July 8, 2009

የቅ/ሲኖዶስ ስብሰባ ቀጥሏል

(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 8/2009)
ያለ ፓትርያርኩ ፍላጎትና ፈቃድ፣ ፓትርያርኩን ያልጨመረው የመጀመሪያው የቅ/ሲኖዶስ ስብሰባ በማካሄድ ላይ ይገኛል። ስብሰባው ዛሬ ረቡዕ ጠዋት ሲጀመር ጉባዔውን ለማቋረጥ ብዙ ሙከራ ያደረጉት ቅዱስነታቸው ሳይሳካላቸው ቀርቷል ተብሏል። በመጨረሻም አጀንዳው ቀርቦ ሊጸድቅ ችሏል። የዕለቱ ብቸኛ አጀንዳ “በቅዱስ ፓትርያርኩ የተፈጸሙ አስተዳደራዊ በደሎች” በመሆናቸው ይህንን አጀንዳ ለመመልከት በሕገ ቤተ ክርስቲያን መሠረት ቅዱስነታቸው መውጣት እንዳለባቸው ሲነገራቸው አሻፈረኝ ብለዋል። በዚህ መልኩ ለብዙ ሰዓታት ብጥብጡ ቀጥሎ በመጨረሻ ቅ/ሲኖዶሱ ሁሉጊዜም ከሚካሄድበት አዳራሽ በመውጣት አባቶች ባገኙት በሌላ ሥፍራ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

ጉባዔው ስብሰባውን ሲቀጥል ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ በሰብሳቢነት እንዲመሩ የመረጣቸው መሆኑም ታውቋል።
ይህንን ጉባዔ ለማካሄድ ብዙ እንቅፋት ገጥሞት እንደነበር የደጀ ሰላም ምንጮች አስታውቀዋል። በተለይም የቅዱስነታቸው ደጋፊዎች የሆኑት ብፁዓን አበው ገብርኤል፣ ይስሐቅ፣ ገሪማ፣ ኤርምያስና ሙሴ አደናቃፊ ተግባራትን ሲፈጽሙና ሲያስፈጽሙ ነበር ተብሏል። በተጨማሪም ብፁዓን አባቶችን በስልክ “እንገላችሁዋለን፣ እናጠፋችሁዋለን” እያለ የሚያስፈራራው የወ/ሮ እጅጋየሁና የግብረ አበሮቻቸው ቡድን በዚሁ ተግባሩ ቀጥሏል ተብሏል። ሴትዬዋ ሽጉጥ መታጠቃቸውን ቢያንስ በሁለት አጋጣሚዎች ያሳዩ ሲሆን በሙስናና በቤተ ክርስቲያን ዝርፊያ ሀብታም የሆኑት ሰዎች ቡድን በብፁዓን አባቶች ላይ አደጋ እንዳይጥል መንግሥት ጥበቃ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ጉዳዩን በጥሞና በመከታተል ላይ የሚገኘው መንግሥት “የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ እንደሚቀበል” ፍንጭ ማሳየቱ ታውቋል። ነገሩ በርግጥ በዚህ መልክ ከቀጠለ እና መንግሥት የቤተ ክርስቲያን አባቶችን ውሳኔ አክብሮ ከተቀበለ በማስፈራራትና “ወየውላችሁ መንግሥት ከኔ ጋር ነው” የሚለው ቅዱስነታቸው ዛቻ ፍሬ ያጣል ተብሎ ይጠበቃል። ይህም ቤተ ክርስቲያን በርግጥም ራሷን በራሷ በእውነተኛ ነጻነት ማስተዳደር የምትጀምርበት አዲስ ምዕራፍ እንዲከፈት ያደርገዋል።
ጸልዩ በእንተ ሰላመ ቤተ ክርስቲያን!!!!!!!!
ቸር ወሬ ያሰማን
አሜን

7 comments:

Anonymous said...

Egzihabeher Yefekedewn Ersu Yemkeberebeten Be kiduse Sinodose Yesera. Amen!

Anonymous said...

YeAbatachin YeTsadiqu Abune Tekle Haimanot Amlak Yirdan! Bezih Kiffu Weqt Tewahedo Haimanotachinin'ina Hizbe Kristianun YiTTebiqilin. Seif
Kemezezubin YeDiabilos Meleiktegnoch YeTTifat Mikirina BeDem YeTTaTTebe Ejachew Yadinen

KeMiTTadu Wede Welafenu Endaihon Beyalenibet BeQoraTTinet'ina Kristianawi Qinie'at YeDirshachinin EniweTTa.

YeDessie Quidist Arseman Miemenan'ina BeMela Agerachin BeDem Yekefelnewin Meswaetinet Belibachin Yizen Enaleqsalen.

Egzio Meharene Kristos!
BeEnte EgziEtine Mariam Meharene Kristos! Amen.

LOM said...

መጽሐፈ ነህምያ 9- 32
አሁንም አምላካችን ሆይ፥ ቃል ኪዳንንና ምሕረትን የምትጠብቅ ታላቅና ኃያል የተፈራኸውም አምላክ ሆይ፥ ከአሦር ነገሥታት ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በእኛና በነገሥታቶቻችን በአለቆቻችንም በካህናቶቻችንም በነቢያቶቻችንም በአባቶቻችንም በሕዝብህ ሁሉ ላይ የደረሰው መከራ ሁሉ በፊትህ ጥቂት መስሎ አይታይህ።
በደረሰብንም ነገር ሁሉ አንተ ጻድቅ ነህ፥ አንተ እውነት አድርገሃልና፥ እኛም ኃጢአት አድርገናል። ነገሥታቶቻችንም አለቆቻችንም ካህናቶቻችንም አባቶቻችንም ሕግህን አልጠበቁም፥ የመሰከርህባቸውንም ትእዛዝህንና ምስክርህን አልሰሙህም።
በመንግሥታቸውም በሰጠሃቸውም ታላቅ በጎነትህ፥ በፊታቸውም በሰጠኸው በሰባው ምድር አላመለኩህም፥ ከክፉም ሥራቸው አልተመለሱም። እነሆ፥ ዛሬ ባሪያዎች ነን፤ ፍሬዋንና በረከትዋን ይበሉ ዘንድ ለአባቶቻችን በሰጠሃት ምድር፥ እነሆ፥ በእርስዋ ባሪያዎች ነን፥ ስለ ኃጢአታችንም ለሾምህብን ነገሥታት በረከትዋን ታበዛለች፤ ሰውነታችንንም ይገዛሉ፥ በእንስሶቻችንም የሚወድዱትን ያደርጋሉ፥ እኛም በጽኑ መከራ ላይ ነን።

maren yekere belene,beza hunen

Zebe'entiAha leBeteKristian tetsefa'eke bewesete awede kemeteqedesa bedemeke kebure

ጸልዩ በእንተ ሰላመ ቤተ ክርስቲያን

Anonymous said...

ሁላችን በያለንበት፡ የሦስቱን ለጆች ጸሎት እየጸለይን፡ እግዚአብሔርን ደጅ እንጥና፡፡ በሓዋርያት ጾም ማለቂያ፡ ሊያሰማን ያሰበው ይኖር ይሆናል፡፡

በጸሎት እንበርታ!

Anonymous said...

I am glad that we have reached this stage where transparency and accountability is being practiced (though it is at its infant stage). This is how the leadereship works. Let God help our church and our country.

Please, keep on updating us the church related issues and let us know what we have to do to improve the church services accross the country and in the diaspora.

God Bless you

Sebastopol said...

መለስ ዜናዊ ሌላ ጳጳስ ሊቀይርልን አስብዋል። ይህ ምኑ ነው የሚያስፈነድቅ? ወያኔ ሳይፈልግ የሚሰራ አንዳችም ነገር የለም። ፓትሪያሪኩ ህዝብ አልቀበል ስላላቸው ሌላ የተዘጋጀልን አለ ማለት ነው። መንግሰት ጣልቃ አይገባም ነው ያሉት ጸሃፊው? ማነው ሰሞኑን ጣልቃ ገብቶ ወሎ ላይ ምእመናኑን እየፈጀ እያስፈጀ ያለው? እባካችው የመለስ ዜናዊ እቃ እቃ ጨዋታ ይግባችው።

Anonymous said...

የቀራኒዮ በግ ስለ ኢ.ኦ.ተ ልጆች ለተኩላ ስለ በተናችሁ ደሙን ከእጃችዉ ይፈልጋል.

“ማኔ ቴቄል ፋሬስ” በመዳፍ እጃችሁ ይጽፋል.

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)