August 31, 2009

የማፊያው ቡድን አባል በአሜሪካ

(ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 31/2009)፦ የማፊያው ቡድን አባል የሆነ አባ ኃ/ሚካኤል ወ/ተ/ሃይማኖት የተባለ መነኩሴ ከቡድኑ ልሳን ከሆነው ከንጉሴ ወ/ማርያም ጋር በማበር አዲስ የጥቃት ዘመቻ ጀምሯል። ጥቃቱ ለጊዜው ያነጣጠረው በማኀበረ ቅዱሳን ላይ ሲሆን መነኩሴው ከኢትዮጵያ ይዤ መጣኋቸው በሚላቸው “መረጃዎች” ሕዝቡን ለማሳመን ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል። የመኑሴው ዓላማ ማኀበረ ቅዱሳንን ብቻ ማጥቃት ላይ እንዳልሆነ በግልጽ ተናግሯል። በተለይም ግልጽ መግለጫ በማውጣት ቅዱስ ሲኖዶስ የበላይ፣ ቅዱስ ፓትርያርኩ ደግሞ ተጠሪነታቸው ለቅ/ሲኖዶስ መሆኑን ያስረዱት ብፁዕ አቡነ አብርሃምም የጥቃቱ ዒላማ ናቸው።
ሁለት “ደጀ ሰላማውያን” አድማሱና ተክለ-እስጢፋኖስ የጻፉት ጽሑፍና ያቀረቧቸው ጥያቄዎች ለሌሎቻችን መልካም በመሆናቸው እዚህ ለጥፈናቸዋል።

admasu said...
I am writing this mail to the monk who appeared as an insider to 'teklay bete kihinet' and a researcher about the ‘satanic acts of MK’ on Ato Negussie's radio show. If by any chance you read this message, I wish I got answers for the following simple questions;
1. If you are really now in 'America', where is your exact location? Or to be more precise; where are you serving the church now? Who sends you to the US? Is it the Holy Synod or the Holy Patriarch? What is the purpose of your trip? At what capacity are you serving now? Are you still the head of the department? Do you contact any of the members of the Holy Synod residing in North America? Do any of them share your assertions about the church? I am asking these because I believe you are zealous to the church's hierarchy and obedient to its rules.
2. You mentioned that someone from the MK was before the court for libeling a church father. Who was the plaintiff in the case? Did he try to resolve the dispute in other way before he took it to the court? And most importantly what was the verdict?
3. Finally I heard you saying “these bandits of MK deceived the youth from the truth by telling ‘teret teret’ instead of the true Gospel of the Lord.” I think here is the real difference between you and the MK. Can you please tell us some of the ‘terets’ MK teaches the youth?

My brothers and sisters, it is not my intention to divert your attention from the ‘current issue’ but I believe this discussion is part of the church’s problem in two grounds; one, there are a group of people who want to use this forum to deceive participants from the truth and spread their hearsays and by mentioning MK negatively here and there they are trying to hit two birds with a single stone. Two, if we cautiously follow what they are saying and writing we can figure out who these people are and what they really want from our beloved church.
Let’s try to purify our hearts from hatred, since hatred has never been a solution except perpetuating hatred.
God Bless all of us.
Admasu
August 30, 2009
tekle stephnos said...
የተወደድክ አድማሱ፦

የመነኩሴው ክስ እኔንም ግራ አጋብቶኛል። መነኩሴው እዚህ ስለመሆናቸው ምንም ማረጋገጫ የለም። የምናውቀው ሃቅ ግን አለ፤ይሄውም

፩ በርግጥ መነኩሴው እዚህ ካሉ ለዚሁ ተልኮ ሲሉ በአባ ሠረቀ አስተባባሪነት ከቅዱስ ሲኖዶስ እውቅና ውጭ በቅርስ ዘራፊው እና በቤተ-ክህነቱ ማፊያ ቡድን የተላኩ እዚህ በሃገረ አሜሪካ ያለውን የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኝ አሁን ከምንገኝበት የተበላሸ ውጥንቅጡ የወጣ አስተዳደር ለማስተካከል እያደረግ ያለውን መንፈሳዊ ውጊያ ለመበታተን የተላኩ አጭበርባሪ ናቸው። ምክንያቱም ተልኳቸው ይህ ባይሆንማ ኖሮ የቢሯቸው መዝገብ (docment)ይዞ እዚህ ድረስ የሚያስመጣቸው ነገር አይታየኝም።

፪ኛው ደግሞ አማኙ ህዝብ ማስተዋል ያለብን መነኩሴው ካነጋገራቸው መረዳት እንደምንቸለው እዚህ እያገለገሉ ያሉት በእናት ቤተ-ክርስቲያን ስር ባለች ቤተ-ክርስቲያን ውስጥ ካሉን በኋላ ነገር ግን ከሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ከብአቡነ አብርሃም ትዕዛዝ አንደማይቀበሉ እና እንዳልተቀበሉት ነግረውናል። የቤተ-ክርስትያኒቷም ችግር ይሄው የበላይ የሰጠውን መመሪያ እታች ያለው ተቀብሎ አለመፈሠም። መነኩሲው በእብሪት የነገሩን አለመታዘዛቸውን ነው። እነዚህን ተባዮች ነው እንግዲህ መላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኝ ውጊያ የገጠመው። አንድዬ ይርዳን።

August 26, 2009

አቡነ ሳሙኤል በቤተ ክህነቱ ጉዳይ “የተወሰነ የመንግሥት ኃይል ጣልቃ መግባቱን” ወቀሱ

(ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 26/2009)፦ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል በቅዱስ ሲኖዶስና በቅዱስ ፓትርያርኩ መካከል በተነሣውና አሁን ለጊዜው በበረደው እሰጥ አገባ የተወሰነ የመንግሥት ኃይል ጣልቃ መግባቱን በመግለጽ ድርጊቱን መኮነናቸው ተሰማ።

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ፓትርያርኩ ረዳት የነበሩትና በፓትርያርኩ እግድ ተጥሎባቸው ቤታቸው ዘግተው የተቀመጡት ሊቀ ጳጳሱ ባለፈው ሳምንት ድምጻቸውን ከነጋድራስ ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ባሰሙበት ወቅት እንደተናገሩት መንግሥት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አልገባም የሚል ፖሊሲ ቢኖረውም ከመንግሥቱ ወገን የሆኑ የተወሰኑ ክፍሎች ግን ታልቃ በመግባት መንቀሳቀሳቸውን ተናግረዋል።

ብፁዕነታቸው ከሀገረ ስብከታቸውና ከሥራቸው እስከ ጥቅምት የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ድረስ የታገዱ ሲሆን መታገዳቸውና የብፁዓን አባቶች ቤተ መሰባበርና የጥቃት ሰለባ መሆንም ከእንቅስቃሴያቸው እንደማይገድባቸው ተናግረዋል። ጉዳዩ ለብዙ ዘመናት “ታፍኖ ቆየ ነገር ስለሆነ መፍትሔ ለመስጠት ችግር መፍጠሩ አይቀርም እንዳሉ የተጠቀሰው ሊቀ ጳጳሱ “አንዳንድ ለሆዳቸው ያደሩ” ሰዎች፣ በቅርስ ሽያጭና ዝርፊያ የሚተባበሩ በሙሉ ችግሩን በማወሳሰብ ላይ ይገኛሉ ማለታቸው ተሰምቷል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የቅዱስ ፓትርያርኩ አስተዳደር መበላሸትን በመቃወሙ ሒደት ግንባር ቀደም የሆኑት ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ከሚኖሩበት ከቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ግቢ እንዲወጡ ግፊት እየተደረገባቸው መሆኑን ምንጮቻችን ገለፁ። ከኮሌጁ ወጥተው ወደ ቤተ ክህነት ግቢ እንዲገቡ ግፊት እየተደረገባቸው ያሉት እኒሁ አባት ወደ ቤተ ክህነት የመግባት ፍላጎት እንደሌላቸው አሳውቀዋል ተብሏል። ያልፈለጉበት ምክንያት የማፊያው ቡድን የጥቃት ሰለባ ላለመሆን ፈርተው ይሆናል ተብሏል።

August 24, 2009

ወደ ቅዱስ ሲኖዶስ የሚላክ የምእመናን ፔቲሽን ዝግጅት

(ደጀ ሰላም፣ ኦገስት 24/2009): ደጀ ሰላማውያን በሆኑት በ“ዳን እና ተዋሕዶ” አሳሳቢነት፣ በደጀ ሰላም ደጋፊነት፣ አንድ ፔቲሽን ተዘጋጅቶ እንዲላክ ሐሳብ ቀርቧል። ይህ ፔቲሽን በምን በምን ዙሪያ ማተኮር እንደሚገባውና ማን እንደሚያዘጋጀው የምንነጋገርበት ሆኖ ፔቲሽኑ በተወሰኑ ሰዎች ተዘጋጅቶ ሁላችንም ሐሳባችንን “አዋጥተን” አርመነው የሚላክ ይሆናል። ዝግጅቱን በተገቢው ጊዜ ለማድረስ ቢበዛ የ30 ቀን ዕድሜ ያለን ሲሆን በማድረሱ በኩል ደጀ ሰላምና ሌሎች ፈቃደኛ ደጀ-ሰላማውያን ይተባበራሉ።

ለመነሻ ያህል ፔቲሽኑን “ዳን እና ተዋሕዶ” በአማርኛ አዘጋጅተው እንዲያቀርቡልን ደጀ-ሰላም ሐሳብ ትሰጣለች። ልታግዟቸው የምትፈልጉ ትጨመራላችሁ ሌሎች ፈቃደኞች ደግሞ በጥሩ እንግሊዝኛ ከሽነው እንዲያቀርቡልን ይለመናሉ። ከዚያ በኋላ “የምእመናን ድምጽ” ነውና ሁሉም “እንዲፈርምበት” በድረ-ገጽ ላይ ይለቀቃል። ያንን ይዘን ለቅዱስ ሲኖዶስና ለአባላቱ ብፁዓን አባቶች እናቀርባለን ማለት ነው።

August 16, 2009

የቅዱስ ሲኖዶስ ሥራ አስፈጻሚ ሥራውን እንዲቀጥል፣ የተሰጠውን ኃላፊነት እንዲወጣ፣ እኛም የበኩላችንን እናድርግ

ደጀ ሰላም “እነዚህን አበው በስልክም በሰውም ማግኘትና ማነጋገር አለብን፣ ‘አይዟችሁ፣ በርቱ’ ማለት አለብን” ብላ ታምናለች!!!

(ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 16/2009) ያለፈው የቅ/ሲኖዶስ ስብሰባ ለጥቅምት ካደረ ወዲህ አጀንዳው መቀዝቀዝ የጀመረ ይመስላል። አንዳንዶች ተስፋ በመቁረጥ፣ አባቶች ላይም ጥርጣሬያቸውን በማስፋት እንዲያውም የሃይማኖቱን ነገር ችላ እስከማለት ደርሰዋል ይባላል። የማፊያው ቡድን ብቻ የያዘውን ይዞ “ጥቅምት እንዳትመጣ ባይጸልዪም” ያኔም ቢሆን ጥቅሙን ሳያስነካ፣ ወንበሩን ሳያስደፍር፣ ዝርፊያውን ለመቀጠል ቀንተሌት እየሠራ ነው። ሕብረትም አለው። ሕብረት የሌለውና አሰባሳቢ ያጣው ለቤተ ክርስቲያን የሚያስበው ወገን ነው። ከዚያውም ቢሆን አንዳንዱ “የአባቶችን ገመና አትግለጡ” እያለ ስለ ማፊያው ቡድን እንዳይወራ በጥቅሳጥቅስ ያስፈራራል። ሌላው ደግሞ እኔን ካልነኩኝ እግዜር በፈቀደው ቀን ይፍታው ብሎ መሽጓል። አንዳንዱ ደግሞ ሲያመቸው ከመዘመርና “ሆ” ከማለት ውጪ ነገሩንም ከመጀመሪያው አልሰማውም።

ይህንን ጽሑፍ ለመጻፍ ያነሣሣን ምክንያቱ ግን ቅዱስ ሲኖዶስ የመረጠውና ሰባት ብፁዓን አባቶች ያቀፈው የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሥራውን የማቆሙ ጉዳይ ነው። ቅዱስ ፓትርያርኩ እንደተናገሩት አንዳንድ የኮሚቴው አባላት የሆኑ አባቶች ራሳቸውን ከኮሚቴው ማግለላቸውን ተናግረዋል። አንዳንዶችም “አንሠራም” ባይሉም እየሠሩ አይደለም። በጠቅላላው ኮሚቴው ማንም “ፈርሰሃል፣ ተበትነሃል” ሳይለው በራሱ ጊዜ እየፈረሰ ነው ወይም ፈርሷል። የቅዱስ ሲኖዶስን እንቅስቃሴ የሚጠላው ክፍል የሚፈልገው ይኽንን ነበር፤ እየሆነለት ነው። እና ሁላችንም እንዲህ ቁጭ ብለን ጥቅምት ትድረስ?
ደጀ ሰላም አንድ ሐሳብ ለመጠቆም ትፈልጋለች። የዚህ ኮሚቴ አባላት ሆኑ አባቶች የተሰጣቸውን ሥራ ሳይሠሩ ማለፍ እንደሌለባቸው ማሳሰብ አለብን ብላ ታምናለች። በርግጥ የነዚህ ብፁዓን አበው ሕይወት አደጋ ላይ መውደቁን ባለፈው ተመልክተናል። ከዚህ በኋላም እንዲህ ዓይነቱ አደጋ እንደማይደርስ ማረጋገጫ መስጠት ባይቻልም መንግሥት ግን ዝም ብሎ ያያል ብላ አታምንም ደጀ ሰላም። አሁን ውይይቱ “መንግሥት ይጠብቃቸዋል ወይስ አይጠብቃቸውም?” የሚል ጉንጭ አልፋ ክርክር ሳይሆን መንግሥት ጠበቃቸውም አልጠበቃቸው አባቶቻችን ግን የጀመሩትን ሥራ አንድ ደረጃ ማስኬድና ለወከላቸው ቅዱስ ሲኖዶስ መልሱን ማቅረብ አለባቸው እንጂ ጥቅምት ላይ ሲገናኙ “ችግር ስለገጠመን ሳንሠራው ቀረን” ማለት ያለባቸው አይመስላትም-ደጀ ሰላም። ለታሪክም ጥሩ አይደለም። በር ሰባሪ ሥራ እንዳይሠራ ማድረግ ከቻለ ነገር ተበላሸ ማለት ነው።
ስለዚህ እነዚህን አበው በስልክም በሰውም ማግኘትና ማነጋገር አለብን፣ “አይዟችሁ፣ በርቱ” ማለት አለብን ብላ ታምናለች -ደጀ ሰላም!!! የኮሚቴው አባላት አባቶች የሚከተሉት ናቸው።
1. ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ (የኮሚቴው ሊቀመንበር)፣
2. ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል (የኮሚቴው ፀሐፊ)፣
3. ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ (አባል)፣
4. ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ (አባል)፣
5. ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ (አባል)፣
6. ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል (አባል)፣
7. ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ (አባል) (ደሴ ላይ ባለው ችግር ምክንያት ከመጀመሪያውኑ በኮሚቴው ውስጥ አልተሳተፉም) ናቸው።
ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን

August 15, 2009

አንድ የኢ/ኦ/ተ/ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ስለ ነገረ ሃይማኖት ወደ ኮፕት ቤተ ክርስቲያን ማመልከቻ አስገባች

(የመግለጫውን ሙሉ ቃል እዚህ ያንብቡ)
(ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 14/2009) በካንሳስ ሲቲ ካንሳስ የምትገኘዉ "የደብረሣህል መድኀኒአለም" የኢ/ኦ/ተ/ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን በነገረ ሃይማኖት ምክንያት ያላትን ጥያቄ ወደ ኮፕት ቤተ ክርስቲያን ማመልከቻ ማስገባቷን፣ ማመልከቻውም መልስ ይዞ በመምጣቱ ስብሰባ መጥራቷን አስታወቀች።

“የዛሬ አምስት ዓመት በከተማችን በካንሳስ ሲቲ ካንሳስ በምትገኘዉ በደብረብርሃን ኪዳነምህረት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ/ክ እመቤታችን ቅድሰት ድንግል ማርያምን አሰመልክቶ ስለ ጥንተ አብሶ (Originl Sin) ተነስቶ በነበረዉ የሃይማኖት ዉዝግብ ምክንያት ቤተክርስቲያን ለሁለት መከፈሉ ይታወሳል። በወቅቱ የሰሜን አሜሪካ ሐገረስብከት ሊቀጳጳስ የነበሩት ብፁእ አቡነ ማቲያሰ በደብራችን ተገኝተዉ የወሰኑትን ዉሳኔ ሙሉ በሙሉ በመቃወም ዛሬ ደብረሣህል መድኀኒአለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርሰቲያንን የመሰረቱት ምእመናን ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ/ክ ቅዱስ ሲኖዶስ፥ ለቅዱስ ፓትርያርኩ አቡነ ጳዉሎስ እና ለሊቃዉንት ጉባኤዉ የሚከተሉትን ዐበይት ጉዳዮች ተመልክተዉ ለተወሰነው ዉሳኔ ማረሚያ አልያም በማሰረጃ የተደገፈ ማብራሪያ እንዲሰጡን በተደጋጋሚ አሰከቅርብ ጊዜ ድረስ ያለምንም ዉጤት በፍጹም ትህትና ስንጠይቅ ቆይተናል” የሚለው ይኸው የቤተ ክርስቲያኒቱ መግለጫ “፩ኛ አሀት አብያተ ክርሰቲያናትና መላው የዓለም የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያናት የሚያወግዙትን (Immaculate Conception) በመባል የሚታወቀዉን የካቶሊክ እምነት እንዴትና ለምን ቅድስት ቤተክርስቲያናችን ተቀበለች? ፪ኛ በአባታችን በቀሲስ አስተርዓየ ጽጌ ላይ የተፈጸመዉ ግፍ፥ ሰህተት እንደሆነና ጉዳዩ በድጋሚ ታይቶ መፍትሄ እንዲያገኝ” ፈልገው እንደነበር ያብራራል።

“ተስፋ ባለመቁረጥ ከዛሬ ነገ መልስ እናገኛለን ስንል ጊዜ ጊዜን እየወለደ አምስት አመት አለፈ፡፡ ሆኖም ሃይማኖት ነዉና እግዚአብሔርን ተስፋ በማድረግ ጩኸታችንን ወደ አሀት አብያተክርስቲያናት በማዞር ለግብፅ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ/ክ ቅዱስ ሲኖዶስ እና ቅዱስ ፓትርያርክ ፖፕ ሽኑዳ ፫ኛ ጉዳዩን ገልጸን በማስረዳት ነገረ ሃይማኖቱን በተመለከተ መልስ እንዲሰጡን በጽሑፍ በጠየቅነዉ መሰረት የግብፅ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ/ክ ሊቀ ጳጳስ ብፁእ አቡነ መቃርዮስ በ august 15, 2009 from 2:00 - 5:00pm በግብጽ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ/ክ ተገኝተን ከቅዱስ ፓትርያርክ ፖፕ ሽኑዳ ፫ኛ የተሰጠዉን መልስና በሊቀ ጳጳሱ የሚሰጠዉን ትምህርትና ቡራኬ ለመቀበል ማንኛዉም ጉዳዩ የሚመለከተዉና የሚያሳስበዉ ሰዉ በሙሉ ተገኝቶ እንዲሰማና ጥያቄም ካለዉ እንዲጠይቅ በትህትና መጋበዙን ለአካባቢዉ ህዝብ እንድናሳዉቅ በተጠየቅነዉ መሰረት ይህን የስብሰባ ጥሪ አቅርበናል” ሲል ደብዳቤው ያብራራል።

ስብሰባው ነገ ቅዳሜ እንደሚካሄድም ተብራርቷል። በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የቅርብ ጊዜ ታሪክ አንድ የኢትዮጵያ አጥቢያ በነገረ ሃይማኖት ምክንያት እንደ ጥንቱ ወደ እስክንድርያ ቤተ ክርስቲአን ጥያቄ ሲያቀርብ የካንሳስ ቤተ ክርስቲያን የመጀመሪያዋ ትሆናለች ማለት ነው።

የአሜሪካ ካህናትና ምእመናን ጉባዔ መግለጫ አወጣ

(ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 14/2009)
“በሰሜን አሜሪካ የኢ/ኦ/ተ/ ቤተ ክርስቲያን ካህናትና ምእመናን ጉባዔ” የሚባለውና በአሜሪካ የሚገኙ በተለምዶ “ገለልተኞች/ ገለልተኛ” የሚባሉ አብያተ ክርስቲያናትን ያቀፈው ስብስብ በቤተ ክርስቲያን አባቶች መካከል የተፈጠረውን ውዝግብ አስመልክቶ ዛሬ መግለጫ አወጣ።
“ስለ ቅድስት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ ሁኔታ ከሰሜን አሜሪካ የካህናትና ምእመናን ጉባኤ የወጣ መግለጫ” በሚል ርዕስ የተዘጋጀውና ዛሬ ለ”ደጀ ሰላም” የተላከው ባለ 5 ገጽ መግለጫ በቅዱስ ሲኖዶስና በቅዱስ ፓትርያርኩ መካከል ሕገ ቤተ ክርስቲያንን በተመለከተ የተነሣውን አለመግባባት የዳሰሰ ሲሆን መፍትሔ የሚለውንም አቅርቧል።

ብዙ አስተያየት ሰጪዎች “እነዚህ አብያተ ክርስቲያናት በአስተዳደር ችግር ምክንያት ነው የተለየነው ሲሉ ኖረው እንዴት በዚህ የቤተ ክርስቲያን የጭንቅ ወቅት ድምጻቸውን አያሰሙም” ሲሉ የነበሩ ሲሆን ምንም እንኳን በቤተ ክህነቱ ስር ባለመኖራቸው ተጽዕኖ ለማምጣት ባይችሉም ይህንን መግለጫ ማውጣታቸው ብቻ በታሪክም በሕዝብም ዘንድ ከበሬታ ያሰጣቸዋል ተብሏል።
ከዚሁ ጋር በተገናኘ ብዙ አብያተ ክርስቲያናት ለቅዱስ ሲኖዶስ ያላቸውን ወገንተኝነት በማሳየት፣ “በቅዱስ ፓትርያርኩ በመፈጸም ላይ አለ ያሉትን ሕገ ወጥ ተግባር” በመቃወም መግለጫ እያወጡ እንደሚገኙ መዘገባችን ይታወሳል።
(የመግለጫውን ሙሉ ቃል እዚህ ያንብቡ)
ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን

August 12, 2009

Bravo "Ben": Of course You reported, we judged!


(Deje Selam; August 11/2009): The popular Ethiopian website EthiopiaFirst confirmed today the incarceration of Abba Enqubaherey, patriarch aid. We applaud Ben for this update. As we said, we have nothing against fellow website or for that matter "journalist". Ben cleaned himself from the guilt of Nigussie and the likes. We, on the part of Deje Selam, would like to make clear that our aim is not defaming christians but safe guarding the sanctity of our holy, apostolic Church.

In this regard, we appreciate Ben's initiative to validate news about our esteemed fathers. May be, when Ben gets to know what is really going on in our Church quite for some time now, he will take side with the Church not people. As Ben said, to quote him, "he reported, we judged" and this time, he reported well and we judged well.
(Listen Ben's Interview HERE)

August 11, 2009

(ልዩ ቅንብር) ንጉሴ ወ/ማርያም ትናንትና እና ዛሬ፦ “በአንድ ራስ ሁለት ምላስ”

ሊሰማና ሊደመጥ የሚገባው በድምጽ የተዘጋጀ ልዩ ቅንብር

(ደጀ ሰላም፤ ኦገስት10/2009)
የማፊያው ቡድን ድምጽ የሆነው የ“ሀገር ፍቅር” ሬዲዮ አዘጋጅ ንጉሤ የሚያምነው ነገርም ሆነ አቋም የሌለው በመሆኑ ትናንት ሲያመሰግን የነበረውን ዛሬ ይሰድባል፣ ዛሬ የሚሰድበውን ነገ ከማመስገን የሚከለክለው ምንም ነገር አይኖርም።
የሚገርመው “ግልገል አዘጋጁ” (ረዳቱ?) ዶ/ር በላይም እንዲሁ “ነጭ ውሸት” የለመደበት “ንጉስ” እያለ የሚያቆላምጠው አለቃው የምግባር አጋሩ ነው። ይህ ሬዲዮ ጣቢያ ዛሬ የተጀመረ አይደለም። ዓመታት አስቆጥሯል። የዓመታት የስድብና ሰውን የማዋረድ ልምድ ያለው “ዕውቅ” ሬዲዮ ነው። የሚሳደበው ሁሉ ጊዜ ያልከፈለውን መሆኑ ነው - ችግሩ ። ከተከፈለው ዛሬ የሚሳደበውን ነገ ሲያመሰግን ይገኛል።
ለምሳሌ፦
1. የኢትዮጵያ መንግሥት፦ ንጉሴ ትናንትና የስድብ ላንቃውን ያላቅቅበት የነበረው መንግስት ዛሬ “የምስጋና ዝናም” የሚፈስለት ሆኗል፤
2. ፓትርያርክ ጳውሎስ፦ ትናንት “አባ ዲያቢሎስ” ይላቸው እንዳልነበረ ዛሬ “ከርሳቸው በላይ ቅዱስ ተፈጥሮም አያውቅ” እያለን ነው። እንዲህ ማለቱ ባልከፋ፣ ችግሩ የቁልቢን ብር ወደ ዶላር እየተለወጠ እየተላከለትና እየበላ ማመስገኑ ነው።
ይህንን ሁሉ የምንለው ከራሳችን ፈልስፈን ሳይሆን በማስረጃ አስደግፈን “በአንድ ራስ ሁለት ምላስ” በሚል ርዕስ ኢትዮጵያውያን አዘጋጅተውት ከተወሰኑ ዓመታት በፊት የተደመጠውን ይህንን ዝግጅት እንድታዳምጡ ስንጋብዝ በደስታ ነው። አንድ ይቅርታ የምንጠይቅበት ጉዳይ በዚህ የጾም ወቅት “በዘፈን የደመቀ” ቅንብር እንድትሰሙ ማድረጋችን ነው። ነገር ግን ዝግጅቱ ካለው ጠቃሚነት አንጻር ይህንን ታግሳችሁ ትሰሙ ዘንድ በትህትና እናሳስባለን። እነሆ !!!!!
ቸር ወሬ ያሰማን
+++++
ከፍልስጣ በላይ እኩይ ፍልስጣ፦ ከመምህሩ ደቀ መዝሙሩ
(ከዘመቻ)
አጋንንት በወገን ብዙ ናቸው መንፈስ ጽርፈት፣ መንፈሰ ዝሙት፣ መንፈሰ ትዕቢት… ከአጋንንት መካከል የሰውን የእለት ተእለት ኃጢአት የሚመዘግብ እኩይ ፍልስጣ የሚባል አለ። የሀገር ፍቅር ሬዲዮ አዘጋጅ ንጉሴ እኩይ ፍልስጣን መሆን ብቻ ሳይሆን አስከንድቶታል። ከሆኑ አይቀር እንዲህ ነው። ከመምህሩ ደቀ መዝሙሩ እንዲሉ፡፡ ገንዘብ የሰውን ህሊና እንዴት እንደሚነሳ በንጉሴ ታዘብኩ። ከቅዱስ ፓትርያርኩ መቶ ሺህ ብር እንደተቀበለ ለቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በቀረበው ጥናታዊ ጽሁፍ የተገለጸ መሆኑን ንጉሴ ከሚኮንናት፣ በመላ አሜሪካ ያሉ ምእመናን ደግሞ በቀን ቢያንስ ሶስት ግዜ ከሚጎበኙዋት “ደጀ ሰላም” ላይ ገሃድ ወጥቶ ለማንበብ በቅተናል። እድሜን፣ ብርታትና ጥንካሬን ለደጀ ሰላም ያጎናጽፍልንና ንጉሴም ይህ የዘወትር ተግባሩ ስለተገለጸበት “ደጀ ሰላም”ን ያዘጋጃል ብሎ የሚጠረጥረው ማህበር ላይ (ራሱ ንጉሴ ለዘመናት ያህል እግዚብሄርን ሳይፈራ ሰውን ሳያፍር ተሸክሞት የሚኖረውን የርክሰት የኃጢአት ሸክም) ያለ እዳው ለማህበሩ ሊያሸክመው ሲቃትት አስተውለነዋል። እዚህ ላይ ዝምታ ለበግም አልበጃትም እንደተባለው ማህበሩ ባልዋለበት እንደዋለ ባልሰራው እንደሰራ ተደርጎ ከሁሉ በላይ ደግሞ በአንድ ሚዲያ ላይ የጋዜጠኝነት ስነ ምግባር ብቻ አይደለም የምንኖርባት ሀገር ህግን በጣሰ መልኩ የሚወርደውን የሥም ማጥፋትን፣ ክብር-ነክ የሆኑ አነጋገሮችን፣ የሬዲዮኑ አፍ ማሟሻ የሆነው ማህበርም ሆነ ስማቸው እየተነሳ የስም ማጥፋት ዘመቻ የተደረገባቸው ግለሰቦች ሁሉ ይህን ዋልጌ መረን የወጣ ጋዜጠኛ ተብዬ የነገር ጡቱን እያጠባ እያሳደገው ካለው ቡችላው ጋር በህግ ልትፋረዱት ይገባል። እብድን ማን ይሰማዋል ብላችሁ በቸልታ ማለፉ አግባብ አይደለም። ባለማወቅ በእብድ ውሻ የሚለከፉ መኖራቸውን አትዘንጉ።
በተለይ በቅዱስ ሲኖዶስ እውቅና አግኝቶ ለቤተ ክርስቲያኒቱ የጀርባ አጥንት ሆኖ እያገለገለ ያለውን፣ በብዙ መቶ ሺህ የሚቆጠሩ አባላቶች ያሉትን ማህበር ምንም ባልተጨበጠ ነገር “በፓትርያርኩ ላይ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላትን አነሳስቷል” በማለት ያንን ሁሉ ርግማንና ወንጀል (እኔ በምድር ላይ ያለ ኃጢአት ሁሉ የቀረ አይመስለኝም) በማህበሩ እየተፈጸመ እንደሆነ አድርጎ ሲለፍፍ ከሰደበኝ የደገመው እንዲሉ የእርሱን ስድብ እየመዘዛችሁ እንኪያ ሰላምታ ከእርሱ ጋር ፍጠሩ አይደለም እንዲሁም እንደ ቁራ ቢጮህ ማን ም አይሰማውም ተብሎም በቸልታም መታለፍ የለበትም። በእርግጥ በንጉሴ አንደበት የሚሰደቡ የጽድቅን ተግባር እየፈጸሙ ያሉ መሆናቸውን በሰማዕያኑ ግንዛቤን ቢፈጥርም ምክንያቱም ያ ከእግሩ ስር ቁጭ ብሎ ስድብ የሚቀጽለው (“ደቀ መዝሙር” ብለው የሚበዛበት መሰለኝ፤ ግዴለም እሱም አይከፋውም ቡችላው ልበለውና) እንደሚጠራው ልጥራውና “ንጉስ” የሚያወድሳቸውና በንጽህና እርካብ ላይ የሚያስቀምጣቸው ከእጃቸው በረከትን የተቀበለውን ወንጀለኞችና ሀሰተኞችን ነው። ስለዚህ ለቤተ ክርስቲያን ያበረከታችሁት አስተዋጽኦ እንደ እንጉዳይ በየገዳሙ በየአድባሩ ፍንድቅ ብሎ እየታየ ነው። ዳሩ ንጉሴ እግር አድርሶት ኢትየጵያም ቢሄድ የፓትርያርኩን ቤተ መንግስት ተሳልሞ ከመመለስ ውጭ ወደ ገዳማቱ ጎራ ብሎም የሚያውቅ አይመስለኝም። ጎራ ቢል ኖሮ ምን አልባት ህሊናውን ቆንጠጥ የሚያደርገው ነገር ይዞ ይመጣ ነበር። ግና ገንዘብ ያሳወረው ንጉሴ የሙስና አሞሌ በላሰበት ምላሱ ርኩሱን ቅዱስ ሲያደርግ፣ ቅዱሱን ደግሞ ሲያረክስ መስማት ህሊና ላለው ሰው ታግሶ መስማቱ በራሱ የኢዮብን ያህል ትእግስትን ይጠይቃል። “በሚሰድቡአችሁና በሚያሳድዱዋችሁ ግዜ ስለ እኔም እየዋሹ ክፉውን ሁሉ በሚናገሩባችሁ ግዜ ብፁዓን ናችሁ ደስ ይበላችሁ ሀሴትንም አድርጉ ዋጋችሁ በሰማያት ብዙ ነውና ከእናንተ አስቀድመው የነበሩ ነቢያትንም እንዲሁ አሳድደዋቸው ነበርና” የሚለውን የጌታን ቃል በመዘንጋት አይገባም። መልካሙን ተጋድሎ እየተጋደላችሁ ሳለ በቤተ ክርስቲያኒቱ ስም እየማለ ቤተ ክርስቲያኒቱን ለማጥፋት ከሚያሴሩት የጥፋት ኃይሎች ጋር አንድነትና ህብረት ያለው የንጉሴ ላንቃ ለስድብ ስለተከፈተ ከአላማችሁ እንደማትዛነፉ፣ እርሱንም ንቃችሁት እንደተዋችሁት በራሱ ግዜ በኖ ይጠፋል። የማህበሩ እንቅስቃሴ ከእግዚአብሄር እንጂ ከሰው አይደለም በሚል ጽኑ እምነትና በየግዜው ሰይጣን ከሚያስፈነጥረው የጥፋት ፍላጻ በእግዚአብሄር ቸርነት በእናቱ አማላጅነት ተጠባቃችሁ መኖራችሁን ተማምናችሁ እንደሆነ እገነዘባለሁ። ቢሆንም ግን ይህን ዋልጌ የህግ የበላይነት ሰፍኖ ባለበት ሀገር እየኖረ ሳይሆን የመንፈስ አባቱ የአስተዳደር ድክመት አለ ብለው የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ ጥረት ባደረጉ አባቶች ላይ አይደለም ከመንፈሳዊው መንደር ከአለማውያን መንደር እንኩዋን በማይጠበቅ መልኩ የሥድብና የመርገም መጥሀፍ አስፅፈው እንዳስበተኑና ምንም እንዳልተባሉ እርሱም እንደርሱ በገንዘብ ተገዝተው ማሩን አምርረው ወተቱን አጥቁረው የግብር አባታቸው የዲያብሎስን ስራ ተግባራዊ እንዳደረጉት ሁሉ እርሱም የአባቱን በረከት ተቀብሉዋልና በበላበት እየጮኸ ነው እርሱ ዋሽቶ ቀጥፎ መብላት ስራው ነው በመንግስት የተፈቀደለት ሳይሆን ኅሊናውን አሳምኖ የገባበት የማህበረ ቅዱሳን የስራ አመራር አባላትም የማሕበሩን ህላውና የማስጠበቅ ኃላፊነት እንዳለባችሁ አትዘንጉ ሸማ በየፈርጁ ይለበሳል እንዲሉ አበው ሁሉን በአግባቡ ልታስኬዱ ይገባል እላለሁ
ንጉሴ የአቦን ግብር የበላ ይለፈልፋል እንደሚባለው ካልሆነ እርሱን በሲኖዶስ አባላትና በቅዱስ ፓትርያርኩ መካከል በተፈጠረው አለመግባባት ምን ዶለው? በአቡነ ሳሙኤል በአቡነ ፋኑኤል በአቡነ አብርሃምስ ላይ የነገር ድሪቶውን ለመደረት ልቡናውን ያተጋው በእውነት የቤተ ክርስቲያን ፍቅር ነው ቅዱስ ፓትርያርኩንስ በእውነት ወዶ ነው ከዚህ በፊት የዲያብሎስ ታናሽ ወንድም እድርጎ ያስቀመጣቸውን ዛሬ ምን ቢያገኝ ነው? ይሄ ሳይታለም የተፈታ ነው የንጉሴ ምስ ያው ገንዘብ ነው
በአፈ ጮሌነትና በቅጥፈት የእግዚአብሄር መንግስት የሚወረስ ቢሆን ኖሮ ከምላሴ ጸጉር ይነቀል ንጉሴን የሚቀድም በወረንጦ ቢለቀም አይገኝም ግን እግዚአብሄር ፈታሄ በርትህ ኮናኔ በጽድቅ ነውና ለሁሉም እንደየስራው ይከፍላል መንፈሰ ጽርፈት ያደረብህ አንተ ንጉሴም የምትዘብትበት አምላክ ከላይ ሆኖ እየታዘበህ ነውና አንድ ቀን የስራህን ይከፍልሃል ህሊናህ እያወቀው እውነትን ትቢያ አልብሰህ ሀሰትን ለማንገስ እየጣርህ ያለህ በመሆኑ የዲያብሎስ የግብር ልጅ መሆነህን አረጋግጠሃል በእርግጥ ሰው ሁሉ ማንነትህን አውቆት አንቅሮ የተፋህ ስለሆነ ጩኸትህ ሁሉ የተስፋ መቁረጥ ጩኸት ነው:: ወደ ህሊናህ ተመለስ አለበለዚያ የቤተ ክርስቲያን አምላክ ይመጣብሃል::
+++++++++++++++++++++
(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 22/2009)
ምላስህ ለሰላው ለሀገር ጠላቱ፣
ይደረስህ ጦማሬ ለንጉሴ ከንቱ።
ዛሬ ደግሞ መጣህ አብረህ ከጳውሊ፣
አበው ሲተርቱ አህያ ካመዱ፣
ሞስሰው ተገኙ ጳውሊ ከንጉሱ።


ድሮውንስ ቢሆን ገና ከጅምሩ፣
ያፈረሰ ዲያቆን ኮቶሊክ ባትርያርክ፣
ስምምነት ደርሰው ውሸትን ለመስበክ፣
ጳውሊም አሰናድቶ መቶ ሺ ብር ወረት፣
አትርፎ ለመምጣት ንጉሴ ሲዋትት፣
ሊያፈርሰው ጀመረ የቅዱሳንን በዓት፣
ገበያውም ደርቷል ዲሲ-ቤተ ክ’ነት።

ይሉኝታ የላቸው ፈጣሪን አይፈሩ፣
አንደበታቸው መርዝ ቀና አይናገሩ፣
ወይ ዘይት የላቸው መብራት አያበሩ፣
ጨለማ ሆነዋል በብርሃን እየኖሩ።

ምዕመናን እንንቃ ጊዜው የሥራ ነው፣
ቤታችን ፈት ናት ጠባቂው ጳውሊ ነው።
ያሬድ ቄሰ ገበዝ ሰባኪው ንጉሴ፣
ተስፋ እንዳንጠብቅ ከነዚህ ሕዳሴ።

ጊዜው ሳይመሽብን ለሥራ እንነሳ፣
ጸሎትን እንጨምር በጾምም እንበርታ፣
ከሰማይ መልስ አለ በቃሉ ለፀና፣
ተዋሕዶ ንጽሕት ታብባለች ገና።
(ስንታየሁ ከሰሜን አሜሪካ)

August 10, 2009

"Foolish" Discussion

(By Mulugeta Negash)
As the forces of Satan are getting smarter and stronger, we, the “foolish” Orthodox Christians all over the world exhaust a great deal of energy and time in petty infighting; many hierarchies, particularly in Eastern Europe, have almost no personal contact with their flocks. Many hierarchies and clergy are arrogant and condescending toward the faithful.

No one in the Islamic world is talking about abolishing or shortening Ramadan, but some in the Orthodox world are talking about abolishing some fasting periods, shortening others. Muslims maintain the appearance of their faith, while many Orthodox clergy are embarrassed or ashamed to be seen in public looking like Orthodox clergy. Muslims maintain the tradition of stopping to pray at the given times several times a day, while Orthodox Christians are seeking to reduce the already scant time we spend in the Divine Services.

One could go on with such comparisons, but the point has to do with commitment, discipline and self-control. And these qualities shouldn't be obtained by force or by the sword, like the Muslim community obviously show, but by our self-generated initiatives, because, if other humans force us to execute our faith-related duties with the fear factor (dread of devils), we'll of course be driven far away from the holy spiritual work, from the one and true God.

Faith can only be challenged by faith; commitment can only be faced with commitment. We, as Orthodox Christians cannot offer anything that will counter a committed Islamic missionary effort while we are occupied only with provincial and local problems, with petty self-interest, with "defending MY turf" against other Orthodox clergy. The divided state of the Orthodox Church today, world-wide, and the internecine power struggles undermine and weaken the Orthodox Christian witness. Self-interested fear of each other on the local level can only make the problems we face more systemic and pervasive. Moreover, they are a betrayal of the true Gospel and of the powerful faith.

All make themselves more aware of this challenge and that we struggle, primarily with our own selves, to overcome our own pettiness and find a greater unity of spirit and purpose. Instead of having a delusion of "competition," we should be sharing the resources that each has to offer, and strengthening the commitment of our selves and the faithful. Everyone has some ability to offer, and we need to be willing to share our "self" with all for the sake of the Gospel and in order to face, with a unity of love for Christ, the challenges and temptations that are so rapidly arising before us.

The devil does not get desperate, however strong, the person whom he fights is. The devil wants to resist God's Kingdom by every means and rejoices when he is able to overthrow "if possible, even the elect." (Matt 24:24).

Our faith, our Kingdom will continuously be tempted, but we need to restore our confidence in learning that the temptation of Christ by Satan is a comfort for us in all our trials.

"Put on the whole armor of God, that you may be able to stand against the wiles of the devil. For we do not wrestle against flesh and blood, but against principalities, against powers, against the rulers of the darkness of this age, against spiritual hosts of wickedness in the heavenly places." (Eph. 6:11, 12)

August 8, 2009

የፓትርያርኩ ረዳት አባ ዕንቁ ባሕርይ በዋስ ተፈቱ

(ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 8/2009)
አባ ዕንቁ ባሕርይ የተባሉት የፓትርያርኩ ረዳት (አቡነ ቀሲስ) በዋስ መለቀቃቸው ታወቀ።

አቡነ ቀሲሱ ባለፈው ሳምንት ታስረው እንደነበር መዘገባችን ይታወቃል። የ14 ቀን ቀነ ቀጠሮ ተጠይቆባቸው የነበሩት አባ ዕንቁ ባሕርይ ከ3 ቀን ላላነሰ ጊዜ መታሰራቸው ሲታወቅ የተፈቱበትን እርግጠኛ ቀን ማወቅ አልቻልንም። ትናንት በፓትርያርኩ ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት የታዩት አባ ዕንቁ ባሕርይ ለእስር የተዳረጉበት ምክንያት በቤተ ክህነቱ የአባቶች ቤት ሰበራ ወንጀል መሆኑ ይታወቃል።

የቤተ ክህነት ግቢ የጥበቃ ሃላፊ አቶ ብርሃኔ ከአባ ዕንቁ ባሕርይ ትዕዛዝ ተቀብለው ሁለት መኪና ሰዎችን በድብቅ ማስገባታቸውን ካመኑ በሁዋላ የወንጀሉ ምርመራ ወደ እርሳቸው እንደመራ ታውቋል።
ፖሊስ የነገሩን ጭራ መያዙን ብዙዎች ያመኑ ሲሆን “ከዚህ በሁዋላ የሚቀረው ነገር ጀሌውን ብቻ ልያዝ ወይስ ዋነኛውን የወንጀሉን ባለቤት?” የሚል ጥያቄ ብቻ እንደሆነ አስተያየት ሰጪዎች ይገልጻሉ።
የማፊያው ቡድን አቀናባሪና “ያልተሾመች ጳጳስ” የሚባሉት ወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ ወንጀሉ በተፈጸመበት ሌሊት በጊቢው ውስጥ እንደነበሩ ውስጥ አዋቂዎች ይናገራሉ። “የነገሩን በዕቅዱ መሠረት መከናወን ስትመለከት ነበር” ሲሉም ይተቻሉ።

የቅዱስ ፓትርያርኩ ጋዜጣዊ መግለጫ

(ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 8/2009):- ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ትናንት አርብ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጡ። ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄም መልስ ሰጡ። የአሜሪካ ድምጽ ሪፖርተር መለስካቸው አምሃ ያቀረበውን ዜና ተንተን አድርገን ስንመለከተው የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦች እናገኛለን። የፓትርያርኩ ዋነኛ የመግለጫቸው አንኳር ሐሳብ “ቤተ ክርስቲያን በልማት ሥራ እየተሳተፈች ነው” የሚል ነው። የልማት ኮሚሽንን ተግባራት በመጥቀስ ሦስት ሚሊዮን ችግኝ መተከሉን፣ የአፈርና የድንጋይ ግድብ መሠራቱን፣ የውሃ ጉድጓድ መቆፈሩን ተናግረዋል።

ልማት መልካም ነው። ፓትርያርኩ ከሌሎቹ ነገሮች ሁሉ መርጠው ስለ ልማት መናገር የፈለጉበት አንድ ምክንያት አላቸው። የመንግሥት ቀልብ ለመሳብ፣ “ልማት ልማት” የሚለውን መንግሥት “እኔ የልማት አጋር ነኝ፣ እዩ የሠራኹትን ሥራ” ለማለት የቀረበ እጅ መንሻ ነው። ስለ በጀትም ሲናገሩ የተናገሩት “ለልማት የተያዘውን 104 ሚሊዮን ብር” ነው። ሌላውስ የቤተ ክርስቲያኒቱ አገልግሎት? ስብከተ ወንጌሉ? የሰንበት ት/ቤቶች ጉዳይ? የገዳማቱና አድባራቱስ? ሌላውስ ሌላውስ?
የቤተ ክርስቲያኒቱ ልማት ኮሚሽን በተለያዩ የፈረንጅ ሀገሮች የሚረዳ፣ ከሌላው የቤተ ክህነቱ አሠራር ጋር ሲመዛዘን ሙያ ባላቸው ባለሙያዎች የሚንቀሳቀስ ድርጅት እንደሆነ ይታወቃል። ስለዚህ ድርጅት መናገር ምን ጥቅም አለው። ከተናገሩ መናገር ያለባቸው ስለ ቤተ ክህነቱ ነው። ጋዜጠኞቹም የጠየቋቸው ስለዚያው ነው።
ፓትርያርኩ በቤተ ክህነት ውስጥ “የተበላሸ አሠራር” መኖሩን አልካዱም። “የተበላሸ አሠራርን ለማጣራት ሰዎች ተመርጠዋል። ይህ ተበላሸ፣ ይህ ቅጥ አለው፣ መልክ አለው ብለው መናገር የሚችሉት እነርሱ ናቸው” ብለዋል። ነገር ግን ከሰባቱ ኮሚቴ አባላት መካከል ከአራት አላነሱት ሥራውን ለቀዋል። ኮሚቴው በስም አለ፣ በሥራ ግን የለም።
ሌላው የፓትርያርኩ መልስ በማፊያው ቡድን ሊጣል ስለተሞከረው አደጋ ነው። ፓትርያርኩ እንደመለሱት ነገሩ አሳዝኗቸዋል። “ለመንግሥት አቤቱታ ከማቅረብ አልፎ ምንም ማድረግ አይቻልም” ሲሉ አጠቃለዋል። በርግት ለመንግሥት ያቀረቡት አቤቱታ የሚኖረው ውጤት ወደፊት የሚታይ ይሆናል።

August 6, 2009

"ቅኔ የአብነት ትምህርቱ ፍልስፍና መሠረት": ማኅበረ ቅዱሳን ያዘጋጀው የቅኔ ዐውደ ጥናት

• ስለቅኔ ታሪካዊ አመጣጥና ትርጓሜ የመምህራኑና የተማሪዎቹን ሕይወትን የሚዳስስ ዘጋቢ ፊልምም ተመረቀ
"ቅኔ የአብነት ትምህርቱ ፍልስፍና መሠረት"
(በሔኖክ ያሬድ)
(ሪፖርተር ጋዜጣ: 05 AUGUST 2009):-የቅኔና የግእዝ ትምህርት ከዘመኑ ጋር ማደግና መስፋፋት ሲገባው እድገቱ እየተገታ በመምጣቱ የከፍተኛ ትምህርትና የቤተ ክህነት የትምህርት ተቋማት ከፍተኛ ትኩረት እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረበ፡፡
ባለፈው ቅዳሜ ሐምሌ 25 ቀን 2001 ዓ.ም. በማኅበረ ቅዱሳን አዘጋጅነት በተካሄደው ዐውደ ጥናት ላይ እንደተመለከተው፣ በተለይ ከ20ኛው ክፍለ ዘመን በኋላ በተለያዩ ችግሮች ምክንያት የአገሪቱ ጥንታዊ ትምህርት ከዘመኑ ጋር ማደግና መስፋፋት ሲገባው እድገቱ እየተገታ መጥቷል፡፡

በተለይ የፍልስፍና፣ የሒሳብና የሥነ ከዋክብት ትምህርቶች እንደሌሎቹ አገሮች ለትውልድ ሳይተላለፉ ጉባኤዎቹ የታጠፉበት ዘመን ላይ ተደርሷል፡፡


"ቅኔ የአብነት ትምህርቱ ፍልስፍና መሠረት" በሚል መሪ ቃል በተካሄደው ዐውደ ጥናት የማኅበሩ ሰብሳቢ ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ሥዩም እንደተናገሩት፣ የአብነት (ቆሎ) ትምህርት ቤቶች ከእምነት ተቋምነታቸው ባሻገር የሀገሪቱ የትምህርት፣ የፍልስፍና፣ የሥነ ጥበብ፣ የሥነ ሕንፃና የሥነ ጽሑፍ ተቋማት ሆነው እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡

የቅኔ ትምህርት ሃይማኖትን፣ የሀገር ታሪክን፣ የቀድሞ አባቶችና የአሁን ዘመን ሊቃውንት ፍልስፍናና ጥበብ፣ ማኅበራዊ ሒስ የተላለፈበት የዕውቀት ዘርፍ ቢሆንም ተገቢ ትኩረት ባለማግኘቱ እያሽቆለቆለ ይገኛል፡፡

በቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ አገላለጽ፣ የቅኔ ትምህርት የውጭ ሀገር ምሁራን ለጥናትና ምርምር ሲረባረቡበት በኢትዮጵያ በኩል የተሰጠው ትኩረት ግን አናሳ በመሆኑ የሁሉንም ርብርብ ይጠይቃል፡፡

ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ "ቅኔ የግእዝ ቋንቋና ሥነ ጽሑፍ" በሚል ርእስ ጥናት ያቀረቡት ዶክተር ሥርግው ገላው፣ በቅኔ፣ ታሪክ እንደሚጠናበት፣ እንደሚዘከርበትና እንደሚጠበቅበት፣ ከፍተኛ ጥበብ ያለውና ልዩ የአገላለጽ ስልት በየዘመናቱ እያሳየ መሆኑን፣ በአሁን ዘመን ግን የኅብረተሰቡ ድጋፍ በመቋረጡ የቅኔ ትምህርት ቤቶች እያሽቆለቆሉ መምጣታቸው፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲም ቀደም ሲል የነበረውን ደረጃ አጥቶ እየተዘጋ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

ቀደም ባሉት ዓመታት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ግእዝ ቋንቋንና ቅኔውን አስተባብሮ በ24 የግንኙነት ጊዜ (ክሬዲት ሀወርስ) ትምህርት ይሰጥበት የነበረበት ሁኔታ አሁን በሁለት የግንኙነት ጊዜ መገደቡና በሥነ ትምህርት ኮሌጅም ግእዝ ከሥርዓተ ትምህርቱ እንዲወጣ መደረጉን ዶ/ር ሥርግው ጠቁመዋል፡፡ ሌሎች ሀገሮች ዘመናዊ ትምህርትን በራሳቸው ነባር ትምህርት ላይ ተመሥርተው መገንባታቸው ለስርፀትም ሆነ ለስኬት እንዳበቃቸው ያመለከቱት ዶ/ር ሥርግው፣ በኢትዮጵያ ግን የረዥም ጊዜ የአገሪቱን የትምህርትና የጥናት ሂደት ወደ ኋላ መጣሉ አግባብ እንዳልሆነ አመልክተዋል፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ትምህርት ኮሌጅ ቀደም ሲል የተቀረጸው ለአማርኛና ትግርኛ ተማሪዎች ይሰጥ የነበረው የግእዝ ትምህርት፣ ክፍሉ ለምን እንዳስወገደው ግልጽ አይደለም ያሉት መምህሩ፣ የውጭ ዩኒቨርሲቲዎች ለግእዝ የሰጡትን ትልቅ አክብሮት ያህል ሊነፈገው እንደማይገባ አሳስበዋል፡፡

"በግእዝ ሥነ ጽሑፍ ላይ በአብዛኛው የሠሩትና ታሪካችንን የሚያስተምሩን የውጮቹ ናቸው፡፡ ከእኛው ግእዝ ወስደው ግእዙንና ታሪካችንን አጥንተው ነው የሚያስተምሩን፡፡ እኛ ግን በተገላቢጦሹ የምንማርበት አንዳችም ምክንያት ያልታየን ግእዝን ለመረዳት ስላልቻልን ነው" ብለዋል፡፡

ቅኔና ሥነ ቃል

ቅኔ በግጥም የሚሰጥ ራሱን የቻለ የትምህርት ዓይነት ነው፡፡ የራሱ ሕግጋትም አሉት፡፡ ሰዎች በሕይወታቸው የሚያጋጥሟቸውን ክስተቶች፣ ሐዘን ይሁን ደስታ ሁሉንም የሚያሳዩበት የጥበብ ዘርፍ ነው፡፡

ከሃይማኖታዊ ይዘት ባሻገር የአገሪቱ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ጉዳዮችም በቅኔ ይዳሰሳሉ፡፡ ዶ/ር ሥርግው ባቀረቡት ጥናት ላይ በምሳሌነት እንደጠቆሙት፣ በመካከለኛው ዘመን ሰምና ወርቅ የሌለው ደረቅ ቅኔ ታሪክ ተመዝግቦበታል፡፡

በ16ኛው ምእት ዓመት ግራኝ አህመድ የተነሳበት ጊዜ ነበር፡፡ ማዕከላዊ መንግሥቱን ይመሩ የነበሩት አፄ ልብነድንግል ግራኝ አህመድ በሚያሳድዳቸው ጊዜ፣ ለሠራዊታቸውና ለሕዝባቸው መልዕክት ያስተላለፉት በቅኔ ነበር፡፡

ዓይነቱ "ደረቅ ቅኔ" የተሰኘውም እንደ ዛሬ ዘመን ግጥሞች ሰምና ወርቅ የሌለው በመሆኑ ነው፡፡ "ስለ እናንተ የታመመውና የሞተውን ስሙን አትካዱ፡፡ ኢአማኒ ቢማርካችሁ፣ ሰይፍም ቢያሰቃያችሁ፣ የግፉ ዋጋ ወደ ፊት ይጠብቃችኋልና ስሙን አትካዱ" የሚል ነበር፡፡

ቅኔዎች ለይዘታቸው ማጠናከሪያ ከሚጠቀሱት ከመጽሐፍ ቅዱስና ከሌሎች ታሪካዊ ድርሳኖች ሌላም ሥነ ቃልን የሚጠቀሙም ሞልተዋል፡፡

ሊቃውንቱ፣ ኅብረተሰቡ የቅኔን መንገድ በቅርበት እንዲያውቅ ለማድረግ፣ ከቅዱሳት መጻሕፍቱ ሌላ በዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ የሚዘወተሩ ሥነ ቃሎችን (ተረትና ምሳሌዎችን) በቅኔዎቻቸው ያስገቡ ነበር፡፡

"ቅዱሳት መጻሕፍቱን የሚያውቁት ሁሉም አይደሉም፡፡ ሥነ ቃልን ሁሉም ያውቀዋል፤ ሰው ግእዙን ከቻለና አካሄዱን ከተረዳ ከሥነ ቃሉ በመነሳት ብዙ ሰዎችን ማሰልጠን ይቻላል፡፡" የሚሉት ዶ/ር ሥርግው ለማሳያነት የሚከተለውን ጠቅሰዋል፡፡

ዐፄ ምኒልክ ወራሪውን የኢጣሊያ ሠራዊት ለማስወገድ ወደ ዓድዋ ሲዘምቱ ወሎ ውስጥ እረፍት አድርገው ነበር፡፡ በእንግድነት ካደሩበት ቤት ሲወጡ ለባለቤቱ ሴት አገልጋይ (አመት) ሰጥተው ነበር የሄዱት፡፡ ድል አድርገው ሲመለሱ ያገኟቸው ባለቤቱ ሌላ ሴት አገልጋይ ጨምሩልኝ ለማለት ቅኔውን ተቀኙ፡፡

" ምኒልክ ሠዊት ዘትፈሪ ምእተ
ድግመኒ ዐመተ ዐመተ፡፡"
(መቶ መቶ የምታፈራው ምኒልክ እሸት
ዓመት ዓመት ድገመኝ)

የእሸት ወቅት ደርሶ እሸቱ ከተበላ በኋላ "ዓመት ዓመት ድገመኝ" የሚሰኝ አባባል አለ፡፡ ይህን ብሂል ባለቅኔው ይዞ በአፄ ምኒልክ ከደረሰለት በረከት ጋር አያይዞ አቀረበው፡፡ (ዐመት በዓይኑ ዐ ሲነበብ ዘመንን፣ በአሌፉ "አ" ሲነበብ ደግሞ ሴት አገልጋይ ማለት ነው"፡፡

በዐውደ ጥናቱ፣ ስለ ቅኔ አገልግሎትና ያለበትን ደረጃ በተመለከተ ማብራሪያ በሰጡት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ልሳን መምህር ደሴ ቀለብ አገላለጽ፣ በርካታ ሊቃውንት ያፈራው፣ ቀደም ሲል ከተማሪው ብዛት የተነሳ በትልቅ ገበያ የሚመሰለው የዋሸራ ቅድስት ማርያም የቅኔ ማስመስከሪያ ጉባኤ ቤት፣ ዛሬ በጣት የሚቆጠሩ ተማሪዎች ብቻ ቀርተውታል፡፡ በአሁን ሰዓት አሉ የሚባሉ ጥቂት የቅኔ ትምህርት ቤቶች ይህ እጣ ፈንታ ሳይደርስባቸው ሕዝቡና የሚመለከታቸው ተቋማት ምንነቱንና ጠቀሜታውን ተገንዝቦ እንዲንከባከባቸውና እንዲጠብቃቸው ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

በዐውደ ጥናቱ ላይም ስለቅኔ ታሪካዊ አመጣጥና ትርጓሜ የመምህራኑና የተማሪዎቹን ሕይወትን የሚዳስስ ዘጋቢ ፊልምም ተመርቋል፡፡

ፊልሙ የቅኔ ትምህርት ለሃይማኖት መጎልበት፣ ከሥነ ጽሑፍና ከትርጓሜ መስፋፋት አኳያ ያለውን ድርሻ የሚዘግብና ስመጥር የቅኔ ሊቃውንትና ትምህርት ቤቶችን የሚያስተዋውቅ ነው፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላይ የፈጸሟቸው ዐበይት ችግሮች

(ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 5/2009)
ውድ አንባብያን፣
ይህ አጭር ጽሑፍ የተወሰደው “የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዋና ዋና አንገብጋቢ ችግሮች እና መፍትሔዎች፦ ከፍተኛ ትኩረት የሚሻ” ከሚል በግንቦት 2001 ዓ.ም ተዘጋጅቶ ለቅዱስ ሲኖዶስ ቀርቧል ከተባለ ዘገባ ላይ ነው። የዶኩመንቱ አዘጋጅ ስም፣ ለምን ዓላማ እንደተዘጋጀ፣ በማንና ለማን ወይም ለነማን እንደቀረበ አይጠቅስም። ይሁን እንጂ ከያዘው መሠረታዊ የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ አንጻር “ስለ ቅዱስ ፓትርያርኩ” የሚናገረውን ብቻ ቀንጭበን አውጥተነዋል። ያወጣንበት ዓላማ ከተራ ስድድብና መወጋገዝ በመውጣት፣ ከግለሰቦች ደጋፊነትና ወገንተኝነት በመጽዳት ቅዱስ ፓትርያርኩም ከዚህ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ለማሳሰብ ነው።


መልካም ንባብ፤
ደጀ ሰላም
+++
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላይ የፈጸሟቸው ዐበይት ችግሮች የሚከተሉት ናቸው፦

(To read in a PDF format, click HERE.)
1. ለዘመናት በአንድነቷ የምትታወቀው ቤተ ክርስቲያናችን ቅዱስ ፓትርያርኩ ለግል ዝናና ስልጣናቸው ሲሉ በእልህ በሚፈጽሙት ድርጊት ቤተ ክርስቲያኒቱ ለሁለት ተከፍላለች፡፡ በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ በሚገኙ ምዕመናን መካከል ከፍተኛ ልዩነት ተፈጥሯል፡፡ በአባቶች መካልም በጥርጣሬና በጥላቻ ከመተያየት ባሻገር መወጋገዝን አስከትሏል፡፡ ይኸውም ዛሬ ከፈጠረው ችግር ባሻገር ለነገዋ ቤተ ክርስቲያን ለትውልድ የሚተርፍ ከፍተኛ ፈተና ነው፡፡ ለዚህም አንዱና ዋናው ምክንያት ቅዱስ ፓትርያርኩ ምንም ዓይነት የእርቅና የስምምነት በር እንዳይከፈት በማድረግ ወይም በመዝጋት እርቅ እንዳይመጣ ሰላምም እንዳይወርድ አፍነው በመያዛቸው ነው፡፡ ለምሳሌም በጥቅምት ወር 2000 ዓ.ም የቀረበውን የእርቅ ጥያቄ ውድቅ ማድረጋቸው ይጠቀሳል፡፡

2. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የሥራ አስፈጻሚነትና የአስተዳደር ሥልጣን በተመለከተ በሕገ ክርስቲያን አንቀጽ 30 ቁጥር 1 እስከ 21 እንደሰፈረው፡-
1. የቅዱስ ሲኖዶስ አስተዳደር በየጊዜው የሚወስናቸውን ጉዳዮች ከየቤተ ክርስቲያናቱና ከልዩ ልዩ መ/ቤቶች የሚቀርቡትን ጥያቄዎች በሕጉ መሠረት መፈፀምና ማስፈፀም፣
2. ዋናውን መ/ቤት፣ የኮሚሽኑን፣ የቦርዶችን፣ የድርጅቶችንና የመምሪያዎችን በአጠቃላይ በቤተ ክርስቲያኒቱ ሥር የሚገኙትን የሥራ ዘርፎችን ሁሉ ማስተዳደርና መምራት፣
3. ማንኛውንም የቤተ ክርስቲያኒቱን ገንዘብ በትክክል ገቢ መሆኑንና በሕጋዊ መንገድ ወጪ እየሆነ ለቤተ ክርስቲያኒቱ አገልግሎት መዋሉን መቆጣጠር፣
4. የመምሪያና የልዩ ልዩ ድርጅቶች ሓላፊዎችን እያጠና እና ፓትርያርኩን እያስፈቀደ መሾም፣ የሥራ ሓላፊዎችን የሥራ ዝውውርና ዕድገት በአስተዳደር ጉባኤ እየተጠና እየተወሰነ እንዲፈፀም ማድረግ፣
5. በየደረጃው ያለውን የሠራተኛ መብትና ግዴታ ማለትም የጡረታ፣ የጤና አጠባበቅ፣ የደረጃ ዕድገት፣ የፈቃድ አሰጣጥ፣ የዲስፕሊን ውሳኔ አፈጻጸም እና የመሳሰሉትን ሁሉ በሕጉ መሠረት መፈጸማቸውን መቆጣጠርና አመራር መስጠት፣
6. በበጀት የተመደበውን ማንኛውንም የቤተ ክርስቲያኒቱ ንብረት በፊርማው ማንቀሳቀስ፣
7. ማናቸውም የቤተ ክርስቲያኒቱ ገንዘብ ገቢና ወጪ በሕጋዊ የሂሳብ አያያዝና ደንብ መሠረት መሠራቱን መታተልና መቆጣጠር. . . ወዘተ እንደሚያካትት ተደርግጓል፡፡

ነገር ግን ይህን ድንጋጌ በመጣስና የጠቅላይ ቤተ ክህነቱን ዋና ሥራ አስኪያጅ ስልጣን በመጋፋት ቅዱስ ፓትርያርኩ በማን አለብኝነት አመመራቸው የወደዱትን ለመጥቀም ሲሉ አላግባብ ሹመዋል፣ የደረጃ እድገት ሰጥተዋል፣ ቀጥረዋል፣ አዛውረዋል፡፡ በግል የጠሉትንም ከቅዱስ ሲኖዶስ መመሪያ ውጪ ሽረዋል፤ ከደረጃ ዝቅ አድርገዋል፣ ደመወዝ አግደዋል፣ ከሥራ አባርረዋል፡፡ በዚህም የቤተ ክርስቲያኒቱን ገንዘብ ለከፍተኛ ብክነት ዳርገዋል፡፡

3. የሲኖዶሱን ሥልጣን በተመለከተ በሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ 7 በቁጥር 11 እና 12 ላይ ማለትም፡-
• በውጭ አገር ለአገልግሎት የሚመደቡ እንዲሁም በአገር ውስጥ ትምህርት ተምረው የውጭውን ትምህርት መማር የሚችሉ ካህናትን እየመረጠ እንዲላኩ የማድረግ፣
• ማንኛውም ሰው ቤተ ክርስቲያኒቱን ወክሎ ለሥራም ሆነ ለጉብኝት ወደ ውጭ አገር በሚላክበት ጊዜ ቅዱስ ሲኖዶስ እየፈቀደ መሆኑን ይደነግጋል፡፡
• እንዲሁም የፓትርያርኩን ሥልጣንና ተግባር በሚገልጸው አንቀፅ 15 ቁጥር 12 ላይ ፓትርያርኩ በውጭ ስብሰባ ለመገኘትም ሆነ ጉብኝት ለማድረግ በሚፈልጉበት ጊዜ ስለ ተልእኮው ጉዳይ አስቀድሞ በቅዱስ ሲኖዶስና ቋሚ ሲኖዶስ ማስወሰን እንደሚገባቸው ተደንግጓል፡፡

ነገር ግን ፓትርያርኩ ለቅዱስ ሲኖዶስ ባላቸው ንቀት ምልዓተ ጉባኤውን ሳያስፈቅዱ ክብረ ቤተ ክርስቲያንን በሚያስነቅፍ መልኩ ፕሮቶኮል ያልጠበቁ እንቅስቃሴዎችን አድርገዋል፡፡ ያለምንም ብቁ ምክንያትና ተልዕኮ በየጊዜው በቤተ ክርስቲያኒቱ ብር በተራ ስብሰባዎች ላይ ለመገኘት በተለያዩ ዓለማት አጀብ በማስከተል በመውጣት፣ የቤተ ክርስቲያኒቱን ገንዘብ ለስብከተ ወንጌል ከማዋል ይልቅ መንሸራሸሪያ አድርገውታል፡፡ በዚህም የድሀይቱን ቤተ ክርስቲያን ገንዘብ በከፍተኛ ደረጃ እንዲባክን አድርገዋል፡፡

4. የታላላቅ ገዳማት አበምኔቶችና የታላላቅ አድባራት አስተዳዳሪዎች በየሀገረ ስብከቱ ሊቃነ ጳጳሳት እየተመረጡ ሲቀርቡላቸው መዓርግ ስም እየሰጡ መሾም ሲገባቸው ከተሰጣቸው ሥልጣን ገደብ አልፈው ማንንም ሳይጠይቁ በመሾምና በመሻር ፓትርያርኩ ሕግን ተላልፈዋል፡፡ በተጨማሪም የተመደበ በጀት ይኑር አይኑር ሳይጠናና ሳይረጋገጥ “ዓላማዬን ያሳኩልኛል” ያሏቸውን ሰዎች ወደ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤትና አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት በመላክ፣ በግዴታም እንዲቀበሉ በማስገደድ ከሕግ የወጣ ተግባር ፈጽመዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ሀገረ ስብከቱንና አድባራቱን የእዳ ተሸካሚ አድርገዋቸዋል፡፡

5. የቤተ ክርስቲያኒቱ የሀገረ ስብከት አወቃቀር መሠረት የሚያደርገው የዞን አስተዳደርን ስለሆነ እንደመንግሥት አወቃቀር ከክልል መስተዳድሮች ጋር በቀላሉ ተቀራርቦ ለመሥራት የሚያስችል አሠራር የለም፡፡ ይህን ችግር ለመፍታት የመዋቅር ማስተካከያ ያስፈልጋል፡፡ በተለይም በአማራ፣ በትግራይ፣ በኦሮሚያ እና በደቡብ ክልሎች ቤተ ክርስቲያኒቱን በክልል ደረጃ ሊወክል የሚችል አሠራር ተዘርግቶ ቤተ ክርስቲያኒቱ ከየክልሎቹ መንግሥታት አሠራር ጋር በቀላሉ ተቀራርባ መሥራት የሚያስችላትን አወቃቀር መፍጠር ነበረባት፡፡ ሆኖም ፓትርያርኩ ስልጣኔን ይሸራርፍብኛል ከሚል አቋም ይህን ለመተግበር ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ችግሩ እስከ አሁን ዘልቋል፡፡

6. ጋጠ ወጥ በሆኑ ዘፈኖቿ በዓለም ዘንድ የምትታወቀውንና እነዚህ ዘፈኖቿን ኢትዮጵያ ውስጥ ለመዝፈን የመጣችውን (ቢዮንሴ የምትባል) ዘፋኝ በቤተ ክርስቲያን ዓውደ ምሕረት የቤተ ክርስቲያንን፣ የአባቶችንና የምዕመናን ክብር በሚነካ መልኩ የፈጸሙት አሳዛኝ ታሪካዊ ስህተት የእርሳቸውን መንፈሳዊ መሪነት ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ነው፡፡ በእርግጥ ግለሰቧ ቤተ ክርስቲያንን መጎብኘት ከፈለገች እንደማንኛውም ጎብኚ ልትጎበኝ ትችላለች፡፡ ነገር ግን ያ ሁሉ የዐውደ ምሕረት አጀብ አስፈላጊ አልነበረም፡፡ እርሳቸውም ቢሆኑ መነጋገር ካስፈለጋቸው በእንግዳነቷ በቢሮአቸው ጋብዘዋት ማነጋገር ሲችሉ ብጹዓን አባቶችን ሰብስበው ለስምንት ሰዓታት ሙሉ በቤተ ክርስቲያን ዐውደ ምሕረት ሲጠብቁ መዋላቸው የቤተ ክርስቲያኒቱን ክብር የሚያጎድፍና የምእመናንን አንገት ያስደፋ ተግባር ነው፡፡

7. የቅዱስ ሲኖዶስን ፈቃድና እውቅና ሳያገኙና የቤተ ክርስቲያኒቱን ቀኖና ሳይጠብቁ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናትን እንደ ቀበሌ ጽ/ቤት በመቁጠር የራሳቸውን ምስል ማስለጠፋቸውና ለዚህም የስዕል ሰሌዳ ያለ ቅዱስ ሲኖዶስ ፈቃድ የቤተ ክርስቲያኒቱን ገንዘብ ለግለሰቦች መበልጸጊያና ለብክነት መዳረጋቸው ቤተ ክርስቲያኒቱንና ምእመናንን ያሳዘነና በማሳፈር ላይ ያለ ጉዳይ ነው፡፡

8. ሕገ ቤተ ክርስቲያን በሚያዝዘው መሠረት ቅዱስ ሲኖዶስ ሳይፈቅድና አመራር ሳይሰጥ በራሳቸው የግል ፈቃድ ዝክረ ቤተ ክርስቲያን በማለት በሽልማት ስም ቤተ ክርስቲያንን የማይወክሉ ሰዎችን በማሰባሰብ ግልጽ ባልሆነ መንገድ በቤተ ክርስቲያኒቱ ስም በርካታ ገንዘብ የገቢና ወጪ ሕጋዊ አሠራር በሌለው መንገድ ከቤተ ክርስቲያኒቱም ጭምር እንዲሰበሰብ አድርገዋል፡፡ በዚህም ምዕመናን ቤተ ክርስቲያኒቱን በጥርጣሬ እንዲመለከቷት በር ከፍተዋል፡፡ ከራስ ወዳድነታቸው የተነሳ ለራሳቸው ስጋዊ ዝና ሲሉም የቤተ ክርስቲያኒቱን ታሪክ በትውልድ ፊት አጉድፈዋል፡፡

9. በመከራ ውስጥ አልፎ የቤተ ክርስቲያኒቱን ትምህርት ለተማረው ተገቢ ሥራ መደብ ከመስጠት ይልቅ ቤተ ክርስቲያኒቱን እንደግል ድርጅት በመቁጠር በዘመድ አዝማድ ወይዘሮዎችና አቶዎች ወሳኝ የቤተ ክርስቲያኒቱን ቦታዎች እንዲይዙ በማድረጋቸው ቤተ ክርስቱያኒቱን ለከፍተኛ ምዝበራና ውርደት አጋልጠዋል፡፡ እንዲህ ዓይነት ሥነ ምግባር የሌላቸው ወይዘሮዎችን በማረም ፈንታ ሽፋንና ደጋፊ በመሆን ቤተ ክርስቲያን ላይ ከፍተኛ በደል እየፈጸሙ ነው፡፡

10. በቤተ ክርስቲያኒቱ ገንዘብና ንብረት ላይ በማን አለብኝነት በማዘዝ ዛሬ ቤተ ክርስቲያኒቱ በከፍተኛ የገንዘብ እጥረት ላይ እንድትገኝ አድርገዋል፡፡

11. በአምባገነናዊ አስተዳደር ሂደታቸው የቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ፈረሰ፣ ንብረት ተዘረፈ፣ ገንዘብ ተመዘበረ፣ ቀኖና ተፋለሰ፣ አድልዎ ነገሰ፣ የሰው መብት ተጣሰ፣ ወዘተ በማለት ማስተካከያና እርምት እንዲደረግ የሚጠይቁ ብፁዓን አባቶችን ለማስደንገጥ ከሀገረ ስብከታቸው ያነሳሉ፣ በጠላትነትም ይፈርጃሉ፡፡ በመንግሥት ባለስልጣናት ስምም ያስፈራራሉ፡፡

12. ከሀገር ውጭ ያለችውን ቤተ ክርስቲያን እንዲያገለግሉ ብቃት ያላቸውን ሰዎች ከመላክ ይልቅ በገንዘብና በዘመድ አዝማድ የሚላከው ይበልጣል፡፡ በዚህ መልኩ የተላኩት ብዙ ሰዎች ለቤተ ክርስቱያኒቱም ዕድገት ሳይሆን ከሃገር መውጣታቸውን ለግል ጥቅማቸው ማስፈጸሚያ በማድረግ፣ ቤተ ክርስቲያኒቱን በማዋረድ ምዕመናንን እያሳቀቁ ከፍተኛ በደል እየተፈጸመ ነው፡፡
13. ለቤተ ክርስቲያኒቱ አገልጋዮች በመጡ የተለያዩ የውጭ የትምህርት ዕድሎች ዘመዶቻቸውን በቤተ ክርስቱያኒቱ ስምና ገንዘብ ልከዋል፡፡ የሔዱትም ሰዎች አብዛኞቹ በዚያው ስለሚቀሩ የተያዩ ኤምባሲዎችና ቆንስላ ጽ/ቤች ለቤተ ክርስቲያኒቱ ያላቸው እምነት በከፍተኛ ደረጃ ዝቅ እያለ መጥቷል፡፡ ይህም ለቤተ ዘመድ የሚሠሩት ተራ ጥቅማ ጥቅም ቤተ ክርስቲያኒቱን ብዙ የውጭ ሀገር ሰዎች በዝቅተኛ አይን እንዲመለከቷት አድርጓል፡፡

14. በዘመነ ፕትርክናቸው ከምንጊዜውም በላይ የስብከተ ወንጌል አገልግሎት መዳከሙ ብቻ ሳይሆን መጥፋቱ ግልጽ ነው፡፡ ለዚህም አንዱ ማሳያ ቤተ ክርስቲያኒቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ ያላት የምዕመናን ቁጥር መቶኛ ድርሻ በተዓምራዊ ፍጥነት እየቀነሰ መምጣቱ ነው፡፡ በአንጻሩም የሌሎች እምነት ተከታዮች በከፍተኛ ጥፍነት እያደገ መሆኑን የ1999 እና 2000 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የህዝብና ቤት ቆጠራ ውጤት በግልጽ እያሳየን ነው፡፡

15. በሙስናና በተለያዩ ከፍተኛ ችግሮች በደል ተገኝቶባቸው ከመንግሥት በግምገማ የሚባረሩ አካላትን ከጥፋታቸው ሳይታረሙ ከነችግራቸው በማቅረብ ቤተ ክርስቱያኒቱን የዘራፊዎች ዋሻ አድርገዋልታል፡፡

16. ያለምንም ይሉኝታ በቤተሰብና በቤተዘመድ በእውቅና እንዲፈጸም በሚያደርጉት የቅጥር ሂደት ባለሙያዎችና ምሁራን በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ ምንም ድርሻ አግኝተው ሙያቸውን ለቤተ ክርስቲያን ማበርከት እንዳይችሉ አድርገዋል፡፡

17. በየአህጉረ ስብከቶች የሚገኙ ገዳማት፣ አድባራትና አብያተ ክርስቱያናት እየተዘጉ ካህናትና አገልጋዮቿ በረሀብና በመተዳደሪያ እጦት እየተሰደዱ ባሉበት በአሁኑ ወቅት ፓትርያርኩ ግን ለዚህ አንዳች መፍትሔ ከመፈለግ ይልቅ ስለራሳቸው ዝናና ክብር የህዝብ ግንኙነት ሥራ እንዲሠራላቸው አሜሪካን ሃገር ለሚገኘው የሃገር ፍቅር ሬዲዮ አዘጋጅ 100‚000.00 (መቶ ሺህ ብር) እንዲሰጥ ማድረጋቸው ዕለት ዕለት የሚያስጨንቃቸው የራሳቸው ስምና ዝና መታወቅ እንጅ የቤተ ክርስቲያን ችግር መፍትሔ ማግኘቱ አለመሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡

18. ከቤተ ክርስቲያኒቱ አስተዳደር ጋር ተያይዞ በሀገር ውስጥ በየክልሉ እንዲሁም ከሀገር ውጭ በሚፈጠሩ ችግሮች በስተጀርባ እርሳቸው የተለያየ የጥቅም ግንኙነት ስለሚያደርጉ ለችግሮቹ መፍትሔ ለመስጠት አስቸጋሪ ደረጃ ላይ ተደርሷል፡፡ ለችግሮቹ መፍትሔ ከስጠትም ይልቅ ችግሮቹ በተከሰቱበት ሀገረ ስብከት አስተዳደር ውስጥ ጣልቃ በመግባት ግጭቶች እንዲባባሱ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡

19. በተለያዩ ጊዜያት የቤተ ክርስቲያኒቱን የኢኮኖሚያዊ ልማት ተሳትፎ ያሳድጋሉ፣ ገዳማትንና የአብነት ትምህርት ቤቶችን ከመዘጋት ያድናሉ ተብለው የታመባቸው የተለያዩ የልማት ፕሮጀክት ጥናቶች ለምሳሌ የቱሪዝም፣ የግብርናና ወዘተ ተግባራዊ እንዲሆኑ በቅዱስ ሲኖዶስ ከተወሰነ በኋላ ሥራ ላይ እንዳይውሉ ሆን ብለው አምባገነናዊ ሥልጣናቸውን በመጠቀም ተዳፍነው እንዲቀሩ አድርገዋል፡፡

20. ፓትርያርኩ በሚሰጧቸው የልብ ልብ ስለ ፓትርያርኩ እንጂ ስለ ቤተክርስቲያን የማያውቁና የማይጨነቁ ቤተ ዘመዶቻቸው ሊቃነ ጳጳሳትን ሳይቀርና እውነተኞች የቤተ ክርስቲያኒቱን አገልጋዮች እየገላመጡ እና እያሳቀቁ ነጻነት እንዳይሰማቸው ያደርጋሉ፡፡

21. የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽንና የኪራይ ቤቶች አስተዳደር የገንዘብ ስርጭት እና አጠቃቀም ላይ የእርሳቸውን የግል ጥቅም በሚያስከብር ስውር መንገድ የሚሠራበት ሁኔታ በመኖሩ ቤተ ክርስቲያኒቱን ለከፍተኛ ሙስና እየዳረግዋት ነው፡፡ ለምሳሌ ቢያንስ በወር ውስጥ ለግል ጥቅማቸው ህጋዊ ባልሆነ አሠራር ከቤቶች ኪራይ እስከ 10‚000.00 (አሥር ሺህ) ብር ይወስዳሉ፡፡ ይህም በቤተ ክርስቲያኒቱ ሀብት ላይ በማን አለብኝነት እንደፈለጋቸው እያዘዙ መሆኑን በግልጽ ያሳያል፡፡

22. የቤተ ክርስቲያኒቱን ሚዲያዎች በተገቢው መንገድ አደራጅቶ ለምዕመናን የማስተማሪያ እና ቤተ ክርስቲያኒቱን ማስተዋወቂያ መንገድ ከማድረግ ይልቅ ያለምንም ኤዲቶሪያል ፖሊሲና ግልጽ አሠራር ለራሳቸው መጠቀሚያ እንዲሁም ማሳደሚያ አድርገዋቸዋል፡፡ ይህም ሰዎችን ስለ ቤተ ክርስቲያኒቱ የተሳሳተ ስዕል እንዲኖራቸው አድርጓል፡፡
23. በአጠቃላይ ቤተ ክርስቲያኒቱ ራዕይ አልባ እንድትሆን ማድረጋቸው አስቸኳይና አፋጣኝ መፍትሔ የሚፈለግለት ጉዳይ ሆኗል፡፡ በመሆኑም አስፈላጊ የሆነውን የመፍትሄ ሃሳብ ከልብ አጢኖ አፋጣኝ እርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል፡፡

ምንጭ፦ “የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዋና ዋና አንገብጋቢ ችግሮች እና መፍትሔዎች፦ ከፍተኛ ትኩረት የሚሻ” (ግንቦት 2001 ዓ.ም)፤ ከገጽ 3-9።


ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፣ ወእጬጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣
ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱምና የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ለሰላም የክብር ፕሬዚደንት፣
በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላይ የፈጸሟቸው ዐበይት ችግሮች
ምንጭ፦
“የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዋና ዋና አንገብጋቢ ችግሮች እና መፍትሔዎች፦ ከፍተኛ ትኩረት የሚሻ”
(ግንቦት 2001 ዓ.ም)፤
ከገጽ 3-9።
ቅንብር፦
“ደጀ ሰላም” http://deje-selam.blogspot.com/

August 5, 2009

“ደጀ-ሰላም” አዲስ የሃይማኖት ጡመራ ፈር መቅደዷ ተዘገበ

(ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 5/2009)፦ “ደጀ-ሰላም” በሃይማኖት ላይ ብቻ በማትኮሯ አዲስ የጡመራ ፈር መቅደዷን አንድ የአማርኛ ተወዳጅ ጋዜጣ ዘገበ፤ የአዘጋጆቹ ማንነት ደግሞ እያወዛገበመሆኑን መሰከረ። “አዲስ ነገር” የተባለው ታዋቂ የአዲስ አበባ ጋዜጣ በቅዳሜ ኦገስት 1/2009 እትሙ “የሃይማኖት ብሎጎች ዳዴ” በሚል ርእስ ባወጣው ዘገባ “ደጀ ሰላም” የጡመራውን መስመር በአንባቢ ብዛት በመምራት ላይ እንደምትገኝ ገልጿል።

በቅርቡ በቤተ ክህነቱ በተፈጠረው ግርግር የአንባቢ ብዛቷ ከፍ እንዳለላት የተለያዩ አንባቢ መቆጣጠሪያ ዘዴዎችን አጥንቶ የዘገበው “አዲስ ነገር” ጋዜጣ ከሌሎች ኢትዮጵያዊ የእምነት ድርጅቶች ጋር (ለምሳሌ እስልምናና ፕሮቴስታንቲዝም) ሲነጻጸር ግን የአንባቢዋ ቁጥር አሁንም አነስተኛ መሆኑን አስቀምጧል። ጋዜጣው “ደጀ ሰላም” ለብሎጊንግ የሰጠቻቸውን ስሞች ተውሶ “ጡመራ፣ መጦመር” እያለ ዘገባውን ያቀረበ መሆኑም ታውቋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በኢትዮጵያ ባለው “የብሎጊንግ ወይም የጡመራ ግርዶሽ” (Blog Blocking የሚለውን ሐሳብ ለመግለጥ ፈልገን ነው) ምክንያት በኢትዮጵያ በቀላሉ የማትነበበው “ደጀ ሰላም” በቤተ ክህነቱ ዘንድ ታዋቂ መሆኗን የዘገበው “አዲስ ነገር” የአዘጋጆቹን ማንነት ለማወቅ ጉጉት እንዳለ ገልጿል። በስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ የቅርብ እትሙ “አትወክለኝም” በማለት መግለጫ የሰጠውን ማህበረ ቅዱሳንንም በማስረጃነት ማንሳቱ ታውቋል።
ከዚህ በፊት ቅዱስ ፓትርያርኩና ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ስለ “ደጀ ሰላም” አንስተው መናገራቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

የማፊያው ቡድን በብፁዕ አቡነ አብርሃምና ሌሎች ተቃዋሚዎቹ ላይ የቃላት ጦርነቱን ጀምሯል

(ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 4/2009)፦ የማፊያው ቡድን ድምጽ የሆነው “ሀገር ፍቅር” ሬዲዮ “ሕገ ቤተ ክርስቲያን ይከበር” በሚሉ አባቶችና ክፍሎች ላይ የጀመረውን ጥቃት በማጠናከር በቅርቡ የግል አስተያየታቸውን በመስጠት መግለጫ ያወጡት ብፁዕ አቡነ አብርሃም ላይ ዘመቻ መጀመሩን አወጀ።
የዚሁ የማፊያ ቡድን ጋዜጠኛ ንጉሤ ወልደ ማርያምና የእንስሳት ሐኪሙ ዶ/ር በላይ ሀብተ የሱስ በያዙት በዚሁ አዲስ ዘመቻ በውጪ ሀገር የሚገኙ አባቶችን ስም ለማጥፋት ዝግጅት በማከማቸት ላይ እንደሚገኙ በይፋ ተናግረዋል።

ንጉሤ ወልደማርያም ከጥቂት ዓመታት በፊት “አባ ዲያቢሎስ፤ የሰይጣን መልእክተኛ፤ የወያኔ ፓትርያርክ” ይላቸው የነበሩትን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስን በአሁኑ ወቅት ደግሞ “ከርሶ በላይ ቅዱስ የለም፣ አልቦ እም ቅድሜከ ወአልቦ እም ድኅሬከ” ማለት “ከእርሶ በፊት እንደርሶ ዓይነት ቅዱስ ተፈጥሮ አያውቅም ከዚህ በኋላም አይፈጠርም” እያለ ማሞካሸት መጀመሩ ይታወቃል።
ሬዲዮው ዘመቻውን የሚያደርገው “ሕገ ቤተ ክርስቲያንን” በተመለከተ መግለጫ ባወጡት በሌሎች አብያተ ክርስቲያናት ላይም ይሁን በብፁዕ አቡነ አብርሃም ላይ ብቻ ለጊዜው የታወቀ ነገር የለም። ጊዜው ሲደርስ የምናየው ይሆናል።
ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን
++++++
የወቅቱን የቤተ ክርስቲያን ችግር አስመልክቶ ብፁዕ አቡነ አብርሃም ጥሪ አስተላለፉ

Here below, you will find comment from Azikiri blog.


Help them Loose hope NOT!!!
the Ninjas look to be effective in two fronts. The first is to make the fathers who were steel strong to expell them out of the house feel hopless and pesimist about the October Synodal Meeting. Some of them are reported to say that they will boycot the meeting as they did when the so called resolution was drafted. If this will happen, we will stay painful looking at the pains of our mother church. The second one is on persuading those archbishops to line themselves with the other wing. There is an ongoing effort to double the number of the supporters of their evil idea. If this continues, many afraid that the viruses will stay in the house. So it would be helpful to call all the Archbishops and make our points. Let us help them to be optimistic than pesimistic.

AD21


Regarding Comments: Editorial

Dear Dejeselamaweyan,
(Deje Selam; August 4/2009):-We have read different comments regarding comment-moderation. Some say, posting comments should be open while others stand against it. Some of you even go as far as aliening Deje Selam with people like Tesfa and blasphemers. One writer said, quote:

If you continue to give space to the anti-Tewahedo harangues of the protestant "tesfa",and his likes, you are responsible for the propaganda damage caused by these people against our Tewahedo Orthodox Church. Many have repeatedly asked you to remove any and all anti-Tewahedo comments.


Well, we have two options here: we should either shut the comment page or leave it ope so that we may share ideas. We, on the part of Deje Selam team, can not let open at the same time go after each and every comment to delete the bad ones. That is technically impossible. We have many things to do, friends. Come on!!! Blogging is not our full time job. Thus, let us forget the bad ones, and try to win over them. Let us not read what they write. Just ignore them and read what is good for us.
Unless we see the bad ones and ignore or stand them, how can we be called Christians? Why don't you ask God to dstroy Satan alltogether sothat people will no more be cheated by him? That is very fulish guys. There are good and evil people every where. We fight the evil, and go with the good ones. Ok? That is how we see it. If there are people who do not accept this and think we are supporting whoever is writing bad here, we cant help it. Go open your blog and do whatever you want to do. This is a free world. We are trying to do our best.

Cher Were Yaseman,
Amen

August 4, 2009

የምእመናን ቀን በዓል

ውድ ደጀ ሰላማውያን
(ኦገስት 3/2009)፡- የአንድነትና አብሮ የመሥራት ዜና በጠፋበት በዚህ ሰሞን “የዲሲ ምእመናን ዜና” የሚያበረታታ ሆኖ አግኝተነዋል። ደጀ ሰላም በበኩሏ ደጀ-ሰላማዊ ጦማሪዋን አቤል ዘቀዳማዊን እያመሰገነች፣ በሥፍራው ባትገኝም የዘቀዳማዊን ዓይን ዓይን አድርጋ ተመልክታ፣ በአስተያየቱ ተደስታ፣ ለእናንተም “እነሆ” ትላለች። ወንድማችን በጡመራህ ቀጥል ተብለሃል። መቸም የአሜሪካ ድምጡ አዲሱ አበበን የሰኞ ዘገባ ሳታዳምጡት አልቀራችሁም ብላ ደጀ ሰላም ተስፋ ታደርጋለች። ካልሰማችሁ ግን መስማታችሁ ስለ ጉባዔው ሙሉ መረጃ ይሰጣችሁዋል።


(Picture: Children singing Mezmur at the ceremony)
ስለ ዲሲው የምእመናን ቀን በዓል አቤል ዘቀዳማዊ እንደዘገበው
ጅምር ሆኖ እንዳይቀር እንጂ በዋሽንግተን ዲሲ ሀምሌ 22 እና 26 2001 ዓ.ም የተካሄደው የምእመናን ቀን በዓል ይበል በርቱ የሚያሰኝ ነበረ። ጅምር ሆኖ እንዳይቀር ያልኩበት ምክንያት እዚሁ አካባቢ ያሉት አብያተክርስቲያናት በተለያዩ ጊዜያት ስለ አንድነት እንዲሁም አንድ ሆነናል በማለት ይናገራሉ፤ ነገር ግን ፍፃሜያቸው ወደ ቀደመው ግብራቸው ነው። ከዚሁ በዓል አዘጋጆች እንደተረዳሁት ዋናው ዓላማቸው የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ምእመናንን አንድ ማድረግ የሚል ነው። የዝግጅቱም መልዕክት “ምንም እንኳ አባቶች ቢለያዩም እኛ ምእመናን ግን ከአንዲት ተዋሕዶ እምነት የተወለድን ስለሆንን አንለያይም አንድ ነን” የሚል ነበር። ታድያ አንድነትን ማን ይጠላል? ይህ የታለመው አንድነት እንዲመጣ ግን የአንድነት መሠረት ምን መሆን አለበት የሚለው መታወቅ አለበት። በእርግጥም ከአንዲት ተዋሕዶ ሃይማኖት መወለዳችን አንድ ያደርገናል። በአባቶች መከፋፈል ምክንያት እኛም ምእመናኑም ተከፋፍለናል።
ስለዚህ የዚሁ የተቀደሰ ዓላም አዘጋጆች አንድ ነገር እንድታስቡበት እወዳለሁ፤ ይውም ወደ ፍጹም አንድነት እንድንመጣ ከዝግጅቱ አንድ ክፍል ውስጥ ለእይታ ያቀረባችሁት የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ የአስተዳደር መዋቅር የሚለው እዚሁ እኛ ያለንበት አካባቢ በተግባር እንዲውል ከሚመለከተው ክፍል ሁሉ ብትነጋገሩበት ሥራችሁ የበለጠ ዋጋ ያገኛል። የአድነቱም መሰረት መሆን ያለበት እሱ ነው፤ ዝም ብለን አንድ እንሁን የምንል ከሆነ ግን ሁል ጊዜም ከተለያዩ አንደበተ ርዕቱ ሰባኪን ወንጌል የምንሰማው ቃል ነው። በዘላቂነት አንድነታችን የሚጸናው ቤተክርስቲያናችን አንድ ስትሆን ብቻ ነው። አንድነቷም የአስተዳደር መዋቅሯ ከላይ ከቅዱስ ሲኖዶስ እስከ ታች አጥቢያ ቤተክርስቲያን ድረስ ያለው ሁሉም ሲጠብቀው ብቻ ነው።
ከዚህ በፊትም በዚሁ በደጀ ሰላም አንድ አስታያት መስጫ ቦታ ላይ እንደገለጽኩት በሰሜን አሜሪካ በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢዋ ማለትም ዲሲ፤ ሜሪላንድና ቨርጂኒያ ውስጥ በኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ስም የሚጠሩ በብዛታቸው 18 (አስራ ስምንት) በአስተዳደር አይነታቸው ደግሞ 7 (ሰባት) የተለያዩ አብያተክርስቲያናት ይገኛሉ። የአብያተክርስቲያናቱ አይነት እኔ የማውቃቸውን ልንገራችሁ፦
1. ራሱ ስደተኛ ሲኖዶስ ብሎ የሚጠራው ቡድን ውስጥ የሚተዳደሩ አብያተክርስቲያናት
2. ራሳቸው ገለልተኛ ነን በማለት የሚጠሩ በገለልተኝነት የሚተዳደሩ አብያተክርስቲያናት
3. በግለሰብ ስም የአባ ኤገሌ ወይም የአቶ ኤገሌ ተብለው የሚጠሩና በግለሰቦቹ የሚተዳደሩ አብያተክርስቲያናት
4. ፓትርያርኩን እንቀበላለን ነገር ግን ሀገረ ስብከት አንቀበልም የሚሉ አብያተክርስቲያናት
5. የኢትዮጵያ ቅዱስ ሲኖዶስ እንቀበላለን ነገር ግን ፓትሪያርክ አባ ጳውሎስ አንቀበልም የሚሉ አብያተክርስቲያናት
6. ከአሜሪካ ውጪ በሚገኙ ሊቃነ ጳጳሳት ወይም ቆሞሳት በበላይ ጠባቂነት ወይም በባለቤትነት የሚመሩና የሚተዳደሩ አብያተክርስቲያናት
7. የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን አስተዳደራዊ መዋቅር በመጠበቅ በሀገረ ስብከት የሚተዳደሩ አብያተክርስቲያናት
እስቲ ስለቤተክርስቲያናችን አንድነት እንወያይ ጎበዝ!!! የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ቃለ ዓዋዲ ወይም የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ደንብ ስለ የቤተክርስትያን አስተዳደር ምን ይላል?
እግዚአብሔር የቤተክርስቲያናችን አንድነት ይጠብቅልን። አሜን!!!

++++
A presentation of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church (Washington DC, DC, VA, MD)

A presentation of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church

Come and learn about the rich history and tradition of the church which has held on to the faith of the apostles for over 2000 years.

Exhibition in Amharic and English featuring:

* Presentation on the contributions of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church to Ethiopia and the world
* The Ecclesiastical Melodies of Saint Yared
* Audiovisual presentation of the Monasteries and Churches in Ethiopia
* A display of sacred objects
* A special area for children
* Sermons on unity
* Information about charitable organizations that works closely with the church
* Testimonials of miracles that are being seen in today's Ethiopia
* Hymns, poems, plays, and much more.

Location:
Washington Monument Grounds, 15th and Constitution Ave, NW

Date/Time:
Saturday, August 1st, 2009, 11:00 AM - 7:00 PM
Sunday, August 2nd, 2009, 11:00 AM - 7:00 PM

For more info: EOTCDAYDC@gmail.com
Coordinator: Nibure'ed GebreHiwot Melissie
Yohannes Teklu, Tel 301 899 6521
Shewakena Habteyes, Tel 301 404 7582
Amarech Tademe, Tel 202 297 0610


ቅዱስ ፓትርያርኩ ሕገ ቤተ ክርስቲያን የማሻሻል ርምጃ ጀምረዋል

• ቋሚው ሲኖዶስ የፓትርያርኩን ሕግ የማሻሻል ጥያቄ አልተቀበለውም ነበር፤
(ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 3/2009)፦ በግንቦት 2001 ዓ.ም የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ከብፁዓን አባቶች በተነሣባቸው ጥያቄና አስተያየት ተቃውሞ የገጠማቸው ቅዱስ ፓትርያርኩ “ሕገ ቤተ ክርስቲያን” ተባለውን የቅዱስ ሲኖዶስ መመሪያ ለማሻሻል እንቅስቃሴ ጀመሩ። ታማኝ ምንጮች ለደጀ ሰላም እንደገለፁት በ1991 ዓ.ም ወጥቶ በሥራ የሚገኘውንና ፓትርያርኩ ከብፁዓን አባቶች ጋር ክርክር በገጠሙበት ወቅት አላፈናፍናቸው ያለውን ሕግ ለመቀየር ቆርጠው መነሣታቸው ታውቋል።

ከጥቅምቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ በፊት ሕጉን ለውጠው ለመቅረብ የወሰኑት ቅዱስነታቸው ይህንኑ እንዲያስፈጽሙ ለሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በደብዳቤ መመሪያ ሰጥተዋል ተብሏል። ጉዳዩን አስቀድመው ለቋሚ ሲኖዶስ ያቀረቡት ቅዱስነታቸው ቋሚ ሲኖዶሱ “ሕጉን ለማሻሻል መብት የለኝም፣ ሕጉን ለማሻሻልም አሁን በቂ ምክንያት አላገኘሁም” በማለቱ ነገሩ ወደ ሌሎች ሊቃውንት ሊመራ እንደቻለ ተጠቁሟል።

“ሕገ ቤተ ክርስቲያንን ማጥናት ስለማስፈለጉ” በሚል መሪ አጀንዳ በቅዱስነታቸው የተጻፈው ይኸው ደብዳቤ ፓትርያርኩ የቁልቢ ገብርኤልን በዓል ለማክበር ከመሄዳቸው በፊት ተጽፎ ተሰራጭቷል። ደብዳቤው የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥርዓት ባልጠበቀ መልኩ ግልባጭ ሊደረግላቸው የሚገቡ ግለሰቦችንና ቢሮዎችን ሳይጠቅስ አልፏል ተብሏል። ደብዳቤው ለሥራ አስኪያጁ ለብፁዕ አቡነ ይስሐቅ ብቻ ግልባጭ የተደረገ ሲሆን ለቋሚ ሲኖዶስ እንኳን ግልባጭ አልተደረገም ተብሏል።

የቤተ ክርስቲያኒቱን ቀኖናዊ ሥርዓት የሚጥስ፣ የቤተ ክርስቲያኗን አንድነት የሚያደፈርስ አዝማሚያና ችግር ሲገጥም ሊቃውንት ተሰብስበው ዕቅድ አውጥተው፣ ለተከሰተው ችግር መንስዔ የሆነውን ሕገ ደንብ በመመርመር ሕጉን በማሻሻልና አስፈላጊውን መፍትሔ በማሳለፍ መፍትሔን እንደሚያስገኙ ይታወቃል።

“እንደሚታወቀው ሁሉ የሰሞኑ ዘርፈ ብዙ ችግር ጊዜያዊ መፍትሔ ያገኘ ቢሆንም የዘለቄታውን የሥራ ደህንነት በተመለከተ ከፍትሕ መንፈሳዊ፣ ከሌሎች ቀኖናዊ ሥርዓት ካላቸው መንፈሳዊ መጻሕፍት፣ ከቤተ ክርስቲያኒቱ ተጨባጭ የሥራ እንቅስቃሴና ቀደምት አበው ሲሰሩባቸው ከኖሩት የታሪክ መዛግብት አንጻር አሁን እየተሠራበት ያለውን ሕገ ቤተ ክርስቲያንን በማየት ወጥ ሕገ ቤተ ክርስቲያን አዘጋጅታችሁ ታቀርቡ ዘንድ ይህ የቤተ ክርስቲያናችን የጥሪ መልእክት እንዲደርሳችሁ ማድረግ አስፈልጓል”

የሚለው የቅዱስነታቸው መመሪያ ተግባራዊ ይሆን ዘንድ ብፁዕ አቡነ ገሪማ የኮሚቴው ሊቀ መንበር ሆነው ተሰይመዋል።

ደብዳቤው የተጻፈውም
1. ለቀሲስ ዶ/ር ምክረ ሥላሴ ገብረ አማኑኤል፣
2. ለመጋቤ ብሉይ ሰይፈ ሥላሴ ዮሐንስ፣
3. ለሊቀ ካህናት ብርሃኑ ገብረ አማኑኤል፣
4. ለንቡረ ዕድ ኤልያስ አብርሃ፣
5. ለመላከ ታቦር ተሾመ ዘሪሁን፣
6. ለዶ/ር አዲስ የሻነው (የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ መምህር)፣
7. ለአቶ ይስሐቅ ተስፋዬ፣
8. ለመጋቤ ሠናያት አሰፋ ሥዩም (የዚህ ኮሚቴ ፀሐፊ ሆነዋል)፣ እና
9. ለብፁዕ አቡነ ገሪማ መሆኑ ታውቋል

August 2, 2009

ሰበር ዜና (Breaking News) የፓትርያርኩ ረዳት በቁጥጥር ሥር ዋሉ

• “ታዝዤ ነው” የጥበቃ ክፍል ኃላፊ አቶ ብርሃኔ

(ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 1/2009): የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ረዳት (አቡነ ቀሲስ) አባ ዕንቁ ባሕርይ ከቤተ ክህነቱ የብፁዓን አባቶች ቤት የሌሊት ድብደባ ጋር በተገናኘ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ውስጥ አዋቂዎች ገለፁ።

Dear Dejeselamaweyan,
This news is refuted by Ben of Ethiopiafirst.com. Ben also insulted Deje Selam, for the reasons we did not know yet. We have one thing to say to brother Beniam though: this whole issue is not about you and us; it is about our Mother Church. Please stop the unwanted cyber war both of us do not want to wage. OK, brother? We don't think you understand the Church issue as an outsider. Leave the Church alone. As per the incarceration of Abba Enqu Baherey, we have reconfirmed his imprisonment. If there is any development as of then, we will report accordingly.
Cher Were Yaseman,
DS

+++++

ጁላይ 15/2009 ሌሊት ጨለማን ተገን አድርገው ወደ ብፁዓን አባቶች መኖሪያ ሕንጻ በመግባት ጥቃት ያደረሱትን ወንጀለኞች ጉዳይ በመመርመር ላይ የሚገኘው ፖሊስ የቤተ ክህነቱን ጥበቃ ክፍል ኃላፊ አቶ ብርሃኔን ... ባለፈው ረቡዕ በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ ማድረጉም ታውቋል። ግለሰቡ የግቢውን ጥበቃ የሚቆጣጠሩ እንኳን ሰው ወፍ ዝር ብትል የሚያውቁ ሆነው ሳለ ይህንን የሚያህል ትልቅ ወንጀል ሲፈጸም “ምንም አላውቅም” ማለታቸው ይታወሳል። ስለ ጉዳዩ ቃለ ምልልስ ልታደርግ የደወለችውን የዶቼቬሌ ጋዜጠኛ “ልጃቸው ነኝ” በማለት ለማታለል የሞከሩት አቶ ብርሃኔ ለፖሊስ ጉዳዩን እንዲፈጸም ያደረኩት “ታዝዤ ነው” ካሉ በሁዋላ በዋስ እንደተለቀቁ ታውቋል። አቶ ብርሃኔ ነገሩን ለማመን የተገደዱት ሌሎች ሁለት የጥበቃ ሰራተኞች ስለ መሩባቸው ነው ተብሏል።

ፖሊስ ምርመራውን በመቀጠል ጉዳዩ ወደ ቅዱስ ፓትርያርኩ ጽ/ቤት የመራው ሲሆን በዚሁ ምክንያት ለአቶ ብርሃኔ ትዕዛዝ በመስጠት ወንጀሉ እንዲፈጸም አስደርገዋል የተባሉት የፓትርያርኩ ረዳት አባ ዕንቁ ባሕርይ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ታውቋል። ለአቶ ብርሃኔ ትዕዛዝ ሰጥተዋል የተባሉት አባ ዕንቁ ባሕርይ “ያዘዝኩበት ወረቀት የታለ” በማለት ለማምለጥ መሞከራቸው ተሰምቷል። ጉዳዩ በዚሁ ከገፋ አባ ዕንቁ ባሕርይ ራሳቸው ከማን ትዕዛዝ እንደተቀበሉ በጉጉት የሚጠበቅ ምስጢር ይሆናል ማለት ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ወንጀሉን የፈጸሙት ሰዎች በሁለት መኪና ተጭነው ወደ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ግቢ የገቡት ሁሉም ሰው በሚገባበት በር ሳይሆን ፓትርያርኩና የተወሰኑ እንግዶች (ቪ.አይ.ፒዎች) የሚገቡበት የፓላሱ ዋና መግቢያ በር እንደሆነ ታውቋል። ከአባቶች ስልክ የተደወለለት ፖሊስ በሌላኛው በር ለመግባት ሲሞክር የጥበቃ ሰራተኞች “አገር ሰላም ነው” እያሉ የመለሱት በዚህ ምክንያት ነው ተብሏል።

አባ ዕንቁ ባሕርይ ሐሙስ ከተያዙ በሁዋላ ፍርድ ቤት ቀርበው የ14 ቀን ቀነ ቀጠሮ ተጠይቆባቸው ወደ ማዕከላዊ እስር ቤት ገብተዋል። ስለ ጉዳዩ አስተያየታቸውን የጠየቅናቸው ውስጥ አዋቂዎች አንድ አቡነ ቀሲስ (ረዳት) በራሳቸው ፍላጎት እንዲህ ዓይነት ትዕዛዝ ለመስጠት እንደማይሞክሩ ተናግረው ትዕዛዙ ከርሳቸው በላይ ከሆነ ሰው ሳይመጣ እንዳልቀረ ገምተዋል።

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)