July 12, 2009

የጥብዐት ቁልፍ - Key To Resolution

Dear Deje_Selamaweyan,
Greetings to you all. Here follows you get a wonderful article by one "Deje-Selamawi/t".
Thank you Nahuda Nahuda for your contribution.
Cher Were Yaseman,
Amen
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++


(By Nahuda Nahuda)
“ገድል” የሚለውን ቃል በመጽሐፍ ስምነቱ ስለምናውቀው (ገድለ-ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ገድለ-አቡነ ተክለሃይማኖት ወዘተ. እንደምንለው) ፤ ገድል በግብር ስምነቱም ጭምር የቅዱሳን ሰማዕታት፣ የጻድቃን፣ የደናግል የመነኮሳት፣ የሊህ ብቻ፤ መስሎ የሚታየን ጥቂቶች አይደለንም። ነገር ግን ኀጢአት “እገባ እገባ” ስትል፤ እኛ “አናስገባ አናስገባ” በማለት እየተመካከትን እንድንታገላት ያስተማረን ቅዱስ ጳውሎስ የማንኛውም ክርስቲያን ሕይወት ገድል ወይም ተጋድሎ መኾኑን በግልጽ ያስረዳናል። ገድል ከታዘዘ እኛም ልንፈጽመው ይገባል። ኾኖም ከኀጢአት ጋር የሚደረገው ግብ ግብ ባንድ ጀንበር የሚያልቅ ሳይኾን ዛሬ የሚባል ዕድሜያችን እስካለ ድረስ የሚቀጥል ነውና እስከመጨረሻው ጸንተን ገድላችንን ለመፈጸም (ፍጹም ለማድረግ፣ ለማጠናቀቅም) ጥብዐት (ጭካኔ፣ ቁርጥ ሐሳብ) ያሻናል። እንደኔ እንደኔ ዛሬ ያጣነው ገድላችንን የምንፈጽምበት ጥብዐት ነው። ስለዚህም ጥብዐት የሚገኝበትን ቁልፍ የሚያሳየን ስለመሰለኝ ከዚህ በታች ያለውን መዝሙር ለአንባቢዎች ለማካፈል ወደድኹ፦
“ኦ ሰብእ ዕለተ-ሞትከ ተዘከር፤
ወጊዜ ፀኣታ ለነፍስከ፤
ዑቅ፣ ወጠይቅ፣ አእምር፣ ወለቡ፤
ብዕሉሰ ለሰብእ ከመ-ጽጌ-ገዳም፤
ወከመ-ሣእር ድኩም።”
(መዝ መክ ኢሳ)
እንዲያው በግርድፉ፦ “ዖቀ” ማለት “ዐወቀ፣ ጠነቀቀ (know/cognize) ፣” “ጠየቀ” ማለት “ተረዳ (ascertain/find out) ፣” “አእመረ” ማለት “ዐወቀ፣ አስተዋለ (be conscious/aware of)፣” “ለበወ” ማለት “ለበመ፣ ልብ አለ (understand/comprehend)” ማለት ነው። በግእዝ ቋንቋ ኹለት ተመሳሳይ ፍች ያላቸው (synonym) ግሦች በ“ወ” (በ“እና”) ተጫፍረው ሲመጡ፤ ደራሲው ነገሩን በአጽንዖት ለመግለጽ እንደተጠቀማቸው በማመን “ፈጽሞ…” ተብለው ይፈታሉ። ለምሳሌ፦ “ሖረ ወኀለፈ” ሲል “ፈጽሞ ኼደ፣” “ከተበ ወጸሐፈ” ሲል “ፈጽሞ ጻፈ” ያሰኛል ማለት ነው። እዚህ ላይ ታዲያ ደራሲው በምር እንዲገባን የፈለገውን ምስጢር ባራት አናቅጽ ኅብረት የፍች አንድነት እንዴት ያለ ጽንዕ እንደሰጠው ለማመልከት የትኛውን አንቀጽ አጎላማሽ (adverb) መጠቀም እንደሚቻል አላውቅም (እጅግ ፈጽሞ፣ ፈጽሞ ፈጽሞ፣ አካቶ ፈጽሞ፣ ፍጽምጽም አድርጎ…? እሊህ ኹሉ ለጆሮ አይጥሙም፤ ለልብም የሚረዱ መኾናቸውን እንዳኢ)። እንዲህ ባለ አጽንዖት የተገለጸ ሌላ ምሳሌ እንዳልፈልግ እንኳ ዐቅሜ ትንሽ ነው። ዳዊት በቃላቸው፣ ድጓ በጉንጫቸው ያለላቸው ሊቃውንት ለያመጡልን ይችሉ ይኾናል። እኔ በትንሿ ዐቅሜ የተረዳኹትን ምስጢር እላይ ከጠቆምኩት ነጥብ አኳያ ባጭር ወደማስታወሱ ልመለስ።
ሞት፣ ጸአተ-ነፍስ፣ ኅልፈተ-ብዕል (የሀብት፣ የክብር ማለፍ)። እሊህን ነው እንግዲህ ዕለት ዕለት እንድናስባቸው፣ እንድንገነዘባቸው፣ እንድንረዳቸው፣ እንድናውቃቸው፣ እንድንለብማቸው-- በምር፣ ፈጽመን ልብ እንድንላቸው (ከልባችን ጥልቅ አድርገን እንድናስገባቸው) የሚያሳስበን፤ ይኸውም እጅግ በሚጣፍጥ ጣዕመ-ዜማ። ቁም ነገሩም እሊህን ካሰብን በሚኾነው ነገር ኹሉ ቁርጥ ሐሳብ ማድረግ፣ ጥብዐት ማግኘት እንችላለን ማለት ነው።
ታዲያ ብዙዎቻችን--ይልቁንም “ብፁዐኑ፣” “ቅዱሳኑም” ሳይቀሩ--እንዲህ ያለውን ቃል እየሰማን እና እያሰማን፤ ነገር ግን ጥቃቅን ኀጢአት ከመሥራት አልፈን ደጋጉን አበሳ በማግበሰበስ፣ ህላዌኣችንን እንዴት አካተን “ህላዌ-ግፍዕ” (ግዙፍ ግፍ!) አድርገን ልንገፋው ቻልን!? ዕፁብ ነው። ኾኖም አንዱ ምክንያት አንዳችንም አንዳችን፣ ባእምሮም ይኹን በኢያእምሮ፣ እንዲህ ብለን ስለምናስብ ይመስለኛል፦ “‘ሰብእ (ሰው)’ አለ እንጂ፤ እኔን መቸ አለ? አዎ ሰው ይሞታል፤ ሰው ዐላፊ ንብረቱም ክብሩም ጠፊ ነው፤ ሰው ከንቱ ነው፤ ወዘተ.፤ ይህ ኹሉ ግን እኔን፤ የኔን ንብረት፣ የኔን ክብር አይመለከትም!” አለዚያማ፦ ይህን የመሰለ ቀለም ከዜማው አጣጥሞ የሚዘምር ሰው ይቅርና ሲዘመር የሰማ ከጥቃቅን ስሕተት መለየት ቢሳነው እንኳ ለሞተ-ነፍስ ለሚያበቃ ኀጢአት እና ዐይን ላወጣ ግፍ ተጨልጦ ተገርኝቶ ለመገዛት ምክንያት ያገኝ ነበር? ኧረ እግዚኦ! ኢትሚጦ ለልብየ ውስተ-ነገር እኩይ ለአመክንዮ-ምክንያት ለኀጢአት…
የገዛ ራሳቸውን ሞት፣ የገዛ ራሳቸውን ብዕል እና የገዛ ራሳቸውን ክብር ከንቱነት ዕለት ዕለት እያሰቡ ለኛም የኛኑ የራሳችንን የሚያሳሰቡን፤ ይህንኑ በምር ዐውቀው፣ ተረድተው፣ አስተውለው፣ ለብመው ለኛም በምር እስክናውቅ፣ እስክንረዳ፣ እስክናስተውል፣ እስክንለብም በትጋት የሚያስተምሩ እውነተኛ መሪዎች ሊቃውንትን ይስጠን። (“አሜን” ያንባቢ ድርሻ ነው።) እንዲህ ከኾነ፤ ገድላችንን ከፍጻሜ ለማድረስ እጅግ አስፈላጊ የኾነውን የጥብዐትን ቁልፍ አገኘን ማለት ነውና።

5 comments:

Anonymous said...

Our church fathers are fighting over worldly power and wealth. Would you please remind us what it means to be a "menekuse" according to EOTC traditions and canons? Please do it in Amharic so that we would all understand our respected church fathers' current behaviour including our patriarch's special love for anything white and golden!

Anonymous said...

kale hiywot yasemalin

"MENEKOSE " malet mote malet neber
" BEKEME FEKEDE YIGEBIR WEBE KEMEHALEYE YIFEXIM"
cher were yaseman
betselot eniberta

Anonymous said...

dኢትዩ.ሁለት አንስት በሚሊኒየሙ ወለደች
1.ሰት ጀግና ወ/ት ብርቱካን ሚዸከሳ
2.ሰት አሸባሪ ወ/ሮ እጅጋየሁ/የዘመናችን ኤልዛቤል/


ጸልዩ ከሚኒሶታ

Anonymous said...

please senbet new
sile betekristiyan andinet eniyseliye
yih hulu yehaxiyatachin waga new ena

begna zemen edih aynet negrochin mayetachinim hone mesmatachin bexam asazagn new. Betekiristiyan sitinor new eng yemininorew ena please "tseliyu be ente selama betekiristiyan"
"ABTU KINIDIHIN LAKINA AND ADRGEN"

AMEN CHER WERE YASEMAN

selamu said...

esti Egziabhear yeabatochachinin libe 1 adrigo firuhanun yehonutinm tibuan edihonu adrigo yenegewan elet yebetekrstianachin liyu yetaric mierafe endiyadergligne ewnetegna yetewahido lijoch please kelb entseliy
lehualachinem melkanun zena yaheman
seytinin yasafirlgne

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)