July 20, 2009

“ፓትርያርኩ አሸነፉ” መባሉን አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች ተቃወሙ፤ ሌሎች ደገፉ

(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 17/2009)

በቅርቡ የተጠናቀቀው የቅ/ሲኖዶስ ስብሰባ በተፈለገው መልኩ ባይሄድም “ፓትርያርኩ አሸነፉ” መባሉን ግን እንደማይቀበሉ አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች ገለፁ። ሌሎች ደግሞ ደገፉ:: እነዚሁ በክህነት አገልግሎትና በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የተሰማሩ አስተያየት ሰጪዎች እንደተናገሩት ጉዳዩ ለጥቅምት የተቀጠረ በመሆኑ ፓትርያርኩን “አሸንፈዋል” ማለት እንደማይገባ አስረድተዋል።

ከተወሰኑት ውሳኔዎች መካከል የፓትርያርኩ ሕገ ቤተ ክርስቲያንን መቀበል፣ የበላኢ ቅ/ሲኖዶስ እንጂ ፓትርያርኩ አለመሆናቸውን መቀበላቸው እንዲሁም ሥራ አስፈጻሚው ሥራውን እንዲቀጥል መፍቀዳቸው መልካም ዜናዎች መሆናቸውን የተናገሩት አስተያየት ሰጪዎቹ የአቡነ ሳሙኤልን አለመመለስ ብቻ ተመልክተን ፓትርያርኩን አሸናፊ ማድረግ አይገባም ብለዋል።


ይህንን የሚተቹ ሌሎች አስተያየት ሰጪዎች በበኩላቸው አሁን በቤተ ክርስቲያን የተፈጠረውን ሁኔታ ለማሻሻል እድል ቢኖርም ውሳኔዎቹ ግን ከላኢ እንደተገለጸው ለቤተ ክርስቲያናችን መልካም ሆነው የሚገኙ አይደሉም ብለዋል። ሥራውን እንዲቀጥል የተፈቀደለት ሥራ አስፈጻሚ ተጠሪነቱ ለፓትርያርኩና ለሥራ አስኪአጁ መደረጉ ትልቅ ውድቀት መሆኑን በአብነት ያነሳሉ።

እስቲ እናንተስ ምን ትላላችሁ?

5 comments:

Anonymous said...

በመጀመሪያ ሀሳባቸውን በሰጡ ሰዎች ሀሳብ እስማማለሁ:: የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ የሚለው " ታግዶ የነበረው የቅዱስ ሲኖዶስ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ዕግዱ ተነስቶለት ሊመራበት የሚያስችለው ውስጠ ደንብ ከሚመደቡለት ባለሙያዎች ጋር በመሆን አዘጋጅቶ እንዲያቀርብ የሚዘጋጀው የመተዳደሪያ ደንብ እስከሚቀርብ ድረስም ከቤተ ክርስቲያኒቱ የአመራር አካላት ጋር እየተመካከረ እንዲሰራ ተወስናል::" ነው:: ሥራውን እንዲቀጥል የተፈቀደለት ሥራ አስፈጻሚ ተጠሪነቱ ለፓትርያርኩና ለሥራ አስኪአጁ መደረጉ " የሚለው አባባል ሰዎች ከራሳቸው አመንጭተው ካልሆነ በስተቀር በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ውስጥ ያለው "እየተመካከረ እንዲሰራ" የሚለው ቃል አዲስ አማርኛ ካልመጣ መስተቀር ተጠሪነቱ ለፓትርያርኩና ለሥራ አስኪአጁ " የሚል ትርጉም በጭራሽ አይሰጥም:: ደጀሰላሞችም ለወደፊቱ እንዲሁ ወደቀ ሲባል ተሰበረ የሚል ነገር እንደማይደግማችሁ እተማመናለሁ::

http://www.ethiopiafirst.com/news2009/July/Synod_Meglecha_17July09.pdf
የቤተ ክርስቲያ አምላክ ቤተ ክርስቲያናችንን ይጠብቅ::

Anonymous said...

I understand why the majority of people said 'tesebere' when they hear 'wodeqe'. We need change and that sense of feeling the change was ignited by the still banned Archbishop (Abune Samuel). So when we couldn't hear his ban was lifted, we become disappointed. But as to me, it is really a great development and no one won but the Church which deserve the much needed change.

Anonymous said...

የውሃ የዉሃ ምን አለኝ ፍልውሃ አይነት ካልሆነ በስተቀር "እየተመካከረ እንዲሰራ" ማለት????

ድርድር እንደ ደርድር ማለት አይመስልም?

Anonymous said...

I think it is fair to say that in the long run our church, including the clergy(Mahebere Kahenat), and followers of the Ethiopian Orthodox Church have won. The whole episode have brought out in the open the maner in which our beloved church has been miss-run for the past 17 years(For those of us who did not know). We have heard from great fathers of the church in plain language how Abune Paulos abused the power he had been entrusted with and reduced the church to another cash coffer to his cronies. I hope there will now be many more people(kahenat and memenane)who with calm mind, with deep prayers for God's help, and with purpose think forward on how the church admistration can be enhanced and be made transparent. People should be able to distinguish between what is the religion(the one we all accept without quetioning and deep faith) and the adminstrative roles of the various organs of the church which should be evolving all the time. If our church is to blossom and be a force for good for the followers and the country as a whole, lots of questions need to be raised and answered.

Anonymous said...

ደም ያለበት ጳጳስ
(የመነኩሴው ደም ይጮኻል!)
ከምዕመን (ናይሮቢ - ኬንያ) መስከረም 1999 ዓ.ም.
ከዘፍጥረት ዓለም - ከኦሪት ትዕዛዛቱ
… “አትግደል” … ነበር ቃሉ - አንደኛው ከአሥርቱ፤

እግዚኦ ማኅረነ ክርስቶስ …!
ነፍሰ-ገዳይ ሲሆን ጳጳስ …
ያውም “ብፁዕ ወቅዱስ …”

(… ቃለ-ክርስቶስ ከጥንት የምናውቀው
ሳዑል ወደ ጳውሎስነት ሲቀየር ነው፤
በኛስ ዘመን ጉድ መጣብን
ጳውሎስ ሳዑል ሲሆንብን!!)

… የመነኩሴው ደም ይጮኻል - የፈሰሰው ከታቦቱ ስር
የሰማዕትነት ዋጋ - እማይዘነጋ ለዘወትር!

… ንስኀ ሳይገባ ለራሱ
ሳትማር ተኮናኝ ነፍሱ
እንዴት ሊያስተምረን ነው ጳጳሱ?!

አባታችን ሆይ የሰማዩ - በቃ! በለን አሁንስ
“ነፍሰ-ገዳይ” ጳጳስ እየዞረ - ምናለ ታቦት ባያረክስ?
አቡነ ዘበሰማያት … - ኢትዮጵያን ይቀር በላት
ነፍሰ-ገዳይ ጳጳስ - ዳግም እንዳይነግሥባት!

አቤቱ ኧረ ተለመነን!?
ለዘላለም ዓለም አሜን!!!

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)