August 5, 2009

“ደጀ-ሰላም” አዲስ የሃይማኖት ጡመራ ፈር መቅደዷ ተዘገበ

(ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 5/2009)፦ “ደጀ-ሰላም” በሃይማኖት ላይ ብቻ በማትኮሯ አዲስ የጡመራ ፈር መቅደዷን አንድ የአማርኛ ተወዳጅ ጋዜጣ ዘገበ፤ የአዘጋጆቹ ማንነት ደግሞ እያወዛገበመሆኑን መሰከረ። “አዲስ ነገር” የተባለው ታዋቂ የአዲስ አበባ ጋዜጣ በቅዳሜ ኦገስት 1/2009 እትሙ “የሃይማኖት ብሎጎች ዳዴ” በሚል ርእስ ባወጣው ዘገባ “ደጀ ሰላም” የጡመራውን መስመር በአንባቢ ብዛት በመምራት ላይ እንደምትገኝ ገልጿል።

በቅርቡ በቤተ ክህነቱ በተፈጠረው ግርግር የአንባቢ ብዛቷ ከፍ እንዳለላት የተለያዩ አንባቢ መቆጣጠሪያ ዘዴዎችን አጥንቶ የዘገበው “አዲስ ነገር” ጋዜጣ ከሌሎች ኢትዮጵያዊ የእምነት ድርጅቶች ጋር (ለምሳሌ እስልምናና ፕሮቴስታንቲዝም) ሲነጻጸር ግን የአንባቢዋ ቁጥር አሁንም አነስተኛ መሆኑን አስቀምጧል። ጋዜጣው “ደጀ ሰላም” ለብሎጊንግ የሰጠቻቸውን ስሞች ተውሶ “ጡመራ፣ መጦመር” እያለ ዘገባውን ያቀረበ መሆኑም ታውቋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በኢትዮጵያ ባለው “የብሎጊንግ ወይም የጡመራ ግርዶሽ” (Blog Blocking የሚለውን ሐሳብ ለመግለጥ ፈልገን ነው) ምክንያት በኢትዮጵያ በቀላሉ የማትነበበው “ደጀ ሰላም” በቤተ ክህነቱ ዘንድ ታዋቂ መሆኗን የዘገበው “አዲስ ነገር” የአዘጋጆቹን ማንነት ለማወቅ ጉጉት እንዳለ ገልጿል። በስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ የቅርብ እትሙ “አትወክለኝም” በማለት መግለጫ የሰጠውን ማህበረ ቅዱሳንንም በማስረጃነት ማንሳቱ ታውቋል።
ከዚህ በፊት ቅዱስ ፓትርያርኩና ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ስለ “ደጀ ሰላም” አንስተው መናገራቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)