August 15, 2009

አንድ የኢ/ኦ/ተ/ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ስለ ነገረ ሃይማኖት ወደ ኮፕት ቤተ ክርስቲያን ማመልከቻ አስገባች

(የመግለጫውን ሙሉ ቃል እዚህ ያንብቡ)
(ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 14/2009) በካንሳስ ሲቲ ካንሳስ የምትገኘዉ "የደብረሣህል መድኀኒአለም" የኢ/ኦ/ተ/ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን በነገረ ሃይማኖት ምክንያት ያላትን ጥያቄ ወደ ኮፕት ቤተ ክርስቲያን ማመልከቻ ማስገባቷን፣ ማመልከቻውም መልስ ይዞ በመምጣቱ ስብሰባ መጥራቷን አስታወቀች።

“የዛሬ አምስት ዓመት በከተማችን በካንሳስ ሲቲ ካንሳስ በምትገኘዉ በደብረብርሃን ኪዳነምህረት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ/ክ እመቤታችን ቅድሰት ድንግል ማርያምን አሰመልክቶ ስለ ጥንተ አብሶ (Originl Sin) ተነስቶ በነበረዉ የሃይማኖት ዉዝግብ ምክንያት ቤተክርስቲያን ለሁለት መከፈሉ ይታወሳል። በወቅቱ የሰሜን አሜሪካ ሐገረስብከት ሊቀጳጳስ የነበሩት ብፁእ አቡነ ማቲያሰ በደብራችን ተገኝተዉ የወሰኑትን ዉሳኔ ሙሉ በሙሉ በመቃወም ዛሬ ደብረሣህል መድኀኒአለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርሰቲያንን የመሰረቱት ምእመናን ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ/ክ ቅዱስ ሲኖዶስ፥ ለቅዱስ ፓትርያርኩ አቡነ ጳዉሎስ እና ለሊቃዉንት ጉባኤዉ የሚከተሉትን ዐበይት ጉዳዮች ተመልክተዉ ለተወሰነው ዉሳኔ ማረሚያ አልያም በማሰረጃ የተደገፈ ማብራሪያ እንዲሰጡን በተደጋጋሚ አሰከቅርብ ጊዜ ድረስ ያለምንም ዉጤት በፍጹም ትህትና ስንጠይቅ ቆይተናል” የሚለው ይኸው የቤተ ክርስቲያኒቱ መግለጫ “፩ኛ አሀት አብያተ ክርሰቲያናትና መላው የዓለም የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያናት የሚያወግዙትን (Immaculate Conception) በመባል የሚታወቀዉን የካቶሊክ እምነት እንዴትና ለምን ቅድስት ቤተክርስቲያናችን ተቀበለች? ፪ኛ በአባታችን በቀሲስ አስተርዓየ ጽጌ ላይ የተፈጸመዉ ግፍ፥ ሰህተት እንደሆነና ጉዳዩ በድጋሚ ታይቶ መፍትሄ እንዲያገኝ” ፈልገው እንደነበር ያብራራል።

“ተስፋ ባለመቁረጥ ከዛሬ ነገ መልስ እናገኛለን ስንል ጊዜ ጊዜን እየወለደ አምስት አመት አለፈ፡፡ ሆኖም ሃይማኖት ነዉና እግዚአብሔርን ተስፋ በማድረግ ጩኸታችንን ወደ አሀት አብያተክርስቲያናት በማዞር ለግብፅ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ/ክ ቅዱስ ሲኖዶስ እና ቅዱስ ፓትርያርክ ፖፕ ሽኑዳ ፫ኛ ጉዳዩን ገልጸን በማስረዳት ነገረ ሃይማኖቱን በተመለከተ መልስ እንዲሰጡን በጽሑፍ በጠየቅነዉ መሰረት የግብፅ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ/ክ ሊቀ ጳጳስ ብፁእ አቡነ መቃርዮስ በ august 15, 2009 from 2:00 - 5:00pm በግብጽ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ/ክ ተገኝተን ከቅዱስ ፓትርያርክ ፖፕ ሽኑዳ ፫ኛ የተሰጠዉን መልስና በሊቀ ጳጳሱ የሚሰጠዉን ትምህርትና ቡራኬ ለመቀበል ማንኛዉም ጉዳዩ የሚመለከተዉና የሚያሳስበዉ ሰዉ በሙሉ ተገኝቶ እንዲሰማና ጥያቄም ካለዉ እንዲጠይቅ በትህትና መጋበዙን ለአካባቢዉ ህዝብ እንድናሳዉቅ በተጠየቅነዉ መሰረት ይህን የስብሰባ ጥሪ አቅርበናል” ሲል ደብዳቤው ያብራራል።

ስብሰባው ነገ ቅዳሜ እንደሚካሄድም ተብራርቷል። በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የቅርብ ጊዜ ታሪክ አንድ የኢትዮጵያ አጥቢያ በነገረ ሃይማኖት ምክንያት እንደ ጥንቱ ወደ እስክንድርያ ቤተ ክርስቲአን ጥያቄ ሲያቀርብ የካንሳስ ቤተ ክርስቲያን የመጀመሪያዋ ትሆናለች ማለት ነው።

32 comments:

Anonymous said...

The issue of "original sin" seems to me to be at least a projection of alien concepts, if not a complete category mistake!

ቀሲስ አስተርአየ ጽጌን ያወቅዃቸው ኢንተርኔት ላይ ባነበብኳቸው ጽሑፎቻቸው ነው። ከጽሑፎቻቸው ይዘት እንዳቅሜ በተረዳኹት መሠረት ቀሲስ፦ ትምርት ያደላደሉ ምስጢር ያስተዋሉ ብቻ ሳይኾን፤ ስለቤተክርስቲያናችንም ስላገራችንም ቁጭት ያላቸው ታላቅ ሊቅ እንደኾኑ አስባለኹ። እንዲህ ባላስብ ይችን ማስታወሻ ለመጻፍ ባልተነሣኹም ነበር። የማላከብረው ሰው እንደማይሰማኝ ስለማውቅ።

ፈላስፎቹ "category mistake" የሚሉትን ነገር ቀሲስ በደንብ እነድሚያውቁት አምናለኹ። ታዲያ በ"ጥንተ-አብሶ" ስም የምንጨቃጨቅበት ጉዳይ ምናልባት እንዲህ ያለ ስሕተት ይኖርበት ይኾን ቢባል መሠረት-የለሽ ጥርጥር ነው ወይስ "አሀ" የሚያሰኝ ግንዛቤ? ነገሩ "category mistake" ባይኾን እንኳ የገዛ ራሷ ምንጻር (perspective) ያላት የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ሊቃውንት በባዕዳን ቋንቋ በተፀነሰ ሓሳብ በባዕዳን መንደር በተተከለ ችግር (projection of alien concepts) እስ-በሳቸው ሲጣሉ መኖር አለባቸው ወይ? (ይኸን ጉዳይ የጎደዩት ኮተሊኮቹም ኾኑ ሽንጣቸውን ገትረው የሚከራከሯቸው መለካውያኑ በነገረ-ተዋሕዶ ዘመዶቻችን እንዳልኾኑ ይታወቃል። በእስላም ተወረው ትምህርታቸውን ማስፋፋት ቀርቶ ባግባቡ መጠበቅ ያልቻሉት ወገኖቻችን ቅብጦቹም ኾኑ ሶርያዎቹ ሕይወታቸውን ለማቆየት አንዴ ካንዱ ሌላ ጊዜ ከሌላው እየተለጠፉ--በቊርባን እስከመተባበር ድረስ ደርሰው--የሚያወሩትንም ማስተጋባት በነጻነት ምስጢረ-መለኮትን ስታራቅቅ የኖረች የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያንን ሊቃውንት ደረጃ የሚመጥን አይመስለኝም። ኧረ በነእምየ ቅዱስ ያሬድ፣ ኧረ በነእምየ አባ ጊዮርጊስ! ምነው ምነው?)

እስኪ ልብ በሉት። ይህ ችግር ከጥንት በቤታችን የነበረ ቢኾን መነሻ ቦታው ሊኾን የሚችለው የት ላይ ነበር?

እንደኔ እንደኔ፦ ከሌሎች ንባቦች በተጨማሪ እመቤታችን በትንቢታዊ ጸሎቷ "...ወትትሐሠይ መንፈስየ በአምላኪየ ወመድኀኒየ" ባለችው ላይ ሊኾን እንደሚችል እገምታለኹ። ሊቃውንቱ ታዲያ ይኸን ሲተረጉም በሐተታቸው የጠቆሙን ምንድን ነው? "...ከምን አድኗታል ቢሉ ከንዴተ-ህላዌ፣ ከልማደ-አንስት"

ልብ በሉ።

የኔ ነጥብ "ጥንተ-አብሶ" አለባት የለባትም ሳይኾን፤ ይኸ ፅንሰ-ሐሳብ "ርእሰ-ጉዳይ" ኾኖ ሊታተት ይችል በነበረበት ቦታ ላይ ጭራሽ አለመነሣቱ ነው። በምትኩ "ንዴተ-ህላዌ" የሚል ቃል እናገኛለን። ምናልባት "በጥንተ-አብሶ" ስም የምንከራከረውን ክርክር በዚኽኛው ፅንሰ-ሐሳብ መሠረት ብንወያየው የተለየ ኹኔታ ይኖረው ይኾን? በጥልቀት እና በስፋት ገና ስላላሰብኩበት ወደዚህ በዝርዝር አልገባም።

ምናልባትስ የጥያቄውን አተካከል አንድ ደረጃ ገፋ አድርገን (ማለትም፦ ከእመቤታችን ጋራ ከመያያዙ አስቀድሞ) "ጥንተ-አብሶ ቅሉ ምን ማለት ነው?" በማለት ብንጀምርስ? በብሉይ ሳይቀር "አበው ጮርቃ በበሉ የውሉድ ጥርስ ጠረሰ" ለሚለው ክስ የተሰጡትን መልሶች ከመመልከት ብንጀምርስ? "በከመ-ነፍሰ-አብ ዚአየ ይእቲ ከማሁ ነፍሰ-ወልድኒ፣" "አሐዱ አሐዱ ይመውት በኀጢአቱ" ወዘተ.

ሌላም ብዙ ብዙ አቀራረብ ይታየኛል። ከኹሉ በላይ ግን፦

ኧረ "እንኑር" እስኪ ወዳጆቸ!!!
ኧረ "እንኑር" እስኪ ወዳጆቸ!!!
ኧረ "እንኑር" እስኪ ወዳጆቸ!!!

ምክንያተ-ህላዌኣችን የኾነው ነገር (raison d'etre) ጥያቄ ላይ ወድቆ እንዳለ አይታያችኹም እንዴ??? ኧረ በፅንሰታ፣ ኧረ በልደታ፣ ኧረ በፍልሰታ... ኧረ በእምየ ማርያም! ልብ እንግዛ። ልብ እንግዛና፤ ይችን ቤተክሲያን፣ ይችን አገር እንዲታደጋት እንጩኽ!!!


P.S.: correction of Geez letters in the letterhead:
ትክክለኛው አጻጻፍ "ደብረ-ሣህል መድኀኔ-ዓለም...ተዋሕዶ..." ነው። ልብ በሉ፦ "ህ" "ኔ" "ሕ"
ዕርማት ለመስጠት የደፈርኹት "letterhead" ስለኾነ ነው። ባጠፋኹ ይቅርታ።

Anonymous said...

Yabayin Lij Wuha temat
What i am seeing is , things are really going out of control. Why do these brothers and sisters want to go to coptic church . Their justification , as written is, is to get an answer for the qusetion they have on orginal sin of Saint Mary. But this issue is intensively and extensively discussed by many church scholars. The Holly Book Haymanote Abew, states so many things in detail about this issue. Prominent scholars of the church, like Melake Birhan Admasu Jenbere in his book Kokih Haymanot and Medlote Amin, Aleka Ayalew in his book Mec Telemedena Ketekula Zimdina, another Church Scholar in his book Sirwe Haymanot and many scholars have cleary explained this issue. All scholars explain that Saint Marry is free of any sin.I dont know why we want even to go that far. The book which we always read daily ,Teamire Maryam also clearly depicts this. why is this clear thing an issue ?If some argue that it is pressing issue, Our church do have many spiritual scholars . They could have invited those teachers . I can mention the wel known teacher of Holly books both for Old testament and Testament from promonent monasteries like Dere Libanos, Hayk Estifanos, Gondar etc and etc. Having tele conference with members of the Holly Synod is the other option. They could have got the answer. Let alone them , secular jounalists are daily interviwing our fathers and they are giving explanations. i , by no means , think that this move is normal. i am feeling of some hidden agenda.
Every Ethiopian must remeber the crime of coptic church. Though we feel that they are our brothers , they were and are still conspiring to take our monasteries in Jerusalem ( DEER SULATAN). That church was semding fake pops for us. ( please read the book of Abuna Gorgorios YeEthiopia bete Kirstian tarik).
we shoud really take care of our move with ....
Ze debre zeit Rufael

Anonymous said...

ጎበዝ፦ ይኸ "ግብፅ፣ ግብፅ" ማለት የመጣው በምን ምክንያት እንደኾነ ይገባኛል። ኾኖም ግን በዛ። ተንዛዛ። አቅለሸለሸኝ።

አባ ሸኖዳ አባ ሸኖዳ የምትሏቸውም ቢኾኑ፤ ከገዛ ወገኖቻቸውም ጭምር የተቀበላቸው የለም እንጂ፤ በ"ቪየና ኮንሰልቴሽን" የነገረ-ተዋሕዶን ምስጢር ባፋለሰ ዶክመንት ላይ የፈረሙ "ሥልጡን" የኮተሊክ አሽቀባጭ ናቸው።

አትድከሙ።

የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ከጥንት ጀምሮ በምእመናኗ የውሀት፣ በሊቃውንቷ ትምህርት ነው የኖረችው። በቃ። ሊቃውንት ስላችኹም ግዴታ ጳጳሳት፣ መነኮሳት፣ ቀሳውስት ማለት አይደለም። እምነታቸውን በትምርት፣ በምግባር እና በትሩፋትም ጭምር ገልጦ ለማስረዳት እና ለሌሎች አብነት ለመኾን የበቁ መምህራንን ነው። እንደስመ-ጥሩዎቹ አንደነ አቶ አደራህን ያሉትን ኹሉ።

አኹንም ቢኾን አቶ የለ ዲያቆን፤ ቄስ የለ መነኵሴ ሃይማኖታችንን ተረድተን በምግባር በትሩፋት ለመግለጥ ደፋ ቀና የምንል ኹሉ ቤተክርስቲያናችንን ለመረከብ መዘጋጀት አለብን። ባርባ በሰማንያ ቀን ለተጠመቅነው ኹሉ እኩል ርስታችን ናትና። ሌላው (ጉልቱ) ትርፍ ነው። የሚጠቅም ከመሰላቸው አንዱም አንዱ ይጎለቱበት።

አዎ ስለዚህ፦

ለኔ፦ ነገ ቅዳሜ የሚሰማው ያባ ሸኖዳ ፍርድ የሚጨምርልኝም የሚቀንስብኝም አይኖረውም

Anonymous said...

የሃይማኖትን ነገር እንደ ቀላል ነገር ገፋ አድርገን ወይም ለሰዎች ደስታም ይሁን ሀዘን አለያም ለቡድንም ይሁን ለይሉኝታ ብለን የምንተወው ጉዳይ አይሆንም ::

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ; በአሁኑ ወቅት የተለያዩ ቴዎሎጅያንም ሆኑ ምሁራን እንዲሁም ምእመናን ተፈርተውና ታፍረው የከረሙና በሽፍንፍን ሲሄዱ በነበሩ ጉዳዮች (ዶክትሪንም ይሁን ሥርዓት ) ላይ ጠንካራ ጥያቄዎችና ትችቶች እየቀረቡ ነው ::

ጊዜው ሁሉም ነገር የተገላለጠበት : ሁሉም ነገር በመረጃ የተደገፈ ማብራሪያ የሚፈልግበት ስለሆነ : እንደ ጥንቱ ዘመን በውግዘትና በማስፈራራት ነገሮችን ማሳለፍ አልተቻለም ::

ቅዱስ ሲኖዶስም መሰረታዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ወቅታዊና የማያሻማ መልሶችን መስጠት የግድ ይላል ::

የቄስ አስተርአየን ጉዳይ በጥልቀት ባልረዳውም ::

ጥንተ አብሶ የሚባለው ነጥብ ግን : ሰፊ ማብራሪያና ትንታኔ የሚያስፈልገው መሆኑ ግልጽ ነው ::

ለምሳሌ :
ጥንተ - አብሶ ማለት ቃል በቃል ትርጉሙ ::
የመጀመሪያ በደል : ማለት ነው ::

የመጀመሪያው በደል ደግሞ አዳምና ሄዋን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ማፍረሳቸው ነው ::

እንግዲህ : እየተነጋገርን ያለነው : ስላጠፉት ጥፋት ሳይሆን : ስለ ተላለፈው መርገምና ቅጣት ነው ::

ይህም መርገም በዚህ በደል ምክንያት የመጣ ነው ::

እርግማኑም : በሶስቱም :
. በአዳም
. በሄዋን እና
. በዕባብ ላይ ተላልፏል ::

በሶስትቱም ላይ የተላለፈው መርገም የተለያየ ሲሆን ::
ከክርስቶስ ሞትና ትንሳኤ በኋላ : እኛ ክርስቲያኖች በጥምቀት ያስወገድነው ኃጢአት የነፍሱን መርገም (ኩነኔ ) ብቻ ሲሆን ::
የሥጋው ግን እስከ ምጽአት ድረስ ይቀጥላል ::

በሥጋ ላይ የተላለፈ ቅጣት

አዳም ወይም ለጠቅላላው የሰው ልጅ
. መሬት ነህና ወደ መሬት ትመለሳለህ (ይህ ሞተ ሥጋን የሚመለከተው ሲሆን የነፍስ ሞት በጥምቀት ይሰረያል )
. ወጥተህ ወርደህ ወርደህ በላብህ ወዝ (ደመ -ወዝ ) ምግብህን ትበላለህ

በሄዋን (በሁሉም ሴቶች ) ላይ
በምጥ ትወልጃለሽ : ከወለድሽ በኋላም ፈቃድሽ ወደ ባልሽ ይሆናል (ምጥሽን ትረሻለሽ ) የመሳሰሉት ናቸው ::

እነዚህ ነገሮች ምድባቸው ከየትኛው ነው ? ስስንል የሥጋ ቅጣቶች መሆናቸውን እንረዳለን ::

ክርክሩ የሚጀምረውም : የተነሱና ያልተነሱ መርገሞች ከሚለው ይመስለኛል ::

ወደ እመቤታችን ስንመጣ

. ጌታን ከመውለዷ ከመውለዷ በፊት በንጽህናዋ እንደ መላእክት ናት :

. ከወለደውች በኋላ ግን : ከመላእክት ትበልጣለች : እነሱ ለሚሰግዱለት ጌታ እናት ሆናለችና (ይእቲ ተዓቢ እምኪሩቤል ወትፈደፍድ እምሱራፌል )

. አንጺሖ ሥጋሃ (ሥጋዋን አነጽቶ ተዋሃዳት ) የሚለው ቃል : ከማኅፀን ጀምሮ የሆነውን ለመናገር ነው :
እሷ ግን : ቅድመ ወሊድ - ጊዜ ወሊድ - ድኅረ ወሊድ : ንጽህት ናት : (ወኢረኩሰት በምንትኒ እምዘፈጠራ ...)

. ዘእምጥንተ ሥጋሁ ለአዳም : (አዳም ሳይበድል በነበረው የከበረ ልጅነት ተወለደት ) መንፈ ቅዱስ ዐቀባ እምከርሰ እማ :

: ቀደሰ ማኅደሮ ልዑል - ልዑል ማደሪያውን ቀደሰ ) መዝ 45

ቡርክት አንቲ እምአንስት - ከሴቶች ተለይተሽ የተባረክሽ
ነሽ : ማለትም መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ የሌለብሽ ..... ነሽ ::

ይህ ሁሉ ቃል እመቤታችን ከአዳም በደል የነጻች መሆኗን የሚናገር የቤተ ክርስቲያኗ ትምሕርት ነው ::

ቀሲስ አስተርአየ : ጥንተ አብሶ አለባት ብለው ከሆነ : እንዲህ ለማለት ያበቃቸው መሰረታቸው ምን እንደሆነ መስማት እንፈልጋለን ::

ይህ ከላይ የሰፈረው ትምሕርት ግን ከጥንት ገና ከመጀምሪያው የነበረ እምነት እንጅ : በፍጹም ከካቶሊክ የተቀዳ አይደለም ::

ካቶሊኮች : ኃይል አራያማዊት ነው :: ይህም ማለት የመላእክት ወገ ናት ሰው አይደለችም : ማለት ነው ::

ይህ ኑፋቄ ቤተ ክርስቲያን አትቀበለው ::
ምክንያቱም
እመቤታችን ሰው አይደለችም ማለት : ጌታም ሰው አልሆነም ማለት ነው :: ጌታ ሰው አልሆነም ማለት ደግሞ : ዓለም አልዳነም ማለት ስለሆነ : እጅግ የከፋ ኑፋቄ ነው ::

አንዱን ከአንዱ ማምታታት ደግም አይደል ::

ጥርት ያለ የመወያያ ነጥብ ይዞ መነሳት ያስፈልጋል ::

እንደተባለው : ሲኖዶሱ ይህ ጉዳይ ቀርቦለት ከሆነ በወቅቱ መርምሮ መልስ አለመስጠቱ ትክክል መስሎ አይታይም ::
ሌሎች ሰዎችን ሊበክል ስለሚችል እንዲህ አይነቱ ጥያቄ ፈጣን ምላሽ ያሻዋል ባይ ነን ::

ቅዱስ ሲኖዶስ በጉዳዩ ላይ ውሳኔ ለመስጠት : ግን በመናፍቅነቱ ክሕነቱ የተያዘበት ግለሰብ : በሲኖዶሱ ፊት ቀርቦ : እንዲህ ያለበትን ምክንያት በዝርዝር ማስረዳት አለበት ::
ይህን ሳያደርጉ : አሜሪካ አገር ቁጭ ብሎ በቀላጤ ወረቀት ቅዱስ ሲኖዶስን ለማዘዝ መሞከርና ከእኔ ኑፋቄ ጋር ካልተባበራችሁ ..... እያሉ መፎከሩ የሚያዋጣ አይመስልም ::

እንዳነበብነው : ወደ ግብጾች ሄዱ የተባለው እውነት ከሆነ ችግሩን ሸፋፍኖ ለመቀጠል የታሰበ ሸፍጥ ይመስላል ::

Anonymous said...

http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=34892

Anonymous said...

"Ato Asteraye"????
Shame on you to say this. I don't think you have the gut to discuss what happend,but give name. Typical of an ignorant person's behavior.
May God forgive you.

Anonymous said...

Ato Tsige????
Abune Mathias is the one who messed up with this issue. I don't want to say this, but before the weyane tanks came to addis ababa Abune MathAis was 'Ato'. Becuase our holysynod is always in turmoil, it is very easy name calling in our church. Ato,menafik,tehadisso,...akrary,taliban,alqaida.
Please God give us the way out of this mess

Anonymous said...

Here is the Coptic teaching:
St. Mary & Actual Sins:
Some Fathers do not believe her to be without faults,
such as St. Irenaeus, Origen, St. John Chrysostom…. but these
opinions do not represent the widespread mariological tradition
in the Early Church.
The Church members believe that St. Mary’s holiness is
unique, and that it surpasses heavenly creatures:- even the
Cherubim and the Seraphim….
She passed all her life in holiness, as the True Ark of the
Covenant, which was made of incorruptible wood laid in by gold
inside and outside.(1)
The following are some quotations from the writings of
the Fathers to this effect.
* I do not propose to have a single question raised on the
subject of sin in regard to the Holy Virgin Mary, out of
respect for the Lord.
St. Augustine(2)
* How could I paint the picture of this marvellous,
beautiful one, with ordinary colour….. too exalted and
too glorious is the image of her beauty.....
She was wise and filled with the love of God ....
She was never defiled by bad desires, had remained
from childhood steadfastly just and has always walked
along the right way without fault or stumbling…
St. Jacob of Sarug(1) (451-521)
* The Word of the Father came forth from His Bosom,
and in another He put on a body.
From one Bosom He came forth to another.
These pure bosoms were filled with Him.
Blessed is He who dwells in us.
St. Ephram the Syrian (2)
St. Mary & The Original Sin:
The Orthodox Church, whose love towards St. Mary is
deeprooted, considers her more holy than all the heavenly
creatures, whilst a natural member of the human race. We do not
however, set her apart from the human race by assuming that she
was born without original sin, as if she was born not of human
seed.
This reality is declared in the following Theotokia: (3)
“How deep is God’s abundance and wisdom,
that the womb under judgement
brought forth children by incurring pain;
she became a fountain of immortality,
bringing forth Emmanuel without human seed,
so that He might destroy corruption of our nature”.
Thus, the Church makes a distinction between St. Mary’s
life before and after the moment of divine Incarnation.
In another Theotokia we say: (1)
“The Holy Spirit filled you completely,
filled every part in your soul and body,
O Mary, the mother of God”.
St. Mary, herself declared her joy to God, her Saviour…
for indeed she was in need of salvation.
To this effect St. Ambrose says: (2)
“When the Lord wanted to redeem the world, He began
His work with Mary, that she, through whom salvation
was prepared for all, should be the first to draw the fruit
of salvation from the Son”.
St. Augustine also says: (3)
“Mary sprang from Adam, and died in consequence of
sin; Adam died in consequence of sin; and the flesh of
the Lord, sprang from Mary, and died to destroy sin”.
But why is it difficult for them to accept our church teaching? I think our church has got more than enough answer. I think they are other motives behind the curtains...

hamaressa said...

wey zendero yemayisema yelem degmo yihe min yemilut new?? Who is kesis Asteraye...who can tell me about him?

Egziabher yirdan!
Hamaressa

Anonymous said...

“ቀሲስ አስተራየ” ስማቸው ዳግም በደጀ ሰላም ላይ በተያያዘ ጉዳይ ብቅ ማለቱ የሚጠበቅ ነው፡፡ ከዚህ በፊት በ www.ethiomedia.com ላይ በተደጋጋሚ የሚያወጧቸውን ጽሑፎች ጠጋ ብሎ የመረመረ፡ ሰውየው እልም ያሉ መናፍቅ እንደሆኑ ይረዳል፤ ምክንያቱም፡ የሚጽፉት ሁሉ፡ አንዱ መስመር ትክክል የሚመስል፤ ሌላው ደግሞ እልም ያለ ክሕደት የሆነ ጽሑፎች ናቸው፡፡ ለምሳሌ፡ የጥምቀት በአል አከባበርን፡ ትንሽ አወድሰው ሲያበቁ፡ ቀጠል አድርገው ደግሞ፡ አከባበሩ ባሕላዊ እንጂ ሃይማኖታዊ እንዳልሆነ የሰበኩበት “ጽድቅን ሁሉ ልንፈጽም ይገባናል” የሚለው ጽኹፋቸው በጣም አሳፋሪ ነበር፡: በክርስትና ምንኩስናን የተማርነው ከቡድሃ እምነት ነው የሚለውን ቅርሻታቸውን ያቀረሹበት “ምንኩስና በኢትዮጵያ” የሚለው ጽሑፋቸውም ሰውየው ጤነኛ እንዳልሆኑ የሚያሳይ ትልቅ ማስረጃ ነው፡፡ ደግሞ እኮ የአባ እንጦንስ ከመላኩ የተማረው የምንኩስና ሥርዓተ አኗኗር እንኳ ጠፍቶአቸው አይደለም፤ ነገር ግን፡ ሃይ የሚላቸው በመጥፋቱ፡ ማሩን አምርረው ወተቱን አጥቁረው ይቀባጥራሉ እንጂ፡፡ እጅግ በጣም ዘባራቂ እና ደፋር ስለሆኑ፡ ቅስናውን ከእግዚአብሔር ቤት ለእግዚአብሔር አገልግሎት ሳይሆን፡ ከሌላ ቦታ ለሌላ አገልግሎት ይዘውት እንደሚዞሩ ለማወቅ ሩቅ መሄድ አያስፈልግም፡፡ ጽሑፎቻቸውን መከታተል ብቻ ብዙ ይነግረናል፡፡
“ግብጽ!” “ግብጽ!” የሚል አባዜ ወፍፎ አናቱ ላይ የወጣበት የተሃድሶ እንጂ የተዋሕዶ ቡድን እንዳልሆነ ልብ እያላችሁልኝ ሂዱ ውድ ኦርቶዶክሳውያን፡፡
ብርሃናዊት

Anonymous said...

መነሳት ያለበት በርካታ ጥያቄዎች አሉ ቤ/ ክርስቲያኒቱ በአሁኑ ሰዓት ከባድ ጥያቄ ውስጥ ናት
ለምሳሌ ለቤ/ክርስቲያኒቱ በመጽሐፍ ከቀረቡት ውስጥ
1ኛ ገደል ውይስ ገደል?[በመምህር ጌታቸው
2ኛይነጋል [በመምህር ጽጌ የጳውሎስ ትምህርት ቤት ምሩቅ
3ኛ የዘመናት እንቆቅልሽ ሲፈታ [በመርጌታ ሰረቀ
እነዚ መጻሕፍት ለኢትዮጵያ ቤተ ክር/ ከባድ ጥያቄዎች ሆነው እያስቸገሩ ናቸው ነገሩ እንዴት ነው ጎበዝ?
ሌላው የዘመኑ ጥያቄ "ያቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጉዳይ ነው"
ግብጻዊ ናቸው ወይስ ኢትዮፕያዊ ?ግብጽ አልውቃቸውም ብላለች ይባላል እኒህ ሰው ማን ናቸው?
አንዳዶች የኦሮሞ ህብታም ብዙ ከብት የነበራቸው ባላባት ናቸው ይላሉ
ሌሎች የይፋት መርጌታ ነበሩ ይላሉ
ለሎች ደግሞ ጀርመናዊ ናቸው ይላሉ በመጨረሻ ጠፍተው ወደ ጀርመን እንደተመለሱ ይነገራል ሊቃውንቱ "ዜና መቅብርከሰ በ ኢየሩሳሌም አጸድ ወቦ ዘይቤ ሀለወ በከብድ" ማለት መቃብርህ በ ኢየሩሳሌም ነው በምድረ ከብድ ነው የሚሉም አሉ "እያሉ የሚያዜሙት ትክክለና ታሪክ ስሌላቸው ነው ይባላል
ሌላው ጥያቄ ተክለሃይማኖት ዘቡልጋ ፖለቲከኛ ነበሩ የሚለው የኪዳነ ወልድ ክፍሌ ጽሁፍ በቂ መልስ ያስፈልገውዋል በነዚህ ሁሉ በርካታ ጥያቄዎች ተወጥሮ የሚገኘው ይህ ትውልድ ከቤተ ክርስቲያኒቱ በቂ መልስ ያስፈልገዋል መሸፋፈን አያዋጣም የበለጠ ለአደጋ እያጋለጠን ይመጣል
ቸር ወሬ ያሰማን

Anonymous said...

I remembers he was preaching in Dc kedest marriam church .
The fires time it was nice preaching after few days he start terrible and irreverent preaching , he want back to Kansas and then Abun Matias was asking him to stop this kind preaching , and
Abun Matias bagging him to stay out of this terrible mistake and also once kedus synods
Yedengegewen endekbel negerewut ashafereg bemaletu awgezewetal If it is change anything ,KEDUS SINODOS has mandate to change not k.Asteray. if he think like lekawent he can go back Ethiopia convince or challenge them not for memenan
I do not understand, why they want to ask Coptic church .already it has written LEBELWAT YASEBEWATEN JEGERA KOKE NESHE YELWATAL.
ABUNE MATIAS YEKEDUS SINODOS ABALE ENA YE SEMAN AMERICA LEK PAPASE MEHONACHEWEN YERESAW AYEMESEJEME.KEDUS SINODOS HULE GEZA MELES SEASET MENOR YELEBETEM.Tanks to Berhanawet ADENAKESHE

Anonymous said...

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አህዱ አምላክ አሜን!!

ሰዎች አሁን የእመቤታችን ጉዳይ አንገብጋቢ ነው ወይ? ለእኛ ህይወትስ ጠቀሜታው ምንድን ነው? ሌሎች አንገብጋቢ ነገሮች የሉንም ወይ?

መጽሐፍ ቅዱስ ግልጽ ነው እኮ እመቤታችን የአዳም የውርስ ሐጥያት አለባትትት. ይህ ሰው በመሆኗ እናት አባት ስላላት የወረሰችው እንጅ እርሷ በድላ አይደለም፤ ልክ ኤች አይ ቪ ያለባቸው ወላጆ የሚወልዱት ህጻን ሊወርስ እንደሚችል ማለት ነው።

ጌታን ልትወልድ ስትል ግን መንፈስ ቅዱስ መጣ እና ጋረዳት (ከ እርሷ ወደ ጌታ) አልተላለፈም ጌታችን ኢየሱስ ብቻ ንጹህ አለቀ እርሱ አዳም (የስጋ አባት) የለውም እና። አንጽቶ ቀድሶ አደረባት ያለው ቅዱስ ያሬድ ለዛ ነው።

እርሶም መድኃኒቴ አለቸው ለምን? መድኃኒቷ ስለሆነ። ኦሮቶዶክሳውያን ይህን ይቀበላሉ። እባካችሁ አታምታቱት!!

Anonymous said...

በለው ትናንት ወጣት ኢትዮጵያውያንን ተሀድሶ፣ ቲዮሎጅ ተማሪዎችን ተሀድሶ፤ ምሁራን ጳጳሳትን ተሀድሶ፣ ዛሬ ደግሞ የግብጽ ኦርቶዶክስት ተሀድሶ ጉድ በል ድሬ። ከዚህ ሁሉ ነገር መጽሐፍ ቅዱስን እንደ እግዚአብሔር ቃል መቀበል አይቀለም? ይህ የእመቤታችን ጉዳይ፣ ገድላት (ልብ ወለድ ድርሰቶች) ኦሪታዊ አመለካከት ከልባችን አውጥተን የቀደሙ ኦርቶዶክሳውያን አባቶቻችን ያስተማሩንን እውነት በንቀበል እረፍት ይሆንልናል።


ሐና እና እያቄምስ ጥንተ አብሶ አለባቸው ወይ? ኖ እመቤታችን ንጽሁ እንድትሆነ እነርሱም ንጹህ ነበሩ፡ የ እነርሱ አባቶችስ ኦ እነርሱም ንጹሀን ነበር ኢሂሂሂ። ቀልደኞች
ዲ ዳንኤል

Anonymous said...

Selam the last Anony,

Keberon be-beg qoda memtatu mannetun aylewtewm... yaw qebero new!

ZE TEWAHEDO said...

በመንፈስ ቅዱስ ላልታገዘ እና ላልተመራ ጽሑፍ የሚደናበርም ሆነ የሚወናበድ ኦርቶዶክስያዊ የለምም አይኖርምም። ከወደቀበት አዘቅት መነሣት ሲከብደው ሌሎችንም አዘቅት ውስጥ ለመክተት ለምንፍቅናው ተስማሚ የሆነ መልስ ለማግኘት ወደ ግብጽ ደብዳቤ የጻፈው ሰው ሃይማኖታችንን ሰድቦ ለሰዳቢ የሚሰጥ አመለካከቱ ውስን፤ አስተሳሰቡ ጠባብ የሆነ ብቻ ነው። የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ክብር ለመግለጽ ሙሴ ጽላቱን ከእግዚአብሔር እጅ ሲቀበል ይርድና ይንቀጠቀጥ ነበር ብሎ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንደተናገረው በብዙ መፍራትና መንቀጥቀጥ መሆን ነበረበት። በመንፈስ ቅዱስ ያልተመራና ያልታገዘ ሰው እንዴት እመቤታችንን ንጹሕ ናት ማለት ይችላል? ይኼ ምንፍቅና የጀመረው ጸሐፊው አዋሳ በነበረበት ሰዓት ነው ወይንስ እዚሁ ምድረ አሜሪካ ነው? በሃይማኖት ለማደግ የእግዚአብሔር እናት የሆነችውን ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያምን ሊያንስ የማይገባውን ክብሯን አሳንሶ በመናገር አይደለም። እግዚአብሔር የመረጣትን እና ያከበራትን ጥቂት መናፍቃን የቤተ ክርስቲያኒቷ ልጅ ለመምሰል ሁለት ገጽ ሙሉ በግዕዝ ቢጽፉ፤ በአንዳንድ ሰዎች አመለካከት ምስጢር ያደላደሉ፤ አገር ወዳድ እና ሊቅ ተብለው ቢነገርላቸው ሊቅነታቸው በክህደት፤ ምስጢር ማደላደላቸው በምንፍቅና አገር ወዳድነታቸው በአፍአ ብቻ ነው። ኢትዮ ሚድያ ላይ ኀምሳ ገጽ ጽሑፍ ሲጻፍ ቢዋል፣ ሃይማኖት ያልገባቸው ጥቂት ሰዎች ያወቁና የተረዱ መስሏቸው ይህን ብስለት የጎደለውን አጻጻፍ ከጽሕፈት ቆጥረው አበጀህ በማለት ቢያሞካሹትም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለዚህ ምንፍቅና ስትብረከረክና ቦታ ስትሰጥም አትገኝም። ነቢያት በመንፈስ የመረመሩትን እና ቅዱሳን በጾም በጸሎት የተረዱትን ቀሲስ አስተርአዬ ከካንሳስ ቢቃወሙት የተቃወሙት ምስጢር ገላጭ የሆነውን እግዚአብሔርን እንጂ ሃይማኖታችንን አይደለም። እነቅዱስ ኤፍሬም እና እነአባ ሕርያቆስ ያመሰጠሩትን ምስጢር፤ ነብዩ ዳዊት ነገን ተመልክቶ ልዑል ማደሪያውን ቀደሰ ያለውን ትንቢት፤ የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጭ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል በማለት በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝታ ቅድስት ኤልሳቤጥ የመሰከረችውን ምስክርነት ካንሳስ ተቀምጦ ክብሯን ዝቅ ለማድረግ መሞከር ክህነት አለኝ ከሚል ሰው የሚጠበቅ አልነበረም። ለጸሎት ጊዜ ጠፋና የእመቤታችንን ነገር አመስጥሮ ከመናገር ይልቅ ጥቂት ከሀዲያንን ለማስደሰት እና የግብራቸው ተባባሪ ለመሆን መነሣት እራስን መጉዳት እንጂ ክብሯን ማሳነስ አይደለም። እውን አስተርአዬ በጻፍከው ጽሕፈት ሰውን ከስህተት ወደ ትክክለኛ መንገድ የመራኸው ይመስልኻል? ኃጢአት አለባት ብለህ ስለመሰከርክስ እግዚአብሔር እውነተኛ ሰው በምድር ተገኘ የሚልህ ይመስልኻል? መጽሐፍ ቅዱስን መመርመር እና መረዳት ማለትስ እመቤታችን ኃጢአተኛ ናት ብሎ ለመናገር ነውን? ከዚህ የሚቀጥለው ክህደትህ ደግሞ እንደ አርዮስ ወልድ ፍጡር ነው ለማለት መዘጋጀት ነውን? ከንጹሕ ያልተወለደ ንጹሕ አይደለም፤ የውርስ ኃጢአት ካለባት እናት የተወለደ ኢየሱስ ክርስቶስም የውርስ ኃጢአት አለበት ለማለትስ ተዘጋጅተኻልን?...ስለዚህ አንተም ተከታዮችህም ለማትታነጹበት ትምህርት ተደላድላችኋልና እግዚአብሔርን ባላወቃችሁት መጠን አእምሮአችሁን ለማይረባ ነገር አሳልፎ ሰጥቶባችኋል። የዛሬው ምንፍቅና እና ግብጽን ለምስክርነት መጥራት ነገ ደግሞ ከአሳማው ለመቅመስ እና ከሲጋራው ለመምጠጥ መዘጋጀት ነው። እኛ ከእንግዲህ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንዳስተማረን ከሰማይ መላእክት እንኳን መጥተው ቢሰብኩልን አንቀበልም፤ እንኳንስ ከካንሳስ ያለጾም ጸሎት ከሚሳደብ መናፍቅ ትምህርት ልንቀበል። እኛ እረኛችንን ካወቅን ቆይተናል፤ የምንከተለው ማንን እንደሆነም በአግባቡ ተረድተናል። የካንሳስ ጉባኤ ውጤት ከተሰማ በኋላ በሌላ ጽሑፍ እስከምንገናኝ ለአሁኑ ይቆየን እላለሁ።

Dan said...

ለመሆኑ "ቀሲስ" አስተርአየ ይህን ጠንቅቀው ሳያጠኑ ኖሯል ክህነት ቅስና የተቀበሉት:: አንድ ሰው ግራ ያጋባው ወይም ያላወቀው ነገር ካለ አስተምሮ ለክህነት ብቃት አለው ብሎ ያቀሰሰውን መምሕሩን ጠይቆ ይማራል:: እንኳን ሊያስተምሩ ራሳቸው ጠንቅቀው ሳይማሩ ይቀስሱና: የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ሊቃውንት እንደን ቅዱስ ያሬድ ያስተማሩትን የጻፉትን ማንበብ መረዳት ተስኗቸው ግብፆች ጋ ሩጫ::

በሁለተኛ ደረጃ-
በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 3 ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ " ስለ ምድራዊ ነገር በነገርኋችሁ ጊዜ ካላመናችሁ፥ ስለ ሰማያዊ ነገር ብነግራችሁ እንዴት ታምናላችሁ?" ብሎ አለ::
በማርቆስ ወንጌል "ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ። ያመነ የተጠመቀም ይድናል፥ ያላመነ ግን ይፈረድበታል።" ያለውን በመከተል ወንጌል ላልተሰበከላቸው ወገኖቻችን እንደማስተማር እመቤታችን ቅድሰት ድንግል ማርያምን አሰመልክቶ ስለ ጥንተ አብሶ አለባት የለባትም ብሎ መነታረክ ማቴዎስ ማርቆስ ሉቃስ ዮሐንስ እና ጳውሎስ ያልተከራከሩበትን ማንሳትና መጣል መከራከር ነፍሳት የሚድኑበትን የወንጌልን ስብከት ማሰናከል ነው::

እዚህ አስተያየት ከሰጡት አንዱ ይህ ክርክር "ለእኛ ህይወትስ ጠቀሜታው ምንድን ነው? ሌሎች አንገብጋቢ ነገሮች የሉንም ወይ?" እንዳለው እኛው የፈጠርነው እኛው ልንፈታው ከሚገባን አሁን ካለንበት ችግር ለማዘናጋት ይሆን?

በቀረውስ በትካዜ"እጃችሁንም በአፋችሁ ላይ አኑሩ።" የምንልበት ደረጃ ደርሰናል::

Anonymous said...

This is to the person who said ... if marry to be free of original sin, her parents "Hana" and "Eyakem" need to be free of the original sin... Let us see this perspective:
1. The cleansing of the original sin is done through the Holy Spirit, who is "Mentsihe- a cleanser". So it is not about St. Mary, but the Holy Spirit work in preparing her to be the Mother of the Most High... Heb:10:5: Wherefore when he cometh into the world, he saith, Sacrifice and offering thou wouldest not, but a body hast thou prepared me.... This word is spoken when the Word is entering this world ( when he partake our flesh)... He said ... you prepared me a body... whose body do you think is prepared for Christ? and our salivation is not an abrupt decision by God to save the human race but a long thought salivation process .... Eph:1:4: According as he hath chosen us in him before the foundation of the world... so St. Mary's body is prepared for the salivation process from the start ...
2. Isa:1:9: Except the LORD of hosts had left unto us a very small remnant, we should have been as Sodom, and we should have been like unto Gomorrah... who is the remnant? please understand the word that "remnant" refers to" something that is left behind from what had existed before"... St. Mary is the remnant of Adam from which God partake the flesh... It is written about Christ... Heb:2:16: For verily he took not on him the nature of angels; but he took on him the seed of Abraham... therefore it is that seed of Abraham, St. Mary, from whom Christ took the flesh is called remnant... This signifies her uniqueness...
3. Lu:1:28: And the angel came in unto her, and said, Hail, thou that art highly favoured, the Lord is with thee: blessed art thou among women... he called her highly favored( full of grace).... she has got all the grace that Adam has lost when he sinned against God....
4. About St. John the Baptist, it is written... Lu:1:15: For he shall be great in the sight of the Lord, and shall drink neither wine nor strong drink; and he shall be filled with the Holy Ghost, even from his mother's womb.... Why do you get surprised if the church teaches that St.Mary is chosen from the start? The Holy Spirit is with her from the time of her conception to save her the original sin.
5. Some people quote ... Lu:1:47: And my spirit hath rejoiced in God my Saviour... and preach that she need to be saved, that is why she said my Savior... but we believe St. Mary is the second eve...Why Adam who said... Ge:3:12: And the man said, The woman whom thou gavest to be with me, she gave me of the tree, and I did eat.... called Eve... Ge:3:20: And Adam called his wife's name Eve; because she was the mother of all living.... while she had brought death? Adam called the woman with this name because he understood what God spoke about her saying... Ge:3:15: And I will put enmity between thee and the woman, and between thy seed and her seed; it shall bruise thy head, and thou shalt bruise his heel.... Here we look the Savior is going to come from the seed of a woman... She has been thought from the start to be the Mother of God... that is why the prophet David said... Psalms:46:5: God is in the midst of her; she shall not be moved: God shall help her, and that right early... St. Mary is the Second Eve and said.. Lu:1:47: And my spirit hath rejoiced in God my Saviour.For he hath regarded the low estate of his handmaiden.... speaking on behalf of Eve... even though she is a highly favored one...

Hamaressa said...

ZE TEWAHEDO....Egziabher edmewoten yarzimew!!

Hamaressa

Anonymous said...

is it useful or burning issue for our church?

Anonymous said...

I dont think so

tad said...

Is is the right time? No. But if I were Kesis Asteraye I will do everything in my power to clear my name.As a matter of fact the issue involving "original sin" is only for theology scholars consumption, it should not have been brought to the public. It is pity that we have to entertain this at this time.

Anonymous said...

DEJE SELAM, COULD YOU PLEASE TELL US HOW THE KANSAS CONVENTION WAS GOING ON YESTERDAY REGARDING TO ASTERAYE'S APPLICATION?

Anonymous said...

Abune Mekarios sent from Pop Shenoda told us that St. Mery had original sin. That is what abune Mekarios said on behalf of Egypt Coptic church in Kansas city yesterday.

orthodox unit said...

Tad, I agree with you. There some things which are not important for us. This is what theologicians should discuss. we don't need such things

Anonymous said...

"የእንጦጦ መምህር ቢናገር ባመት ያውም ሬት" የተባለበትን ምክንያት በደንብ የምታውቁ ካላችኹ አብራሩልን እባካችኹ። ታሪኩ ጥርት ብሎ ትዝ ሊለኝ ባለመቻሉ ቆጨኝ። ኾኖም ግን እንደነአባ መቃርዮስ ያለ ጳጳስ ሲያጋጥም ሊጠቀስ የሚገባው ይመስለኛል።

Anonymous said...

lelayignaw mels:-
በአጼ ምኒልክ ዘመነ መንግሥት እንጦጦ ራጉኤል ላይ ሃይማኖታቸውን ደብቀው የነበሩ አንድ ካቶሊካዊ „መምህር“ ነበሩ:: ከአንድ ዓመት በኋላ ሲያሰተምሩ የሁለት ባህርይን ካቶሊካዊ ትምህርት በማስተማራቸው ሊቃውንቱ ነገሩን እንዲህ ገለጡት፣ ኋላም ከአስተማሪነቱ አንጻር በትርጓሜ ውስጥ አስገብተውታል::

Anonymous said...

ይቅርታ እኔ የሰማኹት ግን እንዲህ አይመስለኝም። እንግዲያው እንዴት ነው የሚል ጥያቅ ቢነሣብኝስ ብየ ከወዲሁ መልስ እንዳልሰጥም ድንግዝግዝ ነገር ማውራት ስለማልወድ ነው።

Girmie said...

PRAYER OF THE ETHIOPIANS

IN EXALTATION OF THE HOLY MOTHER.


Our Holy Mother Mary! With the Words of Greeting of the Angel Saint Gabriel,
we bow to You in solemn salutation saying, “Hail, O Favoured One!” You are Virgin
both in soul and in body. Because of Your perfect chastity, You became the Mother of
the Almighty God. And so, You deserve such glorious salutation.

Your womb bore the Holy Adam who is the Sacred Fruit of the Tree of Life.
Hence, You are the Holy Eve, the Chosen and the Blessed One among all the women.

In the early times, the Prophets spoke of You as “Ethiopia stretches out Her
Hands to God”, and we addressed you as ‘Our Mother Zion’.

Rejoice, O Our Queen in Heavens and on Earth! God, through Your
instrumentality fulfilled His promise of our Salvation and granted His Eternal Covenant
of Mercy to His Creation. And so, we always praise You saying. “You are the Blessed,
full of Grace.”

In the Words of Jesus Christ, our Saviour, Priest and King, we are Your children,
committed to Your Maternal guardianship; and You are our Holy Mother, entrusted to
our spiritual dedication. Thus, we believe Your Motherhood that has never forsaken Your
beloved Son will always be with us.

We thank Our Gracious Father, God the Most High, for His Benevolence of such
magnitude. World without end, Amen.


source: www.thechurchofethiopia.com

chere said...

Keses , ! what funny guy he is . Dont answer him anything he is confused and cant hear anything. he got a small church with five members and he is syang like he is one of the EOC in America. He is not Kese he is Menafik. He's been dismissed from Kedane Miret long time ago . He has ten members who disapear from K. Miret b/c they got conflict of interst.
Dont worry guys Kansas has A popular preacher who is winning over this Yewishet Kese . A lot of members Rejoined the K. Miret church b/c of Aba Tesfa Mariam of the K. Miret. He is a great great EOC kese. Everyone can proud of him . I dont think asteraya get ground in hear in Kansas . He will get the church empty soon. Everybody is coming to our church K miret. Dont worry guys we will handel this pm. We dont let him spray his posien in our community.

Anonymous said...

Chere you wish the church to be empty let me tell you know one close GOD Church belive me "any one trying to distroy GOD Church God say I will distroy him" be wise MK.

አሐዱ said...

ሰዎች ሆይ ለምን እንሳሳታለን አሁን እየሰደብን እና እየናቅን ያለነው እመቤታችንን ሳይሆን ‹‹ፈጣሪያችንን እግዚአብሔርን›› ነው ሎቱ ስብሐት ክብር ለእርሱ ይሁንና እርሱ ዓምን ሳፈጥር ገና በእናታችን ማኅጸን ሳንሆን ያውቀናል፡፡ ስለዚህ አዳምን ሳይፈጥር እናቱን ቅድስት ድንግል ማርያምን ያውቃታል፡፡ ስለዚህ የድንግሊቱን ክብር ብንንቅ ብናቃልል እዳችንን እንቀበላለን እባካችሁ በእንግዳ ትምህርት አንወሰድ በተማርነውና በተረዳነው ነገር ጸንተን እንድንኖር ታዘናልና እንጽና ማንም እንዳያስተን እንጠንቀቅ እርሷ ‹‹ድንግል በክልኤ›› ዘላለማዊ ድንግል መርገመ ስጋ መርገመ ነፍስ የሌለባት ጽንህት በድንግልና ስርጉት በቅድስና ናት፡፡ አትሳቱ ድንግልናዋን ክብሯን አቃልላችሁ አትሙቱ፡፡
በአማላጅነቷ ትጠብቀን
ከመሐሪው ልጇ ታስታርቀን አሜን፡፡

አሐዱ

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)