July 22, 2009

“ብሩን መልስና ተመለስ ወደ እውነት” (ለንጉሴ ወ/ማርያም)


(ከደጀ-ሰላማዊው)
ዜና አስውቦ ማቅረብ ገንዘብህ ነበረ፣
አሁን ሐሰት ገዛህ ተከተተ ቀረ።
ቅንነት የሌለህ ለጥቅም የተጋህ፣
ለካስ ትንሽ ሰው ነህ ገንዘብ የሚገዛህ።
ወሬ ለአገር ላይጠቅም ሥልጣን ላያረጋ፣
ሰጪ እና ተቀባይ ሥራውን ዘነጋ።


ምን ነበረ ቢቀር ጉዳችሁ ባይወጣ፣
በአንድ መቶ ሺህ ብር የሚሊዮን ጣጣ።
አተርፋለሁ ብለህ ንጉሤ ተሞኘህ፣
ላትገፋው ጀምረህ ግብርህ አጋለጠህ።
ለእናት ኢትዮጵያ ተቆርቋሪ መስለህ፣
ዜና ስታሰማ ጉቦ በሉ ብለህ፣
ብዙ ጊዜ ሰማን የአንተ አድማጮች ሆነን፣
ዛሬ ተረኛ ነህ አንተ ደግሞ አድምጠን።
ይኼ ነው ንጉሤ አሰማኸን ብሥራት፣
አንተው ጉቦ በላህ የዜናው ባላባት።
ምን ዓይነት ሎተሪ ምን ዕጣ ገጠመህ?
“አባ ይፍቱኝ” ልትል ልትሳለም ሄደህ፣
መፍታቱን ተዉና እነሆ ጉድ ሠሩህ፣
በአንድ መቶ ሺህ ብር የፊጥኝ አሰሩህ።
ያለ ግብሬ ልግባ እንዲህ ከሆናችሁ፣
ሰጪና ተቀባይ እግዚአብሔር ይፍታችሁ።
የሰየምከው ጣቢያ “ሀገር ፍቅር” ብለህ፣
“ፀረ ሀገር” ተብሏል በቃ አድማጭም የለህ።
ሁለት ሞት አትሙት በጉቦ እና በሐሰት፣
ብሩን መልስና ተመለስ ወደ እውነት።
((ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 21/2009: ይህ ግጥም የተጻፈው ለሀገር ፍቅር ሬዲዮ አዘጋጅ፣ $10000 ዶላር ተቀብሎ አባቶችን በማንጓጠጡ በተቀየሙ አንድ ምእመን ነው።)
Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)