July 29, 2009

‘‘ለሀገር ፍቅር ሬዲዮ" አዘጋጅ ለአቶ ንጉሤ የተሰጠ መጠነኛ አስተያየት

ዳሳሽ ⁄ዘፍኖተ አበው⁄
አቶ ንጉሤ
መቼም አንተ አምላክህ የላይኛው ሳይሆን ዓለምን ይገዛል ተብሎ የተነገረው የሰው ልጆች ጠላት ገንዘብ ነው። ለገንዘብና ለእግዚአብሔር በአንድ ላይ መገዛት ስለማይቻል አንዱን መምረጥ ግድ ነው።
አንተ ደግሞ ምርጫህን አስተካክለሃል ፈጣሪህን ክደህ ገንዘብን አምላኬ ፈጣሪዬ ጌታዬ ብለሃል። ያዝልቅልህ ካዘለቀህ። ለመሆኑ ንጉሤ ቤተክርስቲያኒቱን ለማወክ ከማፍያዎቹ ጋር የተስማማኸው በስንት ዶላር ነው? ማለት የተሻለ የሚከፍልህ ካገኘህ ፊትህን ስለምታዞር ለማንኛውም እወቀው ብለን ነው? የፖትሪያርኩ ወገኖች ይህን ያህል ከፍለውኛል የተሻለ ከተገኘ በጨረታው አልገደድም የሚል ማስታወቂያ ብትሰራ ያተርፍሃል ብለን እናስሳለን።

አቶ ንጉሜ ኘሮግራምህ ፖትሪያርኩን የሚጎንጥ አንደሆነ እመለከታለሁ። ለመሆኑ ይህን የምታደርገው ሆን ብለህ ነው ወይስ ሳታውቀው። አንድ ነገር ላስታውስህ በ7⁄19⁄09 የተሰራውን የዕለተ ሰንበት ዝግጅትህን አድምጬዋለሁ። በአንተም በዚያ ጨዋ እንግዳህ ⁄ጨዋ ስንለው ደስ ሊለው ይችላል። ጨዋ ማለት ያልተማረ ደንቆሮ… ነው⁄ ዝግጅት እጅግ ተደንቀናል። ለማንኛውም ከአንተ ልጀምር።
ሲኖዶሳችንን በሁለት ለመክፈል ሞክረሃል1. የቤተ ክርስቲያን ትምህርት እውቀታቸው የተመሰከረላቸው የጎጃም የጎንደር የቅኔ የዜማና የመጻሕፍተ ብሉያት ወሐዲሳት ትርጓሜ ምስጢር የገባቸው እነዋሸራ… መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲዎች ብቃታቸውን የመሰከሩላቸው የዕለት ዕራታቸውን ከውሻ ጋር ታግለው ያገኙ የነበሩ፣በብትውናቸው የሚታወቁ፣ ንጽሕናቸው የተመሰከረላቸው
2. በዘመድ በጓደኛ፣ በብርና በወርቅ ምልጃ በብልጣብልጥነት ሰርገው የገቡ ከገዳም ኑሮ የፈረንጅ አገሩ በልጦባቸው ሕዝባቸውንም እርግፍ አድርገው ትተው። የየቀኑን የዌስተርን ቴሌቪዥን ሳፖኘራ ሲመለከቱ ቆይተው ዶላር ጭነው አጋጣሚ ሲያገኙ ወደ ናቋት አገር ገብተው የተሾሙ ብለሃል።
ከዚያም ከውጭ የገቡትን ኮንነህ ሲኖዶሱ መንፈሳዊ እንዳይሆን አደረጉት ብለሃል። ለነገሩ ይሄ ሁሉ ሐተታ አንድ ሰው ለመሳደብ መሆኑን ኋላ ላይ ከምትናገረው መረዳት ይቻላል። ነገር ግን ሳታውቀው ሐተታህ ከአቡነ ጳውሎስ ጋር ያፋጥጥሃል። ለመሆኑ ከአንደኛውና ከሁለተኛው ቅዱስ ፖትሪያሪኩ የትኛውን ቦታ ሰጠሃቸው። ባህታዊ ሊቅ ⁄የዋሸራ የትርጓሜ የቅኔ ሊቅ⁄ ንጽሕናቸው የተመሰከረላቸው …አልካቸው? ወይስ ፈረንጅ አገር ከርመው ሶፓኘራ ሲመለከቱ ቆይተው ዶላር ጭነው ድንገት ዘው ካሉት መደብካቸው… መልሱን ለአንተና ለአንባቢዎቻችን ትቸዋለሁ። ለማንኛውም ፖትሪያርኩ ይሄ የችግር ቀን ሲያልፍ ጎንጠኸኛል ብለው ስለሚነሱብህ ከአሁኑ ቁርጥህን እወቀው። አንተ እንደው አታፍር የተነሱብህ ቀን ደግሞ ‘‘አባ ዲያብሎስ‘‘ ስትል እንሰማህ ይሆናል።
በሌላ በኩል ጳጳሳቱን ለመሳደብ ብለህ ዶላር ጭነው ሄደው ተሾሙ ብለሃል። ይኸም ፖትሪያርኩ ዶላር ጭኖ የሄደን ይቀበላሉ በጉቦ ይሾማሉ ያሰኝብሃል። ለምን አንድ ጊዜ ብቻ አስበህ ትጽፋለህ ..ሁለት ጊዜ አስበህ ብትዘጋጅ ይሻልሃል። ድንቄም ጋዜጠኛ አንተ ጋዜጠኛ ሳይሆን የመንደር መርፌ ወጊ ብትሆን ይሻልህ ነበር። እንጥል ቆራጩ ሁሉ በሰለጠነበት ዘመን ያገኘኸውን ትናገራለህ። የሚሰማህ ታዝቦህ ታዝቦህ እንደኩፍኝ ወጥቶለታል። ያንተን ነገር ⁄መጨረሻ⁄ ፈጣሪ ያሳየን ብሎ ትቶታል።
ሌላው ንጉሴ ዶ⁄ር ተብዬ ባልደረባህ ስለማኅበረ ቅዳሳን ያቀረበውን ሐተታ ⁄ጥናት⁄ ሰምቼ ሆዴ እስኪቆስል ስቄያለሁ። ለመሆኑ ዶክተሩ Drive through ነው ወይስ…። መጀመሪያ የቤተክርስቲያን ቃላት እንዲያጠና መዝገበ ቃላት ብትሰጠው። አቡነ ቀውስጦስ እላለሁ ብሎ አቡነ ቀውጢዎስ ሲል ስሰማው አሳፋሪ ነው። ጥናቱን አጥንቼ ቀርቤያለሁ ብሎ ቀርቦ አስር ጊዜ ሲታረም ለሰማ የማንነው ደፋር ያሰኛል። በዚያ ላይ ስለማኅበረ ቅዳሳን ያቀረበው ጥናት ላይ አንዳንድ ነገሮች ልጠቁምልህ፤
• በመጀመሪያ ደረጃ ጥናቱን ለማጥናት መረጃ አድርገህ ያቀረብከው Google የሚለውን ሳይት ነው። Google በየት ሀገር ነው ለጥናት መረጃ የሚሆነው። ያገኘ ሁሉ በሚጽፍበት ማንም ተነስቶ የወረወረውን ሁሉ አነሱም እንዲህ ብሏል ተብሎ የሚቀርብበት የአስተያየት ጥርቅም ውስጥ ገብተህ መዋኘትህ ያሳዝናል። Google Christ ክርስቶስ ብትለው። ክርስቲያኖች ያሉትንም Anti C hristየሰነዘሩትንም ሁሉ ደባልቆ ያቀርብልሃል። መለየት የአንባቢው ፈንታ ነው። አልያ ጥሩ መረጃ ታማኝ ምንጭ መፈለግ ይገባል። ክርስቶስ ሲባል የሁሉንም ሐሳብ ይዞ ቀርቦ እንደሚናገር አላዋቂ አጥኚ ሆነሃል። Google Ethiopia ብትለው የኢትዮጵያን በጎ ጎን የተጻፈለትንም እነ Oxford famine ረሃብ ብለው ሲተረጉሙ ምሳሌ ያደረጉበትንም ያቀርብልሃል። እንዳንተ ያላ አላዋቂ አጥኚ ያገኘው ዕለት ኢትዮጵያ ማለት ረሃብ እንደሆነ ከGoogle አግኝቻለሁ ሊለን ነው ማለት ነው።

ስለ ማኅበረ ቅዳሳን Google ከምትል የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያንን ራሷን ተቋሟን ጠይቃት። አንተ እንዳልከው ቤተ ክርስቲያኒቱ የማታውቀው ማኅበር አይደለም። የሲኖዶስ አባላት የፈረሙበት ደንብ ያለው ሕጋዊ እውቅና ያለው ማኅበር ነው። ይህንን ቤተ ክርስቲያኒቱ ራሷ ትነግርሃለች።
• በሌላ በኩል ማኅበረ ቅዱሳን ራሱን ካደራጀ በኋላ ‘‘ከቤተ ክርስቲያናችን ሱበካ ጉባኤ ጋር ራሱን እንደለጠፈ ይናገራል።‘‘ ብለሃል። ማኅበረ ቅዳሳን በጠቅላይ ቤተ ክህነት ደረጃ በሰንበት ት⁄ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሥር የሚንቀሳቀስ ማኅበር ነው እንጂ በሰበካ ጉባኤ መምሪያ ሥር አይደለም። አባባልህ በራሱ በጣም ግልጽ ያልሆነና የተምታታ መሆኑን የቤተ ክርስቲያን ልጆች የሆኑ ሁሉ ይረዱታል።
• ከቤተ ክርስቲያናችን ሰበካ ጉባኤ ጋር ራሱን እንደለጠፈ ስትል ከየትኛው ሰበካ ጉባኤ ከአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ወይስ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ደረጃ ካለው የሰበካ ጉባኤ መምሪያ? ይኸን እንኳን መለየት የማትችል ደካማ ቢጤ ነህ። አባላት በአባልነት የአጥቢያ ሰበካ ጉባኤ አባላት ናቸው። ይኸንን ማንም አይከለክላቸውም። ማኅበሩ በማኅበርነት ግን የሰንበት ት⁄ቤቶች ማ⁄መምሪያ አካል ነው። እስኪ ይሄንን እንኳን ለማጥናት ሞክር አጥንቻለሁ ከማለትህ በፊት።
• አቡነ ቴዎፍሎስን ለማስገደል የሞከሩ ናቸው የሚል ቅብጥርጥር ካወራህ በኋላ በተለይም የስብከት ጉባኤው ለመበረዝ የተነሱ ናቸው ብለሃል። የትኛውን የስብከት ጉባኤ? የስብከተ ወንጌል እንቅስቃሴውን ማለትህ ነው? የሰበካ ጉባኤያትን ማለትህ ነው? አማርኛህ ዲቃላ መነሻና መድረሻ የሌለው አፍንጫና ዓይን የሌለው ስለሆነ ግራ ተጋብተህ ግራ ታጋባለህ። ይቅር ይበልህ ፈጣሪ። ማኅበረ ቅዱሳን ስብከተ ወንጌል አስፋፋ እንጂ አልበረዘም ይኸንን የቀመሱት ይመሰክሩል። በየኮሌጅና ዩኒቨርሲቲው ያሉ የማኅበሩ ፍሬዎች በመላው ዓለም ያሉ አባላቱ በአገልግሎቱ የተጠቀሙ ምእመናን ሁሉ ይንገሩህ። ሲገባህ አይደል ለነገሩ።
ለማንኛውም ጥናትህ በሙሉ ውሸት ነው
1. ቤተ ክርስቲያን አታውቃቸውም ሕጋዊ አይደሉም ብለሃል ፤ ውሸት
2. ከሰበካ ጉባኤ እንደተለጠፉ ይናገራሉ ብለሃል፤ በሰ⁄ት⁄ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሥር ነው ማኅበሩ ስለዚህ ውሸት
3. ስብከት ጉባኤውን ለመበረዝ ያልከውም አማርኛውን ላቃናልህና ስብከቱ ወንጌሉን ለመበረዝ ቢባል እንኳን ውሸት
4. አቡነ “ቀውጢዎስን” ⁄ይታረምና አቡነ ቀውስጦስን⁄ ተሳደቡ ብለሃል። ሊቀጳጳሱ ያወጡትን መጽሐፍ ያከፋፍል የነበረ ማኅበረ ቅዱሳን ነው። በዋሽንግተን ዲሲ የተዘጋጀውን ኤግዚቤሽን ⁄የማኅበረ ቅዱሳን⁄ ባርከው የከፈቱለት እርሳቸው ናቸው። ማኅበረ ቅዱሳንና አቡነ ቀውስጦስ ተጣልተውም አያውቁም መቼም አይጣሉም፤ ያጣላሃቸው አንተ ነህ፤ ይህም ፈጠራህ ውሸት ነው።
ለማንኛውም ዶ⁄ር በላይ ፊደል ተማር፣ ታሪክ አጥና። በቤተ ክርስቲያን አጠገብ እንዳላለፍክ ያስታውቃል ከቤተ ክርስቲያን ትንሽ ለማወቅ ሞክር ክርስቲያን ትሆን…ባላየ አንደበትህ ትችት አይቅናህ እላለሁ። እናንተም ቀጥሉበት።
እኔም እቀጥላለሁ ያገናኘን
Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)