጳሳትን ሳይቀርና እውነተኞች የቤተ ክርስቲያኒቱን አገልጋዮች እየገላመጡ እና እያሳቀቁ ነጻነት እንዳይሰማቸው ያደርጋሉ፡፡

21. የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽንና የኪራይ ቤቶች አስተዳደር የገንዘብ ስርጭት እና አጠቃቀም ላይ የእርሳቸውን የግል ጥቅም በሚያስከብር ስውር መንገድ የሚሠራበት ሁኔታ በመኖሩ ቤተ ክርስቲያኒቱን ለከፍተኛ ሙስና እየዳረግዋት ነው፡፡ ለምሳሌ ቢያንስ በወር ውስጥ ለግል ጥቅማቸው ህጋዊ ባልሆነ አሠራር ከቤቶች ኪራይ እስከ 10‚000.00 (አሥር ሺህ) ብር ይወስዳሉ፡፡ ይህም በቤተ ክርስቲያኒቱ ሀብት ላይ በማን አለብኝነት እንደፈለጋቸው እያዘዙ መሆኑን በግልጽ ያሳያል፡፡

22. የቤተ ክርስቲያኒቱን ሚዲያዎች በተገቢው መንገድ አደራጅቶ ለምዕመናን የማስተማሪያ እና ቤተ ክርስቲያኒቱን ማስተዋወቂያ መንገድ ከማድረግ ይልቅ ያለምንም ኤዲቶሪያል ፖሊሲና ግልጽ አሠራር ለራሳቸው መጠቀሚያ እንዲሁም ማሳደሚያ አድርገዋቸዋል፡፡ ይህም ሰዎችን ስለ ቤተ ክርስቲያኒቱ የተሳሳተ ስዕል እንዲኖራቸው አድርጓል፡፡
23. በአጠቃላይ ቤተ ክርስቲያኒቱ ራዕይ አልባ እንድትሆን ማድረጋቸው አስቸኳይና አፋጣኝ መፍትሔ የሚፈለግለት ጉዳይ ሆኗል፡፡ በመሆኑም አስፈላጊ የሆነውን የመፍትሄ ሃሳብ ከልብ አጢኖ አፋጣኝ እርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል፡፡

ምንጭ፦ “የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዋና ዋና አንገብጋቢ ችግሮች እና መፍትሔዎች፦ ከፍተኛ ትኩረት የሚሻ” (ግንቦት 2001 ዓ.ም)፤ ከገጽ 3-9።


ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፣ ወእጬጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣
ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱምና የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ለሰላም የክብር ፕሬዚደንት፣
በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላይ የፈጸሟቸው ዐበይት ችግሮች
ምንጭ፦
“የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዋና ዋና አንገብጋቢ ችግሮች እና መፍትሔዎች፦ ከፍተኛ ትኩረት የሚሻ”
(ግንቦት 2001 ዓ.ም)፤
ከገጽ 3-9።
ቅንብር፦
“ደጀ ሰላም” http://deje-selam.blogspot.com/

36 comments:

Anonymous said...

Yihu hulu sile min deresebin?????????????????

tad said...

Why it took the EOC Holy Synod 17yrs to expose those accusations?. There are a lot of people who argue that the Holy Synod does't make mistake.So what was going on for 17 yrs with in the Holy Synod?. If we are not able to ask those questions and look at things broadly, I think we are looking for the scapegoats.Let the Holy Synod as a whole ask for forgivenness. Where were MK for all those yrs?. Were they not defending this patriarch here and there? unconditionally.Mk is fast in telling people who is tehadiso and who is not. You see where I don't get it.If MK thinks the survival of its organization is more important than the existance of EOC, I think it is heading for its dooms.

tesfa said...

በውነቱ ፓትሪያርኩ ጥሩ ሰው አለመሆናቸውን ብዙ ቢሮአቸው ተመላልሸ አይቻቸዋለሁ ነገር ግን እንደዚህ ከከፍተኛ ሥፍራ ላይ ወድቀው መሰበራቸውን አላውቅም ነበር "እንግዲህ ከወዴት እንደወደቅህ አስብ"የሚለው ቃል ትዝ አለኝ በተለይም በተራ ቁጥር 14፤17እና23 ላይ ያለው ቃል ልቤን አደምቶታል እኔም ያንገበገበኝ ይኸው ነው ማለት ወንጌልን ማጥፋታቸው፤ቤተ ክርስቲያኒቱን ራእይ አልባ ማድረጋቸው ፤የቤተ ክርስቲያኒቱ ሊቃውንት በድህነት መፈናቀላቸው ፤
ለዚህ ሁሉ በደል ምክንያት ወንጌል አለመሰበኩ ነው ወንጌል ካልተሰበከ በደል አይጠፋም በደልና ግፍ ካለ ደግሞ ራእይ አይኖርም፤ራእይ ከሌለ ህልውና አይኖርም። ለዚህ ነው ወንጌልን እንስበክ ከዚህ ከወደቅንበት ገደል የሚያነሣን ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው የምንለው።በነገራችን ላይ አባታችን ሳይታመሙ አይቀርም ፎታቸውን በየቤተ ክርስቲያኑ ለጥፈው ስመለከት መታመማቸውን ነው ይተገነዘብሁት ሰውየው ታመዋል ወይም በክፉው ተይዘዋልና እንጸልይ 1ኛዮሐ 3፤19 ለኒህ አባት ምክር መስጠት ፤ለማስተካከል መሞከር አይቻልም ፡ምን አልባት ሬሳ ምቀስቀስ እንዳይሆንብን ሰውየው ታመውል እንጂ በጤናቸው አይደሉም አትፈረዱባቸው ያልገባንስ መታመማቸውን ያላወቅን ሞኞች እኛ ነን

dan said...

ይሄ ርእስ "ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላይ የፈጸሟቸው ዐበይት ችግሮች" መወያያው ጉዳዩ በቤተ ክርስቲያናችንና በክርስቲያን ልጆቿ ላይ ፓትሪያርኩ ያደረሱት ቁጥራቸው የበዛ በደል ሙስና ላይ ብቻ ያተኮረ እንዱሆን:

ሎሎች ሃሳቦች ወይም ነጥቦች እየተወረወሩ ከዚህ አሳሳቢ ጉዳይ እንዳያዘናጉን::

ለማዘናጋት የምትሞክሩ ሰሚ/አንባቢ አይኖራችሁም::

ሃሳባችሁን በቦታው አስፍሩ:: ለምሳሌ "የማሕብረ ቅዱስን" ንትርክ/ውይይት በሚገባው ቦታ ይሁን::

Unknown said...

Dan,
Thank you for the above comment.
DS

Unknown said...

My FELSETA prayer for our nation and our church

Oh Lord who are in haven, bless us with the grace of our father and forgive our sins with your Merci. We indeed have trespassed you and never sought your forgiveness. Ethiopia raises her hands to you once more to bring freedom and unity through you. We plead to you in leading us to the passage of wisdom seeking your will in finding the right leader that will unite us.

Oh Lord hear our plea and send the Holy Spirit to our Fathers whom you have entrusted your sacred church. Please bring the division to come to end and bring us all from the long exodus away from you. Pacify your church once more by your holy anointment of the rightful father that will guard your kingdom here on earth.

Forsake us not especially now at your holy place where we worship you, protect our church from the wolves that will do harm to your flocks. Rescue your church from the money changer, and from those who take away the surrender of the innocent for their own fame and glory.

I ask you all these not in my name but in the name of St Mary our interceder who is in thy kingdom. Amen!

Wesebahat L'Egziabher

Anonymous said...

Dan:
I don't think the patriarch did all those things by himsellf. If DJ doesn't try to hold everybody accountable, I am afraid we can't diagnose the chronicic illness of EOC. In my opinion the issue is not Abune Paulos. It is our beloved EOC.
Thanks

Unknown said...

Dear last anonym,
Please explain what you mean by "If DJ doesn't try to hold everybody accountable,".
DS

Anonymous said...

His Holiness Abune Theophilos, the Martyr did recieve all sorts of accusations (of this kind) before he was executed.

Anonymous said...

I wish DS and others have the moral ground before daring post such a long list of accusations on His Holiness. I always wonder when we will reflect on our own sins and problems. We always find someone and something to blame. If we think blaming others is a solution... that is like lam alegn be-semay... at least spiritually.
God bless our nation.

Anonymous said...

I think the main cause of all these problems is bebete kiristiyanua adir bayoch mebzatachew new. hodamoch. ende esist melkachewn yemiqeyayru. one of the esistoch bezarewa bete kiritian is mahebre kidusan. kemerqryos gara melke tsedeqin ke paulos gara geriman iyemeselu bete krstyanuan yamisalu. kesemonu ye mk lesan yehonw hamer metshet azegaj wode norway zelqo yiqleselesal. ene emilew enzh sewuch beadebabay yeminagerutn lemn beguada yishirutal. awudami hula. ke mestr yilq wore mawurat kemiwodut yemk memheran anu yehonew yihe berhanu yemibalew sew bewunet yehinin mesirnetachewn yimesekiral. behulet kara meblat. kehulum alehu alehu malet. gud yiwotal.

Anonymous said...

About Abune Paulos and the other Bishops: What were they doing for the last 17 years?? They were teaching us about truth and honesty but they themselves..... How can we follow what any of these fathers are saying after all these? They were preaching about the life they didn't practice at all. They should say no and have to stop before this man destroy the church structure for one and for all. Please let's inform the Bishops and fathers we know about the seriousness of the issue.

I'm happy to see strong fathers like Abne Abrham. We have to stand beside such fathers.

"yalnorubetin kirstina yemisebku abatoch nachewu weyis....?" I better not say it.

"Esme albo neger Zeysa'eno leEgziabher!

Yihuna.

cher yaseman.

Anonymous said...

As it was said many times, those who have business with MK if you have the gut to do it, go and open another blog where you can post your ideas.I believe MK is a very small organization in the EOTC. Let's us focus on the main agenda. Once we solve these we can back to clear our small differences.

zemeca said...

17. በየአህጉረ ስብከቶች የሚገኙ ገዳማት፣ አድባራትና አብያተ ክርስቱያናት እየተዘጉ ካህናትና አገልጋዮቿ በረሀብና በመተዳደሪያ እጦት እየተሰደዱ ባሉበት በአሁኑ ወቅት ፓትርያርኩ ግን ለዚህ አንዳች መፍትሔ ከመፈለግ ይልቅ ስለራሳቸው ዝናና ክብር የህዝብ ግንኙነት ሥራ እንዲሠራላቸው አሜሪካን ሃገር ለሚገኘው የሃገር ፍቅር ሬዲዮ አዘጋጅ 100‚000.00 (መቶ ሺህ ብር) እንዲሰጥ ማድረጋቸው ዕለት ዕለት የሚያስጨንቃቸው የራሳቸው ስምና ዝና መታወቅ እንጅ የቤተ ክርስቲያን ችግር መፍትሔ ማግኘቱ አለመሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡
ውሻ በበላበት ይጮኻል የንጉሴ ጩኸት ገባን

tad said...

DS and Dan:
Let us see the first accusation on Abune Paulos."...the church has been splitted in two...".Come on guys. Are you kidding me. Are you saying a physician has to treat a cancer patient only on his head? Does he not have to check if it has been spread all over his body? Are you saying Abune Paulos doesn't have hands,legs,lungs,heart,kidneys...? There were a lot of his hands,legs,kidneys,lungs....who were working day and night for his evil mission of splitting EOC tirelessly for 17yrs.
DS please stay to moderate independently so that we can pressure each of us to come to repentance. Scapegoats didn't work during Abune Theophilos' or Abune Merkorious' time. If we, the EOC members, don't learn from our past mistakes, I think there is no way we can get out of the vicious circle of patriarch change.

Anonymous said...

ጳውሎስ የመፃፉ ብርታቱ አይደለም ለክርስቶስ ለአይሁድ ሥርዓት የነበረው ቅናት የትየለሌ ነበር።የኛው ጳውሎስ ትጋቱ ብርታቱና ቅናቱ ለክርስቶስ ሳይሆን ለስሙ ብቻ ሆነና 3000 በማጥመቅ ፈንታ 3ሚሊዮን በጎችን በተነ!

ይሁና!!!

Alemu said...

Egzyoo Maheren Chrstos (12x)

"For the love of money is the root of all evil: which while some coveted after, they have erred from the faith, and pierced themselves through with many sorrows"

The financial factor takes 5/6th of the whole letter. Why are we giving that much weight to money? Didn't our Holy Church survive all the tribulations of the past 2000 years without money having any particular significance?

May the Almighty God turn our eyes away from money!

Anonymous said...

ይድረስ ለአቶ ተስፋ (ለአሰልቺው አስተያየት ሰጭ)

አቶ ስላልሁህ ቅር እንደማትሰኝ ተስፋ አደርጋለሁ። ደጀ ሰላምን መጎብኘት ከጀመርሁበት ጊዜ አንስቶ በየተነሱት ርእሶች አስተያየት ደግመህ ደግመህ ስተሰጥ አስተውላለሁ። አስተያየት መስጠቱ ባልከፋ።ግን ህመምተኛ ትመስለኛለህ።በአንተ ቤት አስተያየትህን የሚያነብብ ሁሉ የሚሰበክልህ ይመስልሃል? የተለያየ አስተያየት የሰጠሁ ይመስልሃል እንጅ ‘የሞኝ ልቅሶ መልሶ መልሶ’ የምትሰጠው ሐሳብ እኮ አንድና አንድ ነው ‘ያው እንታደስ’ አይደል የምትለው? አባ ጳውሎስ ቤተ ክርስቲያኗን በደሉ ስትባል ‘እንታደስ’ ስለ ቅኔ ትምህርት ሲነሳ ‘እንታደስ’ ጳጳሳት ተደበደቡ ስትባል ‘እንታደስ’ በእውነት እብድ ነህ። ዘጠኝ ጊዜ ዝርጠጣ ብትጽፍ ትርጉም የለውም ከአንተ ጋር ማስረጃ ማጣቀሻ መጻፉም መቅለል ነው የሚሆነው።ልምከርህ አስተያየትህ ልክ ያለው ይሁን። በመስደብ ትርፍ እንደማታገኝ እወቅ። ዘጠኝ ጊዜ አስተያየትህን በ ‘እንታደስ’ ስለደዘደዝኸው ተሰለች እንደሆን እንጅ ተከታይ አታገኝም፤አትድከም። አስተያየት ለመስጠት ከፈለግህ ርእሱን የጠበቀና ገንቢ ይሁን ስድብ ከሆነ በ ‘እንታደስ’ ስብሰባህ ብትለው ይሻላል። የያዘህን ክፉ ጋኔን ያውጣልህ።

Cheru said...

SelaM Wegenoch and Deje-Selamawyan

I just read the 23 points. May God deliver his mercy on our church and country.

Although I knew about most of the issues raised, reading them still hit me hard.

I have one question though : Why is deje-selam, or any one, use the title 'Besue Wekedus' or 'His Hollines' when addressing Aba Paulos? Is this not simply mocking such great titles?

If we know he has done so much wrong to our church and fathers, if we know he is causing so much damage to the faith and the belivers, when would it be acceptable AT THE VERY LEAST to stop calling him with this great titles???.

It is so easy to add the list of crimes he committed against the faith, the church and the country.

How long for the hypocracy??

ewnetu said...

በእውነት አባ ገብረ መድህን ይሄን ብቻ አይደለም ከዚህም 100 000 እጥፍ አድርገዋል ቢባል አምናለሁ ግን ምነው ዛሬ ሆነ የማቅ መንቃት ማቆች አይደላችሁ እንዴ ህጋዊውን ፓትርያሪክ መርቆሬዎስ ከወያኔ ጋር ተሻርካችሁ የጣላችሁትና ገ/መድህንን የሾማችሁት ምነው ዛሬ ልክ እነደማናውቅ ደርሳችሁ ተቆርቁሪ ለመምሰል የምትሯሯጡት እስተውሉ
በተዋህዶ አብራክ ውስጥ ሆናቸሁ የፈጸማችሁት በደል ለጊዜው ባይታያችሁም በይም ብትደብቁትም በተዋህዶ ልጆች ተገልጾ ይታያል ሊነጋ ሲል ይጨልማል

ከነ አባ ገ/መድህን የበለጠ
ተዋህዶን ተዋህዶአውያን መስላችሁ ምስኪኑን ህዝብ ግራ አጋብታችሁታል ግን ለተዋሀዶ የሞታላት አምላክ አይተዋትም እና ዛሬም አጠገቧ ነው ያለው እናንተው እነደ ጉም ተናችሁ ትጠፋላችሁ ለማየት ደግሞ ያብቃችሁ

እግዚአብሔር ተዋህዶን ከነ አባ ገ/መድህን አይነት ፓትርያሪክ ተብዬ ከና አባ ተከስተና አባ ቃለ ጽድቅ ወንበዴ ጳጳስ ተብዬ እነዲሁም ለተዋሀዶ ሃሰተኛ ተቆርቁሪ መሳይ ከሆነው የሴይጣን ማህብር እሱ የሞታላት ጌታ ይጠብቃት ክፏኛ የሚያሳዝን ዘመን ሆነ እንግዲህ ምን እንበል

የጌታ ፍቃድ ይሁን ብለን ዝመ እልን

ይቆየን

Anonymous said...

I want to know what this Patriarche feels. Sometimes i wonder what is there in his mind. Did he forget that God exists. Is he not able to remind God sees everything and pays him as per his acts. I have read that he do have doctorate in theology. what was he learning?. Did he really know the commandments of the Bible. What did Gragn Ahmed did beyond this.
Ebakachu niseha saygebu endaymotu Nisiha endigebu mikeruachew. Kirstianu dokltiyanos hono eko.

ሰናይ said...

ለወንድሜ ቸሩ፡

ቅዱስታቸው ከሰሩት እና እየሰሩት ካለው ወደር የሌለው ጥፋት አይደለም ቅዱስ የሚለው ስም ቀርቶ ጳውሎስ የሚለው ራሱ ላይገባቸው ይችላል። ግን ግን ይሄንን ስም የቀፀለችላቸው ቤ/ክ ናት ባልሳሳት።ስለሆነም ማዕረጋቸውን ማክበር ሰጪዋን(ቤ/ክንን) ማክበር ነው። ምንም እንኻን እሳቸው በያቀሉትም ፕትርክናው ታላቅ መሆኑን ለማጠየቅ ማዕረጉን መጠቀም ያለብን ይመስለኛል። ሰውን ማክበር ሥርዓታችንም ይመስለኛል። ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኖ አባ ... ይባሉ እስካላለን ድረስ።

ከተሳሳትኩ አርሙኝ

Anonymous said...

Truth will take time, but it comes out one Day. Okay, the blame may goes to our patriarch, what about our contribution? What I am saying have we done our share, at least have we thought him in our prayers so that the Almighty grant him the wisdom to lead the followers? or that God give us the good Shepherd?

Anonymous said...

I like the following.
You too will like it.
For sure many of you have already listened it before.
Here is it:
http://www.tewahedo.org/feleseta.html

Melkam Filseta

Cheru said...

Selam Senay

1: In my understanding Aba Paulos is an appointee of the current ethinic based regime. Chosen by the Woyane admistration to serve their political interest and extend their divide and rule tactic with in the church and amongst the clergy.

Can we say his appointment was in accordance with Serate Bete Chirstian??

2: Needless to repeat the various things he did against the interest of the church, but it is evident that those around him are not with him out of duty but rather out of fear of reprisal or out of greed.

The decision of the Kidus Synod has been disregarded by Aba Paulos time and again.

As we speak Aba Paulos is changing "Serate Bete Chirstian" to satisfy his desiers and that of his inner circle/ family followers.

Some of the changes probably include formalising the process of making the Synod powerless to pass any judgement against him.

I agree it is necessary for us to respect one another, let alone elderly clergy persons.

But this is beside the point. In continuing to give only lip service to "his hollines" we are doing more harm to him, to ourselves and the church. Ye afe shingela yehonena malet newe.

Enastewul said...

Ewnetu = Wushetu,

Why don't you tell all what you posted to Negussie of "Hager Fikir Radio". It will be intertaining for him.

Don't forget to pray, if you are an orthodox christian. Use the time to pray, you lack spirituality....use the current "Tsome Filseta".

Miihiret Yilakilih

Ere Tewu said...

Dear tad,

I have been reading your comments under different topics....your focus looks different.

If you really want to contribute your share, try to focus on the topic.

Cher Werie Yaseman

tad said...

Dear Ere Tewu:
Could you please point out?
Thanks

ewnetu said...

part1
Haymanotawi or Poleticawi Kewes


ሕመሙን የደበቀ ፈውሱን ደበቀ እንደሚባለው የችግሮቻችን መንስኤዎች በቅጡ ተለይተው መታወቃቸው ድልን የመቀዳጀት ያህል የሚፈጥርብን ደስታና ስሜት ባይፈጥሩልንም ውለው አድረው የሚያመሩን ወደዛ ሃሴት ነውና ገና ለገና መፍትሔ የሚመስሉ ግን የየዋኁን ልብ የሚበክሉ ከድጡ ወደ ማጡ የሚያንከባልሉ ለማንም የማይበጁና እርባና ቢሶች አስተያየቶችና ነጥቦችን ከመጫር፣ ጊዜያአችንን በከንቱ አጥፍተን የሌላውንም ወገን ጊዜ እንዲሁ በከንቱ ከመብላት ይልቅ ቅድስት ቤ/ያን ለዚህ ቀውስ በዳረጋትን የችግሮቻችን መንስኤዎች ቀጥተኛ በሆነ መልኩ (መንገድ) ከግላዊ አጀንዳዎችንና አስተሳስባችን ርቀን ጭብጥ ባላቸው መረጃዊ በሆነ ውይይት እንደ ባለ አእምሮ በጭዋነት መንፈስ በመጠባበቅ አንስተን መወያየቱና ለምፍትሔ መደማመጡ ዘለቄታ ያለው ሰላምና እረፍት ያመጣል የሚል እምነት አለኝ። በማስቀደም በአሁኑ ሰዓት በቅድስት ቤተ-ክርስትያናችን ለተፈጠረው ወቅታዊ መቆራቆስ የተሰማኝ ከፍተኛ ሀዘን ለመግለጽ ስወድ ይህን ጽሑፍ የማንብብ አጋጣሚ ላጋጠማችሁ በቅርብም በሩቅም ለምትገኙ የቅድስት ቤ/ያን ልጆች ከእግዚአብሔር አብ ከመድሐኒታችንም ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ምህረት ሰላምም ይሁን እላለሁ።

“በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን የተከሰተውን ወቅታዊ ችግር ኃይማኖታዊ ወይስ ፖለቲካዊ ቀውስ ነው ይላሉ?” በሚል ርዕስ የበኩሌን ለመፃፍ የተገደድኩበት ዋና ምክንያት ችግሩ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ እስከ ዛሬ ዕለት ድረስ ጉዳዩን አስመልክተው ከተለያዩ ዓይነት ሰዎች የተለያዩ ገንቢና አፍራሽ ሃሳቦችን በተለያዩ ድህረ ገጾች በማንበቤ ነገሩ አቅጣጫውን ስቶ ወደ አላስፈላጊ አቅጣጫ እያመራ እንዳለ በመረዳት “ውሃ ከምንጩ ነገር ከባለ ቤቱ ሲሆን ይጥማል” እዳሉት አበው ይህን ጽሑፍ እንደ እግዚአብሔር ሰው እንደ መንፈሳውያን ለሚያስቡና ለሚመላለሱ ለእግዚአብሔር ልጆች ለመልካም ነገር ይተጉና በሮቻቸውና ጆሮቻቸው ከጠላት አሰራር ይጠበቁ ዘንድ አዘጋጀሁት።
ለመሆኑ በቤተ-ክርስትያን መካከል ችግር ይፈጠራል ወይ … ? የብዙዎች “ኑ በአምላካችን በእግዚአብሔር ቤት
ዘልአለማዊ ሰላምና ዕረፍት አለ …” እያልን ከምንሰብካቸውና የምስራች የሆነውን ወንጌል ከምንነግራቸው በውጭ ካሉ ሰዎች የሚሰማና የሚነሳ ተገቢ ጥያቄ፣ ለምን? ሰላምን ታገኛለህ ታርፋለህ ብሎ የሚናገርና የሚሰብክ ሰው አስቀድሞ ራሱ ሰላምና ዕረፍትን የተላበሰ ሰው ሆኖ መገኘት ይጠበቅበታልና።

በቤተ-ክርስትያን መካከል ለሚፈጠረው ማንኛውም ዓይነት ችግር ቅድስት ቤተ-ክርስትያን ተጠያቂ አይደለችም በማለት ሐተታየን ጀመርኩ። በመቀጠልም የቤተ-ክርስትያን ባለቤትና መሥራች ስህተትና ህጸጽ የማያውቀው እግዚአብሔር ነው አልኩ። ስቀጥል ደግሞ ቤተ-ክርስትያን እግዚአብሔር አምላክ በአንድያና ተወዳጁ ልጁ በክርስቶስ ኢየሱስ ንጽህ ደም የመሠረታት የሰማያዊት ኢየሩሳሌም ተምሳሌት እንጂ መዘጋጃ ቤት ወይንም የቀበሌ ፍርድ ሸንጎ ክፍል አይደለችም በማለት ለዛሬ ያዘጋጀኋትን ጦማር በመግብያዬ አሰፈርኩ።
በቤተ-ከርስትያን መካከል ለሚፈጠረው ትልቅም ትንሽም ችግር ተጠያቂው እግዚአብሔር ሳይሆን በአደራ
በተሾሙት ገለሰቦች ሥጋዊ ፍቃድና ምኞት ተከትሎ የሚመጣውን ራስን የአለመግዛት ውጤት ነው የሚል ጽኑ መጽሐፍ ቅዱሳዊ እምነቴ ነው።

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በእምነት ለወለደው ለመንፈሳዊ ልጁ ለጢሞቲዎስ በጻፈው 2ኛ መልዕክቱ ምዕራፍ ስድስት ከቁጥር አራት ጀምሮ እንደጻፈው በቤተ-ክርስትያን መካከል ችግር ሊፈጠር እንደሚችል ሳይደብቅ ችግር ሊፈጠር እንደሚችል በመግለጽ የችግር ፈጣሪዎች ማንንነትና መገለጫ ባህሪ (ስብእና) አክሎም አስፍረዋል። ሙሉ የቃሉ ይዘት እንዲህ ይላል “ከእነዚህም ቅንዓትንና ክርክርን ስድብም ክፉ አሳብም እርስ በርስ መናደድም ይወጣሉ አእምሮአቸውም በጠፋባቸው እውነትንም በተቀሙ እግዚአብሔርን መምሰል ማትረፍያ የሚሆን በሚመስላቸው ሰዎች ይገኛሉ እንደነዚህ ካሉ ራቅ።” እንዲል። በዋናነት ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለጢሞቲዎስ ለማሳየት የፈለገው ከዚህ ከተጻፈው አምላካዊ ቃል በግልጽ ለመረዳት እንደሚቻለው በቤተ-ክርስትያን ለሚሆነው (ለሚፈጠረው) ኢ-ክርስቲያናዊ የሆኑ ተግባሮች ማለት እርስ በርስ መናቆርና ማባላት የመሰሉ አስቀያሚ ሰይጣናዊ ድርጊቶች ከእግዚአብሔር ልጆች የሚጠበቅ የህይወት ፍሬ ሳይሆን እግዚአብሔር አብ ያልተከላቸው በጊዜው ደግሞ የሚነቅላቸው የተጠሩትን ሰላምና ዕረፍት ብሎም ትርፋማ ህይወት አይተው ሳይጠሩ ተድበስብሰው በቀላዋጭነት የሚኖሩ በመስኮት የተቀመጡ በተከፈለ ልብ የሚመላለሱ በልባቸው በሸፈቱ ምናምንቴዎች የሚፈጠር ነው በማለት ጢሞቲዎስን ሲያረጋጋው እንመለከታለን። ዛሬ ተፈጠረ የሚባለውን ችግር አንስተን ስናወራ አብሮ ደግሞ ስማቸው ጎልቶ የሚታወቀው ያሉ የቤተ-ክርስትያን መሪዎች ህይወት ማንነት (ስብዕና) በዚህ አምላካዊ ቃል መመርመሩ ድፍረት አይመስለኝም። የእግዚአብሔር ቤትንና የእግዚአብሔር ህዝብ እያወኩና እያበጣበጡ ያሉ ግለሰቦች እውነት ሁሉን የሚያውቅ ሰማይ ዝፋኑ ምደር የእግሩ መረገጫ የሆነ የእስራኤል ቅዱስ እግዚአብሔር ህዝቡን ይመሩና ያስተዳድሩ ዘንድ የጠራቸው ካህናት ናቸው ወይስ ሰዎች ለፖለቲካ ጥቅማቸው የቀብዋቸው ወታደሮች? አይመስለኝም! እግዚ አብሔር በመንገድ ሁሉ ጻድቅ ነው። ደግሞም በዘመናት ሁሉ የተበተነውን ለመሰብሰብ የወደቀውን ለማንሳት የተሰበረውን ለመጠገን ተስፋ ያጣችውን ነፍስ በአዲስ ጎዳና በህይወት ለማኖር አገልጋዮችን ላከ እንጂ ህዝቡንና ቤቱን ለማበጣበጥና ለማወክ ሰዎችን አልጠራም አገልጋዮቸን አላከም።

ewnetu said...

part2
ሐዋርያው ያዕቆብ በመልዕክቱ ምዕራፍ አራት ቁጥር አንድ ላይ ደግሞ እንዲህ ይላል “በእናንተ ዘንድ ጦርና ጠብ ከወዴት ይመጣሉ? በብልቶቻችሁ ውስጥ ከሚዋጉ ከእነዚህ ከምኞታችሁ አይደለምን?” እንዲል እንደ ተልባ መንጣጣቱ አጉል ጥብቅና መቆሙ መነታረኩ ለጊዜው ይቅርና ለዚህ ጥያቄ (ለሐዋርያው ያዕቆብ ጥያቄ) የሚኖርዎት ምላሽ ምን ይሆን? በምንስ ለማመካኘት ይሞክሩ ይሆን? ማስተባበያ ቃልዎስ ምን ይሆን? አንድ የሚሉት ቃል ይኖርዎት ይሆን? በቤተ- ክርስቲያን ለሚፈጠረው ችግር ከዚህ የተለየ ምክንያት ይኖሮታል?
የተወደዳችሁ የቅድስት ቤተ-ክርስትያን ልጆች ሰላም ወዳዶች ምእመናን የምናመልከው አምላክ እግዚአብሔር
አይዘበትብትም! ተብሎ እንደ ተጻፈ እንደ ሞኝነት በሚያስቆጥር ቃል ማንም አያታልላችሁ! ለማለት እወዳለሁ ሰው ሰለ እግዚአብሔር ቤት እና ስለ እግዚአብሔር ህዝብ ከእግዚአብሔር በላይ ሊያስብ አይችልም። የሚቃጣው የተገኘ እንደሆነም ውሸት ነው።
ሰዎች ግላዊና ሥጋዊ ግጭቶቻቸው ኃይማኖታዊ ግጭት ለማስመሰል ፖለቲካዊ ቅርያናቸው ኃይማኖታዊ ቅርጽ ለማስያዝ በሚያደርጉት ፍልምያ ግብግብ ለምን ደምህን ደመ ከልብ ታደርጋለህ? አንዳንዶች የተመኙትን አግኝተዋል ከተሸሙት ጥቂት ጊዜያቸው በመሆኑ ምኞታቸው በየመገናኛ ብዙሃን ስማቸውንና ፎቶ ግራፋቸው ማስተዋወቅ ነበርና እንዳሰቡት ተከናወነላቸው ተሳካላቸው ሌላ የሚታወቁበት እወቀትና ጥበብ የላቸውማ! ወዳጄ ጊዜዎንና ጉልበትዎን መስዋዕት አድርገው የገጠሙት ሙግትና እያፋፋሙት ያለውን እሳት እውነት በእውነተኛ መንፋሳዊ ቅናት የቤተ-ክርስትያን ጉዳይ ግድ ብሎት ነው ወይስ በሥራ ብዛት የተወጠረውን አእምሮ አልያም በቤተሰብ ናፍቆት በሃሳብ የተያዘውን ህሊና አጋጣሚውን በመጠቀም ለመዝናንት ያህል ነው? በተለያዩ ድህረ ገጾች ከ ይመለከተናል ባዮች ቁጥራቸው የማይናቅ ወገኖች መሰል አስተያዮችን ማየት ስለቻኩ ነው የተጠቀምኩት ቋንቋ ቢከብድም። ታድያ ግድ የሚልዎት የቤተክርስቲያን ጉዳይ ከሆነ አንዱን በመደገፍ ሌላውን ከማጥላላትና ከመወረፍ ከመንፈሳውያን ሰዎች የማይጠበቁ ጽያፍ ቃላቶችን አለቦታቸውን በመጠቀም ለቤዛ ቀን የታተመውን በውስጣችን የሚኖረው የእግዚአብሔር መንፈስ ከማሳዘን ይልቅ ሰላም እንደሚሻና እንደተጠማ የእግዚአብሔር ሰዎች በአንድ ድምጽ የችግሩ መንስኤ ለማወቅ መጠየቅ በተገባ ነበር የዓለማውያን መዝናኛ ቃላቶችን እያነበብን ጠፍተን ለማጥፋት ከምንተጋ።

የእግዚአብሔር ሰዎች ለዓለም መልዕክት ሰጪዎች እንጂ ከዓለም ተቀብለው መንፈሳቸውን የሚረብሹ ወንድሞቻቸውን የሚያናጉ ቤተቻቸውንም የሚያውኩ አይደሉም።
እውነት ከማይጠፋ ዘር ከተወለድክ ከራስህ አልፈህ ስለሌላው የምታውቀው በእግዚአብሔር መንፈስ እንጂ በከበሮ መቺዎች ልሳን አይደለም። ራስህን መርምር ተገቢ ነው ሰለምትናገረውና ሰለምትጽፈው ነገር ተጠያቂ ነህና! መዓቱም ለልጅ ልጅህ ነው። ቀልድ አይደደልም ሽንጥህን ገትረህ እየተከራከርክበት ያለኸው ርእስ የእግዚአብሔር ስም አንስተህ ነው ስለ እግዚአብሔር ቤት ነው እየተከራከርክ ያለኸው። የክርስትና አምላክ ስንፍናን የሚጠላ አምላክ እንጂ ስንፍናን የሚያበረታታ አምላክ አይደለም። ከስንፍና የተንሳ ደግሞ በራስህ ላይ ፍርድን ታከማቻለህ እንጂ ምህረትን አታገኝም። ማቴ 7፤21 እግዚአብሔር ፈታሔ ነው ይሉኝታ ይዞት የሚቀለብሰው ፍርድ አይኖርም። ይህን ማወቃችን ከዛሬ ጀምሮ በእግዚአብሔር ስም የምንሰራቸውን የድፍረት ኃጢአት የአመጻ ስራችን ገደብ እናበጀለታለን። ብርሃን ከጨለማ ህብረት እንደሌለው ሁሉ እግዚአብሔር ከሰዎች ዓመጽ ጋር ምንም ክፍል የለውም። በቤተ-ክርስትያን መካከል ያለ እውቀት የምናደርጋቸው ማናቸውም ዓይነት ተሳትፎዎች እግዚአብሔር የለበትም። ቅናቱ ካለን እውቀቱ ያላቸውን ሰዎች ከመንቀፍ በመታቀብ እውቀቱ ካላቸው ሰዎች ተጠቃሚዎች ለመሆን መንፈሳችንን ማዘጋጀት ልባችንን በቅንነት መስጠት ይጠበቅብናል። እያደርግኩት ያለሁት ተግባር እየሰራሁት ያለሁት ስራ እግዚአብሔር የሚከብርብት ቤተ-ክርስትያን የምትጠቀምበት የእግዚአብሔር ህዝብ የምያርፍበት የሚሳርፍ ነው ወይ? በማለት ራሳችንን መመርመር ይኖርብናል ራሳችንን በእግዚአብሔርና በእግዚአብሔር ሰዎች ትዕዝብት ከመጣላችን በፊት።

ewnetu said...

part3
የምንሰራው ሥራ ሁሉ እግዚአብሔር ደስ ለማሰኘት አይደል? ዋጋችንን ከእግዚአብሔር ለመቀበል አይደለም? ታድያ ስራችን ከእግዚአብሔር የሚያራርቀን ሆኖ ከተገኘስ? የምንሰራው ሥራ ለማን ነው? መልስ የሚሻ ጥያቄ ነው። ሰው አይደርስብኝም በማለት የብዕር ስም በመጠቀም ብትጽፍም አድራሻህ ከቶ ሁሉን ከሚያውቅ ከልዑል እግዚአብሔር ህልውና የተደበቀ አይደለም። የመዘንጠል አመል ያለው የልብን የሚያደርሱ ብዙ መወያያ ርዕስ ያላቸው መድረኮች አሉ እዛው በመገኘት እስኪወጣሎት ድረስ መፏነን ይችላሉ ከዘላለም ፍርድ ለማምለጥ ባይችሉም በሥጋ ዘመንዎ እንደሆነ እግዚአብሔር በምህረቱ ብዛት ያኖሮታል።
አሁንም በድጋሚ ላሰምርበት የምፈልገው ነጥብ ቢኖር በበል ልበልህ እና በቃላት ብዛት የሚመጣ ለውጥ እንደሌለ
በመረዳት እያንዳንዱ የቤተክርስትያን ልጅ የችግሩን መንስኤ ራሱን ችሎ ከማናቸውም ተጽእኖዎች ራሱን በማንጻት ለማወቅ ጥረት ቢደረግ ድምጹን በአንድነት ቢያሰማ የተሻለ ነው እላለሁ ለምን? ዘመኑ ሰዉ እውነቱ ሲነገረው ስላልድረሰበት እውነት ግራ ቀኙን አይቶ በማስተዋል ከመናገር ይልቅ የተነገረውን ሃሳብ ውሸት ሰውየውን ወንጀለኛ ማድረግ ስለ ሚቀናው ነው።

ለዚህም ነው እላለሁ ብዙ የቤተ-ክርስትያናችን ሊቃውንት መምህራን ደቀ-መዛሙርት የእግዚአብሔር ሰዎች ብዙ ከማለት የተቆጠቡ። ማን በሰነፍ በትርና ምላስ መገረፉ ይወዳል ብላችሁ ነው? አዎ! ልባችሁን ስታሰፍሉን የምንላችሁ ነገር ይኖራል ጌታ ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ አበክሮ ካስተማራቸው ትምህርቶች መካከል አንዱ ዘራቸውን አለ ቦታው አለ ጊዜውና አለ አግባብ እንዳይዘሩ ጥንቃቄ ማድርግ እንደሚገባቸው ነው። ራሱ ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ያለው እንዲህ ነው “በጎቼ ያውቁኛል እኔም አውቃቸዋለሁ ድምጼንም ይሰማሉ ይከተሉምኛል።” እንዲል ክፍል አንድ ጽሑፌን ለማገባደድ ያህል ብከብድባችሁም በቅድስት ቤተ-ክርስትያናችን የተፈጠረው ችግር ምንም ዓይነት አስተምህሮአዊም ሆነ አስተዳደራዊ ችግር አለመሆናቸው እና ችግሩም ለውስጥ አዋቂዎች አዲስና አንግዳ እንዳልሆነ ለመንፈሳውያን የቤተ-ክርስትያን ልጆች ለመግለጽ እወዳለሁ። በክፍል ሁለት በስፋት ከምንመለከታቸው ዝርዝር ኃሳቦች በከፊል ለማስተዋወቅ ያህል ቀደም ብዬ ለመግለጽ እንደሞከርኩት በ2ኛ ጢሞቲዎስ 6፤4 መሰረት  የአድዋ ተወላጅ “አባ” ጳውሎስም ሆኑ በእንጀራ ስማቸው የሚታወቁ የሽሬ ተወላጁ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት “አባ” ተከስተ በመጀመሪያ እነዚህ ግለ ሰቦች እውነት እግዚአብሔር የጠራቸው ካህናት ናቸው ወይስ የፖለቲካ ሰዎች ለፖለቲካ ጥቅማቸው የሾምዋቸው ወታደሮች ናቸው?
 ቀጥሎ ደግሞ ዘመናት ያስቆጠረ የተብላላ ጊዜንና አጋጣሚን የሚጠብቅ በፖለቲካ መሪዎች በተለይ በአድዋ ተወላጆችና እና በሽሬ ታጋዮች መካከል ያለውን ያለመግባት የመቃቃር መንፈስም መዘንጋቱ የዋህነት ይመስለኛል ይህንም በስፋት ተካተዋል።
 ትናንት ብብዙ ምልጃና ፖለቲካዊ አጋጣሚ የተሾመ “አባ” ተከስተ ለምን በ “አባ” ጳውሎስ ላይ ሊያምጽ ቻለ? ለመሆኑ “አባ” ተከስተ ራሱን ችሎ የሚንቀሳቀስ ሙሉ ሰው ነው ወይ? ካሜራ አዳኙ “አባ” ተከስተ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀ-መዛሙርት የአስተዳደር ችግር አለብን በማለት ጥያቄቸውን ሲያቀርቡ ለምን መፍትሔ አልሰጠም? ዛሬ ነው ረዳት ፓትሪያሪክ መሆኑ የነቃ ወይስ ለተሾሙበት ዓላማ የሚቆሙበት ጊዜና ሰዓት በመድረሱ ነው?
 “በአባ” ተከስተ እና አብሮአቸው ከተሾሙት ሊሎች ሁለት “መነኮሳት” መሾም ያልተስማሙ የትግራይ ሊቀ ጳጳስ አቡነ መርሃ ክርስቶስ ለምን እነዚህ ሰዎች ከተሾሙ ቆቤን አነሳለሁ እስከ ማለት ደረሱ? አቡነ መርሃ ክርስቶስ የ
“አባ” ተከስተ ሹመትን የተቃወሙበት ዋና ምክንያታቸው ምን ነበር? በማንና በምንስ ነጥብ አቡነ መርሀ ክርስቶስ ከጽኑ አቋማቸው ሊመለሱ ቻሉ? ይህም በተጨባጭ መርጃ ተዘጋጅተዋል፣
 “አባ” ተከስተ እውነት ተቆርቋሪ፣ ቤተ-ክርስቲያን የማስተዳደር ችሎታና መፍትሔ የማምጣት አቅም ቢኖሮው ራሱን ችሎ የቆመ ዓይነት ሰው ቢሆን ኑሮ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀ-መዛሙርት የአስተዳደራዊ ችግር ጥያቄ ሲያቀርቡ ጥያቄውን ወደጎን በመተው በምርጫ ባልተሳካላቸው በቅንጅት አባላት ቤተ-ክርስትያንን ለመረበሽ የተመከረ ምክር ነው ሲሉ የተደመጡ ለምንድን ነበር?

 ነፍሳት እንደ ቅጠል ሲረግፉ ደማቸው ሳይደርቅ (የጅማ ነዋሪዎች) ወንድም እህቶቻችን የቀብር ሥነ-ሥርዓት ሳይፈጸም ከገዢው ፓርቲ ጎን በሞቆም “እስላምና ክርስትያን አንድ ነው በአከባቢው ምንም ዓይነት ኃይማኖታዊ ችግር አልተፈጠረም” በማለት የተሰጠውን ወረቀት ያነበበና የተሾመበትን አደራ የፈጸመ ነፍሰ ገዳይ አይደለም ወይ “አባ” ተከስተ ማለት? “ናበይ ግመል ሰሪቅካ ጉንብሕ ጉንብሕ!”

ewnetu said...

part4
 የፈረንጁ ቀይ አፈር ረግጦ በመምጣቱ ብቻ የተሾመ “አባ” ተከስተ የመልካም አስተዳደር ታጋይ ከሆነ በአዲስአበባ ሀገረ ስብከት የጋዜጣ ክፍል ዋና አዘጋጅ ሆነው ያገለግሉ የነበሩ ቅድስት ቤተ-ክርስትያናችን ካፈራቻቸው ወጣቶች ሊቃውንት መምህራን አንደበተ ርቱዕና ባለ ቅኔ መ/ም ተመስገን ያለአንዳች ማስጠንቀቅያ በአዘጋጁነት በሚመሩ ጋዜጣ ርዕሰ አንቀጽ የሰፈረው የአዘጋጁ እምነትና የቤተክርስትያን ጥቅም ማዕከል ያደረገ ጽሑፍ ለወያኔ መንግሥት የማይመች ሆኖ በመገኘቱ ሀገር ሰላም ነው ብለው የቢሮ ሰዓታቸውን ጠብቀው በሚገቡበት ሰዓት ከስራ ገበታቸው ሲታጉዱ ለአላስፈላጊ የህይወት ዋስትና የሌለው ህይወት ሲዳረጉ “አባ” ተከስተ ምን ይጠብቅ ነበር? ይሄ ነው የመልካም አስተዳደር መርህ?

 “ጠርጥር በገንፎ ውስጥ አይታጣም ስንጥር።” ለምን? በመንፈሳዊ ዓለም ውስጥ “የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው”የሚል መርህ ቦታ የለውምና። ምንም እንኳ “አባ” ጳውሎስ ከተጣለባቸው ሐላፊነት አንጻር በሥራቸው ምንደኛ ሆነው በመገኘታቸው ተቋውሞአችን ብናሰማ “አባ” ጳውሎስን የተቋወመ ሁሉ ግን የቤተ-ክርስትያን ወዳጅ ነው ማለት አይደለም። ተቋዋሚ አካል ወይም ግለሰብ የተቋውሞው ነጥብ ምንድ ነው? ለመሆኑ እርስዎ አባ ጳውሎስን የሚቃወሙበትን ነጥብ ምንድ ነው በተጨባጭ ለማስቀመጥ ይችላሉ? እንግድያውስ አስቀድመው ነጥቦትን በማስታወሻ ደብተርዎን ለማስፈር ይሞክሩ በመቀጠል ደግሞ “አባ” ጳውሎስን ከተቃወሙበት ነጥብ የጸዳ ነው የሚሉት ግለሰብ ወይንም ደግሞ ማንኛውም ዓይነት ድርጅት በ”አባ” ጳውሎስ ላይ ያሰማውን (የሚያሰማውን) የተቃውሞ ነጥብን በተመሳሳይ መልኩ በማስታውሻ ደብተርዎን ለማስፈር ይሞክሩ ይህን ካደረጉ በእውነት ድምጽዎንና ልፋትዎን አንድ ቀን ዋጋ ይኖረዋል። ይህ ሁሉ ልፋትዎ ግን በስሜት በስሚ ስሚና በአጉል ድፍረት የሆነ እንደሆነ ግን ለመገንባት ያመቻቹትን ለማፍረስ ያዘጋጁትን እንደ ሆነ አይዘንጉ። የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት “አባ” ተከስተ “አባ” ጳውሎስን በመቃወማቸው ብቻ በምንም ዓይነት መልኩ አባ ተከስተን የምንደግፍበት ምንም ዓይነት ተጨባጭና አሳማኝ ነጥብ የለንም።

“ሌባ ሲሰርቅ ይስማማል ሲካፈል ይጣላል” እንዳሉት ነው ቁምነገሩ። በተንኮልና በክፋት ተረግዘው በአመጻ የተወለዱ የአጋንንት መነሃርያ የሰይጣን ማህበር “የማህበረ ቅዱሳን” ድርሻም መዘንጋት የለብንም መቼም ሐበሾች ስንባል መርዝ ይገድላል እየተባልን እንኳ ካልቀመስኩት ማለት ነው የሚቀናን ይሁን እና ጓዳችን ካልገባ በቀር ጥፋቱና ኃጢአቱ አልታይ ያለን የሰይጣን ማህበር ከግድግዳ የመላተም ያህል እንዳይከደው ትናንት
የውጪውን ለማዳከም በሀገር ውስጥ ከሚጋኘውን ሲኖዶስ በመጣበቅ ከእናንተ ጋር ነን በማለት በውጭ የሚገኙትን አባቶች ስምና ዝና በማጉደፍ እፎይታ ተሰምቶት ሲያበቃ ዛሬ ደግሞ እንደገና ጉልበቱን አድሶ ከላይ የተመለከትናቸውን አበይት ነጥቦችን ሊሎች እንደ መግቢያ ቀዳዳ በመጠቀም በአባቶች መካከል የሃሳብ መለያየት በማምጣት ሊዚህ ዳርጎናል የተወድዳችሁ የቅድስት ቤተ-ክርስትያን ልጆች እነዚህንና ሌሎች አንኳር አንኳር ነጥቦች ይዤ ልቦናችሁን ያሰፋችሁልኝ ያህል በድጋሜ መፍትሔን የሚጠቁሙ ሃሳቦችን ይዜ የመጨረሻ በሆነው የክፍል ሁለት ጽሑፌን እስክንገናኝ ድረስ የእግዚአብሔር ሰላም ከሁላችን ጋር ይሆን ዘንድ የዘወትር ጸሎቴ ነው።
የእስራኤል ቅዱስ እግዚአብሔር ሀገራችንና ቤተ-ክርስትያናችን ይጠብቅ! ጊዜና ዕድል ግን ሁሉን ያገናኛል!__

Ewntu
በጣም ታላቅ ጽሁፍ ነው እኔን በጣም አስተምሮኛል አባዝታችሁ ለሰው ስጡት

ይቆየን

Anonymous said...

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን።

ታስቦበት ተዘጋጅቶ በዚህ ለሲኖዶስ ጉባዔ ሊቀርብ በነበረው ጽሑፍ ላይ በፓትርያርኩ ላይ ከርትዕት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ጋር በተያያዘ በአለቃ አያሌውና በሌሎችም እውነተኛ አባቶች የተጠቀሱ ችግሮች፤ በባሕታዊው ላይ የተካሄደው ግድያ፤ በእርሳቸው ዘመን በጅማና በኢሉባቡር ክርስቲያኖች ላይ በገጀራና በጦር የተካሄደው ጭፍጨፋ አቤት ሳይባልበትና ማንም በእውነተኛ ሕግ ፊት ተጠያቂ ሳይሆን የታለፈበት ሁኔታ፤ እርሳቸውና ሌሎችም ብዙሃን ደጋፊና ተቃዋሚ ጳጳሳት በሲኖዶሱ መንፈሳዊ ስልጣን በነበሩበት ዘመን የቤተክርስቲያን ቦታ ሳይቀር እየተነጠቀ የተስፋፉት መስጊዶችና ከዚያ ጋር ተያይዞ በቤተክርስቲያን ላይ የተጠናከረው የስነልቦና ጥቃት ያለመጠቀሱ ተገቢ አይደለም። በሪፖርቱ በብዛት ከተጠቀሱት የሙስናና የዘመድ ስራ በበለጠ ሲኖዶሱን እጅግ ሊያሳስበው የሚገባውና ቤተክርስቲያንን ዛሬም ሆነ ወደፊት አብዝቶ የሚጎዳትና ሕልውናዋንም የሚፈታተነው መንፈሳዊው ነገር ነው። የፓትርያርኩን ስራ ተቃዋሚወችም ሆኑ ደጋፊ ጳጳሳት ለተሰራው ስራ ከዚህ ቀደም በዚሁ በደጀሰላም እንደተዘገበው “ቤተክርስቲያንን በመቅበር” ብቻ ሳይሆን ከፓትርያርኩ ጋራ “በመግደሉም” እንደነበሩበት ራሳቸውን ጨምረው ፍጹም በመክሰስና አሁንም መንግስትን ያስቀይማል ብለው የሰጉበትን እውነት በመተው ሳይሆን እውነቱን በማስረገጥ በጽናት ከቆሙ ቢዘገይም ውጤቱ ያማረ ይሆናል (በሌሎች ጉዳዮች ተግባብቶ መስራቱ እንደተጠበቀ ሆኖ እምነትን በሚመለከት የመንግስት ፖሊሲና የቤተክርስቲያን ተልዕኮ ለየቅል መሆኑ የተረዳ ነገር ነው)። እነሱም ለእውነቱ ብቻ በመቆም የእውነትን ገድል በመጋደል የቀደሙትን እውነተኛ አባቶች ስራ በመድገም ከእውነት ጋር ብቻ ደስ የሚለውንና በባሕሪው ፍጹም ቅዱስ የሆነውን እግዚአብሔርን ደስ ያሰኙበታል፤ ዋጋ ያገኙበታል፤ ለቤተክርስቲያንና በስሯ ለተጠለሉት ልጆችዋም ኩራት ይሆናሉ። ራሳቸውን ከጠፋው ጥፋትና ከተፈጸመው በደል ንጹሕ በማድረግና ከእውነቱ በመሸሽ በ”ዲፐሎማሲው” መንገድ ከቀጠሉበት እንደሚታማው የተጀመረው ተቃውሞ ሌላ “ባለጊዜ ጳጳስ” ካነሳሳውና ምቹ ጊዜ ጠብቆ ከተቀነባበረ ሴራ የማይለይ ይሆናል። ይህ ደግሞ አሁን ቤተክርስቲያናችን ላለችበት ችግር የሚሆን እውነተኛ መፍትሄ አያመጣም። ምዕመናንም የአሁኑ ካሳለፍነው ጊዜ አይበልጥምና በግብታዊነት ሳይሆን በትዕግስትና በመንፈሳዊነት ቆም ብለን በማስተዋል ለእውነተኛ፤ ዘላቂና የማያዳግም መፍትሔ ብንተጋና አባቶችንም በዚሁ አቅጣጫ ብናበረታታ በውጤቱ እጅግ ተጠቃሚዎች እንሆናለን የሚል እምነት በበዙዎች ዘንድ አለ። አለባብሰን ብናርስ ጉልቻ መቀያየር ይሆንብንንና በአረም መመለስ ይመጣል። በመጀመሪያ እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት ያስፈልጋል። እውነተኞቹ አባቶችም ሆኑ ምዕመናን ለእውነት የሚቆሙበት ወርቃማ ጊዜ አግኝተዋል። ይህን ዕድል ሊያልፉት አይገባም። እውነቱ ደግሞ አባቶችም ምዕመናንም ከተነሱበት ምክንያት መጀመር አለበት።
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፤ ለወለደችውም ድንግል። አሜን።
በእምነት

Anonymous said...

ጥንተ ጠላታችን ዲያብሎስ ዛሬ በሃይማኖታችን ላይ ጥላቻን መለያየትን ለመፍጠር ይታገላና እየተሯሯጠ ነው። በመጀመሪያው በመላእክት ጉባኤ ውስጥ መለያትን ፈጠረው ሰይጣን አሁን በመንፈሳዊያን አባቶችና በህዝበ ክርስቲያኑ መካከል ጥልን ክርክር እንድያደረግ ወሬዎችን እውንት ያልሆውን እውነት እያስመሰል በማቅርብ እምነታችንን በማቃለል ላይ ይገኛል። ዮሐ 8፡44 እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ፤ ሐሰትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል። የእግዚአብሔር ቅዱስ ቃል የሚያስተምረን ፍቅርን ከመላያየት ወደ አንድነትና ወደ ቅዱስ መስቀሉ እንድንቀርብ ያስተምረናል። አምላካችንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ በነበረበት ወቅትም ያ ጥንተ ጠላታችን ሰይጣን በደቀ መዛሙርቱ መካከል በመግባት በይሁዳ አድሮ ጌታችን እንድያዝና እንድገደል ያደረገው ክፉ መንፈስ አሁንም በኦርቶዶክስ ሃይማኖት ላይ አንደበቱን በታላቅ ጩከትና ቁጣ አፉን ከፍቷል። ራይ 13፤6 ስለዚህ የክርስቶ ወገኖች ፖለትካን ከሐይማኖት ጋር ለማቆራኘት የሚደረገው ጥረት የእግዚአብሔርን መንግሥት የማያዋርስ ስለሆነ ወደ ፈጣሪያችን ማልቀስ መለመን ይገባናል እንጅ ለሰይጣን መንፈስ በር መክፈት አያስፈልግም። እግዚአብሔር እጅግ ከሚጠላቸው ነገሮች ውስጥ በወንድምሟሟቾች መካከል መልያየትን የሚፈጥር ነው ምሳሌ 6፡19። እባካችሁ የዘመኑ ፖለትከኞች እጃችሁን ከሐይማኖታችን ላይ አንሱ ይልቁንም ለሀገራችን የሚበጀው ወደ እግዚአብሔር በአንድነት ሆነ በጋር ጥላቻ በሌለበት መንፈስ መጸለይ ያስፈልገናል።
በሚቀይጥለው እስክንገናኝ ቅዱሱ እግዚአብሔር ሐይማኖችንን ሀገራችን መላው ህዝባቸን መለያየት መለለበት ቅዱስ መንፈሱ ይጠብቅልን። አሜን

wolde sadike

Anonymous said...

ለምን በመንፈሳዊያን አባቶች ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ ይካሄዳ?
ይህ አካሄድ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት በለሎች እምነት ዘንድ ለማስነቀፍ የሚደረገው ጉዞ መልካም አይደለም። በዓለማችን ሆነ በሀገራችን ብዙ የሐይማኖት ድርጅቶች ይገኛሉ። ነገር ግን ለኢትዮጵያ ሕዝብ የቆሙ መስለው እምናችን ለማዳከምና ሕዝበ ክርስቲያኑንም ግራ በማጋባት ለሌሎች እምነት ድርጅቶች ሰላባ እንድሆኑ የሚካሄድ ስለሆን እያንዳንዱ ክርስቲያን በክርስቶስ የሚያምን ሁሉ ከእንድህ ዓይነቱ ክፉ መንፈስ ድርግቶች በመቃወም ከሐይማኖታችን ላይ እጃቸውን እንዲያነሱ ልመክራቸው ይገባናል። እኔ እንደወደድኳችሁ እርስ በርሳችሁ ትዋዱ ዘንድ ትዕዛዜ ይህች ናት። ዮሐ 15፡12
የቀደመው አባታችን ከገነት የተባረረው የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ በማፍረሱ ነው አትብላ የተባለውን በመብላት አፈረሰው። ታዲያ ለምን አዳምን እንወቅሰዋለን እኛስ ዛሬ ትዕዛዙን በማፍረስ ላይ እንገኛለንና። አምላካችን ተዋደዱ ብሎ አስተምሮን ሳለ
ሰይጣን ደግሞ በማስመሰል ተለያዮ እያለ ነው። ወገኖቼ የሚንከተለው ማንን ነው?
እግዚአብሔርን ወይስ ዲያብሎስን? ይህ ሁሉ ዘመቻ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሐይማኖትን ለማጥፋት የተጀመረው ሙከራ በመጀመሪያ ከላይ አባቶች በመከፋፈል በመቀጠልም ሕዝበ ክርስቲያኑን በመጨረሻም የቤተ ክርስቲያን ደጆችን ለመዝጋት የሚደረግ ጉዞ ስለሆነ ከአሁኑ መቆም አለበተ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ።
ወልደ ፃዲቅ

Anonymous said...

Hi....ALL
አቡነ ጳውሎስ ዛሬ ደግሞ ይባስ ብለው ቤተ ክርስቲያን በር ላይ በስማቸው የተሰራ ጣኦት አቁመውላቹሐል !!ጉድ በሉ!!ጉድ..ጉድ...
የናንተው በቀለ
ሐምሌ.15/2002.

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)