August 15, 2009

የአሜሪካ ካህናትና ምእመናን ጉባዔ መግለጫ አወጣ

(ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 14/2009)
“በሰሜን አሜሪካ የኢ/ኦ/ተ/ ቤተ ክርስቲያን ካህናትና ምእመናን ጉባዔ” የሚባለውና በአሜሪካ የሚገኙ በተለምዶ “ገለልተኞች/ ገለልተኛ” የሚባሉ አብያተ ክርስቲያናትን ያቀፈው ስብስብ በቤተ ክርስቲያን አባቶች መካከል የተፈጠረውን ውዝግብ አስመልክቶ ዛሬ መግለጫ አወጣ።
“ስለ ቅድስት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ ሁኔታ ከሰሜን አሜሪካ የካህናትና ምእመናን ጉባኤ የወጣ መግለጫ” በሚል ርዕስ የተዘጋጀውና ዛሬ ለ”ደጀ ሰላም” የተላከው ባለ 5 ገጽ መግለጫ በቅዱስ ሲኖዶስና በቅዱስ ፓትርያርኩ መካከል ሕገ ቤተ ክርስቲያንን በተመለከተ የተነሣውን አለመግባባት የዳሰሰ ሲሆን መፍትሔ የሚለውንም አቅርቧል።

ብዙ አስተያየት ሰጪዎች “እነዚህ አብያተ ክርስቲያናት በአስተዳደር ችግር ምክንያት ነው የተለየነው ሲሉ ኖረው እንዴት በዚህ የቤተ ክርስቲያን የጭንቅ ወቅት ድምጻቸውን አያሰሙም” ሲሉ የነበሩ ሲሆን ምንም እንኳን በቤተ ክህነቱ ስር ባለመኖራቸው ተጽዕኖ ለማምጣት ባይችሉም ይህንን መግለጫ ማውጣታቸው ብቻ በታሪክም በሕዝብም ዘንድ ከበሬታ ያሰጣቸዋል ተብሏል።
ከዚሁ ጋር በተገናኘ ብዙ አብያተ ክርስቲያናት ለቅዱስ ሲኖዶስ ያላቸውን ወገንተኝነት በማሳየት፣ “በቅዱስ ፓትርያርኩ በመፈጸም ላይ አለ ያሉትን ሕገ ወጥ ተግባር” በመቃወም መግለጫ እያወጡ እንደሚገኙ መዘገባችን ይታወሳል።
(የመግለጫውን ሙሉ ቃል እዚህ ያንብቡ)
ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን

3 comments:

orthodox unit said...

Go on fathers, this is I the best proposal that I have seen. And this is my proposal:
1. The two synods should discuss things wisely and come in to being one
2. Administration problems have to be solved once and for all
3. The church should have modern adminstration system
4. The synod should be strong that will not be influenced by fleshly works
5.The synod has to revise cannons of the church every time
6.We should stand as one People, one Church who serve God
7.People who advocate hater, division among christians and disobdience have to get spritual treatment and if insist on their work should be separted from the church
8. The church should be lead by scholars
9. Preachers have to teach the people about the difference of dogma and traditions in order to avoid confusions among some people
10. etc..
God bless Ethiopia and its church

tad said...

Go Orthodox unit. May God bless you orthodox unit. I am with you.

Beimnet said...

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን።

እስካሁን ከቀረቡት መግለጫዎች ሁሉ ክርስትናንና የቤተክርስትያናችንን ስርአት ተመርኩዞ በማስተዋል የተዘጋጀ ሁሉንም ለመዳሰስ የሞከረ መግለጫ በመሆኑ ደስ የሚያሰኝ ነው። እንዲህ እንዳሁኑ ሁሉም በግልጽ ሳይነገርና ተቃውሞውም ሳይበረክት አስቀድመው በቤተክርስቲያን ያለውን የአስተዳደር ችግር በመረዳት፤ ችግሮቹን ከሞላ ጎደል ዘርዝረው በመግለጽ የቤተክርስቲያን ችግር እንዲታረም ከመጠየቅ አልፈው “ችግሮች እስኪፈቱ በአስተዳደር ጉዳይ በገለልትኝነት እንቆያለን” በማለት ተቃውሞአቸውን በገሃድ ያሳዩ ወገኖች በመሆናቸው ስብስቡ መልካም አባቶችና ምእመናን ያሉበት መሆኑን የሚያሳይ ነው። ይልቁንም ይህንን ጎዳና ሞክረው በየጊዜው የተፍረከረኩና በአስተዳደር ለአቡነ ጳውሎስ እጃቸውን የሰጡ አብያተክርስቲያናት በአሜሪካም በካናዳም መኖራቸውን ስናይ ዲያቆን ዳንኤል “ምላስና ልብስ” በሚል ርዕስ በጋዜጣ ባሳተመው ድንቅ ጽሑፍ አሳምሮ እንደጠቀሰው በዚህ እውነቱን እንኳን የሚናገር አባት በጠፋበት ክፉ ዘመን እንዲህ ያሉ አባቶች መኖራቸው የሚያጽናና ነው። ለአባቶች እርቅ እያደረጉ ያሉት ጥረት ከዚህ በተጨማሪ እጅግ የሚያስደስት ነው። በርትተው እንዲገፉበት አደራ ከማለት በቀር የምጨምረው የለም።
ይህንን ካልሁ በኃላ በመግለጫው ላይ ጥቂት አስተያየት ለመስጠት እፈልጋለሁ። በመግለጫው የተጠቀሱት ሁሉም ነጥቦች አንክዋር መሆናቸው አያጠያይቅም። ይሁን እንጂ ሌሎችም የሚቀሩ ነጥቦች መኖራቸው የሚታወቅ ነው። በፓትርያርኩ ላይ ከርትዕት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ጋር በተያያዘ በአለቃ አያሌውና በሌሎችም እውነተኛ አባቶች የተጠቀሱ ችግሮች፤ በቅዱስ እስጢፋኖስ ቤ/ክ በባሕታዊው ላይ የተካሄደው ግድያ፤ እርሳቸውና ሌሎችም ብዙሃን ደጋፊና ተቃዋሚ ጳጳሳት በሲኖዶሱ መንፈሳዊ ስልጣን በነበሩበት ዘመን የቤተክርስቲያን ቦታ ሳይቀር እየተነጠቀ የተስፋፉት መስጊዶችና ከዚያ ጋር ተያይዞ በቤተክርስቲያን ላይ የተጠናከረው የስነልቦና ጥቃት፤ ከየአጥቢያ አብያተክርስቲያናት ተመዝብረው በተለያዩ አለማትና በድረ-ገጽ ሳይቀር ለገበያ የበቁት መተኪያ የማይገኝላቸው የቤተክርስቲያን ቅርሶችና ንዋየ ቅድሳት ጉዳይና ሌሎችም አባቶችና መዕመናን የሚያነስዋቸው ነጥቦች ተዘርዝረው መጠቀሳቸው ተገቢ ነው። አንዳንዶቹ በማስረጃ የተጠናከሩ አይደሉም ብሎ በአስተዳደር ገለልተኛው ወገን የሚያምን ቢሆን እንክዋን መላው የኢትዮጵያ ሕዝብና ይልቁንም የቤተክርስትያናችን ምዕመን በየጊዜው ሮሮ ሲያሰማባቸው የነበሩ አሳሳቢ ጉዳዮች ስለሆኑ በገለልተኛ ወገን እንዲጣሩ መግለጫው መጠየቅ ይገባው ነበር። በጽሑፍ እንደገና ባይቻል እንክዋን አሁንም ጊዜው ስላለ እንዲታሰብበትና በተገኘው የግንኙነት መስመር ሁሉ እንዲጠቀስ በማለት ነው የግሌን ለመሰንዘር የተነሳሁት። እግዚአብሔርንና የእግዚአብሔርን ሕዝብ ያሳዘኑ ነገሮች ካሉ እነሱ በገለልተኛ ወገን ተጣርተው እልባት ሳያገኙና ያጠፋን ሁላችንም ንስሓ ሳንገባ አለባብሰን አልፈን ዛሬ ቤተክርስቲያናችን የምትፈልገው አይነት እውነተኛና ዘላቂ መፍትሔ እናገኛለን ብለን ማሰብ አስቸጋሪ ነው። ይህ “አለባብሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱ” የሚለውን የአባቶች ብሂል ያስታውሰናል። ለመልካም ውጤት ለመብቃት በመጀመሪያ ፍትኅንና እውነትን የሚወደውን እግዚአብሔርን ማስደሰት ያስፈልጋልና።

ከዚህ በተረፈ በመፍትሔ አፈላላጊነት ያቅዋቅዋማችሁት ስብስብ ከወገናዊነት፤ ከሌሎች የስጋ አስተሳሰቦችና መንግስትንም ሆነ ሌላ ወገን ከመስጋት ከሚፈጠር ሽንገላና የዲፕሎማሲ አካሄድ ርቆ በጸሎት ተወስኖ በመንፈስቅዱስ መሪነት እውነተኛ መፍትሔ እንደሚያፈላልግ እምነቴና ጸሎቴ ነው።

ወስብሓት ለእግዚአብሔር።

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)