July 17, 2009

ስውሩ የአቡነ ጳውሎስ እጅ ድል አደረገ፤ ስብሰባው “የፓትርያርኩን አቋም በመደገፍ” ተፈጸመ፤ ጋዜጣዊ መግለጫም ተሰጠ

(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 17/2009)

• የአቡነ ሳሙኤል ዕገዳ አልተነሣም፣
• እንደተለመደው www.ethiopiafirst.com እና ሀገር ፍቅር ሬዲዮ ውሳኔውን ያውጁታል፣

. We have the English translation at the end of this article,

ለብዙ ዕለታት፣ ቀንና ሌሊት ሲወጣ ሲወርድ፣ በየሰዓታቱ ሲለዋወጥ በመጨረሻም አባቶች ላይ ጥቃት ሲሞክር የከረመው የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባዔ ያለምንም ውጤት የቅዱስ ፓትርያርኩን “መመሪያ” ሰምቶና ተቀብሎ፣ “እሺ በጄ” ብሎ ተበተነ። ስውሩ የአቡነ ጳውሎስ እጅም አሸነፈ።

ዛሬ በተካሄደው የቅ/ሲኖዶስ ጉባዔ ላይ ፓትርያርኩ በፈለጉትና በወደዱት መልክ ነገሮችን ለማስኬድ የቻሉ ሲሆን “ዱርዬዎች ያዘጋጁት” ያሉትን ሕገ ቤተ ክርስቲያን “ተቀብዬአለሁ” ከማለት በስተቀር አንድም ፋይዳ ያለው አጀንዳ አልተነሣም ተብሏል።


ይህ በእንዲህ እንዳለ የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስና የፓትርያርኩ ተቃዋሚ እንዲሁም የቅ/ሲኖዶስ አበው ቡድን ሁነኛ መሪ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል በሀ/ስብከታቸው ላይ የተጣለባቸው እገዳ እስከ ጥቅምት ጉባዔ ድረስ እንዲጸናባቸው ተፈርዶባቸዋል። ብፁዕነታቸው በደህንነታቸው እየተሳበበ “በቤት ውስጥ እገታ” ከስብሰባ እንዲቀሩ ሲደረግ ሰንብቶ ዛሬ ውሳኔው ተላልፎባቸዋል ተብሏል።

በዛሬው ስብሰባ ላይ የአባቶች ጥበቃ ጉዳይ ከመጤፍ ሳይቆጠር ከመታለፉም በላይ በማፊያው ቡድን የተሰባበረው የብፁዕ አቡነ ቄርሎስ በር እስካሁን እንዳልተሠራ ታውቋል። የማፊያው ቡድንና ሌላው “ስውር እጅ” አባቶች ላይ ከፍተኛ ሥነ ልቡናዊ (ሳይኮሎጂካል) ጫና በማሳደራቸው አባቶች ደፍረው ለመናገር ሳይችሉ ቀርተዋል።

ጉዳዩ በዚህ መልክ እንዲጠናቀቅ ያላሰለሰ ጥረት ያደረጉት ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ፣ አባቶች በፍጥነት እንዲፈርሙ በማግባባት በኩል ተሳክቶላቸዋል ተብሏል። ስብሰባው እንደ ተጠናቀቀም ጋዜጣዊ መግለጫ የተሰጠ ሲሆን “ሰላም ወርዷል” ተብሎ ሲነገርም ተሰምቷል። አቡነ እስጢፋኖስ፣ አቡነ ሙሴ፣ አቡነ ገሪማ፣ አቡነ ገብርኤል፣ አቡነ ጎርጎርዮስና አቡነ ይስሐቅ የፓትርያርኩ ቀኝ እጅ በመሆን “ቅዱስ ሲኖዶስን አፍርሰው ቤተ ክርስቲያኒቱን ገድለዋታል” ሲሉ አስተያየት ሰጪዎች መስክረዋል። ከዚህ በሁዋላ የቅ/ሲኖዶስን ውሳኔ እደግፋለሁ ባለው መንግስት አማካይነት ፓትርያርኩ ተቃዋሚዎቻቸውንና ለቤተ ክርስቲያን የቆሙትን፣ ቅ/ሲኖዶስ አይደፈር ያሉትን በሙሉ በበቀል እንደሚያጠፉ ይጠበቃል።

የፓትርያርኩና የማፊያው ቡድን ከ”ስውሩ እጅ” ጋር በመሆን የበቀል በትሩን በአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች ላይ፣ የቤተ ክህነት ሠራተኞች ላይ፣ በብፁዓን አባቶች ላይ እንዲሁም ከመጀመሪያው “እጁ አለበት” ባሉት ላይ ሁሉ ይነዝራሉ ተብሏል። ቤተ ክርስቲያን በቅርብ ጊዜ ታሪኳ እንዲህ ዓይነት ውርደትና ውድቀት ገጥሟት አያውቅም ተብሏል። “ምዕመኑ መከፋፈሉን ትቶ ቤተ ክርስቲያኑን እንዲያድን” አባቶች መጠየቅ ጀምረዋል።

የቤተ ክርስቲያን አምላክ ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን
++++++++++++++++++++++++++++
Deje-Selam, Jul 17/2009)
. The “invisible hands” of Abune Paulos have won – The meeting end by supporting the Patriarch’s opinion – A press release was given
. The ban on Abune Samuel has not been raised ,,
. Read the News in Amharic HERE,
. As usual Ethopiafirst and Hager Fiker are announcing the verdict!
+++++

The issue , raised in the Holy Synod assembly has been going back and forth for the several weeks with controversial decisions and resulting in the assault of the Arch Bishops, has ended by hearing and fully accepting the course of action of the holy patriarch.

On the assembly held today, the Patriarch had been full in control of the strength and led the meeting in his way. He has verbally said “I accept” the Canon of the Church which he has called a ‘Vagabond deed” on yesterday’s meeting.

Abune Samuel, the Arch Bishop of Addis Ababa Archdiocese was one of the opponents of Aba Paulos, was banned from His service at the diocese and it has been decided that the banning will not be lifted a until October. His Grace has not been able to attend the meeting because he has bee house arrested by the militia who claim that this is for his safety
The attack on Wednesday was over looked in today’s meeting and the property damage on
Abune Kyrllos’s home has not been fixed. The mafia group and the invisible hands of Aba Paulos has caused a great psychological pressure on the fathers.

Abune Estiphanos, who played a great role in diverting the meeting principles, made the fathers to sign the agreement as soon as possible. A press release was given and acted as if “Peace has been accomplish”.Some have commented that “Abune Estiphanos,Abune Muse,Abune Gabriel,Abune Yisak,Abune Gorgoriyos had been the right hand of Abune Paulos and have defied the impartiality of the Holy Synod and have destroyed the Church”.By government ,that has initially declared that it will accept the decision of the Holy Synod,Abune Paulos is believed to start his revenge on all who have stood by the Church’s canon and rites.
The Patriarch and the Mafia group with the ‘invisible hands’ will start its vengeance on Addis Ababa church and monastery heads,Bete Kehnet employees, Bishops and on any one they think are involved in the act. Ye Ethiopia BeteKristian(EThioan Chruch) has never in history faced such a disgrace.”Laity should stop the division and save their Church” was the pleading heard from some fathersPost a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)