July 11, 2009

የብፁዕ ወቅዱስ ሥልጣን “ልጓም እንዲበጅለት” የሚፈልጉ ወገኖች እነማን ናቸው?


(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 11/2009)
የብፁዕ ወቅዱስ ሥልጣን “ልጓም እንዲበጅለት” የሚፈልጉ ወገኖች እነማን ናቸው?
ይህንን ጥያቄ ስጠይቅ ራሴም በመጀመሪያ ሳስበው ከነበረው በላይ ጥያቄው ራሴኑ ጠየቀኝ። “የቅዱስነታቸው ሥልጠና እንዳይጸና የሚፈልጉ አሉ ማለትህ ነው?” አለኝ ሌላው እኔነቴ። “አዎ” ብዬ መለስኩለት። “እንግዲያውስ ከእነርሱ ለምን አንጀምርም?” አለኝ አንዱ ጎኔ። “እሺ” አልኩኝ። ስለዚህ ከእነርሱ እጀምራለሁ። ደጀ-ሰላማውአን ትቀጥሉበታላችሁ ዝርዝሩን (ሊስቱን)።

የብፁዕ ወቅዱስ ሥልጣን “ልጓም እንዲበጅለት” የሚፈልጉ ወገኖች!!!
1. ሕገ ቤተ ክርስቲያን፣ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን፣
ቤተ ክርስቲያናችን ኦርቶዶክሳዊት እንጂ ሮማዊት/ካቶሊካዊት ስላልሆነች ፓትርያርኩ አይሳሳትም የሚል እምነት የላትም። የቤተ ክርስቲያኒቱ የመጨረሻ ወሳኝ አካልም ፓፑ/ ፓትርያርኩ ሳይሆን ቅ/ሲኖዶሱ ነው። ስለዚህ የፓትርያርኩ ሥልጣን ይገደብ የሚለው ሕጋችንና ቀኖናችን ነው።

2. ለሕገ ቤተ ክርስቲያን የሚገዙ “አባቶች ካህናት፣ ወንድሞች ዲያቆናት፣ አባቶች፣ እናቶች” በጠቅላላው ክርስቲያኖች፣
“አባቶች ካህናት፣ ወንድሞች ዲያቆናት፣ አባቶች፣ እናቶች” የሚለው አባባል በየስብከቱና ፕሮግራሙ የሚባል ግሩም አባባል በመሆኑ ወሰድኩት።

3. ሊስቱን/ ዝርዝሩን ቀጥሉበት፣ ሙሉበት


የብፁዕ ወቅዱስ ሥልጣን “ልጓም እንዲበጅለት” የማይፈልጉ ወገኖች!!!
1. ራሳቸው ፓትርያርኩ
ሥልጣናቸው አጼያዊ ነው። ኢትዮጵያ ንጉሳዊ አስተዳደር የላትም። ቤተ ክህነት ግን ንጙሥ አላት። ንጉሱም ፓትርያርኩ ናቸው። “ንጉስ አይከሰስ፣ ሰማይ አይታረስ” የሚባለው ቀርቶ “ፓትርያርክ አይከሰስ/አይወቀስ፣ ሰማይ አይታረስ” ሆኗል። ፓትርያርኩ ፈለገውን ይሾማል፣ የፈቀደውን ይሽራል፣ ይቀጥራል፣ ያባርራል፣ ይገዛል፣ ይነዳል። እንደፈቀደው ነው። የሚፈራው መንግሥትን ብቻ ነው። ከዚያ ውጪ ቅ/ሲኖዶሱ ራሱ የርሱ ታዛዥ፣ አፋሽ፣ አጎንባሽ ነው። ስለዚህ ይህንን የመሰለ ስልጣን እንዴት ተደርጎ ይቀነስባቸው? ? ? ?
2. ዘመዶቻቸው
የፓትርያርኩ ዘመድ መሆን ማለት “ሀብት ነው”። ባይማሩም ያስሾማል፣ ባያውቁም ሊቅ ያስብላል። ውጪ ለመውጣት፣ ለመነገድ፣ ጥሩ ደሞዝ ለመብላት፣ ወደ መንግስት ቀረብ ለማለት ወዘተ ያስችላል። ስለዚህ ስልጣናቸው እንዲነካ አይፈልጉም።

3. ጥቅመኞች
የፓትርያርኩ አምባ-ገነንነት ለጥቅመኞች ይመኛል። ምሳሌ? ወ/ሮ እጅጋየሁ/ኤልዛቤል። ምን አደረጉ ወይዘሮዋ? የቤተ ክርስቲያን ሕንጻዎችን በትንሽ ገንዘብ ተከራይተው “አየር ባየር” መልሰው እያከራዩ ቁጭ ብለው ብር ይሰበስባሉ። ሰዎችን ወደ ውጪ ሀገር ለመላክ ጉቦ እየተቀበሉ በቤተ ክህነት ደብዳቤ ከኤምባሲዎች ቪዛ ያሰጣሉ። ፈረንጆቹ “የሰው ኮንትሮባንድ” (human trafficking) የሚሉት። ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደ ቤተ ክህነት ማስረጃ ዋጋ የሌለው ተቋም የለም። ውሸት መነዋ!!! የፓትርያርኩን ደብዳቤ ጨምሮ። እነዚህ ሰዎች ፓትርያርኩ ከሚነኩ የቀረው ቢቀር ደስታቸው ነው። በቤተ ክርስቲያን “ዐውደ ምሕረት” የሚቦተልከውንም እዚህ አስገቡልኝ።

4. ፓትርያርኩን መሳደብ “እንጀራቸው” የሆኑ ሰዎች
እነዚህ ደግሞ ውጭ ሀገር ተቀምጠው ፓትርያተርኩን በመሳደብ፣ ተቃዋሚ በመመምሰል የሚኖሩ ናቸው። “ስደተኛ ሲኖዶስ” በሉት፣ “ገለልተኛ ቤተ ክርስቲያን” በሉት፣ ዌብ ሳይቶች በሏቸው፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሏቸው፣ እነዚህ ሁሉ ጥሩ ፓትርያርክ ከመጣ እንጀተራ ስለሚያጡ “አቡነ ጳውሎስን ያኑርልንም፣ የበለጠ ክፉ ያድርግልን፣ የርሳቸው ዓይነት አባት አያሳጣን” ብለው የሚጸልዩ ናቸው። በዚህ ሰሞን ግርግር ትንፍሽ ያላሉት ለምን መሰላችሁ? እርሳቸው ስልታጣናቸው “አደብ’ ከተበጀለት ማንን ይቃወማሉ?

4. እስቲ እናንተ ደግሞ ቀጥሉበት!!! የቤተ ክርስቲያናችን ጠላቶች እንወቃቸው!!!

ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን

Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)