July 30, 2009

+++++++ - - - - - - ???? ?? About Mahibere Kidusan


Dear Deje Selamaweyan,
Greetings to you all.
Although our mother Church is in great problem, most of us tend to argue about some points only, one of which is Mahibere Kidusan.

For the Church's sake, please limit all your comments about Mahibere Kidusan here. Positive, negatives or questions about MK should and must be posted here. Please be civil!!!
The burning issue for Deje Selamaweyan should be what we should do untill Tikimt. We will re bring that topic to the forfront.

Chere Were Yaseman,
amen
+++++++++++++++++++++++++
(አቤል ዘቀዳማዊ)
ደጀ ሰላም ከምታቀርብልን የመወያያ አርስት እየወጡ በተለያዩ አርስቶች ግርጌ እነ እውነቱ እና መሰሎቹ የማኅበረ ቅዱሳንን ሥም እያነሱት ነው። ለመሆኑ ማኅበረ ቅዱሳን የሚጠሉ ሰዎች እነ ማን ናቸው? በአጠቃላይ ማኅበረ ቅዱሳንን የሚጠሉ ሰዎች በሦሥት ከፍለን እንያቸው፦
፩. በዓላማ እንዲጠፋ የሚፈልጉ ናቸው
• አክራሪው የእስልምና ቡድን
• የቤተክርስቲያን የውስጥ መናፍቃን(ተሃድሶ)
• መናፍቃን(“ጴንጤ”)
እነዚህ ከላይ የጠቀስኳቸው ቡድኖች የማኅበሩን አገግሎት በደንብ ጠንቅቀው ያውቁታል፤ እንዲሁም ዓላማውም በሚገባ ተረድተውታል። አክራሪው እስላም በቤተክርስቲያን ላይ በተለያዩ ጊዜያት የሚያደርሱት ጥፋት እየተከታተለ መረጃ እየሰበሰበ እኩይ ተግባራቸውን እያጋለጣቸው ስለሆነ የማኅበሩን መኖር የእግር እሳታቸው ነው። ወደፊትም ላቀዱት ጥፋት ይከታተለናል ብለው ስለደመደሙ ማኅበሩ እንዲጠፋ ደፋ ቀና እያሉ ነው።ይህ ማኅበር ኢትዮጵያን የማስለም ዓላማ ተግባራዊ ለማድረግ እንቅፋት ሆኖብናል ብለው በግልፅ በተለያዩ የእስልምና ፓል ቶክ ውይይት እየሰማናቸው ነው።
ሌሎቹ ሁለቱም መናፍቃን የውስጡም የውጩም ግብራቸውና ዓላማቸው ማኅበሩ በሚገባ አውቆት አጥብቆ ስለሚቃወማቸው እነሱም ይሄንን ስለተረዱት የተለያዩ አጋጣሚዎች በመጠቀም ስሙን ሲያነሱት እናያቸዋለን፤ እዚህ ላይ እውነቱን(ውሸቱን) ልብ በሉልኝ። እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ሁለቱም መናፍቃን የተዋህዶ እምነትን የማጥፋት ዘመቻቸው ማህበሩ እስካለ ድረስ ማስፈጸም አንችልም ብለው ስለወሰኑ በማንኛውም መንገድ እንዲሁም ከአክራሪው እስላሙ ጋር ተባብረውም ቢሆን ሊያጠፉት ይፈልጋሉ።
፪. የቢተክህነቱ ወሮበሮች(ማፍያ/ጨለማን የወ ደዱ) አካላት
እነዚህኞቹ ደግሞ በጊዜአዊ ጥቅምና ሥልጣን የሰከሩ ናችው። አቶ ንጉሴም ከነዚህኞቹ ቡድን ጋር መድቤዋለሁ። ማኅበሩን የሚጠሉበት ዓላማቸው ማኅበሩ በያዘው የቅዱስ ሲኖዶስ ልዕልና ይከበር የሚለው ጥብቅ አቋሙ ነው። ይኸው እነዚህ ሆዳቸው አምላክ የሆነባቸው ወገኖች ማኅበሩን ቢችሉ ለማፍረስ ነበረ፤ ነገር ግን ስላልቻሉ የማኅበሩን ስም የማጥፋት ዘመቻ ተቀጣሪው ጀሌያቸው አቶ ንጉሴ ጀምሮታል።
፪. የማኅበሩን አገልግሎትና ዓላማ ያልተረዱ ወገኖች
እነዚህ ወገኖች ማኅበረ ቅዱሳንን በሥም ብቻ ያውቁታል። የማኅበሩ ሥም እንኳ የሰሙት ከተሃድሶ መናፍቅ፤ ከአቶ ንጉሴ ወይ ደግሞ ከአክራሪው እስላም ነው። እናም አንድ ጊዜ የሰሙት ወሬ ብቻ ይዘው ማኅበሩን ይጠሉታል። እንደው ማኅበረ ቅዱዳን ማን ነው፤ ዓላማው ምንድ ነው፤በቤተክርስቲያኒቱስ የትኛው መዋቅር ሥር ነው ያለው፤ ብሎ ለመጠየቅ ጆሮዋቸው የዘጉ ባይጠፉም፤ ለመጠየቅ ተዘጋጅተው አጋጣሚው ያላገኙ ወገኖች እንዳሉም እገምታለሁ።
እግዚአብሔር ተዋህዶ ሃይማኖታችን ይጠብቅልን!!! አሜን።
አቤል ዘቀዳማዊ

+++++++
የሀገር ፍቅር ራዲዮ - አለመታደል!

ዘክርስቶስ

አገር ቤት ከርሜ መጣሁ። መቼም የኛ ነገር ”መለያየት ሞት ነው” ሳይሆን ”መለያየት ሕይወት ነው” የተባለ ይመስል ”መለያየት መለያየት አሁንም መለያየት” ሆኗል ሥራችን። ለምሳሌ ስሙን ”አንድነት” ብሎ የሰየመው ፓርቲ ወደ መለያየት እያመራ መሆኑ ለሰማ ሰው ባይገርም ደስ አይልም። እጅግ በጣም እጅግ አሳዛኙ ነገር ግን በቅዱስ ሲኖዶስ ዙሪያ የሆነው እና እየሆነ ያለው ነገር ነው። ደጉ ንጉሥ ክርስቶስ መፍትሔውን ይስጠን!
አገር ቤት ሆኖ ብሎጎችንና እና አጽራረ መንግሥት የሆኑ ገጸ ድሮችን ማየት አይቻልምና ለ፮ ሳምንታት እዛ ያሉትን ሚድያዎች ነበር የምከተታለው። በፕሮክሲ ስሞክርም ያው አንዴ መብራት አንዴ ስልክ እየጠፋ አገር ቤት እየሆነ በነበረው ነገር ዙሪያ በዝርወት ያሉት ድረ ገጾች እና ራዲዮኖች ምን እያሉ እንደሆነ በኢንተርኔት ዳሰሳ ለማወቅ አልቻልኩም ነበር። እናም ትላንት ወደ ሁለተኛው አገሬ መጥቼ ማንበብና ማዳመጥ ያዝኩ። ቀልቤን የሳበው በማኅበረ ቅዱሳን ዙሪያ የዘነበው የሀገር ፍቅር ራዲዮ የስድብ ሞገድ ነው።
የ፲፩ ዓመት የራዲዮው አድማጭ እንደመሆኔ መጠንና ማኅበረ ቅዱሳንን በቅርብ የማውቄን ያህል ራዲዮው ስለማኅበሩ ባቀረባቸው ዝግጅቶች ዙሪያ አንድ ሁለት ነገር ለማለት እነሆ ተነሳሁ።
በሚመስለኝ ነገር ወይም በምመኘውና በምገምተው ነገር ሳይሆን በማውቀው ነገር ላይ ነው የማተኩረው። አቶ ንጉሤና ዶ/ር በላይ በማኅበረ ቅዱሳን ዙሪያ እያቀረቡት ያለው ነገር ፍጹም ሐሰት ከመሆኑም በላይ ታላላቅ ጉዳዮችን እንደ ጥቃቅን፤ በጎ ነገሮችን እንደ በደል፤ ያልተደረጉ ነገሮችን እንደተደረጉ፤ የተደረጉ ነገሮችን እንዳልተደረጉ አድርጎ የሚያቀርብ እጅግ የወረደ ዝግጅት ነው ብለው ደረጃውን አይገልጸውም። ታላላቅ ነገሮችን ከራሱ ስሜት፡ ጥቅምና አቅም ብቻ የሚመለከት ሰው መቼም ያልታደለ ነው ብዬ አምናለሁ።
እስቲ ከሚሉት ነገር አንዳንዱን ላንሳ።
ስለ አመሠራረቱ
ማኅበሩ ባልነበረበት ዘመንና ቦታ ነበረ ማለት የማይገናኙ ነገሮችን በማገናኘት ኢህአፓን ሉሲ ነች ያቋቋመችው ወይም ኢህአፓ በነሉሲ ዘመን ነበር ከሚለው ተረት ጋር ሲነጻጸር ልዩነቱ የዘመን ርዝማኔ ብቻ ነው ።
ስለ አደረጃጀቱና ስለ አባላቱ
ከጥሩ ጭንቅላት የሚወጣን ጥሩ ንግግር የሚያደርገውን ልጅ ”ተንኮለኛ” እያለ በሚጠራ ማኅበረሰብ ያደግን ነና የኛ ነገር መውቀስ የምንፈልገው አካል ካለ የሚያስወቅስ ነገር ይኑረውም አይኖረውም ሳይገደን በጎ ነገሩን ሁሉ እየጠቀስን እንደ መጥፎ ነገር ነው የምናወራው። ሀገር ፍቅሮችም የማኅበረ ቅዱሳንን ጠንካራ አደረጃጀትና የአባላት የማንነት ስብጥርን በተመለከተ ሲናገሩት ጥሩ ሆኖ እያለ ሲያቀርቡት ግን መጥፎ ለማስመስል ታትረዋል - ባይሳካላቸውም።
የተጠያቂነት ነገር
ስለ ኦዲትና ስለ ሂሳብም ከተነሳ በራሱ አሠራርና በፈቃጅ አካሉ እውቅና ያለው አሠራር አለው - ማኅበሩ። ይልቁንም የአድባራትና ገዳማት ሂሳብና ኦዲት ዘመናዊ አሠራር እንዲከተል ለማድረግ የሚያግዝ አቅም አለው - ስንታደል የምንጠቀምበት።
የገቢ ምንጭን በተመለከተ
ለቤተ ክርስቲያኒቱ መሠራት ካለበት ነገር አንጻር ማኅበሩ እጅግ ብዙ ገንዘብና ሌላ ቁሳዊ ግብአት የሚያስፈልገው ሥራ መሥራት ይቀረዋል። ከተመሠረተበት ጊዜ አንጻር ግን እግዚአብሔር ይመስገንና እጅግ ደስ የሚያሰኝ ሥራ ሠርቷል። እየሠራም ነው። ወደፊትም እንደ እግዚአብሔር ቸርነትም ከአባቶችና እና ኃላፊነታቸን ከሚወጡ ምእመናንን ጋር ሆኖ ይሠራል። እንኳን ታላላቅ ሥራዎችን ለመሥራት ቀርቶ እነ አቶ ንጉሤም እንኳን ራዲዮናቸውን ለማስቀጠል ገንዘብ ያስፈልጋቸዋል። እናም አነጋጋሪ ጉዳይ መሆን ያለበት የማኅበሩ ገቢ ማስገኛ ነገሮችን መክፈት ሳይሆን የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ጉዳያችን ለሆንን ሰዎች ሁሉ የሚያስቆጭ ነገር የማኅበሩ የገቢ ምንጭ ከሥራው አንጻር በበቂ ሁኔታና በብዛት አለመስፋፋቱ ነው። ለዚህም የሁላችን አስተዋጽኦ ያስፈልጋል።
ማኅበረ ቅዱሳን የሰዎች ስብስብ ነውና አባላቱ ድካም ይኖርባቸዋል። በቅዱሳን ስም እና የቅዱሳንን በረከት ምርኩዝ የእግዚአብሔርን ቸርነት መከታ አድርጎ የተቋቋመውም ድካም ያለባቸው ሰዎች ስብስብ በመሆኑ ነው። አባላቱ ከማንኛውም ሰው ጋር የሚጋሩትን ድካም ጠቅሶ ጥላሸት መቀባት ግን አየር ላይ በሚታዩ የፖለን ዱቄቶች ምክንያት የፀሐይ ብርሃንን ውበት አጣጥሎ ብርሃን አይደለም ጨለማ ነው ማለት እንዳይሆን ሁለቴ እናስብ።
በነፃ አገር በነፃ አየር የሀገር ፍቅር ራዲዮን የምትሰሙም ሆናችሁ ምንጭ ያደረገውን የስድብ መፅሐፍ የምታነቡ ወደ በአካል ወደ ማኅበሩ በመጠጋት ስለማኅበሩ ተረዱ። በአካለ ሥጋ ለማትችሉ የሚከተሉት ገጸ ድሮች ይጠቅማሉ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።
http://www.eotc-mkidusan.org/ http://www.mahiberekidusan.org/
http://www.tewahedomedia.org/
ስለሚታወቀው ነገርና መረጋገጥ ስለሚችል ነገር መናገር የማይችል ሰው ስለማይታወቀው ነገርና መረጋገጥ የማይችለውን ነገር በመጥቀስ ማስፈራራቱ የተለመደ ነው። አድማጮችና አንባቢዎች ግን ከዚህ ወጥመድ ውጡ። እንደሚታወቀው ስሜት፡ ወሬ እና ጤዛ በዛው መጠን እና ይዘት የሚቆየው ያው የጽድቅ ፀሐይ እስኪወጣ ብቻ ነው። ይህ የጽድቅ ፀሐይም ሁሌ እንደወጣ ነው።
እስከዛ ግን በዶክተር በላይ ማፈሬ ነው።

Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)