July 31, 2009

ጠቅላይ ቤተ ክህነት “አዲስ ነገር ጋዜጣን” ከሰሰ

• መጋቤ ካህናት ኃ/ሥላሴ “ደጀ ሰላም”ን ነቀፉ፣

(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 30/2009)
መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት “አዲስ ነገር ጋዜጣን” መክሰሱ ተሰማ። ከግንቦት 2001 ዓ.ም እስከ ሐምሌ አጋማሽ ድረስ በቅዱስ ፓትርያርኩና በቅ/ሲኖዶሱ መካከል የተፈጠረውን ውጥረትና አለመግባባት ስትዘግብ የነበረችው ሳምንታዊ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ታምራት ነገራ እና ጉዳዩን ሲከታተል የነበረው ሪፖርተር አብርሃም በጊዜው በፖሊስ ተጠርተው የቀረቡት አዲስ አበባ ፖሊስ (አራዳ ክ/ከተማ) ሲሆን ቃላቸውን ሰጥተው በዋስ መለቀቃቸው ታውቋል።


የቅዱስ ፓትርያርኩን ስምና ክብር በማጉደፍ፣ በሐሰት ስማቸውን በማጥፋት እንዲሁም ሐሰተኛ ዜና በማቅረብ የተከሰሱት ጋዘጤኞቹ የምርመራ መዝገባቸው ወደ አቃቤ ሕግ ከተላከ በሁዋላ የሚያስከስሳቸው ሆኖ ከተገኘ ፍርድ ቤት ሊቀርቡ እንደሚችሉ ተጠቁሟል። ጋዜጠኛ አብርሃም ይህንኑ ዘግቦ ሲመለስ ባልታወቁ ሰዎች መደብደቡን መዘገባችን ይታወሳል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በቤተ ክርስቲያን ጉዳይ “ደጀ ሰላም”፣ ቪኦኤና አንዳንድ የሀገር ውስጥ ጋዜጦች ከጋዜጠኝነት ሥነ ምግባር ጋር የሚቃረን ሥራ ሠርተዋል፣ የቤተ ክርስቲያንን ክብር አዋርደዋል ሲሉ አንድ የቤተ ክህነት ባለስልጣን ተናገሩ። ባለስልጣኑ መጋቤ ካህናት ኃ/ሥላሴ ዘማርያም “መሰናዘሪያ” ከተሰኘ ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ሚዲያዎቹን ከወቀሱ በሁዋላ በዚህ ጉዳይ አሉበት የተባሉትን ብፁዕ አቡነ ሳሙኤልን “ተሳስተዋል” ማለታቸው ታውቋል።

መጋቤ ካህናት ኃ/ሥላሴ ወደ ካህናት አስተዳደር ከመምጣታቸው በፊት በድሬዳዋ ሀ/ስብከትና በቤቶች አስተዳደር የሰሩ ሲሆን በተለይም በቤቶች አስተዳደር ውስጥ በሚሰሩበት ወቅት የቤተ ክርስቲያኒቱን ቤቶች ቁልፍ በመሸጥ ሀብት ያካበቱ “የማፊያው ቡድን” አባልና “ሙሰኛ (ኮራፕት)” መሆናቸው ይነገራል። በዚህ ምግባራቸው ይታወቁ እንጂ ማንም ደፍሮ የማይናገራቸው በትግሉ ዘመን መሳሪያ አንስተው ከተዋጉትና ስልጣን በኢሕአዴግ እጅ ከገባ በሁዋላም ቀደም ብሎ በትግራይ የሰሩ ነባር ታጋይ በመሆናቸው ሳይሆን አይቀርም ተብሏል።

29 comments:

Anonymous said...

megabe aba paulos hayle diabilos ze kersaam beluu ingii yihi simnaa siltan ayigebaachewum. yeisachewu tsiwa silalmola maniinim mekses yichlalu " gize yestewu qil dingayi yisebral "

Anonymous said...

Dear deje sela
Thanks for information, keep up
God will be helping them. yaldefers ayteram
God bless EOTC

tesfa said...

አዲስ ነገር ጋዜጣ የማህበረ ቅዱሳን ድብቅ ጋዜጣ መሆኑን እሰማለሁ ምን ያህል እውነት ነው? እውነት ከሆነ ይገርማል ጥሩ
ነው ።ግን ውስጥ ለውስጥ መንገድ ማበጀታቸው ወደፊት ለኢትዮጵያ አይጠቅምም ይህ የውስጥ ለውስጥ መንገድ አራት ኪሎ ቤተ መንግሥት ያደርሰናል ብለው አስበው ከሆነ ጥሩ ነው ወያኔ ከደደቢት አራት ኪሎ የደረስው ግልጽ በሆነ መንገድ ነው ፤ቅንጅት ደግሞ ከያቅጣጫው በተለያየ መንገድ ትጉዞ አራት ኪሎ ሳይደርስ ተበተነ ፤ማህበረ ቅዱሳን ደግሞ ካምስት ኪሎ አራት ኪሎ ለመግባት እየተንኻተተ ነው ከተሳካ በጣም ጠቃሚ ጉዞ ነው ይህን ያልሁት አምራጭ የፖለቲካ ድርጅት ስለሌለ ነው
በጣም አሣሳቢው ጉዳይ ግን ኢየሱስ ክርርስቶስን ለመሸፈን አዲሱ ትውልድ ያባቶቼ በሚል የስህተት ትምህርት መበከሉ ነው።
ማህበበረ ቅዱሳን ወጣቱን አሰባስቦ ፖለቲካዊም ሆነ ኢኮኖያዊ ለውጥ ለማምጣት የሚደርገው ን ትግል እጋራለሁ ለዚህም የራሱ የገቢ ምንጭ ቢኖረው ደስተኛ ነኝ እኔም እለግሳለሁ ።ነገር ግን ኢየሱስ ክርስቶስን መቃወሙና የሐሰት ድርሳንና ገድል ያልተረገ የፈጠራ ትምህርት እያስተማረ ትውልድ መበከሉን ግን አጥብቄ የምዋጋው ነገር ነው በርካታ የቤተ ክር/ ልጆች ተሐድሶ እየተባሉ በረንዳ ላይ የወደቁት በማህበረ ቅዱሳን አስዳጅነት ነው ይህ ስደት በበዛ ቁጥር ተህድስዎችም እየበዙ ነው በያንዳዱ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቢያንስ አሥር ተሃድሶዎች አይጠፉም በተ ክርስቲያኒቱ በተሃድሶዎች በሚገባ ተወራለች ግን እንደ ማህበረ ቅዱስን መግነን ሳይፈልጉ ውስጥ ውስጡን በውንጌል እየመደምዱ መሆኑን በርካታ ምልክቶች ይታያሉ ፡፤ማህበረ ቅዱሳን በከንቱ ይደክማል እንጅ የተቀጣጠለውን የተሃድሶ እንቅስቃሴ ማዳፈን አይችልም ይልቁንስ በርካታ የውሸት ጽሑፎች ወደ አደባባይ ወጥተው ከማፈራችን በፊት እርማት ያስፈልጋል ተሃድሶ ማለት የህይወት ለውጥ ማምጣት ማለት ነው እንጂ የሐይማኖት ለውጥ ማለት አይደለም የህይወት ለውጥ የሚመጣውም በኢየሱስ ክርስቶስ ነው ለዚህ ነው ተሃድሶዎች ኢየሱስን ይየሚሰብኩት ታዲያ ማህበረ ቅዱሳን ለምን የህን እንደሚቃወም አይገባኝም ለምሳሌ የምርትነሽን መዝሙር "ኢየሱስ የግዚአብሔር ልጅ ወዳጄ ድረስልኝ" የሚለውን መዝሙር ማህበረ ቅዱሳን ለምን ተቃወመ? ችግሩ ምንድን ነው ተው ኢየሱስን በመቃወም የሚመጣ ምንም አይነት ለውጥ የለም ኢኮኖምያዊም ፖለቲካዊም። ማህበረ ቅዱሳንን የምንቃወመው ኢየሱስን በመቃወሙ እንጂ ለፖለቲካና ለኢኮኖሚ ለውጥ የሚያደርገውን ምጢራዊም ይሁን ገሃዳዊ እንቅስቃሴ እንደግፋለን ጋዜጣውንም እናነባለን ።ስለኢየሱስ የሚዘመሩ መዝሙሮችን ፡ስለኢየሱስ የስበኩ ስብከኦችችን የሚቃወም ከሆነ ግን ከኢየሱስ አይበልጥብንምና ዘወር በል እንለዋለን።
ቸር ወሬ ያስማን

Anonymous said...

teklay byte khnet degmo gazytegnawn mekses gemerachu? enanten ymykes tefto brun stsrku abatochn staglaru endefelegachu ena egziabhern satferu aynachun aftachu gudoch nachu eko ykr ybelachu moshlakoch amlak yfred emye maryam tfred kdus mykal kdus gebrael seyfachwn ymzeaut stakelafu kenu desebachu kepatryyark eske papasat ketkit papasat besteker ahunm frd yeamlak new beytun liasedaw tenestual nsha lagbu yach enchet lekma engera gagra ewnetegna hebtamm kalew leegziabher blo yesetewn meba enkt adrgachhu belachut yemegeberia sndy yebla ylefelfal ybalal ena enantme keses sygebachu metaserm sygebachu yabyen wede emy endylu ayn aewtawoch enante kesash honachu yethiopiya aemlak yfred

amyn

Anonymous said...

aba pawlos keene achafarywchwo gar lngerachu syetyewam satker bewchim yalu american newyork seattle yalew menkusy batekalay pawlosn aelehulh yemiel mahbere frsrs yemybalu yesewn sra newna yemyserut yeegziabhern ttew yfred begocheb tebku bylachw leawrye settew astarku bylachew ataltew tareku bylachtetaltew endyhu kerachu kahnat mastarek stchlu satastarku metarek stchlu sattareku endyhu tkeru eyalu sealy kasa ke 1956 aete mhret gemre biynegruachhu alsema blachhu eziyh lay desesachhu ygermal yadnen sewoch lmkerachhkerbaulnau gyziachhun bekentu aetchrsu selu slot yeniserawn rayalachhu gytam lehewryatu siastemr yh hulu yenyhonew besom beselot new blwal ena bertu elalehu edmye ystenna yasayen sndywm keenkrdadu lyleyw kerbbual ena bertu

Anonymous said...

Dear tesfa from above,አዲስ ነገር ጋዜጣ is not and can't be የማህበረ ቅዱሳን. May be some of the memebre can be the writer or reporter due to employed. This also can't say አዲስ ነገር ጋዜጣ is የማህበረ ቅዱሳን. Member of MK are employed from small organization upto big organization (Govermental & NON gevermental, so do you mean that these all organizations are MK's? I am Sure You agree that it can't be.
Let me come to the point, the bad thing is what our church leadrs are doing? They did not want to tell the truth. True is alwyes True. Ewuneten Ymenageru andebet endet yamaru nachewu. So every body can concluded that Aberham was bited by one of thier Mafia. It is very sham,history never forget it.
I am afraid of them for DS.
Chere were Yaseman
Lebetecrstian andenet Tseliyu.
kzequal

qedamawi said...

ጉድ በሉ ጎበዝ! የቤተክህነቱ ማፍያ/ጨለማው ቡድን እውነትን በመክሰስ ለፍርድ ፖሊስ ጣቢያ ያቀረቡበትን ዜና ከአሚሪካ ሬድዮ ሳዳምጥ እጅግ በጣም አዘንኩ። ኧረ ጎበዝ ምን አይንት ዘምን ላይ ነው ያለነው? እውነት ፍርድ ቤት፤ጨለማን ተገን አድርጎ ማጅራት መቺው ተንደላቆ ከሳሽ ሲሆን? እንዲህ እነ ብጹህ አቡነ ቄርሎስም እቤቶ ለምን ተሰበረ ተብለው ፍርድ ቤት ሊያቆሟቸው ነዋ? ትንቢት ተናገርክ አትበሉኝ እንጂ ሊቃነ ጳጳሳቱም ስም አጥፍታችኋል ተብለው በአጭር ግዜ ውስጥ ፍርድ ቤት መቅረባቸው እንደማይቀር ነው።

Anonymous said...

የማኅበረ ቅዱሳን ችግሮቹ ሁለት ናቸው

1ኛ . በተለያየ ዲፓርትመንት የዘመናዊ ትምሕርት የተካነውን ትውልድ በአንድ ድርጅት ስር አቅፎ እንደ አንድ ሰው እንዲያሰብ ለማድረግ የሚያደርገው ሙከራና ሂደት ነው ::

2ኛው ደግሞ : ቀደም ሲል በዚህ መስመር በማኅበረ ቅዱሳን ውስጥ ትልቅ ቦታ የነበራቸው ግለሰቦች :
በኋላ ላይ ይህ የቄስ አካሄድ አልጥም ስላላቸው እና በሌላም የውስጥ ችግር ምክንያት : ከማኅበሩ እየወጡ ወይም ጎን ለጎን ወደ ፖለቲካው መስመር ዘው ዘው እያሉ መምጣታቸው ነው ::

በኢህዲግ አብዮታዊ ዲሞክራሲ ፕሮግራም መሰረት
ከራሱ ከኢሀዲግና ከአጋር ድርጅቶች (አሻንጉሊቶች ) ውጪ "

ምንም ዓይነት ጠንካራ እንቅስቃሴ :
ፖለቲካዊም ይሁን ኢኮኖሚያዊ
ሃይማኖታዊም ይሁን ማኅበራዊ ተቋም እንዲኖር አይፈቀድም ::

በዚህ ምክንያት የማኅበረ ቅዱሳን አለቅጥ እየተለጠጠ መሄድ ለኢህዲግ የራስ ምታት ከሆነ ሰንበትበት ብሏል ::

እነ በረከትና መለስም ይህንን ሳያስቡት የተቀጣጠለ እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር አጋጣሚ እየጠበቁ እንደሚገኙ ሳይታለም የተፈታ ነው ::

በአንዳንዶች ግምት : ማኅበረ ቅዱሳን

የተማረውን ትውልድ በማሰባብሰብ : የመንግስትን ስልጣንም ይሁን ቤተ -ክህነትን እጅ ለማድረግ የተደራጀ ቡድን እንደሆነ ይገመታል ::

ነገር ግን እስካሁን ድረስ ግልጽ የሆነ በቂ መረጃ ስላልተገኘ : ከጠንካራ ጥርጣሬ በቀር እርግጡን ለማወቅ የተቻለ ስለመሆኑ እርግጠኞች አይደለንም ::

አሁን አሁን : እንደነ (ዲ /ን ) ዳንኤል ክብረት ዓይነቶቹ ነባርና ታዋቂ አባላቱ : በግል ጋዜጦች ላይ : ማኅበረ ቅዱሳን ከሚከተለው አካሄድ ወጣ ያለ ነጻና አንዳንዴም ግልጽ ተቃውሞ እየተሰማ በመሆኑ : ማኅበረ ቅዱሳን አባላቱን በተለያየ መስመር እያደራጀ ወደ ዋናው መንበረ ስልጣን (አራት ኪሎ ቤተ መንግስት) ለመግባት ዳዴ በማለት ላይ እንደሆነ በሰፊው ስጋት መኖሩ ሳይታለም የተፈታ ጉዳይ ሆኗል ::

በአሁኑ ሰአት ያለው የቤተ ክህነት አስተዳደርም : ሌላው የኢህዲግ የትግል መሳሪያ መሆኑ የታወቀ ስለሆነ በሁለቱም አቅጣጫ በማህበረ ቅዱሳ ላይ ጣት እየተቀሰረበት ነው ::

ነገር ግን ነገር ግን ነገር ግን

እውነትም ማኅበሩ : ሰዎች እንደሚያስቡት ሆኖ ከተገኘ : ይጠፋል ::

ያ : ሳይሆን ቀርቶ ማኅበሩ እስከ መጨረሻዋ ሰአት ድረስ ዓላማውን ጠብቆ ከተገኘ ግን :
ይህ ስራ ከእግዚአብሔር ነውና ማንም ሊያጠፋው አይቻለውም ::

Anonymous said...

As a member who firmly believe that the missions and goals of MK is true, I am extremely exhausted by the trush and sometimes unchristian comments ill advised people are posting on this blog. I think the owner of the blog is contributing for this to happen.

Unknown said...

Dear all have blessed day:
I know MK as I am still member. I really appreciate the devotion of MK as well as its members to the church and growth of gospel to the world. This is the true and unbiased information according to MY Understanding:
Why MK:
MK is established by university students to serve themselves. And as already said, it is teaching thousands of university students every year. If the church were able to do this by itself, there was no need for MK. But it is MK who is able to take responsibility for this even before the church thoughts about it. MK is the one that designed the teaching resources and is currently giving more than 18 courses for university students. It is MK that is helping the churches in secular knowledge including Civil works, electric, IT, Accounting, projects etc.
Financially MK is financing church scholars, Adbarat and Gedamat and traditional church students.
Notice that there are lots of associations in Addis Ababa which are small but performing same service /make donations to churches and make preachings to country side/ like MK. Some of which I know include Tsirha Tsion, Mahibere Mariam, Mahibre Eyesus, Mahibere Selam, Mahibre Yared, Mahibere Georigs (Hawariat) etc.
MK, Church Culture and Jesus Christ:
MK, as association under church has to teach the church’s teaching and has to respect the culture of the church. If it is possible to say this: MK members as sons and daughters of church know Jesus Christ more than any one (according to my understanding). I am saying this because I learnt about Jesus Christ from them. But I understand MK people are not preaching about Jesus as theologians are preaching.
According to my understanding it is because to keep churches culture and their teaching is most of the time educational rather than declaration. No preaching about Jesus rather the target is making people to live in words of Jesus. (if I express it in good manner). I believe this to be improved somewhat.
Problems that I perceive in MK (according to my understanding):
As member of MK, I am happy to know the problems and I am also to share my executive committee members about the problems that we have.

Unknown said...

Continued From above

According to my understanding there are some problems with us which include:
1. Our Members teaching methodology should be changed in such a way that will attract the people that die of sin. In current situation the teaching is most of the time for strong spiritual people
2. The way that we are expressing Jesus to the people should be changed. To tell the truth our teachers are not calling Jesus alone. We call HIM Jesus Christ or Lord and God Jesus Christ or Christ. And it is known that the name Jesus has powerful by itself and calling by name Jesus is culture of bible, sister orthodox churches and our church in early times. For this we can check the liturgy (kidasie) and kidan prayers. And I remember one person was called “Menafik” because he was saying Jesus repeatedly which I opposed on the time.
3. Usually we are bothering about culture. I am not saying we shouldn’t bother about church culture. I strongly believe the cannon of the church have to be respected but most of the time I feel bad because most members act badly or strongly on culture of the church. To me this is like Ferisawinet. Things have to be exercised according to conditions.
4. Cooperation with other church servants: As everybody is serving God and is serving based on the gifts that he/she has, it is necessary to respect others and work with others in parallel. Everybody cannot have same talent and view but if the goal is one, to preach God to the world and work for the development of the Orthodox Church, let us work together. I heard preachers from MK who don’t want to go with other preachers for service.
MK and Gedlate
As MK is association in the church. It should teach what the church believes. It is religious association so it has to respect the religion. And we are members of the church. I believe in all the dogmas of the church and expect all members to believe in the dogmas of the church.
If there are problems in dogmas it is the synod which has to improve it. If there is any problem in our books, it is responsibility of the synod to check. But I don’t think the synod has moral to do such things. As Tehadisos are always shouting about Gedilate the synod should check if there are some problems.
According to my knowledge MK writers have written for improvement of mistaken beliefs in the church and improving some mistaken ideas in the Gedlate books. To give u example, read the following two books:
1. To check this out read Hamere Tewahedo No 1 (Chapter: Awalede Mesahifit)
2. Kalkidan Benegere Dihenet ( Chapter: Adbaratin Mesalem).
Please read and understand what is written there before giving any comments.
Finalization: According to my understanding, MK is important to the church which anybody should help it for better performance. As an association that has young members, it cannot be free from any mistake. Mk has to imporve some things especially that are related to declaring about Jesus Christ and relations with and approaches to other servants of the church.

God Bless all orthodox members, God give good mind for our opponents and God give us to improve ourself

Anonymous said...

መልስ ለተስፋ፦
ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እየተሰበከ ያለውን ስብከት የሚቃወም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አባል ያለ አይመስለኝም። በጽሑፍህ ላይ በሰፊው የተተነተኑት ማኅበረ ቅዱሳን አንተ እንዳልከው ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳይሰበክ እንቅፋት የሆኑ አይመስለኝም፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ያልተሰበከ ሌላማ ማን ይሰበካል። እውን አንተ እንዳልከው ተሃድሶ ማለት የሕይወት ለውጥ ነው? የሃይማኖት ለውጥ ለማምጣት ካልተፈለገስ አንዳንድ መስመር የሳቱ ሥርዓቶች ለምን አስፈለጉ? እኔ ከአንተ እንዳውቅ፤ ሌሎችም ከመልእክትህ እንዲማሩ እስኪ በሰፊው ተንትነህ የተሃድሶን ሁኔታ አብራራልን። በጽሑፍህ ቤተ ክርስቲያኒቱ በተሃድሶዎች በሚገባ ተወራለች፤ ግን እንደ ማህበረ ቅዱስን መግነን ሳይፈልጉ ውስጥ ውስጡን በወንጌል እየመደምዱ መሆኑን በርካታ ምልክቶች ይታያሉ ፤ማህበረ ቅዱሳን በከንቱ ይደክማል እንጅ የተቀጣጠለውን የተሃድሶ እንቅስቃሴ ማዳፈን አይችልም፤ ይልቁንስ በርካታ የውሸት ጽሑፎች ወደ አደባባይ ወጥተው ከማፈራችን በፊት እርማት ያስፈልጋል፤ ተሃድሶ ማለት የህይወት ለውጥ ማምጣት ማለት ነው እንጂ የሐይማኖት ለውጥ ማለት አይደለም። ብለህ አስፍረኻል። ምናልባት ተሃድሶ ማለት ምን ማለት እንደሆነ በሰፊው ብታብራራልኝ እወዳለሁ። በእኔ በኩል ግን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳይሰበክ የሚጥር ሰው ቢኖር እርሱ የክርስቶስ አይደለም። ማኅበረ ቅዱሳንም በዚህ በኩል ተወቃሽ ይሆናሉ ብዬ አልገምትም። ዘወትር ቅዳሴ በሚቀደስበት ቤተ ክርስቲያን የሚያገለግሉ ሰዎች እንዴት ወንጌል እንዳይስፋፋ እንቅፋት ይሆናሉ? ለልዩነት ሳይሆን ለአንድነት እናስብ። ለማንኛውም ፈቃድህ ከሆነ አሁንም ደግሜ እላለሁ የተሃድሶን ምንነት እና ማንነት በደንብ አብራራልኝ።

YeAwarew said...

Selam all:

It seems to me that most comment writers don’t even bother to read the “Main article” on the top. We are supposed to comment on the topic of the article, aren’t we?

It is kind of boring to see that most are writing comments that are so far away from the “Main Topic”. Totally boring! And one more thing: Didn’t Deje Selam ask us to post all our comments on “MK org” on the Article page - “+++++++ - - - - - - ???? ?? About Mahibere Kidusan”
Why are we arguing about MK org here again ? Boring! At least make it short and to the point.
I miss the good comment writers.

Comment to Deje Selam: can you do something about this ? May be, move the comments from this page on “Mk org” to the comment page above. Thank you.

Going back to the topic,
I was expecting this to happen. Because the so called “Teqlay Bete-kihnet office” members have done this to many in the past. It is sad but what do you expect in this country of ours. That is why “Change” is necessary. And a few who understood that (like Addis Neger) try to bring it about. May God help the Editors of Addis Neger, this is one of the few newspapers that is really good to read (most of the time).

Yiqoyen, May God protect His Church and the true Fathers, Amen!

YeAwarew

tesfa said...

ተሃድሶ ማለት ምን ማለት ነው? ለሚለው ጥያቄ ባጭሩ ለመመለስ እሞክራለሁ
ተሐድሶ ማለት ራስን መገምገም ነውር ወይም ነቀፋ እንዳለብን መፈተሽ እና ነውርና ነቀፋ ቢገኝብን ያንን ነውራችንን ማስወገድ ማለት ነው ነውርን ከሐገር ፤ከቤተ ክርስቲያን ፤ከግለሰብ ፤ከቤተ ሰብ ማስወገድ ማለት ነው።
ነውራችንን እንዴት ማየት እንችላለን ?
ነውራችንን ማየት የምንችለው የግዚአብሔርን ቃል በማጥናት ና እግዚአብሔር እንደተናገረው ብቻ ሳንጨምር ወይም ሳንቀንስ በሕይወታችን ሙሉ መታዘዝ ነው
የግዚአብሔር ቃል የተነገረው ለስዎች ነው ይህም የህይወታችን ዋና ነገር ነው ማንም የፈለገውን ቢናገር የሚለወጥ ነገር የለም እግዚአብሔር በቃሉ የጸና ነው።ታዲያ ተሐድሶ ማለት ወደ እግዚአብሔር ቃል እንመለስ ማለት ነው።ንጹሑን የግዚአብሔር ቃል እንዝራ መቀላቀል የለበንም ነው የሚለው ተሐድሶው።
ምን የተቀላቀለ ነገር አለ? ልትለኝ ትችላለህ ቆጥሬ ልጨርሰው አልችልም አንድ ሁለቱን ግን ልጥቀስልህ
1ኛ ብኪ ድኅነ ዓለም"ዓለም ባንቺ ዳነ" የኪዳን ሰላም ላይ ሁሌ የሚባል ለመሆኑ አለም የዳነው በማን ነው? ይህን ጥያቄ ለጠያቂዬ እተወዋለሁ
2ኛ ደብረ ልባኖስን የተሳለመ ሰባት ትውልድ እምርልሃለሁ
3ኛ ግሸንን የተሳለመ ኃጢያቱ ይሰረይለታል እንደ አርባቀን ህጻንም ይሆናል።
4ኛ ዝቃላን ይተሳለመ አሥር ትውልድ እምርልሃለሁ
5ኛ ክርስቶስ ሰምራን የዘከረ አሥራሁለት ትውልድ ድረስ ይድናል
ይህን የጻፍሁት አንተ የሚገባህን ብቻ ትንሹን ነገር ነው
ደም ሳይፈስ የኃጢአት ሥርዬት የለም የሚለው የግዚአብሔር ቃል ተሽሮ ነውን?ግሸን በመሔድ ኃጢአት የሚሠረየው?ዕብ9፡28
ኃጢአትን ለማስተስረይ የክርስቶስ ደም አይበቃምን? እንዴት እግዚአብሔር ከክርስቶስ ደም ውጭ የኃጢአት ሥርየት አለ ብሎ በሌላ ዘመን ለኢትዮጵያውያን ሌላ ወንጌል ሊሰብክ ቻለ?
ይህ ነው ይተሐድሶዎች ጥያቄ ወደ ወንጌል እንመለስ ነው ትግሉ ህዝባችን በየተራራውና በየበርሃው ኃጢአቱን ለማስተሥረይየሚንከራተተው የክክርስቶስ ደም አላረካው ብሎ ነው?
ጳውሎስ በገላትያ 1፡8 ላይ "ነገር ግን እኛ ብንሆን ውይም ከደምይ መላክ ከስበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌል ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን"ይላል ሐዋርያት የሰበኩት ወንገል የትኛው ነው የኢትዮጵያ ተራራዎንና በርሃወችን ራሳቸውን ወይስ የክርስቶስን አዳንነት ? እንግዲህ ተሓድሶዎች ወደ ሐዋርያት ወንጌል እንመለስ አምልኮታችን ትምህርቶቻችን ይፈተሹ በማለት ጥያቄ አንስተዋል እርግማኑንም የማስወገድ ሥራ እንሥራ እያሉ ነው። ማህበረ ቅዱሳን ደግም ከላይ ይተመለከትነውን ዓይነት ማለቂያ የሌለው ልዩ ወንጌል በስተማር በመርገም ላይ መርገም ይጨምርብናል ትምህትርታችን እና አምልኮታችን በቃሉ እንዲፈተሽ አይፈልግም ወንጌልን ይጠቅሳል ግን እያጣመመ ይተረጉማዋል ።ባጭሩ በተሃድሶዎችና በመህበረ ቅዱሳን መካከል ያለው ልዩነት ይህ ነው ማለት ተሃድሶዎች እንፈተሽ ይላሉ ማህበረ ቅዱሳን አንፈተሽም ይላል ።
እናንተስ ምን ትላላችሁ?

Anonymous said...

ማህበረ ቅዱሳን እኮ በሰንበአት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ ስር የሚገኝ ትንሽ ተቁዋም ነው። ከቅዱስ ሲኖዶስ እኩል እንደትልቅ ነገር መወያያ መሆኑ ይገርመኝኛል። አይጥጥ ዝሆን ለማከል ብላ ከአቅሟ በላይ ውሃ ጥጠጥታ የደረባት አይነት ነገር እኮ ነው። ከአባቶች በላይ ለቤተክርስቲያን እናስባለን የሚልሉ ገና ክርስትናው ያልገባችሁ ማህበር አምላኪ ወጣቶች። እኔ አውቃለሁ እያላችሁ እውር ለእውር ከምትመራሩ አባቶች ሥር ሆናችሁ ክክርስትናን መማሩን ብታስቀድሙ ይሻላል።

Anonymous said...

እግዚአብሔር በቃሉ የጸና ነው።

"...ለሚወድዱኝ፥ ትእዛዜንም ለሚጠብቁ እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ ምሕረትን የማደርግ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና:: Exodus ምዕራፍ 20:6

"...እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፥ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል። 41 ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል፥ ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል። 42 ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ጽዋ ውኃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ፥ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋው አይጠፋበትም።"

Jesus Christ, The Son Of God, Lords of Lord Kings of King, Who is the Master of our church.

Melkamu said...

Blesse you, dear Tewahdo for your clarification.

But I think we don't need to defend our Church bodies and our teachings all the time, because that's the intention of our enemies. Many who post on this blog aren't even Christians. I've tracked one of the frequent posters here, and I have found out that they belong to a non-Christian denomination which is using our own weakness to confuse and weaken us. We should be happy to learn that it is them who are hating our Mahiber and church. It's a good sign! So, let's stop going back to the same old discussion spirit that we used to have some 7 years ago.

Melkamu said...

When the Archangel Michael argued with the devil, they were arguing over the body of Moses. But Michael didn't dare to hand down a judgment against the devil. Instead, Michael said, "May the Lord reprimand you!"

A religious life is the most safe, happy, comfortable, and honorable life that is. We are most apt to speak evil of those persons and things that we know least of. These are our fathers, mothers, brothers and sisters. Please, let's not judge, let's not use foul, unholy words to/with one another.

Our Church leaders are exposed more to temptation by Satan then many of us. Please let's remember, they are the first and desperately wanted victims of the Lucifer – the evil angel. In our eyes, they might have done the most unexpected, horrendous, evil, terrible and awful things, but the Almighty Lord might one day forgive them if they repent and overcome all the temptations of devil. Do you all remember the biography of our own “St. Moses The Ethiopian” who used to be the leader of a gang of thieves, and was ordained a priest in his old age and founded later a monastery ?

In the Eastern Orthodox Churches they sing about our Moses like this:

Troparion (Tone 1)

You made the wilderness your dwelling, O our Father Moses, the Bearer of God; you became an angel in the flesh and a wonderworker. Through fasts, vigils, and prayers, you obtained from God special graces to heal the sick and sanctify the souls of those who come to you with trust. Glory to the one who gave you strength! Glory to the one who crowned you! Glory to the one who, through your intercession, grants healing to all!

FYI: St. Moses is a Patron-Saint of an Orthodox Church in Michigan http://www.firebirdvideos.com/stinnocentchurch.htm

Anonymous said...

To DS let come to the points to what synodes could rady for Tikimit.
To melkamu please do not state the name. betekelhaymanot bileh
To tesfa
Tehadiso is/was the bridge of protestant,True. You and me know that some of member of EOTC start thinking about tehadiso after a time they joined to protestant, example g,d,k, .... and u r on the way. Ke ahiya gr yewalech gider ... temira metach endelu.
Any Mk was/is not compromise with tehadiso, it has big experience that tehadiso is children of protestant.
Ye egiziabeherin kal yenegeruachhun .......eberawuan 13:7-14, "እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፥ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል። matt10:41-42 ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል፥ ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል። ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ጽዋ ውኃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ፥ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋው አይጠፋበትም።" matt12:40-44,egizeabeher be kidusanu lay adro sirawu dinike new,mezimur dawit. Ye tsadik metasebiya lebereket ewu.mezimur111:6 etc.... Ready the correct version of EOTC Bible.
So your stand is thining to increase your tehadiso memebers. Try but you can't. All memebers of Our church know well about tehadiso. So MK was/is standing for true church. EOTC yegehaneb dejoch enqan ayashenifatim, bkirstose eras yetemeseretech silehon.
Tseliyu selebete kirstian andenet.
ke waldiba

tesfa said...

ለጠየቁኝ ሁሉ
"ነቢይን በነቢይ ስም የተቀበለ ጻድቅን በጻድቅ ስም የተቀበለ እኔን ይቀበላል ማንም በደቀ መዝሙር ቀዝቃዛ ጽዋ ውሃ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ እውነት እላችኃለሁ ዋጋው አኡጠፋበትም"ይየሚለው ን ቃል ባለመረዳት የተሳሳተ ትምህርት ለሚያስተምሩ ሁሉ ።ነቢይን በነቢይ ስም ፡ማለት ነቢይ ነው ብሎ ማለት ነው።ጻድቅን ጻድቅ ነው ብሎ ።በደቀ መዝሙር ስም ማለት ፡የጌታ ደቀመዝሙር ነው ብሎ መቀበል ማለት ነው ።ቀዝቃዛ ጽዋ ውሃ የሚያጠጣ ማለት ደግሞ እነርሱ የወንጌል አገልጋዮች ስለሆነ ሀብትና ገንዘብ እንዳይሰበስቡ ተነግራቸዋል ለምንገዳቸው ስንቅ እንካ እንዳይዙ ተምረዋል ታዲያ ለነዚህ የጌታ አገልጋዮች የሚያስፈልጋቸውን ማድረግ እስከ ቀዝቃዛ ጽዋ ውሃ ድረስ የምንሰጠው እርዳታ በረከትን ከጌታ እንደሚያሰጠን የሚናገር ነው ይህ ማለት ለራሳቸው ለደቀመዛሙቱ መስጠት እንጂ በነሱ ስም ለሌላ ሰው መስጠት አይደለም በማቴዎስ ላይ ያለውን ይህን ቃል በማርቆስ ወንጌል ደግሞታል እንዲህ ይላል"የክርስቶስ ስለሆናችሁ በስሜ ጽዋ ውሃ የሚያጠጣችሁ ሁሉ ዋጋው እንዳይጠፋበት እውነት እላችኃለሁ"ማር9፡41ይህ የሚያመለክተው በምድር ላይ ውንገል የሚሰብኩ ደቀመዛሙርትን በጌታ ስም በደቀ ምዝሙርነት ተቀብሎ ማስተናገድን ነው ጳውሎስም በቆላስይስ 3፡17 ላይ በቃል ቢሆን ወይም በሥራ የምታደርጉትን ሁሉ በጌታ በኢየሱስ ስም አድርጉት"ይላል
ታዲያ ህዝባችን የሚያደርገውን ሁሉ በማን ስም ነው እያደረገ ያለው? ከዚህ በፊት አገልግለው ወደጌታ በሄዱ ነቢያት ጻድቃን ስም አይደልምን ? የጻድቅ መተሳቢያ ማለትም ጻድቅ በምድር ላይ እያለ የሰራው ጥሩ ሥራ ማለት ነው ያንን ማሰብ ተገቢ ነውለምሳሌ የጳውሎስ መታሰቢያ የሰበከው ወንንጌል ነው የጊዮርጊስ መታሰቢያ በኢየሱስ መከራን መቀበሉ ነው ይህን ስናስብ እኛም ይህ በረከት እዲኖረን እንነሳሳለን ማለት ነው ፡ከዚህ ውጭ ጠላ በጥመቅ ፤ዳቦ በመጋገር በስማቸው ኃጢአታችንን እናስተሰርያለን ማለት አይደለም
ይህ ትምህርት ድግስ መብላት ያማራቸው ወይም ደሞዛቸውን ማሳደግ ያሰቡ የድሮ ደብተራዎች የፈለሰፉት የሥህተት ትምህርት ነው ከዘጸአት የጠቀስህልኝ ሰው አለህ ቃሉን በደንብ አስተውል"ለሚወዱኝ ትዛዜንም ለሚጠብቁ እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ ምህረትን የማደርግ"ነው የሚለው ልብ በል ትዛዙን ለሚጥብቁ እንጂ ጽድቅን ፍለጋ በየተራራውና በየበርሃው ስለተንከራተን ጠላ ጠምቀን በሞተ ሰው ስም ስላጠጣን አይደለም እዚአብሔር ምህረት የሚያደግልን በዳቦና በጠላ እንዲሁም አፈር ስለደቀደቅን ሳይሆን ትዛዙን ስንጠንብቅና ስንወደው ብቻ ነው።ይህ ቃል ድርሳንና ገድል ከሚያወራው ጋር ምንም አይገናኝም ደግሞም በግዚአብሄር ለሚታመኑ እንጂ ከኛ በፊት በነበሩ ሰዎች ለሚያምኑ አይልም ይልቁንም በሐዲስ ኪዳን ስለ "ስም"እንዲህ ተብሎ ጠጽፋል "መዳንም በሌላ በማንም የለም እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ ስም የለም"የሐዋ 4፡12 ታዲያ ስምህን የጠራ ስምሽን የጠራ የሚለው የክህደት ትምህርት ከሄት መጣ ?መንፈስ ቅዱስ ይህን ለሐዋርያት የተናገረውን ቃል ሽሮታል ማለት ነው? ወግገኔ ለሰዎች የተሰጠው ስም ኢየሱስ የሚለው ነው ለሎች ስሞችን እንድጠራ ይሚያስተምሩ የጌታን ቃል የናቁ ብቻ ናቸው ።ሐዋርያት "የምታደርጉትን ሁሉ በጌታ ቢኢየሱስ ስም አድርጉት "ብለው አስተምረው እያለ የኛ ሰዎች ግን በሌላ ስም እንድናደግ ያጣምሙናል ።እንግዲህ የተሐድሶዎች ጥያቄ ወደዚህ ወደ ሐዋርያት ትምህርት እንመለስ የሚለው ነው

Anonymous said...

ተስፋ፡

የጌታን ቃል ለማስተሃቀር የምታረገው ልፋት የሚገርም ነው፡፡ ጌታ በማቴዎስ ወንጌል ላይ በግልጥ “በደቀመዝሙር ስም” አለ እንጂ “በጌታ ስም ለደቀመዝሙር” አላለም፡፡ በማቴዎስ ወንጌል ላይ “ነቢይን በነቢይ ስም” “ጣድቅን በጣድቅ ስም” የሚቀበል አለ እንጂ “ነቢይን በጌታ ስም የሚቀበል” አላለም፡፡ በግልጥ የቅዱሳንን ስማቸውን አክብሮአል፡፡ በማርቆስ ወንጌል ላይ የተገለጠው ደቀመዛሙርትን በጌታ ስም መቀበልም ሆነ በማቴዎስ ወንጌል ላይ የተገለጡት ቅዱሳንን በቅዱሳን ስም ተቀብሎ፡ በስማቸው ችሮታ ማድረግ፡ ሁለቱም ዋጋ የሚያሰጡ ምግባራት ናቸው፡፡

በግድ ከጌታ ጋር ክርክር ገጥሞ፡ እርሱ ያለውን ለማስተባበል መሞከር፡ ተስፋ መንግሥተ ሰማያት የጨለመባቸው የአጋንንት ምግባር ነው እንጂ የክርስቲያን አደለም፡፡ የተጣፈውን ቁልጭ ያለ ፊደል ማንበብ የምንችል ማገናዘቢያ አእምሮም ያለን በጥምቀትም መንፈስ ቅዱስን ተቀብለን የምናነበውን በመንፈስ ቅዱስ እንድንረዳው የሚያደርግ ፀጋን የተቀበልን ነንና፡ ያንተ አስተርጉዋሚነት አያስፈልገንም፡፡ ምናልባት አላውቅህ ከሆነ- ብዙ ሰዎች አማርኛ ማንበብ ይችላሉ- ያውም ካንተ በተሻለ ሁኔታ፡፡ ለዚያ ነው፡ “በደቀመዝሙር ስም” የሚለውን ቃል ሳንጨማምርና ሳንቀናንስ፡ ሳንጨራርፍና ሳናጠጋጋ፡ የጌታን ቃል ከርሱ በላይ ሆነን ለማረም ሳንሞክርለት እንዳለ የምንቀበለው፡፡

ውሸትህና አጋንንታዊ ትምህርትህ የተጋለጠበት ሌላው ክህደትህ ደሞ- አንተ የተናገርከውን አንተው መልሰህ መንቀፍህ ነው፡፡ ባንተ አባባል መሠረት፡ ማቴዎስ ወንጌልን በደቀመዝሙር ስም ዝክር ማድረግ ነው ብለው ያስተማሩ ካህናት መብላት መጠጣት ስላማራቸው ነውና ያንን ያደረጉት፡ ሁለተኛ አናስተናግዳቸውም ብለን እጃችንን አጣጥፈን እንቀመጥ፡፡ ታድያ ማርቆስ ወንጌል ላይ የተጻፈውን አልተገበርንም ማለት አደለም ወይ? ካህናትን አላበላም አላጠጣም፡ ማቴዎስ ወንጌል ስህተት ነው ብለን ዝም ካልን እንግዲያ ማርቆስ ወንጌል ላይ ያለው አገልጋዮችን መቀበል ደሞ መቼ ሊተገበር ነው? ደሞ ዳቦና ጠላ አያስፈልግም ልትል ዳድቶሃል፡፡ በጣም ትገርማለህ! ካህኑ ውይም ሰባኪው ወይም አገልጋዩ ቤቴ ሲመጣ፡ ማቴዎስ ወንጌል ቀዝቃዛ ውሃ አጠጡ ብቻ ነው የሚለው ብዬ ቀዝቃዛ ውሃ ብቻ አጠጥቼ ዳቦ ወይም እንጀራ ሳላበላው ልደር? ሃሳብህ አገልጋዮችን በርሃብ መግደል ነው? የተራበን ማብላት የሚለው ምግባርስ መቼ ሊተረጎም ነው? ያውም በአገልግሎት ለደከሙ አገልጋዮች?

እናንተ ሰፈር ፓስተሮች ሲመጡ ውስኪና ቢራ ሁሉ ይከፈትላቸዋል አደለም እንዴ? ታድያ ምን ዓይነት ሰይጣናዊ ጭካኔ ነው- ከቀዝቃዛ ውሃ በቀር ሌላ ለካህናት እንዳትሰጡ ብሎ መከራከር? ማብላትና ማጠጣት፡ እንኩዋንስ ለራስ ወገን፡ ለተማረከ የጠላት ወታደር እንኩዋ በችሮታ የሚደረግ ነገር አደለም ወይ?

የስደተኛ ካምፕ እንኩዋ የማያስበውን አረመኔ አስተሳሰብ ይዘህና፡ ካህናት ተርበው እንዲሞቱ እየተመኘህ በጌታ ቃል ለማሳበብ መሞከርህ፡ በላይህ ላይ ያደረው ሰይጣናዊ መንፈስ፡ አውሬ እንዳደረገህ ያሳያል፡፡ ክብር ይግባውና- ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስስ፡ ቀዝቃዛ ውሃን የጠቀሰው፡ ምንም ልፋት የማትጠይቅ ትንሱዋ ችሮታ እርሱዋ በመሆኑዋ፡ እንኩዋንስ ሌላው ትልልቁ ዝግጅትና ችሮታ (ጠላው፡ ዳቦው፡ እንጀራው፡ ወጡ..) ቀርቶ፡ እሱዋ እንኩዋ ዋጋ እንዳላት ለማሳየት የተጠቀመው አባባል እንጂ፡ ላገልጋይ ከውሃ ወጭ ሌላ ሳታበላው በርሃብ ጨርሰው ለማለት አደለም፡፡

ቃሉን በአውሬያዊ መንገድ ላጣመምክበት ንስሃ ግባ! ለማብላት ለማጠጣት የሚስገበገብ ሰው፡ ትልቁ የስስት መንፈስ ላዩ ላይ ስላለ፡ ስለርሱ ሊጸልይና ጋኔኑን ከላዩ ላይ ሊያርቅ ይገባዋል፡፡

አንተን ከያዘህ ከዚህ ዓይነት ስግብግብነትና ጨካኝ አውሬነት ይሰውረን! አሜን!

orthodoxawit said...

እንደ ሳውል ወይስ እንደ ድመት ?

ቃላት ባልረከሱበት ዘመን ነገሥታት ሕዝባቸውን በጥቂት የተግሳጽ አዋጅ ቃላት በሰላም በአንድነት ይመሩ ፣ ሕዝቡም የንጉሥን ቃለ ትዕዛዝ አክብሮ እሺ ብሎ የተበደለም ቅያሜውን ትቶ የበደለም ስለ ክፉ ሥራው ተጸጽቶ ከእኔ ይልቅ ሀገሬ ከእኔ ይልቅ ወንድሜ ብለው በቤተ ክርስቲያን ደጅ ይቅርታ ተጠያይቀው እግዚአብሔርንም በመካከላቸው እየገባ የሚያጣላቸውን ክፉ ክፉ የሚያሳስባቸው ያረቅላቸው ዘንድ ተማጽነው ላልክድህ ላትክደኝ ሙት ሙት ብለው ቃል ኪዳን ተገባብተው በሰላም ይኖር ነበር፡፡ በመቶን ከዛ ባነሱ ዓመታት ውስጥ ነገር ሁሉ የተገላቢጦሽ ሆነና ከሀገር በፊት የእኔ ብሔር (ጎሳ፣ ዘር) ከቤተ ክርስቲያን በፊት የእኔ ሐሳብ የእኔ ጥቅም ይቅደም፣ ከሥራ ይልቅ ወሬን፣ ከስምምነት ይልቅ መነቃቀፍን፣ እኔ ነኝ ልክ እኔን ተቀበሉኝ አልያ ግን የራሴን ወገን ይዤ እነሳለሁ የዛኔ ወደህ ሳይሆን በግድህ ታምናለህ በሚል መንፈስ ለራሳችን እኩይ ተግባር የቅዱሳን አባቶችን ገድል እና ታሪክ አውሪዎች የእውነተኞቹን ነገሥታት ወግ ተራኪዎች ሆነናል፡፡ ታዲያ እንደድሮ እንኳን የአገር መሪ ይቅርና ውሉደ ብርሃን የተዋህዶ ልጆች በጥቂት ቃላት መስማማት ቀርቶ በብዙ ገጾችም ጽፈንም ተናግረንም መግባባት አቅቶናል፡፡ አንዱ አባ መርቆርዮስን ሲነቅፍ ሌላው አባ ጳውሎስን ሲነቅፍ አንድ ግብጾችን ሲነቅፍ ሌላው ሲደግፍ አንዱ ማኅበረ ቅዱሳንን ሲደግፍ አንድ ሲነቅፍ ሌላው ደግሞ ነቃፊውን ሲደግፍ ውይም ሲነቅፍ እንዲሁ መሽቶ ይነጋል፡፡
ከአድዋ ድል በኋላ ጀምሮ አውራን አባት እንደ አቡነ ጴጥሮስ መሪ እንደ ሚኒሊክ ስንል ኖርን፡፡ የክርስትና (የክርስቶስ) ፍቅር ወይም ሀገር ፍቅር የማጣት አይመስለኝም፡፡ ነገር ግን ይህ ፍቅር አቅጣጫውን የሳተ እንደ ሳውል ወይ ድመት ያለ ፍቅር ይመስለኛል፡፡

ነገሬን ልግለጥላችሁ
ሳውል በጠርሴስ የተወለደ በገማልያል እግር አጠገብ ያደገ ሕግ አዋቂ ለእግዚብሔር “ቀናተኛ” የነበረ ሰው ነበር፡፡ ስለ እግዚአብሔር ብሎ ወንዶችንም ሴችንም እያሳረ ወደ ወኅኒ አሳልፎ ይሰጥ ነበር፡፡ በደማስቆ ያሉትንም ታሥረው እንዲቀጡ ያደርግ ነበር፡፡ አንዳንዶቻችን ዛሬ እንደዛ የሆንን ይመስለኛል፡፡ ለእግዚአብሔር እና ለቤተ ክርስቲያን ቀናይ የሆንን እየመሰለን ፣ እግዚአብሔርን እና ቤተ ክርስቲያንን የጠቀምን መስሎን አንዱን ለፍርድ ለማቅረብ አንዱን ለማሰር ስንሞክር ቤተ ክርስቲያን ለማዋረድ ክብርዋን ለመግፈፍ በአደባባይ ካቆሟት ጋር ተስማምተን መብራት ይዘንላቸው የቆምን ጥቂቶች አይደለንም፡፡ በዚህ ስሜት ደግሞ እግዚአብሔርንም አናገኘውም፣ ቤተ ክርስቲያንንም መቼም አንታደጋትም፡፡
ግብረ ሳውል - እግዚብሔር ከእኛ የሚፈልገውን አለማወቅ ነው
ግብረ ሳውል - ፍኖተ ቅዱሳንን አለማወቅ ነው፣
ግብረ ሳውል - እግዚአብሔር በደሙ የመሠረታትን ቤተ ክርስቲያን ሕጓን ሥርዓቷን አለማወቅ ነው
ግብረ ሳውል - እኔ እኔ ፣ የእኔ ሐሳብ ፣ የእኔ አካሔድ፣ የሚያሰኝ ስልጣንን እውቀትን ገንዘብን ዘመድ ወገንን የተመለከተ አካሄድ ነው

ድመት፡- ድመት በተፈጥሮዋ ከነብር ከአንበሳ ወገን ስትሆን ከቤት እንስሳም በይበልጥ የአውሬነት ጠባይ ያላት ናት፡፡ ቤቷን እንጂ ባለቤቷን የማታውቅ ፣ አትንኩኝ ባይ፣ በልታ የምታድረው በራሷ እንጂ በባለቤትዋ ቸርነት የማይመስላት ምስጋና ቢስ ጥፍረት ናት፡፡
ድመት ከሚያስደንቀው ተፈጥሮዋ አንዱ ልጆቿን ከመውደዷ የተነሳ ፍቅርዋን የምትገልጠው በልታቸው ተመልሰው ሆድዋ ውስጥ ሰቀመጡ ነው፡፡ የዛኔ ልቧ ይረካል፡፡ አንዳንድ ጊዜ የእኛም የቤተ ክርስቲያን ፍቅር እንደዚህ ይመስለኛል፡፡ ቤተ ክርስቲያንን እየበላናት ነው የምንወዳት ፡፡ለሀገራችንም ያለን ስሜት እንደዛ ነው እርስ በእርሳችን እንበላላ ሌላው ግን አይንካን እርስ በእርሳችን እንነቃቀፍ ሌላው ግን ቀና ብሎ አይየን ቤተ ክርስቲያን ከባስሊዮስ ወደ ቴዎፍሎስ ወደ ተክለሐይማኖት ወደ መርቄርዮስ ወደ ጸውሎስ ስለተላለፈ ጥቂት እየተበላች በ14ኛው ክፍለ ዘመን ወርቃማው ክፍለ ዘመን እንዳልተባለለት ሁሉ አሁን ዘመንዋ እየጨለመ መጥቷል፡፡ የቤተ ክርስቲያኒቱ መሪዎች አንሶ ሕዝቡም አብሮ ትንሽ ትንሽ ሲበላት /ስንበላት/ ቆይተናል፡፡ ማዕደ ብዙ ስንዱ እመቤት ሆነችና አላልቅ አለችን እንጂ በእኛ አያያዝማ እንደ ቱርክ ቤተ ክርስቲያን ደብዛዋን አጥፍተናት ነበር፡፡

ውድ ደጀሰላማዊያን
ሳውላዊ ድመቶች ሆነናል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ጥሪዋ ሌላ ሆኖ ሳለ እኛ በድንግዝግዝ እየሄድን ምእመናንዋን ለአሕዛብ እና ለመናፍቃን ወኅኒ አሳልፈን እየሰጠን የእኔ የእኔ በሚል ስሜት እኔ ከምሸነፍ ቤተ ከርስቲያን ሥርዓትዋ ይሸነፍ ብለን ዘረኛ ፣ ስደተኛ፣ ገለልተኛ፣ በሚል ስያሜ ብዙ ቦታ ከፋፍለናታል፡፡ የእምነት ፍሬ የሆኑትን ልጆችዋን፣ ሀብትዋን፣ ንብረትዋን በጉልበት በኃይል በማንአለብኝነት በልተነውል፡፡ በእንስሳዊ ጠባይ ተነስተን በዓለም አደባባይ እርቃንዋን አቁመን ግጠን በልተናታል፡ለዚህ ሁሉ ተጠያቂ እነ አባ እገሌ ብች አይድሉም ሁላችንም ነን ምክንያቱም እነ አባ እገሌ ተከታይ አጫፋሪ ካልገኙ እንደልባቸው አሆኑማ..

ስለዚህ…
ወደ መፍትሄ ሐሳብ እንሂድ ምን ይሻላል ምን እናድርግ እንበል ሳውላዊ አስተሳሰብን አስውግደን ሕሊናችንን ወደ አንድነት ወደ ስምምነት የሚያመጣን ሐሳቡ እንዲያፈልቅ እናድርግ ኮብጦች የሉም ያለነው እኛ ነን ማኅበረ ቅዱሳን እንድሆነ የራሱ አንደበት አለው መናገር ይችላል እኛም በሳይበር ፎከራ ሳይሆን በትክክለኛው መንገድ የማኅበሩን ተወካዮች መጠየቅ እንችላለን ፡፡ ምዕመናን ማኅበረ ቅዱሳንን አይደልም ቅዱስ ሲኖዶስን (ጠቅላይ ቤተ ክህነትን) እንኳን ስለ አሠራሩ መጠየቅ ፣ አስተያየት መስጠት ፣ የተበላሸ ካለ ኢዲስተካከል ማድረግ እንዲሚችል በቃለ ዓዋዲው በግልጥ ተቀምጧል፡፡ሁሉም ግን በሥርዓት ሊሆን ይገባል፡፡ አባቶች ውይም እነገሌ ስላጠፉ እኛም አብረን እናውድም የሚል ምክንይተ ቢስ አካ,ሄድ ሊኖረን አይገባም ነፍሳችን የሚትጠየቀው ምንተ ገበርኪ እንጂ ምን ሠሩ አይደለም ይህ ሲባል ግን እስመ ቅንዐተ ቤትከ በልአኒ እንዳለው ቅዱስ ዳዊት ለእግዚአብሔር ቤት ቅናት የሚደለግ ሁሉ በመንፈሳዊ ድፍረት እና እውነትን እውነት ለማለት በሚያስችን ውኔ መሆን አለበት፡፡ብእራችንም ለመጻፍ መፋጠን ያለብት ይህንኑ ነው ለመስማማት ተስማምተን ከወቀሳ በፉት ንግግርን ከነቀፋ በፊት መጠየቅን እናስቀድም

ለደጀ ሰላም
1.የመፍትሔ ሐሳብ በድንብ እንድናብላላው በነጥብ በነጥብ ተዘርዘሮ ቢቀመጠልን
2.ከየት እንጀምር የሚለው ሐሳብ በድንብ ብንወያይበት፡፡
የሚልነው የእኔ ሐሳብ ካጠፋሁ ለመታረም ዝግጁ ነኝ

እግዚብሔር እንደ ሐናንያን ያለ ሐዋርያ ልኮ የዓይናችንን ክርፊት ያነሳልን ዘንድ ልንጸልይ ይገባል

ሰላማዊት ሰላም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሰላምን ትስጠን

ሰናይ said...

ውድ ኦርቶዶክሳዊት፤

ቃለ-ህይወት ያሰማልን! ወደ ህሊናችን ተመልሰን እንድናስተውል የሚረዳን ትምህርት ሰጥተውናል።ፀጋዎትን ያብዛሎት።

Anonymous said...

ato heyleslasiy kemekses kemekases atastarkm wegen zemed kemalet yetebetenutn begoch mesebseb ayshalm esty patryarku altegeletelachwm ena ngeruachew lb ystachu

Mehari Meharene said...

Dear Orthodoxawit,
I think you are tuning the discussion to a very good direction.

Deje-Selam: It is time, for you the editor,to guide on the specific topic. Because there are many issues which are being pointed out.

"Eyerusalemin Basebin Gize alekesign" tebilo endetesafe

Let us pray for us, for our church and for our unity. A single "abune zebesemayat" + " Selam leki" has a lot to do if we do it truely.

One thins is for sure "Betekiristiyanin Yemitebik Ayankelafam"
Selame Egziabher Ayileyegn Amen!

brx said...

Befor all i would like to extend my greeting for all fellow country men specially eotc members and Dejeselam editors.

i need to comment the following.

Befor posting all idea please edit those unessesary writings which writes by peoplese of ethiopia and menafekan,because their main motive is to insert bad words and heat to the people.we know from their main idea posted.

The other is that those people who raise unwanted question about mahiberekidusan, Because they know what mk is doing and going to do.

Mk is stablished in belate i know that i was there and done a very good thiings for our church unity and development and also uncovered those people who work underground to destroy the church such as Tehadeso stablished by Dn.Geremew who mislead a lot of inosent peoples and convert them into Protestant.so mk makes these type of people worried for their existance and remove them from our church.that is why the dog is barking.

Finalil we must underestand that those people who write negatively about mk is a messenger of menafekan and the enemy of the church.

GOD bless ethiopia and our church.

Anonymous said...

እራስክን፡ተስፋ፡እያልክ፡ፀረ-ተዋህዶ፡የሆነውን፡
"ተሃድሶ"=ፕሮቴስታንቲስምን፡በተዋህዶ፡ውይ
ይት፡መሃል፡ገብተህ፡የምናውቀውን፡ፀረ-ማርያም፤ስብከት፡ምናልባትም፡አንተ፡ሳትወለ
ድ፡ከመጀመርያዎቹ፡የዚህ፡ጥፋት፡አምጪዎች፡
ከሁኑት፡ነጮች፡ሰምተነው፡ነበር።ባገራቸው፡ክር
ስትናን፡ደርምሰው፡በየክርስቲያኑ፡አገር፡እየሄዱ፡
ጥንታዊ፡ክርስትናን፡በማፍረስ፡ለጂሃዲትስቶች፡
በር፡ከፋች፡መርዝን፡በደጊቱ፡አገራችን፡ኢትዮጵ
ያም፡ይኸው፡ከፋፋዮችን፡በየቀለሙ፡ተክለውብን፡
ሄዱ።

በማህበረ፡ቅዱሳን፡ላይ፡እንዲህ፡የምትዘምቱት፡እ
ንዳሞራ፡ልትጠልፏቸው፡የዘመታችሁባቸውን፡የ
ተዋህዶ፡ልጆች፡እየመነጠቀ፡ካፋችሁ፡በማስጣል፡
በተውህዶ፡ስላጸናቸውና፡በዚህምና፡በሌላም፡በኩ
ል፡ለጥፋት፡እቅዳችሁ፡ታላቅ፡እንቅፋት፡ስለሆነ
ባችሁ፡ነው!!!

በነገራችን፡ላይ፡የናንተን"እየሱሳውያን"ፀረ-እየሱስ፡ክርስቶስ፡ሥነ፤ምግባር፡በአሜሪካና፡በአው
ሮጳ፡እንዲሁም፡በገቡባቸው፡ሌሎችም፡አገሮች፡በ
ደንብ፡ተስተውሏል!ተዋህዶ-ኢትዮጵያን፡ለቀቅ፡
አድርጋችሁ፡ጂሃዲስቶችን፡ታገሉ።ለተዋህዶ፡ልጆ
ች፡እናንተም፡ሆናችሁ፡ፈጣሪያችሁ፡ሉተር፡ስለ፡
መድኃኔ፡ዓለም፡ክርስቶስ፡እንኳን፡"ማስተማር"
ይቅርና፣ስሙንም፡በኛ፡ዘንድ፡ልትጠሩት፡ገና፡ብ
ቃትም፡የላችሁ!ይልቅስ፡ሉተር፡አገር፡ሄዳችሁ፡
ስንቶች፡"ቤተ፡ክርስቲያናት"እንደተዘጉና፡የፀረ-ክርስትና፡በር፡ተከፍቶ፡ለሌሎች፡ነጣቂ፡አሞራዎ
ች፡ሥንቶች፡ወደቁ?!ባይሆን፡እዚያ፡ሂዳችሁ፡ብ
ታለቅሱ፡ምናልባት፡"አዛኝ"ታገኙ፡ይሆናል!

ለመደምደም፡ያክል፤በዚህ፡ጦማር፡የተጀመረው፡
ውይይት፡የተዋህዶ፡የወሥጥ፡ጉዳይና፡እናንተን፡
አይመለከታችሁም!ባልጦማሩም፡መድረኩን፡አ
ስከብርልን!

በማጅራት፡መቺዎች፡የተደፈረችውን፡ቤተ፡ክርስ
ቲያናችንን፡ከአውሬው፡መንጋጋ፡ለማዳን፡የምናደ
ርገው፡በተገቢ፡አረስቶች፡ላይ፡የተመረኮዘ፡ውይይ
ትና፤የጋራ፡ጥረት፡ይከበር!

ከአርዕስቱና፡ከተዋህዶ፡ውጭ፡የሚቀርቡትን፡ማን
ኛቸውንም፡ዋግጋየለሽ፡ትችቶች፡አስወግድልን።

በእንተ፡እግዚእትነ፡ማርያም፡መሃረነ፡ክርስቶስ!
አጽራረ-ተዋህዶን፡ከመሃከላችን፡ታስወግድልን፡
ዘንድ፡በቀናተኛ፡አገልጋዮችህ፡በሙሴ፣በእያሱና፡
በካሌብ፡ወልደ፡ዮፎኒ፡ሥም፣ጥቃት፡የደረሰብን፤
የአገልጋይህ፡የጻድቁ፡አባ፡ተክለ፡ሃይማኖት፡ልጆ
ች፡እንለምንሃለን!!

በተውህዶ-ኢትዮጵያ፡ላይ፡የተለኮሰው፡እሳት፡
ለኛ፡የድኅነት፣ለጥፋት፡ርኩሰት፡የውድመት፡እ
ንዲሆን፡አድርግልን!
አሜን፡፡

ዘደብረ፡ሊባኖስ፡ነኝ።

tesfa said...

ዘደብረ ሊባኖስ የምትጽፈው ጽሑፍ ኢትዮጵያዊነት የሚል ይዘት ያለው ነው ኢትዮጵያዊ ስሜትህን አከብረዋለህ እኔም ካንተ የባሰ ስሜት አለኝ ነገር ግን የዘለዓለም ሕይወትን የምናገኘው በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን እንጂ በኢትዮጵያዊነታችን አይደለም እኛ እያወራን ያለነው ስለዘልለዓለም ሕይወት ነው ባህላችንን ማክበር አለብን ማለት ባህላችንን እንደ ኢትዮጵያ ሃይማኖታችንን እንደ መጽሐፍ ቅዱስ መያዝ ነው ያለብን የተክለ ሃይማኖት ልጆች ያልሃቸው እነማንን ነው የግዚአብሔር ቃል ግን "አብርሃም አባት አለን በማለት የምታመልጡ አይምሰላችሁ"ማቴ3፡5 ይላል በክርስቶስ ስም በማመናችን ደግሞ የግዚአብሐር ልጆች ሆነናል
ያንተ ሙግት ደግሞ የተከለ ሃይማኖት ልጆች እንሁን የሚል ነው
ችግር ምንድን ነው? ኢየሱስ ክርስቶስ በኢትዮጵያ ቢሰበክ አንተን የሚያሰጋህ ምንድንር ነው? እኔ እንደምገምተው ኢየሱስ ክርስቶስ የኢትዮጵያ ሕዝብ አባት ከሆነ የተክለ ሃይማኖት አባትነት ጥያቄ ውስጥ ይገባል ለዚህ ነው ወንጌል ን አጥብቀህ የተቃወምኸው
እስኪ ስጋትህን በሚገባ ግለጥልኝ።

Anonymous said...

እራስክን፡"ተስፋ፡"እያልክ፡ለምትጽፈውና፡በተ
መሳሳይ፡መልክ፡ተዋህዶ፡ኦርቶዶክስን፡ለምትገ
ዳደሯት፡ሁሉ፡-
አቶ፡"ተስፋ፡አንብበህ፡ለመናገርና፡ለመጻፍ፡ሞ
ክር።ያልተባለውን፡ተብሏል፡ብለህ፡የምትከራከ
ረው፡ከትዋህዶ፡ጋር፡ብቻ፡ሳይሆን፣ተዋህዶን፡በ
ደሙ፡ከፈጠራት፡እግዚእነ፡እየሱስ፡ክርስቶስ፡
ጋር፡ነው!

እስቲ፡የሚከተለውን፡ደግመህ፡አንብበው።ተዋህዶ-ኢትዮጵያ፡ሥሯና፡መሠረቷ፡መድኃኔ፡ዓልም፡
ክርስቶስ፡ስለሆነና፣ሓዋርያት፡አባቶቻችንን፡እን
ድናስባቸው፣ህጉ፣ቃሉና፡ትእዛዙም፡ስለሆነ፣ለእኛ፡
ይህ፡የእምነታችን፡መሠረት፡ነው።

«በነገራችን፡ላይ፡የናንተን"እየሱሳውያን"ፀረ-እየሱስ፡ክርስቶስ፡ሥነ፤ምግባር፡በአሜሪካና፡በአው
ሮጳ፡እንዲሁም፡በገቡባቸው፡ሌሎችም፡አገሮች፡በ
ደንብ፡ተስተውሏል!ተዋህዶ-ኢትዮጵያን፡ለቀቅ፡
አድርጋችሁ፡ጂሃዲስቶችን፡ታገሉ።ለተዋህዶ፡ልጆ
ች፡እናንተም፡ሆናችሁ፡ፈጣሪያችሁ፡ሉተር፡ስለ፡
መድኃኔ፡ዓለም፡ክርስቶስ፡እንኳን፡"ማስተማር"
ይቅርና፣ስሙንም፡በኛ፡ዘንድ፡ልትጠሩት፡ገና፡ብ
ቃትም፡የላችሁ!ይልቅስ፡ሉተር፡አገር፡ሄዳችሁ፡
ስንቶች፡"ቤተ፡ክርስቲያናት"እንደተዘጉና፡የፀረ-ክርስትና፡በር፡ተከፍቶ፡ለሌሎች፡ነጣቂ፡አሞራዎ
ች፡ሥንቶች፡ወደቁ?!ባይሆን፡እዚያ፡ሂዳችሁ፡ብ
ታለቅሱ፡ምናልባት፡"አዛኝ"ታገኙ፡ይሆናል»
ትንግዲህ፡ንሥሐ፡ገብተህ፡ወደ፡አያትና፡ቅድመ፡
አያቶችህ፡ተዋህዶ፡ኦርቶዶክስ፡ሃይማኖት፡ተመለስ፡፡
ይህ፡ላንተ፡ብቻ፡ሳይሆን፡ለፀረ-ማርያሞች፡የተለገሰ፡
ምንፈሳዊ፡ምክር፡ነው።

መድኃኔ፡ዓለም፡ክርስቶስ፡ተዋህዶን፡በደሙ፡ስ
ለዋጃትና፡ስሙ፡ዘወትር፡ስለሚጠራባት፣እርሱ፡በ
ስሙ፡በማሳበብ፡"ክርስቶስ፣ክርስቶስ"እያሉ፡ከሚ
ጮሁ፡የጊዜው፡ፍፃሜ፡ምልክት፡ከሆኑት፡የአውሬ
ው፡ነጣቂ፡አሞራዎች፡ይጠብቃታል!

ይህ፡"ውይይት፡"ከጦማሩ፡የመወያያ፡አርዕስቶች፡
ውጪ፡ስለሆነ፡በኔ፡በኩል፡ይህ፡የመጨረሻ፡ዘገባ፡ነው።

የተዋህዶ፡ልጆች፡በራሳችን፡የአስተዳደር፡ችግር፡
ስለምንወያይ፡ባለጦማሩ፡ይህን፡በዚህ፡እንዲገድ
ብልን፡እንጠይቃለን።

የአቡነ፡ተክለ፡ሃይማኖት፡አምላክ፡ተዋህዶ-ኢትዮጵያን፡ከጥፋት፡ርኩሰት፡ጠብቃት!

ዘደብረ፡ሊባኖስ፡ነኝ።

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)