August 8, 2009

የፓትርያርኩ ረዳት አባ ዕንቁ ባሕርይ በዋስ ተፈቱ

(ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 8/2009)
አባ ዕንቁ ባሕርይ የተባሉት የፓትርያርኩ ረዳት (አቡነ ቀሲስ) በዋስ መለቀቃቸው ታወቀ።

አቡነ ቀሲሱ ባለፈው ሳምንት ታስረው እንደነበር መዘገባችን ይታወቃል። የ14 ቀን ቀነ ቀጠሮ ተጠይቆባቸው የነበሩት አባ ዕንቁ ባሕርይ ከ3 ቀን ላላነሰ ጊዜ መታሰራቸው ሲታወቅ የተፈቱበትን እርግጠኛ ቀን ማወቅ አልቻልንም። ትናንት በፓትርያርኩ ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት የታዩት አባ ዕንቁ ባሕርይ ለእስር የተዳረጉበት ምክንያት በቤተ ክህነቱ የአባቶች ቤት ሰበራ ወንጀል መሆኑ ይታወቃል።

የቤተ ክህነት ግቢ የጥበቃ ሃላፊ አቶ ብርሃኔ ከአባ ዕንቁ ባሕርይ ትዕዛዝ ተቀብለው ሁለት መኪና ሰዎችን በድብቅ ማስገባታቸውን ካመኑ በሁዋላ የወንጀሉ ምርመራ ወደ እርሳቸው እንደመራ ታውቋል።
ፖሊስ የነገሩን ጭራ መያዙን ብዙዎች ያመኑ ሲሆን “ከዚህ በሁዋላ የሚቀረው ነገር ጀሌውን ብቻ ልያዝ ወይስ ዋነኛውን የወንጀሉን ባለቤት?” የሚል ጥያቄ ብቻ እንደሆነ አስተያየት ሰጪዎች ይገልጻሉ።
የማፊያው ቡድን አቀናባሪና “ያልተሾመች ጳጳስ” የሚባሉት ወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ ወንጀሉ በተፈጸመበት ሌሊት በጊቢው ውስጥ እንደነበሩ ውስጥ አዋቂዎች ይናገራሉ። “የነገሩን በዕቅዱ መሠረት መከናወን ስትመለከት ነበር” ሲሉም ይተቻሉ።
Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)