July 7, 2009

ቅ/ሲኖዶስ ዛሬም ሳይሰበሰብ ቀረ


(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 7/2009)
ለዛሬ ማክሰኞ ተቀጥሮ የነበረው የቅ/ሲኖዶስ ስብሰባ በፓትርያርኩ አልሰበስብም ባይነት ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ ሳካሄድ መቅረቱ ተረጋገጠ። ቅዱስነታቸው ለመሰብሰብ የመጡ 38 ሊቃነ ጳጳሳትን አልሰበስብም ሲሉ አሁን በተፈጠረው ችግር ለቅዱስ ሲኖዶስ ሳይሆን ለፓትርያርኩ በመወገን የቆሙት ሦስቱ ሊቃነ ጳጳሳት ማለትም ብፁዕ አቡነ ገሪማ፣ ብፁዕ አቡነ ገብርኤልና ብፁዕ አቡነ ሙሴ ደግሞ “ቤተ ክርስቲያን ምረቃ” ብለው ወደ ወሊሶ አካባቢ መሄዳቸው ተሰምቷል። ስብሰባው ነገ ይካሄዳል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ለቅዱስ ፓትርያርኩ ፍላጎት ተንበርክከው “ፈቃደ ፓትርያርክ” ፈጻሚዎች ከሆኑ ቤተ ክርስቲያኒቱ ከዚህ በሁዋላ “ቅዱስ ሲኖዶስ ነው ያላት” ለማለት እንደማያስደፍር አንዳንድ ደጀ ሰላም ያነጋገረቻቸው ሊቃውንት ተናግረዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የቅዱስ ፓትርያርኩ ደጋፊና ቅዱስ ሲኖዶሱ አገልግሎት እንዳይፈጽም በማወክ ላይ ካሉት ሕገ ወጦች በመሪነታቸው የሚጠቀሱት የቀድሞዋ የአርቲስት መሐሙድ አሕመድ ባለቤት ወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ በበኩላቸው አንዳንድ መፍቀርያነ ፓትርያርክ የሆኑ ሰዎችን በመሰብሰብና በቤተ ክህነቱ አዳራሽ በመሰብሰብ ግርግ ለመፍጠር ሲሞክሩ ውለዋል ተብሏል። ሴትዬዋ በቅርቡ ዋሺንግተን ዲሲ በሚገኘው የሀገር ፍቅር ድምጽ ሬዲዮ ቀርበው “እያንዳንዳቸውን እናውቃቸዋለን” ሲሉ በጳጳሳት ላይ ውስጠ-ዘ የሆነ ማስፈራሪያ ሲናገሩ ተደምጠዋል።


Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)