July 28, 2009

እስከ ጥቅምት ቅ/ሲኖዶስ ስብሰባ ምን እንሥራ?

(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 28/2009)

ያለፈው የቅ/ሲኖዶስ ስብሰባ እንዳይሆን ሆኖ ከተበተነና ለጥቅምት ካደረ ወዲህ አጀንዳው መቀዝቀዝ የጀመረ ይመስላል። አንዳንዶች ተስፋ በመቁረጥ፣ አባቶች ላይም ጥርጣሬያቸውን በማስፋት እንዲያውም የሃይማኖቱን ነገር ችላ እስከማለት ደርሰዋል ይባላል። የማፊያው ቡድን ብቻ የያዘውን ይዞ “ጥቅምት እንዳትመጣ ባይጸልዪም” ያኔም ቢሆን ጥቅሙን ሳያስነካ፣ ወንበሩን ሳያስደፍር፣ ዝርፊያውን ለመቀጠል ቀንተሌት እየሠራ ነው። ሕብረትም አለው። ሕብረት የሌለውና አሰባሳቢ ያጣው ለቤተ ክርስቲያን የሚያስበው ወገን ነው። ከዚያውም ቢሆን አንዳንዱ “የአባቶችን ገመና አትግለጡ” እያለ ስለ ማፊያው ቡድን እንዳይወራ በጥቅሳጥቅስ ያስፈራራል። ሌላው ደግሞ እኔን ካልነኩኝ እግዜር በፈቀደው ቀን ይፍታው ብሎ መሽጓል። አንዳንዱ ደግሙ ሲያመቸው ከመዘመርና “ሆ” ከማለት ውጪ ነገሩንም ከመጀመሪያው አልሰማውም። እና ሁላችንም እንዲህ ቁጭ ብለን ጥቅምት ትድረስ?

ደጀ ሰላም አንዳንድ የመፍትሔ ሐሳቦች እንዲሰጡ ስትጋብዝ ከዚህ በፊት በወጡ በሌሎች ጉዳዮች ላይ የሞቀ ውይይትና ምልልስ የያዛችሁትን ደጀ ሰላማውያንም “ያንን ገታ አድርጋችሁ፣ ሌላ ጊዜ እንመለስበታለንንና፣ ወደዚህኛው ኑ” በማለት ነው።
የውይይት ነጥቦች:-
1. እስከ ጥቅምት አባቶቻችንን እያጽናናን፣ አይዟችሁ እያልን እናበርታቸው፣ ተስፋ አትቁረጡ እንበላቸው፣
2. ለጥቅምቱ ስብሰባ ምእመናን እንዲያስቡበት፣ እንዲጸልዩበት መረጃውን እናድርስ፤ በተለይም ለሰ/ት/ቤት ወጣቶች ስለ ነገሩ እናስረዳቸው፣
3. በመንግስት በኩል ላሉ ሰዎች ጉዳዩ የእምነት ጉዳይ እንጂ የነርሱን “ወንበርና ሥልጣን” ፍለጋ እሽቅድምድም ላይ እንዳልሆንን እንግለጽላቸው። እንደከዚህ በፊቱ “ከወያኔ ጋር አልሰራም” በማለት ምንም የሚለወጥ ነገር አይመጣም፤
4. እስቲ እናንተ ደግሞ ጨምሩበት
ማጠቃለያ
እዚህ የሚቀርቡትን ሐሳቦች አጠናቅረን ለብፁዓን አባቶች፣ ለአበቶችና ለሚመለከታቸው ሰዎች ለማድረስ መቻል ይኖርብናል።
ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን

Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)