August 26, 2009

አቡነ ሳሙኤል በቤተ ክህነቱ ጉዳይ “የተወሰነ የመንግሥት ኃይል ጣልቃ መግባቱን” ወቀሱ

(ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 26/2009)፦ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል በቅዱስ ሲኖዶስና በቅዱስ ፓትርያርኩ መካከል በተነሣውና አሁን ለጊዜው በበረደው እሰጥ አገባ የተወሰነ የመንግሥት ኃይል ጣልቃ መግባቱን በመግለጽ ድርጊቱን መኮነናቸው ተሰማ።

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ፓትርያርኩ ረዳት የነበሩትና በፓትርያርኩ እግድ ተጥሎባቸው ቤታቸው ዘግተው የተቀመጡት ሊቀ ጳጳሱ ባለፈው ሳምንት ድምጻቸውን ከነጋድራስ ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ባሰሙበት ወቅት እንደተናገሩት መንግሥት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አልገባም የሚል ፖሊሲ ቢኖረውም ከመንግሥቱ ወገን የሆኑ የተወሰኑ ክፍሎች ግን ታልቃ በመግባት መንቀሳቀሳቸውን ተናግረዋል።

ብፁዕነታቸው ከሀገረ ስብከታቸውና ከሥራቸው እስከ ጥቅምት የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ድረስ የታገዱ ሲሆን መታገዳቸውና የብፁዓን አባቶች ቤተ መሰባበርና የጥቃት ሰለባ መሆንም ከእንቅስቃሴያቸው እንደማይገድባቸው ተናግረዋል። ጉዳዩ ለብዙ ዘመናት “ታፍኖ ቆየ ነገር ስለሆነ መፍትሔ ለመስጠት ችግር መፍጠሩ አይቀርም እንዳሉ የተጠቀሰው ሊቀ ጳጳሱ “አንዳንድ ለሆዳቸው ያደሩ” ሰዎች፣ በቅርስ ሽያጭና ዝርፊያ የሚተባበሩ በሙሉ ችግሩን በማወሳሰብ ላይ ይገኛሉ ማለታቸው ተሰምቷል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የቅዱስ ፓትርያርኩ አስተዳደር መበላሸትን በመቃወሙ ሒደት ግንባር ቀደም የሆኑት ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ከሚኖሩበት ከቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ግቢ እንዲወጡ ግፊት እየተደረገባቸው መሆኑን ምንጮቻችን ገለፁ። ከኮሌጁ ወጥተው ወደ ቤተ ክህነት ግቢ እንዲገቡ ግፊት እየተደረገባቸው ያሉት እኒሁ አባት ወደ ቤተ ክህነት የመግባት ፍላጎት እንደሌላቸው አሳውቀዋል ተብሏል። ያልፈለጉበት ምክንያት የማፊያው ቡድን የጥቃት ሰለባ ላለመሆን ፈርተው ይሆናል ተብሏል።

24 comments:

Anonymous said...

What? yeAzeb ejis yemengist ej aydelem?

Unknown said...

"ሊቀ ጳጳሱ “አንዳንድ ለሆዳቸው ያደሩ” ሰዎች፣ በቅርስ ሽያጭና ዝርፊያ የሚተባበሩ በሙሉ ችግሩን በማወሳሰብ ላይ ይገኛሉ ማለታቸው ተሰምቷል።"


እግዚኦ፡መሐረነ፡ክርስቶስ!
እግዚኦ፡መሐረነ፡ክርስቶስ!
እግዚኦ፡መሐረነ፡ክርስቶስ!
በእንተ፡እግዚእትነ፡ማርያም፡መሐረነ፡ጅርስቶስ!!!

ዘደብረ፡ሊባኖስ፡ነኝ።

tad said...

"Limited regime interference"???
By saying 'limited' is he suggesting that it is not the regime's plocy to remote control EOC?.Please don't try to fool us now and then. Enough is enough. To the rest of EOC members, let's not deny the depth of our beloved EOC problems.Le's not try to cure the symptoms,but the root causes.
May God lead us

Anonymous said...

እውነት አርነት ታወጣችኋለች። እባካችሁ ደጀ ሰላሞች ብሎጋችሁን የእውነት እንጂ የድጋፍ መድረክ አታድርጓት። የመንግስት እጅ ከተባል ቀኙም ሆነ ግራው እጁ ያው ነው። ቀኝ እጁ (እን አባይ ጸሐይዬ)ፓትርያርክ ጳውሎስን ሲደግፉ። የባሰውና የከፋው ግራ እጅ (እነ በረከት ስሞንና አዜብ መስፍን) የአባ ሳሙኤል ደጋፊና ለዚህ ሁሉ ችግር መንስኤዎች መሆናቸው የአደባባይ ምሥጢር ነው። እንደውም የአባቶች መንገላታኣ የመንግስት ግራ እጅ የጉዳዩን አቅጣጫ ለማስለወት ሆን ብሎ የፈተረው ችግር ሊሆንም ይችላል ይባላል።

ታዛቢዉ... said...

እዉነቱ እንደ ዝንብ ሁሉም ቦታ ጥልቅ ካላልክ አይሆንልህም ማለት ነዉ?
ይሄንን የተጠናወተህን አባዜ እንድያርቅልህ ወደ እግዚአብሔር ጸልይ
ለነገሩ ድሮስ ከተሃዲሶ/መናፍቅ ምን ይጠበቃል? ይሄዉ አይደል

orthodox unit said...

My friends we have been talking so much lots of times but “No One Hears”. Let us focus on love and mutual respect if we are true Christians. For Deje Selam, I also suggest you to filter Heresies. By any means your blog should not allow Nufakie. But I don’t mind the debate between MK and Tehadiso. They can argue their arguments toward improving themselves.
Dear Ewunetu, for the sake of your sole don’t insult people. Insulting is a sin which our lord Jesus Christ hates. So take care of yourself as a Christian.
Know the truth, practice it and declare to others

Anonymous said...

Thank you Deje Selam for your up-to-date information. Let God pay your work, if you are truthfully standing for the resurrection of our Orthodox Religion. I read a lot of unnecessary blogs and it takes alot of time to respond for those who purposly divert the issue form the main point. Let us concentrate to the core issue and forward our thoughts to alivate the serious problem faced our church.The question is, who is the ultimate decision maker of the church issues? Is that the Holy Patriarck or the Holy Synod. If the Holy Synod is the head of the church and the Holy Patriaric should recpect the Church's rule and lead the church by Holy Spirit and bring peace and tranqulity to our church. Our responsibility is to write the truth and pray to God to send to all of us His guidance in this difficult time.
If some of the bloggers have a problem with MK, let them bring tangable accusationas and let us talk about it. But jusst to blame MK is a distraction form the main issue. We can discuss what is MK is doing right now and what is the problem of the association. We can make truthful critisizmes and help the association to do spritual services instead of standing passive as if nothing happens.

Let God save our church and true- Fathers.

orthodox unit said...

Ewunetu, Can u post the problems with MK so that we will discuss on them? But be sure what you are going to send us should be one that:
1. Can be supported with evidence
2. that is based on real facts
3. Free from hate
4. You also should be present the positive thing that they have, at least some if they have?
5. Don't include heresy (Nufakie)

tad said...

If,If,If DS and some of the bloggers are unconditional supporters of specific bishops, then I don't see any real progress. In both camps I see biased comments.Please work for EOC,not individuals/groups.Be broad minded and pragmatics.
Defend EOC dogmas and cannon laws intellectually not emotionally.

tekle stephnos said...

ዉድ ሃይማኖት
የንጉሴን፡ ሬድዮ፡ ለማስተዋወቅ ከሆነ፡ ይህ ፡ ሁሉ ፡ ጥረት፡ ይህን ያህል ድካም አያስፈልግም ነበር። ሬድዮው በጣም ዘግናኝ እና አሳፋሪ ገበናውን ከማሳየቱ በፊት ግዘፍ ያነሳ ታዳሚዎች እንደነበሩት ብዙዎቻችን እንመስክራለን። ሰውየው በፍቅረ ንዋይ የነነደደ ስለሆነ ለሱ ከገንዘብ በላይ ሰዉ ሆኖ መገኘት ከእሳቤ በላይ ሆኖበት ነዉ ብቻዉን እያቅራራ ያለዉ።

ሃይማኖት

ምናልባት ንጉሴ ፦ከድሆች ቤተሰቦቼ መቀነት ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ከሚጥሏት ሳንቲም ላይ እየተዛቀ በሚሰጠዉ ብር የቅዱስነታቸዉን ስም ማሞካሸት እና በጋለሞታዋ የሚመራዉን የዘራፊ ቡድን በእናት ቤተ-ክርስትያን ላይ ምን እየሰራ እንደሆነ ከህዝብ ለመሰወር እና የአማኒዉን ጆሮ በዉሸት ለማደንቆር ተፈልጎ የተገኘዉ ባንዳ ይሄው ጉድ ብቻ ነዉ። በመሆኑም ይህን የውሸት መዝሙር ከጀመረ ሳምንታት እንደ አስቆጠረ ሰምቻለሁ። አንዳንዴ አስቂኝ ነገር እሰማበታለሁ። ይህ በዉሸት የተካነዉ ባንዳ ታዲያ ከጭንቀት የተነሳ ይመስላል የቀጣሪዎቹን ስሜት ለማርካት የዉሸት መነባነብ በመፍጠር እሱን በግብር መስለዉ ለሚዋሹለት መሰሎቹ እየሰጠ ሲያስቀባጥራቸዉ ሰማሁ ልበል?

ባለፈዉ ሰንበት የያነጋገራቸዉ መነኩሴ ተብዪ ልብ ይሏል፦ ያንን የሬድዮ ድራማ አዘጋጅቶ የሰጣቸዉ እሱዉ ሲሆን እሳቸዉም የተሰጣቸው የቤት ስራ በትክክል አልፈዋል። አፈር ልብላለዎት። ግሩም ድራማ ነበር ።
ይህ በሃይማኖት የሚነገረን commercial ደግሞ plan B መሆኑ ነዉ። እውነት እውነት ነው። እውነት ክርስቶስ ነው። እናማ ክርስትናችን በደም የተገዛ ነው። ቤተ ክርስትያናችን ደግሞ የተተከለችው በዚያ ተተኪ የሌላትን ህይወት አሳልፎ በሰጠ ጌታ ደም ላይ ነው። ማን ነበረ ንጉስ የሚልህ ?ያ የተማረ ደንቆሮ ፦እናማ በእለተ ሰንበት እየጠበቅህ ማህበረ ቅዱሳንን ትራገማለህ አሉ። እኔን ያልገባኝ ግን አንድ ነገር አለ ፦ ይሄውም የወቅቱ ችግር እኮ ማህበረ ቅዱሳን አልነበረም፣አይደለም። ሀገር ቤት ያለው አማኝም በትክክል ያውቃል። ምኑን ብትለኝ የዐሣ ግማቱ ከጭንቅላቱ መሆኑን አበውስ ሲተርቱ እንደዛ አይደል የሚሉት የቤታችንም ችግር እንደ እንስሳይቱ ከላይ ተበላሸንና የታቹን ሁሉ በከሉት። ይህ ይስተካከል ነው የተባለው። ታድያ ምኑ ነው ከማህበር ቅዱሳን ጋር እንዲህ የሚያናጭህ። የሰማሁትን አልደብቅህም፦ ከቀጣሪዎህችህ የተሰጠህ የቤት ስራ ነው። የተሰጠህ ግዳጅ ላንተ ብዙም አይከብድህም፡ ለምን ብትልኝ የስድብ ድርሳናት ፤የውሸት ድርሳናት ሁሉ ያንተ ገንዘቦች በመሆናቸው መራጮችህ አመራረጥ ያውቃሉ። ትግልህም ይህ ከሆነ ግን በጣም ተሳስተሃል።ከቤተ-ክርስቲያን በላይ አእምሮንና ስጋን በአንድነት የሚገዛ የለምና እሱን እርሳው።

ውድ ሃይማኖት፦ ይህንን መልእክት በትትክል እንድታደርስ አደራየ የጠበቀ ነዉ። ለዚህ ታማኝነትህም በቅድሚያ በእናትና በልጁ ስም ምስጋናዪን አቀርባለሁ።

Anonymous said...

Thank you Tekle Estophanos. Berta

Unknown said...

It usually and/or almost always gets worse before it gets better. That is for Day Brake as well!What is taking place was something long overdue.I admire the courage of those who are in the forefront.This, I believe, is not a fightfor the survivle of the EOC as we know it but for the soul and body of Ethiopia.
Besides Nothing to Fear but Fear Itself. Menekosé...Moté
As for the Separation of Church and State!!Give Me a Barke! That sounds MORE like the joke of the century!
Ganta Garo

Anonymous said...

ke Zinjero Qonjo Min Yimeraritual

Unknown said...

Ato "Haymanot",

I dont think you know a civilized discussion. You can write whatever you want to write. What we are asking you is to obey "the rule of the game". Your comments should be limited to the topic under discussion. What you want is only and oly insulting Mahibere Kidusan. Fine with us. You can insult them day-in day-out. But not on every topic which has nothing to do with them.

Advice from Deje Selam:
Please go here (http://mahaberaerkusan.blogspot.com/), a blog exclusively designed to insult MK and write whatever you want.

If you dont understand this, what can we say? Call Nigussie of Hager Fikir Radio, and insult them "lebeh eskitefa".

DS

tekle stephnos said...

ውድ ሃይማኖት፡
ሃይማኖት/ሙሉጌታ/ ንጉሴ ፦ እኛ ያላወቅነው ላንተ የተገለጠልህ የእውነቱ አስተያየት እንዴት ላንተ ብቻ ሊከሰትልህ ቻለ? በስማችሁም ሆነ የሃሰት መዝሙራችሁ በጥልቀት ለተመለከተው አንድነት እና ሦስትነት አለው። በጅብ ቆዳ የተሰራ ከበሮ ሲመታ ቅኝቱ እንብላው እንዲሉ አበው። ቅዱስ ጳውሎስ ለገላትያ በእምነት ለደከሙት ክርስቲያኖች በላከላቸው መልእቱ እንዲህ ብሎ ነበር፦ ም፡9ቁ፡1"በእምነት የደከመውን ተቀበሉት በሃሳቡም ላይ አትፍረዱ" ብሎናል።

tekle stephnos said...

እውነቱ ነኝ አልከኝ
እውነት እኮ ራሱ የራሱን ማንነት በኩራት ይመሰክራል። ላንተ ግን ይህ የመረጥከው ስም በጣም የከበደ ነው። ለነገሩ ሰይጣንስ ስሙ ሳጥናዔል አልነበር። በመሰረቱ እዚህ ባህር ማዶ ያለው የግብር ታናሽህ ፦ ስለ አንተ ሲያስደምጠን የቀዳሜ ሰማዕቱን ማዕረግ ከፊት አስቀድሞ ስምህን በማስከተል ሲጣራ ሰማሁትና the truthfighter.ራስህን መሰላል ሰቅለህ የሞነጫጨርከውን ላነብ ገባሁ።

ወንድሜ ሙት አልልህም ያየሁትን ማመን አልቻልኩም ።ያጠፋሁት ግዜ በጣም አሳዘነኝ። ያነበብትን የሰው ልጅ ያሰፈረው ለማለት በጣም ያስቸግራል።ይህን የጥላቻ መንፈስ ይግብር አባትህ ሳጥናዔል እንኳ ይህን ያህል የጥላቻ የቃላት ጥርቅም ለመቀመር ጭንቅላቱም ትዕግስቱም የለውም።

እናም በጣም አዘንኩልህ። ምን አይነት የጥላቻ ህይወት እንደ ምትኖር አሰብኩና ከልቤ አዘንኩልህ። ምን ነበር ያልከኝ የማመልከውን ጌታ አልከኝ ፦ የትኛውን እንደሆነ ስላልገባኝ ነው፤ግን ደግሞ በጨዋነቴ አትቀየመኝ። ስለ መፍቀሬ ስብዕ ከሆነ ግን የምታወራኝ በርግጥ ታመሃል ማለት ነው። የተረዳሁህ ነገር ቢኖር ምን መሰለህ ከዚህች ከነጠፈች አዕምሮም ምንም አይወለድም ከጥላቻ በቀር ።
እውነቱ

ብልጠት በእጅጉ ይጎልሃል፡ ወንጌሉ ሳይገባህ ፤አንድምታው ሳይገባህ በዱልዱም አዕምሮ ልትተቸው ተነሳህ ዛዲያ ከዚህ በላይ ጨዋነት ከየት ሊገኝ ይችላል። ፊደል መቁጠር የመጀመሪያው እርከን ነው እንጂ

Haymanot said...

Tekle stifanos,

"Alebabsew Biarsu, Be- arem yemelesu" Endilu abatochachen, antem kemesadeb yilik, Ewnetun Egziabher yeglesilehe. Sideb hatiyat neww. Ayzohe ewnetun (yesusn) lemawek atfera, ersu yaberalehal.
God lead you to the truth EOTC Christian. Amen.

ትዝብት said...

ደጀ ሰላሞች እንዲሁም ንጹሐን ምእመናን

እስካሁን የተለያዩ መወያያዎ መድረኮቻችሁን እየተከታተልኹ በመታዘብ ላይ ነበርኹ:: ታዲያ የሚገርመው ነገር አንዳንድ ጥሩ ስም ያላቸው ሰዎች የውይይት ሥርአትን ባልጠበቀ ሁኔታ መጻፋቸው መጀመሪያ አለማወቅ መስሎኝ ነበር:: አሁን ግን ሳጤነው በየርእሶቹ የሚሰጡት አስተያየት ተመሳሳይና ሙሉ ለሙሉ መናፍቃዊ ሐሳብ የሚያንጸባርቅ ነው:: እናም እውነተኛ ኦርቶዶክሳውያን እንዳንወያይ እያዘናጉን መሆኑን ተረድተን ወደቀረቡት ርእሶች ብንመለስ መልካም ነው እላለለሁ:: እንደዚህ ተግተው መሥራታቸው ግን "ሰይጣን አትጊ ባላጋራ" መሆኑን ያስታውሰናል:: ግን ይህ ትጋታቸው እኛ ላይ ብቻ ይሆን ወይስ በቤታቸውም? ልቡናቸውን ወደ ቀናችው መንገድ ይመልስልን!!!

ታዛቢ ከአውሮፓ

Anonymous said...

ደጀ ሰላሞች እንዲሁም ንጹሐን ምእመናን

እስካሁን የተለያዩ መወያያዎ መድረኮቻችሁን እየተከታተልኹ በመታዘብ ላይ ነበርኹ:: ታዲያ የሚገርመው ነገር አንዳንድ ጥሩ ስም ያላቸው ሰዎች የውይይት ሥርአትን ባልጠበቀ ሁኔታ መጻፋቸው መጀመሪያ አለማወቅ መስሎኝ ነበር:: አሁን ግን ሳጤነው በየርእሶቹ የሚሰጡት አስተያየት ተመሳሳይና ሙሉ ለሙሉ መናፍቃዊ ሐሳብ የሚያንጸባርቅ ነው:: እናም እውነተኛ ኦርቶዶክሳውያን እንዳንወያይ እያዘናጉን መሆኑን ተረድተን ወደቀረቡት ርእሶች ብንመለስ መልካም ነው እላለለሁ:: እንደዚህ ተግተው መሥራታቸው ግን "ሰይጣን አትጊ ባላጋራ" መሆኑን ያስታውሰናል:: ግን ይህ ትጋታቸው እኛ ላይ ብቻ ይሆን ወይስ በቤታቸውም? ልቡናቸውን ወደ ቀናችው መንገድ ይመልስልን!!!

ታዛቢ ከአውሮፓ

orthodox unit said...

I read Ewunetu’s /Mulugeta’s book from the website he gave us. I am really surprised by the words he used. I am not defender of Mahibre Kidusan or I am not against Mulugeta. But I saw he is very weak in argument as well as writing skill. Why did he write insulations? He is full of hater.
Even the book that he wrote about Muslims is not acceptable in my mind. It is unmatured and more of hater rather than teaching them. So please my friend Ewunet, if you have interest to be Christian specially an orthodox Christian who believes salivation is both by Grace and work, you have to change your mind first. God is love and those who don’t love their brother don’t know God.
People who know Ewunet have to counsel him. He might have some personal problem with MK but this is not the way. MKs if accuse of people for thing they don't do, take care of it.

I agree that one should write what he likes to write but it should be constrictive and based on truth. It is also possible to point out weaknesses of some party. If we write accusation without facts while pretending to be Christians, that is going to be danger for us.
So let us avoid hater and unit toward the truth.

So Ewunetu write more in the future but learn hope, love and hospitality from Our Lord Jesus before that.

God bless Ethiopia and our beloved church.

tad said...

Is it " too naive?" to fingure point at the regime when it interferes with the EOC affairs?. It seems to me that most of the sunday school members silent on this issue.Please help me. I am lost.
Thanks

petrosawi said...

Dear you all how are you?

It is not long since I start read comments on Deje Selam. I presume I will get good ideas. but I am looking now is something worthless. I disscution was to give an idea on the posted title. But everybody goes out of the agenda.I think this is because
1. the blogers are not from Menafikan or other denomination or those superficial EOTC members.
2.They can't provide any good idea except offending others.
3.they may be those conserned guys to divert the idea.

So please, let us get out from darkness. let us discuss raising constructive ideas. let us struggle for the better future of our church and our country.

we become like bibilonians. when they were asked for stone they would provide mud.

Dear all let us pray for ourthelves just we are not in a good condtion. All of you think what christianity mean. It is not insuling others,or offending purposely others ideas.

Ye'Efugnit Lijot eyehonin ayimesilachihum?????
cher yigtemen.

admasu said...

I am writing this mail to the monk who appeared as an insider to 'teklay bete kihinet' and a researcher about the ‘satanic acts of MK’ on Ato Negussie's radio show. If by any chance you read this message, I wish I got answers for the following simple questions;
1. If you are really now in 'America', where is your exact location? Or to be more precise; where are you serving the church now? Who sends you to the US? Is it the Holy Synod or the Holy Patriarch? What is the purpose of your trip? At what capacity are you serving now? Are you still the head of the department? Do you contact any of the members of the Holy Synod residing in North America? Do any of them share your assertions about the church? I am asking these because I believe you are zealous to the church's hierarchy and obedient to its rules.
2. You mentioned that someone from the MK was before the court for libeling a church father. Who was the plaintiff in the case? Did he try to resolve the dispute in other way before he took it to the court? And most importantly what was the verdict?
3. Finally I heard you saying “these bandits of MK deceived the youth from the truth by telling ‘teret teret’ instead of the true Gospel of the Lord.” I think here is the real difference between you and the MK. Can you please tell us some of the ‘terets’ MK teaches the youth?

My brothers and sisters, it is not my intention to divert your attention from the ‘current issue’ but I believe this discussion is part of the church’s problem in two grounds; one, there are a group of people who want to use this forum to deceive participants from the truth and spread their hearsays and by mentioning MK negatively here and there they are trying to hit two birds with a single stone. Two, if we cautiously follow what they are saying and writing we can figure out who these people are and what they really want from our beloved church.
Let’s try to purify our hearts from hatred, since hatred has never been a solution except perpetuating hatred.
God Bless all of us.
Admasu

tekle stephnos said...

የተወደድክ አድማሱ፦

የመነኩሴው ክስ እኔንም ግራ አጋብቶኛል። መነኩሴው እዚህ ስለመሆናቸው ምንም ማረጋገጫ የለም። የምናውቀው ሃቅ ግን አለ፤ይሄውም

፩ በርግጥ መነኩሴው እዚህ ካሉ ለዚሁ ተልኮ ሲሉ በአባ ሠረቀ አስተባባሪነት ከቅዱስ ሲኖዶስ እውቅና ውጭ በቅርስ ዘራፊው እና በቤተ-ክህነቱ ማፊያ ቡድን የተላኩ እዚህ በሃገረ አሜሪካ ያለውን የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኝ አሁን ከምንገኝበት የተበላሸ ውጥንቅጡ የወጣ አስተዳደር ለማስተካከል እያደረግ ያለውን መንፈሳዊ ውጊያ ለመበታተን የተላኩ አጭበርባሪ ናቸው። ምክንያቱም ተልኳቸው ይህ ባይሆንማ ኖሮ የቢሯቸው መዝገብ (docment)ይዞ እዚህ ድረስ የሚያስመጣቸው ነገር አይታየኝም።

፪ኛው ደግሞ አማኙ ህዝብ ማስተዋል ያለብን መነኩሴው ካነጋገራቸው መረዳት እንደምንቸለው እዚህ እያገለገሉ ያሉት በእናት ቤተ-ክርስቲያን ስር ባለች ቤተ-ክርስቲያን ውስጥ ካሉን በኋላ ነገር ግን ከሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ከብአቡነ አብርሃም ትዕዛዝ አንደማይቀበሉ እና እንዳልተቀበሉት ነግረውናል። የቤተ-ክርስትያኒቷም ችግር ይሄው የበላይ የሰጠውን መመሪያ እታች ያለው ተቀብሎ አለመፈሠም። መነኩሲው በእብሪት የነገሩን አለመታዘዛቸውን ነው። እነዚህን ተባዮች ነው እንግዲህ መላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኝ ውጊያ የገጠመው። አንድዬ ይርዳን።

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)