July 15, 2009

የሥራ አስፈጻሚው ዕገዳ ተነሣ

(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 15/2009)
በመንግሥት አደራራሪነት ዛሬ ዝግ ስብሰባ ተቀምጦ የዋለው የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ የሥራ አስፈጻሚውን ዕገዳ በማንሳት ለዛሬ እረፍት አደረገ። ከዚሁ ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ላይ የተጣለው ዕገዳ ላይ መነጋገር የተጀመረ ቢሆንም የጉዳዩ ባለቤት የሆኑት ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል በስብሰባው ላይ ባለመገኘታቸው ጉዳዩ ንግግር እንዳይደረግበት አባቶች በመጠየቃቸው ለነገ ተላልፏል። ብፁዕነታቸው በዛሬው ስብሰባው ያልተገኙት እንዳለፈው ሳምንት “ለደህንነታቸው” በሚል እገታ ሳይሆን እንዳልቀረ ተነግሯል። ስለዚሁ ጉዳይ በአባቶች የተጠየቁት የመንግሥት ባለሥልጣናት ስለ ነገሩ እንደማያውቁ መልሰዋል።


ይህ በእንዲህ እንዳለ ቅዱስ ፓትርያርኩ አሁን በመካሄድ ላይ ያለው የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ እንዲደናቀፍና ወደ ጥቅምት እንዲሸጋገር በመታገል ላይ ናቸው። ቅዱስነታቸው ይህንን የሚያደርጉት በተጠና ዝግጅት ለመቅረብ ዕድል ስሊሚሰጣቸው እንደሆነ የጉዳዩ ተንታኞች መስክረዋል። ፓትርያርኩ ራሳቸውን ከሕገ ቤተ ክርስቲያን በላይ እንደሚያደርጉ ትናንት ማክሰኞ የዘገበው የአሜሪካ ድምጽ ሲያቀርብ የደጀ ሰላም ምንጮች ደግሞ ሲኖዶሱም ተጠሪነቱ ለእርሳቸው እንደሆነ አድርገው መናገራቸውን መስክረዋል።

ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን

3 comments:

Anonymous said...

እንኳን በተዋሕዶ ቤተክርስቲያን፤ በመለካውያኑ የምስራቅ ኦርቶዶክስ አብያተክርስቲያን ሳይቀር ፓትርያርክ "ከእኩዮች የመጀመሪያው" (the first among equals) እንጂ፤ ከዚያ ያለፈ ድርሻ የለውም። ሲኖዶስም ተጠሪነቱ ለመንፈስ ቅዱስ ነው። ይህን የሚያፋልስ ሥራት፤ የተራ ቀኖና ጉዳይ ሳይኾን፡ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት የማመን-እና-ያለማመንን ነገር የሚያመለክት ነው።

ከ5ኛው መቶ ክፍለ-ዘመን ጀምሮ የሮማ ቤተክርስቲያን በሥጋዊ ዐሳብ በታጨቁ መሪዎቿ አማካይነት የቅዱስ ጴጥሮስን ትከሻ (መቃብር) በመታከክ መሪየ የቤተክርስቲያን ራስ፣ መንበሬም የመላው ዓለም አህጉረ-ስብከት ማዕከል ነው እያለች እንደምትለፍፍ ይታወቃል። ነገር ግን የቤተክርስቲያን ራሷ ለመላው ዓለም ድኅነት ደሙን ያፈሰሰ ጌታ እንደመኾኑ፤ ከዚህም ጋር መድኀኒትነቱን የፈጸመው “ወገብረ መድኀኒተ በማዕከለ-ምድር” እንዲል፤ “ኅንብርታ ወአክሊላ ለምድር” በምትባል በኢየሩሳሌም ስለኾነ፤ ኹለቱም የሮማ ቤተክርስቲያን ቅዠቶች ፉርሽ ኾነው ይገኛሉ።

ይኹንና ታዲያ ይኽንን ነገር አሁን እየሰማን ካለው ዜና ጋር አያይዘን ስናነጻጽረው በዚህ ዘመን “በዐላዊ ንጉሥ በመናፍቅ ጳጳስ” እየተገዛን ያለን መኾናችንን ወለል አድርጎ አያሳይም ወይ? ለምን ራሳችንን እንሸውዳለን? ስንት ገና ትምህርት ያላደላደሉ ምስጢር ያላስተዋሉ ወጣት ሰባክያንን (አንዳንዶቹን እንዲያው በዳኅፀ-ልሳን ምክንያት ሳይቀር) “መናፍቅ” እያሉ ጥላሸት ሲቀቡ የነበሩ ኹሉ (ማ.ቅ.ንን ጨምሮ) በዐበይቱ ዘንድ እያየነው ያለውን እንዲህ ያለውን ዐይን ያወጣ ተግባር ለማጋለጥ የማይደፍሩት ለምንድን ነው? እንደኔ እንደኔ ጉዳዩ፦ ካስተዳደርም፣ ከቀኖናም ያለፈ ነገር አለበት--የሃይማኖት ነገር! ችግሩም “ኑፋቄ” አይመስለኝም፤ “ክህደት” እንጂ። ነቢዩ ዳዊት “ወኀለፈ እምትዕቢት ልቦሙ…ወአንበሩ ውስተ-ሰማይ አፉሆሙ፤ ወአንሶሰወ ውስተ-ምድር ልሳኖሙ።” እንዳለ፤ እነዚህ ሰዎች ልቡናቸው ከትዕቢት ወደ ትዕቢት አየኼደ ነው፤ አንደበታቸውንም በሰማይ ያኖሩት በምድርም እያመላለሱት ያሉ ይመስላል፤ ማለትም፦ በሰማይም በምድርም አምላክ የለም (ልብ በሉ፦አምላክ የለም!) ያሉ ይመስላል።
ይልቁንስ የዚች ቤተክርስቲያን ነገር በውነት ግድ የሚለን ካለን፤ ይኽንን ኹኔታ በምር እንረዳ እና “ምን ይሻላል?” ብለን ራሳችንን እንጠይቅ፤ በየምናገኘውም አጋጣሚ ርስበርስ እንመካከር።

Nisir said...

በእውነት የፓትርያርኩ ጉዳይ የሐይማኖት ችግር እንጂ የአስተዳደር ችግር አይደለም። አንዲት ሴት ወይዘሮ ጳጳሳትን በሽጉጥ እያስፈራራች ፤ በጳጳሳት ላይ የተጻፈ አስነዋሪ ስም ማጥፊያ መጽሐፍ በቤተ ክህነት ግቢ ውስጥ እንዲሸጥ ከማድረግ፤ እንደ ተራ ፖለቲከኛ የመገናኛ ዘዴዎች ላይ እየቀረቡ ማግለጫ መስጠት እና ለጋዜጠኞች እና ደህንነቶች የቤተ ክርስቲያኗን ገንዘብ አውጥቶ በመስጠት፤ ከቤተ ክርስቲያኗ እውቅና ውጪ ከሮም ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ጋር በጉብኝት ሽፋን ሚስጥራዊ ግንኙነቶች ማድረግ፤ ስለ
ቤተ ክርስቲያን የተከራከሯቸውን አባቶች በዝውውር ሰበብ ካጠገባቸው በማራቅ፤ ቀስቅውስት እና ምዕመናን በአክራሪ ሙስሊሞች ሲታረዱ ቤተ ክርስቲያንን እያንቋሸሹ መጽሐፍትን ሲጽፉ ስለቤተ ክርስቲያን በመቆም ፈንታ ዝም በሉ አትናገሯቸው በማለት ሰባኪያንን ከማስፈራራት ሌላ ምን የከፋ ነገር አለ። በእውኑ ይህ በደል ሱሱኒዎስ የሮም ካቶሊክን በመቀበል በቤተ ክርስቲያን ላይ ካደርሰው በደል በምንድን ነው የሚሻለው?
በርግጥ ፓትርያርኩ ዘመናዊውን ትምህርት መማራቸው ቃላትን እያሳመሩ ለረጅም ዓመታት በማስመሰል እንዲቆዩ አድርጓቸዋል። እንዲህ ያሉትን አጽራረ ቤተ ክርስቲያን እውነተኞቹ የቤተ ክርስቲያን ሰዎች ካላጋለጡ የቱ ላይ ነው ለተዋህዶ መቆማቸው? የቤተ ክርስቲያን ሰባኪያን እና የመገናኛ ዘዴዎች እውነቱን ካልተናገሩ፤ ምዕመኑ መሪ አጥቶ ዝም ቢል፤ ፓትርያርኩ እንደ ሪፖርተር፤ ኢትዮጵያ ፈርስት፤ ንጉሴ ሬድዮን ያሉትን በምጠቀም ፕሮፓጋንዳቸውን ከቀጠሉበት እውነተኛውን ድምጽ ከየት እንስማ? ለምንስ ድምጻችን የተበታተነ ጩኸት ይሆናል?

Anonymous said...

yes, this will be the begining of the end.
'patriarck' pawlos is not chrstian or muslim .We know that in history EOTC lead by muslim Bishop when she appoint the bishop from Egipt,now a day the church is leading by pagan for the last 17 years.
Meharene kirestos

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)