August 24, 2009

ወደ ቅዱስ ሲኖዶስ የሚላክ የምእመናን ፔቲሽን ዝግጅት

(ደጀ ሰላም፣ ኦገስት 24/2009): ደጀ ሰላማውያን በሆኑት በ“ዳን እና ተዋሕዶ” አሳሳቢነት፣ በደጀ ሰላም ደጋፊነት፣ አንድ ፔቲሽን ተዘጋጅቶ እንዲላክ ሐሳብ ቀርቧል። ይህ ፔቲሽን በምን በምን ዙሪያ ማተኮር እንደሚገባውና ማን እንደሚያዘጋጀው የምንነጋገርበት ሆኖ ፔቲሽኑ በተወሰኑ ሰዎች ተዘጋጅቶ ሁላችንም ሐሳባችንን “አዋጥተን” አርመነው የሚላክ ይሆናል። ዝግጅቱን በተገቢው ጊዜ ለማድረስ ቢበዛ የ30 ቀን ዕድሜ ያለን ሲሆን በማድረሱ በኩል ደጀ ሰላምና ሌሎች ፈቃደኛ ደጀ-ሰላማውያን ይተባበራሉ።

ለመነሻ ያህል ፔቲሽኑን “ዳን እና ተዋሕዶ” በአማርኛ አዘጋጅተው እንዲያቀርቡልን ደጀ-ሰላም ሐሳብ ትሰጣለች። ልታግዟቸው የምትፈልጉ ትጨመራላችሁ ሌሎች ፈቃደኞች ደግሞ በጥሩ እንግሊዝኛ ከሽነው እንዲያቀርቡልን ይለመናሉ። ከዚያ በኋላ “የምእመናን ድምጽ” ነውና ሁሉም “እንዲፈርምበት” በድረ-ገጽ ላይ ይለቀቃል። ያንን ይዘን ለቅዱስ ሲኖዶስና ለአባላቱ ብፁዓን አባቶች እናቀርባለን ማለት ነው።

14 comments:

ትውፊት said...

ሰላም ደጀሰላማውያን እንኳን ለእመቤታችን በዓለ እርገት በሠላም አደረሳችሁ አደረሰን

በጣም የተቀደሰ ሃሳብ ነው ይህ ነው የድርሻን መወጣት ማለት፡፡ ይህ ታሪካዊም ብቻ ሳይሆን ግዴታን መወጣትም ጭምር ነው፡፡ የምናቀርባቸው ዝርዝር ጉዳዮች ግን ምክንያታዊና መረጃን መሰረት ያደረጉ መሆን ይገባቸዋል ብዬ አምናለሁ፡፡

ዋናው ጉዳያችን ማጠንጠን አለበት ብዬ የማምነው
1 ብልሹ አሠራር እንዲታረም
2 በአባቶች ላይ የተደረገው ዛቻነና ማስፈራራት እንዲወገዝ
3 ቤተክርስቲያን በቤተክርስቲያኗ አባቶች ብቻ እንድትመራ
4 የቤተ ክርስቲያናችን ማዕከላዊ መዋቅር እንዲጠናከርና በባለቤትነት እንዲሠራ ሙሉ ስልጣንና ኃላፊነት እንዲሰጠው
5 በጥቃቅንና መሰረታዊ ባልሆኑ ጉዳዮች የሚታየው ጣልቃ ገብንት እንዲቀር

የሚሉትንና ከዚህ ጋር የተዛመዱትን ጉዳዮች የሚያብራራ ጥያቄ አዘል ፔቲሽን ቢሆን ጥሩ ነው እላለሁ

አመሰግናለሁ
ትውፊት ነኝ ከባህር ጫፍ
(ትውፊት መዝገብ ዘሃይማኖት)

Unknown said...

Thank you Tewfit.
DS

Unknown said...

In the Name of The Father The Lord And Holy Sprite One God Amen!

Thank you Deje Selam, for considering the comment and starting practical solutions. I will try to write my idea to be presented to Synod and will send to you.

Let us have united heart and work for our beloved church

Unknown said...

Hi Ferecha,
Please read our comments policy. Limit yourself to what is stated on the title of the article. I am going to delete your posting for the third time. Ok?

Deje Selam

Unknown said...

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አህዱ አምላክ አሜን!!!

እግዚአብሔር ይስጥልን ደጀ ሰላሞች በጣም ጥሩ ሀሳብ ነው።

እኔም ቤ/ክችን ተጠናክራ እንድትወጣ እና የዘመኑን ፈተናዎች ታልፋቸው እና ለዘላቂ መፍትሄ ይሆን ዘንድ

1 - የቤ/ክ ራስ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፣ ቤ/ክ የእርሱ ናት ስለሆነም በዙፋኑ ሆኖ የቤ/ክንን ጉዳይ ከሁላችን በላይ ይከታተላል። ስለዚህ ሙሻራው ክርስቶስ ይመጣል ተብሎ በጉጉት የሚጠበቅ ከሆነ ቤ/ክ እንደ ሙሽሪት ራሱን አንጽታ መጠበቅ አለባት። "እድፈት ወይም የፊት መጨማደድ ወይም እንዲህ ያለ ነገር ሳይሆንባት ቅድስትና ያለ ነውር ትሆን ዘንድ ክብርት የሆነችን ቤተ ክርስቲያን ለራሱ እንዲያቀርብ ፈለገ።" ኤፌ 5፡27 በራይ ዮሐንስ ላይ ለተጠቀሱትን ቤ/ክ የላከላቸውን ደብዳቤ እነመልከት

2 - ወደ ለላ እምነት እየፈለሰ ያለውን ምእመን በቤ/ክኑ ረክቶ ከመቅበዝበዝ እንዲድን የተጠናከረ የወንጌል ስርጭት ቢኖር መልካም ነው። የእስልምናውም መስፋፋት በበለጠ ሊታሰብበት ይገባል።


3 - በሀገር ቤት ያሉት አባቶችም ሆኑ በውጭ ወገር ያሉት የተለያዩት ሁለት ሲኖዶስ አንድ መሆን አለባቸው ለዚህም ሰፊ ጊዜ ተሰጥቶት አስቸኳይ መፍትሄ ሊፈለግለት ይገባል።

4 - በቴዩሎጅይ ሙሁራን እና በማህበረ ቅዱሳን ውስጥ ያለው የአካሄድ ልዩነት መፍትሄ ተፈልጎለት በጋራ ለአንዲት ሀዋርያዊት እና ቅድስት ቤ/ክ እድገት መስራት ያስፈለጋል እላለሁ።የአባቶቻችን የቅዱሳን አምላክ ቤ/ክንን እና ሀገራችንን ኢትዮጵያን ይጠበቅ

እህታችሁ ወለቴ ነኝ!!

Unknown said...

ደጀ፡ሰላም፡ከመናፍቃን፡ጸድታ፡ማየቱ፡አንድ፡በጎ፡
እርምጃ፡ነው!እንግዲህ፡እንበርታና፡ቤተ፡ክርስቲያ
ናችንን፡ከደረሰባት፡ጥቃት፡የምትወጣበትን፡የጋራ፡
ጥረት፡እናጠናክር።

ልዑል፡እግዚአብሔር፡ቸሩን፡ያሰማን!
ዘደብረ፡ሊባኖስ፡ነኝ።

Unknown said...

ይህ የሚዘጋጀው ግልጽ ደብዳቤ Petition በተወሰነ ጉዳይ ላይ ይህም ሲኖዶሱን በሚመለከት ብቻ ቢሆን ይመረጣል::

የሲኖዶሱን ህልውና አስመልክቶ ከጥንትም ሲኖዶሱ አመራሩ የተመሠረተው በሚወያይባቸው ጉዳዮች ተወያይቶ በአንድ ልብ ላይ ለመድረስ (collective leadership) ፥ ማንም የቬቶ ስልጣን የለውም:

in Greek "በአንድ ልብ" ("with one accord" "ὁμοθυμαδόν" በኛ ዘንድ የተዘነጋ ይመስላል OR is not fully understood)

ይህ የግሪክ (ሐዲስ ኪዳን የተጻፈበት ቋንቋ) ቃል "በአንድ ልብ" "with one accord" ὁμοθυμαδόν በግብረ ሐዋርያት ቢያንስ አስር ጊዜ ተጽፏል, (ለምሳሌ ም.1 ቁ. 14, ም.2 ቁ. 1 ወዘተ... ሆኖም በኛ ቋንቋ ትርጉሙ ላልቷል::

ቢያንስ የቃሉ ትርጉም (with one mind, with one accord, with one passion) ማለት ነው የሚሉም አሉ:: የግሪክ ቋንቋ ያጠና በተሻል ያስረዳን::

ስለዚህም አንዳዶች የሲኖዶስ አሰራር "በአንድ ልብ" ልክ እንደ "Passion Of The Christ Symphony" "የክርስቶስ ሕማማት"ያያችሁ የሰማችሁ እንደምሳሌ ብታዩት እያንዳዱ የተለያየ የሙዚቃ መሳርያ ተጫዋችን የSymphonyው መሪ ወይም concert master አስተባብሮ እንደሚመራው ለሰሚው/ለተመልካች አጣፍጦ አቀናብሮ እንደሚያቀርበው

እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስም እያንዳንዱ የሲኖዶስ አባል ያለውን ተሳትፎ ሃሳብና ድካም/ሥራ (effort) አቀናብሮ የሲኖዶሱን ሥራ አጣፍጦ አቀናብሮ ይመራል:: ይህ ነው መንፈስ ቅዱስ የሚመራው "ቅዱስ ሲኖዶስ" ተብሎ የሚጠራው የሚከበረው::

ምናልባት የገጠመን ችግር ውሎ ያደረ ቢሆንም ማስተካከልና ማረም የሚቻለው

እያንዳዱ የሲኖዶሱ አባል ግዳጅና ኃላፊነቱን ሲያውቅ ሲያረጋግጥ

ሲኖዶሱ ሥልጣኑና ኃላፊነቱ ተጠሪነቱ ለማን እንደሆነ ሲያረጋግጥ ::

ራሱንና ሥራዓትን የሚያስከብር ሲኖዶስ ተቀባይነት ይኖረዋል: ውሳኔውም ይከብራል::

ቤተ ክርስቲያን ብዙ ችግሮች ገጥሟታል ወዱፊትም ይገጥማታል
ማንኛውም ችግር የሚፈታው የሐዋርያትን አርአያ (የሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 1: 13 ተመልከቱ
"በገቡም ጊዜ ወደሚኖሩበት ሰገነት ወጡ፥ ጴጥሮስና ዮሐንስም፥ ያዕቆብም፥ እንድርያስም፥ ፊልጶስም፥ ቶማስም፥ በርተሎሜዎስም፥ ማቴዎስም፥ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብም፥ ቀናተኛ የሚባለው ስምዖንም፥ የያዕቆብ ልጅ ይሁዳም። 14 እነዚህ ሁሉ ከሴቶችና ከኢየሱስ እናት ከማርያም ከወንድሞቹም ጋር
በአንድ ልብ ሆነው ለጸሎት ይተጉ ነበር።") ስንከተል ነው::

ግልጽ ደብዳቤው DRAFT LETTER ይዘጋጅና ሽማግሌዎች እናቶች አባቶች የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት የቤተ ክርስቲያን ልጆች በረጋና በሰፈነ መንፈስ
ተወያይተውበት --የሚላከው Petition እንደኔ ምኞት በአሁኑ ጊዜ, this time, ሲኖዶሱ ሥልጣንና ኃላፊነቱ ላይ ብቻ ያተኮረ ቢሆን
ሌላ ጉዳዮች ባያነሳ የቤተ ክርስቲያን ልጆች ሁሉ -በአጠቃላይ ዩኒቨርሳል Petition ተዘጋጅቶ:

-በኢትዮጵያ ከየአጥቢያ ቤተ ክርስቲያናት
ከገዳማት: ከትምህርት አቅዋማት ወዘተ
ከመላው አፍሪካ
አውስትራልያ ኤስያ
መካከለኛው ምስራቅ ከቅድስት ሃገር ኢየሩሳሌም
ከአውሮፓ
ከሰሜን አሜሪካ -ካናዳ ካሪቢያንና ደቡብ አሜሪካ- ካሉ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ቢሆን:
ቢያንስ አምስት : አስር ሚሊዮን የምንሆን ድጋፍ
የምንልከው ለሁሉም ለፓትርያርኩ ለሲኖዶስ አባላት በሙሉ ቢሆን:

ቀኖና ቤተ ክርስቲያን ይከበር እናክብር ስላሉ ፈተና ለድረስባቸው በጸሎትና ጠንካራ ድጋፍ አብረን እንደቆምን::
ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን ላፈነገጡ እንዲመለሱ አለዚያ "ጨው ሆይ ብትጣፍጥ ጣፍጥ ያለዚያ ድንጋይ ነህ ብለን እንወረውርሃልን" እንደተባለው ይሆናል እንደምንል በማያመነታ ለመግልጥ:

ይህንንም በማስትባበር
ለምሳሌ በሰሜን አሜሪካ የኢ/ኦ/ተ/ ቤተ ክርስቲያን ካህናትና ምእመናን ጉባዔ

(የጉባዔው መግለጫና ውስኔ የሚመሰገን ሥራ ነው::)

ተመሳሳይ የካህናትና ምእመናን ጉባዔ
በአፍሪካ
በአውስትራልያ ኤስያ
በመካከለኛው ምስራቅ በከቅድስት ሃገር ኢየሩሳሌም
በአውሮፓ ወዘተ ቅድሚያ ቢወስዱ::

ጌታ መንፈስ ቅዱስ ያስተምረን ይምራን::

Unknown said...

Dear Dan,

I think it is a good idea that we focus on the Holy Syond. Please try to come up with the proposal and we will edit and re-edit beofre final submission. Go brother, go.

Cher Were Yaseman,
DS

Unknown said...

Dear Deje Selam, I have some proposal. Shall I post it or shall i send it to u? If I should send to u can you send me your email. You can send me your email through christtewahedo@gmail.com

Thanks, Tewahedo

Unknown said...

Dear Tewahedo,
Please send to us at dejeselam@gmail.com. In the mean time, Dan, can you send us your e-mail so that we can share with you?

Cher Were Yaseman.

Unknown said...

Dear Deje Selam, I have sent my proposal though email. Please check your email.

God Bless Our church

Anonymous said...

+++ one GOD amen.
Thank You DS.
The right decision at the right time. Now I am very happy by your strict decisions. I will help our church by pary to good finalization under the lelp of GOD.
Cherwere Yaseman
Ke Asebot Gedam

Anonymous said...

The idea of petition for people who can fear their followers.

These people are not fearing God Let alone us. Therefore, the idea of petition, in my opinion, is west of time. There should another mechanism to correct those papasat who are breaching the church laws.

Thanks

orthodox unit said...

Dear Anonymoue,

Who knows they (synod members) may be touched by such trial from members of the church. We try God will do what ever He want. But let us never be tired of trying such thing every time in our life. God always has ways to solve complicated problems. What is needed from us is united hearts.

God bless our beloved church!
Let us have united faith against Evil works

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)