July 6, 2009

አስቸኳዩ የቅ/ሲኖዶስ ስብሰባ እንዳይካሄድ ከፓትርያርኩ ተቃውሞ ቀረበ


• ፓትርያርኩ ከጠ/ሚኒስትር መለስ ጋር የግል ውይይት አድርገዋል
(ደጀ ሰላም፤ ጁን 6/2009) በቤተ ክርስቲያን ያለው ችግር በተለይም ቅ/ሲኖዶስ በቅርቡ ባቋቋመው የሥራ አስፈጻሚና በቅዱስ ፓትርያርኩ መካከል የተፈጠረውን ችግር አስመልክቶ ለመወያየት ለነገ ማክሰኞ የተጠራው አስቸኳይ የቅ/ሲኖዶስ ስብሰባ እንዳይካሄድ ከፓትርያርኩ ተቃውሞ እየቀረበበት መሆኑ ታወቀ።

ብፁዓን አባቶች እንዲሰበሰቡና እንዲወያዩ አልፈለጉም፣ ሥራ አስፈጻሚውም በፓትርያርኩ የደረሰበትን ሕገ ወጥ ነው ያለውን አሠራር እንዳያቀርብ ይፈልጋሉ የተባሉት ቅዱስ ፓትርያርኩ ስብሰባው እንዳይካሄድ የተለያዩ ሰንካላ ምክንያቶች እያቀረቡ ነው እየተባሉ እየተተቹ ነው። “የቅ/ሲኖዶስን ስብሰባ የሚያስጠራ ምንም አዲስ ነገር የለም” ብለዋል የተባሉት ፓትርያርኩ “አስቸኳይ ስብሰባ የሚጠራም እንኳን ከሆነ የአህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆች፣ የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ገዳማትና አድባራት አንዳንድ አስተዳዳሪዎች፣ ሌሎች ግለሰቦች” ሊኖሩበት ይገባል ማለታቸው ታውቋል። ይህንን ሐሳብ የሚቃወሙት አባቶች በበኩላቸው ከዚህ በፊት ያልሆነውን የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ያልሆኑ ግለሰቦችን ካልገባችሁ የሚለው የቅ/ፓትርያርኩ አስተያየት ትክክል አለመሆኑን በመተች ሐሳባቸውን ውድቅ አድርገውታል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ አስቸኳዩ የቅ/ሲኖዶስ ስብሰባ ይደረጋል ተብሎ ከሚጠበቅበት ከነገ ማክሰኞ ስብሰባ በፊት አንዳንድ የጸጥታ ሁኔታዎችን ለመቆጣጠር ይመች ዘንድ ከዛሬ ሰኞ ጀምሮ ፓሊስ በአካባቢው ይገኝ ዘንድ በደብዳቤ እንደተጠራ የታወቀ ሲሆን ቅ/ፓትርያርኩም አጠቃላይ ሁኔታዎችን በተመለከተ ከአቶ መለስ ዜናዊ ጋር መወያየታቸው መንጮቻችን ገልጸዋል። የውይይታቸው ፍሬ ሐሳብና ውጤት እንደደረሰን የምንገልጽ ሲሆን ነገሩ ፓትርያርኩ ከሲኖዶሱ ጋር በገቡት ችግርና በወደፊት የርሳቸው ዕጣ ፈንታ ላይ ሳይሆን እንዳልቀረ ምንጮቻችን ተናግረዋል። ከፓሊስም ባሻገር ስብሰባውን ለመከታተል ይችል ዘንድ ተወካዩን እንዲልክም ተጠይቋል ተብሏል። መንግሥት ቤተ ክርስቲያኒቱ በገባችበት ሁኔታ ላይ ሙሉ አቋም ለመያዝ መቸገሩን የገለፁ የደጀ ሰላም ምንጮች እንደተናገሩት በተለይ በአዲስ አበባ አካባቢ የሚገኙ የደህንነት ሃይሎችና ለፓትርያርኩ ቅርበት ያላቸው ባለሥልጣናት ብፁዓን አባቶችንና የቅ/ሲኖዶስን ውሳኔ ሊቀበሉ ይችላሉ የተባሉ መንፈሳዊ ማህበራትን ሳይቀር ለማንገላታት (harrase ለማድረግ) እንደሚሞክሩ ታውቋል።

እንደታቀደው ይህ አስቸኳይ ስብሰባ የሚካሄድ ከሆነ ለቤተ ክርስቲያን የወደፊት አገልግሎት ወሳኝ የሆነ ውሳኔ ይተላለፍበታል ተብሎ ይጠበቃል።

1 comment:

Anonymous said...

In the Name of the Holy Trinity One God Amen!
To all members of the Holy Synod. Peace of Christ be with you. All you did in your assembly conducted in May in the one which we christians have been seeking for many Years. God Bless you all. Concerning the new decision of Abune Paulos, I expect he will get support from governement officials like PM Melese. But our fathers you are the one who have for the church and to our people. So we are asking you again to insist on your position what so ever is the decision and interference of the government. Your decision with help of Holy Sprit have great impact on tomorrow's church.

Though we your children all over the world don't want you to be hurted, we need you take some sacrifie to the church of God as our apostilic fathers did. And we will pray so that God will help us and bring the church out of such problems.

My brothers and sisters around the world let us pray so that God will help Our fathers who stand for the benefit of the church.

God Bless Orthodox Tewahedo, God Bless Ethiopia, God Bless the World.

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)