July 9, 2009

ወ/ሮ እጅጋየሁ ወይስ የዘመኗ ኤልዛቤል?


"Selam Deje Selam,
Thank you for your updates. Who is Woizoro Ijigayeheu? It seems she is an active player in all this, but I perhaps like many do not understand what her role is."

ውድ ጠያቂ
ለጥያቄዎ እናመሰግናለን። ስለሴትዬዋ ብዙ የሚባል ነገር አለ። ዛሬ ስለርሳቸው ለመነጋገር ጊዜው አይደለም። ከዚያ የሚበልጠው የቅ/ሲኖዶሱ ጉዳይ ስላለ። ለጊዜው አንድ አንባቢያችን የጻፉትን እንዲያነቡ እንዲሁም ዓባይ ሚዲያ ያወጣውን የሴትዮዋን “ግማሽ ገጽ” ፎቶ እንዲመለከቱ ልጋብዞት።
በነገራችን ላይ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የሥዕል ይትባህል “ግማሽ ገጽ እና አንድ ዓይን ብቻ” የሚሳለው ለመናፍቃን፣ ለከሃድያን፣ ለአረማውያንና ለአጽራረ ቤተ ክርስቲያን ነው።
ቸር ወሬ ያሰማንወ/ሮ እጅጋየሁ ወይስ የዘመኗ ኤልዛቤል
አንድ ወ/ሮ እጅጋየሁ ላሰቡት ዓላማ እስከማስፈራራት ደርሰው የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ ያስቀይራሉ ማለት አይቻልም፤ ምንም እንኳን ብዙ ወ/ሮ እጅጋየሁዎች ስማቸው ያልተጠራ ከኋላ እንዳሉ የአደባባይ ምስጢር ቢሆንም።

ኤልዛቤል የተባለች ሴት የናቡቴ ደም እንዲፈስ ሥራዋን ብትሠራም ኤልዛቤል ለራስዋ እንደማትሆን ሊረዱ ያስፈልጋል። አሁን ሰዓቱ እግዚአብሔር ኢትዮጵያን እያሰበበት ያለው ሰዓት ስለሆነ ለተልካሻ ምክንያት የሚንበረከክ የሲኖዶስ አባላት አይኖርም።
አስተዳደር ይስተካከል ሲባል ለዕለት ጥቅማቸው ያደሩ እና አጭር ዘመናቸው እስከሚፈጸም ድረስ ብቻ ራእይ ያላቸው ሰዎች የሩቅ ተስፋ ያላትን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ብርሃን አያደበዝዙም።

በዚች በያዝናት በሐምሌ ወር በፋሽስት ጣልያን ተደብድበው ሕይወታቸው ያለፈው ሰማዕታት ደም ዛሬም ይጮኻል። እግዚአብሔር ለኢትዮጵያ ምድር ያስባል፤ ሥርዓት የጠፋበትን እና ማንአለብኝነት የነገሠበትን አሠራር ቆርጦ ይጥለዋል። ዛሬም የእግዚአብሔር ጣት በብልጣሶር የእራት ግብዣ አዳራሽ ውስጥ ማኔ፣ ቴቄል ፋሬስ ብሎ እንደጻፈ እግዚአብሔር መዝኗቸው ቀለው ለተገኙ የአስተዳደር ሰዎች ሁሉ ማኔ፣ ቴቄል ፋሬስ ብሎ ይጽፋል፤ ፍርዱንም ይሰጣል።
የእግዚአብሔርን ጣት ከመጻፍ የሚያግዳት የትኛው ባለሥልጣን ይሆን? ወ/ሮ ኤልዛቤል እና ይህ ታሪካዊ ሥራ እንዲከሽፍ የምትሯሯጡ ሁሉ የመውጊያውን ብረት ብትቃወም በአንተ ይብሳል ተብሎ እንደተጻፈ እራሳችሁን መርምሩ እላለሁ።

በእሳት መካከል እያለፋችሁ ያላችሁና ተከታዮቻችሁንም እሳታዊ ኃይል እንዲኖረን ያነሣሣችሁ እናንት በዘመናት መካከል የተነሣችሁ የታሪክ ሰዎች ለእውነተኛዋና ለቀጥተኛዋ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖትና ሥርዓት ተቆርቁራችሁ ከኋላችሁ ምንም ዓይነት የጥቅም እና የዘር አድልዎ ሳይኖርባችሁ ቆርጣቸሁ ተነሥታችሁ ከሆነ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ነው። አደራችሁን እርም ይዛችሁ እንዳትገኙ።
ወ ስ ብ ሐ ት ለ እ ግ ዚ አ ብ ሔ ር ! !

July 09, 2009

No comments:

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)