July 20, 2009

ሰበር ዜና (Breaking News) መንግሥት “ፓትርያርኩን ተቃወሙ” ያላቸውን ማነጋገር ጀምሯል


(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 20/2009)

በቅርቡ በቅዱስ ሲኖዶስና በፓትርያርኩ መካከል በተፈጠረው ችግር “ፓትርያርኩን ተቃውመዋል”፣ በተለይም ከብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ጋር ግንኙነት አላቸው ያላቸውን ሰዎች መንግሥት በማነጋገር ላይ እንደሚገኝ ለመንግሥት ቅርበት ያላቸው ታማኝ ምንጮች ገለፁ። ያለ ምንም መጥሪያ ወይም ስብሰባ ሰዎቹን ከተለያዩ ቦታዎች በመያዝ በሚደረገው በዚህ ምርመራ አከል ጥያቄና መልስ አሁን የተወሰነውን ውሳኔ ሕዝቡ እንዳይቃወም፣ እነርሱም በተቃውሞ እንዳይሰለፉ ሲናገሩ ተሰምተዋል።

በዚሁ የጅምላ ጥያቄና ምርመራ ከተጠየቁት መካከል የአስኮ ገብርኤል ፀሐፊ ቀሲስ ሰሎሞን ቶልቻ፣ የዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ቤተ ክርስቲያን ፀሐፊ መምህር ሰሎሞን በቀለ፣ መምህር ሱራፌል ወንድሙ፣ ባሕታዊ ሶፎንያስ፣ የልደታ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ቀሲስ ኃ/ገብርኤል፣ የጴጥሮስ ወጳውሎስ አስተዳዳሪ አባ ገብረ ሕይወት፣ የአራዳ ጊዮርጊስ አስተዳዳሪ መልአከ ፀሐይ በቀለ እንዲሁም የቀጨኔ ቤተ ክርስቲያን ቁጥጥር ክፍል ኃላፊ መምህር ሽታ እና ሌሎችም እንደሚገኙበት ምንጮቻችን አብራርተዋል። ተመርማሪዎቹ “ለብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ጋር ስላላቸው ግንኙነት ከመጠየቃቸውም በላይ ሕዝቡ ወደ ተቃውሞ እንዳይገባ እንዲያረጋጉ፣ ይህ ባይሆን ግን ለሚፈጠር ማንኛውም የሕዝብ ተቃውሞ ተጠያቂዎች እንደሚሆኑ ተገልጾላቸዋል ተብሏል።


እነዚሁ በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ላይ የተሰማሩና ለቤተ ክርስቲያን ባላቸው ቅንዓት የፓትርያርኩን ቤተ ዘመዳዊ አሠራር የተቃወሙ ሰዎች ለምን ማስፈራሪያ እንደሚደርስባቸው እንዳልገባቸው ተናግረዋል። ጉዳዩን የገለጽንላቸው የደጀ ሰላም ተባባሪ አባት እንደተነተኑት መንግሥት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩን ለመደገፍ ከመፈለግ ሳይሆን ጉዳዩ ከእጁ እንዳይወጣ ከመፍራት እያደረገው ያለው እንቅስቃሴ መሆኑን ተናግረዋል። በርግጥም መንግሥት በዚህ አካሄዱ ከገፋበት “መንግሥት ከነቀዘው አስተዳደር ጋር ቆሟል ያሰኘዋልም” ብለዋል።

የቅ/ሲኖዶስ ስብሰባ ተጠናቀቀ በተባለበት ወቅት ቅዱስነታቸው ባስነበቡት መግለጫ መጨረሻ ላይ “ሰላምና መረጋጋት” የምትለውን ቃል የተጠቀሙት የመንግስትን የልብ ትርታ ለማነሳሳትና ከራሳቸው ጎን ለማቆም በመፈለግ እንደሆነ ተንታኞች ይናገራሉ። የኢሕአዴግ መንግሥት መንበረ ሥልጣኑን ከተቆጣጠረበት ከ1983 ዓ.ም (1991) ጀምሮ በየዘማነቱ ከሚጠቀምባቸው ቃላት “ፋሽኑ ያላለፈባት” ብቸኛ ቃል ብትኖር “ሰላምና መረጋጋት” የምትለው መሆኗን ያስታወሱት ተንታኞች “በሰላምና መረጋጋት ስም የቤተ ክርስቲያናችን አጀንዳ ተዳፍኖ ሊቀር ይችላል” ብለዋል።

በዚህ በኩል ያሉ ሒደቶችን እየተከታተል እናቀርባለን፣ ተከታተሉን።

ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን

6 comments:

Anonymous said...

Thank You. Keep it up Ds.

Anonymous said...

thank you deje selam
we are with our holy father please tall them.yaldeferes ayteram araya yemihonene abate nafeken esty yastemerun hawareyanet ende Jema kerestian gena lega woche motu enanetes teferu yehon !!!!! egzehabehar menalebat lemedan yehene geza endy denubet felego yehon .denachehu enedan.please tall my comment


g

Anonymous said...

"አርድ አንቀጥቅጥ" የሆነው የቤተ ክርስቲያን አገዛዝ በመንፈስ ቅዱስ እንደማይመራ የታወቀ ነው። ውጭ በስደት ያሉት አባቶች እና በሀገር ያሉ አባቶች በይቅርታ በንስሀ ተነጋግረው ችግራቸውን ካልፈቱ መላ የልውም።
1ኛ - በውጭ ያሉትን አባቶች ሲያወግዙ ጽላት የላቸውም፡ ቅድስት ድንግል ማርያምን አያከብሩም፡ ቅዳሴ በፕያኖ ነው፡ ቅዱስ ያሬድ ዜማን አይጠቀሙም ወ.ዘ.ተ ንስሀ የሚያፈልገው ጉዳይ ነው።
2ኛ - የሊቀ ሊቃውንት አለቃ አያሌው እና የኔታ መንክር ጉዳይ
3ኛ - አዲሳ አበባ ቅዱስ እስጢፋኖስ ላይ የፈሰስው የአባታችን ደም እና የአ.አ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ጉዳይ፡
4ኛ - ጎንደር ላይ የፈሰው ደም እና የአባ አመሀሰላሴ ጉዳይ እግዘአብሔር ቸል አላለወም እና እስኪ በነሰሀ እነመለስ

free_me_or_kill_me said...

Meles is scared of the uprsing of the people of Ethiopian Orthdox church.Those who view this blog must keep in their mind that Ethiopians are led by visble and invisible group.The visible one is the so called Government and acting like sensible and concerned stateship.But the corrupted and mafia group is the invisible group even beyond the power of Meles.They are group of people from TPLF ,Intelligent people and rich people who got everything overnight.The only thing to remove this group is to raise the armed group.Some people think that arm struggle is the eveilish act.But Many times we can read from the bible that fighting is common against tyranny and dictator.Almighty God directs us the right way.

Anonymous said...

Source: Ethiopian reporter

ለቅዱስ ፓትርያርኩ፣ "ገለልተኛ የተባለው ኮሚቴ እነማንን ይይዛል? ተቃውሞ የሚያነሳን ወገን ከኃላፊነት ማንሳት መፍትሔ ይሆናል? ቤተ ክርስቲያን በቤተ ዘመድ በመሞላቷ ሀብቷ እየባከነ ነው ስለሚባለው ጉዳይ፣ ኮሚቴው ለምን ባስቸኳይ ሥራውን እንዲጀምር አልተደረገም? ተፈጥሮ በነበረው ውዝግብ ምዕመናን አዝነዋል፣ ግራ ተጋብተዋል፤ ምዕመናንን ይቅርታ ለመጠየቅ የታሰበ ነገር አለ?" የሚሉ ጥያቄ ቀርበውላቸዋል፡፡

ጥያቄዎቹ ከቅዱስ ሲኖዶሱ እውቅና ውጭ በተለያዩ ጋዜጦችና መጽሔቶች ሲነገሩ የነበሩ በመሆናቸው ምንም የሚሉት ነገር እንደሌላቸው ገልጸው፣ "ቅዱስ ሲኖዶስ አንድ ነው፤ አብሮ ነው የሚኖረው፡፡ በግልፅ ይነጋገራል፤ ይወያያል፤ አንድነቱ አይከፋፈልም" ብለዋል፡፡

ረቡዕ ምሽት ሐምሌ 8 ቀን 2001 ዓ.ም. አቡነ ቄርሎስ፣ አቡነ መልከ ጸዴቅ፣ አቡነ ኤጲፋኒዮስ፣ አቡነ ሉቃስና አቡነ ሳዊሮስ የመኖሪያ ቤታቸውን በር በማንኳኳትና እስከ መስበር ተደርሶ እንደነበር ተገልጾ፣ በቤተ ክርስቲያኒቷ እስከ ዛሬ ድረስ ተደርጐ የማይታወቅ ጉዳይ ለምን ሊከሰት እንደቻለ ተጠይቀው፤ እንደዚህ ዓይነት ክስተቶች በዓለም ላይ በየቀኑ እንደሚከሰቱ መግለጽ ፣ "ሁላችንንም አስገርሞናል፡፡ በአንድ ዓለም ላይ ስለምንኖር እንዲህ ያለ ክስተቶች ሲፈጠሩ ለሚመለከተው አካል ማሳወቅ ስለሆነ፤ እኛም ለሚመለከተው አካል አመልክተን ጉዳዩን እየተከታተልን ነው" ብለዋል፡፡

I am very very sad with HH response.

Goitom

Anonymous said...

"አርድ አንቀጥቅጥ" የሆነው የቤተ ክርስቲያን አገዛዝ በመንፈስ ቅዱስ እንደማይመራ የታወቀ ነው።” በማለት ጽሑፍህን ለጫጫርከው ወንድም መልስ ይሆንህ ዘንድ ይኼን ልኬልኻለሁ፦ አራት ነጥቦችን ጠቅሰኻል፤ ሦስቱ ትክክል መሆኑን ሁላችን በገሐድ እናውቀዋለን፤ ንስሐ እንግባ ማለትህም እሰየው ያስብላል። እኔ ያልገባኝ ነገር ቢኖር ዛሬም እንደ ትናንቱ ይኽን የፒያኖ ጉዳይ ትደግፋለህ ልበል? ዛሬም በውጭ አገር ሲኖዶስ አለ ከሚሉት ጋር ወግነኻል? አጻጻፍህ ጣፋጩን በሬት የለወሰ ዓይነት ነውና እውነት በንስሐ እንመለስ ላልከው ቋንቋ በቁጥር አንድ ላይ የጠቀስከውን ቃል ደግሜ ጽፌልሃለሁና ተመልክተህ ስለ ኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ስትሉ ተመልሳችሁ ንስሐ ግቡ፤ ይኼ ሁሉ ጥፋት የእናንተ ነው ብለህ ጽሑፍህን ብትጀምር እንዴት መልካም ነበር። 1ኛ - በውጭ ያሉትን አባቶች ሲያወግዙ ጽላት የላቸውም፡ ቅድስት ድንግል ማርያምን አያከብሩም፡ ቅዳሴ በፕያኖ ነው፡ ቅዱስ ያሬድ ዜማን አይጠቀሙም ወ.ዘ.ተ ንስሀ የሚያፈልገው ጉዳይ ነው። ውጭ በስደት ያሉት አባቶች እና በሀገር ያሉ አባቶች በይቅርታ በንስሀ ተነጋግረው ችግራቸውን ካልፈቱ መላ የለውም።

“ሹመት ያዳብር” ብሎ መልእክት አስተላልፎ፣
እውነቱን ታሪኩን በመጽሐፍ ጽፎ፣
ከሰማን ካወቅን ካነበብን ኋላ፣
የመቼ ቅኝት ነው እንዲህ ዓይነት መላ፣
መንበር በአገር የለም ሲኖዶስ ተሰዷል
በኬንያ አቋርጦ አሜሪካ ደርሷል፣
መንበሩን ተመስገን ይዘነው መጥተናል፣
ሰሜን አሜሪካ ጳጳሳት ሾመናል።
የሚሉትን ሰዎች የሚወግን ካለ፣
አእምሮው ተነክቷል ይመርመር ከቻለ።
መንበር በአገር የለም ያሉትን መከተል፣
መጨረሻው ሞት ነው ወድቆ ወደ ገደል።

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)