July 16, 2009

አባቶች አካላዊ ጉዳት እንዳልደረሰባቸው ታወቀ

(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 16/2009)

ረቡዕ ከምሽቱ አራት ሰዓት ጀምሮ በአካባቢው ያለውን የመብራት መጥፋት ተገን ያደረጉ ሰዎች በብፁዓን አባቶች ላይ አደጋ ለመጣል በተደረገው ሙከራ ከንብረት ውድመትና አባቶችን ከማጎሳቆል ባለፈ አካላዊ ጉዳት በሚያደርስ መልኩ አደጋ የደረሰበት አባት እንደሌለ ታወቀ።

ብዙ የጥበቃ ሠራተኞች በሚተራመሱበት የቤተ ክህነት ግቢ ውስጥ በሚገኘው የብፁዓን አበው መኖሪያ ሕንጻ ላይ በተሰነዘረው በዚህ አደጋ የቅዱስ ሲኖዶስ መብት አስጠባቂነቱን ስብሰባ በመምራት ላይ የሚገኙት የብፁዕ አቡነ ቄርሎስ ቤት በሮች ከተሰባበሩ በሁዋላ እርሳቸው ግን በእግዚአብሔር ቸርነት ሲተርፉ በተመሳሳይ መልኩም የብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ቤት በር ተሰባብሯል ተብሏል።

ከሌሎቹ በተለየ የብፁዕ አቡነ ቄርሎስ ቤት ለአደጋ የተጋለጠበት ምክንያት የአባቶች ፊርማ ያረፈበት ቃለ ጉባዔ እርሳቸው ዘንድ ስለሚገኝ ሊሆን እንደሚችል ምንጮቻችን አብራርተዋል። ከርሳቸው በተጨማሪ ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ለተወሰነ ጊዜ “ታፍነው፣ ማስፈራሪያና ዛቻ” ደርሶባቸው ተለቀዋል የተባለ ሲሆን ሌሎች ምንጮች በበኩላቸው ምንም እንዳልደረሰባቸው ይናገራሉ።

ይህ ሁሉ ሲሆን የግቢው የጥበቃ ክፍል ምን ይሠራ እንደነበር፣ የት እንደነበር ገና ምርመራ ያስፈልገዋል። አደጋውና በር- ሰበራው ለጆሮም ለዓይንም የማይሰወር፣ እንኳን የጥበቃ ሠራተኞች ራሳቸው ፓትርያርኩም ሊሰሙት የሚችሉት እንደሆነ ተገልጿል። አባቶች ስለ ቤተ ክርስቲያን ያላቸውን አቋም በመግለጻቸው ብቻ ጥበቃ ሊደረግላቸው ሲገባ ለአደጋ በሚጋለጡበት ሁኔታ መተዋቸው የተደፈረችው ቤተ ክርስቲያን መሆኗን ያሳያል ተብሏል። አደጋው መድረሱን ያወቁ አንድ አባት ለጥበቃ ሰዎች ቢናገሩም የሚደርስ ሰው አለመገኘቱ ሲታወቅ መንግሥት በእምነት ደረጃ የሃይማኖት አባቶች፣ በዜግነት ደረጃ አረጋውያን የሆኑ አቅመ ደካማ ዜጎቹን ለመጠበቅ አለመቻሉ አነጋግሯል።

ዛሬ ጠዋት አባቶች በአካል በተገናኙበት ወቅት ስለ ጤንነታቸውና ስለ አጠቃላዩ ሁኔታ ሲነጋገሩ መታየታቸው ታውቋል። በዚህ የመንፈስ መረበሽና የሴኪዉሪቲ እጦት መንፈስ ምን ዓይነት ስብሰባ ሊያኪያሂዱ እንደሚችሉ ብዙዎችን ግራ አጋብቷል። በዚህ ወንጀል ውስጥ ሊሳተፉና ሊመሩ የሚችሉ እነማን ሊሆኑ ይችላሉ የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ የራሳቸውን መላምት የሚሰጡ ምንጮቻችን እንደሚናገሩት በፓትርያርኩ መሪነት እርሳቸውን ተገን አድርገው የሚንቀሳቀሱት ማፊያ ቡድኖች፣ በተለይም የእጅጋየሁ በየነና የቅዱስነታቸው የወንድም ልጅ የሆነው የያሬድ ጋሻ ጃግሬዎች ሳይሆኑ አልቀሩም ይላሉ። ሌሎችም በበኩላቸው መንግሥት የሚጫወተው ድራማ ወይም በቁልቢ ብር የተገዙ የደህንነት ሠራተኞች የሚሰሩት ሕገ ወጥ ድርጊት ይሆናል ሲሉ ግምታቸውን ይናገራሉ።

በትናንት ረቡዕ ስብሰባ ፓትርያርኩ “ሕገ ቤተ ክርስቲያን የምትሉትን አልቀበልም፣ የማንም ዱርዬ የሠራው ነው፣ … ሲኖዶሱ ተጠሪነቱ ለፓትርያርኩ ነው” የሚለው ክርክራቸው ከከሸፈ ወዲህ በትልቅ የተስፋ መቁረጥ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ። ነገሩ በዚህ ካለቀ ችግር ውስጥ የሚገባው የፓትርያርኩና የማፊያዉ ቡድን ወደ ጥቃት የተሸጋገረው ለዚህ ሳይሆን አይቀርም ተብሎ ተገምቷል። ሲኖዶሱ በመንግሥት ባለሥልጣናት አሸማጋይነት የጀመረው ስብሰባ ዛሬም ቀጥሎ በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ ሳሙኤል እግድና በሌሎች አጀንዳዎች ዙሪያ ለመነጋገር ቀጠሮ ነበረው።

ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን

14 comments:

Anonymous said...

What a sad news!!
Let us cry infront of God to save our church. Let us cry... beyond prayer!!
G.Kidan

Anonymous said...

Let alone threatening yared,mulugeta and other relatives of HH can do worse. They aren't their because they're believers, they are in pursuit of their money making scheme... we all know that. Shame, the church is becoming the house of gangsters! ... just like Christ said!

Unknown said...

In the Name of Holy Trinity One God Amen!
We are really sorry to see such things. As Jesus said "Yetifate Erkuset betkedesewu bota Sitayu Anbabiwu Yastewul" Enastewul. Let us Pray again so that God will end this with out division. Even though there is temptation form Satan, Aba Paulos's action is not acceptable. He should be totally removed from the church's admin.

Geta Holy Ante Tawukaleh, Sile Kidusan bileh bechernetih Eyen!!!

Nisir said...

ጸሎት እና መናገር ማሳወቅ የሁላችንም ድርሻ ነው። ክርስትና እውነትን ከመናገር ትጀምራለች። የሱሱኔዎስ ወራሽ የሆኑት ፓትርያርክ እና መሰል የጨለማ አበጋዞቻቸውን ሥራ ማጋለጥ አንዱ ድርሻችን ነው
እንግዲህ በአራቱም ማዕዘን እምነት ያጡት፡ በነቢብ እና በገቢር አጽራረ ቤተ ክርስቲያንነታቸውን ያስመሰከሩት ፓትሪያርክ እና መሰሎቻቸው በምን ስሌት ይሆን መንፈሳዊ መሪዎች ሆነው የሚቀጥሉት?

Anonymous said...

Ebakachwu Abatoch begeziabher fekad endetenqequ bqrb lemtggnu kiristianoch hulu aderawu ynant chmr nwu.
Medehanealem Yirdan. Amen

Anonymous said...

ሰላም ደጀ ሰላሞች
እናንተ ራሳችሁ አሸባሪዎች ናችሁ አንዳንዴ ዘገባችሁ ግራ ያጋባል። እባካችሁ ተጨባጩን ወሬና ሪፖርት ሳትይዙ እንዲህ ሆነ እንዲህ ተባለ እያላችሁ እኛንም አታስጨንቁን እባካችሁ ስለ እግዚአበሔር ብላችሁ። በተለይ እኔ በጣም እየተረበሽኩ ነውና እውነት የሆነውንና ትክክለኛ ማስረጃ ያለውን እየተከታተላችሁ አስነብቡን።

Anonymous said...

እግዚአብሔር ይመስገን አባቶቻችንን ስለጠበቀልን ጉዳዩ አሁንም አሳሳቢ ቢሆንም ያለው መፍትሔ አንድና አንድ ብቻ ነው እርሱም ጸሎት ማድረግ ነው እባካችሁ በያላችሁበት ቤተክርስቲያን ላሉ አባቶች ንገሩ ምህላ ጸሎት እንዲያደርሱ በግልም ጸልዩ ሰዎች ሳይሆኑ እግዚአብሔር እንዲፈርድ አርሱ መድኃኔዓለም ለዚህች ቤተክርስቲን ደሙን ያፈሰው እንዲዳኛት በግልም በማህበርም ጸልዩ

ድንግል ማርያም በምልጃዋ ታስምረን

በትረድንግል

arbaminch said...

I agree with those of my brothers or sisters who commented that Prayer is the solution for our church problems. In addition to that we have to fix ourselves. For example if our heart is divided in to two; sometimes we get religious(we fast and pray) and the next day we are at a music party dancing with the uncommitted world. So It doesn't give sense to pray for one united church where as we have our heart ,which we have total control of, divided in to several parts.
Dear brothers and sisters christians, we need to Pray with undivided heart and GOD shall give our church unity.

Christians should not be amazed by what is happening today. There is no new thing in this world. Things worse than this has happened in history of Christianity.

So, Let's all pray with one undivided heart ; that GOD shall send his holly spirit to make our fathers(with no exceptions) live by one heart.

Anonymous said...

"Emebete hoy yikir beyin. Minew Ethiopia lay chekenshibat" Yabune Petros tselot neber. Yabune petros tshelot yismerlin.

Tadesse

YeAwarew said...

Selam all:
Thank you, Deje Selam, for the update.
It is very heartrending, it makes me cry that we have to witness this in our life time in the Church of our great fore-fathers/mothers like Abune Teklehaimanot, Abune GebreMenfesQidus… who have been loved by all. Oh! It is just heart wrenching. May God protect everyone of them.

But like some of the above comment authors, I don’t just believe everything I hear and I read. I always try (make an effort) to “take it with some salt”, as the Holy Bible puts it.
I know Deje Selam Editor reports it as he sees fit, what is said by the reporters close to the Fathers. If Deje Selam has to hold on a report till there is evidence, investigation report, audio or video record or something that collaborates it, we wouldn’t hear/read any of it. That is it.

So when we read a report like this and if we want to dig in more, I suggest, call the folks back home in Addis or …. And ask the people we know that are close to the “Papasat” and find out what is going on. That is what I do. Most of the time I find out that Deje Selam is reporting the same thing. But I remain to get the full (sides of ) the story, not just one side, as much as I can.

In the mean time, let us all present our fervent prayers to the Almighty. He is the One and Only that can bring about change. (Psalm 50:1-)

We can never rely on ourselves or on people to do the right thing, every human being is fallible. Only with the help of the Almighty God are such things possible .
May God protect His Church and the True Fathers,

Cher neger yaseman

YeAwarew

Dan said...

I can safely assume that these lawless and vagabonds did their terror work with the knowledge and consent of aba paulos. Aba Paulos and his terror squad’s aim is to intimidate those who demand the RULE OF LAW and COLLECTIVE CHURCH LEADERSHIP of the Synod, and to silence them. Not long time ago what happened inside the St. Stephanos Church and the killing of a monk/Bahtawi in the presence of Aba Paulos was never investigated. This intimidation of member of the Synod may never fully investigate.

Who knows the Church money is being used to bribe those with weapons and encouraged these hoodlum thugs to do his dirty work. Now we know Aba paulos is the chief thug.

I do hope members of each Church everywhere avoid him and express their sadness and disapproval of his leadership.

I also hear he is not in good health condition that he has Diabetes disease that his days might be numbered.

This crisis would have been his chance to rehabilitate himself in front of God and the Church by limiting his remaining life to prayer and repentance. The Lord would forgive him and there will be more joy in heaven over his repents as Christ the Lord said in Luke 15:7

Does he have a confessor or someone who can privately tell him, that he has hurt many and has done enough damage to the Church?

Girmay said...

This is very sad news.It is a complete disaster.It is the first time in history that Ethiopian Orthodox church is under siege by mafia groups.We should ban all activities from taking with Aba PAULOS.If Synode does not take action,we must take action as soon as possible.I have seen in so many web posted that Ejigayehu and yared are the leading one on orchestrating this mafia act.But there is one hidden guy never mentined before.He is Ato Tekabu who was the administrator in Theology college.He is the relative of Hailesilassie who is the top intelligent guy in TPLF.He has the authority to instruct the Federal Police.Aba Pulos brought to his office Ato Takabu knowing that he can assist Aba Pualos by making link to Security office.Haileselassie is one of the right hand of Meles and he cannot do anything without Hailesilasie involvement.Shame for Meles and Aba Paulos

Anonymous said...

መንፈሳዊነት ከሊቅነት በሚገባ አስተባብረው ይዘው የነበሩት the late Abuna MerhaKerestos used to say: "ይኸ ሰይጣን (አባ ጳን!) ቤተክርስቲያናችንን ሊያጠፋት ነው"

I wish now and do pray that each and every member of the HS could once for all say: "እክህደከ ሰይጣን!!!"


"O spare me, that I may recover strength, before I go hence, and be no more."

Anonymous said...

+++
መቼስ ምን ይባላል? አንገት የሚያስደፋ ድርጊት ነዉ እየተከናወነ ያለዉ። የቅድስት ቤተክርስቲያን ጠባቂዋ እርሱ ባለቤቱ ጌታችንና መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አይተወንም፡፡ እርሱ ዓላማ አለዉ፡ ምናልባትም ቤቱን የሚያጠራበት ጊዜ ደርሶ ይሆናል። የቀደሙ አባቶቻችንን ያፀና ልዑል እግዚአብሔር ለብፁዓን አባቶቻችን ጽናቱን ያድልልን። መስማማቱን ይስጥልን፡፡ እስቲ እኛም ከመቼዉም በላይ በጸሎት እንትጋ። ደጀሰላማዉያን(ት) ትክክለኛዉን መረጃ እንደሚታቀብሉን እተማመናለዉ። ቸር ወሬ ያሰማን።
ሀ.ገ.

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)