August 11, 2009

(ልዩ ቅንብር) ንጉሴ ወ/ማርያም ትናንትና እና ዛሬ፦ “በአንድ ራስ ሁለት ምላስ”

ሊሰማና ሊደመጥ የሚገባው በድምጽ የተዘጋጀ ልዩ ቅንብር

(ደጀ ሰላም፤ ኦገስት10/2009)
የማፊያው ቡድን ድምጽ የሆነው የ“ሀገር ፍቅር” ሬዲዮ አዘጋጅ ንጉሤ የሚያምነው ነገርም ሆነ አቋም የሌለው በመሆኑ ትናንት ሲያመሰግን የነበረውን ዛሬ ይሰድባል፣ ዛሬ የሚሰድበውን ነገ ከማመስገን የሚከለክለው ምንም ነገር አይኖርም።
የሚገርመው “ግልገል አዘጋጁ” (ረዳቱ?) ዶ/ር በላይም እንዲሁ “ነጭ ውሸት” የለመደበት “ንጉስ” እያለ የሚያቆላምጠው አለቃው የምግባር አጋሩ ነው። ይህ ሬዲዮ ጣቢያ ዛሬ የተጀመረ አይደለም። ዓመታት አስቆጥሯል። የዓመታት የስድብና ሰውን የማዋረድ ልምድ ያለው “ዕውቅ” ሬዲዮ ነው። የሚሳደበው ሁሉ ጊዜ ያልከፈለውን መሆኑ ነው - ችግሩ ። ከተከፈለው ዛሬ የሚሳደበውን ነገ ሲያመሰግን ይገኛል።
ለምሳሌ፦
1. የኢትዮጵያ መንግሥት፦ ንጉሴ ትናንትና የስድብ ላንቃውን ያላቅቅበት የነበረው መንግስት ዛሬ “የምስጋና ዝናም” የሚፈስለት ሆኗል፤
2. ፓትርያርክ ጳውሎስ፦ ትናንት “አባ ዲያቢሎስ” ይላቸው እንዳልነበረ ዛሬ “ከርሳቸው በላይ ቅዱስ ተፈጥሮም አያውቅ” እያለን ነው። እንዲህ ማለቱ ባልከፋ፣ ችግሩ የቁልቢን ብር ወደ ዶላር እየተለወጠ እየተላከለትና እየበላ ማመስገኑ ነው።
ይህንን ሁሉ የምንለው ከራሳችን ፈልስፈን ሳይሆን በማስረጃ አስደግፈን “በአንድ ራስ ሁለት ምላስ” በሚል ርዕስ ኢትዮጵያውያን አዘጋጅተውት ከተወሰኑ ዓመታት በፊት የተደመጠውን ይህንን ዝግጅት እንድታዳምጡ ስንጋብዝ በደስታ ነው። አንድ ይቅርታ የምንጠይቅበት ጉዳይ በዚህ የጾም ወቅት “በዘፈን የደመቀ” ቅንብር እንድትሰሙ ማድረጋችን ነው። ነገር ግን ዝግጅቱ ካለው ጠቃሚነት አንጻር ይህንን ታግሳችሁ ትሰሙ ዘንድ በትህትና እናሳስባለን። እነሆ !!!!!
ቸር ወሬ ያሰማን
+++++
ከፍልስጣ በላይ እኩይ ፍልስጣ፦ ከመምህሩ ደቀ መዝሙሩ
(ከዘመቻ)
አጋንንት በወገን ብዙ ናቸው መንፈስ ጽርፈት፣ መንፈሰ ዝሙት፣ መንፈሰ ትዕቢት… ከአጋንንት መካከል የሰውን የእለት ተእለት ኃጢአት የሚመዘግብ እኩይ ፍልስጣ የሚባል አለ። የሀገር ፍቅር ሬዲዮ አዘጋጅ ንጉሴ እኩይ ፍልስጣን መሆን ብቻ ሳይሆን አስከንድቶታል። ከሆኑ አይቀር እንዲህ ነው። ከመምህሩ ደቀ መዝሙሩ እንዲሉ፡፡ ገንዘብ የሰውን ህሊና እንዴት እንደሚነሳ በንጉሴ ታዘብኩ። ከቅዱስ ፓትርያርኩ መቶ ሺህ ብር እንደተቀበለ ለቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በቀረበው ጥናታዊ ጽሁፍ የተገለጸ መሆኑን ንጉሴ ከሚኮንናት፣ በመላ አሜሪካ ያሉ ምእመናን ደግሞ በቀን ቢያንስ ሶስት ግዜ ከሚጎበኙዋት “ደጀ ሰላም” ላይ ገሃድ ወጥቶ ለማንበብ በቅተናል። እድሜን፣ ብርታትና ጥንካሬን ለደጀ ሰላም ያጎናጽፍልንና ንጉሴም ይህ የዘወትር ተግባሩ ስለተገለጸበት “ደጀ ሰላም”ን ያዘጋጃል ብሎ የሚጠረጥረው ማህበር ላይ (ራሱ ንጉሴ ለዘመናት ያህል እግዚብሄርን ሳይፈራ ሰውን ሳያፍር ተሸክሞት የሚኖረውን የርክሰት የኃጢአት ሸክም) ያለ እዳው ለማህበሩ ሊያሸክመው ሲቃትት አስተውለነዋል። እዚህ ላይ ዝምታ ለበግም አልበጃትም እንደተባለው ማህበሩ ባልዋለበት እንደዋለ ባልሰራው እንደሰራ ተደርጎ ከሁሉ በላይ ደግሞ በአንድ ሚዲያ ላይ የጋዜጠኝነት ስነ ምግባር ብቻ አይደለም የምንኖርባት ሀገር ህግን በጣሰ መልኩ የሚወርደውን የሥም ማጥፋትን፣ ክብር-ነክ የሆኑ አነጋገሮችን፣ የሬዲዮኑ አፍ ማሟሻ የሆነው ማህበርም ሆነ ስማቸው እየተነሳ የስም ማጥፋት ዘመቻ የተደረገባቸው ግለሰቦች ሁሉ ይህን ዋልጌ መረን የወጣ ጋዜጠኛ ተብዬ የነገር ጡቱን እያጠባ እያሳደገው ካለው ቡችላው ጋር በህግ ልትፋረዱት ይገባል። እብድን ማን ይሰማዋል ብላችሁ በቸልታ ማለፉ አግባብ አይደለም። ባለማወቅ በእብድ ውሻ የሚለከፉ መኖራቸውን አትዘንጉ።
በተለይ በቅዱስ ሲኖዶስ እውቅና አግኝቶ ለቤተ ክርስቲያኒቱ የጀርባ አጥንት ሆኖ እያገለገለ ያለውን፣ በብዙ መቶ ሺህ የሚቆጠሩ አባላቶች ያሉትን ማህበር ምንም ባልተጨበጠ ነገር “በፓትርያርኩ ላይ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላትን አነሳስቷል” በማለት ያንን ሁሉ ርግማንና ወንጀል (እኔ በምድር ላይ ያለ ኃጢአት ሁሉ የቀረ አይመስለኝም) በማህበሩ እየተፈጸመ እንደሆነ አድርጎ ሲለፍፍ ከሰደበኝ የደገመው እንዲሉ የእርሱን ስድብ እየመዘዛችሁ እንኪያ ሰላምታ ከእርሱ ጋር ፍጠሩ አይደለም እንዲሁም እንደ ቁራ ቢጮህ ማን ም አይሰማውም ተብሎም በቸልታም መታለፍ የለበትም። በእርግጥ በንጉሴ አንደበት የሚሰደቡ የጽድቅን ተግባር እየፈጸሙ ያሉ መሆናቸውን በሰማዕያኑ ግንዛቤን ቢፈጥርም ምክንያቱም ያ ከእግሩ ስር ቁጭ ብሎ ስድብ የሚቀጽለው (“ደቀ መዝሙር” ብለው የሚበዛበት መሰለኝ፤ ግዴለም እሱም አይከፋውም ቡችላው ልበለውና) እንደሚጠራው ልጥራውና “ንጉስ” የሚያወድሳቸውና በንጽህና እርካብ ላይ የሚያስቀምጣቸው ከእጃቸው በረከትን የተቀበለውን ወንጀለኞችና ሀሰተኞችን ነው። ስለዚህ ለቤተ ክርስቲያን ያበረከታችሁት አስተዋጽኦ እንደ እንጉዳይ በየገዳሙ በየአድባሩ ፍንድቅ ብሎ እየታየ ነው። ዳሩ ንጉሴ እግር አድርሶት ኢትየጵያም ቢሄድ የፓትርያርኩን ቤተ መንግስት ተሳልሞ ከመመለስ ውጭ ወደ ገዳማቱ ጎራ ብሎም የሚያውቅ አይመስለኝም። ጎራ ቢል ኖሮ ምን አልባት ህሊናውን ቆንጠጥ የሚያደርገው ነገር ይዞ ይመጣ ነበር። ግና ገንዘብ ያሳወረው ንጉሴ የሙስና አሞሌ በላሰበት ምላሱ ርኩሱን ቅዱስ ሲያደርግ፣ ቅዱሱን ደግሞ ሲያረክስ መስማት ህሊና ላለው ሰው ታግሶ መስማቱ በራሱ የኢዮብን ያህል ትእግስትን ይጠይቃል። “በሚሰድቡአችሁና በሚያሳድዱዋችሁ ግዜ ስለ እኔም እየዋሹ ክፉውን ሁሉ በሚናገሩባችሁ ግዜ ብፁዓን ናችሁ ደስ ይበላችሁ ሀሴትንም አድርጉ ዋጋችሁ በሰማያት ብዙ ነውና ከእናንተ አስቀድመው የነበሩ ነቢያትንም እንዲሁ አሳድደዋቸው ነበርና” የሚለውን የጌታን ቃል በመዘንጋት አይገባም። መልካሙን ተጋድሎ እየተጋደላችሁ ሳለ በቤተ ክርስቲያኒቱ ስም እየማለ ቤተ ክርስቲያኒቱን ለማጥፋት ከሚያሴሩት የጥፋት ኃይሎች ጋር አንድነትና ህብረት ያለው የንጉሴ ላንቃ ለስድብ ስለተከፈተ ከአላማችሁ እንደማትዛነፉ፣ እርሱንም ንቃችሁት እንደተዋችሁት በራሱ ግዜ በኖ ይጠፋል። የማህበሩ እንቅስቃሴ ከእግዚአብሄር እንጂ ከሰው አይደለም በሚል ጽኑ እምነትና በየግዜው ሰይጣን ከሚያስፈነጥረው የጥፋት ፍላጻ በእግዚአብሄር ቸርነት በእናቱ አማላጅነት ተጠባቃችሁ መኖራችሁን ተማምናችሁ እንደሆነ እገነዘባለሁ። ቢሆንም ግን ይህን ዋልጌ የህግ የበላይነት ሰፍኖ ባለበት ሀገር እየኖረ ሳይሆን የመንፈስ አባቱ የአስተዳደር ድክመት አለ ብለው የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ ጥረት ባደረጉ አባቶች ላይ አይደለም ከመንፈሳዊው መንደር ከአለማውያን መንደር እንኩዋን በማይጠበቅ መልኩ የሥድብና የመርገም መጥሀፍ አስፅፈው እንዳስበተኑና ምንም እንዳልተባሉ እርሱም እንደርሱ በገንዘብ ተገዝተው ማሩን አምርረው ወተቱን አጥቁረው የግብር አባታቸው የዲያብሎስን ስራ ተግባራዊ እንዳደረጉት ሁሉ እርሱም የአባቱን በረከት ተቀብሉዋልና በበላበት እየጮኸ ነው እርሱ ዋሽቶ ቀጥፎ መብላት ስራው ነው በመንግስት የተፈቀደለት ሳይሆን ኅሊናውን አሳምኖ የገባበት የማህበረ ቅዱሳን የስራ አመራር አባላትም የማሕበሩን ህላውና የማስጠበቅ ኃላፊነት እንዳለባችሁ አትዘንጉ ሸማ በየፈርጁ ይለበሳል እንዲሉ አበው ሁሉን በአግባቡ ልታስኬዱ ይገባል እላለሁ
ንጉሴ የአቦን ግብር የበላ ይለፈልፋል እንደሚባለው ካልሆነ እርሱን በሲኖዶስ አባላትና በቅዱስ ፓትርያርኩ መካከል በተፈጠረው አለመግባባት ምን ዶለው? በአቡነ ሳሙኤል በአቡነ ፋኑኤል በአቡነ አብርሃምስ ላይ የነገር ድሪቶውን ለመደረት ልቡናውን ያተጋው በእውነት የቤተ ክርስቲያን ፍቅር ነው ቅዱስ ፓትርያርኩንስ በእውነት ወዶ ነው ከዚህ በፊት የዲያብሎስ ታናሽ ወንድም እድርጎ ያስቀመጣቸውን ዛሬ ምን ቢያገኝ ነው? ይሄ ሳይታለም የተፈታ ነው የንጉሴ ምስ ያው ገንዘብ ነው
በአፈ ጮሌነትና በቅጥፈት የእግዚአብሄር መንግስት የሚወረስ ቢሆን ኖሮ ከምላሴ ጸጉር ይነቀል ንጉሴን የሚቀድም በወረንጦ ቢለቀም አይገኝም ግን እግዚአብሄር ፈታሄ በርትህ ኮናኔ በጽድቅ ነውና ለሁሉም እንደየስራው ይከፍላል መንፈሰ ጽርፈት ያደረብህ አንተ ንጉሴም የምትዘብትበት አምላክ ከላይ ሆኖ እየታዘበህ ነውና አንድ ቀን የስራህን ይከፍልሃል ህሊናህ እያወቀው እውነትን ትቢያ አልብሰህ ሀሰትን ለማንገስ እየጣርህ ያለህ በመሆኑ የዲያብሎስ የግብር ልጅ መሆነህን አረጋግጠሃል በእርግጥ ሰው ሁሉ ማንነትህን አውቆት አንቅሮ የተፋህ ስለሆነ ጩኸትህ ሁሉ የተስፋ መቁረጥ ጩኸት ነው:: ወደ ህሊናህ ተመለስ አለበለዚያ የቤተ ክርስቲያን አምላክ ይመጣብሃል::
+++++++++++++++++++++
(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 22/2009)
ምላስህ ለሰላው ለሀገር ጠላቱ፣
ይደረስህ ጦማሬ ለንጉሴ ከንቱ።
ዛሬ ደግሞ መጣህ አብረህ ከጳውሊ፣
አበው ሲተርቱ አህያ ካመዱ፣
ሞስሰው ተገኙ ጳውሊ ከንጉሱ።


ድሮውንስ ቢሆን ገና ከጅምሩ፣
ያፈረሰ ዲያቆን ኮቶሊክ ባትርያርክ፣
ስምምነት ደርሰው ውሸትን ለመስበክ፣
ጳውሊም አሰናድቶ መቶ ሺ ብር ወረት፣
አትርፎ ለመምጣት ንጉሴ ሲዋትት፣
ሊያፈርሰው ጀመረ የቅዱሳንን በዓት፣
ገበያውም ደርቷል ዲሲ-ቤተ ክ’ነት።

ይሉኝታ የላቸው ፈጣሪን አይፈሩ፣
አንደበታቸው መርዝ ቀና አይናገሩ፣
ወይ ዘይት የላቸው መብራት አያበሩ፣
ጨለማ ሆነዋል በብርሃን እየኖሩ።

ምዕመናን እንንቃ ጊዜው የሥራ ነው፣
ቤታችን ፈት ናት ጠባቂው ጳውሊ ነው።
ያሬድ ቄሰ ገበዝ ሰባኪው ንጉሴ፣
ተስፋ እንዳንጠብቅ ከነዚህ ሕዳሴ።

ጊዜው ሳይመሽብን ለሥራ እንነሳ፣
ጸሎትን እንጨምር በጾምም እንበርታ፣
ከሰማይ መልስ አለ በቃሉ ለፀና፣
ተዋሕዶ ንጽሕት ታብባለች ገና።
(ስንታየሁ ከሰሜን አሜሪካ)
Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)