July 14, 2009

አቡነ ገብርኤልና አቡነ ሙሴ ለምን ያውካሉ?


(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 13/2009)
እንደሚነገረው የቅዱስ ሲኖዶስን ስብሰባ በማወክ ላይ ከሚገኙት አባላት መካከል ግንባር ቀደሞቹ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል (ፎቶው ላይ ያሉት) እና አቡነ ሙሴ (ፎቷቸውን ለጊዜው የለንም)ናቸው። በእውነቱ እንዲህ እንዳያደርጉ ብፁዓን አባቶች “ሃይ፣ ይተዉ” ካላሏቸው እኛስ ዝም ልንላቸው ይገባል?


እነሆ ስልካቸው (አቡነ ገብርኤል 001- 251 - 911 - 90 96 10)፤ አቡነ ሙሴ (001- 251 - 913 – 38 11 28) እየደወልን “አባቶቻችን አዝነንባችሗል፣ አፍረንባችሗል” እንበላቸው። ክርስቲያናዊ ጨዋነትን በተላበሰ መልኩ አናግሯቸው። በታሪክና በእግዚአብሔር ፊት ተጠያቂ ከመሆን ይዳኑ እንበላቸው።

የሰው ሀጢአትና በደል ቆጣሪ ከመሆን ያድነንና የብፁዕ አቡነ ገብርኤል የቅርብ ጊዜ ተግባራት (ሬዙሜ) የሚከተለውን ይመስላል፦
1. በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተ/ሃይማኖት ዘመነ ፕትርክና በጻፉት ኑፋቄ ያዘለ መጽሐፍ ተወግዘው ነበር፣
2. ከአቡነ ጳውሎስ ጋር “ተጣላሁ” ብለው ወደ ዲሲ ሸሽተው፣ እርሳቸውንም ሲያወግዙ ነበር፣
3. አቡኑ “ታረቅሁ” ብለው ከተመለሱ ወዲህ ሲያዋርዷቸውና ሲሰድቧቸው የነበሩትን ፓትርያርክ “ታላቅነት” በመለፈፍ ላይ ናቸው፤

አቡነ ሙሴም በተመሳሳይ መልኩ
1. ከአቡነ ጳውሎስ ጋር “ተጣላሁ” ብለው ወደ ውጭ ሀገር ሸሽተው፣ እርሳቸውንም ሲያወግዙ ነበር፣
2. አቡኑ “ታረቅሁ” ብለው ከተመለሱ ወዲህ ሲያዋርዷቸውና ሲሰድቧቸው የነበሩትን ፓትርያርክ “ታላቅነት” በመለፈፍ ላይ ናቸው፤
3. ወዘተ ወዘተ

ቸር ወሬ ያሰማን

++++++++++++++++++++++++

የጥንተ-ጠላታችን መርዝ የመጨረሻ ቅምሻ?
(By Nahudda)
የዘመደ-እጓለመሕያው/የትዝምደ-ሰብእ/የደቂቀ-አዳም/የውሉደ-ሔዋን/የሰው ዘርዕ በሙሉ የጥንት-ጥንት ጠላታችን እኛ ኢትዮጵያውያን ሰይጣን/ዲያብሎስ፤ ዕብራውያን “ሳጣን፣” ዐረቦች “ሾይጣን”/“ኢብሊስ፣” ጽርአውያን “ዲያቦሎስ” የሚሉት ከሳሽ፣ አሳጭ፣ አሳሳች፣ በጦር በነገር የሚከታተል ባላጋራ፣ ወደረኛ ክፉ መልአክ ሳጥናኤል ነው።
እንደ-ተዋሕዶ ኢትዮጵያውያን ደግሞ በተለይ ከ16ኛው መቶ ክፍለ-ዘመን ወዲህ ጥንተ-ጠላታችን ኾና የተነሣችብን ተንኮለኛ ወደረኛ የኮተሊክ ቤተክሲያን ናት። ይኸውም ሊታወቅ በፈረጠመ ጡንቻዋ በየጊዜው መርዟን ልትግተን ሞክራለች። ከከንፈራችን አልፋ ከጉረሯችን ብታደርሰውም እኛ ግን ባለመዋጣችን አልሞትንላትም። የጉልበቱ ባይሳካላት ዛሬ ደግሞ መርዙን ማር አስመስላ በገዛ እጃችን (በነአባ ገብርኤል፣ በነአባ ሙሴ፣ ይልቁንም የዘር ፖለቲካ በነእጨጌ በትረ-ጊዮርጊስ መዐርግ ባስቀመጣቸው በነአባ ጳውሎስ ልታውጠን በምላሷ እያግባባችን፣ በገንዘቧ እያባበለችን ትገኛለች። (በነአባ ገብርኤል ላልኩት፦ የኹለት ባሕርይ ትምርታቸውን የቀረሹበትን መጽሐፍ እናስታውስ፤ በነአባ ሙሴ ለሚለውም፦ በሊቃውንት ተርታ ስም-የለሹ ይኸ ደግሞ አዲግራት ያደረጉትን ማስታወስ በቂ ነው፤ ይልቁንም የዘር ፖለቲካ በነእጨጌ በትረ-ጊዮርጊስ መዐርግ ባስቀመጣቸው በነአባ ጳውሎስ ያልኩበት ምክንያት፦ እጨጌ ዘመንበረ-ተክለሃይማኖት ተብየው “ወረከብናሁ ለበትር ዘይቀጠቅጣ ለሮሜ፤ ጽሩበ በንባብ ወቅሩፀ በትርጓሜ” የተባለላቸው እጨጌ በትረ-ጊዮርጊስ በተቀመጡበት መንበር ተዘርፍጠው፦ እምየ የልብ ዐይናማው አለቃ አያሌው ታግለው ባያስቀሩት ኖሮ፤ የኮተሊክን ቤተክሲያን ሥራት እንዳለ ሕግ አድርገው ሊጭኑብን መሞከራቸውን አባ ገብርኤል ሳይቀሩ ለግል ጠባቸው ማዳመቂያ ሲሉ ነግረውናል። እንዲህ ያለ ዐይነተኛ የሥራት ለውጥ ለማምጣት መሻታቸው በዕውር ልባቸው ተደብቆ ያለ የውሳኔ-ሃይማኖት [የዶግማ] ችግር መኾኑ ግልጥ ነው። የሥራት ለውጥ ነው የተባለውም ቢኾን በቀጥታ ሃይማኖትን የሚነካ መነበሩን የተረዱት አለቃ፦ የመንፈስቅዱስን ድርሻ ልውሰድ የሚል ሰው “ጣዖት” መኾኑን በሚገባ ጠቁመውን ነበር፤ የሰማቸው ጠፋ እንጀ። ኹሉም “ዘከርስ” እንጂ “ዘመንፈስ ቅዱስ” ስላልነበረ።)
አሁን ታዲያ፦ አባቶች ተብየዎቹ በነአባ ጳውሎስ እጅ እንደመድኀኒት ካልጠጣችኋት ተሞታላቸኹ እየተባሉ የሚጋበዙትን የጥንተ-ጠላታችን የኮተሊክ ቤተክሲያን ብሎም የጥንት-ጥንት ጠላታችን የዲያብሎስን ግብዣ “እንብየ” ብለው ተፍተው ቤተክርስቲያናችንን ይታደጓት ይኾን??? እንዲህ ካደረጉ በአምላከ-ኢትዮጵያ ቸርነት ይኸ የመጨረሻ ቅምሻ ይኾናል ብየ ተስፋ አደርጋለኹ።
Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)