July 18, 2009

አንዳንድ ነጥቦች ስለ ሕገ ቤተ ክርስቲያን

(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 18/2009)
(አቤል ዘቀዳማዊ እንደጻፈው)
እንግዲህ የዛሬው የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ የእናተው ዘገባ ካየሁ በኋላ፤ ከራሴ ጋር ብዙ ጥያቄዎች በማንሳት ተከራከርኩና ህገ ቤተ ክርስቲያንም ማገላበጥ ጀመርኩ ።
ከጥያቄዎችም መካከል፦
• የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት የቤተ ክርስቲያኒቱን ሕግ ያውቁታል ወይስ አያውቁትም ?
• የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ያለባቸው ኃላፊነትስ በትክክል ተረድተውታል ወይ?
• ከዚህ በኋላስ ሊቃነ ጳጳሳቱ በምን ሞራል ነው ልጆቻቸው መባረክ የሚችሉት?
• ለቤተ ክርስቲያኒቱ ህግና ሥርዓት ተቆርቃሪዎች እውነተኞቹ ነገር ግን በቁጥር ትንሽ የሆኑት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት እንዴት ከሕዝበ ክርስቲያኑ ጋር ሊገናኙ ይችላሉ?

እስቲ ቅዱስ ፓትርያርኩም ሆነ ብዙዎቹ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት የማይቀበሉት ህገ ቤተክርስቲያን ስለ ፓትርያርክ ስልጣንና ተግባር ምን ይላል? ለዚሁ ጥያቄ መልስ ለማግኘት በራሳቸው በቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ተቀባይነት ያላገኘውን ህገ ቤተክርስቴያን ካነበብኩት ላካፍላችሁ
1. ፓትርያርክ ተጠሪነቱ ለቅዱስ ሲኖዶስ ነው (ሕገ ቤተክርስቲያን 1991)
2. ፓትርያርክ የቅዱስ ሲኖዶስና የቋሚ ሲኖዶስ ስብሰባዎችን ይመራል
3. በቅዱስ ሲኖዶስ መመሪያ ለብፁዓን ጳጳሳት የሊቀ ጵጵስና መዓረግ ይሰጣል
4. ለታላላቅ ገዳማት አበ ምኔቶችና በሀገረ ስብከቱ ለተመረጡ ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች የመዓረግ ስም ይሰጣል
5. ከቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጡና የተላለፉ ሕጎች፤ ደንቦች፤መመሪያዎችና ልዩ ልዩ ውሳኔዎች በተግባር መዋላቸውን ይከታተላል
የፓትርያርክ ከስልጣን መውረድስ ህገ ቤተክርስቲያን ምን ይላል?


ፓትርያርኩ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ ከተሾመ በኋላ የተቀበለውን ኃላፊነት በመዘንጋት፦
• የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ትምህርተ ሃይማኖት የሚያፋልስ፤ቀኖና ቤተክርስቲያንን የሚያስነቅፍ ተግባር ፈጽሞ ከተገኘ
• በፍትህ መንፈሳዊ አንቀጽ አምስት ከቁጥር 172 እስከ 208 በተደነገገው መሰረት በደለኛ ሆኖ ከተገኘ
• በኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በ1991 በወጣው ሕገ ቤተክርቲያን አንቀጽ 13 ንዑስ አንቀጽ ሰባት መሰረት በተሾመበት ቀን የገባው ቃለ መሐላ ያልጠበቀ እንደሆነ
በአጠቃላይ ታማኝነቱ፤መንፈሳዊነቱና አባትነቱ በካህናትና በምእመናን ዘንድ ተቀባይነት ያጣ ሆኖ ቤተክርስቲያንን የሚያስነቅፍ መሆኑ በትክክል ከተረጋገጠ ከስልጣኑ ይወርዳል። በሱ ምትክም ሌላ ተመርጦ ይሾማል። ፓትርያርክ እስኪሾም ግን ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክ ይመረጣል። የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ያወጣው ሕገ ቤተክርስቲያን 1996 አንቀጽ 16
ሕገ ቢተክርስቲያን ይህ ሆኖ ሳለ የአሁኑ ፓትርያርክ ከላይ የተጠቀሱት ህጎች ሁሉ እያፈረሱ፤ እኛም እያየነቸው የቅዱስ ሲኖዶሱም አባላት እያዩዋቸው እስካሁን ድረስ በዝምታ ታልፈዋል። ከዚ በኋላስ መፍትሔው ምንድ ነው? ተስፋ ቆርጦ መተው ወይስ ከጥቂቶቹ ለሕገ ቤተክርስቲያን ተቆርቋሪ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ጋራ አይዞዋችሁ እኛም ከጎናችሁ ነን በማለት መስራት? መልሱን ለውድ ደጀ ሰላማውያን/ት በመተው አንድ ነገር ግን ላሰምርበት እወዳለሁ የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን በፓትርያርክ ላይ ፓትርያርክ የሚል ህግም ደንብም የላትም።
እግዚአብሔር ተዋህዶ ሃይማኖታችን ይጠብቅልን!!! አሜን
Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)